Event Addis Media
9.49K subscribers
6.26K photos
14 videos
4 files
4.87K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
ሼህ አላሙዲን 5 ዘመናዊ ሆቴሎች ሊያስገነቡ ነው

ንብረትነቱ የባለሀብቱ ሼህ አላሙዲን የሆነው​ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው 32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ዝግጁ የሚሆኑ 5 ዘመናዊ ሆቴሎችን በአዲስ አበባ እንደሚገነባ አስታውቋል።

​በአዲስ አበባ የሚሰሩት እና የሚታደሱት የትኞቹ ናቸው?

1. ሸራተን ግቢ: አሁን ካለው በተጨማሪ "ሸራተን አዲስ" የሚለውን ስያሜ የሚይዝ እጅግ ዘመናዊ ሆቴል።

2.ሚሊኒየም አዳራሽ: "Moxy by Marriott" የተሰኘ ዘመናዊ ሆቴል።

3.መሀመድያ መንደር.....ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/65
8👏2
📌"80 በመቶ ደንበኞቼ በአገልገሎቴ ደስተኛ ናቸው "
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

በበርካቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ቅሬታ የሚያቀርቡበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚሰጠው አገልግሎት የደንበኞቹ የእርካታ ደረጃ ከ80 ከመቶ መድረሱን ባካሄድኩት ጥናት አረጋግጫለሁ ሲል ዛሬ ይፋ ማድረጉን ኖር ሬድዮ ሰምቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ከዚህ ቀደም በአገልግሎት አሰጣጡ  ላይ በጥቂቱም ቢሆን ይታዩ ነበሩ ያላቸውን ከአሠራር ... ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/66
🤣103👎174😁4
📌ሎሬት መላኩ በላይ የክብር ሜዳሊያ ተሸለመ

ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፈው ኢትዮጵያዊው የዳንስ ባለሙያ እና የፈንድቃ ባህል ማዕከል መስራች መላኩ በላይ፤ ከፈረንሳይ መንግሥት የተሰጠውን ከፍተኛ የክብር ሜዳሊያ ሽልማት በክብር ተቀብሏል።

ባለሙያው የፈረንሳይን "ኦፊሴር ዴ ላ ኦርደሬ ዴስ አርትስ እና ዴስ ሌትረስ" (Officier de l'Ordre des Arts et des Lettres) ሜዳሊያ የተቀበለው በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ከሆነው አሌክስስ ላሜክ (Alexis Lamek) እጅ ነው። ይህ የክብር ሜዳሊያ በስነ-ጥበብ እና በስነ-ጽሁፍ ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የሚሰጥ ከፍተኛ ዕውቅና ነው።

ሽልማቱን በተቀበለበት ወቅት መላኩ በላይ ባስተላለፈው መልዕክት፤ የተሰማውን ጥልቅ ደስታ ገልጾ ሽልማቱ የጋራ ስኬት መሆኑን ተናግሯል፦"ይህ ክብር እኔን እና ፈንድቃን ለደገፉን ሁሉ ነው" ያለ ሲሆን፤ በአለም ዙሪያ ያሉ ታዳሚዎች በፈንድቃ ላይ ላሳዩት እምነት ምስጋና አቅርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
28🔥6😁5👏4👍2
📌የድምፃዊ ሳምቮድ እና ሜራ ኤቨንት ውዝግብ

ባለፈው ቅዳሜ ጥር 16 ቀን በግዮን ሆቴል በተዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ እንዲቀርብ ይጠበቅ የነበረው፣ በቅጽል ስሙ "ሳምቮድ" በመባል የሚታወቀው ድምፃዊ ሳሚ ካሳ፣ ከዝግጅቱ ውጪ ሆኗል።

"ሜራ ኢቨንት" ባዘጋጀው በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ እና ዳዊት ፅጌን ጨምሮ ሳሚ ካሳ እንደ "ሰርፕራይዝ" (ልዩ እንግዳ) ተጋብዞ የነበረ ቢሆንም፣ በመጨረሻው ሰዓት ከዝግጅቱ እንደተሰረዘ ይፋ ተደርጓል።

ሳሚ ካሳ በመጀመሪያ ከፕሮግራም አዘጋጆቹ ጋር በተስማማው ክፍያ መሠረት እንዲከፈለው የጠየቀ ቢሆንም ..ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/69

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
8👎31
📌"ሃያ ሶስት" መጽሐፍ ነገ በድምቀት ይመረቃል

