📌ኢትዮጵያዊቷ ሴት በፎርብስ የፊት ገጽ ላይ
ታዋቂዋ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ-ጥር የሆነችው ኢትዮጵያዊት ስራ ፈጣሪ ቤተልሔም ጥላሁን ዓለሙ፤ በማርች 2026 የፎርብስ አፍሪካ መጽሔት እትም ላይ በክብር ሰፍራለች።
"Build Something People Will Love" በሚል መሪ ቃል የቀረበው ይህ ዘገባ፤ ቤተልሔም በሁለት ዘርፎች እያመጣች ያለውን ለውጥ በዝርዝር ዳስሷል።
ቤተልሔም ጥላሁን ከጫማ እስከ ጤፍ፣ ከጤፍ እስከ ኤሌክትሪክ መኪና የኢትዮጵያ የስራ ፈጠራ ተምሳሌትነቷን በተግባር እያሳየች የምትገኝ ኢትዮጵያዊ ስራ ፈጣሪ ነች።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

❤37👏5🥰2🙏1
📌ኖር ሬድዮ በዩቲዩብ አማራጭ ወደ ስራ ገባ
የEvent Addis media (እህት ካምፓኒ በሉት) አሪፍ የሚዲያ አማራጭ የሆነው "ኖር ሬድዮ" በዩቲዩብ አማራጭ ወደ ስራ ገብቷል።
ቀሪውን መልዕክት ከታች አንብቡት!
በመዝናኛ እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርገው "ኖር ሬድዮ" ዲጂታል ሚዲያ በዩቲዩብ ወደ ስራ ገብቷል።
ኖር ሬድዮ ዛሬ የካቲት 8 2018 ዓ.ም ስራውን የጀመረው "ወሬ ገበያ "በተሰኘው የወሬ ሰዓቱ ነው።
"ወሬ ገበያ" በኖር ሬድዮ በመጀመሪያ ቪዲዮው ተከታዮቹን ወሬዎች ለአድማጮች ያቀርባል።
1. ኢትዮጵያዊቷ ታደጊ በቲክቶክ አስተያየቶች ምክንያት ራሷን አጠፋች
2. "ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን እስክታሸንፍ ድረስ ፀጉሬን አልቆርጥም" ያለው ፈረንጅ መነጋገሪያ ሆኗል
3.በተከታታይ እየጨመረ የሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም የታሪፋ ዋጋ ከአቅማችን በላይ ነው ያሉ ተጠቃሚዎች ቅሬታ አቀረቡ
4. ኤምሬትስ ከቤት ሠራተኞ ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን ከረቸመች
መረጃዎቹን በዩቲዩብ ገጻችን ይከታተላሉ:-
https://youtu.be/tXjrE5tBylg?si=of8etFG4Zw9xxWAf
በተጨማሪም የፌስቡክ ገጻችንን ይወዳጁ!
https://www.facebook.com/profile.php?id=61558246481526
የቴሌግራም ቻናላችንን ብትቀላቀሉም ደስተኛ ነን
https://t.me/NorRadio1
እናመሰግናለን !

❤12🔥3
📌የአማን ፍሰሃፅዮን ስንብትና የቀብር ሥነሥርዓት
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መስራችና ስራ አስኪያጅ አማን ፍስሃፅዮን ባሳለፍነው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ይታወሳል።
የአስከሬን አቀባበል የክብር ስንብት እና የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው የስንብት ስነ-ስርዓቱን እንደሚከተለው አዘጋጅቷል።
የስንብት መርሃግብሩ የሚካሄደው የፊታችን ሐሙስ የካቲት 12 2018 ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም ነው።
ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጉዞ ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ አድዋ ሙዚየም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ለስንብት መርሃግብር ስርዓት አስከሬኑ አደዋ ሙዚየም ይደርሳል።
ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አስከሬኑ ወደ መጨረሻ ማሪፊያው ጉዞ ይጀምራል። ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር የግብዓተ መሬት ስነ-ስርዓት ይፈጸማል።

