Event Addis Media
9.58K subscribers
6.04K photos
12 videos
4 files
4.66K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌 "ያልተመለሱ ዳናዎች" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

በደራሲ ካህሳይ አብርሃ ብስራት (አማኑኤል ማንጁስ) የተዘጋጀው «ያልተመለሱ ዳናዎች» የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ይመረቃል።

ደራሲ ካህሳይ አብርሃ ከዚህ ቀደም "የአሲምባ ፍቅር" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍54
📌አርቲስት ሰብለ ተፈራ የክብር መታሰቢያ ተደረገላት

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት እየተከበረ በሚገኘው የቤቶች ድራማ 13ኛ ዓመት ልዩ ክብረ በዓል ላይ፣ ለቀድሞዋ የድራማው ተዋናይ አርቲስት ሰብለ ተፈራ (ትርፌ) የክብርና የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዷል።

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የሚተላለፈው የቤቶች ድራማ ተዋናዮች እና የዝግጅት ክፍሉ አባላት ለአርቲስቷ የክብር አበባ አኑረዋል።

"መቼም ከውስጣችን የማትጠፋዋ" በሚል የታወሰችው አርቲስት ሰብለ ተፈራ፣ በቤቶች ድራማ ትርፌ የተሰኘችውን ገጸ ባህሪ ወክላ በብቃት መጫወቷ ይታወሳል።

አርቲስት ሰብለ ተፈራ በ2008 ዓ.ም ሕይወቷ ማለፉ አይዘነጋም።

©️ኢቢሲ ዶትስትሪም

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
26👍7🕊1
የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ቅጥር ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ፥ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ገለልተኛ የምርጫ ጣቢያ ሠራተኞችን በጊዜያዊነት ለመቅጠር እንደሚፈልግ አስታውቋል።

መስፈርቱን የምታሟሉ በሁሉም ክልሎች ላይ “በምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚነት” ማገልገል የምትፈልጉ አመልካቾች ማመልከት ትችላላችሁ ብሏል።

ማመልከቻ ቀን፦

ከታኅሣሥ19  እስከ ታኅሣሥ 28  ቀን 2018 ዓ.ም  ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት

የምልመላ መሥፈርት፦

• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦ 12ኛ እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ ቦርዱ በሚያቋቁማቸው የምርጫ ጣቢያዎች፣
• የክልሉን የስራ ቋንቋ መናገር እና መጻፍ የሚችሉ
• የሥራ ቆይታ ፦ ለ2 ወር፣
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

ለማመልከት ፦

https://nebe-election.org/recruitment ላይ ማመልከት ትችላላችሁ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

https://t.me/EventAddis1

https://t.me/EventAddis1
5👎1
📌አነጋጋሪው የኢትዮ ቴሌኮም ዋጋ ጭማሪ

ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ አገልግሎቶቹ (ፓኬጆች) ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል። ይህም ጭማሪ በተለያዩ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ እንደመሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

ከዚህ ቀደም በ400 ብር ይሸጥ የነበረው ሳምንታዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት ፓኬጅ ወደ 550 ከፍ ብሏል። ይህም በአንድ አገልግሎቱ ላይ ብቻ ከ150 ብር በላይ ጭማሪ ማለት ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ ስለ ዋጋ ጭማሪው ተከታዩን ብሏል" እየታዩ ያሉትን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች፣ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች እየጨመሩ ያሉ የካፒታልና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት መጠነኛ የታሪፍ ማስተካከያ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👎289🥰1
📌"ግጥም ሲጥም በብሔራዊ ቤተመንግስት"

"ግጥም ሲጥም" ዝግጅት በብሔራዊ ቤተመንግስት በአዲስ ሐውስ ኦፍ ካልቸር ውስጥ ታህሳስ 25 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

በዕለቱም በገጣሚ ታዴዎስ አዲሱ "አያምንምና ቀድሞም ያልካደ" መጽሐፍ ዙሪያ ልዩ መሰናዶ ተዘጋጅቷል።

የግጥም ሲጥም አዘጋጆች ስለ መጽሐፉ ጸሐፊ ተከታዩን ብለዋል " ታዴዎስ አዲሱ በ2017 “አያምንምና ቀድሞም ያልካደ” ሲል የሰየማትን የግጥም ስብስብ ስራውን ካደረሰን ወዲህ በርካታ መድረኮች ላይ ተሰጥዖውን እያካፈለ ያለ ወጣት ነው።

