Event Addis Media
9.49K subscribers
6.26K photos
14 videos
4 files
4.87K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌የሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም አዲስ መጽሐፍ

ሙሉ ሕይወታቸውን ለስነ-ጽሑፍ የሰጡት አንጋፋው ደራሲ ሳህለ ሥላሴ ብርሃነማርያም "የእሳቤ ሰዎች በኢትዮጵያ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለአንባቢያን አቅርበዋል።

ደራሲው የዓለምን ታላላቅ ስራዎች እንደ "መከረኞች" እና "የሁለት ከተሞች ወግ" ያሉትን ወደ አማርኛ በመተርጎምም ይታወቃሉ። በርካታ መጸሐፍትን ጽፈዋል። አዲሱ መጽሐፋቸው በኤዞፕ መጻሕፍት አሳታሚነት ለገበያ ቀርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4🙏4
📌ቴዲ አፍሮ እና ሮቤል ሚደቅሳ ተጣምሩ

በቅርቡ "ከበር አፍ" በሚል ርዕስ የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጮች ያቀረበውና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ ሮቤል ሚደቅሳ፣ ከድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ጋር የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ እንደሆነ ተሰምቷል።

ይህ የሙዚቃ ዝግጅት በኬንያ ሞምባሳ የሚካሄድ ሲሆን፣ የዘንድሮውን የፍቅረኛሞች ቀን ምክንያት በማድረግ ከአርብ የካቲት 6 እስከ ሰኞ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ይሆናል ተብሏል።

በዝግጅቱ ላይ ቴዲ አፍሮ፣ ሮቤል ሚደቅሳ እና ኤደን አይሸሹም ከአቡጊዳ ባንድ ጋር በመሆን የሙዚቃ ኮንሰርታቸውን ያቀርባሉ።

በተጨማሪም ታዋቂ ዲጄዎች በዝግጅቱ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል። የዚህ ዝግጅት ተጓዦችም በቀን በባህር ዳርቻ የመዝናናት፣ በምሽት ደግሞ በሙዚቃዊ ዝግጅቶች የማሳለፍ ዕድል ይኖራቸዋል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏8❤2
📌የሰለሞን ሳህለ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የገጣሚ ሰለሞን ሳህለ "በምስራቅ በኩል" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ጥር 30 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጽሐፍት መደብር ይመረቃል።

"በምሥራቅ በኩል" በሚል ርዕስ ለንባብ የበቃው ይህ መጽሐፍ፣ በእውነተኛ ታሪክ ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን፤ ደራሲው ካሳለፋቸው የጥበብ ዘውጎች ወጣ ባለ መልኩ ታሪክን እና ሰውን በጥልቀት የመረመረበት ሥራ እንደሆነ ተመላክቷል።

ሰለሞን ሳህለ ከሃሳብ ደደር፣ ከስሜት ኮስተር፣ ከእድሜ መተር ባለ ሁኔታ የሰውን ልጅ ማንነትና የታሪክ ኩነቶችን የመረመረበት ይህ አዲስ መጽሐፍ፤ በሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ጉጉትን ፈጥሯል።

በተለይ ከዚህ ቀደም ከለመድናቸው የግጥም ሥራዎቹ ባሻገር፣ አሁን የያዘው ረዥም የታሪክ ዘውግ ምን አይነት ለየት ያለ ጥበብ ይዞ መጣ የሚለው ነጥብ በብዙዎች ዘንድ ተጠባቂ ሆኗል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🙏3
📌ሀብታሙ አለባቸው ከአድናቂዎቹ ጋር ሊገናኝ ነው

በኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ ዘርፍ ባበረከታቸው ተወዳጅ የመጽሐፍት ስራዎቹ የሚታወቀው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው ከአንባቢያኑ ጋር የሚገናኝበት ልዩ መርሐግብር ተዘጋጅቷል።