😢13❤2
📌መልቲቾይስ ኢትዮጵያ ለመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና ዕድል አስጀመረ
መልቲቾይስ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ከፍተኛ አቅም ያላቸውን ተማሪዎች በዲጂታል እውቀትና በኮዲንግ ክህሎት ለማብቃት የሚያስችለውን “የኢትዮጵያ የወደፊት ባለ ክህሎቶች" የተሰኘ የሥልጠና ዕድል በይፋ አስጀመረ።
ይህ ሥልጠና የኩባንያው የማኅበራዊ ኃላፊነት (CSI) ስትራቴጂ አካል ሲሆን፣ መልቲቾይስ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ተኮር አጋርነቱን ለማጠናከርና በሀገር ተስፋዎች ላይ የአቅም ግንባታ ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
የመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገሊላ ገብረሚካኤል እንደገለጹት፣ የመልቲቾይስ አፍሪካ “ሕይወትን ማበልጸግ” መርህ ተጨባጭ ተፅዕኖ በመፍጠር ላይ የተመሰረተ ነው። "ይህ የቴክኖሎጂ ሥልጠና ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዲጂታል ክህሎቶችን በሚገባ እንዲጨብጡና በቀጣዩ የዲጂታል ዓለም በልበ ሙሉነት እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚያነሳሳ ትልቅ እርምጃ ነው" ሲሉም አክለዋል።
ለ12 ሳምንታት በሚቆየው በዚህ የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና፣ ካመለከቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች መካከል 30 ተማሪዎች ተመርጠው ሥልጠናውን የጀመሩ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 50 በመቶው ልጃገረዶች መሆናቸው ልዩ ያደርገዋል።
ሥልጠናው ጥራቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሰጥ መልቲቾይስ ኢትዮጵያ ከየኔታ ኮድ አካዳሚ ጋር በመተባበር እያከናወነው ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተጀመረው ይህ ፕሮግራም፣ ወደፊት ወደ ክልል ከተሞችም የመስፋፋት ዕቅድ እንዳለው ታውቋል።

❤6👏1
📌ቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ የመዘጋት ስጋት ላይ ነው
የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ፣ ከመንግስት የሚሰጠው በጀት ካልቀጠለ በስተቀር በሚቀጥሉት ሰባት ሳምንታት ውስጥ ስራውን ሊያቆም እንደሚችል ተነገረ።
የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር ቲም ዴቪ እንዳስታወቁት፣ የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ዓመታዊ በጀት 400 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን፣ አብዛኛው የሚሸፈነው ከአገር ውስጥ የፍቃድ ክፍያ ነው። የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለፈው ዓመት 137 ሚሊዮን ፓውንድ አስተዋጽዖ ያደረገ ቢሆንም፣ ይህ የገንዘብ ድጋፍ በመጋቢት ወር መጨረሻ (እ.ኤ.አ. March 2026) ያበቃል።
እስካሁን ድረስ ከዚያ በኋላ የሚሆን ምንም ዓይነት የገንዘብ ዋስትና ወይም ዕቅድ የለም።
የቀድሞው የተመድ ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን "ብሪታንያ ለዓለም የሰጠችው ትልቁ ስጦታ" ሲሉ የገለጹት ይህ ተቋም፣ በ43 ቋንቋዎች የተለያዩ ይዘቶችን ያሰራጫል። (የአማርኛ አገልግሎትን ጨምሮ ማለት ነው) በሳምንት 313 ሚሊዮን ሰዎችን ይደርሳል።
በኢራን፣ አፍጋኒስታን፣ ዩክሬን፣ ጋዛ እና ሱዳን ባሉ የጦርነት ቀጣናዎች ለሚገኙ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ብቸኛው የመረጃ ምንጭ እና የሕይወት አድን መስመር ነው።
የቢቢሲ መዳከም በዓለም አቀፍ የመረጃ ፍሰት ላይ ትልቅ ክፍተት ይፈጥራል ተብሎ ተሰግቷል።
የቢቢሲ መሪዎች እንደሚከራከሩት፣ ወርልድ ሰርቪስ የእንግሊዝን ባሕል እና ተጽዕኖ ለዓለም ከማስተዋወቅ ባለፈ የሀገሪቱ የብሔራዊ ደሕንነት አካል ነው። ሐሰተኛ መረጃዎች እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በበዛበት በዚህ ዘመን፣ ዕውነተኛ ጋዜጠኝነትን የሚተካ ምንም ነገር እንደሌለ ትንታኔው ያመለክታል።

