Event Addis Media
9.43K subscribers
6.32K photos
15 videos
4 files
4.93K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
🔶የቴዲ አፍሮ ም/ማናጀር በፖሊስ ተወሰደች

የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ምክትል ማናጀር እና ቃል አቀባይ ማህሌት ሰለሞን በፖሊስ እንደተወሰደች ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ዘግበዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤬4211😁7🤔6😭4😡1
🔶"ሩቢያት የኪን ምሽት" ወርሃዊ የኪነ-ጥበብ መርሃ-ግብር ነገ ቅዳሜ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታወቁ።

ነገ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በሚከወነው በዚህ መድረክ ላይ ግጥሞች፣ ሙዚቃ፣ ወጎችና የሥዕል ጥበቦች ለታዳሚ እንደሚቀርቡ ታውቋል።

ዝግጅቱ የተለያዩ የጥበብ ዘርፎችን በአንድ መድረክ በማጣመር ለኪነ-ጥበብ አፍቃሪያን ልዩ የደስታ ጊዜን ለመፍጠር የታለመ መሆኑ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5😴1
🔶ጆኒ ተጋጣሚዉን አሸነፈ

በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዉ በሆነዉ በድብልቅ ማርሻል አርት ውድድር ጆኒ ተጋጣሚዉን በማሸነፍ የ1 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆነ

በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተዉ እና በርካታ ተመልካቾችን ያስገረመዉ ታሪካዊ የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር በስዊት ቦክስ እና በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል።

ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው ይህ ስፖርታዊ ዉድድር በዐድዋ ድል መታሰቢያ መዘጋጀቱ አዲስ አበባን በስፖርት ቱሪዝም ረገድ ተመራጭ ከማድረጉም በላይ መዲናዋ የዲፕሎማሲ ማዕከል ብቻ ሳትሆን የተለያዩ ዉድድሮች የሚካሄዱባት የስፖርት ማዕከል መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ነው።

በንቃተ ህሊና እና የጆኒ መካከል በተደረገዉ ብርቱ ፉክክር ጆኒ ተጋጣሚውን በመጀመሪያው ዙር በማሸነፍ የ1ሚሊዮን ብር ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተረክቧል።

በመድረኩ ላይ ከዋናው የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ፍልሚያ በተጨማሪ፣ የቦክስ እና የሞይታይ (Muay Thai) ውድድሮች ተካሂደዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የቲክቶክ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የስፖርት አፍቃሪዎች መታደማቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
9👏4
🔶የፌደራል ፖሊስ እና ቴዲ አፍሮ

በድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የቅርብ ሰዎች ላይ ተደርጓል የተባለውን እስርና ክልከላ እንዲሁም የስቱዲዮ ዝርፊያ በተመለከተ ምላሽ የሰጡት የፌዴራል ፖሊስ ሃላፊው መረጃው መሠረተ ቢስና ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባበሉ።

የታዋቂው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ  ኢትዮሪካ የተሰኘ አልበሙን ለህዝብ ይፋ ካደረገ በኃላ በዙሪያው ያሉት ሰዎች ላይ እስር መፈጸሙ እንዲሁም “የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ አካላት የድምፃዊውን ስቲድዮ እቃዎች እና ለህዝብ ጀሮ ያልደረሱ ስራዎቹን ተዘርፈዋል" መባሉን ተከትሎ ጥያቄዎች ቀረበዋል።

ፖሊስም “የፌዴራል ፖሊስ እንዲህ ዓይነት ወንጀል አይሰራም። ሰብዕናውም አይደለም”ምላሹን ሰጥቷል።

ፖሊስ ይህንን ቢልም አርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ድርጊቱ እንደተፈፀመ ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን  ተናግረዋል። ምክትል ማናጀሩም ታስረዋል በሚል መዘገቡ ይታወሳል።

