Event Addis Media
9.43K subscribers
6.32K photos
15 videos
4 files
4.93K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌መልቲቾይስ ኢትዮጵያ ለመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና ዕድል አስጀመረ

መልቲቾይስ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ከፍተኛ አቅም ያላቸውን ተማሪዎች በዲጂታል እውቀትና በኮዲንግ ክህሎት ለማብቃት የሚያስችለውን “የኢትዮጵያ የወደፊት ባለ ክህሎቶች" የተሰኘ የሥልጠና ዕድል በይፋ አስጀመረ።

ይህ ሥልጠና የኩባንያው የማኅበራዊ ኃላፊነት (CSI) ስትራቴጂ አካል ሲሆን፣ መልቲቾይስ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ተኮር አጋርነቱን ለማጠናከርና በሀገር ተስፋዎች ላይ የአቅም ግንባታ ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

የመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገሊላ ገብረሚካኤል እንደገለጹት፣ የመልቲቾይስ አፍሪካ “ሕይወትን ማበልጸግ” መርህ ተጨባጭ ተፅዕኖ በመፍጠር ላይ የተመሰረተ ነው። "ይህ የቴክኖሎጂ ሥልጠና ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዲጂታል ክህሎቶችን በሚገባ እንዲጨብጡና በቀጣዩ የዲጂታል ዓለም በልበ ሙሉነት እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚያነሳሳ ትልቅ እርምጃ ነው" ሲሉም አክለዋል።

ለ12 ሳምንታት በሚቆየው በዚህ የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና፣ ካመለከቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች መካከል 30 ተማሪዎች ተመርጠው ሥልጠናውን የጀመሩ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 50 በመቶው ልጃገረዶች መሆናቸው ልዩ ያደርገዋል።

ሥልጠናው ጥራቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሰጥ መልቲቾይስ ኢትዮጵያ ከየኔታ ኮድ አካዳሚ ጋር በመተባበር እያከናወነው ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተጀመረው ይህ ፕሮግራም፣ ወደፊት ወደ ክልል ከተሞችም የመስፋፋት ዕቅድ እንዳለው ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤6👏1
📌ቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ የመዘጋት ስጋት ላይ ነው

የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ፣ ከመንግስት የሚሰጠው በጀት ካልቀጠለ በስተቀር በሚቀጥሉት ሰባት ሳምንታት ውስጥ ስራውን ሊያቆም እንደሚችል ተነገረ።

የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር ቲም ዴቪ እንዳስታወቁት፣ የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ዓመታዊ በጀት 400 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን፣ አብዛኛው የሚሸፈነው ከአገር ውስጥ የፍቃድ ክፍያ ነው። የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለፈው ዓመት 137 ሚሊዮን ፓውንድ አስተዋጽዖ ያደረገ ቢሆንም፣ ይህ የገንዘብ ድጋፍ በመጋቢት ወር መጨረሻ (እ.ኤ.አ. March 2026) ያበቃል።

እስካሁን ድረስ ከዚያ በኋላ የሚሆን ምንም ዓይነት የገንዘብ ዋስትና ወይም ዕቅድ የለም።

የቀድሞው የተመድ ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን "ብሪታንያ ለዓለም የሰጠችው ትልቁ ስጦታ" ሲሉ የገለጹት ይህ ተቋም፣ በ43 ቋንቋዎች የተለያዩ ይዘቶችን ያሰራጫል። (የአማርኛ አገልግሎትን ጨምሮ ማለት ነው) በሳምንት 313 ሚሊዮን ሰዎችን ይደርሳል።

በኢራን፣ አፍጋኒስታን፣ ዩክሬን፣ ጋዛ እና ሱዳን ባሉ የጦርነት ቀጣናዎች ለሚገኙ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ብቸኛው የመረጃ ምንጭ እና የሕይወት አድን መስመር ነው።

