Event Addis Media
9.49K subscribers
6.26K photos
14 videos
4 files
4.87K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
በመዲናችን 'ሰው አልባ' የፖሊስ ጣቢያ ሊከፈት ነው

በአፍሪካ የመጀመሪያ እንደሆነ የተነገረለትና ሰው አልባ ወይም ዘመናዊ የፖሊስ ጣቢያ (Smart Police Station) በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደምስ ይልማ ተናገሩ።

ይህ ዘመናዊ ጣቢያ ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በተለየ መልኩ ተገልጋዮች በአካል ፖሊስን ሳያገኙ፣ በዲጂታል መንገድ በዋናው ማዕከል ከሚገኙ የፖሊስ ኦፊሰሮች ጋር በቪዲዮ እና በድምጽ በመገናኘት ጉዳያቸውን የሚያስፈጽሙበት ነው።

ምንም እንኳን ወንጀልን ለመከላከል የሰው ኃይል አስፈላጊ ቢሆንም፤ ይህ ቴክኖሎጂ አንድ ግለሰብ ወንጀል ሲፈጸምበት በፍጥነት ሪፖርት በማድረግ እና በጂፒኤስ (GPS) እንዲሁም በካሜራ የታገዘ መረጃ ለፓትሮል  ፖሊስ በማስተላለፍ  ወንጀለኞችን  በፍጥነት  ለመያዝ  ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል።

አገልግሎቱ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሱማሊኛ፣ እንግሊዝኛ እና በሌሎችም ቋንቋዎች  እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

በቦሌ ድልድይ አካባቢ የሙከራ ፕሮጀክት ሆኖ የተጀመረው ይህ አገልግሎት ÷ውጤታማነቱ ታይቶ እንደ መርካቶ እና መገናኛ ባሉ ወንጀልና የህዝብ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች በስፋት እንደሚተገበር ኮማንደር ደምስ ለታዲያስ አዲስ አብራርተዋል።

©️ሀና ሰይፉ (ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 )

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁32👏119👍2
📌ድምጻዊ ጆኒ ራጋ ምላሽ ሰጠ

ስለተፈጠረው ነገርም ማብራሪያ ሰጥቷል

በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተካሄደው "ጀማው" የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ድምጻዊ ጆኒ ራጋ የሚጠበቅበትን ያህል እንዳልተጫወተና ኮንሰርቱ ቶሎ እንደተጠናቀቀ በመግለጽ ከአድናቂዎቹ ለቀረበበት ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል።

ጆኒ ራጋ እንደገለጸው፤ ለኮንሰርቱ ልዩ ዝግጅት አድርጎ የነበረ ቢሆንም፣ ከእሱ በፊት መድረክ ላይ የነበረው ድምጻዊ ልጅ ሚካኤል ከተሰጠው የሰዓት ገደብ በላይ ...ተጨማሪውን ያንብቡ:- https://t.me/NorRadio1/93

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5👍2🕊1
📌ኢዜማ ፓርቲ "እየሞከርኩኝ ነው" አለ

ኮሜዲያን ያሲኖ በጀመረውና በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን ባገኘው "እየሞከርኩኝ ነው" በሚለው አነጋጋሪ የቪዲዮ ቻሌንጅ ላይ ኢዜማ ፓርቲም እንደተሳተፈ ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

ፓርቲው በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ እንደገለጸው፣ ይህንን አገላለጽ የተጠቀመው በሀገሪቱ ያለውን የሙሰኝነት ችግር ለመታገል ያለውን ቁርጠኝነት ለመግለጽ ነው።

ኢዜማ ባስተላለፈው መልዕክት፦"እየሞከርን ነው! ኑሮህን ያከበደብህን ሙሰኝነት በአማራጭ ሐሳብ ለመለወጥ፤ እየሞከርን ነው!" ሲል አስፍሯል። ፓርቲው የዜጎችን የኑሮ ውድነት እና ለሙስና መስፋፋት መፍትሔ ናቸው ያላቸውን አማራጭ የፖሊሲ ሐሳቦች ለማስተዋወቅ ወቅታዊውን የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ ተጠቅሞበታል።

©️ኖር ሬድዮ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁5110👎4👏4🖕1
📌ቴአትርን ከመሀል ከተማ በማውጣት ወደ ነዋሪው ደጅ ለማምጣት የተደረገ "ይበል" የሚያሰኝ ጅምር

