Event Addis Media
9.43K subscribers
6.32K photos
15 videos
4 files
4.93K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌 "ሐረግ" ቴአትር ወደ መድረክ ተመለሰ

ተቋርጦ የነበረውና "ሐረግ" የተሰኘው የአንድ ሰው የሙሉ ጊዜ ተውኔት ዛሬ አመሻሹን በድጋሚ ወደ መድረክ እንደሚመለስ አዘጋጆቹ ለኤቨንት ሚዲያ አስታውቀዋል።

ይህ በደራሲና አዘጋጅ ክብይናድ አሰፋ የተዘጋጀው ተውኔት፤ በትያትር አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን፣ አሁን ላይ በቋሚነት ለዕይታ ዝግጁ መሆኑ ተረጋግጧል።

ተውኔቱ ዘወትር ማክሰኞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ለታዳሚ እንደሚቀርብ ታውቋል።

በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ በሚቀርበው በዚህ ሥራ፣ ተዋናይት ሃና ጌትነት በብቸኝነት ትተውናለች።

የዝግጅቱ አስተባባሪዎች እንደገለጹት፣ ተውኔቱ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳዮችን በጥልቀት የሚዳስስ ሲሆን፣ በትያትር ጥበብ ውስጥ ከፍተኛ አቅም የሚጠይቀውን የአንድ ሰው ትወና በልዩ ሁኔታ እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

ማንኛውም የጥበብ አፍቃሪ ዘወትር ማክሰኞ በብሔራዊ ቴአትር በመገኘት ዝግጅቱን መታደም እንደሚችል ተመልክቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤6
📌የ35 ሚሊዮን ብር ልዩነት በአንድ ዓመት ብቻ ?

ዘንድሮ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሽልማቱ ስንት ነው?

በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች የሚያገኙት የሽልማት እና የጥቅማጥቅም መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር እጅግ የወረደ መሆኑ ተሰማ።

የሊጉን የሥርጭት መብት የወሰደው ኦቢኤን (OBN) ቴሌቪዥን ለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በዓመቱ መጨረሻ የሚከፍለው ጠቅላላ ክፍያ 200 ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑ ተገልጿል። ይህም በሊጉ ተሳታፊ የሆኑ 16 ክለቦች የሚያገኙትን የገቢ ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ ዝቅ እንዲል አድርጎታል።

ባለፈው የውድድር ዘመን የዲኤስቲቪ (DSTV) የሥርጭት ስምምነት በነበረበት ወቅት፣ ለክለቦች የተከፋፈለው የገንዘብ መጠን 406 ሚሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፤ ዘንድሮ ግን ይህ መጠን ከ50 ሚሊዮን ብር በታች ሊወርድ እንደሚችል ተመልክቷል።

የሽልማት መጠኑን አስመልክቶ በወጣው መረጃ መሠረት፤ ባለፈው ዓመት የሊጉ ሻምፒዮን የሆነው ኢትዮጵያ መድን 40 ሚሊዮን ብር የተሸለመ ቢሆንም፣ የዘንድሮው የሊጉ አሸናፊ ግን ...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/156


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤2👍2😁1
📌እንዳልክ አሰፋ ትችት ቀረበበት

የ"ዕርቅ ማዕድ" ፕሮግራም አዘጋጅ የነበረው እንዳልክ አሰፋ፣ በቅርቡ በዩቲዩብ ቻናሉ ባቀረበው ዝግጅት የባለታሪኮችን ሰብአዊ ክብር የሚነኩ አቀራረቦችን ተጠቅሟል በሚል ከጋዜጠኞችና ከሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጥብቅ ትችት እየቀረበበት ይገኛል።

ትችቱን ካቀረቡት መካከል ጋዜጠኛ ቃልኪዳን እና እመቤት ደመቀ የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ጋዜጠኛው በፕሮግራሙ ላይ የቀረቡ ሁለት ሴቶችን ፊት ለፊት በማጋጠም እርስ በእርስ እንዲናናቁና እንዲሰዳደቡ መንገድ ከፍቷል ሲሉ ወቅሰዋል።

