Event Addis Media
9.43K subscribers
6.32K photos
15 videos
4 files
4.93K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ሠዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን ሀሳቡን ያጋራል

79ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ ነገ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር በቀለ መኮንን(ፕ/ር) "የቶሪኖው ግብዣና የሚጤሰው ጠረንጴዛ " በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያጋራል።ይህም ውይይት እሁድ የካቲት 22 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤8👍5
📌“ኦዛና ምኒልክ” መፅሐፍ ላይ ውይይት አለ

በደራሲ ንጉሤ አየለ ተካ የተፃፈው፣ ከፍተኛ ምርምር የተደረገበት "ኦዛና ምኒልክ" የተሰኘ መፅሐፍ ዛሬ ቅዳሜ  የካቲት 28 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4 ሰዓት በወመዘክር፡ የብላቴን ጌታ ህሩይ አዳራሽ ውይይት ይደረጋል።

ከዚህ ቀደም "ታላቁ ጥቁር" የተሰኘውን ከፍተኛ ተነባቢነትን ያገኘ በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያ ላይ ያተኰረ መፅሐፍ አሳትሞ ለንባብ ያቀረበው ንጉሤ አየለ አሁን ደግሞ፤ ቀጣይ ክፍል፤ "ኦዛና ምኒልክን" ለንባብ አብቅቷል፡፡

"ኦዛና ምኒልክ" ሾለ ዳግማዊ ምኒልክ ያልተነገሩ ዕውነታዎችን  በዝርዝር የሚያስረዳ ጥልቅ የምርምር ሼል ሲሆን 460 ገፆችንም ይዟል፡፡በተለይም ደግሞ፤ የአድዋ ድል፤ በመላው ዓለም ለሚገኙ ጥቁሮች፤ የባርነትና የቅኝ ግዛትን ቀንበር ለመስበር ለሚያደርጉት ተጋድሎ እንደ አንጸባራቂ ኮከብ ሆኗቸው እንደነበር በዝርዝር ያትታል። በደቡባዊ አሜሪካ አገሮች የነበረውን ሰፊ እንቅስቃሴ በስፋት ያሳያል።

ደራሲ ንጉሤ አየለ ተካ ፣በሚኖርበት አሜሪካን አገር፤ በሚገኙ ታላላቅ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ጊዜውን በማሳለፍ አዳዲስ የታሪክ ዕውነቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንባቢ ፅፎ አቅርቧል።

ደራሲ ንጉሤ አየለ ተካ፣ ከዚህ ቀደም ሐኖስ ፣የገራዶ ዋሽንት፣ ጣዝማ እና ሌሎች 7 መጻሕፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን በ1970ዎቹ አጋማሽ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ- ፅሑፍ ክፍልም ተመርቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤7👍2
📌የኢትዮጵያውያን ሠዓልያን ሥራ የት ገባ?

አዘርባጃን ኤምባሲ ላይ የቀረበው ቅሬታ

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአዘርባጃን ኤምባሲ፣ ከዛሬ አንድ ዓመት ተኩል በፊት ለውድድርና ለአውደ ርዕይ በሚል የወሰዳቸውን የኢትዮጵያውያን ሠዓልያን የፈጠራ ሥራዎችን አልመለሰም ስለመባሉ ተዘገበ።

ኤምባሲው ከአለላ መልቲሚዲያ እና ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "ተጓዥ ኪነ-ጥበባት" በሚል የሰየመውንና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ውድድር ማዘጋጀቱ ይታወሳል።

በውድድሩም 17 ኢትዮጵያውያን ሠዓልያን የተሳተፉ ሲሆን፣ አሸናፊ ለሚሆኑ አራት ባለሙያዎች የገንዘብ ሽልማትና ወደ አዘርባጃን የጉዞ ዕድል ቃል ተገብቶላቸው እንደነበር ተገልጿል።