በፌደራል ፖሊስ  የወንጀል መምሪያ ኦፕሬሽን ዋና ሀላፊ ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳ ፌደራል ፖሊስ የሚሰራው በህግ እና በህግ ብቻ ነው ብለዋል። በርካታ ኦፕሬሽኖችን እንሰራለን ያሉት ም/ኮሚሽነሩ እዚህ  ኦፕሬሽን ውስጥ ከእሱ ጋር የሚገናኙ ነገሮች እኛ ያደረግነው ነገር የለምም ብለዋል።

በተጨማሪም ኮሚሽነሩ  አርቲስቱ በአሁኑ ወቅት በቤቱ በሰላም እየኖረ ይገኛል ያሉ ሲሆን በእሱ ላይ የቀረበ ጥቆማም ሆነ የተጀመረ ምንም ዓይነት የወንጀል ምርመራ የለም ብለዋል።

ፌደራል ፖሊስ አክሎም ጉዳዩን “የሳይበር ጦርነት” ሲል የጠራው ሲሆን  የተወሰኑ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው አካላት አርቲስቱን “መጠቀሚያ ለማድረግ” እየሞከሩ መሆኑን  ተናግሯል።
====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1
👎2721😁5
🔶በኢትዮጵያ የኤአይ ሙዚቃ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ከእሑድ ኤአይ ጋር በመሆን በሀገራችን የመጀመሪያውን የኤአይ (AI) የሙዚቃ ውድድር አዘጋጅተዋል።

በውድድሩ ከ600 በላይ ተወዳዳሪዎች ሥራዎቻቸውን ያስገቡ ሲሆን ÷ ምርጥ 20ዎቹ በዛሬው ዕለት ይለያሉ።

ይህንን በዓይነቱ ልዩ የሆነ ውድድር እሑድ ከሰዓት ከ9:00 ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን እና በፋና ፕላስ ይተላለፋል።
====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
👎31🤮53👍2🤡2😁1
🔶የ"ያንግ አዲስ ፕሮጄክት" ሙዚቃ ኮንሰርት

አዳዲስና ተስፋ የተጣለባቸውን የሙዚቃ ተሰጥኦዎች የሚያስተዋውቀው (Young Addis Project) የሙዚቃ ዝግጅት ሊካሄድ ነው።

በሙዚቀኛ ለታሪክ ጥላሁን እና በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ትብብር የተሰናዳው የ"Young Addis Project" የጃዝ ሙዚቃ ዝግጅት ነገ ማክሰኞ ሚያዚያ 20 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት፣ አሸናፊ ከበደ የኮንሰርት አዳራሽ ይካሄዳል።

ይህ የሙዚቃ መድረክ፤ ጃዝን፣ ዘመናዊ የሙዚቃ ስልቶችን እና ባህላዊ ለዛዎችን ያቀናጁ የቀጥታ የሙዚቃ ትዕይንቶች የሚቀርቡበት ይሆናል። ዝግጅቱ አዳዲስ የሙዚቃ ፈጠራዎችን ለታዳሚ በማስተዋወቅ ረገድ የራሱን አሻራ እንደሚያኖር ይጠበቃል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
5
🔶በኢዮብ ኪታባ አውደርዕይ ላይ ውይይት ተዘጋጀ

በገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ የሥነ-ጥበብ ሙዚየም ላለፉት ቀናት ለዕይታ ቀርቦ የቆየው የሠዓሊ ኢዮብ ኪታባ "ከጣራ በታች" የተሰኘው የሥዕል አውደ-ርዕይ ማጠቃለያን በማስመልክት ልዩ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱ ታወቀ።

ነገ ማክሰኞ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ መድረክ ላይ፤ አቶ ሰርፀ ፍሬስብሃት፣ አቶ አገኘሁ አዳነ እና ዶ/ር ጳውሎስ አዕምሮ በመሪ ተጋባዥነት ተገኝተው የመወያያ መነሻ ሃሳቦችን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል። ዝግጅቱ ለአርቲስት በኃይሉ በዛብህ በታላቅ መታሰቢያነት የሚቀርብ መሆኑም ተገልጿል።