ታዴዎስ በኢትዮጵያ የግጥም ግጥሚያ ሻምፒዮናም ብርቱ ተፎካካሪ ሆኖ ከመቅረቡም ባሻገር በምሽቱ ብቸኛውን ሙሉ ነጥብ ማግኘት ችሎም ነበር"

የዝግጅቱ መግቢያ የግቢውን ጉብኝት ጨምሮ 300 ብር እንደሆነም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
9😁1
📌 የከተማችን ውዱ ኮንሰርት ዛሬ ምሽት ይካሄዳል

መግቢያው 25 ሺ ብር ነው

የፈረንጆች አዲስ ዓመት ሲመጣ ሁሌም ልዩ የሙዚቃ በማሰናዳት የሚታወቀው ሸራተን አዲስ ነው፡፡

ሸራተን ዘንድሮ ከአሜሪካ ታዋቂውን የአር ኤንድቢ አቀንቃኝ ትሬይ ሶንግዝን የሚያስመጣ ሲሆን አብረውትም ድምፃዊ ብዙአየሁ ደምሴና ናቲ ማን ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ አስታውቋል፡፡

ዛሬ አመሻሽ ላይ ለሚካሄደው ለዚህ ኮንሰርት ሆቴሉ ያስቀመጠው የአንድ ሰው መግቢያ 25 ሺህ ብር ነው፡፡

ይህ ክፍያ ምንም እንኳ ምግብና መጠጥን የሚያካትት ቢሆንም ካለፈው አመት ጋር ሲተያይ ግን ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣224👎3
📌ዛሬ እኩለ ሌሊት ላይ ርችት ይተኮሳል

ፈረንጆቹ ዛሬ እኩለ ሌሊት ላይ አዲስ ዓመታቸውን ይቀበላሉ። የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት (2026) መግባት ምክንያት በማድረግ፣ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ በሸራተን አዲስ ሆቴል የርችት ተኩስ እንደሚከናወን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ የርችት ዝግጅቱ ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ለ15 ደቂቃ ያህል የሚቆይ ይሆናል ተብሏል።

ህብረተሰቡ ድንገተኛ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንዳይደናገጥ እና ዝግጅቱ ለበዓል አከባበር ብቻ መሆኑን ተገንዝቦ በተለመደው ሰላማዊ ሁኔታ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣175🤔1🤡1
📌ለያየህይራድ አላመራው ቤተመጽሐፍት ተከፈተ

የግጥምና የዜማ ደራሲ፣አቀናባሪና ኢንተርፕነር ያየህ ይዕራድ አላመራው በስሙ ቤተ-መጻህፍት የተከፈተለት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ነው።

ያየህ ይራድ ከጥበብ ሰውነቱ እኩል አንባቢ እና የተለያዩ ስነ-ጽሐፎችን በመሰብሰብ የሚታወቅ ሲሆን በህይወት እያለ የሰበሰባቸው ከ5000 በላይ መጻህፍትም ለቤተ-መጻህፍቱ ተበርክቷል።

ከመጻህፍቱ ባሻገርም በተለያዩ ጊዜአት ለንባብ የበቁ መጽሔቶች እና ጋዜጦችም ለቤተ-መጻህፍት አገልግሎት በስጦታ ተበርክተዋል።

በእህቱ ሀሳብ አመነጪነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መጻህፍትና ቤተ-መዛግብት አገልግሎት ጋ በተመሰረተ ግንኙነት ስጦታዎቹም ሆኑ በስሙ የተከፈተው ቤተ-መጻህፍት እውን ሊሆን እንደቻለ ተገልጧል። በዚህም መሰረት ለንባብ እንዲሁም ለጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲውሉ ለስሙ መዘከሪያ የሚሆን አንድ ክፍል በቤተ-መጻህፍት መልክ ተደራጅቶ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