ይሁንና አሸናፊ ያልሆኑ ሠዓልያን ሥራዎቻቸው እንዲመለሱላቸው ደጋግመው ቢጠይቁም ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል። ከነዚህም መካከል አርቲስት ምህረቱ ዋሴ፣ በአዝራር የሰራው የኔልሰን ማንዴላ ምስል ያለፈቃዱ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት በስጦታ መበርከቱን በሚዲያ መመልከቱን በመጥቀስ ቅሬታውን አቅርቧል።

አሸናፊ ተብለው የተለዩት ሠዓልያንም ቢሆኑ የተገባላቸው የገንዘብ ሽልማትም ሆነ የጉዞ ዕድል እስካሁን አልተፈጸመላቸውም።

ሠዓልያኑ ሥራዎቻቸውን በራሳቸው ወጪ ማዘጋጀታቸውን ጠቅሰው፣ የፈጠራ ውጤቶቻቸው ያለ እውቅና ለሦስተኛ ወገን መሰጠታቸው "ማጭበርበር ነው" ሲሉ ተናገረዋል።

ኤምባሲውን ለማነጋገር ቢሞክርም፣ ኤምባሲው ጥያቄውን ወደ አለላ መልቲሚዲያ መርቷል። የአለላ መልቲሚዲያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አደራጀው አስፋው በበኩላቸው ድርጅታቸው ሥራዎቹን በአዘርባጃን ለነበረው "ኮፕ 29" ጉባኤ የመውሰድ ዕቅድ እንደነበረ አስረድተዋል።ነገር ሀሳብ አልተሳካም።

©️መሠረት ሚዲያ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5🤔4🤬1
📌የሙዚቀኛ ጣሰው ወንድም የዋሽንት አልበም

በመሶብ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ ውስጥ በዋሽንት ተጫዋችነቱ የምናውቀው ጣሰው ወንድም "ምናባዊ" ቁጥር ሁለት የተሰኘ የዋሽንት የሙዚቃ አልበሙን ዛሬ ለአድማጮች ያቀርባል።

የ"ምናባዊ" ቁጥር ሁለት አልበም ምርቃቱና የሙዚቃ ዝግጅቱ ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በሞሶብ የሙዚቃ ማዕከል በደመቀ ሁኔታ እንደሚከናወን ተገልጿል።

በዚህ የሙዚቃ ምሽት ላይ ሙዚቀኛ ጣሰው ወንድም በዋሽንት ጥበቡ ታዳሚውን የሚያዝናና ሲሆን፣ ስመ-ጥሩው የፒያኖ ተጫዋች አብይ ወልደማርያምም አብሮት በመሆን ጥበባዊ ስራዎቹን እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ባህላዊ የዋሽንት ዜማ ከዘመናዊ የሙዚቃ ቅንብር ጋር አዋህዶ የሚያቀርብ እንደሆነም ይጠበቃል።

"ምናባዊ "ቁጥር ሁለት ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፍ አዲስ የጥበብ ቀለም እንደሚጨምር ተነግሮለታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤8👍2🙏1
📌"ዐውደ ፋጎስ" የውይይት መሰናዶ ነገ ይካሄዳል

የዕውቀትና የውይይት መድረክ "ዐውደ ፋጎስ" 80ኛ ዙር ዝግጅቱን ነገ እሁድ የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በሥነ-አመክንዮ ርዕሰ-ጉዳይ ላይ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

በዕለቱ የሥነ-አመክንዮ መጽሐፍ አዘጋጅ የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ በጉዳዩ ዙሪያ ሰፊ ትንታኔና የመነሻ ጽሑፍ ለታዳሚው የሚያቀርቡ ይሆናል።

መድረኩ በአገራችን የምሁራን ውይይት ባህልን ለማሳደግና ረቂቅ የሆኑ የፍልስፍናና የዕውቀት ዘርፎችን ለሰፊው ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ አልሞ የሚሰራ እንደሆነ ይታወቃል።

ይህ መርሃ-ግብር ነገ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት (ወመዘክር) በሚገኘው በመርስዔ ኃዘን ወልደ ቂርቆስ አዳራሽ የሚከናወን ሲሆን፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የጥበብ አፍቃሪያን በሰዓቱ ተገኝተው እንዲሳተፉ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤3👍2
የዓለማየሁ ገላጋይ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ በሥራዎቹ ስም ያተረፈው ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ፣ "ፈሪሳ" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲሰሰ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመልክታል።

