Event Addis Media
9.43K subscribers
6.32K photos
15 videos
4 files
4.93K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌"ለተጨነቃችሁ ወገኖች በሙሉ፤ አሁን ደህና ነኝ"

ሱሌማን አብደላ ከሦስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ማኅበራዊ ትስስር ገጹ ተመለሰ

ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሱሌማን አብደላ ላለፉት ሦስት ዓመታት ከሚዲያ ዓለም ርቆ ከቆየ በኋላ፣ በይፋ ወደ ማኅበራዊ ትስስር ገጹ መመለሱንና ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን አስታወቀ።ሱሌማን ካሳለፈው አስቸጋሪ የእስር ቤት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለደጋፊዎቹና ለወዳጆቹ ባስተላለፈው መልእክት፣ በቆይታው ለተጨነቁለትና ከጎኑ ለቆሙት ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

ሱሌማን አብደላ ባስተላለፈው መልእክት፦ "ለሦስት ዓመት የሚዲያ መጥፋቴና በአስቸጋሪ እስር ቤት ቆይታዬ ለተጨነቃችሁ ወገኖች በሙሉ፤ አሁን ደህና ነኝ" ብሏል።

የእስር ቆይታውን ሲገልጽም፦ "ቀንና ሌሊቱ በማይለይባቸው፣ ድቅድቅ ጨለማ በለበሱና እጅግ አስቸጋሪ በሚባሉ እስር ቤቶች ውስጥ በጽናት አሳልፌያለሁ" ሲል ገልጾታል።

ሱሌማን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ በጸሎት (በዱዓ) ላሰቡትና እሱን ከእስር ለማስፈታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ደጃፍ ድረስ በመሄድ ድምፅ ለሆኑት ወገኖቹ ያለውን ጥልቅ አክብሮትና ምስጋና ገልጿል።

"ምስጋና መግለጽ ከሚችለው በላይ ሆኖ የቃላት አንደበት ቢያንሳችሁም፣ እጅግ አመሰግናለሁ" ሲል ስሜቱን በጽሑፍ አስፍሯል።

https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
14🤨2👍1🙏1
📌የመለስ ዜናዊ መጽሐፍ በአማርኛ ተተረጎመ

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በብዕር ስም የጻፉት የልብ-ወለድ መጽሐፍ በአማርኛ ተተረጎመ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ "ተስፋይ የኋላሸት" በሚል የብዕር ስም በትግርኛ ቋንቋ የደረሱት "ምኹሕኻሕ ዘይፍልየሉ ማዕፆ" የተሰኘው መጽሐፍ፣ "መንኳኳት የማይለየው በር" በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ ሊበቃ መሆኑን ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

ይህ በልብ-ወለድ ዘውግ የተጻፈው ስራ፣ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የስነ-ጽሁፍ ብቃት የተመሰከረበትና የቋንቋ አጠቃቀማቸውም በከፍተኛ ሁኔታ የተደነቀበት ስራ መሆኑ ይነገርለታል።

መጽሐፉ ቀደም ባሉት ዓመታት ትግርኛ ቋንቋን በሚያውቁና ለስነ-ጽሁፉ ቅርበት ባላቸው ጥቂት አንባቢዎች ዘንድ ብቻ ተወስኖ የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ግን በተስፋየ አድሐኖም ተተርጉሞ ለሰፊው አንባቢ ሊቀርብ ችሏል።

አቶ መለስ ዜናዊ በዚህ ስራቸው በብዙዎች ዘንድ "የትግርኛ ቋንቋው ዳኛቸው ወርቁ" የሚል ቅጽል ስም እስከመሰጠት የደረሰ ከፍተኛ የፈጠራ ክህሎት እንዳሳዩበት ይነገራል።

ደራሲው ከዚህ ስራቸው በተጨማሪ "ገነቲና" የተሰኘ ሌላ የመጀመሪያ የልብ-ወለድ ስራ እንዳላቸውም ይታወቃል።

ይህ በአማርኛ ተተርጉሞ የተዘጋጀው "መንኳኳት የማይለየው በር" መጽሐፍ፣ በቅርቡ በገበያ ላይ ለንባብ እንደሚበቃ ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
29👍1👎1🥰1👏1
📌ዛሬ ዓለም አቀፍ የሬድዮ ቀን ነው