የቢቢሲ መዳከም በዓለም አቀፍ የመረጃ ፍሰት ላይ ትልቅ ክፍተት ይፈጥራል ተብሎ ተሰግቷል።

የቢቢሲ መሪዎች እንደሚከራከሩት፣ ወርልድ ሰርቪስ የእንግሊዝን ባሕል እና ተጽዕኖ ለዓለም ከማስተዋወቅ ባለፈ የሀገሪቱ የብሔራዊ ደሕንነት አካል ነው። ሐሰተኛ መረጃዎች እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በበዛበት በዚህ ዘመን፣ ዕውነተኛ ጋዜጠኝነትን የሚተካ ምንም ነገር እንደሌለ ትንታኔው ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5👍2👏1
📌አስፈሪው አውሬ በምዕራብ ሸዋ ስጋት ፈጠረ

የኤርዶጋን ጋረዶች፣ ባለሂጃቧ ተርጓሚ !

⚓️የዛሬው የኖር ሬድዮ ወሬ ገበያ  የደራ ነው !

እነዚህ ጉዳዮችን ይዟል እነሆ:-

1. አስፈሪው አውሬ በምዕራብ ሸዋ ስጋት ተፈጠር

ደም መጥጦ ከመጣል ውጪ የሰው ስጋ እንደማበላ የተነገረለት አስፈሪ አውሬ የምዕራብ ሸዋ ነዋሪዎችን አስጨንቋል። በህብረተሰቡ ላይም ተደጋጋሚ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ ኖር ሬድዮ ሰምቷል።

2.የኤርዶጋን ጋረዶች፣ ባለሂጃቧ ተርጓሚ !

የፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን
ለየት ያለ አቀባበል፣አረንጓዴ ልብስ ያጠለቁ የደህንነት ጥበቃዎች እና ሃጃብ የለበሰችው አስተርጓሚ ፣እጅግ ለይት ያለው የመኪና ስጦታ፣የፕሬስዳንቱ ያልተጠበቀ ንግግር ልዩ ዘገባ በኖር ሬድዮ ወሬ ገበያ ይዘናል።

ወሬዎቹን ይሄው በዚህ በኩል ያድምጡ

Link:-https://youtu.be/dFfvxZhdAME?si=PvdrFo1FyCo3sJVU

በተጨማሪም የፌስቡክ ገጻችንን ይወዳጁ!

https://www.facebook.com/profile.php?id=61558246481526

የቴሌግራም ቻናላችንን ብትቀላቀሉም ደስተኛ ነን

https://t.me/NorRadio1

እናመሰግናለን !
❤8
📌89ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር 89ኛውን የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል በስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት ፊት ለፊት አክብሯል። በበዓሉ ላይ አባትና እናት አርበኞች በመገኘት የአበባ ጉንጉን በማኖር የሰማዕታቱን መስዋዕትነት ዘክረዋል።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ ወጣቱ ትውልድ አያትና ቅድመ አያቶቹ ለሀገር ፍቅርና ለአንድነት የከፈሉትን የሕይወት መስዋዕትነት በማሰብ፣ ሀገሩን ከጠላት ጥቃት እንዲጠብቅና ልማቷን እንዲያስቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በየጊዜው በውስጥ ባንዳዎችና በውጭ ጠላቶች ሰላሟን ለማደፍረስና ሕዝቧን አንገት ለማስደፋት የሚደረጉ ሙከራዎችን በልጆቿ ጀግንነት ስታከሽፍ የኖረች፣ በደሟ ታፍራና ተከብራ የቆየች ሀገር መሆኗንም ፕሬዝዳንቱ አክለው ገልጸዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤23
📌በጅብ ላይ ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ የህክምና ወጪውን እንዲሸፍን ተፈረደበት 😂

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሂርና ከተማ አስተዳደር  ሀዬታ ቀበሌ ውስጥ ከጫካ የወጣ ጅብ በሰው ተመቶ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን የፖሊስ ፅ/ቤት አስታውቋል።ጉዳት የደረሰበት  ጅብ የህክምና እርዳታ አግኝቶ ወደጫካው መመለሹ ተገልጿል።