❤5👍2👏1
📌አስፈሪው አውሬ በምዕራብ ሸዋ ስጋት ፈጠረ
የኤርዶጋን ጋረዶች፣ ባለሂጃቧ ተርጓሚ !
⚓️የዛሬው የኖር ሬድዮ ወሬ ገበያ የደራ ነው !
እነዚህ ጉዳዮችን ይዟል እነሆ:-
1. አስፈሪው አውሬ በምዕራብ ሸዋ ስጋት ተፈጠር
ደም መጥጦ ከመጣል ውጪ የሰው ስጋ እንደማበላ የተነገረለት አስፈሪ አውሬ የምዕራብ ሸዋ ነዋሪዎችን አስጨንቋል። በህብረተሰቡ ላይም ተደጋጋሚ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ ኖር ሬድዮ ሰምቷል።
2.የኤርዶጋን ጋረዶች፣ ባለሂጃቧ ተርጓሚ !
የፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን
ለየት ያለ አቀባበል፣አረንጓዴ ልብስ ያጠለቁ የደህንነት ጥበቃዎች እና ሃጃብ የለበሰችው አስተርጓሚ ፣እጅግ ለይት ያለው የመኪና ስጦታ፣የፕሬስዳንቱ ያልተጠበቀ ንግግር ልዩ ዘገባ በኖር ሬድዮ ወሬ ገበያ ይዘናል።
ወሬዎቹን ይሄው በዚህ በኩል ያድምጡ
Link:-https://youtu.be/dFfvxZhdAME?si=PvdrFo1FyCo3sJVU
በተጨማሪም የፌስቡክ ገጻችንን ይወዳጁ!
https://www.facebook.com/profile.php?id=61558246481526
የቴሌግራም ቻናላችንን ብትቀላቀሉም ደስተኛ ነን
https://t.me/NorRadio1
እናመሰግናለን !
የኤርዶጋን ጋረዶች፣ ባለሂጃቧ ተርጓሚ !
⚓️የዛሬው የኖር ሬድዮ ወሬ ገበያ የደራ ነው !
እነዚህ ጉዳዮችን ይዟል እነሆ:-
1. አስፈሪው አውሬ በምዕራብ ሸዋ ስጋት ተፈጠር
ደም መጥጦ ከመጣል ውጪ የሰው ስጋ እንደማበላ የተነገረለት አስፈሪ አውሬ የምዕራብ ሸዋ ነዋሪዎችን አስጨንቋል። በህብረተሰቡ ላይም ተደጋጋሚ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ ኖር ሬድዮ ሰምቷል።
2.የኤርዶጋን ጋረዶች፣ ባለሂጃቧ ተርጓሚ !
የፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን
ለየት ያለ አቀባበል፣አረንጓዴ ልብስ ያጠለቁ የደህንነት ጥበቃዎች እና ሃጃብ የለበሰችው አስተርጓሚ ፣እጅግ ለይት ያለው የመኪና ስጦታ፣የፕሬስዳንቱ ያልተጠበቀ ንግግር ልዩ ዘገባ በኖር ሬድዮ ወሬ ገበያ ይዘናል።
ወሬዎቹን ይሄው በዚህ በኩል ያድምጡ
Link:-https://youtu.be/dFfvxZhdAME?si=PvdrFo1FyCo3sJVU
በተጨማሪም የፌስቡክ ገጻችንን ይወዳጁ!
https://www.facebook.com/profile.php?id=61558246481526
የቴሌግራም ቻናላችንን ብትቀላቀሉም ደስተኛ ነን
https://t.me/NorRadio1
እናመሰግናለን !
❤8
📌89ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር 89ኛውን የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል በስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት ፊት ለፊት አክብሯል። በበዓሉ ላይ አባትና እናት አርበኞች በመገኘት የአበባ ጉንጉን በማኖር የሰማዕታቱን መስዋዕትነት ዘክረዋል።
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ ወጣቱ ትውልድ አያትና ቅድመ አያቶቹ ለሀገር ፍቅርና ለአንድነት የከፈሉትን የሕይወት መስዋዕትነት በማሰብ፣ ሀገሩን ከጠላት ጥቃት እንዲጠብቅና ልማቷን እንዲያስቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በየጊዜው በውስጥ ባንዳዎችና በውጭ ጠላቶች ሰላሟን ለማደፍረስና ሕዝቧን አንገት ለማስደፋት የሚደረጉ ሙከራዎችን በልጆቿ ጀግንነት ስታከሽፍ የኖረች፣ በደሟ ታፍራና ተከብራ የቆየች ሀገር መሆኗንም ፕሬዝዳንቱ አክለው ገልጸዋል።