የአቃቂ ቃሊቲ ነዋሪዎች የጥበብ ጥያቄ መልስ ሊያገኝ ነው ፤ በአዲሱ ዘመናዊ አዳራሽ ቴአትርና ፊልም መታየት ሊጀምር መሆኑ ተበስሯል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ጽሕፈት ቤት፣ አዳራሹን ለጥበብ ስራዎች አገልግሎት ለማዋል ዛሬ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከአራዳ ፊሊክስ ኢንተርቴይመንት ጋር የሥራ ስምምነት ተፈራርሟል።

ከዚህ ቀደም በክፍለ ከተማው ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ የቴአትርና የፊልም ማሳያ አዳራሽ ባለመኖሩ፣ ነዋሪው የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት ይቸገር እንደነበር ተገልጿል።

የክፍለ ከተማው ባህልና ኪነጥበብ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፦ "ከዛሬ በኋላ በከተማችን የሚታዩ ታዋቂ የቴአትርና የፊልም ስራዎችን ወደዚህ ዘመናዊ አዳራሽ በማምጣት የነዋሪውን ፍላጎት እናሟላለን" ብለዋል።

ይህ ዘመናዊ አዳራሽ ስራ መጀመሩ ለአካባቢው ነዋሪዎች የጥበብ አማራጭ ከመፍጠሩ ባለፈ፣ ለኪነጥበብ ባለሙያዎችም አዲስ የመድረክ ዕድል ይዞ መጥቷል። ስምምነቱን ተከትሎም በቅርብ ቀናት ውስጥ መደበኛ የኪነጥበብ ስራዎች ማሳየት እንደሚጀመር ይጠበቃል።

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የክፍለ ከተማው ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🔥42👏1
📌ኬንያ "የአፍሪካ ግራሚ አዋርድ" ልታዘጋጅ  ነው

ኬንያ  የግራሚ አዋርድን (Grammy Awards) ወደ አፍሪካ ምድር ለማምጣትና የዝግጅቱ በኩር አዘጋጅ ለመሆን ታሪካዊ የተባለውን ስምምነት አጠናቃለች።

ዝግጅቱ በታዋቂው የሪከርዲንግ አካዳሚ (Recording Academy) የሚመራ ሲሆን፣ ልክ እንደ ላቲን ግራሚ ሁሉ ለአፍሪካ የሙዚቃ ጥበብ ብቻ የተለየ የክብር መድረክ ይሆናል ተብሏል።

ይህን ታላቅ የኪነ-ጥበብ ድግስ ወደ ናይሮቢ ለማምጣት የኬንያ መንግሥት 3.9 ሚሊዮን ዶላር (ወደ 500 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ) የሚጠጋ እጅግ ግዙፍ መዋዕለ-ንዋይ ፈስሷል።

ዝግጅቱ "የአፍሪካ ግራሚ" በሚል ስም ራሱን ችሎ የሚካሄድ ዓለም አቀፍ መድረክ ሲሆን፤ ኬንያ  የማዘጋጀት መብቱን ቀድማ ለመያዝ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ የኬንያ ሽልንግ መድባለች።

ይህ ስምምነት የአፍሪካ ሙዚቀኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገባቸውን እውቅና እንዲያገኙና የኬንያ የቱሪዝም ዘርፍ እንዲነቃቃ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

©️አዲስ አድማስ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
14😁5👏2🤣1
📌የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተጨማሪ ሹመት

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በፓርላማ ሊሾሙ ነው። የኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባል እንዲሆኑ ከታጩት ዘጠኝ ግለሰቦች ውስጥ ስድስቱ አዳዲስ ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን እንደገና ለማቋቋም በ2015 የወጣው አዋጅ፤ የተቋሙ የስራ አመራር ቦርድ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሾሙ ይደነግጋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሐሙስ ጥር 28፤ 2018 በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባው ለኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባልነት በዕጩነት የቀረቡለትን ግለሰቦች መርምሮ ለማጽደቅ አጀንዳ ይዟል።

የኮርፖሬሽኑ ቦርድ፤ የብሔራዊ ቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያዎችን በስሩ የሚያስተዳድረውን ኢቢሲን በበላይነት የሚመራ አካል ነው። ቦርዱ የመገናኛ ብዙሃንን የሚመለከቱ የመንግስት ፖሊሲዎች እና ህጎች በኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ መሆናቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት በአዋጅ ተጥሎበታል።