ከውይይቱ በተጨማሪ የኪነ-ጥበብ ድምቀት የሚሰጡ ዝግጅቶች የተካተቱ ሲሆን፣ ይታገሱ ጌትነት እና ቸርነት ወልደገብርኤል ሲሳይ የግጥም ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ፍራኦል ፍቃዱ ደግሞ በሙዚቃ አቅርቦት መድረኩን እንደሚያደምቁት ታውቋል።

አውደ-ርዕዩ ከተከፈተበት መጋቢት 18 ቀን ጀምሮ መሰል የውይይት መድረኮች እንዲዘጋጁ ሲጠይቁ ለነበሩ የጥበብ ወዳጆችና ፍላጎቱ ላላቸው ታዳሚዎች በሙሉ፤ በዕለቱ በሙዚየሙ ተገኝተው የውይይቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
4
🔶የዳናዊት መክብብ የባንክ አካውንትና ንብረት ታገደ

ታዋቂዋ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢና የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ዳናዊት መክብብን ጨምሮ በአምስት ተከሳሾች ላይ ተመስርቶ የሚገኘውን የአጭበርባሪነት ክስ ተከትሎ፣ የንብረትና የባንክ ሂሳብ እግድ መጣሉ ተሰምቷል።

እንደ ኢትዮጲካንሊንክ ዘገባ፣ ዳናዊት መክብብና ሌሎች አራት ግለሰቦች የተከሰሱት "ወደ ውጭ ሀገር እንልካችኋለን" በሚል ከ13 ከሳሾች እያንዳንዳቸው 437 ሺህ ብር ተቀብለው ....ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/275

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🙊8👏2😱2
🔶ሰይፉ ፋንታሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

ዝነኛው የሚዲያ ሰው ሰይፉ ፋንታሁን እንግዳ የሆነበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር ምሽት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ረቡዕ ሚያዝያ 21 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዕለቱም ታዋቂው ሰይፉ ፋንታሁን "ታዲያስ ሰይፉ" የክብር እንግዳ ሆኖ በመገኘት ሙያዊ ልምዱን ያካፍላል።

ከቀኑ 11: 30 ጀምሮ ግጥም፣ወግ፣ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድቶ እየጠበቃችሁ ነው።

በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ እና ፕሮግራሙ ላይ መታደም የምትፈልጉ የስነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን በመሉ መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ተብላችኋል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
19👍2
🔶የሰንዳፋ በኬ ድምቀት ቱአር ኤን ሰለሞን ሆቴል

በሰንዳፋ በኬ ከተማ በዘመናዊ መልኩ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ቱአር ኤን ሰለሞን ሆቴል ስራ ከጀመረ አንስቶ የብዙዎችን ተወዳጅነት እያገኘ መሆኑ ተነገረ።

ሆቴሉ ለከተማዋ አዲስ ገጽታ ከመስጠቱም ባለፈ፣ ለአካባቢው ነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ተመራጭ የመዝናኛ ማዕከል እየሆነ መጥቷል።

​ሆቴሉ  የብዙዎችን ልብ ለማሸነፍ የቻለባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች፦

የከተማዋን ውበት በጨመረ መልኩ የተገነባው የሆቴሉ ህንፃና የውስጥ ማስጌጫ ለደንበኞች ምቾትን የሚሰጥ ነው።

​የምግብ፣ የመጠጥና የማረፊያ ክፍሎች አገልግሎት በከፍተኛ ጥራትና በዘመናዊ መስተንግዶ የታጀበ መሆኑ ተገልጿል።

​ከከተማዋ ጫጫታ ወጣ ብሎ ለዕረፍትና ለተለያዩ ፕሮግራሞች (ለሠርግ፣ ለስብሰባና ለልደት) ምቹ መሆኑ ተመራጭነቱን ከፍ አድርጎታል።

ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሐን መሥመር የሚጓዝ ተጓዥ ቱ አር ኤን ሰለሞን ሆቴል አረፍ እያለ እየተዝናና መሄዱ ሆቴሉ ምቾት ፈጥሯል።

ይህ ሆቴል በሰንዳፋ በኬ እያሳየ ያለው ስኬት፣ ሌሎች አልሚዎችም በአካባቢው መሰል ኢንቨስትመንቶች ላይ እንዲሰማሩ መንገድ የሚከፍት መሆኑ ተመልክቷል። ሆቴሉ በቀጣይም የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት የከተማዋ ዋነኛ መለያ ሆኖ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

2 rn solomon hotel and spa
የተለያዩ ሰርቪሶችን በመስጠት ይታወቃል
5 አይነት ሩሞች አላቸው።ሁሉም ሩሞች ላይ ቁርስ ፖኬጅ ሲኖር ስዊት ሩም ላይ ደሞ እስቲም እና ሳውናንም ያካትታል።እስከ 300 ሰው መያዝ የሚችል የስብሰባ  አዳራሽ እና ሚኒ አዳራሽም አለው።
👍133👎1
🔶"ንጉስ ዳግማይ ንጉስ" አልበም

የድምጻዊ ፀጋዘአብ ገ/ሥላሴ "ንጉስ ዳግማይ ንጉስ" የተሰኘው አልበም የፊታችን ሀሙስ ሚያዝያ 22 /2018 ይለቀቃል።

"ንጉስ ዳግማይ ንጉስ" የድምጻዊው 4ተኛ የሙዚቃ አልበም ሲሆን 12 ትራኮችን የያዘ እንዲሁም በፍቅርና ባህል ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል::

በአልበሙ ውስጥ የሚገኙትን 12 ሙዚቃዎች ግጥምና ዜማ የሰራው እራሱ ፀጋዘአብ ገ/ስላሴ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን አንዱ ሙዚቃ ግን የህዝብ ነው ተብሏል::

ይህ በርካታ በሀገራችን የሚገኙ የትግርኛ የሙዚቃ ባለሙያዎችን ያሳተፈውና የማኀበራዊ ፣የፍቅርና የባህል ጉዳዮችን የሚያነሳው የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች በራሱ በፀጋዘአብ ገ/ስላሴ ናዶና በተሰኘው በዩቱብ ቻናል እንደሚለቀቅና በሌሎች አለም አቀፍ የዲጂታል መተግበሪያዎችም ለአድማጭ እንደሚደርስ ተገልጿል

የድምፃዊ ፀጋዘአብ ገ/ስላሴ የሙዚቃ አልበም ከ3.5 ሚሊየን ብር በላይ የፈጀና 12 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስራውን ሰርቶ ለማጠናቀቅም 2 ዓመታትን መውሰዱ ተነግሯል፡፡

ድምጻዊ ፀጋዘአብ ገ/ስላሴ ከዚህ ቀደም "እምበይተይ” በሚል ዜማ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሙዚቀኛ ነው

መርሀግብሩን ኤርሚ ኤቨንት ከዳይናሚክ ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር እንዳዘጋጀው ተነግሯል::

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4👍2
🔶ኢትዮጵያ ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ ተዘረፈች

ታዋቂ አርቲስቶችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ መዝረፋቸው በኦዲት ምርመራ መረጋገጡ ተነገረ

በ2018 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ሙስና የፈጸሙ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ታዋቂነታቸውን ተጠቅመው ኅብረተሰቡን የዘረፉ አርቲስቶች 78 ቢሊዮን ብርና 134 ሚሊዮን ዶላር ወይም በወቅቱ ሕጋዊ የባንክ ምንዛሪ ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረሳቸው (ኅብረተሰቡን መዝረፋቸው)በኦዲት ምርመራ
መረጋገጡን፣ የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ይህን ያስታወቀው የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ሲያቀርብ ነው፡፡

ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ኦፕሬሽን መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር፣ ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳ፣ ወንጀል ነክ የሆኑ ምርመራዎች ላይ የሙስና ምርመራ ወንጀሎች እንዴት እንደሚፈጽሙ ሲያብራሩ፣ ሙስና በባህሪው እጅግ ውስብስና ድርጊት ፈጻሚው በረቀቀ መልኩ የሚፈጽመው በመሆኑ፣ ይህንን በማስረጃ ማረጋገጥ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡

የሙስና ወንጀል ፈጻሚው ከራስ አርቆ ውጭ አገሮች ድረስ ንብረት የሚያሸሽና የሚያከማች በመሆኑ፣ እነዚህን ማውጣት ከባድ በመሆኑ ልዩ ሥርዓቶችን በመዘርጋት፣ ከሌሎች ተቋማት ጋር ትብብር ማድረግንና የኦዲት ውጤቶችን የሚጠይቅ ሥራ ነው ብለዋል፡፡

ዘገባው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😱1614😁3👍2😭2🥰1
🔶አዲስ አበባ አንበሳ ባስን ልትዘክር ነው

አንበሳ ባስ ለረጅም ዘመናት የከተማውን ህዝብ አገልግለው በየገራጁ በስብሰው ቆመው የሚገኙት የዳፍ (DAF) አውቶብሶች አገልግሎት ሰጪ ብቻ ሳይሆን የብዙዎች ትዝታ ነበሩ::

የከተማ አስተዳደሩ በተመረጡ የአውቶብስ ፌርምታዎች እነዚህን ቀደምት የአንበሳ ባስ የከተማ አውቶብሶች የአውቶብስ መቆሚያ (ፌርማታ) ለማድረግ ዲዛይኑን አጠናቃል:: ይህም በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍258😁7👏3
🔶የዴማ ሆፕ ሪልስቴት እና የፋስትፔይ ስምምነት

ዴማ ሆፕ ሪልስቴት ከፋስትፔይ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

በሪልስቴት ዘርፍ ፈጣን እድገት እያስመዘገበ የሚገኘው ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት ከፋስትፔይ ጋር ስምምነት ማድረጉን ገልጿል።

ይህ ስምምነት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ የቤት ግዢ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ለማስቻል ያለመ ነው።

ደንበኞች የፋስትፔይን የክፍያ ስርዓት በመጠቀም ከዴማ ሆፕ ሪልስቴት የመኖሪያ ቤት እና የንግድ ሱቆችን ሲገዙ ክፍያዎችን በቀላሉ እና በአስተማማኝ ሁኔታ መፈጸም እንደሚችሉ ተገልጿል።

ዴማ ሆፕ ሪልስቴት በአሁኑ ወቅት ስምንት የሚደርሱ ፕሮጀክቶች እንዳሉት ተገልጿል።

ኩባንያው ካርታ ያላቸውን ቤቶች በመሸጥ እና በግንባታ ፍጥነት ከመታወቁ ባለፈ፣ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመማሪያ ክፍሎችን በመገንባት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።

ፋስትፔይ በበኩሉ ወደ ሀገር ውስጥ የሚላክ የውጭ ምንዛሬን ለማዘመን የተቋቋመ የቴክኖሎጂ ድርጅት ሲሆን፣ በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ ሕጋዊ እውቅና ያለው አገልግሎት ይሰጣል። ተቋሙ ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ በማቅረብ፣ ከአነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ ጋር ከየትኛውም ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ባንኮች ገንዘብ በፍጥነት ለማስተላለፍ የሚያስችል ስርዓት ዘርግቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3
🔶የኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ምላሽ

ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ከቲክቶክ ዝነኛዋ ሀና ግዳይ (ባምቢ ሀበሻ) ጋር በገባው ውዝግብ ምክንያት በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።