በዓለም ዙሪያ ከ44 ሺህ በላይ ሬዲዮ ጣቢያዎች በየዕለቱ መረጃዎችን ለዓለም ህዝብ ያደርሳሉ።

ኖሮ ሬድዮ ስለ ሬድዮ ያሰባሰባቸው እውነታቸው እንደሚያሳዩት ከ5 ቢሊየን በላይ የሚሆኑ የዓለማችን ህዝቦች የሬዲዮ አድማጮች መሆናቸውንም መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የዓለም ራዲዮ ቀን እንዲከበር በስፔን የራዲዮ አካዳሚ አነሳሽነት ጥያቄው በፈረንጆቹ በ2010  ለ(UNESCO) የስራ አመራር ከቀረበ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ጉዳዩን ተቀብሎ ዓለም አቀፍ የራዲዮ ቀን በየዓመቱ የካቲት 13(በኛ የካቲት 6) እንዲከበር ወስኗል።

ከ152 ዓመታት በፊት እንደተፈጠር የሚነገርለት ሬድዮ  ከ100 ዓመታት በላይ ሰዎች በየዕለቱ በስራ ቦታቸው፣ በትራንስፖርት ላይ እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ያደምጡታል።

በሀገራችን የመጀመሪያው ሬድዮ የኢትዮጵያ ሬድዮ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስርጭት ላይ የሚገኙ ከ50 በላይ የሬዲዮ ጣቢያዎች አሉ፡፡

የመጀመሪያው ኤፍ.ኤም የሬዲዮ ጣቢያ ኤፍ.ኤም 97.1 ነው። የመጀመሪያው የግል የሬዲዮ ጣቢያ ሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 ነው።

ሸገር 102.1፣ ፋና ኤፍ ኤም 98.1፣ ዛሚ (የአሁኑ አዋሽ)፣ ብስራት 101.1፣ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8፣አሐዱ 94.3፣ አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 እና ሌሎችም በስርጭት የሚገኙ የከተማችን ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያዎች ናቸው።

የኢኮኖሚና ዋልታ ቡና ቡና፣ ፀሐዬ ደመቀች፣ የተስፋዬ ገብሬ ስፖርት ለጤንነት ፣የአሸናፊ ከበደ እረኛው ባለዋሽንት ክላሲካል ፣ የኢትዮጵያን እንቃኝ የኪሮስ ኃይለስላሴ ድምፅ፣የአይሬ አሆይ፣ የዘፈን ምርጫ ኢንትሮ  እና ሌሎችም የማይረሱ የሬድዮ የሙዚቃ ድምፆች ናቸው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
15👍4🥰3👏1
📌በኢትዮጵያ ከ60 በላይ ሬድዮ ጣቢያዎች አሉ

ኖር ሬድዮ ስለ ኢትዮጵያችን የሬድዮ ጣቢያዎች ብዛት መረጃ አሰባስቧል። በዚህም በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያሉት የሬዲዮ ጣቢያዎች ቁጥር እንደ ፈቃድ አሰጣጥ ዘርፋቸው የሚለያይ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በቅርብ ዓመታት ባወጣው መረጃ መሠረት አጠቃላይ የጣቢያዎቹ ቁጥር ከ60 በላይ ደርሷል።

እነዚህን ጣቢያዎች የመንግሥት ሬዲዮ ጣቢያዎች፣የግል የንግድ ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ የማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች በማለት በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች ከፍሎ ማየት ይቻላል።

የመንግሥት ሬዲዮ ጣቢያዎች በፌዴራል እና በክልል መንግሥታት የሚመሩ ናቸው። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ሬድዮ ፣ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ፣ደቡብ ኤፍ ኤም 100.9 እዚህ ውስጥ ይካተታሉ።

የግል የንግድ ሬዲዮ ጣቢያዎች እነዚህ..ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/128

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5
📌በዓለም ከ44 ሺህ በላይ ሬድዮ ጣቢያዎች ይገኛሉ

በአሜሪካ ብቻ 15ሺ ሬድዮ ጣቢያዎች አሉ

​ዛሬ የካቲት 6፤ ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ቀን ነው። ዘንድሮ ቀኑ ሲከበር ትልቁ መነጋገሪያ "ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ሬዲዮ" የሚለው ጉዳይ ነው።