*ለሁሉም ሚዲያዎች ክፍት ነው

በዳንኤል አብርሃ "ሃያ ሶስት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውና እውነተኛ የስደት ታሪኩን የተረከበት የመጀመሪያ መጽሐፉ ነገ አርብ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጽሐፍት አዳራሽ በድምቀት ይመረቃል፡፡

በምረቃ ዝግጅቱ ላይ ሁለገቡ አርቲስት ተስፋዬ ማሞ፣ገጣሚና ተርጓሚ ቤተማርያም ተሾመ ፣ጋዜጠኛና ተርጓሚ ግሩም ተበጀ፣ጋዜጠኛ ኤልዳ ግዛቸው ፣ጸሐፊና አርታኢ ቢኒያም አቡራ ይገኛሉ።

ጋዜጠኛ ናቲ ማናዬ መድረኩን የሚመራ ሲሆን አንተነህ ምናሉ (ዱንያ) በጊታር ታጅቦ መዚቃውን ያቀርባል።

ስለመጸሐፉ መረጃ ለማግኘትና ለተጨማሪ መረጃ +251928828448 እና +251912675653 መደወል ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
9
📌ባለ 300,000 ሺህ ብሩ ኮንሰርት በቤኑና ቪሌጅ

*የዳይመንድ ቀለበት ዕጣ ተዘጋጅቷል

የቤኑና ቪሌጅ የፊታችን የካቲት 14 እና 15 የሚካሄደው የቫለንታይን ዝግጅት አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል። ዝግጅቱ ለ150 ጥንዶች ብቻ የተገደበ ቢሆንም፣ የተቀመጡት የዋጋ ተመኖች ግን ብዙዎችን አስገርመዋል።

ኖር ሬድዮ ባሰባሰበው መረጃ መሠረት
ለሶስት ጥንዶች የሚሆን የ'Harmony Love 3' ጥቅል በ299,999 ብር እንዲሁም የ'Exclusive Love' ጥቅል በ199,999 ብር ለገበያ ቀርቧል።

ዝቅተኛው የ'Love Nest' ጥቅል ደግሞ...ተጨማሪውን ያንብቡ https://t.me/NorRadio1/72

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3😭31😁1🤔1
📌ትሬቨር ኖህ እና ሚያ ሞትሊ ስለህዳሴ ግድብ

በታዋቂው ኮሜዲያን እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ ትሬቨር ኖህ "What Now?" ፖድካስት ላይ የቀረቡት የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ፣ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና አጨራረስ ታሪካዊ ፋይዳ በሰጡት ምስክርነት ዓለምን አነጋግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞትሊ በቅርቡ የግድቡን ማጠናቀቅ አስመልክቶ በቦታው ተገኝተው የነበረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት የፈጸሙትን ገድል "የ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓድዋ" ሲሉ ገልጸውታል።

ትሬቨር ኖህ ግድቡ የተገነባበት የገንዘብ ምንጭ (Funding) "አስደናቂ" መሆኑን በማንሳት ያቀረበላቸው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር። “ኢትዮጵያ ግድብ ለመገንባት ለረጅም ጊዜ ስትሞክር ቆይታለች። እና ይህ ሂደት፣ ከግብፅ እና ከዓባይ ወንዝ በታች ካሉ ሌሎች ሀገራት ጋር ተያይዞ የራሱ የሆነ ፖለቲካዊ ስሜታዊነት እንደነበረው አውቃለሁ። ነገር ግን… ያደረጉት ነገር በእውነት አብዮታዊ ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የፈለገችው ለስንት ሚሊዮን ህዝብ ለሚሸፍን ክልል ኤሌክትሪክ ለማመንጨት አስፈልጓት ነው?”