በተለይም የሦስት ልጆች እናት የሆነችን ባለታሪክ “ራስሽን አትጠብቂም፣ ዝርክርክ ነሽ” የሚሉ የግል ክብሯን የሚነኩ ንግግሮችን በአደባባይ በማንሳቱ፣ ዝግጅቱ ከዕርቅ ይልቅ የሞራል ስብራትን የሚያስከትል ነው ተብሏል።

ተቺዎቹ አክለውም፣ ጋዜጠኛው የዲኤንኤ (DNA) ምርመራ ውጤቶችን እንደ ውድድር ውጤት “ልብ አንጠልጣይ” ለማድረግ ጊዜ መውሰዱ እና በሰው ስቃይ ....ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/159

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍8😁5❤4👎1👏1
📌 ኢዜአ 6 ሪፖርተሮችን መቀጠር ይፈልጋል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ካለው የሥራ ስፋትና ፍላጎት አንጻር፣ በተለያዩ ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ብቁ የሆኑ አመልካቾችን በሪፖርተርነት አወዳድሮ ለመቅጠር መፈለጉን ገለጸ።ከ2 ዓመት እንዲሁም ከዛም በላይ ልምድ ያላችሁ ባለሞያዎች ትፈለጋላችሁ።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ መስፈርቱን የሚያሟሉና በዘርፉ ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች በተጠቀሰው የጊዜ ገደብና ቦታ በመገኘት ማመልከት እንደሚችሉ አስታውቋል።

ይህ የቅጥር ማስታወቂያ ተቋሙ ያለውን የሰው ኃይል አቅም ለማጠናከርና የሚሰጣቸውን የሚዲያ አገልግሎቶች ጥራት ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተመልክቷል።

አመልካቾች ስለ ቅጥሩ ዝርዝር መረጃ፣ ስለሚያስፈልጉት የትምህርት ዝግጅቶችና የሥራ ልምድ መረጃዎችን ከተያያዘው የቅጥር ሰነድ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111-552300 በመደወል መጠየቅ እንደሚቻል ተቋሙ ጠቁሟል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4
📌በቴሌቪዥን ድራማ ጽሑፍ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ሥነ ጥበባት ማዕከል ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ጽሑፍ ዙሪያ ሙያዊ ውይይት አካሄደ፡፡

በዝግጅቱ ላይ አራት በኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ደራስያን ተገኝተው ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

የፊልም እና ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ደራሲዋ ቤዛ ኃይሉ ውይይቱን ከመምራት ባሻገር ልምዷን በየመካከሉ አካፍላለች፡፡

በዝግጅቱ ላይ “ትርታ”፣ “የእግር እሳት”፣ “የውሃ ሽታ”፣ “መዘዝ”፣ “የባስሊቆስ እንባ”፣ “በስንቱ” ሲትኮም እና የሌሎችም ሥራዎቹ የሚታወቀው ሶፎንያ ታደሰ ተገኝቶ ልምዱን ለወጣቶች ካካፈሉት መካከል አንዱ ነው፡፡

በመቀጠለም “የአቶ እና ወይዘሮ”፣ “ስቄ ልሙት”፣ “ማንያዘዋል”፣ “ሁለት ጉልቻ”፣ “እንደ አንድ” የቴሌቪዥን ድራማ፣ የ”አሻራ” ቴሌ ኖቬላ ደራሲ ኑር አክመል ሌላኛው እንግዳ ነበር፡፡

እንዲሁም “የወደፊት”፣ የ”ሰኔና ሰኞ”፣ የ “ዘጠነኛው ሺ”፣ የ “ምስኪኖቹ”፣ የተማሪ ቤት ድርሰቶች፣ በዳይሬክቲንግ እና በሌሎቹም ኃላፊነቶቹ የሚታወቀው ወንድማገኝ ለማ ተገኝቷል፡፡

የተወዳጁን የሀዲስ አለማየሁ ሥራ የሆነውን “ፍቅር እስከ መቃብር”ን የተከታታይ ቴሌቪዥን ድራማ ጽሑፍ ላይ የተሳተፈው፣ የ“ዕጸ ሕይወት” ቴሌ ኖቬል ድራማና የ“ፓይለቶቹ” ቴሌቪዥን ደራሲ መልካሙ ኃይሌ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