​ብዙዎች እንደሚሉት AI ለሬዲዮ ስራ መፋጠንና መዘመን ትልቅ መሳሪያ (Tool) ነው። ድምፅን ለማጥራት፣ መረጃዎችን በፍጥነት ለማቀናበርና ለትርጉም ስራዎች ወደር የለውም። ነገር ግን AI በራሱ መረጃ (Information) ሊሆን ይችላልን የሚለው ዋነኛ የመወያያ ርዕስ ነው።

ዩኔስኮን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያወጧቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ከ44,000 በላይ ንቁ የሬዲዮ ጣቢያዎች ይገኛሉ።

ባህላዊውን የሬዲዮ ስርጭት (AM/FM) ተከትሎ የመጣው የኢንተርኔት ሬዲዮ እና ፖድካስት (Podcast) የዘርፉን ስፋት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮታል። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በዓለም ዙሪያ ..ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/129

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3👍1🥰1
📌የሮይተርስ የዜና ወኪሎች በኢትዮጵያ ታገዱ

ኢትዮጵያ የሮይተርስ የዜና ወኪል ጋዜጠኞችን በሀገሪቱ የመሥራት መብት እንደነጠቀች የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ።

በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ የሚካሔደውን 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ለሬውተርስ የተሰጠው ፈቃድ እንደተሰረዘ የዜና ወኪሉ ቃል አቀባይ በኢሜይል እንደገለጹ ዘገባው ይጠቁማል። ከዚህ በተጨማሪ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ ሦስት የሬውተርስ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ የመዘገብ ፈቃድ እንዳልታደሰ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

ሬውተርስ የውሳኔው ገፊ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ያለው ነገር የለም። ሁሉም ጋዜጠኞች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሬውተርስ ስለ ኢትዮጵያ በሚሠራቸው ዘገባዎች የጀርባ አጥንት እንደነበሩ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ገልጿል።

ሬውተርስ “ጉዳዩን እየገመገመ” እንደሚገኝ እና “ነጻ፣ ገለልተኛ እና አስተማማኝ በሆነ መንገድ” ስለ ኢትዮጵያ ዘገባዎች መሥራቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በጉዳዩ ላይ ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ እንዳላገኘ በዘገባው ጠቅሷል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባልደረባ ስለ ጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸው መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። 

ሬውተርስ ከጥቂት ቀናት በፊት ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ማሰልጠኛ መከፈቱን የሚዘግብ ሰፊ ሪፖርት አቅርቦ ነበር ሲል ዶቼቬሌ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5😁5👍4🔥1👏1
📌ኢትዮጵያዊቷ ሴት በፎርብስ የፊት ገጽ ላይ

​ታዋቂዋ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ-ጥር የሆነችው ኢትዮጵያዊት ስራ ፈጣሪ ቤተልሔም ጥላሁን ዓለሙ፤ በማርች 2026 የፎርብስ አፍሪካ መጽሔት እትም ላይ በክብር ሰፍራለች።

​"Build Something People Will Love" በሚል መሪ ቃል የቀረበው ይህ ዘገባ፤ ቤተልሔም በሁለት ዘርፎች እያመጣች ያለውን ለውጥ በዝርዝር ዳስሷል።

ቤተልሔም ጥላሁን ከጫማ እስከ ጤፍ፣ ከጤፍ እስከ ኤሌክትሪክ መኪና የኢትዮጵያ የስራ ፈጠራ ተምሳሌትነቷን በተግባር እያሳየች የምትገኝ ኢትዮጵያዊ ስራ ፈጣሪ ነች።

​ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
37👏5🥰2🙏1
📌ኖር ሬድዮ በዩቲዩብ አማራጭ ወደ ስራ ገባ

የEvent Addis media  (እህት ካምፓኒ በሉት) አሪፍ የሚዲያ አማራጭ የሆነው "ኖር ሬድዮ" በዩቲዩብ አማራጭ ወደ ስራ ገብቷል።

ቀሪውን መልዕክት ከታች አንብቡት!