ይህ የመጽሐፍት ፊርማ ሥነሥርዓት ደራሲው ስራዎቹን ከሚያደንቁ አንባቢያኑ ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሚያደርግበት እና በመጽሐፎቹ ላይ ፊርማውን የሚያኖርበት ልዩ አጋጣሚ እንደሚሆን ተነግሯል።

የፊርማ መርሐግብር የሚካሄደው ለገሐር በሚገኘው አዲሱ ጃዕፈር መጽሐፍት መደብር ውስጥ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ ዛሬ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 እንደሚከናወን ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5👍2🙏2
📌በ30 ሆቴሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ በቅርቡ ለሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ወደ አገሪቱ ለሚመጡ እንግዶች አገልግሎት በሚሰጡ 30 ሆቴሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያካሄደ መሆኑን ገለጸ።

ባለስልጣኑ ይህንን እርምጃ የጀመረው አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗን ተከትሎ፣ አገሪቱ መሪዎችን የመቀበል አገራዊ ኃላፊነቷን በብቃት እንድትወጣና መልካም ገጽታዋን እንድታስጠብቅ ለማስቻል መሆኑን ጠቁሟል።

ቁጥጥሩ በተለይ ለጉባኤው ተሳታፊዎች ማረፊያነት የተመረጡ 30 ባለአራት እና ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎችን የሚያካትት ሲሆን፣ የመኝታ ክፍሎች ጽዳትና ደረጃ፣ የምግብ ማብሰያ ቦታዎች የጤና ደህንነት እንዲሁም አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች ላይ የተኮረ መሆኑን ተመላክቷል።

ባለስልጣኑ በቁጥጥር ሂደቱ ወቅት የሚታዩ ክፍተቶችን ከሆቴል ባለቤቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ፈጣን የማስተካከያ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም፣ ሁሉም ሆቴሎች በኢትዮጵያ የቆየ የእንግዳ ተቀባይነት ባህልና ወግ መሠረት የተሟላ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወትሮው የተለየ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተመልክቷል።

ይህ የቁጥጥር ሥራ ጉባኤው እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም እንግዶችን ሊከሰቱ ከሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች መከላከልና ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል በመሆን ያላትን ሚና ይበልጥ ማጠናከር እንደሆነ ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍8❤7🙏1🤡1
📌120 ውሾች ያለበቂ ምክንያት በአንድ ሌሊት መገደላቸው ቅሬታ አስነሳ

በቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 12 በሚገኝ ሼልተር በእንክብካቤ የተያዙ ክትትል የሚደረግላቸው 120 ውሾች በአንድ ሌሊት ተገደሉ። á‹ľáˆ­áŒŠá‰ą የተፈጸመው ድርጅቱ ህጋዊ እውቅና ኖሮት እየሰራ ባለበት ሁኔታ መሆኑ ክስተቱን አነጋጋሪ አድርጎታል ሲል ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

በእንስሳት መብት ተሟጋችነቷ የምትታወቀው ሀና አሰፋ በመንግስት የጸጥታ አካላት በተወሰደ ድንገተኛ እርምጃ መጠለያ ውስጥ የነበሩ 120 ውሾች መገደላቸውን በከፍተኛ ሀዘን ገለጸች።

የእንስሳት መብት ተሟጋቿ ሀና አሰፋ ዛሬን "በህይወቴ ካሳለፍኳቸው እጅግ አሳዛኝ ቀናት አንዱ ነው" ስትል ገልጻዋለች።

ኖር ሬድዮ እንደሰማሁ ከሆነ እነዚህ ውሾች በጎዳና ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ተለቅመው በመጠለያው ውስጥ ህክምና ሲደረግላቸው የቆዩ ....ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/111

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢26❤4💔4🤬2
📌በአንዳንድ ፖሊሶች ስልኮችንን እየተቀማን ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ የጸጥታ አካላት በተለይም ምሽት ላይ በሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች ላይ የሞባይል ስልክ ቅሚያ እያደረሱ መሆኑን ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