ጠቅላይ ሚኒስትሯም ሲመልሱ፣ ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያውያን ...ተጨማሪውን ያንብቡ https://t.me/NorRadio1/74

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
24👍3
📌በላትቪያ ከፍተኛ የወንድ እጥረት ተከስቷል

የባልቲክ ሀገር የሆነችው ላትቪያ በአሁኑ ወቅት የወንዶች ቁጥር በእጅጉ በመቀነሱ ምክንያት ለከፋ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጋልጣለች። በተለይም በቁልፍ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ቁጥር ከወንዶች በ80,000 እንደሚበልጥ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህ በሀገሪቱ የታየው ሰፊ የጾታ ልዩነት በዋነኝነት የተከሰተው በወንዶች ላይ በሚታየው ከፍተኛ የሞት መጠን፣ በአጭር የሕይወት ዘመን የመኖር ኡደት እና ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ወጣት ወንዶች የተሻለ የሥራ ዕድል ፍለጋ ወደ ውጭ ሀገራት በመሰደዳቸው ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

ይህ አሳሳቢ ችግር በአንድ ጀምበር የተከሰተ ሳይሆን በታሪካዊ ግጭቶች እና ቀጣይነት ባላቸው የኢኮኖሚ ጫናዎች ምክንያት ለረጅም ጊዜ የተጠራቀመ ውጤት መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጥንካሬ ከማዳከሙም ባለፈ፣ ዜጎች ቤተሰብ ለመመስረትና ዘላቂ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ለመገንባት ከፍተኛ ችግር እንደሚገጥማቸው ተመራማሪዎች በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ።

©️መናኸሪያ ሬድዮ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🥰43🤔2😁1😢1
📌ሱራፌል ተካ የመኪና ስጦታውን እሁድ ይረከባል

ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ ለአርቲስት ሱራፌል ተካ ቃል የገባውን ዘመናዊ የመኪና ስጦታ የፊታችን እሁድ በደመቀ ሁኔታ እንደሚያስረክብ ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም 1 ሚሊዮን ደርሶ የነበረው የፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ የቲክቶክ ገፅ ተከታዮች ቁጥር፣ ሽልማቱ ሊሰጥ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት 52 ሺህ ተከታዮችን በድንገት በማጣት አሁን ላይ 948 ሺህ ላይ ይገኛል። ይህ ድንገተኛ የቁጥር መቀነስ በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
10👏1
📌ከነገ ጀምሮ ፌስታል ይዞ የተገኘ 5ሺ ብር ይቀጣል

የፕላስቲክ ከረጢት ስስ ፌስታልን ይዞ መገኘት የሚከለክለው አዋጅ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

ኖር ሬድዮ ባሰባሰው መረጃ መሠረት ከነገ ጥር 23 ጀምሮ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን የሚጠቀሙ፣ የሚያመርቱና ወደሀገር ውስጥ የሚያስገቡ አካላት ላይ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ተገልጿል።

ጥቁር፣ ነጭ፣ ትናንሽ እና ትልልቅ በእጅ የሚያዙ ፌስታሎች በእጅ ይዞ የተገኘ ግለሰብ፡- ከ2,000 እስከ 5,000 ብር፤ በሌላ በኩል አምራቾች፣ አከማች እና አከፋፋዮች፡- ከ50,000 እስከ 200,000 ብር ቅጣት እና እስከ አምስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ይጠብቃችኋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁1513🤔5👍2🌚1
📌በረከት ገበሬዋ ከእስር ተፈታች

በረከት ወርቁ (በረከት ገበሬዋ) ከሁለት ወራት የእስር ቤት ቆይታ በኋላ እንደተፈታች ኖር ሬድዮ ዘግቧል።

በብዙዎች ዘንድ በረከት ገበሬዋ በሚል ስያሜ የምትታወቀው ወ/ሮ በረከት ወርቁ እስር ይፋ በሆነበት ቅፅበት አንዳንዶች ''በረከት ገበሬዋ እስር ቤት የገቡት በሹፌሯ ምክንያት በተፈጠረ ቀላል ችግር ነው፣ በቅርቡ ትፈታለች'' የሚል ማረጋጊያ የሚመስል መረጃ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ሲለቁ ተስተውለው ነበር።

በወቅቱ መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ያደረገው ክትትል እንደሚያሳየው ግን ጉዳዩ ከሹፌርም ሆነ ከሌላ አካል ጋር የተገናኘ ሳይሆን ግለሰቧ በከባድ፣አመታትን በፈጀ እና ረጅም ሰንሰለት ባለው የማጭበርበር ድርጊት ላይ ተሳትፋለች በሚል ተጠርጥራ መሆኑን እንዳረጋገጠ መዘገቡ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁8👎1
የበፍያድ “የናፍቆት“ የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ተለቀቀ

የድምፃዊ በፍቃዱ ያደቴ(በፍያድ) "የናፍቆት" የተሰኘ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጮች አቀረበ።