ይህ አዲስ መጽሐፍ ለደራሲው አሥረኛ የልብ-ወለድ ሥራው መሆኑ ተገልጿል። ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ከዚህ ቀደም "ወሪሳ"፣ "በፍቅር ስም"፣ "ታለ በእውቀት ስም"፣ "ሀሰተኛው በእምነት ስም" እና "ውልብታ"ን የመሳሰሉ በአንባቢያን ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፉ የልብ-ወለድ መጻሕፍትን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል።

አዲሱ መጽሐፍ "ፈሪሳ" ምን ዓይነት ጭብጥና የሥነ-ጽሑፍ ጣዕም ይዞ እንደሚመጣ በጉጉት እየተጠበቀ ሲሆን፣ በቅርቡ ለገበያ እንደሚቀርብ ሰምተናል።

ደራሲው በረቂቅ የቋንቋ አጠቃቀሙና በጥልቅ ማህበራዊ ትችቶቹ የሚታወቅ በመሆኑ፣ ይህ አሥረኛ ሥራው በሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ ትኩረት ስቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤23👍3🥰2🤗2👎1🙏1
📌ኢዜማ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ከመሪነት አሰናበተ

አዜማ ፓርቲ በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶውን ያስተዋወቀ ሲሆን፥ በቀጣይ የሚመራበትን 50 ፖሊሲዎችንም ለአባላቱ ይፋ አድርጓል፡፡

ፖሊሲዎቹ በተለይም በሀገር መንግስት ግንባታ፣ በብሔራዊ ጥቅም፣ ልማትና ኢኮኖሚ እንዲሁም በአካታችነትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ኢዜማ በአስቸኳይ ስብሰባው በቀጣይ መሪውን መርጧል...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/154


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤3😁2
📌“ሄር ስቶሪ” የሥዕል አውደርዕይ ተከፈተ

“ሄር ስቶሪ” የተሰኘ የጋራ የሥነ-ጥበብ ዐውደርዕይ ባሳለፍነው ቅዳሜ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ዘ ስፔስ ኢትዮጵያ” ጋለሪ ውስጥ áˆˆá‰°áˆ˜áˆáŠŤá‰žá‰˝ ክፍት ሆኗል። እስከ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስም ይቆያል።

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው በዚህ ዐውደርዕይ ላይ፤ አሌክሳንድራ ምትኩ፣ ብሌን ደረሰ፣ ፍቅርተ አያና፣ ምሕረት እሸቱ፣ ኒና ኡርጌሳ፣ ራፋኤላ ፍቃዱ፣ ሩት አስክንድር እና ሩት ጌታቸው የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለታዳሚ አቅረበዋል።

ይህ ዐውደርዕይ ለቀድሞዋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰቢያነት የተበረከተ መሆኑ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤7👍1🙏1
📌"ዥዋዥዌ የአዲስ አበባ መድበል"

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ስድስት ሴት ከያንያን ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት "ዥዋዥዌ - የአዲስ አበባ መድበል" የተሰኘ ልዩ የሥነ-ጥበብ ዐውደ-ርዕይ በመጪው ቅዳሜ መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከፈት ተገለጠ።

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ሥነ-ጥበባት ማዕከል የሚቀርበው ይህ ዐውደ-ርእይ፤ በታዋቂዋ ፎቶ አንሺ ማህደር ኃይለሥላሴ አሰናጅነት የተዘጋጀ ነው። በኤግዚቢሽኑ ላይ ሳሌም መኩሪያ፣ ዓይናለም ገብረማርያም፣ ጽዮን ኃይለሥላሴ፣ ሄለን ዘሩ፣ ነፃነት ገብረሚካኤል እና ማህደር ኃይለሥላሴ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ያላቸውን የግል እና የጋራ ትስስር በፈጠራ ሥራዎቻቸው የሚዳስሱበት ይሆናል።