ጉዳዩን ለፖሊስ ጣቢያዎች የሚያመለክቱ ዜጎችም "የፖሊስን ስም ለማጥፋት የተጠነሰሰ ሴራ ነው" በሚል ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል።

ለኖር ሬድዮ ቅሬታቸውን ያቀረቡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ የጸጥታ አካላቱ አመሻሽ ላይ መንገድ ላይ የሚያገኟቸውን ሰዎች በማስቆም "ስልክህን አምጣና ፓስወርዱን ክፈት" በማለት ምርመራ ያካሂዳሉ.. ተጨማሪውን ያንብቡ :https://t.me/NorRadio1/107

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍8🤬7😨3❤1🔥1
📌ባካሪ ሳኛ ወደ ዱባይ ከተመለሰ ሳምንት ሆኖታል

የቀድሞው የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ ፈረንሳዊ ኮከብ ተከላካይ ባካሪ ሳኛ፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ።

ኮከቡ በሀገሪቱ ያለውን ቆይታ አጠናቆ ወደ መኖሪያው ዱባይ ከተመለሰ አንድ ሳምንት ቢሆነውም፣ የቆይታው ውጤት ግን ለሀገሪቱ ስፖርትና ኢኮኖሚ አዲስ ተስፋ የሰነቀ ሆኗል።

ባካሪ ሳኛ በ"ሰይፉ ሾው" ላይ በነበረው ቆይታ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ዕቅድ እንዳለው ቢገልጽም፣ ዘርፉን ...ተጨማሪውን ያንብቡ:https://t.me/NorRadio1/112

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤8👏1
Channel photo removed
Channel photo updated
📌"እንዲህም ተኑሯል" መጽሐፍ ሊመረቅ ነው

ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት በስነ-ጽሁፍና በጋዜጠኝነት ሙያ አሻራቸውን ያሳረፉት አንጋፋው ደራሲ፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ አበራ ለማ፤ የሕይወት ጉዟቸውን የዳሰሱበት "እንዲህም ተኑሯል" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሰሞኑ ለንባብ በቅቷል።

በ550 ገጾች ተሰናድቶ ለንባብ የበቃው ይህ የግለ-ታሪክ መጽሐፍ፤ የደራሲውን የልጅነት ትዝታዎች፣ የጦር ግንባር ጋዜጠኝነት ተሞክሮዎችን፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩ እንቅስቃሴዎችንና የስነ-ጽሁፍ ህይወታቸውን በስፋት ይተነትናል።

ደራሲ አበራ ለማ  "ሞገደኛው ነውጤ" "ኩል ወይስ ጥላሸት"፣ "ሕይወትና ሞት" በተሰኙና በሌሎች ከ21 በላይ በሚሆኑ ተወዳጅ ስራዎቻቸው በአንባቢያን ዘንድ ከፍ ያለ ክብርን ያተረፉ የሥነጽሑፍ ሰው ናቸው።

ይህም መጽሐፋቸው የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በወመዘክር (በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ-መጻሕፍትና አገልግሎት ) ወመዘክር ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤14👍2
📌ጥርስ አብቅሎ የተወለደው ሕጻን

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንድ የወተት ጥርስ ያበቀለ ሕጻን መወለዱ ተገልጿል፡፡

በሆስፒታሉ አዋላጅ ነርስ የሆኑት መንግስቱ ኤባ በዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንድ የወተት ጥርስ ያበቀለ ሕጻን መወለዱን ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል፡፡

መሰል ክስተት ሕጻናት ቀድመው ከ6 ወራት በፊት የወተት ጥርስ የሚያበቅሉበት አጋጣሚ እንደሚፈጠር ሁሉ አዲስ ሕጻናት ሲወለዱም አልፎ አልፎ የወተት ጥርስ አብቅለው የመወለድ እድል እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡

ክስተቱ ሲያግጥም በሆስፒታሉ ታሪክ የመጀመሪያ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ አቤ በበኩላቸው ÷ የበቀለው የወተት ጥርስ ለቀጣይ የሕጻኑ ጥርስ አበቃቀል እንዲመች የሚወገድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ክስተቱ በሕጻኑ ጤና ላይ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለው አመልክተዋል፡፡

ማሕበረሰቡም አዲስ በተወለዱ ሕጻናት ላይ መሰል ክስተት አልፎ አልፎ የሚያጋጥም መሆኑን በመረዳት መደናገጥ እንደሌለበት አስገንዝበዋል ሲል FMC ዘግቧል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤12😱4😁2👍1🙏1
📌የወርሃ የካቲት የነገረ መጻሕፍት ፕሮግራም

(ከየካቲት 7 - 28/ 2018 ዓ.ም)

ሁላችሁም በነጻ ተጋብዛችኋል!

አወያይ:- እንዳለጌታ ከበደ

የካቲት 7/ 2018 ዓ.ም፣ ቅዳሜ ከሰአት፣ ከ8:00-12:00።
የተመረጠው መጽሐፍ:- “ሃያ ሶስት”
ተጋባዥ እንግዳ:- ዳንኤል አብርሃ

የካቲት 14/ 2018 ዓ.ም፣ ቅዳሜ ከሰአት፣
ከ8:00 - 12:00።
የተመረጠው መጽሐፍ:- “መመለስ”
ተጋባዥ እንግዳ:- ብርቱካን ሚደቅሳ

የካቲት 21/ 2018 ዓ.ም፣ ቅዳሜ ከሰአት፣ ከ8:00-12:00።
የተመረጠው መጽሐፍ:- “ዮዲታ”
ተጋባዥ እንግዳ:- ሮማን ተወልደብርሃን

የካቲት 28/ 2018 ዓ.ም፣ ቅዳሜ ከሰአት፣ ከ8:00-12:00።
የተመረጠው መጽሐፍ:- “የተከለከለው የኢትዮጵያ ታሪክ”
ተጋባዥ እንግዳ:- አሸናፊ ፈንቴ

አሰናጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ

የዝግጅት ቦታ:- FSS. አዳራሽ

በዝግጅቶቻችን ላይ በአካል በመገኘት መሳተፍ ለምትፈልጉ አድራሻችን:- ቀበና፣ ካቶሊክ፣ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አቅራቢያ፣ ወደ ሳንፎርድ ትምህርት ቤት በሚወስደው መንገድ፣ ባማ አዲስ ሕንፃ አጠገብ፣ FSS አዳራሽ ሲሆን፣ የመገኛ ቦታው Google Map link:-
https://maps.app.goo.gl/2n1myQXCCaTteCw69?g_st=ic

ለበለጠ መረጃ:-    0976066720
                               0900651010

በቴሌግራም ቻናላችንም ቤተሰብ ይሁኑን:-
https://t.me/ZagolBookBank1

ከዚህ ቀደም የተደረጉ ፕሮግራሞችን ለመከታተል:-
https://youtube.com/@endalegetamultimedia?si=hEO0egZkKPtR1mv0
❤14👍6🙏1
📌የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መስራችና ባለቤት አረፉ

የኢቤኤስ ቴሌቭዥን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 4 2018 ቀን ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ኤቢኤስ ቴሌቪዥን አስታውቋል።

አቶ አማን ፍሰሃጽዮን በኢትዮጵያ የግል ቴሌቪዥን ዘርፍ ጣቢያ ፈር ቀዳጅ ከመሆናቸው በተጨማሪ የጣቢያውን በስኬታማነት ያስቀጠሉ አመራር መሆናቸውን ባልደረቦቻቸው ይመሰክሩላቸዋል።

https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
💔17❤10🕊2😭2👍1👎1
📌"ለተጨነቃችሁ ወገኖች በሙሉ፤ አሁን ደህና ነኝ"

ሱሌማን አብደላ ከሦስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ማኅበራዊ ትስስር ገጹ ተመለሰ

ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሱሌማን አብደላ ላለፉት ሦስት ዓመታት ከሚዲያ ዓለም ርቆ ከቆየ በኋላ፣ በይፋ ወደ ማኅበራዊ ትስስር ገጹ መመለሱንና ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን አስታወቀ።ሱሌማን ካሳለፈው አስቸጋሪ የእስር ቤት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለደጋፊዎቹና ለወዳጆቹ ባስተላለፈው መልእክት፣ በቆይታው ለተጨነቁለትና ከጎኑ ለቆሙት ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

ሱሌማን አብደላ ባስተላለፈው መልእክት፦ "ለሦስት ዓመት የሚዲያ መጥፋቴና በአስቸጋሪ እስር ቤት ቆይታዬ ለተጨነቃችሁ ወገኖች በሙሉ፤ አሁን ደህና ነኝ" ብሏል።

የእስር ቆይታውን ሲገልጽም፦ "ቀንና ሌሊቱ በማይለይባቸው፣ ድቅድቅ ጨለማ በለበሱና እጅግ አስቸጋሪ በሚባሉ እስር ቤቶች ውስጥ በጽናት አሳልፌያለሁ" ሲል ገልጾታል።

ሱሌማን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ በጸሎት (በዱዓ) ላሰቡትና እሱን ከእስር ለማስፈታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ደጃፍ ድረስ በመሄድ ድምፅ ለሆኑት ወገኖቹ ያለውን ጥልቅ አክብሮትና ምስጋና ገልጿል።

"ምስጋና መግለጽ ከሚችለው በላይ ሆኖ የቃላት አንደበት ቢያንሳችሁም፣ እጅግ አመሰግናለሁ" ሲል ስሜቱን በጽሑፍ አስፍሯል።

https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤14🤨2👍1🙏1
📌የመለስ ዜናዊ መጽሐፍ በአማርኛ ተተረጎመ

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በብዕር ስም የጻፉት የልብ-ወለድ መጽሐፍ በአማርኛ ተተረጎመ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ "ተስፋይ የኋላሸት" በሚል የብዕር ስም በትግርኛ ቋንቋ የደረሱት "ምኹሕኻሕ ዘይፍልየሉ ማዕፆ" የተሰኘው መጽሐፍ፣ "መንኳኳት የማይለየው በር" በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ ሊበቃ መሆኑን ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

ይህ በልብ-ወለድ ዘውግ የተጻፈው ስራ፣ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የስነ-ጽሁፍ ብቃት የተመሰከረበትና የቋንቋ አጠቃቀማቸውም በከፍተኛ ሁኔታ የተደነቀበት ስራ መሆኑ ይነገርለታል።

መጽሐፉ ቀደም ባሉት ዓመታት ትግርኛ ቋንቋን በሚያውቁና ለስነ-ጽሁፉ ቅርበት ባላቸው ጥቂት አንባቢዎች ዘንድ ብቻ ተወስኖ የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ግን በተስፋየ አድሐኖም ተተርጉሞ ለሰፊው አንባቢ ሊቀርብ ችሏል።

አቶ መለስ ዜናዊ በዚህ ስራቸው በብዙዎች ዘንድ "የትግርኛ ቋንቋው ዳኛቸው ወርቁ" የሚል ቅጽል ስም እስከመሰጠት የደረሰ ከፍተኛ የፈጠራ ክህሎት እንዳሳዩበት ይነገራል።

ደራሲው ከዚህ ስራቸው በተጨማሪ "ገነቲና" የተሰኘ ሌላ የመጀመሪያ የልብ-ወለድ ስራ እንዳላቸውም ይታወቃል።

ይህ በአማርኛ ተተርጉሞ የተዘጋጀው "መንኳኳት የማይለየው በር" መጽሐፍ፣ በቅርቡ በገበያ ላይ ለንባብ እንደሚበቃ ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤29👍1👎1🥰1👏1
📌ዛሬ ዓለም አቀፍ የሬድዮ ቀን ነው

