Event Addis Media
9.43K subscribers
6.32K photos
15 videos
4 files
4.93K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌12 የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች
ስለፊንቴክ መረጃ ተጠየቁ

በ'ፊንቴክ' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ ፖሊስ የጠየቀው የተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ላይ ለመወሰን ፍርድ ቤት ለነገ ቀጥሯል።

ከ"ፊንቴክ" (Fintech) ኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ በከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ በቀሪ የምርመራ ስራዎች ምክንያት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል።

ባለፉት 12 የምርመራ ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ለፍርድ ቤቱ ያስረዳው ፖሊስ፣
12 የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች እንዲሁም ሁሉም የሀገሪቱ ...ተጨማሪውን ያንብቡ:- https://t.me/NorRadio1/235

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
7👍1
🔶ሕይወቷን ማትረፍ አልተቻለም

በተባበሩት አደባባይ በደረሰ የመኪና አደጋ ጉዳት ደርሶባት የነበረችው ህፃን ሔርማ ስንታየሁ አረፈች

በአዲስ አበባ በተባበሩት አደባባይ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ ከባድ ጉዳት ደርሶባት በሕክምና ስትረዳ የቆየችው ህፃን ሔርማ ስንታየሁ (እኩቹ) በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተነገረ።

ህፃን ሔርማ አደጋው ከደረሰባት ጊዜ ጀምሮ ሕይወቷን ለማዳን የሕክምና ባለሙያዎች ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም፣ በደረሰባት ጉዳት ምክንያት ዛሬ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ማረፏ ተረጋግጧል።

የህፃኗ ሥርዓተ ቀብር ዛሬውኑ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ በደብረ ሰላም ሰዓሊተ ምሕረት ካቴድራል ይፈጸማል። በዚህ አሳዛኝ ክስተት ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅና ለዘመዶቿ መጽናናትን እንመኛለን።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
😢31😭25🕊32
🔶የቴዲ አፍሮ ኢትዮሪካ አልበም ሀሙስ ይለቀቃል

የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አዲስ አልበም "ኢትዮሪካ" የፊታችን ሐሙስ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ተገለጸ

በመላው የሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የቆየው የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አምስተኛ ስቱዲዮ አልበም የሆነው "ኢትዮሪካ" (Ethiorica) የቀን ለውጥ ተደርጎለት የፊታችን ሐሙስ እንደሚለቀቅ ታወቀ።

ቀደም ሲል ለዳግማይ ትንሳኤ ዕለት ይወጣል ተብሎ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም፣ አሁን በተገኘው መረጃ መሠረት ግን አልበሙ የፊታችን ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ለታዳሚ እንደሚደርስ ኖር ሬድዮ አረጋግጧል።

ኖር ሬድዮ እንደሰማሁ ከሆነ ይህ አዲስ አልበም "8" ቁጥርን መሠረት ባደረጉ አስገራሚ አጋጣሚዎች የታጀበ ሲሆን፣ ዋና ዋናዎቹም የሚከተሉት ናቸው፦
የሚለቀቅበት ቀን፦ ሚያዝያ 8 ቀን
የሚለቀቅበት ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 ሰዓት
ወሩ፦ ሚያዝያ (በኢትዮጵያ አቆጣጠር 8ተኛው ወር)
ዓመተ ምሕረቱ፦ ሁለት ሺህ 18
የትራኮች ብዛት፦ በውስጡ 18 ዘፈኖችን ይዟል

ድምፃዊው አልበሙን ካቀደው ቀን ቀደም ብሎ ለመልቀቅ መወሰኑ በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ አድናቂዎቹ ትልቅ የምስራች ሆኗል። "ኢትዮሪካ" የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ዳግም ያነቃቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በዕለቱ በተለያዩ የዲጂታል የሙዚቃ መተግበሪያዎችና በድምፃዊው የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በቀጥታ እንደሚለቀቅ ይጠበቃል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
142👍6🥰3🔥1
🔶ኮሜዲያን ፍልፍሉ ድንገተኛ ህመም ገጠመው