በዛሬው መርሐ-ግብር ላይም የያራድ ቤተሰቦች፣የስራ ባልደረቦች እና አድናቂዎችን ጨምሮ አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ፣ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በባህልና ስፖርት ሚኒስትር የባህልና ጥበባት ምኒስትር ዴኤታ፣የሙዚቃ ባለሙያው ሰርጸ ፍሬ ስብሐት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተገኝተዋል ሲል ብራና ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
9👏5
📌በአንዱዓለም ጎሳ እና በቀነኒ ቤተሰቦች መካከል የተጀመረው የዕርቅ ሂደት ተቋረጠ

በወጣት ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረውና በኋላም በዋስ የተፈታው ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ፣ ጉዳዩ በኦሮሞ ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት (በአባ ገዳዎች) እንዲያልቅ ጥረት ሲደረግ ቢቆይም ሂደቱ ሳይሳካ መቅረቱ ተገለጸ።

​የዕርቁ መቋረጥ ዋና ምክንያቶች፡-
የቤተሰብ ቅሬታ፡- የሟች ቀነኒ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ፣ ድምጻዊው በዋስ መፈታቱ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፣ "የልጄን ደምም ሆነ እውነት እስካሁን አላገኘንም" ብለዋል።

የሥርዓቱ አካሄድ፡- የአባ ገዳዎች ስብሰባ (ጋዲሳ) ለሦስት ጊዜያት የተካሄደ ቢሆንም፣ በአራተኛው ቀጠሮ ላይ የሟች አባት ሳይገኙ ቀርተዋል። አባ ገዳ ጎበና ሆላ እንደገለጹት፣ ቤተሰቡ ለዕርቁ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሂደቱ ተቋርጧል።

የእውነት ፍለጋ ልዩነት፡- አቶ አዱኛ "ገዳዮች ሳይለዩና ድርጊቱ ሳይታመን 'ጉማ' (የደም ካሳ) አንቀበልም" በሚል ሂደቱን ተችተዋል። አንዱዓለም በበኩሉ ድርጊቱን እንዳልፈጸመውና እውነቱ እንዲወጣ እንደሚፈልግ ለአባ ገዳዎቹ ሲገልጽ ቆይቷል።

ቤተሰቦቿ ቀናኒ በሰው እጅ እንደተገደለች ሲያምኑ፣ አንዱዓለም ግን ራሷን እንዳጠፋች በመግለጽ መከራከሩ በሁለቱ ወገኖች መካከል መግባባት እንዳይፈጠር አድርጓል።

©️Fastmereja

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😭1110👏8🤔3
📌ታዋቂው የሙዚቃ ጣቢያ MTV ስርጭት አቆመ

ለተከታታይ አራት አስርት ዓመታት የዓለምን የሙዚቃ ኢንዱስትሪና የፖፕ ባሕል (Pop Culture) ሲመራ የቆየው ታዋቂው MTV፣ የቴሌቪዥን ስርጭቱን ስለማቆሙ መረጃዎች እየወጡ ነው።

ጣቢያው በተለይም በፈረንጆቹ 1980ዎቹ እና 90ዎቹ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለዓለም በማስተዋወቅና የበርካታ ታዋቂ አርቲስቶችን ስም በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና ነበረው።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተመልካቾች ወደ ዲጂታል አማራጮች እንደ YouTube እና TikTok መዞራቸው ለጣቢያው መዳከም ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል።

የስርጭቱ መቋረጥ ምክንያቶች፡-

* የዲጂታል አማራጮች መስፋፋት፡ ተመልካቾች የሙዚቃ ቪዲዮዎችን በቴሌቪዥን ከመጠበቅ ይልቅ በማንኛውም ሰዓት በኢንተርኔት ማግኘታቸው።

* የተመልካች ቁጥር መቀነስ፡ የወጣቱ ትውልድ ትኩረት ከባህላዊ የኬብል ቴሌቪዥን ወደ ማህበራዊ ሚዲያዎችናየቀጥታ ስሬጭቶች አገልግሎቶች መሸጋገሩ።

* የይዘት ለውጥ፡ MTV ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሙዚቃ ይልቅ በሪያሊቲ ሾው (Reality Shows) ላይ ማተኮሩ የነበረውን ተቀባይነት እንዲቀንስ አድርጎታል።