ድምፃዊው በራሱ የዩትዮብ ቻናል እና በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በኩል አልበሙን አሰራጭቷል።

በአልበሙ ላይ በግጥምና ዜማ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ እሱባለው ይታየው (የሺ)፣ ናትናኤል ግርማቸው፣ ኤርሚያስ በዛብህ (ፓፓ)እና ሌሎችም ተሳትፈዋል።

ቅንብሩን ሚካኤል ሀይሉ (ጃኖ)፣ Small Axe፣ ክብርአብ ጣሰው እንዲሁም ማስተሪንግ ኪሩቤል ተስፋዬ እና ይትባረክ ክፍሌ ​ሰርተዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍41
📌ድምፃዊ አዲስ ጉርሜሳ "ስጦታ" የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም ለህዝብ አቀረበ

በአንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ ስራዎች ዳግም ስራው (Cover) በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ አዲስ ጉርሜሳ፣ "ስጦታ" የተሰኘ የራሱን የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጮች ማቅረቡን አስታወቀ።

ድምፃዊው ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ በሰጠው መረጃ መሰረት፣ አዲሱ አልበሙ 12 የሙዚቃ ስራዎችን በውስጡ አካቷል።

በአልበሙ ዝግጅት ላይም የሀገራችን ስመጥር የሆኑ የዜማና የግጥም ደራሲያን እንዲሁም የሙዚቃ አቀናባሪዎች በስፋት ተሳትፈውበታል።

አልበሙ በናሆም ሪከርድስ አማካኝነት ለገበያና ለአድማጮች ቀርቧል።

ድምፃዊ አዲስ ጉርሜሳ ቀደም ሲል በነበሩት የነጠላ ዜማዎቹ እና በማህሙድ አህመድ ስራዎቹ ባሳየው ልዩ የድምፅ ብቃት በአድማጮች ዘንድ ከፍተኛ ተስፋ የሚጣልበት ወጣት ድምፃዊ መሆኑ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
7
📌ድምፃዊ ሳሚ ዳን "የዘመኑ ጀግንነት ጦርነትን መጠየፍ ነው" ሲል የሰላም ጥሪ አቀረበ

ታዋቂው ድምፃዊ ሳሚ ዳን በሀገሪቱ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ የሰላም መልዕክት አስተላለፈ። ድምፃዊው አሁን ባለው ተለዋዋጭ ሁኔታ ውስጥ እውነተኛ ጀግንነት ሊለካ የሚገባው ለሰላም በሚሰጥ ዋጋ መሆኑን ገልጿል።

ሳሚ ዳን ባስተላለፈው መልዕክት፣ በተለይ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የነበረውን ግጭትና ተከታይ ጉዳቶችን በማስታወስ "የዚህ ዘመን ጀግንነት መሆን ያለበት ጦርነትን መጠየፍና ሰላምን ማስቀደም ነው" ብሏል። አክሎም "ጦርነትማ ያመጣልንን አየነው" በማለት የጦርነት ትርፍ ጥፋትና ውድመት ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🔥23👍157👏3🕊3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📌የሶማሊያ ምክር ቤት እንደራሴዎች ተደባደቡ

የሶማሊያ ምክር ቤት ጥር 20 ባደረገዉ ጉባኤዉ የሐገሪቱ ጊዜያዊ ሕገ መንግሥት እንዲሻሻል የቀረበዉ ሐሳብ የምክር ቤቱን እንደራሴዎች ለድብድብ ጋብዟል።

የሕገ መንግሥቱን መሻሻል በሚፈልጉ በገዢዉ ፓርቲና ሕገ መንግሥቱ መሻሻሉን በሚቃወሙ በተቃዋሚ እንደራሴዎች መካከል በተነሳዉ ጠብ ምክንያት ጉባኤዉ ተቋርጧል።

ሶማሊያ ከ2004 ጀምሮ ጊዚያዊ ሕገ-መንግሥት ነዉ ያላት።ከ4 ዓመት በፊት ሕገ መንግስቱን ለማሻሻል የተደረገው ተመሳሳይ ሙከራ የተኩስ ልዉዉጥ አስከትሎ ነበር።