ኮሜዲያን ፍልፍሉ በድንገት በገጠመው የስትሮክ (Stroke) ህመም ምክንያት በአሁኑ ወቅት በህክምና ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።

ኮሜዲያኑ ከህመሙ ጋር በተያያዘ በሰጠው ቃልመጠየቅ፣ በአሁኑ ወቅት የመቀመጥና የመቆም ችግር እንዳጋጠመውና በሰውነቱ ላይ የመዛነፍ ስሜት እንደሚሰማው ገልጿል።

"ብድግ ስል ወደ አንድ ጎን ነው የማደላው፣ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም" ሲል የገጠመውን የጤና እክል አስረድቷል።

ኮሜዲያን ፍልፍሉ በአሁኑ ወቅት መራመድ ባይችልም፣ በለመደው የቀልድና የጨዋታ ለዛው ዙሪያውን ያሉ ሰዎችንና የህክምና ባለሙያዎችን እያዝናና ይገኛል።

ስለ ጤና ሁኔታው ሲያስረዳም "እግዚአብሔር ይመስገን፣ ጠንክሬ ነው ያለሁት፤ በራሴ ግፊት እነሳለሁ" በማለት ተስፋውን ገልጿል።

በመጨረሻም ኮሜዲያኑ ለአክሱም ሆስፒታል ሰራተኞች፣ ለታሜ ኮሚኒኬሽን እና ለቤተሰቦቹ ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን፤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ለልጆቹ የመልካም በዓል ምኞቱን አስተላልፏል።

በአሁኑ ወቅትም የቅርብ ጓደኞቹና የሙያ ባልደረቦቹ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያደረጉለት እንደሚገኝ ታውቋል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
14😭7🕊1
🔶የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የ2027ቱን የዓለም አቀፍ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር (AIPS) አመታዊ ጉባኤን ለማዘጋጀት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አገኝቷል።

ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው በዚህ ጉባኤ ላይ :-

- ከ100 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ተሳታፊ ጋዜጠኞች ይመጣሉ

- የተለያዩ አለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት መሪዎች ይሳተፋሉ

- የአለም "ምርጥ የስፖርት ጋዜጠኝነት አመታዊ የሽልማት ፕሮግራም" ይካሄዳል

- የAIPS Young Reporters ስልጠና ይካሄዳል።

ይህ አለምአቀፍ ኹነት ከስፖርት ዘገባ ባለፈ ለኢትዮጵያ ስፖርት ዲፕሎማሲ፣ ኢኮኖሚ እና ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ፋይዳም እንደሚኖረው ይታመናል።

ይህ ጉባኤ ኢትዮጵያ "የስፖርት ቤተሰቡን" በአንድ ጣሪያ ስር በመሰብሰብ በስፖርቱ ዓለም ያላትን ስም የምታድስበት ትልቅ መድረክ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

©️ቲክቫ ስፖርት
====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
102💯1
📌ቃና ቲቪ ማስታወቂያ አውጥቷል

ቃና ቴሌቪዥን በድምፅ እና በምስል ትወና ዘርፍ የባለሙያዎች የቅጥር ምርመራ (Audition) መጥራቱን አስታወቀ።

ጣቢያው ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ቀደም ሲል በድርጅቱ ውስጥ ለመስራት ፍላጎት ኖሯቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ ለነበሩና አዳዲስ ተሰጥኦ ላላቸው ባለሙያዎች በድምፅ እና በምስል ትወና ዘርፎች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዕድል አመቻችቷል።

በዚህ የሙያ ምርመራ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ አመልካቾች ከነገ ሚያዝያ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/247

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
12👏1
🔶ቴዲ አፍሮ በደቂቃዎች ውስጥ ሪከርድ ሰበረ

የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ "አቶሪካ" አልበም በተለቀቀ በደቂቃዎች ውስጥ በዩቲዩብ በቀጥታ ስርጭት ከ114 ሺ በላይ ሰዎች በቀጥታ ስርጭት እየሰማሁ ነው።