❤23
📌በጅብ ላይ ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ የህክምና ወጪውን እንዲሸፍን ተፈረደበት 😂
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሂርና ከተማ አስተዳደር ሀዬታ ቀበሌ ውስጥ ከጫካ የወጣ ጅብ በሰው ተመቶ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን የፖሊስ ፅ/ቤት አስታውቋል።ጉዳት የደረሰበት ጅብ የህክምና እርዳታ አግኝቶ ወደጫካው መመለሱ ተገልጿል።
የሂርና ከተማ መደሀዮታ ቀበሌ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ፅ/ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር ሬድዋን ኢብራሂም ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ጅቡ ከጫካ የወጣው ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ ሲሆን አንድ ግለሰብ ቤት አካባቢ ሲጮህ የቤቱ ባለቤት ጅቡን ለማባረር በወረወረው ድንጋይ ጅቡ በሁለት እግሮቹ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል ።
ጅቡ ጉዳት ሲደርስበት በአካባቢው ፖሊስ እና ባህላዊ ፍርድቤት ግቢ ገብቶ ጥቅልል ብሎ በመተኛት የደረሰበትን ጉዳት በጩኸት ሲገልጽ እንደነበረ ተጠቁሟል ።የጅቡን ጩኸት የተመለከቱ የፖሊስ አባላትም ግቢያቸው የገባውን የጫካ ጅብ ከማባረር እና ከመጉዳት ይልቅ ምግብ እና ውሃ በመስጠት አሳድረውታል።
በነጋታውም ለጅቡ የሚያስፈልገውን በመስጠት ጉዳቱን እንዲታከም የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሞያ እና ሀኪም አፈላልገው በማሳከም ለሶስት ቀናት ካሳከሙት በኋላ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ መጣበት ጫካ በሰላም ሸኝተውታል።
ፖሊስ ከጫካ የወጣውን ጅብ ላይ ጉዳት ያደረሰውን ግለሰብ ተከታትሎ በመያዝ የህክምናውን ወጭ እንዲሸፍን ያደረጉ ሲሆን የሶስት ቀን የምግብ ወጭውንም ፖሊሶች ስጋ በመግዛት አገግሞ ወደ ጫካው እንዲመለስ ማድረጋቸውን ኢንስፔክተር ሬድዋን ኢብራሄም ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ሲል ኤደን ሽመልስ ዘግባለች።

🤣33👏6❤4😁4😭2
📌ኢትዮጵያዊው ኢንጂነር በቡርኪና ፋሶ
የሳተላይት ማምረቻ ፋብሪካ ሊገነቡ ነው
ታዋቂው ኢትዮጵያዊ የቴክኖሎጂ ባለሙያና ሥራ ፈጣሪ ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር፣ አፍሪካ የራሷን ሳተላይቶች የምታመርትበትን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ማዕከል በቡርኪና ፋሶ ለማቋቋም ከስምምነት መድረሳቸውን በይፋ አስታወቁ። ኢንጂነሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደገለጹት፣ ይህንን ታሪካዊ ፕሮጀክት ዕውን ለማድረግ ከቡርኪና ፋሶ መንግሥት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመው ወደ ግንባታ ምዕራፍ ተሸጋግረዋል።
ይህ የሳተላይት ማምረቻ መርሃ-ግብር በቡርኪና ፋሶ በሚገኝ የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚተገበር ሲሆን፣ የአህጉሪቱ ትልቁ የቴክኖሎጂ ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ይጠበቃል። ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር "እንደ አንድ ፓን-አፍሪካኒስት፣ የፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬንና የቡርኪና ፋሶን ታላቅ ራዕይ በመደገፍ አህጉራዊ አሻራችንን ለማሳረፍ እየሠራን ነው" በማለት የፕሮጀክቱን ፋይዳ አስገንዝበዋል።
ይህ ፈር ቀዳጅ ተነሳሽነት አፍሪካ በጠፈር ሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ፣ የራሷን የመረጃና የኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት እንድትገነባ ትልቅ በር ይከፍታል። በቅርቡ ሥራ ይጀምራል የተባለው ይህ ማዕከል፣ ኢትዮጵያውያን በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መድረክ ያላቸውን የላቀ ብቃትና ለአህጉራዊ አንድነት ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም ያስመሰከረ ሆኗል።
©️አዲስ አድማስ ጋዜጣ