©️DW Amharic

ለተጨማሪው: https://t.me/NorRadio1

ለተጨማሪው: https://t.me/NorRadio1

ለተጨማሪው: https://t.me/NorRadio1
😁93👍1
📌የከሸፈው የዝርፊያና እገታ ወንጀል በእንጦጦ ፓርክ

ጉዳዩ ዛሬ ጥር 23 2018 ዓ.ም የሆነ ነው ቦታው ደግሞ በሽሮ ሜዳ በኩል ወደ እንጦጦ በሚወስደው የቁስቋም አቀበት ላይ ነው። ሶስት ዘራፊና አጋች ግለሰቦች፣ ልክ እንደማንኛውም ስፖርተኛና ጎብኝ በመምሰል አሳቻ ቦታ መሽገዋል።

ዓላማቸውም ወደ ፓርኩ የሚያቀኑት የፖላንድ ዜጎች ነበሩ። ነገር ግን አሳዳጅ የሌለባቸው መስሏቸው የዘረጉት የሴራ መረብ፣ ሳይታሰብ በፖሊስ ጥብቅ ክትትል ተበጠሰ።የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው መብረቃዊ ኦፕሬሽን፣ ተጠርጣሪዎቹ ዝርፊያውን ሊፈፅሙ ሲሉ ደርሶባቸዋል።

ግለሰቦቹ ከህግ ለማምለጥ ሲሉ ገደል ገደሉን ቢወርዱም፣ ግንብና አጥር ቢዘልሉም... መጨረሻቸው ግን የብረት ካቴና ሆነ። በፈጣን ሩጫቸው መሀልም ራሳቸው ላይ ጉዳት አድርሰው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ኖር ሬድዮ እንደሰማው ከሆነ ተጠርጣሪዎቹ ከያዙት ስለታም መሳሪያ ባሻገር፣ አንደኛው ተጠርጣሪ ....ተጨማሪውን ያንብቡhttps://t.me/NorRadio1/84

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏129😁8
📌"ሃያ ሶስት" መጽሐፍ በድምቀት ተመረቀ

በዳንኤል አብርሃ እና ቢኒያም አቡራ "ሃያ ሶስት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውና ዳንኤል አብርሃ እውነተኛ የስደት ታሪኩን የተረከበት መጽሐፉ ባሳለፍነው አርብ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጽሐፍት አዳራሽ ተመርቋል።

በምረቃ ዝግጅቱ ላይ ሁለገቡ አርቲስት ተስፋዬ ማሞ፣ገጣሚና ተርጓሚ ቤተማርያም ተሾመ ፣ጋዜጠኛና ተርጓሚ ግሩም ተበጀ፣ጋዜጠኛ ኤልዳ ግዛቸው ፣ጸሐፊና አርታኢ ቢኒያም አቡራ ተገኝተዋል።

አንተነህ ምናሉ (ዱንያ) በጊታር ታጅቦ መዚቃውን አቅርቧል።መጽሐፉ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ መጽሐፍት መደብሮች ለገበያ ይቀርባል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3👍1
የገጣሚ ሰለሞን ሳህለ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

ገጣሚና ደራሲ ሰለሞን ሳህለ "በምሥራቅ በኩል" የተሰኘ ረዥም እና እውነተኛ ታሪክ ላይ ያተኮረ አዲስ መጽሐፉን ለንባብ አበቃ።

"በምሥራቅ በኩል" በሚል ርዕስ ለንባብ የበቃው ይህ መጽሐፍ፣ በእውነተኛ ታሪክ ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን፤ ደራሲው ካሳለፋቸው የጥበብ ዘውጎች ወጣ ባለ መልኩ ታሪክን እና ሰውን በጥልቀት የመረመረበት ሥራ እንደሆነ ተመላክቷል።

ሰለሞን ሳህለ ከሃሳብ ደደር፣ ከስሜት ኮስተር፣ ከእድሜ መተር ባለ ሁኔታ የሰውን ልጅ ማንነትና የታሪክ ኩነቶችን የመረመረበት ይህ አዲስ መጽሐፍ፤ በሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ጉጉትን ፈጥሯል።

በተለይ ከዚህ ቀደም ከለመድናቸው የግጥም ሥራዎቹ ባሻገር፣ አሁን የያዘው ረዥም የታሪክ ዘውግ ምን አይነት ለየት ያለ ጥበብ ይዞ መጣ የሚለው ነጥብ በብዙዎች ዘንድ ተጠባቂ ሆኗል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4👏3
📌ሔኖክ አየለ የክብር ተሸላሚ ሆነ