ኖር ሬድዮ ባለው መረጃ መሠረት በዩቲዩብ ላይ በዚህ መጠን (ከመቶ ሺ በላይ) ሰዎች በቀጥታ ስርጭት አንድን ስራ ሲከታተሉ ይህ የመጀመሪያ ነው። በቴዲም ሪከርድ ተሰብሯል ።

ከዚህ ቀደም አርትስ ቴሌቪዥን የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ የቀጥታ ስርጭትን ሲያተላለፍ ከ70 ሺ በላይ ሰዎች በቀጥታ እንደተመለከቱ ይታወሳል።

በዚህ ሰዓት ቴዲ አፍሮ "ጀንበር"፣ "ስማ ራሴ"፣ "መርከብ"የተሰኙ ሙዚቃዎችን እያስደመጠ ይገኛል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
44👎1👏1
🔶የቴዲ አፍሮ አልበም መታሰቢያነት

የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ስድስተኛ የሙዚቃ አልበም "ኢቶሪካ" ዛሬ ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም (8/8/2018) በይፋ ተለቋል።

ድምፃዊው ይህንን አዲስ ስራውን በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት በማንነታቸው ምክንያት ጥቃት ለደረሰባቸው እና ለተፈናቀሉ ንጹሀን ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ እንዲሆን አበርክቶታል።

ቴዲ አፍሮ ከአዲሱ አልበሙ ሽፋን ጋር ባጋራው ይፋዊ መልዕክት ላይ እንዳሰፈረው፣ አልበሙን ግፍ ለደረሰባቸው ወገኖች መጽናኛ እና መታሰቢያ እንዲሆን አስቧል።

የጥበብ ሰው በአልበሙ ማስተዋወቂያ ላይ ባሰፈረው መልዕክት፤ "ይህ ሙዚቃ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በማንነታቸው ብቻ ተለይተው በግፍ ለተገደሉ ንፁሀን ወገኖቻችን እና እንዲሁም ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ መታሰቢያ ይሁንልኝ" በማለት ጥልቅ የሆነ ሀዘኑን እና አጋርነቱን ገልጿል።

ይህ "ኢቶሪካ" የተሰኘው እና ጥቁር አፍሪካዊነትን በሚያጎላ አርማ (ሎጎ) ያሸበረቀው ስድስተኛው አልበም፣ የህዝብን የልብ ትርታ በማዳመጥ እና ወቅታዊ ሀገራዊ ስሜቶችን በዜማ በማዋዛት የሚታወቀው ቴዲ አፍሮ ዳግም ወደ ሙዚቃው መድረክ የደመቀበት ትልቅ ስራ ነው። የጥበብ ሰውን መልእክት ተከትሎም በርካታ አድናቂዎቹ ለሰብአዊነት ያለውን ተቆርቋሪነት በማድነቅ ላይ ይገኛሉ።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
42🥰3👏2
🔶የቴዲ አፍሮ "ዳስ ጣል" የተሰኘ ሙዚቃው ማኅበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቆታል

የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ስድስተኛ ስቱዲዮ አልበም "ኢቶሪካ" ዛሬ ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በይፋ ለሕዝብ ተለቋል።

አልበሙ በተለቀቀ ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በውስጡ ካካተታቸው የሙዚቃ ሥራዎች መካከል "ዳስ ጣል" የተሰኘው ሙዚቃ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

ሙዚቃው በተለይ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት እየተጋራ ሲሆን፣ በርካታ አድማጮችም ሥራው ስሜትን የሚነካና ጥልቅ መልዕክት ያዘለ መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ።

ኖር ሬድዮ እንደተመለከተው ከሆነ ሙዚቃውን ካደመጡ ታዳሚዎች መካከል የተወሰኑት "ሥራው እጅግ ልብ የሚነካና ውስጣዊ ሕመምን የሚፈነቅል ነው" ሲሉ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው።

አንድ አስተያየት ሰጪ "ዳስ ጣል አስለቅሶኛል፤ ውስጤን አንድዶታል የማይፈነቅለው ሕመም የለም፣ ከአዕምሮ በላይ ነው" ሲል ለሙዚቃው ያለውን አድናቆት ገልጿል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
33🤣6😭2
🔶የቴዲ አፍሮ “ጀምበር” የተሰኘው ሙዚቃ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዕይታዎችን አገኘ