የፓነል ውይይቱ ላይ የፊልም ኢንደስትሪውን የተቀላቀሉ፣ ጀማሪ ጸሐፊያንና ፍላጎቱ ያላቸው ሰዎች ታድመውበታል፡፡ ከመድረኩ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የመድረኩ ዝግጅት አነሳሽ ደራሲ ቤዛ ኃይሉ ውይይቱ ወደፊት በወርክሾፕ መልኩ እንደሚቀጥል ተስፋዋን ገልጻች፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤7👍1
📌"በጉዳዩ በጣም አዝኛለሁ፤ በግኛለሁም"

ታዋቂው ገጣሚ እና ደራሲ ሰለሞን ሳህለ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመጽሐፍት መላኪያ ላይ በጣለው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የተሰማውን ቅሬታና መከፋት በይፋ ገለጸ።

ደራሲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ መሠረት፣ ስድስት መጽሐፍትን በፖስታ ቤት በኩል ወደ ውጭ አገር ላሉ ወዳጆቹ ለመላክ 16 ሺህ 422 (አሥራ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሃያ ሁለት) ብር እንዲከፍል መደረጉን ገልጿል። ይህም ክፍያ ከመጽሐፍቱ ዋጋና ከቀድሞው አሠራር አንጻር እጅግ የተጋነነ መሆኑን በመጠቆም "በጉዳዩ በጣም አዝኛለሁ፤ በግኛለሁም" ሲል ቁጭቱን ገልጿል።

ደራሲ ሰለሞን ሳህለ "አሁን ይሄ ምንድን ነው የሚባለው?" ሲል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ መረጃው ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስና በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥበትም ጥሪ አቅርቧል። በኢትዮጵያ የፖስታ አገልግሎት ድርጅት በኩል በቅርቡ የተደረጉ የዋጋ ማሻሻያዎች መኖራቸውን ተከትሎ፣ መሰል ቅሬታዎች ከሌሎች ደራሲያንና ደንበኞችም እየተሰሙ ይገኛሉ።እስከ አሁን ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ለደራሲው ቅሬታ የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍13❤9
📌ሚሊኒየም አዳራሽን የማፍረስ ስራ ተጀመረ

ባለፉት 18 ዓመታት በኢትዮጵያ ግዙፍ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች ሲያስተናግድ የቆየው ሚሊኒየም አዳራሽ፣ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለታቀደው ሰፊ የመልሶ ግንባታና የማስፋፊያ ስራ እንዲመች የማስፈረስ ሂደት መጀመሩን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

ይህ ታላቅ የአዳራሽ እድሳትና የማስፋፊያ ፕሮጀክት በዋናነት ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው 32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ዝግጅት አካል ሲሆን፣ በቦታው ላይ Moxy by Marriott የተሰኘ ግዙፍና ዘመናዊ ሆቴል...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/162


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👎6🔥2❤1👏1
መጸዳጃ ቤቶቹ የተሸገበት ሆቴል

ዲሊዮ ፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል ከብክለት ጋር በቀረበበት ክስ መጸዳጃ ቤቶቹ ታሸጉ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት የሽንት ቤት ፍሳሽ ቆሻሻን በተደጋጋሚ ወደ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ የለቀቀው ዲሊዮ ፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል ለብክለቱ መነሻ ችግሩ የሆኑ ክፍሎቹን በማሸግ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ድርጊቱ የተፈጸመዉ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ባንቢስ አከባቢ ሲሆን ተቋሙ ከአሁን በፊት የሽንትቤት ፍሳሽን ወደ ወንዝ በመልቀቅ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመሆን የገንዘብ ቅጣት ጥሎበት ነበር።

መጀመሪያ ሆቴሉ ከጥፋቱ እንዲማር 300 ሺህ ብር ቅጣት ጥሎበት ከቅጣፋቱ ሳይማር በመቅረቱ በድጋሚ የቅጣቱን እጥፍ 600 ሺህ ተቀጥቶ ነበር። አሁንም ግን ድርጊቱን ለ3ኛ ጊዜ ባለማስተካከሉ ሆቴሉ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ የመጸዳጃ ክፍሎቹን እንዲታሸግ ተደርጓል።