MTV እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1 ቀን 1981 ስርጭቱን ሲጀምር የመጀመሪያው የቪዲዮ ሙዚቃ "Video Killed the Radio Star" እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይ ደግሞ የኢንተርኔት ዓለም በቴሌቪዥን ስርጭቱ ላይ ተመሳሳይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

ምንም እንኳን ቴሌቪዥን ስርጭቱ ቢቆምም፣ ብራንዱ በዲጂታል መድረኮች እና በተለያዩ ዝግጅቶች (እንደ MTV VMAs ሽልማት) ህልውናውን ሊቀጥል እንደሚችል ይገመታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6😭4👍1
📌በebs የቴክኖሎጂ ፕሮግራም አቅራቢ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሣ ሁለተኛ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

የሰለሞን ሙሉጌታ ካሣ አዲስ መጽሐፍ “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፦ የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ?” የተሰኘ ስያሜ እንዳለውም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የመጽሐፉ ይዘት ኤአይ ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን ከሁለት ዓመታት ጥልቅ ጥናትና የጽሁፍ ድካም በኋላ ለንባብ እንደሚቀርብም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
12👍4👏2
📌የአቢ ላቀው ሙዚቃ 100 ሚሊዮን እይታ አገኘ

ድምፃዊት አቢ ላቀው በ"የኔ ሀበሻ" በሚለው የሙዚቃ ቪዲዮዋ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛውን የዩቲዩብ የእይታ ቁጥር በማስመዝገብ ቀዳሚ ሆናለች።

​ይህ ተወዳጅ ሙዚቃዋ 100 ሚሊዮን እይታዎችን በዩቲዩብ በማስመዝገብ ታሪክ ሰርቷል። ይህም እስካሁን በዩቲዩብ ፕላትፎርም ላይ ለአንድ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቪዲዮ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

"የኔ ሀበሻ" ከተለቀቀበት ጊዜ ጀምሮ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ባሉ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሙዚቃ ሆኗል።

​አቢ ላቀው ለዚህ ታላቅ ስኬት ላበቋት አድናቂዎቿ "አመሰግናለሁ" በማለት ምስጋናዋን ገልጻለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
37👏17
📌ታላቅ የሲንፎኒ ኦኬስትር ኮንሰርት ቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመትን እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት ምሥረታ የአልማዝ ኢዩቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የስትሪንግ ኦርኬስትራ በጋራ ታላቅ ሲነፎኒ ኦኬስትራ ኮንሰርት አቀረቡ፡፡

ሲንፎኒ ስትሪንግ ኦኬስትራው ካቀረበው ኮንሰርት ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ኮንዳክተር ሰለሞን ሉሉ፤" እረኛው ባለዋሽንት" (ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ ፡አክሊሉ ዘውዴ) ‹‹የልቤ ጉዞ›› ኮንዳክተር (አማኑኤል ቡሌ ፤ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ) የአስቴር አወቀ ‹‹ጠይም ዘለግ ያለ›› ‹‹ የክቡር ዶ/ር የጥላሁን ገሠሠ ‹‹እንኳን ቆሜ ብቀበርም..›› ኮንዳክተር ዶ/ር ዕዝራ አባተ ‹‹የተነቃቃ ስሜት›› በረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ የተቀመሩ ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን የዕለቱን ሲነፎኒ ኦኬስትራ ኮንሰርት በ ረ/ፕ አክሊሉ ዘውዴ መራሒ ሙዚቃ መሪነት ቀርቧል፡፡
                                
በዕለቱ የሙዚቃ ተመራማሪና ባለሞያ የኢትዮጵያ ቤተመጽሐፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት ዋና ዳይሬክትር አቶ ሰርጸፍሬ ስብሀት እና ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ የሙዚቃ አፍቃሪያን ተገኝተዋል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
14👏2👍1
📌ዝነኛዋ ዘሪቱ ከበደ በኢትዮጵያ ቡክ ፎረም