የሂርና ከተማ መደሀዮታ ቀበሌ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ፅ/ቤት ሃላፊ  ኢንስፔክተር ሬድዋን ኢብራሂም ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ጅቡ ከጫካ የወጣው ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም  ምሽት ሶስት ሰዓት  ላይ ሲሆን  አንድ ግለሰብ ቤት አካባቢ ሲጮህ የቤቱ ባለቤት ጅቡን ለማባረር በወረወረው ድንጋይ ጅቡ በሁለት እግሮቹ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል ።

ጅቡ ጉዳት ሲደርስበት በአካባቢው ፖሊስ እና  ባህላዊ ፍርድቤት ግቢ ገብቶ ጥቅልል ብሎ በመተኛት የደረሰበትን ጉዳት በጩኸት ሲገልጽ እንደነበረ ተጠቁሟል ።የጅቡን ጩኸት የተመለከቱ የፖሊስ አባላትም ግቢያቸው የገባውን የጫካ ጅብ ከማባረር እና ከመጉዳት ይልቅ ምግብ እና  ውሃ  በመስጠት አሳድረውታል። 

በነጋታውም ለጅቡ የሚያስፈልገውን በመስጠት ጉዳቱን እንዲታከም የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሞያ እና ሀኪም አፈላልገው በማሳከም ለሶስት ቀናት ካሳከሙት በኋላ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ መጣበት ጫካ በሰላም ሸኝተውታል።

ፖሊስ ከጫካ የወጣውን ጅብ ላይ ጉዳት ያደረሰውን ግለሰብ ተከታትሎ በመያዝ የህክምናውን ወጭ እንዲሸፍን ያደረጉ ሲሆን የሶስት ቀን የምግብ ወጭውንም ፖሊሶች ስጋ በመግዛት አገግሞ ወደ ጫካው እንዲመለስ ማድረጋቸውን  ኢንስፔክተር ሬድዋን ኢብራሄም ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ሲል ኤደን ሽመልስ ዘግባለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣33👏6❤4😁4😭2
📌ኢትዮጵያዊው ኢንጂነር በቡርኪና ፋሶ
የሳተላይት ማምረቻ ፋብሪካ ሊገነቡ ነው

ታዋቂው ኢትዮጵያዊ የቴክኖሎጂ ባለሙያና ሥራ ፈጣሪ ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር፣ አፍሪካ የራሷን ሳተላይቶች የምታመርትበትን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ማዕከል በቡርኪና ፋሶ ለማቋቋም ከስምምነት መድረሳቸውን በይፋ አስታወቁ። ኢንጂነሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደገለጹት፣ ይህንን ታሪካዊ ፕሮጀክት ዕውን ለማድረግ ከቡርኪና ፋሶ መንግሥት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመው ወደ ግንባታ ምዕራፍ ተሸጋግረዋል።

ይህ የሳተላይት ማምረቻ መርሃ-ግብር በቡርኪና ፋሶ በሚገኝ የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚተገበር ሲሆን፣ የአህጉሪቱ ትልቁ የቴክኖሎጂ ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ይጠበቃል። ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር "እንደ አንድ ፓን-አፍሪካኒስት፣ የፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬንና የቡርኪና ፋሶን ታላቅ ራዕይ በመደገፍ አህጉራዊ አሻራችንን ለማሳረፍ እየሠራን ነው" በማለት የፕሮጀክቱን ፋይዳ አስገንዝበዋል።

ይህ ፈር ቀዳጅ ተነሳሽነት አፍሪካ በጠፈር ሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ፣ የራሷን የመረጃና የኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት እንድትገነባ ትልቅ በር ይከፍታል። በቅርቡ ሥራ ይጀምራል የተባለው ይህ ማዕከል፣ ኢትዮጵያውያን በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መድረክ ያላቸውን የላቀ ብቃትና ለአህጉራዊ አንድነት ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም ያስመሰከረ ሆኗል።