ተቋሙን በቀጣይ በሕግ ተጠያቂ በማድረግ ላደረሰው ከፍተኛ ጉዳት በሕጉ መሠረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው የተሰሩ ወንዝና የወንዝ ዳርቻዎች ልማቶች በመበከል ለታለመለት ዓላማ እንዳይውል በሚያደርጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ የሚወስደውን አስተዳደራዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለሥልጣኑ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ገልጿል።

Link: https://t.me/NorRadio1

Link: https://t.me/NorRadio1
👏6❤2🫡2
የ“ጃር” ውሃ ጥራት ላይ ጥናት ሊካሄድ ነው

በተለምዶ “ጃር” እየተባለ በሚጠራውና በ20 ሊትር መያዣ ታሽጎ ለገበያ በሚቀርበው የመጠጥ ውሃ ላይ በተደጋጋሚ የሚነሱ የጥራት መጓደል ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያግዝ አገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ እንደሆነ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን ነው።

ባለሥልጣኑ ለአሐዱ እንደገለጸው፣ ጥናቱ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት እና የሕብረተሰቡን ጤና መጠበቅን ዓላማ ያደረገ ነው።

“ከሕብረተሰብ ጤና እና ደህንነት የሚበልጥ ምንም ዓይነት ነገር የለም” ያሉት የባለሥልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈጸም ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙላቱ ተስፋዬ፣ ከተገልጋዮች በየጊዜው የሚደርሱ ጥቆማዎችና አቤቱታዎችን መሠረት በማድረግ ተቋሙ በጃር ውሃ ጥራት ላይ ጥብቅ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ሥራ አስፈጻሚው በማብራሪያቸው የጥራት ችግሩ የዜጎችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ሆኖ ከተገኘ ምርቱ ሙሉ በሙሉ ሊታገድ እንደሚችል ጠቁመዋል።በተጨማሪም “ባለ 20 ሊትሩ የታሸገ ውሃ መያዣ (ጃሩ) ተደጋግሞ ጥቅም ላይ የሚውል በመሆኑ፣ በጽዳት እና ሥርጭት ሂደት ከፍተኛ ጥንቃቄን ይፈልጋል።” ብለዋል።

ባለሥልጣኑ በአሁኑ ወቅት ከአመራረት እስከ ገበያ ያለውን ሂደት በመከታተል እና ናሙና በመውሰድ ምርመራ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በማከፋፈያ ቦታዎች ላይ ጭምር ክትትል እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ የተፈጠረውን የጥራት ስጋት በዘላቂነት ለመፍታት የሚካሄደው አገር አቀፍ ጥናት እንደተጠናቀቀም፣ የምርቱን ደህንነት የሚያረጋግጥ አዲስ መመሪያ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል ተጠቁሟል።

©️አሐዱ ሬድዮ

Link: https://t.me/NorRadio1

Link: https://t.me/NorRadio1
❤13👏5👍1🤨1
📌"አክሊሉ" ታሪካዊ ልቦለድ ነገ ይመረቃል

በታዋቂው ዲፕሎማት ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ሕይወትና የሥራ ዘመን ላይ የሚያጠነጥን "አክሊሉ" የተሸኘ ታሪካዊ ልቦለድ መጽሐፍ፣ ነገ ቅዳሜ መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ይመረቃል።

መጽሐፉን ያዘጋጁት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ሰላማዊት ታደሠ ሲሆኑ፤ ምረቃውም ታዋቂው ዲፕሎማት በተወለዱበት መጋቢት 5 ቀን እንዲሆን መታቀዱ ተገልጿል።

ባለ 296 ገጹ ይህ መጽሐፍ፣ ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ከአሥራ ዘጠኝ ዓመታቸው ጀምሮ አገራቸውን በዲፕሎማሲውና በፖለቲካው መስክ ያገለገሉበትን ታሪክ፣ በተለይም የኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የመቀላቀል ሂደትና ሌሎች ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎቻቸውን በልቦለድ ቅርፅ ለንባብ የሚያበቃ መጽሐፍ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

Link: https://t.me/NorRadio1

Link: https://t.me/NorRadio1
❤5
📌ዳግማዊ  አመለወርቅ ፊይሣ ሊመሰገን ነው

በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ በዳይሬክተርነት እና በደራሲነት ያገለገለው ዳግማዊ አመለወርቅፈይሳ አድናቂዎቹ የሙይጎደኝቹ በተገኙበት የምስጋና መርሀ ግብር ሊደረግለት እንደሆነ ታወቀ።