የቴዲ አፍሮ ኢቶሪካ አልበም ውስጥ የተካተተው ይህ “ጀምበር” የተሰኘው ሙዚቃ ከሦስት ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺ በላይ ዕይታዎችን አግኝቷል።

“ጀምበር” የተሰኘው ሙዚቃ የሚጀምረው “እርፎ መረባ” በሚል “በወሎና አካባቢው እናቶች በሚመርቁበት” ስልት ሲሆን በውስጡ ደግሞ የተለያዩ ድምጾችን አካትቷል።

እነርሱም በኪነ ጥበብ ባለሙያዋ ዓለምጸሃይ ወዳጆ የተደረሰው “ጸሃዬ ደመቀች”፣ የክፍሌ አቦቸር “ኢትዮጵያ ትቅደም” መዝሙሮችንና የቀዳማዊ አጼ ሃይለ ሥላሴን ድምጾች ዋና ዋና ዎናዎቹ ናቸው። ይዘቱም ስለኢትዮጵያ ነው።

ይህ 18 ሙዚቃዎችን የያዘው አልበም ከ“ጀምበር” በተጨማሪ በጉራጊኛ ስልት የተሰራው “ስምምነን፤ የአዛ እምባ፤ ኢቶሪካ፤ ዳስ ጣል/አንሳው” የተሰኙት ሙዚቃዎች ግጥም ይዘትም ሀገር ላይ ያጠነጠኑ ናቸው።

የቴዲ አፍሮ አልበም ልክ በተለቀቀበት አፍታ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ተከታታዮች በቀጥታ ስርጭት የተከታተሉት ሲሆን አልበሙ ሙሉው ተደምጦ እስከሚያልቅ ድረስም ‛ሰብስክራይብ’ ያደረጉት ሰዎች ቁጥር በመቶሺዎች በፍጥነት ጨምሮ ቢያንስ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 1.7 ሚሊዮን ደርሷል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
24👏4👎2👍1
🔶በቴዲ አፍሮ አልበም አስጌ ዴንሻና መኮንን ላዕከ

በድምጻዊ ቴዲ አፍሮ "ኢቶሪካ" አልበም ላይ በጋሞኛ ወላይተኛ ሙዚቃዎቹ የምናውቀው ድምጻዊ  አስገኘሁ አሽኮ(አስጌ ዴንዳሾ) እና ተዋናይ መኮንን ላዕከ  በድምፅ (ፊውቸሪንግ) ተሳትፈዋል።

አስጌ ዴንዳሾ "ቲንታጎ:ፒንታጎ" ሙዚቃ ላይ በወላይተኛ ግጥምና ድምፅ የተሳተፈ ሲሆን ተዋናይ መኮንን ላዕከ "ስማ እራሴ" በተሰኘው ሙዚቃ ላይ በድምፅ ተሳትፏል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
22🔥5
🔶መንግስታዊው ሚዲያ ስለ ቴዲ አፍሮ  የፖሰተውን ዜና ከደቂቃዎች በኋላ አጠፋው

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት(አዲስ ዘመን)  በዛሬው ዕለት የተለቀቀውን የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ አልበምን በሚመለከት "በደጋፊዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ “ኢቶሪካ” አልበም ተለቀቀ" ሲል የሰራውን ዜና ከደቂቃዎች በኋላ ከፌስቡክ ገፁ እንዳጠፋው (እንደሰረዘው) ኖር ሬድዮ ተመልክቷል።

ከአልበሙ መለቀቅ አስቀድሞ ሊሰጥ የነበረው የጋዜጣዊ መግለጫ የተከለከለ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን የዜናው ተፅፎ ወዲያው መጥፋት የሚጠበቅ ነው ተብሏል::

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁44🤣116🤷3
🔶ዛሬ ቡርሃን አዲስ በዛጎል መጻህፍት