©️አዲስ አድማስ ጋዜጣ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤11🔥7👏2😐1
📌የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከሦስት ወራት በፊት ቀድሞ 3,000 ብር የነበረውን የአዳራሽ ኪራይ ወደ 11,500 ብር ማሳደጉ ቅሬታ አስነሳ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በአዳራሽ ኪራይ ላይ ያደረገው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ፣ ቴአትር አዘጋጅ ኢንተርፕራይዞችንና ባለሙያዎችን ከዘርፉ እያራቃቸው መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ።

ፕሮዲውሰሮች ለደራሲ፣ ለአዘጋጅና ለተዋንያን ከሚከፍሉት ክፍያ በተጨማሪ የቲኬት ቀረጥና የመንግሥት ግብር የሚጠብቃቸው በመሆኑ፣ አዲሱ የኪራይ ዋጋ ፕሮዲውሰሮችን ከገበያ የሚያስወጣ ነው ተብሏል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢንተርፕራይዝ ባለቤቶችም የኪራይ ዋጋው በድንገት ከሦስት እጥፍ በላይ መጨመሩ በስራቸው ላይ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት የቴአትር ሥራ አዋጭ ባለመሆኑ ሁለት መቶ ያህል ኢንተርፕራይዞች ሙያውን ትተው ወጥተዋል፡፡ አሁን የቀሩት ከሁለትና ከሦስት የማይበልጡ ኢንተርፕራይዞችም በአዳራሽ ኪራይ ዋጋ መጨመርና በሌሎች ገፊ ምክንያቶች ከሥራው ለመውጣት በመገደድ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ የቴአትር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሌብ ዋለልኝ እንደተናገሩት፣ የቴአትር አዳራሽ ኪራይ ዋጋን በተመለከተ ጥናት ላይ ተመሥርቶ ጭማሪ እንዲደረግ የተወሰነው ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር ብለዋል፡፡ሆኖም በቅርቡ ፀድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ መደረጉ ከጊዜው ጋር ሊጣጣምና መልስ ሊሆን የማይችል ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በዋጋ ጭማሪውም ከኢንተርፕራይዞችና ከቴአትር ፕሮዲዩሰሮች ለቴአትር ቤቱ ቅሬታ እየቀረበ መሆኑን፣ ችግሩ በጥናት ተለይቶ ማስተካከያ ማድረግ የሚያስፈልግ ከሆነ ቴአትር ቤቱ ማስተካከያ ከማድረግ ወደኋላ እንደማይል አቶ ካሌብ አስታውቀዋል፡፡

©️ሪፖርተር ጋዜጣ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤11👎2😢1
📌የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን 20ኛ ዓመት መታሰቢያ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደስላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ታላቁን ደራሲ፣ ገጣሚና የቴአትር ሰው ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የሚዘክር መርሐግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

ይህ መርሐግብር የተዘጋጀው ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ 20ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

በዚህ መርሃ-ግብር ላይ የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን የማይረሱ ግጥሞች ላይ የሥነጽሑፍ ባለሞያ ትንታኔ ያቀርባል።

ለኢትዮጵያ ቴአትር ጥበብ መሰረት የጣሉ ተውኔቶቹም ዳሰሳ ይደረግባቸዋል። በተጨማሪም የደራሲውን ህይወትና ስራዎች የሚመረምረውና በፋሲል ይትባረክ የተጻፈው "ምጥቀት በቅኔ አክናፍ" የተሰኘው መጽሐፍ ላይም ዳሰሳ ለታዳሚው ይቀርባል።

ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን ለ70 ዓመታት ያህል በምድር ላይ በቆየባቸው ጊዜያት በኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ አሻራውን አሳርፏል።