መጋቢት7 ከቀኑ11ሰዓት በኃላ የሙያ ባልደረቦቹ፣ አድናቂዎቹ እና የቅርብ ሰዎቹ በሚታደሙበት በታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሚመሰገነው ዳግማዊ  ፈይሳ በጥበቡ ዓለም 40አመታትን ቆይታ አድርጓል። 

የምስጋና መርሀ ግብሩ አዘጋጅ ሔኖክ የእታገኝ ልጅ እንደሆነም ታውቋል።

"ስሙአተ- ነገር "የሚል ርዕስ ባለው በዚህ መርሀ- ግብር ላይ ልዩ ልዩ ተመስጋኙን የሚመጥኑ የጥበብ ዝግጅቶች ይኖራሉ ተብሏል።

ዳግማዊ ዓመለ ወርቅ ፈይሳ በ1960 ዓ.ም አ.አ አብነት አካባቢ ጠጅ ሳር ሰፈር ነው የተወለደው።

ዳግማዋ ለ17 ዓመታት ያህል ስክሪፕት በመጻፍ፤ ከ 500 በላይ  ዶክመንተሪዎችንና 1000 ማስታወቂያዎችን  በመስራት ድንቅ ባለሙያነቱን አስመስክሯል።

ዓመል የቴሌቭዥን ድራማ፤ የቃቄ  ውርዶዎት  ከመጋረጃ ጀርባ የተሰኙ ቴአትሮችን ጨምሮ
ከ40 በላይ በሚሆኑ የመድረክ ቴአትሮች ውስጥ በትወና በዝግጅትና በድርሰት ተሳትፏል፣በፊልሞች ላይም የራሱን ድንቅ አሻራ ያኖረው ዳግማዊ ዛሬም ለሙያው ያለውን መሰጠት በማሳየት ላይ ይገኛል።

Link: https://t.me/NorRadio1

Link: https://t.me/NorRadio1
❤10
📌አብነት ገብረመስቀል ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

ለተከታታይ 24 ዓመታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ አብነት ገብረመስቀል ኦዳ፣ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን በይፋ አስታወቁ።

አቶ አብነት ውሳኔያቸውን ይፋ ባደረጉበት መግለጫ፤ ክለቡ በአሁኑ ወቅት የገጠመውን ከፍተኛ የፋይናንስ እና የአመራር ፈተና ለመታደግ እንዲሁም ለክለቡ ሰላም ሲባል ኃላፊነታቸውን መልቀቅ አስፈላጊ ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል። ውሳኔው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመመካከር...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/179
❤11🔥1😢1
📌በፊንቴክ ምክንያት የዝነኞቹ ባንክ አካውንት ታገደ

ታዋቂ ግለሰቦች እና የሚዲያ ተቋማት በባንክ የሚያንቀሳቅሱት ጥሬ ገንዘብ እንዲሁም ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረታቸው እንዲታገድ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለ ማስተላለፉ ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

እንደ ኖር ሬድዮ ዘገባ ከሆነ እግዱ የተላለፈባቸው ግለሰቦችና ተቋማት፣ “ፊንቴክ ኢንቨስትመንት” በተባለ ድርጅት አማካኝነት “ተሽከርካሪዎችን እናስመጣላችኋለን” በሚል በተፈጸመ የማጭበርበር ተግባር ውስጥ እውቅናቸውን ተጠቅመው ሕዝብ እንዲሳሳት ምክንያት ሆነዋል በሚል ተጠርጥረው ነው።

የፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ የደረሳቸው አካላት ዝርዝር፦

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፦ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ሰለሞን ቦጋለ፣ ዳንኤል ተገኝ እና ይገረም ደጀኔ።

የሚዲያ ተቋማት እና ድርጅቶች፦ አባይ ቲቪ፣ ናሁ ቲቪ፣ ...ዝርዝሩን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/187


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏19❤12
🔶ሳህለወርቅ ዘውዴ ከፍተኛ ሽልማት አግኝተዋል