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት ዛሬ ቅዳሜ  ሚያዝያ ቀን 10 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ሳምንት የተመረጠው መጽሐፍ "መሆንን መድረስ" የተሰኘ መጽሐፍ ሲሆን በክብር እንግዳነት ቡርሃን አዲስ ይገኛል ተብሏል። የዝግጅቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5
🔶ድምፃውያኑ ለቴዲ አፍሮ ምላሽ ሰጡ

የኦሮምኛ ሙዚቃ ድምፃውያኑ ገላና ጋሮምሳ እና ዮሳን ጌታሁን "Galmee Seenaa" በሚል ርዕስ አርብ ሌሊት በለቀቁት አዲስ ዘፈን፣ ባሳለፍነው ሀሙስ ለተለቀቀው የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) "ኢቶሪካ" አልበም ቀጥተኛ ምላሽ ሰጥተዋል።

በኦሮምኛና በአማርኛ ቋንቋዎች የተሰናዳው ይህ የዘፈን ሥራ፣ በተለይም በአማርኛው የግጥም ስንኝ ውስጥ የተካተቱት መልዕክቶች በቴዲ አፍሮ "የአዞ እምባ" እና "ዳስ ጣል" ለተሰኙት ዜማዎች ምላሽ የሚሰጡ ሆነው ተገኝተዋል።

ኖር ሬድዮ እንደተመለከተው ከሆነ በዘፈኑ ውስጥ የተካተቱት የአማርኛ ግጥሞች ከፊሉ እንደሚከተለው ይነበባሉ፦

"መሃረቡን ስጡት የአዞ እምባ ነው ካለ፤ ሳቅን ካለቀሰ ለቅሶ ዳስ ከጣለ...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/255

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👎32😁53👏3🥱2🤮1💩1
🔶የበሬ ቆዳ ለምግብነት ?

ከኢትዮጵያ የበሬ ቆዳ በጥሬው ለምዕራብ አፍሪካ ለምግብነት እየተላከ መሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎችን እና ጥሬ እቃ አቅራቢዎቻቸውን እያወዛገበ ነው፡፡

ቆዳ አቅራቢዎቹ ያለምንም ልፋት በጥሬው ቆዳውን ለምግብነት ለሚጠቀሙ የአፍሪካ ሀገራት መላካቸው ፋብሪካዎቹን ጥሬ እቃ እያሳጣ ነው ተብሏል፡፡

መንግስት ቆዳ በጥሬው ለውጪ ገበያ የሚያቀርቡትን ለመግታት በበሬ ቆዳ ላይ የ150 በመቶ የታክስ ጭማሪ ስራ ላይ አውያለሁ ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የበሬ ቆዳ ለምግብነት አገልግሎት ...ተጨማሪውን ያንብቡ:- https://t.me/NorRadio1/256

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁4😱42🤮1
🔶"በAi ከፈጣሪ ጋር ላገናኛችሁ?"

አንድ የቻይና ኩባንያ በAi ከፈጣሪ ጋር ላገናኛችሁ ብሎ ስራ ጀምሯል። ለዘመናት ብዙ ክርስቲያኖች ከጌታቸው ጋር በቀጥታ መነጋገር ይፈልጋሉ አሁን ግን ይህንን ፍላጎት መፍትሄ የሚሰጥ “Just Like Me” የተባለ የAI ቻት ቦት ይዘን መጥተናል ሲል የአዲሱ ቴክኖሎጂ ኩባንያ አስታውቋል።

ኩባንያው ይህን “Jesus AI” ልክ እንደ ፈጣሪ መንገድ የሚመራ፣ የሚያበረታታና የሚያግዝ መምህር እንደሆነ ገልጿል።

የኩባንያው ስራ አስፈጻሚ እንደገለፁት የ“Jesus AI” ሞዴል በቅዱስ መፅሃፍና በተለያዩ አስተማሪዎች ስብከቶች ላይ ተመስርቶ ምክሮችን የሚሰጥ ይሆናል፤ የሰዎችን ችግር ለመረዳት የሚያስችል አስተዋይነትም አለው ብለዋል፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን እንዲተካ ተደርጎ እንዳልተዘጋጀ አስታውቀዋል።

ኩባንያው በድረ-ገጹ ላይ “Jesus AI” እውነተኛው ኢየሱስ አይደለም፣ ...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/262