የሥነ-ጥበባት ማዕከሉ እንዳስታወቀው፣ የዐውደ-ርእዩ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ቅዳሜ ከቀኑ 8፡30 ላይ የሚከናወን ሲሆን ማንኛውም የጥበብ አፍቃሪ በዝግጅቱ ላይ እንዲታደም ግብዣ ቀርቧል።

ማዕከሉ የሚገኘው በጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደሆነ ታውቋል።

ይህ ዐውደ-ርእይ በሴቶች ላይ ትኩረት ከማድረጉም ባለፈ፣ የአዲስ አበባን ሁለንተናዊ ገጽታ በሴት ከያንያን እይታ ለመመልከት ዕድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤3
📌 "ሐረግ" ቴአትር ወደ መድረክ ተመለሰ

ተቋርጦ የነበረውና "ሐረግ" የተሰኘው የአንድ ሰው የሙሉ ጊዜ ተውኔት ዛሬ አመሻሹን በድጋሚ ወደ መድረክ እንደሚመለስ አዘጋጆቹ ለኤቨንት ሚዲያ አስታውቀዋል።

ይህ በደራሲና አዘጋጅ ክብይናድ አሰፋ የተዘጋጀው ተውኔት፤ በትያትር አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን፣ አሁን ላይ በቋሚነት ለዕይታ ዝግጁ መሆኑ ተረጋግጧል።

ተውኔቱ ዘወትር ማክሰኞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ለታዳሚ እንደሚቀርብ ታውቋል።

በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ በሚቀርበው በዚህ ሥራ፣ ተዋናይት ሃና ጌትነት በብቸኝነት ትተውናለች።

የዝግጅቱ አስተባባሪዎች እንደገለጹት፣ ተውኔቱ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳዮችን በጥልቀት የሚዳስስ ሲሆን፣ በትያትር ጥበብ ውስጥ ከፍተኛ አቅም የሚጠይቀውን የአንድ ሰው ትወና በልዩ ሁኔታ እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

ማንኛውም የጥበብ አፍቃሪ ዘወትር ማክሰኞ በብሔራዊ ቴአትር በመገኘት ዝግጅቱን መታደም እንደሚችል ተመልክቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤6
📌የ35 ሚሊዮን ብር ልዩነት በአንድ ዓመት ብቻ ?

ዘንድሮ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሽልማቱ ስንት ነው?

በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች የሚያገኙት የሽልማት እና የጥቅማጥቅም መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር እጅግ የወረደ መሆኑ ተሰማ።

የሊጉን የሥርጭት መብት የወሰደው ኦቢኤን (OBN) ቴሌቪዥን ለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በዓመቱ መጨረሻ የሚከፍለው ጠቅላላ ክፍያ 200 ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑ ተገልጿል። ይህም በሊጉ ተሳታፊ የሆኑ 16 ክለቦች የሚያገኙትን የገቢ ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ ዝቅ እንዲል አድርጎታል።

ባለፈው የውድድር ዘመን የዲኤስቲቪ (DSTV) የሥርጭት ስምምነት በነበረበት ወቅት፣ ለክለቦች የተከፋፈለው የገንዘብ መጠን 406 ሚሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፤ ዘንድሮ ግን ይህ መጠን ከ50 ሚሊዮን ብር በታች ሊወርድ እንደሚችል ተመልክቷል።

የሽልማት መጠኑን አስመልክቶ በወጣው መረጃ መሠረት፤ ባለፈው ዓመት የሊጉ ሻምፒዮን የሆነው ኢትዮጵያ መድን 40 ሚሊዮን ብር የተሸለመ ቢሆንም፣ የዘንድሮው የሊጉ አሸናፊ ግን ...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/156


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤2👍2😁1
📌እንዳልክ አሰፋ ትችት ቀረበበት

የ"ዕርቅ ማዕድ" ፕሮግራም አዘጋጅ የነበረው እንዳልክ አሰፋ፣ በቅርቡ በዩቲዩብ ቻናሉ ባቀረበው ዝግጅት የባለታሪኮችን ሰብአዊ ክብር የሚነኩ አቀራረቦችን ተጠቅሟል በሚል ከጋዜጠኞችና ከሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጥብቅ ትችት እየቀረበበት ይገኛል።