በዓለም ዙሪያ ከ44 ሺህ በላይ ሬዲዮ ጣቢያዎች በየዕለቱ መረጃዎችን ለዓለም ህዝብ ያደርሳሉ።

ኖሮ ሬድዮ ስለ ሬድዮ ያሰባሰባቸው እውነታቸው እንደሚያሳዩት ከ5 ቢሊየን በላይ የሚሆኑ የዓለማችን ህዝቦች የሬዲዮ አድማጮች መሆናቸውንም መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የዓለም ራዲዮ ቀን እንዲከበር በስፔን የራዲዮ አካዳሚ አነሳሽነት ጥያቄው በፈረንጆቹ በ2010  ለ(UNESCO) የስራ አመራር ከቀረበ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ጉዳዩን ተቀብሎ ዓለም አቀፍ የራዲዮ ቀን በየዓመቱ የካቲት 13(በኛ የካቲት 6) እንዲከበር ወስኗል።

ከ152 ዓመታት በፊት እንደተፈጠር የሚነገርለት ሬድዮ  ከ100 ዓመታት በላይ ሰዎች በየዕለቱ በስራ ቦታቸው፣ በትራንስፖርት ላይ እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ያደምጡታል።

በሀገራችን የመጀመሪያው ሬድዮ የኢትዮጵያ ሬድዮ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስርጭት ላይ የሚገኙ ከ50 በላይ የሬዲዮ ጣቢያዎች አሉ፡፡

የመጀመሪያው ኤፍ.ኤም የሬዲዮ ጣቢያ ኤፍ.ኤም 97.1 ነው። የመጀመሪያው የግል የሬዲዮ ጣቢያ ሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 ነው።

ሸገር 102.1፣ ፋና ኤፍ ኤም 98.1፣ ዛሚ (የአሁኑ አዋሽ)፣ ብስራት 101.1፣ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8፣አሐዱ 94.3፣ አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 እና ሌሎችም በስርጭት የሚገኙ የከተማችን ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያዎች ናቸው።

የኢኮኖሚና ዋልታ ቡና ቡና፣ ፀሐዬ ደመቀች፣ የተስፋዬ ገብሬ ስፖርት ለጤንነት ፣የአሸናፊ ከበደ እረኛው ባለዋሽንት ክላሲካል ፣ የኢትዮጵያን እንቃኝ የኪሮስ ኃይለስላሴ ድምፅ፣የአይሬ አሆይ፣ የዘፈን ምርጫ ኢንትሮ  እና ሌሎችም የማይረሱ የሬድዮ የሙዚቃ ድምፆች ናቸው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤15👍4🥰3👏1
📌በኢትዮጵያ ከ60 በላይ ሬድዮ ጣቢያዎች አሉ

ኖር ሬድዮ ስለ ኢትዮጵያችን የሬድዮ ጣቢያዎች ብዛት መረጃ አሰባስቧል። በዚህም በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያሉት የሬዲዮ ጣቢያዎች ቁጥር እንደ ፈቃድ አሰጣጥ ዘርፋቸው የሚለያይ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በቅርብ ዓመታት ባወጣው መረጃ መሠረት አጠቃላይ የጣቢያዎቹ ቁጥር ከ60 በላይ ደርሷል።

እነዚህን ጣቢያዎች የመንግሥት ሬዲዮ ጣቢያዎች፣የግል የንግድ ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ የማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች በማለት በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች ከፍሎ ማየት ይቻላል።

የመንግሥት ሬዲዮ ጣቢያዎች በፌዴራል እና በክልል መንግሥታት የሚመሩ ናቸው። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ሬድዮ ፣ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ፣ደቡብ ኤፍ ኤም 100.9 እዚህ ውስጥ ይካተታሉ።

የግል የንግድ ሬዲዮ ጣቢያዎች እነዚህ..ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/128

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5
📌በዓለም ከ44 ሺህ በላይ ሬድዮ ጣቢያዎች ይገኛሉ