❤11🔥7👏2😐1
📌የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከሦስት ወራት በፊት ቀድሞ 3,000 ብር የነበረውን የአዳራሽ ኪራይ ወደ 11,500 ብር ማሳደጉ ቅሬታ አስነሳ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በአዳራሽ ኪራይ ላይ ያደረገው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ፣ ቴአትር አዘጋጅ ኢንተርፕራይዞችንና ባለሙያዎችን ከዘርፉ እያራቃቸው መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ።
ፕሮዲውሰሮች ለደራሲ፣ ለአዘጋጅና ለተዋንያን ከሚከፍሉት ክፍያ በተጨማሪ የቲኬት ቀረጥና የመንግሥት ግብር የሚጠብቃቸው በመሆኑ፣ አዲሱ የኪራይ ዋጋ ፕሮዲውሰሮችን ከገበያ የሚያስወጣ ነው ተብሏል።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢንተርፕራይዝ ባለቤቶችም የኪራይ ዋጋው በድንገት ከሦስት እጥፍ በላይ መጨመሩ በስራቸው ላይ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
ባለፉት ዓመታት የቴአትር ሥራ አዋጭ ባለመሆኑ ሁለት መቶ ያህል ኢንተርፕራይዞች ሙያውን ትተው ወጥተዋል፡፡ አሁን የቀሩት ከሁለትና ከሦስት የማይበልጡ ኢንተርፕራይዞችም በአዳራሽ ኪራይ ዋጋ መጨመርና በሌሎች ገፊ ምክንያቶች ከሥራው ለመውጣት በመገደድ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ የቴአትር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሌብ ዋለልኝ እንደተናገሩት፣ የቴአትር አዳራሽ ኪራይ ዋጋን በተመለከተ ጥናት ላይ ተመሥርቶ ጭማሪ እንዲደረግ የተወሰነው ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር ብለዋል፡፡ሆኖም በቅርቡ ፀድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ መደረጉ ከጊዜው ጋር ሊጣጣምና መልስ ሊሆን የማይችል ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በዋጋ ጭማሪውም ከኢንተርፕራይዞችና ከቴአትር ፕሮዲዩሰሮች ለቴአትር ቤቱ ቅሬታ እየቀረበ መሆኑን፣ ችግሩ በጥናት ተለይቶ ማስተካከያ ማድረግ የሚያስፈልግ ከሆነ ቴአትር ቤቱ ማስተካከያ ከማድረግ ወደኋላ እንደማይል አቶ ካሌብ አስታውቀዋል፡፡
©️ሪፖርተር ጋዜጣ

❤11👎2😢1
📌የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን 20ኛ ዓመት መታሰቢያ
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደስላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ታላቁን ደራሲ፣ ገጣሚና የቴአትር ሰው ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የሚዘክር መርሐግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
ይህ መርሐግብር የተዘጋጀው ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ 20ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።
በዚህ መርሃ-ግብር ላይ የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን የማይረሱ ግጥሞች ላይ የሥነጽሑፍ ባለሞያ ትንታኔ ያቀርባል።
ለኢትዮጵያ ቴአትር ጥበብ መሰረት የጣሉ ተውኔቶቹም ዳሰሳ ይደረግባቸዋል። በተጨማሪም የደራሲውን ህይወትና ስራዎች የሚመረምረውና በፋሲል ይትባረክ የተጻፈው "ምጥቀት በቅኔ አክናፍ" የተሰኘው መጽሐፍ ላይም ዳሰሳ ለታዳሚው ይቀርባል።
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን ለ70 ዓመታት ያህል በምድር ላይ በቆየባቸው ጊዜያት በኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ አሻራውን አሳርፏል።
ሎሬቱ በየካቲት ወር 1998 ዓ.ም በሀገረ አሜሪካ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ይታወሳል።

❤5👍2
📌"የካቲት ወርሃ ገብረክርስቶስ" ዛሬ ይካሄዳል
ሠዓሊና ባለቅኔ ገብረክርስቶስ ደስታን የሚዘክርና በስሙ የተሰየመው ዓመታዊው "የወርሃ ገብረክርስቶስ" መሰናዶ ዘንድሮም እንደሚከበር ተገልጿል።
ለሦስተኛ ጊዜ የሚከበረው ይህ የጥበብ ቀን፣ የካቲት 14 ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ከ8:00 ጀምሮ ስድስት ኪሎ የጀርመን የባህል ማዕከል (ጎተ ኢንስቲትዩት) አጠገብ በሚገኘው የገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ የጥበብ ሙዚየም ውስጥ ይካሄዳል።
የባለቅኔው ገብረክርስቶስ ደስታ ግጥሞች የሚነበቡበትና የጥበብ አፍቃሪያን ስራዎቹን የሚያደምጡበት መድረክ ነው።
የሠዓሊው ዝነኛና ረቂቅ የሆኑ የዘመናዊ ስዕል ስራዎች ለዕይታ የሚቀርቡ ሲሆን፣ ስለ ስራዎቹ ጥልቅ ትንተና ከባለሙያዎች የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።
በዕለቱ ለሚታደሙ የጥበብ አፍቃሪያን፣ ይበልጥ የሚወዱትን የገብረክርስቶስ ግጥም በኮፒ መውሰድ የሚችሉበት ዕድል እንደተመቻቸ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዘጋጆቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህ ልዩ መርሐግብር በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም የሚታሰብ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከማርች 28 እስከ ኤፕሪል 1 2026 ድረስ በአሜሪካ ኦክላሆማ እና ሌሎች ከተሞች በድምቀት እንደሚከበር ታውቋል።

❤4👍2