ትችቱን ካቀረቡት መካከል ጋዜጠኛ ቃልኪዳን እና እመቤት ደመቀ የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ጋዜጠኛው በፕሮግራሙ ላይ የቀረቡ ሁለት ሴቶችን ፊት ለፊት በማጋጠም እርስ በእርስ እንዲናናቁና እንዲሰዳደቡ መንገድ ከፍቷል ሲሉ ወቅሰዋል።

በተለይም የሦስት ልጆች እናት የሆነችን ባለታሪክ “ራስሽን አትጠብቂም፣ ዝርክርክ ነሽ” የሚሉ የግል ክብሯን የሚነኩ ንግግሮችን በአደባባይ በማንሳቱ፣ ዝግጅቱ ከዕርቅ ይልቅ የሞራል ስብራትን የሚያስከትል ነው ተብሏል።

ተቺዎቹ አክለውም፣ ጋዜጠኛው የዲኤንኤ (DNA) ምርመራ ውጤቶችን እንደ ውድድር ውጤት “ልብ አንጠልጣይ” ለማድረግ ጊዜ መውሰዱ እና በሰው ስቃይ ....ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/159

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍8😁5❤4👎1👏1
📌 ኢዜአ 6 ሪፖርተሮችን መቀጠር ይፈልጋል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ካለው የሥራ ስፋትና ፍላጎት አንጻር፣ በተለያዩ ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ብቁ የሆኑ አመልካቾችን በሪፖርተርነት አወዳድሮ ለመቅጠር መፈለጉን ገለጸ።ከ2 ዓመት እንዲሁም ከዛም በላይ ልምድ ያላችሁ ባለሞያዎች ትፈለጋላችሁ።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ መስፈርቱን የሚያሟሉና በዘርፉ ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች በተጠቀሰው የጊዜ ገደብና ቦታ በመገኘት ማመልከት እንደሚችሉ አስታውቋል።

ይህ የቅጥር ማስታወቂያ ተቋሙ ያለውን የሰው ኃይል አቅም ለማጠናከርና የሚሰጣቸውን የሚዲያ አገልግሎቶች ጥራት ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተመልክቷል።

አመልካቾች ስለ ቅጥሩ ዝርዝር መረጃ፣ ስለሚያስፈልጉት የትምህርት ዝግጅቶችና የሥራ ልምድ መረጃዎችን ከተያያዘው የቅጥር ሰነድ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111-552300 በመደወል መጠየቅ እንደሚቻል ተቋሙ ጠቁሟል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4
📌በቴሌቪዥን ድራማ ጽሑፍ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ሥነ ጥበባት ማዕከል ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ጽሑፍ ዙሪያ ሙያዊ ውይይት አካሄደ፡፡

በዝግጅቱ ላይ አራት በኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ደራስያን ተገኝተው ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

የፊልም እና ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ደራሲዋ ቤዛ ኃይሉ ውይይቱን ከመምራት ባሻገር ልምዷን በየመካከሉ አካፍላለች፡፡

በዝግጅቱ ላይ “ትርታ”፣ “የእግር እሳት”፣ “የውሃ ሽታ”፣ “መዘዝ”፣ “የባስሊቆስ እንባ”፣ “በስንቱ” ሲትኮም እና የሌሎችም ሥራዎቹ የሚታወቀው ሶፎንያ ታደሰ ተገኝቶ ልምዱን ለወጣቶች ካካፈሉት መካከል አንዱ ነው፡፡

በመቀጠለም “የአቶ እና ወይዘሮ”፣ “ስቄ ልሙት”፣ “ማንያዘዋል”፣ “ሁለት ጉልቻ”፣ “እንደ አንድ” የቴሌቪዥን ድራማ፣ የ”አሻራ” ቴሌ ኖቬላ ደራሲ ኑር አክመል ሌላኛው እንግዳ ነበር፡፡