ሎሬቱ በየካቲት ወር 1998 ዓ.ም በሀገረ አሜሪካ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5👍2
📌"የካቲት ወርሃ ገብረክርስቶስ" ዛሬ ይካሄዳል

ሠዓሊና ባለቅኔ ገብረክርስቶስ ደስታን የሚዘክርና በስሙ የተሰየመው ዓመታዊው "የወርሃ ገብረክርስቶስ" መሰናዶ ዘንድሮም እንደሚከበር ተገልጿል።

ለሦስተኛ ጊዜ የሚከበረው ይህ የጥበብ ቀን፣ የካቲት 14 ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ከ8:00 ጀምሮ ስድስት ኪሎ የጀርመን የባህል ማዕከል (ጎተ ኢንስቲትዩት) አጠገብ በሚገኘው የገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ የጥበብ ሙዚየም ውስጥ ይካሄዳል።

የባለቅኔው ገብረክርስቶስ ደስታ ግጥሞች የሚነበቡበትና የጥበብ አፍቃሪያን ስራዎቹን የሚያደምጡበት መድረክ ነው።

የሠዓሊው ዝነኛና ረቂቅ የሆኑ የዘመናዊ ስዕል ስራዎች ለዕይታ የሚቀርቡ ሲሆን፣ ስለ ስራዎቹ ጥልቅ ትንተና ከባለሙያዎች የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።

በዕለቱ ለሚታደሙ የጥበብ አፍቃሪያን፣ ይበልጥ የሚወዱትን የገብረክርስቶስ ግጥም በኮፒ መውሰድ የሚችሉበት ዕድል እንደተመቻቸ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዘጋጆቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ ልዩ መርሐግብር በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም የሚታሰብ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከማርች 28 እስከ ኤፕሪል 1  2026 ድረስ በአሜሪካ ኦክላሆማ እና ሌሎች ከተሞች በድምቀት እንደሚከበር ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4👍2
📌የሲሳይ ንጉሱ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

ኢትዮጵያ ዘመናዊ የስነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ በረቂቅ አጻጻፍ ስልቱና በማራኪ ትረካው የሚታወቀው አንጋፋው ደራሲ ሲሳይ ንጉሱ፣ ከረዥም ዓመታት ቆይታ በኋላ "ሳልሳዊ ልደት" የተሰኘ አዲስ የመጽሐፍ ስራውን ለንባብ ሊያበቃ መሆኑን ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ደራሲው በተለይም በታዋቂው "ሰመመን" ልብ-ወለድ መጽሐፉ  በብዙዎች ዘንድ የሚታወስ ሲሆን፣ በተጨማሪም "የቅናት ዛር"፣ "ረቂቅ አሻራ" እና ሌሎች ተወዳጅ መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል።

ደራሲው ለበርካታ ዓመታት ከአዲስ መጽሐፍ ህትመት ርቆ በቆየባቸው ጊዜያት ስራዎቹን በናፍቆት ለሚጠባበቁ አንባቢዎቹ፣ ይህ "ሳልሳዊ ልደት" የተሰኘው መጽሐፍ ትልቅ የምስራች ሆኗል።

ይህ አዲስ ስራው በቅርቡ ታትሞ ለገበያ እንደሚቀርብ የተጠቆመ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያሳረፈው የደራሲው ዳግም መመለስ በዘርፉ ባለሙያዎችና በአንባቢዎች ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤14👍3🤔1🙏1
📌የመዝናኛው ዓለም እየተነጋገረበት ያለ ጉዳይ

በታዋቂዎቹ "ግሬይ አናቶሚ" እና "ዩፎሪያ" ተከታታይ ድራማዎች ላይ በከፍተኛ ብቃቱ የሚታወቀውና በሚሊዮኖች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ተዋናይ ኤሪክ ዴን በ53 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ኤሪክ ዴን ከዚህ ዓለም ከመለየቱ በፊት ከታዋቂው የፊልም አከፋፋይ "ኔትፍሊክስ" ጋር ባደረገው ልዩ ስምምነት መሠረት፣ እርሱ እስኪያርፍ ድረስ ተደብቆ የቆየው የመጨረሻ ቃለ-መጠይቁ ትናንት ምሽት አየር ላይ ውሏል።