በነገው የፓርላማ መደበኛ ሹመታቸው እንደሚጸድቅላቸው ከሚጠበቁት አዳዲስ የቦርድ አባላት መካከል ዲያቆን ዳንኤል ይገኙበታል። ለመሰል ኃላፊነት እንግዳ ያልሆኑት ዲያቆን ዳንኤል፤ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባልነትን ሹመት ለሶስት ተከታታይ ጊዜያት አግኝተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአራተኛ ጊዜ ለሹመት ፓርላማ የሚቀርቡት፤ ከእርሳቸው በፊት የኢቢሲ ቦርድን በሰብሳቢነት ይመሩ የነበሩትን ዶ/ር ለገሰ ቱሉን ለመተካት ነው።

©️ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🖕2016👎3👏2👍1💩1🤡1
📌የፕላስቲክ ቄጤማ ተከለከለ!

የፕላስቲክ ቄጤማ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከተከለከሉት የፕላስቲክ ምርቶች ውስጥ እንደሚካተት ተገለጸ

በሀገሪቱ እየተተገበረ ባለው የፕላስቲክ አጠቃቀም ክልከላ መሠረት የፕላስቲክ ቄጤማ ማምረትና መሸጥ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።

የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ፣ በተፈጥሯዊው ሳር (ቄጤማ) ምትክ እየቀረበ ያለው የፕላስቲክ ምርት በአካባቢና በጤና ላይ ከፍተኛ ብክለት እያስከተለ በመሆኑ ለመጠቀም ከተከለከሉት የፕላስቲክ ምርቶች ውስጥ እንደሚመደብ አብራርተዋል።

“ምርቱ አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል (Recycle) የማይመች በመሆኑ በቀጥታ አካባቢን ይበክላል” ያሉት ኃላፊው፡- ምርቱ በሀገር ውስጥ የሚመረት ከሆነ እንዲቆም፣ ከውጭ የሚገባ ከሆነም ሊታገድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም “እኛ የምናውቀውና የለመድነው ሕይወት ያለውን አረንጓዴ የተፈጥሮ ቄጤማ እንጂ ፕላስቲክ አይደለም” ብለዋል።

ስራ አስኪያጁ አቶ ዲዳ ማብራሪያቸውን ሲቀጥሉ፤ በክልከላው የተካተቱት ሁሉም ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶች መሆናቸውን ጠቅሰው የምርቱ ውፍረት እና መሰል መመዘኛዎች ከግምት ውስጥ እንደማይገቡ ተገልጿል።

የክልከላቸው ዋናው መስፈርት ምርቱ መልሶ ጥቅም ላይ የመዋል ዕድሉና ለአካባቢ በመበከል የሚኖረው አስተዋጽኦ ነው ተብሏል።

ፋብሪካዎች የማምረቻ ማሽኖቻቸውን በማዘመን ለአካባቢ ተስማሚ ወደሆኑ ምርቶች እንዲሸጋገሩ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ይህም እንደ ሥጋት ሳይሆን እንደ አዲስ የሥራ ዕድል ሊታይ እንደሚገባ ተመላክቷል።

©️አሐዱ ሬድዮ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏2212
📌የቱሪዝም ጋዜጠኛው ዘሪሁን ግርማ አረፈ

የቱሪዝም ጋዜጠኛው ዘሪሁን ግርማ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ የቅርብ ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል።

ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ ከአስር ዓመታት በላይ የሀገራችንን ባህል ቱሪዝም እና የሆስፒታሊቲ ኢንቨስትመንት ዝግጅቶችን በተለያዩ ሬድዮ ጣቢያዎች በቆንጆ አቀራረብ  ትውልዱ ስለ ሀገሩ ባህል ወግ እና እሴት እንዲሁም የቱሪዝም ሀብቶች እውቀት እንዲኖረው ብዙ ለፍተሃል።

ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ በሬድዮና ቴሌቪዥን በተለየ በጃኖ ቱሪዝም፣ በኢትዮ ቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ፣እንዲሁም ውብ ሀገር በተሰኙ የቱሪዝም ዝግጅቶቹ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሞያዎች ማኅበር በቱሪዝም ጋዜጠኛው ዘሪሁን ግርማ ድንገተኛ ህልፈት ተከታዩን መግለጫ አውጥቷል "ቱሪዝም ልጇን አጣች፣ቱሪዝምን አውርቶ የማይጠግበው በሀገሩ የሚኮራው በሬድዮ እና በቲቪ የሀገራችንን ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ብዙ ለመስራት ብዙ ለመሮጥ ሀገሩን በሰፊው ለማስተዋወቅ የውብ ሀገር ብሎ የጀመረው የማህበራችን መስራች እና አባል ወንድማችን ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ ድንገተኛ ሞት እጅግ በጣም አዝነናል"።

ነፍስ ይማር !