እንዲሁም “የወደፊት”፣ የ”ሰኔና ሰኞ”፣ የ “ዘጠነኛው ሺ”፣ የ “ምስኪኖቹ”፣ የተማሪ ቤት ድርሰቶች፣ በዳይሬክቲንግ እና በሌሎቹም ኃላፊነቶቹ የሚታወቀው ወንድማገኝ ለማ ተገኝቷል፡፡

የተወዳጁን የሀዲስ አለማየሁ ሥራ የሆነውን “ፍቅር እስከ መቃብር”ን የተከታታይ ቴሌቪዥን ድራማ ጽሑፍ ላይ የተሳተፈው፣ የ“ዕጸ ሕይወት” ቴሌ ኖቬል ድራማና የ“ፓይለቶቹ” ቴሌቪዥን ደራሲ መልካሙ ኃይሌ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

የፓነል ውይይቱ ላይ የፊልም ኢንደስትሪውን የተቀላቀሉ፣ ጀማሪ ጸሐፊያንና ፍላጎቱ ያላቸው ሰዎች ታድመውበታል፡፡ ከመድረኩ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የመድረኩ ዝግጅት አነሳሽ ደራሲ ቤዛ ኃይሉ ውይይቱ ወደፊት በወርክሾፕ መልኩ እንደሚቀጥል ተስፋዋን ገልጻች፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤7👍1
📌"በጉዳዩ በጣም አዝኛለሁ፤ በግኛለሁም"

ታዋቂው ገጣሚ እና ደራሲ ሰለሞን ሳህለ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመጽሐፍት መላኪያ ላይ በጣለው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የተሰማውን ቅሬታና መከፋት በይፋ ገለጸ።

ደራሲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ መሠረት፣ ስድስት መጽሐፍትን በፖስታ ቤት በኩል ወደ ውጭ አገር ላሉ ወዳጆቹ ለመላክ 16 ሺህ 422 (አሥራ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሃያ ሁለት) ብር እንዲከፍል መደረጉን ገልጿል። ይህም ክፍያ ከመጽሐፍቱ ዋጋና ከቀድሞው አሠራር አንጻር እጅግ የተጋነነ መሆኑን በመጠቆም "በጉዳዩ በጣም አዝኛለሁ፤ በግኛለሁም" ሲል ቁጭቱን ገልጿል።

ደራሲ ሰለሞን ሳህለ "አሁን ይሄ ምንድን ነው የሚባለው?" ሲል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ መረጃው ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስና በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥበትም ጥሪ አቅርቧል። በኢትዮጵያ የፖስታ አገልግሎት ድርጅት በኩል በቅርቡ የተደረጉ የዋጋ ማሻሻያዎች መኖራቸውን ተከትሎ፣ መሰል ቅሬታዎች ከሌሎች ደራሲያንና ደንበኞችም እየተሰሙ ይገኛሉ።እስከ አሁን ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ለደራሲው ቅሬታ የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍13❤9
📌ሚሊኒየም አዳራሽን የማፍረስ ስራ ተጀመረ

ባለፉት 18 ዓመታት በኢትዮጵያ ግዙፍ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች ሲያስተናግድ የቆየው ሚሊኒየም አዳራሽ፣ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለታቀደው ሰፊ የመልሶ ግንባታና የማስፋፊያ ስራ እንዲመች የማስፈረስ ሂደት መጀመሩን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

ይህ ታላቅ የአዳራሽ እድሳትና የማስፋፊያ ፕሮጀክት በዋናነት ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው 32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ዝግጅት አካል ሲሆን፣ በቦታው ላይ Moxy by Marriott የተሰኘ ግዙፍና ዘመናዊ ሆቴል...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/162


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👎6🔥2❤1👏1
መጸዳጃ ቤቶቹ የተሸገበት ሆቴል