ዘሪቱ ከበደ ስለ ልጅነቷ ፣ አስዳደግና የሕይወት መንገድ ዙሪያ በጻፈችው "ከልጅነት እስከ ልጁነት" ግለ ታሪክ መጽሐፍ ዙሪያ የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም አሰናኞችና ተሳታፊዎች እሁድ ታህሳስ 26, 2018 ከምሽቱ 2 እስከ 4 ሠዓት ድረስ ውይይት ያደርጋሉ።

የውይይቱ ሊንክ:

https://t.me/ethiopia_book_forum_official?livestream=7de0d0284be2d41c86

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6🔥2👏2😱1
📌 "ሼሙኔ" መጽሐፍ ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

በሆሄ ምዕራፍ ወርኃዊ የመጽሐፍ ዳሰሳ አዘጋጆች አዘጋጅነት በደራሲ መስፍን ወንዶሰን  "ሸሙኔ" መጽሐፍ ላይ ቅዳሜ ረፍድ ላይ  ውይይት ይካሄዳል። ይህ መርሐግብር ታህሳስ 25 ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ወመዘክር እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በውይይቱ ይኩኖአምላክ መዝገቡ እና መሠረት አበጀ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
8
📌ዝነኛዋ ብርቱካን ሚደቅሳ መጽሐፍ ጻፈች

ዝነኛው የፖለቲካ ሰው ብርቱካን ሚደቅሳ "መመለስ የቦጌ ትውስታዎቼ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ልታበቃ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏148😁8🔥1
📌የአፄ ኃይለሥላሴ ቤተሰባዊ ታሪክ ዘጋቢ ፊልም

የኢትዮጵያን የመጨረሻ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ቤተሰባዊ ታሪክ የሚዘክረው "Grandpa Was an Emperor" የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም በዓድዋ ድል መታሰቢያ መታየት ጀመረ፡፡

ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት የሳበው ፊልም፤ የሚያተኩረው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ በሆኑት በልዕልት የሺ ካሳ የግል የሕይወት ታሪክ ላይ ነው።

ፊልሙ በቤተመንግስት ውስጥ የነበረውን የልጅነት የቅንጦት ሕይወት፣ በድንገት የተቀየረበትን የ1966ቱን አብዮት፣ እንዲሁም የቅርብ ቤተሰቦቿ ለዓመታት በእስርና በስደት ያሳለፉትን መራራ ታሪክ በዝርዝር ይተርካል።

ዘጋቢ ፊልሙን ከሌሎቹ የታሪክ ስራዎች ለየት የሚያደርገው፤ ከዚህ ቀደም ለሕዝብ እይታ ያልበቁና በንጉሣዊው ቤተሰብ የግል ካሜራዎች የተቀረጹ ያልታዩ የቪዲዮ ምስሎችንና ፎቶግራፎችን አካቶ መያዙ ነው ተብሏል።

የታዋቂዋ ሲኒማቶግራፈር ኮንስታንስ ማርክስ ስራ የሆነው ይህ ፊልም፤ በታዋቂዋ ድምፃዊትና ተዋናይት ሲንቲያ ኤሪቮ (Cynthia Erivo) አዘጋጅነት (Executive Producer) ለዕይታ የበቃ ነው።

ፊልሙ በፓን አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ የ"Joel Siegel Documentary Award" ሽልማትን ማሸነፉ ይታወሳል።በአሁኑ ወቅት በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኙት ሲኒማዎች ለእይታ ቀርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
23👏4🙏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌ድምጻዊ ናቲ ኃይሌ መድረክ ላይ ግጥም ጠፋበት

ድምጻዊ ናቲ ኃይሌ ከዓመታት በኃላ ትላንትና አመሻሽ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ከሳምቮድ እና ሔኖክ አበበ ጋር በጋራ የሙዚቃ ኮንሰርቱን አቅርቦ ነበር።

በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ናቲ ኃይሌ የአንጋፋውን ድምጻዊ ንዋይ  ደበበ "ሀገሬን አልረሳም" የተሰኘውን ሙዚቃ መድረክ ላይ በሚያቀርብበት ወቅት ግጥም ሲጠፋበት ታይቷል።