ባለፈው ኅዳር ወር ላይ የተቀረጸውና ለሁለቱ ሴት ልጆቹ መታሰቢያ እንዲሆን ያዘጋጀው ይህ ቃለ-መጠይቅ፣ አባታዊ ምክሮችንና አራት ዋና ዋና የሕይወት መልእክቶችን የያዘ ነው።

ኤሪክ ዴን እንዲህ አለ:-

"ዛሬን ብቻ ኑሩ" ኤሪክ ባለፈው ጊዜ ላይ መቆዘም ትርፉ ፀፀት መሆኑንና የወደፊቱም የማይታወቅ በመሆኑ፣ ልጆቹ በያዙት ቅጽበትና በዛሬው ቀን ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው እንዲኖሩ መክሯል።

"ፍቅር ይያዛችሁ" ፍቅር የግድ ከሰው ጋር ብቻ መሆን እንደሌለበት የገለጸው ተዋናዩ፣ እርሱን በትወና ሕይወቱ ውስጥ ያጋጠሙትን አስቸጋሪ ፈተናዎች እንዲያልፍ የረዳው ለሙያው ያለው ጥልቅ ፍቅር መሆኑን ጠቅሷል። "እናንተም የምታፈቅሩትን ነገር ፈልጉ" ሲልም አክሏል።

"ጓደኞቻችሁን በጥንቃቄ ምረጡ" እውነተኛ ጓደኞችን ከመረጡ በኋላ ራስን አሳልፎ መስጠት እንደሚገባና እውነተኛ ጓደኞችም በተመሳሳይ መልኩ ራሳቸውን አሳልፈው እንደሚሰጡ በቃለ-መጠይቁ አስገንዝቧል።

"እጅ አትስጡ" እስከ መጨረሻዋ ቅጽበት ድረስ መታገል እንደሚገባ የገለጸው ኤሪክ፣ የጤናም ይሁን ሌላ ማንኛውም የሕይወት ችግር ሲገጥም ለመሰበር መጣደፍ እንደሌለባቸውና በጽናት መታገል እንደሚገባ በስሜት ተውጦ ተናግሯል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤37👍9👏1
📌የአዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ፍቃድ ተሰረዘ

የአዲስ ስታንዳርድ (Addis Standard) የበየነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን የሥራ ፈቃድ መታገዱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ይፋ አድርጓል።

ኖር ሬድዮ እንደተመለከተው ከሆነ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ከአዲስ ስታንዳርድ የበየነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን ጋር የነበረው የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከዛሬ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መሰረዙን አስታውቋል።

ባለሥልጣኑ ለውሳኔው እንደ ምክንያት ያቀረባቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

ሚዲያው የሚዲያ ሥነ-ምግባርንና የኢትዮጵያ ሕጎችን ..ተጨማሪውን ያንብቡ:-
https://t.me/NorRadio1/141

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👎4👏3❤1
📌"ማስጠንቀቂያ ደርሶኝ አያውቅም "

አዲስ ስታንዳርድ ምላሽ ሰጠ 

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ማምሻውን ፍቃዱ መሰረዙን የገለጸው የአዲስ ስታንዳርድ የበየነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን  ዋና አዘጋጅ ዮናስ ከድር ባለስልጣኑ ያቀረበውን ክስ ውድቅ አድርገዋል።

ዋና አዘጋጁ እንደገለጹት፤ ተቋሙ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት መደበኛ የሕግ ጥሰት እንደፈፀመ የሚያመለከት ማስጠንቀቂያ ደርሶት እንደማያውቅ ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