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሄር ሳህለወርቅ ዘውዴ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 11ኛው ዓመታዊ የፎርብስ ሴት የአፍሪካ መሪ ሴቶች ጉባኤ ላይ የዕድሜ ልክ ስኬት ሽልማት አግኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴት አፍሪካውያን መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምሁራን እንዲሁም ልዮ ልዮ ተቋማት ተገኝተዋል።

ዝግጅቱ ከዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ጋር በሚጣጣም ሁኔታ የተዘጋጀ ሲሆን በወቅቱም ልዩ የሆነ የፓናል ውይይቶች እንዲሁም የአንድ ለአንድ ቃለ-መጠይቆች ተካሄደዋል።

በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት የቀድሞ ርዕሰ ብሄር ሳህለወርቅ ዘውዴ በተባበሩት መንግሥታትና ሃገር በማገልገል ላይ በነበሩበት ወቅት ክብር ለሰጧቸው ወንድ መሪዎች አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

#EBS

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤19👍1
🔶የኖር ሬድዮ የፌስቡክ ገፆን ይወዳጁ!

https://www.facebook.com/profile.php?id=61580759926786

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
1🔥3🥰1👏1
🔶“በነገራችን ላይ” የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተመለሰ

በተመልካቾች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈውና በደረጀ ኃይሌ የሚዘጋጀው “በነገራችን ላይ” የቴሌቪዥን ፕሮግራም፣ አዲስ ምዕራፍ ይዞ ወደ ስርጭት መመለሱ ተገለፀ።

ፕሮግራሙ ወደ አየር ሲመለስ፣ ለአምስት አስርት ዓመታት ያህል በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የኖሩትንና በርካታ ታሪካዊ ውጣውረዶችን ካሳለፉት...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/197

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏12❤8🔥1
📌ሙሴ አበባየሁ በአላቲኖስ እንግዳ ነው

በአላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማኅበር አዘጋጅነት፣ የሙያና ሥራ ጉዞ ዙሪያ የሚያጠነጥን ልዩ የውይይት መድረክ ነገ ሐሙስ መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለፀ።

በሩሲያ ሳይንስና ባሕል ማዕከል (ፑሽኪን አዳራሽ) በሚካሄደው በዚህ መርሃ-ግብር ላይ፣ወጣቱ የፊልም ባለሙያ ሙሴ አበባየሁ በፊልም እና በተለያዩ የጥበብ ዘርፎች የነበረውን የሥራ ተሞክሮና ያለፉባቸውን የሕይወት ውጣውረዶች ለታዳሚው ያካፍላል።

ዝግጅቱ በተለይ በዘርፉ ለተሰማሩ ወጣቶችና ለጥበብ አፍቃሪያን አዳዲስ ዕውቀቶችንና መነሳሳትን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4
📌ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ በአዲሱ የጃዕፈር መጽሐፍ መደብር የመጽሐፍ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ያካሂዳል

አንጋፋው ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ፣ በመጪው ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም የመጽሐፍ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት እንደሚያከናውን ታወቀ።

ይህ የፊርማ መርሃ-ግብር የሚካሄደው በቅርቡ ተመርቆ ሥራ በጀመረው አዲሱ የጃዕፈር መጽሐፍ መደብር ሲሆን፣ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ደራሲው ከአንባቢዎቹ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ለመጽሐፍ አፍቃሪያን ፊርማውን ያበረክታል።

በአዲሱ የጃዕፈር መጽሐፍ መደብር የሚካሄደው ይህ ዝግጅት፣ ለሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያንና ለደራሲው ወዳጆች በሙሉ ክፍት መሆኑ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤15👎2🥰1
📌 በፊንቴክ ምክንያት ዝነኞቹ ታሰሩ

የፌዴራል ፖሊስ ሀገሪቱን እያነጋገረ ባለው እና የበርካታ ዜጎችን ሀብት ባወደመው የ"ፊንቴክ ኢንቨስትመንት" የኤሌክትሪክ መኪና ሽያጭ ማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ ታዋቂ አርቲስቶችን እና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ጀምሯል።

በዚህም መሠረት አንጋፋው አርቲስት እና የማስታወቂያ ባለሙያ ሰራዊት ፍቅሬ፣ አርቲስት ዳንኤል ተገኝ፣ ራሱን ፕሮሞተርና ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው አብርሃም ግዛው...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/200