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢264🕊3👍1
📌የዘሪሁን ግርማ የቀብር ሥነሥርዓት ተፈጸመ

የጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ አስክሬን ከአዲስ አበባ ሀያት 49 ሰፈሩ ወደ አርባ ምንጭ የተሸኘ ሲሆን፣ አሁን ላይ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና የሙያ ባልደረቦቹ በተገኙበት አርባ ምንጭ ከተማ ደርሷል። የቀብር ስነ-ስርዓቱ ዛሬ ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ በአርባ ምንጭ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

ጋዜጠኛ ዘሪሁን ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያን ባህል እና ቱሪዝም ለማስተዋወቅ በታታሪነት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡

በጋዜጠኝነት  ሙያው ለረጅም ዓመታት የሀገራችንን ባህል፣ የቱሪስት መስህቦች ከማስተዋወቅ ባለፈ ለባህልና ለጥበባት ዘርፍ ዕድገትም  የነበረው ፍቅር ወደር የለሽ ነበር፡፡

ባለትዳር እና የ2 ልጆች አባት የነበረው ዘሪሁን የመጨረሻ ስራውን ወደ ከፋ በማምራት መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያንን በተመለከተ ዝግጅት የሰራ ሲሆን፤ ይህንኑም ዝግጅት ከ3 ቀናት በፊት በፌስቡክ ገፁ ላይ አጋርቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢95🕊2
📌የተክለጻድቅ መኩሪያ አዲስ መጽሐፍ

በርካታ የታሪክ መጻሕፍትን ለንባብ ያበቁት የአንጋፋው ምሁር ተክለጻድቅ መኩሪያ "የየካቲት ንቅናቄ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።

ይህ መጽሐፍ እሳቸው ካረፉ በኋላ በቤተሰቦቻቸው ጥረት የሕትመት ብርሃን ያገኘ ሲሆን፣ በስድስት ክፍሎችና በ18 ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው። መጽሐፉ በዋናነት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የየካቲቱን አብዮትና ለአብዮቱ ገፊ ምክንያቶችን በዝርዝር እንደሚዳስስም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6👍3🙏1
📌የሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም አዲስ መጽሐፍ

ሙሉ ሕይወታቸውን ለስነ-ጽሑፍ የሰጡት አንጋፋው ደራሲ ሳህለ ሥላሴ ብርሃነማርያም "የእሳቤ ሰዎች በኢትዮጵያ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለአንባቢያን አቅርበዋል።

ደራሲው የዓለምን ታላላቅ ስራዎች እንደ "መከረኞች" እና "የሁለት ከተሞች ወግ" ያሉትን ወደ አማርኛ በመተርጎምም ይታወቃሉ። በርካታ መጸሐፍትን ጽፈዋል። አዲሱ መጽሐፋቸው በኤዞፕ መጻሕፍት አሳታሚነት ለገበያ ቀርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4🙏4
📌ቴዲ አፍሮ እና ሮቤል ሚደቅሳ ተጣምሩ

በቅርቡ "ከበር አፍ" በሚል ርዕስ የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጮች ያቀረበውና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ ሮቤል ሚደቅሳ፣ ከድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ጋር የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ እንደሆነ ተሰምቷል።

ይህ የሙዚቃ ዝግጅት በኬንያ ሞምባሳ የሚካሄድ ሲሆን፣ የዘንድሮውን የፍቅረኛሞች ቀን ምክንያት በማድረግ ከአርብ የካቲት 6 እስከ ሰኞ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ይሆናል ተብሏል።

በዝግጅቱ ላይ ቴዲ አፍሮ፣ ሮቤል ሚደቅሳ እና ኤደን አይሸሹም ከአቡጊዳ ባንድ ጋር በመሆን የሙዚቃ ኮንሰርታቸውን ያቀርባሉ።

በተጨማሪም ታዋቂ ዲጄዎች በዝግጅቱ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል። የዚህ ዝግጅት ተጓዦችም በቀን በባህር ዳርቻ የመዝናናት፣ በምሽት ደግሞ በሙዚቃዊ ዝግጅቶች የማሳለፍ ዕድል ይኖራቸዋል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏82
📌የሰለሞን ሳህለ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የገጣሚ ሰለሞን ሳህለ "በምስራቅ በኩል" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ጥር 30 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጽሐፍት መደብር ይመረቃል።