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁10🤬6👀3🤪3🌚21👎1
🔶"ሥራ የሚገኘው በዘመድና በዘር መሆኑን አውቃችሁ ተንቀሳቀሱ" — ዶክተር አረጋ ይርዳው

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው፣ ተማሪዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተመርቀው ወደ ሥራው ዓለም ሲሰማሩ ያለው ነባራዊ ሁኔታ "በዘመድ፣ በፓርቲ አሠራር እና በዘር" ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተረድተው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ማቅረባቸውን ኖር ሬድዮ በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ ከተገኙ እንግዶች ሰምቷል።

ዶክተር አረጋ ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የ44ኛው ዙር ተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

ፕሬዚዳንቱ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት የሥራ ዓለም መመሪያ ላይ በሀገሪቱ ያለውን የሥራ ቅጥር ሁኔታ በግልጽ እንደሚከተለው ገልጸውታል፦"ተመርቃችሁ ስትወጡ ሥራ የሚገኘው በዘመድ፣ ...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/264

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😭247😁6🤬1👌1
🔶ብርሃኑ ነጋ ወቸው ጉድ ፖድካስት ላይ ቀረበ

የኢዜማ ፓርቲ ከፍተኛ ኃላፊ እና የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆነው ብርሃነ ነጋ (ፕ/ር) በርካታ ወጣቶች በሚከታተሉት "ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ በእንግዳነት ቀረቦ የሕይወት ልምዱን እያካፈለ ይገኛል።

በፖድካስቱ የዩቲዩብ ቻናል ፕሪሚየር እየተሰራጨ የሚገኘውን ይህንን ዝግጅት ከ4 ሺ በላይ ሰዎች በቀጥታ እየተመለከቱት ይገኛሉ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣166😱1
🔶በቲክቶክ አነጋጋሪው "Kalu Putic" ፋሽን

በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ቲክቶክ "Kalu Putic" በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ወጣት ኢትዮጵያዊ፣ እያቀረባቸው በሚገኙ ልዩ የፋሽን ይዘቶች የበርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን እና የዘርፉን ባለሙያዎች ትኩረት መሳብ ጀምሯል።

ወጣቱ የሚያቀርባቸው ይዘቶች ጥራትና የፈጠራ ብቃት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆናቸውን ተከትሎ፣ በፋሽን ላይ ትኩረት የሚያደርጉ የተለያዩ የውጭ ዲጂታል ሚዲያዎች ስለ ሥራዎቹ ሰፊ ሽፋን እየሰጡት ይገኛሉ። ይህም ወጣቱ ኢትዮጵያዊ በዓለም አቀፉ የፋሽን መድረክ ተቀባይነትን ለማግኘት ያለውን ሰፊ ዕድል የሚያመላክት ሆኗል።

ይህንኑ ተሰጥኦውን የተመለከቱ በርካታ ግለሰቦች ለወጣቱ የቁሳቁስና የትምህርት ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የጥበብ ባለሙያዎች እንደሚጠቁሙት፣ ወጣቱ ካለው የተለየ የመፍጠር አቅም አንጻር ከዕለት ድጋፍ ባለፈ በዓለም አቀፍ የፋሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ደረጃ ላይ ሊያደርሰው የሚችል ሙያዊ ድጋፍና ስፖንሰርሺፕ እንደሚያስፈልገው እየተገለጸ ነው።

ይህ ወጣት አሁን ያለውን አጋጣሚ በአግባቡ መጠቀም የሚችል ከሆነ፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የፋሽንና የዲጂታል ይዘት ፈጠራ መድረክ ወካይ ከሆኑ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
👏3416🙏3
🔶የቴዲ አፍሮ "ዳስ ጣል" ሙዚቃ 10 ሚሊዮን ገባ

በድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ ) "ኢቶሪካ" አልበም ውስጥ የተካተተው "ዳስ ጣል" ሙዚቃ በሶስት ቀናት ብቻ ከ10 ሚሊዮን በላይ የዩቲዩብ ዕይታን አግኝቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍5427👎1