“አዲስ ስታንዳርድ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች ደርሰውታል የሚለው ክስ ከእውነት የራቀ ነው። የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን ቀደም ሲል ስለነበሩ የሕግ ጥሰቶችም ሆነ ስለተወሰዱ እርምጃዎች ለአዲስ ስታንዳርድ የዜና ክፍል በይፋ ያሳወቀው ነገር የለም” ብለዋል።

አክለውም የጋዜጣው አሳታሚ የሆነው ጃኬን ፐብሊሺንግ (JAKENN Publishing PLC) መብቱን ለማስከበርና የሕግ የበላይነት መከበሩን ለማረጋገጥ ያሉትን የሕግ አማራጮች እየገመገመ እንደሚገኝ áŒˆáˆáŒ¸á‹‹áˆá˘

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አዲስ ስታንዳርድ የበየነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን  “በሚዲያ ዘርፉ ላይ የሙያ ስነምግባር እና የሀገርና የህዝብ ብሔራዊ ጥቅም አክብሮ እንዲሰራ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ለመታረም ፈቃደኛ አልሆነም” ሲል “በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ መሰረት” ከዛሬ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ  ፍቃዱ መሰረዙን ገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤6👍2
የባህል ጣዕም በቶቶት
የፆም ብፌ ድግስ ይጠብቃችኋል!

​በኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች ዝግጅትና መስተንግዶ ስሙ ገኖ የሚጠራው ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ፣ ለፆሙ ወቅት ልዩ ትኩረት የሰጠ የብፌ ድግስ ይዞላችሁ ቀርቧል። ለቤተሰብ፣ ለጓደኛሞች ወይም ለማንኛውም ድርጅታዊ ዝግጅት ምቹና ባህላዊ ድባብ ያለው ስፍራ ለሚፈልጉ ቶቶት ተመራጭ ነው።

​ለምን ቶቶትን ይመርጣሉ?

​ልዩ የፆም ብፌ፦
በልዩ ጣዕም የተዘጋጁ የፆም ምግቦች እንደ ልብዎ እንዲመገቡ ተከሽነው ቀርበዋል።

​ሁልጊዜም ዝግጁ፦
ከሰኞ እስከ እሁድ የባህል ድግሱ አይቋረጥም (የፍስክ አማራጮችም እንደተጠበቁ ናቸው)።

​ባህላዊ ድባብ፦
የምግቡ ጣዕም ብቻ ሳይሆን የቦታው ድባብ የኢትዮጵያን እንግዳ ተቀባይነት በሚያንፀባርቅ መልኩ የተዋበ ነው።

ለበለጠ መረጃ፣
ቦታ ለመያዝ ወይም ለትዕዛዝ በሚከተሉት ስልኮች ይደውሉ፦

​📞 0116 46 07 18
​📞 0909 00 44 00

​ቶቶት — የኢትዮጵያ ባህልና ጣዕም መገናኛ!
❤10👍5
ዳናሽ ፊልም በናሆም መልቲሚዲያ !

በሲኒማ ቆይታው ብዙ ፍቅርና አድናቆት ያተረፈው "ዳናሽ" ፊልም አሁን ከአዲስ ጉልበት ጋር ወደ እናንተ ሊመለስ ነው።

ታዋቂው ተዋናይ ሄኖክ በሪሁን እና ኤደን አይሸሹም የተሳተፉበት፣ በአብርሃም ታደሰ ተፅፎና ተዘጋጅቶ የቀረበው ድንቅ የፍቅር ፊልም—ዳናሽ!

🗓 መቼ?፦ አርብ የካቲት 20

📍 የት?፦ በናሆም መልቲሚዲያ (Nahom Multimedia) ዩቲዩብ ቻናል

ስሜት፣ ፍቅር እና አስደናቂ ትረካ የተዋሃደበትን ይህን ፊልም ለማየት ዝግጁ ናችሁ? ቀኑን አትርሱ!