በአሜሪካ ብቻ 15ሺ ሬድዮ ጣቢያዎች አሉ

​ዛሬ የካቲት 6፤ ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ቀን ነው። ዘንድሮ ቀኑ ሲከበር ትልቁ መነጋገሪያ "ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ሬዲዮ" የሚለው ጉዳይ ነው።

​ብዙዎች እንደሚሉት AI ለሬዲዮ ስራ መፋጠንና መዘመን ትልቅ መሳሪያ (Tool) ነው። ድምፅን ለማጥራት፣ መረጃዎችን በፍጥነት ለማቀናበርና ለትርጉም ስራዎች ወደር የለውም። ነገር ግን AI በራሱ መረጃ (Information) ሊሆን ይችላልን የሚለው ዋነኛ የመወያያ ርዕስ ነው።

ዩኔስኮን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያወጧቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ከ44,000 በላይ ንቁ የሬዲዮ ጣቢያዎች ይገኛሉ።

ባህላዊውን የሬዲዮ ስርጭት (AM/FM) ተከትሎ የመጣው የኢንተርኔት ሬዲዮ እና ፖድካስት (Podcast) የዘርፉን ስፋት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮታል። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በዓለም ዙሪያ ..ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/129

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤3👍1🥰1
📌የሮይተርስ የዜና ወኪሎች በኢትዮጵያ ታገዱ

ኢትዮጵያ የሮይተርስ የዜና ወኪል ጋዜጠኞችን በሀገሪቱ የመሥራት መብት እንደነጠቀች የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ።

በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ የሚካሔደውን 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ለሬውተርስ የተሰጠው ፈቃድ እንደተሰረዘ የዜና ወኪሉ ቃል አቀባይ በኢሜይል እንደገለጹ ዘገባው ይጠቁማል። ከዚህ በተጨማሪ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ ሦስት የሬውተርስ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ የመዘገብ ፈቃድ እንዳልታደሰ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

ሬውተርስ የውሳኔው ገፊ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ያለው ነገር የለም። ሁሉም ጋዜጠኞች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሬውተርስ ስለ ኢትዮጵያ በሚሠራቸው ዘገባዎች የጀርባ አጥንት እንደነበሩ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ገልጿል።

ሬውተርስ “ጉዳዩን እየገመገመ” እንደሚገኝ እና “ነጻ፣ ገለልተኛ እና አስተማማኝ በሆነ መንገድ” ሾለ ኢትዮጵያ ዘገባዎች መሥራቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በጉዳዩ ላይ ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ እንዳላገኘ በዘገባው ጠቅሷል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባልደረባ ሾለ ጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸው መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። 

ሬውተርስ ከጥቂት ቀናት በፊት ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ማሰልጠኛ መከፈቱን የሚዘግብ ሰፊ ሪፖርት አቅርቦ ነበር ሲል ዶቼቬሌ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5😁5👍4🔥1👏1
📌ኢትዮጵያዊቷ ሴት በፎርብስ የፊት ገጽ ላይ

​ታዋቂዋ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ-ጥር የሆነችው ኢትዮጵያዊት ስራ ፈጣሪ ቤተልሔም ጥላሁን ዓለሙ፤ በማርች 2026 የፎርብስ አፍሪካ መጽሔት እትም ላይ በክብር ሰፍራለች።

​"Build Something People Will Love" በሚል መሪ ቃል የቀረበው ይህ ዘገባ፤ ቤተልሔም በሁለት ዘርፎች እያመጣች ያለውን ለውጥ በዝርዝር ዳስሷል።

ቤተልሔም ጥላሁን ከጫማ እስከ ጤፍ፣ ከጤፍ እስከ ኤሌክትሪክ መኪና የኢትዮጵያ የስራ ፈጠራ ተምሳሌትነቷን በተግባር እያሳየች የምትገኝ ኢትዮጵያዊ ስራ ፈጣሪ ነች።

​ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤37👏5🥰2🙏1