"በምሥራቅ በኩል" በሚል ርዕስ ለንባብ የበቃው ይህ መጽሐፍ፣ በእውነተኛ ታሪክ ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን፤ ደራሲው ካሳለፋቸው የጥበብ ዘውጎች ወጣ ባለ መልኩ ታሪክን እና ሰውን በጥልቀት የመረመረበት ሥራ እንደሆነ ተመላክቷል።

ሰለሞን ሳህለ ከሃሳብ ደደር፣ ከስሜት ኮስተር፣ ከእድሜ መተር ባለ ሁኔታ የሰውን ልጅ ማንነትና የታሪክ ኩነቶችን የመረመረበት ይህ አዲስ መጽሐፍ፤ በሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ጉጉትን ፈጥሯል።

በተለይ ከዚህ ቀደም ከለመድናቸው የግጥም ሥራዎቹ ባሻገር፣ አሁን የያዘው ረዥም የታሪክ ዘውግ ምን አይነት ለየት ያለ ጥበብ ይዞ መጣ የሚለው ነጥብ በብዙዎች ዘንድ ተጠባቂ ሆኗል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🙏3
📌ሀብታሙ አለባቸው ከአድናቂዎቹ ጋር ሊገናኝ ነው

በኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ ዘርፍ ባበረከታቸው ተወዳጅ የመጽሐፍት ስራዎቹ የሚታወቀው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው ከአንባቢያኑ ጋር የሚገናኝበት ልዩ መርሐግብር ተዘጋጅቷል።

ይህ የመጽሐፍት ፊርማ ሥነሥርዓት ደራሲው ስራዎቹን ከሚያደንቁ አንባቢያኑ ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሚያደርግበት እና በመጽሐፎቹ ላይ ፊርማውን የሚያኖርበት ልዩ አጋጣሚ እንደሚሆን ተነግሯል።

የፊርማ መርሐግብር የሚካሄደው ለገሐር በሚገኘው አዲሱ ጃዕፈር መጽሐፍት መደብር ውስጥ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ ዛሬ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 እንደሚከናወን ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5👍2🙏2
📌በ30 ሆቴሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ በቅርቡ ለሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ወደ አገሪቱ ለሚመጡ እንግዶች አገልግሎት በሚሰጡ 30 ሆቴሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያካሄደ መሆኑን ገለጸ።

ባለስልጣኑ ይህንን እርምጃ የጀመረው አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗን ተከትሎ፣ አገሪቱ መሪዎችን የመቀበል አገራዊ ኃላፊነቷን በብቃት እንድትወጣና መልካም ገጽታዋን እንድታስጠብቅ ለማስቻል መሆኑን ጠቁሟል።

ቁጥጥሩ በተለይ ለጉባኤው ተሳታፊዎች ማረፊያነት የተመረጡ 30 ባለአራት እና ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎችን የሚያካትት ሲሆን፣ የመኝታ ክፍሎች ጽዳትና ደረጃ፣ የምግብ ማብሰያ ቦታዎች የጤና ደህንነት እንዲሁም አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች ላይ የተኮረ መሆኑን ተመላክቷል።

ባለስልጣኑ በቁጥጥር ሂደቱ ወቅት የሚታዩ ክፍተቶችን ከሆቴል ባለቤቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ፈጣን የማስተካከያ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም፣ ሁሉም ሆቴሎች በኢትዮጵያ የቆየ የእንግዳ ተቀባይነት ባህልና ወግ መሠረት የተሟላ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወትሮው የተለየ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተመልክቷል።

ይህ የቁጥጥር ሥራ ጉባኤው እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም እንግዶችን ሊከሰቱ ከሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች መከላከልና ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል በመሆን ያላትን ሚና ይበልጥ ማጠናከር እንደሆነ ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍87🙏1🤡1
📌120 ውሾች ያለበቂ ምክንያት በአንድ ሌሊት መገደላቸው ቅሬታ አስነሳ

በቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 12 በሚገኝ ሼልተር በእንክብካቤ የተያዙ ክትትል የሚደረግላቸው 120 ውሾች በአንድ ሌሊት ተገደሉ። ድርጊቱ የተፈጸመው ድርጅቱ ህጋዊ እውቅና ኖሮት እየሰራ ባለበት ሁኔታ መሆኑ ክስተቱን አነጋጋሪ አድርጎታል ሲል ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

በእንስሳት መብት ተሟጋችነቷ የምትታወቀው ሀና አሰፋ በመንግስት የጸጥታ አካላት በተወሰደ ድንገተኛ እርምጃ መጠለያ ውስጥ የነበሩ 120 ውሾች መገደላቸውን በከፍተኛ ሀዘን ገለጸች።

የእንስሳት መብት ተሟጋቿ ሀና አሰፋ ዛሬን "በህይወቴ ካሳለፍኳቸው እጅግ አሳዛኝ ቀናት አንዱ ነው" ስትል ገልጻዋለች።

ኖር ሬድዮ እንደሰማሁ ከሆነ እነዚህ ውሾች በጎዳና ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ተለቅመው በመጠለያው ውስጥ ህክምና ሲደረግላቸው የቆዩ ....ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/111

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢264💔4🤬2
📌በአንዳንድ ፖሊሶች ስልኮችንን እየተቀማን ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ የጸጥታ አካላት በተለይም ምሽት ላይ በሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች ላይ የሞባይል ስልክ ቅሚያ እያደረሱ መሆኑን ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

ጉዳዩን ለፖሊስ ጣቢያዎች የሚያመለክቱ ዜጎችም "የፖሊስን ስም ለማጥፋት የተጠነሰሰ ሴራ ነው" በሚል ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል።

ለኖር ሬድዮ ቅሬታቸውን ያቀረቡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ የጸጥታ አካላቱ አመሻሽ ላይ መንገድ ላይ የሚያገኟቸውን ሰዎች በማስቆም "ስልክህን አምጣና ፓስወርዱን ክፈት" በማለት ምርመራ ያካሂዳሉ.. ተጨማሪውን ያንብቡ :https://t.me/NorRadio1/107

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍8🤬7😨31🔥1
📌ባካሪ ሳኛ ወደ ዱባይ ከተመለሰ ሳምንት ሆኖታል

የቀድሞው የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ ፈረንሳዊ ኮከብ ተከላካይ ባካሪ ሳኛ፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ።

ኮከቡ በሀገሪቱ ያለውን ቆይታ አጠናቆ ወደ መኖሪያው ዱባይ ከተመለሰ አንድ ሳምንት ቢሆነውም፣ የቆይታው ውጤት ግን ለሀገሪቱ ስፖርትና ኢኮኖሚ አዲስ ተስፋ የሰነቀ ሆኗል።

ባካሪ ሳኛ በ"ሰይፉ ሾው" ላይ በነበረው ቆይታ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ዕቅድ እንዳለው ቢገልጽም፣ ዘርፉን ...ተጨማሪውን ያንብቡ:https://t.me/NorRadio1/112

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
8👏1
Channel photo removed
Channel photo updated
📌"እንዲህም ተኑሯል" መጽሐፍ ሊመረቅ ነው

ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት በስነ-ጽሁፍና በጋዜጠኝነት ሙያ አሻራቸውን ያሳረፉት አንጋፋው ደራሲ፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ አበራ ለማ፤ የሕይወት ጉዟቸውን የዳሰሱበት "እንዲህም ተኑሯል" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሰሞኑ ለንባብ በቅቷል።

በ550 ገጾች ተሰናድቶ ለንባብ የበቃው ይህ የግለ-ታሪክ መጽሐፍ፤ የደራሲውን የልጅነት ትዝታዎች፣ የጦር ግንባር ጋዜጠኝነት ተሞክሮዎችን፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩ እንቅስቃሴዎችንና የስነ-ጽሁፍ ህይወታቸውን በስፋት ይተነትናል።

ደራሲ አበራ ለማ  "ሞገደኛው ነውጤ" "ኩል ወይስ ጥላሸት"፣ "ሕይወትና ሞት" በተሰኙና በሌሎች ከ21 በላይ በሚሆኑ ተወዳጅ ስራዎቻቸው በአንባቢያን ዘንድ ከፍ ያለ ክብርን ያተረፉ የሥነጽሑፍ ሰው ናቸው።

ይህም መጽሐፋቸው የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በወመዘክር (በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ-መጻሕፍትና አገልግሎት ) ወመዘክር ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
14👍2