ዲሊዮ ፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል ከብክለት ጋር በቀረበበት ክስ መጸዳጃ ቤቶቹ ታሸጉ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት የሽንት ቤት ፍሳሽ ቆሻሻን በተደጋጋሚ ወደ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ የለቀቀው ዲሊዮ ፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል ለብክለቱ መነሻ ችግሩ የሆኑ ክፍሎቹን በማሸግ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ድርጊቱ የተፈጸመዉ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ባንቢስ አከባቢ ሲሆን ተቋሙ ከአሁን በፊት የሽንትቤት ፍሳሽን ወደ ወንዝ በመልቀቅ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመሆን የገንዘብ ቅጣት ጥሎበት ነበር።

መጀመሪያ ሆቴሉ ከጥፋቱ እንዲማር 300 ሺህ ብር ቅጣት ጥሎበት ከቅጣፋቱ ሳይማር በመቅረቱ በድጋሚ የቅጣቱን እጥፍ 600 ሺህ ተቀጥቶ ነበር። አሁንም ግን ድርጊቱን ለ3ኛ ጊዜ ባለማስተካከሉ ሆቴሉ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ የመጸዳጃ ክፍሎቹን እንዲታሸግ ተደርጓል።

ተቋሙን በቀጣይ በሕግ ተጠያቂ በማድረግ ላደረሰው ከፍተኛ ጉዳት በሕጉ መሠረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው የተሰሩ ወንዝና የወንዝ ዳርቻዎች ልማቶች በመበከል ለታለመለት ዓላማ እንዳይውል በሚያደርጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ የሚወስደውን አስተዳደራዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለሥልጣኑ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ገልጿል።

Link: https://t.me/NorRadio1

Link: https://t.me/NorRadio1
👏6❤2🫡2
የ“ጃር” ውሃ ጥራት ላይ ጥናት ሊካሄድ ነው

በተለምዶ “ጃር” እየተባለ በሚጠራውና በ20 ሊትር መያዣ ታሽጎ ለገበያ በሚቀርበው የመጠጥ ውሃ ላይ በተደጋጋሚ የሚነሱ የጥራት መጓደል ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያግዝ አገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ እንደሆነ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን ነው።

ባለሥልጣኑ ለአሐዱ እንደገለጸው፣ ጥናቱ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት እና የሕብረተሰቡን ጤና መጠበቅን ዓላማ ያደረገ ነው።

“ከሕብረተሰብ ጤና እና ደህንነት የሚበልጥ ምንም ዓይነት ነገር የለም” ያሉት የባለሥልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈጸም ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙላቱ ተስፋዬ፣ ከተገልጋዮች በየጊዜው የሚደርሱ ጥቆማዎችና አቤቱታዎችን መሠረት በማድረግ ተቋሙ በጃር ውሃ ጥራት ላይ ጥብቅ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ሥራ አስፈጻሚው በማብራሪያቸው የጥራት ችግሩ የዜጎችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ሆኖ ከተገኘ ምርቱ ሙሉ በሙሉ ሊታገድ እንደሚችል ጠቁመዋል።በተጨማሪም “ባለ 20 ሊትሩ የታሸገ ውሃ መያዣ (ጃሩ) ተደጋግሞ ጥቅም ላይ የሚውል በመሆኑ፣ በጽዳት እና ሥርጭት ሂደት ከፍተኛ ጥንቃቄን ይፈልጋል።” ብለዋል።

ባለሥልጣኑ በአሁኑ ወቅት ከአመራረት እስከ ገበያ ያለውን ሂደት በመከታተል እና ናሙና በመውሰድ ምርመራ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በማከፋፈያ ቦታዎች ላይ ጭምር ክትትል እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ የተፈጠረውን የጥራት ስጋት በዘላቂነት ለመፍታት የሚካሄደው አገር አቀፍ ጥናት እንደተጠናቀቀም፣ የምርቱን ደህንነት የሚያረጋግጥ አዲስ መመሪያ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል ተጠቁሟል።

©️አሐዱ ሬድዮ

Link: https://t.me/NorRadio1

Link: https://t.me/NorRadio1
❤13👏5👍1🤨1
📌"አክሊሉ" ታሪካዊ ልቦለድ ነገ ይመረቃል

በታዋቂው ዲፕሎማት ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ሕይወትና የሥራ ዘመን ላይ የሚያጠነጥን "አክሊሉ" የተሸኘ ታሪካዊ ልቦለድ መጽሐፍ፣ ነገ ቅዳሜ መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ይመረቃል።