በመዝናኛ እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርገው "ኖር ሬድዮ" ዲጂታል ሚዲያ በዩቲዩብ ወደ ስራ ገብቷል።

ኖር ሬድዮ ዛሬ የካቲት 8 2018 ዓ.ም ስራውን የጀመረው "ወሬ ገበያ "በተሰኘው የወሬ ሰዓቱ ነው።

"ወሬ ገበያ" በኖር ሬድዮ በመጀመሪያ ቪዲዮው ተከታዮቹን ወሬዎች ለአድማጮች ያቀርባል።

1. ኢትዮጵያዊቷ ታደጊ በቲክቶክ አስተያየቶች ምክንያት ራሷን አጠፋች

2. "ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን እስክታሸንፍ ድረስ ፀጉሬን አልቆርጥም" ያለው ፈረንጅ መነጋገሪያ ሆኗል

3.በተከታታይ እየጨመረ የሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም የታሪፋ ዋጋ ከአቅማችን በላይ ነው ያሉ ተጠቃሚዎች ቅሬታ አቀረቡ

4. ኤምሬትስ ከቤት ሠራተኞ ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን ከረቸመች

መረጃዎቹን በዩቲዩብ ገጻችን ይከታተላሉ:-

https://youtu.be/tXjrE5tBylg?si=of8etFG4Zw9xxWAf


በተጨማሪም የፌስቡክ ገጻችንን ይወዳጁ!

https://www.facebook.com/profile.php?id=61558246481526

የቴሌግራም ቻናላችንን ብትቀላቀሉም ደስተኛ ነን

https://t.me/NorRadio1

እናመሰግናለን !
12🔥3
📌የአማን ፍሰሃፅዮን ስንብትና የቀብር ሥነሥርዓት

የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መስራችና ስራ አስኪያጅ አማን ፍስሃፅዮን ባሳለፍነው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ይታወሳል።

የአስከሬን አቀባበል የክብር ስንብት እና የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው የስንብት ስነ-ስርዓቱን እንደሚከተለው አዘጋጅቷል።

የስንብት መርሃግብሩ የሚካሄደው የፊታችን ሐሙስ የካቲት 12 2018 ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም ነው።

ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጉዞ ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ አድዋ ሙዚየም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ለስንብት መርሃግብር ስርዓት አስከሬኑ አደዋ ሙዚየም ይደርሳል።

ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አስከሬኑ ወደ መጨረሻ ማሪፊያው ጉዞ ይጀምራል። ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር የግብዓተ መሬት ስነ-ስርዓት ይፈጸማል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢132
📌መልቲቾይስ ኢትዮጵያ ለመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና ዕድል አስጀመረ

መልቲቾይስ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ከፍተኛ አቅም ያላቸውን ተማሪዎች በዲጂታል እውቀትና በኮዲንግ ክህሎት ለማብቃት የሚያስችለውን የኢትዮጵያ የወደፊት ባለ ክህሎቶች" የተሰኘ የሥልጠና ዕድል በይፋ አስጀመረ።

ይህ ሥልጠና የኩባንያው የማኅበራዊ ኃላፊነት (CSI) ስትራቴጂ አካል ሲሆን፣ መልቲቾይስ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ተኮር አጋርነቱን ለማጠናከርና በሀገር ተስፋዎች ላይ የአቅም ግንባታ ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

የመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገሊላ ገብረሚካኤል እንደገለጹት፣ የመልቲቾይስ አፍሪካ “ሕይወትን ማበልጸግ” መርህ ተጨባጭ ተፅዕኖ በመፍጠር ላይ የተመሰረተ ነው። "ይህ የቴክኖሎጂ ሥልጠና ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዲጂታል ክህሎቶችን በሚገባ እንዲጨብጡና በቀጣዩ የዲጂታል ዓለም በልበ ሙሉነት እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚያነሳሳ ትልቅ እርምጃ ነው" ሲሉም አክለዋል።

ለ12 ሳምንታት በሚቆየው በዚህ የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና፣ ካመለከቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች መካከል 30 ተማሪዎች ተመርጠው ሥልጠናውን የጀመሩ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 50 በመቶው ልጃገረዶች መሆናቸው ልዩ ያደርገዋል።

ሥልጠናው ጥራቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሰጥ መልቲቾይስ ኢትዮጵያ ከየኔታ ኮድ አካዳሚ ጋር በመተባበር እያከናወነው ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተጀመረው ይህ ፕሮግራም፣ ወደፊት ወደ ክልል ከተሞችም የመስፋፋት ዕቅድ እንዳለው ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6👏1
📌ቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ የመዘጋት ስጋት ላይ ነው

የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ፣ ከመንግስት የሚሰጠው በጀት ካልቀጠለ በስተቀር በሚቀጥሉት ሰባት ሳምንታት ውስጥ ስራውን ሊያቆም እንደሚችል ተነገረ።

የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር ቲም ዴቪ እንዳስታወቁት፣ የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ዓመታዊ በጀት 400 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን፣ አብዛኛው የሚሸፈነው ከአገር ውስጥ የፍቃድ ክፍያ ነው። የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለፈው ዓመት 137 ሚሊዮን ፓውንድ አስተዋጽዖ ያደረገ ቢሆንም፣ ይህ የገንዘብ ድጋፍ በመጋቢት ወር መጨረሻ (እ.ኤ.አ. March 2026) ያበቃል።

እስካሁን ድረስ ከዚያ በኋላ የሚሆን ምንም ዓይነት የገንዘብ ዋስትና ወይም ዕቅድ የለም።

የቀድሞው የተመድ ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን "ብሪታንያ ለዓለም የሰጠችው ትልቁ ስጦታ" ሲሉ የገለጹት ይህ ተቋም፣ በ43 ቋንቋዎች የተለያዩ ይዘቶችን ያሰራጫል። (የአማርኛ አገልግሎትን ጨምሮ ማለት ነው) በሳምንት 313 ሚሊዮን ሰዎችን ይደርሳል።

በኢራን፣ አፍጋኒስታን፣ ዩክሬን፣ ጋዛ እና ሱዳን ባሉ የጦርነት ቀጣናዎች ለሚገኙ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ብቸኛው የመረጃ ምንጭ እና የሕይወት አድን መስመር ነው።

የቢቢሲ መዳከም በዓለም አቀፍ የመረጃ ፍሰት ላይ ትልቅ ክፍተት ይፈጥራል ተብሎ ተሰግቷል።

የቢቢሲ መሪዎች እንደሚከራከሩት፣ ወርልድ ሰርቪስ የእንግሊዝን ባሕል እና ተጽዕኖ ለዓለም ከማስተዋወቅ ባለፈ የሀገሪቱ የብሔራዊ ደሕንነት አካል ነው። ሐሰተኛ መረጃዎች እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በበዛበት በዚህ ዘመን፣ ዕውነተኛ ጋዜጠኝነትን የሚተካ ምንም ነገር እንደሌለ ትንታኔው ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5👍2👏1
📌አስፈሪው አውሬ በምዕራብ ሸዋ ስጋት ፈጠረ

የኤርዶጋን ጋረዶች፣ ባለሂጃቧ ተርጓሚ !

⚓️የዛሬው የኖር ሬድዮ ወሬ ገበያ  የደራ ነው !

እነዚህ ጉዳዮችን ይዟል እነሆ:-

1. አስፈሪው አውሬ በምዕራብ ሸዋ ስጋት ተፈጠር

ደም መጥጦ ከመጣል ውጪ የሰው ስጋ እንደማበላ የተነገረለት አስፈሪ አውሬ የምዕራብ ሸዋ ነዋሪዎችን አስጨንቋል። በህብረተሰቡ ላይም ተደጋጋሚ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ ኖር ሬድዮ ሰምቷል።

2.የኤርዶጋን ጋረዶች፣ ባለሂጃቧ ተርጓሚ !

የፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን
ለየት ያለ አቀባበል፣አረንጓዴ ልብስ ያጠለቁ የደህንነት ጥበቃዎች እና ሃጃብ የለበሰችው አስተርጓሚ ፣እጅግ ለይት ያለው የመኪና ስጦታ፣የፕሬስዳንቱ ያልተጠበቀ ንግግር ልዩ ዘገባ በኖር ሬድዮ ወሬ ገበያ ይዘናል።

ወሬዎቹን ይሄው በዚህ በኩል ያድምጡ

Link:-https://youtu.be/dFfvxZhdAME?si=PvdrFo1FyCo3sJVU

በተጨማሪም የፌስቡክ ገጻችንን ይወዳጁ!

https://www.facebook.com/profile.php?id=61558246481526

የቴሌግራም ቻናላችንን ብትቀላቀሉም ደስተኛ ነን

https://t.me/NorRadio1

እናመሰግናለን !
8