እሸቱ መለሰ "እንደዚህ ዓይነት ፕሮግራም ድሮ ነበር መጀመር የነበረብኝ፤ ስለዘገየሁ የተከበረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ሲል በይፋ መግለጫ ሰጥቷል።

ኮሜዲያኑ አክሎም ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ እንደማይመለስና በሥራው እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

ውዝግቡ በሁለቱ ግለሰቦች መካከል ከፍተኛ የሃሳብ ልዩነት የፈጠረ ሲሆን፣ የብዙዎችን ትኩረት መሳቡም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
22👎6🤮5👍3
🔶የጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው ንጉሥ ተብሎ ለሚጠራው ለክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ የሚሆን ግርማ ሞገስ ያለው ሐውልት 6 ኪሎ አምበሳ ግቢ አጠገብ ተሠርቶ ዛሬ ሚያዝያ 27 2018 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለታላቁ የጥበብ ሰው ያለውን አክብሮት ለመግለጽ ያስገነባው ይህ ሐውልት፣ በስድስት ኪሎ አካባቢ ወደ ምኒልክና ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ መገናኛ ላይ ቆሟል።

ጥላሁን ገሠሠ ስለ ሀገር፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ እናትና ስለ ጀግንነት ያልዘፈነበት ርዕስ የለም። በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በሱዳንኛ ዜማዎቹ ህዝብን ሲያቆራኝ የኖረ ባለውለታ ነው።

ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለየንም፣ ዜማዎቹ ግን ከትውልድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም የነፍሳችን ምግብ ናቸው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
18😁9
🔶የኢቲቪው አብዲ ከማል አረፈ

የቀድሞም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (etv) ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ባጋጠው የጤና እክል ዛሬ ጧት በአዲስ አበባ እንዳረፈ ተሰምቷል። ሥርዓተ ቀብሩ ዛሬ (ማክሰኞ) ቀትር ላይ በኮልፌ የሙስሊም የመቃብር ስፍር  እንደሚፈፀም የሥራ ባልደረባው ላሉ ኢታላ ጽፏል።

ጋዜጠኛ አብዲ ከማል በኢህአዴግ ጊዜ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን "አኬልዳማ" የተሰኘውን ዶክመንተሪ ጨምሮ የተለያዩ ዘጋቢ ፊልሞችን በማዘጋጀት ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢173😱2
🔶ደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
በ90ኛ ዓመት የልደት በዓሉ ተዘከረ

የ75ኛው የአርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል በሚከበርበት በዛሬው ዕለት፣ ደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር የተወለደበት 90ኛ ዓመት የልደት በዓል በወዳጆቹ ተዘክሯል።

የደራሲው ህልፈት 14 ዓመታት ቢቆጠሩም፣ አድናቂዎቹና የጥበብ ወዳጆች በአዲስ አበባ ውቤ በረሃ አካባቢ በሚገኘው ሐውልቱ ስር በመሰብሰብ ለደራሲው ያላቸውን ፍቅር ገልጸዋል።

"እኔ የምሞተው በሰዎች ልብ ውስጥ ስሞት ነው" የሚለውን ንግግሩን በማስታወስ፣ ደራሲው ዛሬም በስራዎቹ እና በታሪኩ በብዙዎች ልብ ውስጥ ህያው ሆኖ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በዚህ ዝግጅት ላይ ደራሲያኑ ዓለማየሁ ገላጋይ፥ዘነበ ወላ፣ኃይለመለኮት መዋዕል እና ሌሎችም ተገኝተዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
34
🔶ድምጻዊ ሳሚ ዳን ለአርሰናል ዘፈነ

ታዋቂዉ የሬጌ አቀንቃኝ ሳሚ ዳን ከ22 ዓመታት በኃላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ላሸነፈው አርሰናል ክለብ ዘፈን ሰርቷል።

ዛሬ ምሸት 12:00 ሰዓት አርሰናልን የተመለከተ አዲስ ዘፈን እንደሚለቅም ይፋ አድርጓል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣5314👍2👎1