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏16❤2
📌"ከእንግዲህ በዘፈኑ ዓለም የለሁም"

ታዋቂው ዘፋኝ አቤል ሙሉጌታ ከዓለማዊ የዘፈን ህይወት ሙሉ በሙሉ በመውጣት ወደ መንፈሳዊ አገልግሎት መመለሱን በይፋ አስታወቀ።

ድምፃዊው ይህንን ውሳኔ ያስታወቀው "ከእንግዲህ በዘፈኑ ዓለም የለሁም" በሚል ጠንከር ባለ መልዕክት ነው።

ባለፉት ዓመታት በዘፈን ስራዎቹ የሚታወቀው አቤል፣ የዘፈን ዓለም "ውስብስብና አጋንንታዊ አሰራር ያለበት" መሆኑን በመጥቀስ፣ በተደጋጋሚ ወደ መንፈሳዊ ህይወት ለመመለስ ቢሞክርም ሳይሳካለት መቆየቱን ገልጿል። ይሁን እንጂ አሁን ላይ "የጠፋው ልጅ ተገኝቷል" በማለት ዳግም ወደ ቀድሞ እምነቱ መመለሱን አረጋግጧል።

አቤል የዘፈን ዓለምን "ቆሻሻ፣ ውሸትና ከንቱ" ሲል የገለጸው ሲሆን፣ በተለይም የዘፋኝነት ህይወት ከስካር ጋር የተቆራኘ መሆኑን ጠቁሟል::

ከ2005 እስከ 2007 ዓ.ም ለሁለት ዓመታት ያህል ዘፈን አቁሞ እንደነበረና በኋላ ግን ተመልሶ እንደገባ አስታውሷል።

ለዘማሪ በረከት አለሙ የሰጠውና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው "እሰይ" የተሰኘው ዝማሬ፣ ገና በ2003 ዓ.ም "በጨለማው ዓለም" ሆኖ የአባቱን (የፈጣሪን) ቤት ናፍቆ የጻፈው እንደነበር ገልጿል።

ድምፃዊው ከእንግዲህ ወደ ዘፈን ዓለም እንደማይመለስና ህይወቱን ለፈጣሪ አገልግሎት መስጠቱን ገልጾ፣ በዘፈን ዓለም ያሉ ጓደኞቹም የእሱን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤25😁23🤮5👍3👎2🙏2🔥1
📌ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ በቦሌ አትላስ

ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ በቦሌ አትላስ ባለ 15 ወለል የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በዛሬው እለት ለተጠቀሚዎች ለሽያጭ ማቅረቡን አስታወቀ።

የኮምፓስ ፕሮፐርቲስ ማርኬቲንግ ማናጀር ማርታ ወርቁ በቦሌ አትላስ መሸጥ የሚጀምረው የመኖሪያ ቤት ከ800 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ወይም ከ8 ሚሊየን ብር ጀምሮ አጠቃላይ ክፍያ ለቤት ገዢዎች ሽያጮችን እያቀረበ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ቤቶቹ ከባለ አንድ መኝታ እክስ ባለ ሶስት መኝታ የያዙ መሆኑን ነው አራዳ የሰማው።

ለሽያጭ የቀረቡት መኖሪያ አፓርትመንቶች ከ80 ካሬ ጀምሮ እስከ 160 ካሬ መሆናቸውን ማርኬቲንግ ማናጀሯ ገልፀዋል።

ድርጅቱ የራሱን ሪልስቴቶች ገንብቶ ከማቅረብ በተጨማሪ እንደ ጊፍት እና አያት ሪል ስቴት ያሉ ድርጅትች ላይ ስራዎችን በተቋራጭ ኮንስትራክሽን በመረከብ እየገባ ይገኛል ተብሏል።

ድርጅቱ ከዚህ በፊት በቄራ እና በመስቀል ፍላወር መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት የቤት ባለቤት ማድረጉን አስታውቋል።

አሁን ላይ ለሽያጭ ከቀረበው የቦሌ አትላስ ግንባታ በተጨማሪ በካዛንችስ የንግድና የመኖሪያ ቤቶችን በአንድ ላይ የያዘ ባለ 19 ወለል ህንፃ እየገነባ እና ለሽያጭ እያቀረበ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏12❤6