*የእንድሪያስ ፊልም ኮሌጅ 250 ተማሪዎችን አስመረቀ

በበርካታ የፊልም ሥራዎቹ የሚታወቀውና በዘርፉ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው ተወዳጁ የፊልም ሰው ሔኖክ አየለ፤ በዛሬው ዕለት ልዩ የክብር ተሸላሚ ሆኗል።

ይህ የክብር ሽልማት የተበረከተለት የፊልም ባለሙያዎችን በማፍራት ላይ ከሚገኘው የእንድሪያስ ፊልም ኮሌጅ ሲሆን፤ ሽልማቱም ባለሙያው ባለፉት ዓመታት ለኢትዮጵያ የፊልም ዘርፍ እድገት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽዖ እውቅና ለመስጠት የታለመ መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የፊልም ዘርፍ ውስጥ የባለሙያዎችን ክፍተት ለመሙላት ላለፉት ስምንት ዓመታት በዘርፉ ሲሰራ የቆየው እንድሪያስ ፊልም ኮሌጅ "የፊልም አሰራር ጥበብን" በደረጃ 1 እስከ 4 (ዲፕሎማ) እንዲሁም በአጫጭር ፕሮግራሞች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ከ250 በላይ ተማሪዎችን ዛሬ በድምቀት አስመርቋል።በዚህኛው ዓመት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ዮዲት ሰለሞን ተሸላሚ ሆናለች።

በዕለቱ በታዳሚው ዘንድ ትልቅ ስሜት የፈጠረው ክስተት ደግሞ፣ በቅርቡ በሞት ለተለየን የጥበብ ሰው አርቲስት ነፃነት ወርቅ የተደረገው የህሊና ጸሎት ነበር።

በዕለቱም በክብር እንግድነት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ዴዔታ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) ፣የሙዚቃ ባለሞያው ሰርፀ ፍሬስብሃት፣አርቲስት ስዩም ተፈራ፣አርቲስት ደሳለኝ ኃይሉ፣ አርቲስት ፍቃዱ ከበደ እና ሌሎችም ተገኝተዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
16👍2
📌ድምጻዊ ጆኒ ራጋ በታዳሚያን ቅሬታ ቀረበበት

ድምጻዊ ጆኒ ራጋ ጀማው ኮንሰርት ላይ ባሳየው ብቃት ከአድናቂዎቹ ቅሬታ ቀረበበት።

"ጀማው" የሙዚቃ ኮንሰርት ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት ተካሂዷል። ይሁን እንጂ ምሽቱ በደስታ ብቻ ሳይሆን በቅሬታም የታጀበ ነበር። በተለይም ድምጻዊ ጆኒ ራጋ በመድረክ ላይ ያሳየው ብቃት ብዙዎችን ቅር አሰኝቷል።

አንዳንድ ኮንሰርቱን የታደሙ ሁኔታውን ለኖር ሬድዮ ሲያብራሩ "ጆኒ እንደጠበቅነው፣ እንደናፈቅነው..ተጨማሪውን ያንብቡ https://t.me/NorRadio1/89


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😎2👎1
📌ለአንድ ሴት ሁለት ሽምግልና

ለአንዲት ወጣት ሴት ሁለት የተለያዩ
የሽምግልና ቡድኖች በተመሳሳይ ቀን የወላጆቿ ቤት መገኘታቸው መነጋገሪያ ሆነ

ኖር ሬድዮ እንዳገኘው መረጃ ከሆነ ለአንዲት ወጣት ሴት ሁለት የተለያዩ የሽምግልና ቡድኖች በተመሳሳይ ቀን የወላጆቿ ቤት በመገኘታቸው አካባቢውን መነጋገሪያ አድርገውታል።

ክስተቱ የተጀመረው ጠዋት ላይ ሲሆን፣ የመጀመሪያው የሽምግልና ቡድን በወላጆች ቤት ተገኝተው ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ወላጆችም በቀረበው ጥያቄ ተስማምተው "ልጃችንን ሰጥተናል" በማለት ቡራኬያቸውን ሰጥተዋል። እንደ ባህሉና እንደ ስርአቱ ቤተሰብ እና ሽማግሌዎች በደስታ ወደ ምግብ ገበታ ቀርበው፣ የምስራች እየተባባሉ ባሉበት ወቅት ነበር ሌላ ያልተጠበቀ ድምጽ የተሰማው...ተጨማሪ ያንብቡhttps://t.me/NorRadio1/88

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁296👍1🤔1