መጽሐፉን ያዘጋጁት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ሰላማዊት ታደሠ ሲሆኑ፤ ምረቃውም ታዋቂው ዲፕሎማት በተወለዱበት መጋቢት 5 ቀን እንዲሆን መታቀዱ ተገልጿል።

ባለ 296 ገጹ ይህ መጽሐፍ፣ ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ከአሥራ ዘጠኝ ዓመታቸው ጀምሮ አገራቸውን በዲፕሎማሲውና በፖለቲካው መስክ ያገለገሉበትን ታሪክ፣ በተለይም የኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የመቀላቀል ሂደትና ሌሎች ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎቻቸውን በልቦለድ ቅርፅ ለንባብ የሚያበቃ መጽሐፍ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

Link: https://t.me/NorRadio1

Link: https://t.me/NorRadio1
❤5
📌ዳግማዊ  አመለወርቅ ፊይሣ ሊመሰገን ነው

በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ በዳይሬክተርነት እና በደራሲነት ያገለገለው ዳግማዊ አመለወርቅፈይሳ አድናቂዎቹ የሙይጎደኝቹ በተገኙበት የምስጋና መርሀ ግብር ሊደረግለት እንደሆነ ታወቀ።

መጋቢት7 ከቀኑ11ሰዓት በኃላ የሙያ ባልደረቦቹ፣ አድናቂዎቹ እና የቅርብ ሰዎቹ በሚታደሙበት በታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሚመሰገነው ዳግማዊ  ፈይሳ በጥበቡ ዓለም 40አመታትን ቆይታ አድርጓል። 

የምስጋና መርሀ ግብሩ አዘጋጅ ሔኖክ የእታገኝ ልጅ እንደሆነም ታውቋል።

"ስሙአተ- ነገር "የሚል ርዕስ ባለው በዚህ መርሀ- ግብር ላይ ልዩ ልዩ ተመስጋኙን የሚመጥኑ የጥበብ ዝግጅቶች ይኖራሉ ተብሏል።

ዳግማዊ ዓመለ ወርቅ ፈይሳ በ1960 ዓ.ም አ.አ አብነት አካባቢ ጠጅ ሳር ሰፈር ነው የተወለደው።

ዳግማዋ ለ17 ዓመታት ያህል ስክሪፕት በመጻፍ፤ ከ 500 በላይ  ዶክመንተሪዎችንና 1000 ማስታወቂያዎችን  በመስራት ድንቅ ባለሙያነቱን አስመስክሯል።

ዓመል የቴሌቭዥን ድራማ፤ የቃቄ  ውርዶዎት  ከመጋረጃ ጀርባ የተሰኙ ቴአትሮችን ጨምሮ
ከ40 በላይ በሚሆኑ የመድረክ ቴአትሮች ውስጥ በትወና በዝግጅትና በድርሰት ተሳትፏል፣በፊልሞች ላይም የራሱን ድንቅ አሻራ ያኖረው ዳግማዊ ዛሬም ለሙያው ያለውን መሰጠት በማሳየት ላይ ይገኛል።

Link: https://t.me/NorRadio1

Link: https://t.me/NorRadio1
❤10
📌አብነት ገብረመስቀል ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

ለተከታታይ 24 ዓመታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ አብነት ገብረመስቀል ኦዳ፣ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን በይፋ አስታወቁ።

አቶ አብነት ውሳኔያቸውን ይፋ ባደረጉበት መግለጫ፤ ክለቡ በአሁኑ ወቅት የገጠመውን ከፍተኛ የፋይናንስ እና የአመራር ፈተና ለመታደግ እንዲሁም ለክለቡ ሰላም ሲባል ኃላፊነታቸውን መልቀቅ አስፈላጊ ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል። ውሳኔው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመመካከር...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/179
❤11🔥1😢1