ፊልሙ የሚለቀቅበት ቻናል ሊንክ ይኸው

https://youtube.com/@nahommultimedia?si=YqGl8THSPt1GIv7D
❤8👍2👎2
📌 ዳናሽ ፊልም በናሆም መልቲሚዲያ ተለቀቀ

ታዋቂው ተዋናይ ሄኖክ በሪሁን እና ኤደን አይሸሹም የተሳተፉበት፣ በአብርሃም ታደሰ ተፅፎና ተዘጋጅቶ የቀረበው ዳናሽ በናሆም መልቲሚዲያ የዩቲዩብ ቻናል በኩል ተለቋል።

ፊልሙን ይመልከቱ ሊንክ ይኸው:-

https://youtu.be/Tyl5PGNU4Sc?si=PMhQENnEu--BrQSG
👍2
📌ዓድዋ የሥዕል አውደርዕይ

130ኛውን የዓድዋ ድል በዓልን በኪነ-ጥበብ ሥራዎች ለማዘከር የታለሙ ሁለት የሥዕል አውደርዕዮች በጣይቱ የባህል እና ትምህርት ማዕከል እንዲሁም በፈንድቃ የባህል ማዕከል በድምቀት ተከፈቱ።

በጣይቱ የባህል እና ትምህርት ማዕከል ከሕብር ሰዓልያን ቡድን ጋር በመተባበር የተሰናዳውና "የድል አርማ" የተሰኘው 8ኛው ዝክረ ዓድዋ የሥዕል አውደርዕይ፤ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለተመልካች ክፍት ሆኗል። በዚህ አውደርዕይ ላይ የሕብር ሰዓልያን ቡድን አባላትና ተጋባዥ ታዋቂ ሰዓልያን ስለ ዓድዋ ድል፣ ስለ ኢትዮጵያዊነትና ስለ ጀግንነት የሳሏቸው ድንቅ ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን፣ አውደርዕዩ ለአንድ ወር ያህል ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል።

በተመሳሳይ ዜና፣ ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል በሚገኘው የፈንድቃ የባህል ማዕከል "ዓድዋ" የተሰኘ ሌላ የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ተከፍቷል። ሰባት ታዋቂና ወጣት ሠዓሊያን የተሳተፉበት ይህ አውደርዕይ፤ የድሉን ታላቅነት በሠዓሊያኑ የፈጠራ ክህሎትና ታሪካዊ እይታ በማጣመር የቀረበ ድግስ ነው። ይህ አውደርዕይ እስከ የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ለተከታታይ ሳምንታት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል።

የሁለቱም አውደርዕዮች አዘጋጆች እንደገለጹት፤ የዝግጅቶቹ ዋነኛ ዓላማ የዓድዋን ድል በሥነ-ጥበብ ሥራዎች በማዘከር፣ የድሉን ፋይዳና ሀገራዊ ክብር ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሆነ ገልጸዋል።

For more: https://t.me/EventAddis1

For more: https://t.me/EventAddis1‌‌
❤3👍2
📌የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን አቋረጠ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ወደ አንዳንድ ከተሞች የሚደረጉ በረራዎችን በጊዜያዊነት የሚያቋርጥ መሆኑን አስታውቋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በተቀሰቀሰው አለመረጋጋት እና የፀጥታ ስጋት ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንዳንድ ከተሞች የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለጊዜው የሚያቋርጥ መሆኑን አየር መንገዱ አረጋግጧል።

የአየር መንገዱ ከፍተኛ ሃላፊ " በክልሉ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እና ከሚመለከታቸው አውሮፕላን ማረፊያዎች ካሉ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣናት ጋር የሚመካከር መሆኑን " ገልጸዋል።

በምክክሩም መሰረት " በመሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ ከተሞች የሚያደርገውን በረራ ለጊዜው ያቋርጣል " ብለዋል።

በተጨማሪም " በአሁኑ ሰዓት፣ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ውስጥ (በአውሮፕላን ማረፊያ) የቆመ ምንም ዓይነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የለም " ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4👍1