ኤቨንት አዲስ ሚዲያ እንደታዘበው ከሆነ ይህም አጋጣሚ በተለያዩ ሰዎች ዘንድ መነጋገሪያ አድርጓታል። ለምን ግጥሙን በሥርዓቱ አጥንቶ አይዘፍንም? የሚሉ ጥያቄዎች እንዲሁም ያልተዘጋጀበትን በአግባቡ ያላጠናውን ዘፈን ባይዘፈን መልካም ነው  የሚሉ አስተያቶችም ተሰምተዋል።

📸ቪዲዮውን ይመልከቱ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁515👎1🤔1🌚1👀1
📌የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ከኃላፊነት ተነሱ

ከተሾሙ 12ተኛ ወራቸውን የያዙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን(ዶ/ር) ከኋላፊነታቸው ተነሱ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን የሚያቋቁመው አዋጅ የባለስጣኑ ዋና ዳይሬክተር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሾም ይደነግጋል።

በዚሁ መሠረትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ታኅሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ በላኩት ደብዳቤ አቶ ሳምሶንን የሚተኩ ዕጩ ተሿሚ ማቅረባቸውን ሪፖርተር አረጋግጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ በላኩት ደብዳቤም፣ "ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀ ወርቅነህ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ እንዲሾሙ እጠይቃለሁ" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ በሥራ ላይ የሚገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) ከኋላፊነት የተነሱበትን ምክንያት አይገልጽም።

ወ/ሮ ሐይማኖት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽፈት ቤት በም/ቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሀላፊ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ደግሞ በመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በዳይሬክተርነት ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በከፍተኛ አዘጋጅነት ያገለገሉ ናቸው።

©️ሪፖርተር ጋዜጣ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3🙉3
📌በላሊበላ የእንግዶች ቁጥር መቀነሱ ተነገረ

የገና በዓልን ለማክበር ላሊበለ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት  የሚያደርጉ ባለሆቴሎች፣ የእንግዶች ቁጥር መቀነስ እንዳሳሰባቸው ተናገሩ፡፡የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ግን ከ12 ሺሕ በላይ ቱሪስቶች መግባታቸውን ገልጿል፡፡

ከኮሮና ወረርሽኝ ቀጥሎ በነበረው የሰሜኑ ጦርነትና በአሁኑም ወቅት በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ባለው ግጭት ወደ ከተማዋ የሚገቡ የውጭ አገር ጎብኝዎች ቁጥር በመቀነሱ፣ ለሠራተኞች ደመወዝ መክፈል እንዳልቻሉና ያለባቸውን የባንክ ዕዳ ለመክፈል መቸገራቸውን፣ ዘንድሮ ግን ይህ ሁኔታ ካልተለወጠ ለበለጠ ችግር እንደሚዳረጉ በላሊበላ ከተማ የሚገኙ የሆቴልና የሎጅ ባለቤቶች ለሪፖርተር ተናግረዋል።

አንዳንድ የሆቴል ባለቤቶች እንዳሉት ኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱ በፊት ከስድስት ወር በፊት የመኝታ ክፍሎቻቸውን ለቱሪስት አስይዘው ይጨርሱ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ግን በዓሉ ቀናት ቢቀሩትም ምንም ዓይነት እንግዳ አለመቀበላቸውን አስረድተዋል ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4🕊3🙏1
📌ለአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር መንገዶች ይዘጋሉ 

በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ  የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

መርሀ ግብሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅም፡- 
👉 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ  የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ
👉 ከቦሌ በጌቱ ኮሜርሻል  ወደ መስቀል  አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ወይም ደንበል አካባቢ 
👉 ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል የሚወስደው መንገድ በተለምዶ ጋዜቦ አደባባይ
👉 ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪዎች  አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ፤ ለቀላል ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ
👉 ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ  ለገሃር መብራት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያ መስቀለኛ
👉 ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ  ለገሃር መብራት
👉 ከአምባሳደር  መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት
👉 ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ- መንግሥት  የሚወስዱ መንገዶች ከታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ መርሀ ግብሩ እስኪጠናቀቅ ለተሽከርካሪ የሚዘጉ ሲሆን ከዛሬ ታህሳስ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በሚዘጉ መንገዶች ላይ ለረጅም ሆነ ለአጭር ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍1310🕊1