Event Addis Media
9.6K subscribers
6.05K photos
12 videos
4 files
4.67K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌በስንቱ ድራማ የኢቤኤስ ቆይታው ተጠናቀቀ

ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የነበረው ተወዳጁ በስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ፕሮዲዩሰር የሆነው አብሪኮም መልቲሚዲያ፤ ከጣቢያው ጋር የነበረውን የሥራ ውል ማጠናቀቁን መልቲሚዲያው አሳውቋል።

አብሪኮም መልቲሚዲያ ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር የነበረው የሥራ ቆይታ መጠናቀቁን ተከትሎ፤ ተወዳጁ በስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ድራማ ከታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን እንደማይተላለፍ እና በበስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ዙሪያ የሚኖሩ ተጨማሪ መረጃዎችን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ መልቲሚዲያው ገልጿል።

ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር ሰላማዊ እና ጥሩ የሥራ ቆይታ እንደነበራቸው የገለጸው አብሪኮም፤ ለጣቢያው ባለቤቶች እና ሠራተኞች የቀና ምሥጋና አቅርበዋል።

©️ይትባረክ ዋለልኝ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢197👍5🔥3👏3
📌ደራሲ አዳም ረታን በአካል የምታገኙበት እድል

ደራሲ አዳም ረታን በአካል የምታገኙበት እድል በጃፋር መጽሐፍት መደብር በኩል ተዘጋጅቷል።

ደራሲ አዳም ረታ ከነገ በስቲያ ሐሙስ ታህሥሣ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በአዲሱ የጃዕፋር መፅሐፍት መደብር የመጽሐፍት የፊርማ ሥነሥርዓት ያከናውናል።

በተጨማሪም ከአድናቂዎቹ ጋር ስለ ስራዎች በተናጥል ይጨዋወታል። የፎቶግራፍ መርሐግብርም እንደሚያካሂድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
37🔥10
📌ደራሲ አዳም ረታን የምታገኙት ዛሬ ነው

ደራሲ አዳም ረታን በአካል የምታገኙበት እድል !

ደራሲ አዳም ረታን በአካል የምታገኙበት እድል በጃፋር መጽሐፍት መደብር በኩል ተዘጋጅቷል።

ደራሲ አዳም ረታ ዛሬ ሐሙስ ታህሥሣ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በአዲሱ የጃዕፋር መፅሐፍት መደብር የመጽሐፍት የፊርማ ሥነሥርዓት ያከናውናል።

በተጨማሪም ከአድናቂዎቹ ጋር ስለ ስራዎች በተናጥል ይጨዋወታል። የፎቶግራፍ መርሐግብርም እንደሚያካሂድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
11👍8
📌የአእላፋት ሳምንት አውደርዕይ ዛሬ ይጀምራል

የመጀመሪያው የአእላፋት ሳምንት አውደርዕይ እና ፎረም ዛሬ አርብ ታህሥሣ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 በጊዮን ሆቴል ግራውንድስ በይፋ ይጀምራል።

ከታህሣሥ 18 እስከ ታህሣሥ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከጠዋት 4:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 2፡00 ሰዓት ድረስ ዐውደ ርዕዩ ለምዕመናን በአጠቃላይ ክፍት ይሆናል፡፡

ሃይማኖታዊ ትምህርቶች ይሰጣሉ፣መጽሐፍት ይመረቃሉ፣ጥናታዊ ፅሁፎችም ይቀርባሉ፡፡

በኢትዮጵያ ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማህበር የሚዘጋጀው ይሄ ዝግጅት በግዮን ሆቴል ግራውንድስ ይደረጋል።

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በአዲስ አበባና በድሬደዋ ከተማ የሚያዘጋጀው የ2018 የ3ኛው የአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር ታህሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይና በድሬ ለገሀር አደባባይከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ማህበሩ አስታውሷል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏118👍2
"ዳንቴል" የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ስራ ጀመረ

በዳንቴል ሶፍትዌር ኃ.የተ.የግ.ማኀበር የተዘጋጀው "ዳንቴል" የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ስራ ጀምሯል።

"ዳንቴል" መተግበሪያ ተጠቃሚዎች በመተግበሪያው ላይ የሚገኙ ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው እንደ ቴሌግራም፣ ፌስቡክና ቲክቶክ በማጋራትና ሽያጭ እንዲከናወን በማድረግ የኮሚሽን ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

ይህ አሰራር በተለይ የስራ ልምድ ያላቸው ነገር ግን ወደ ስራው ዓለም ለመግባት በካፒታል እጥረት ለተቸገሩ ወጣቶች እንደ ትልቅ ድልድይ ያገለግላል ተብሏል።

መተግበሪያው ተጠቃሚዎች የትኛውን ምርት፣ በምን አይነት የገበያ ሁኔታ እና በምን ያህል ካፒታል መጀመር እንዳለባቸው የሚያማክር የራሱ የሆነ የAI ስርዓት እንዳለውም ተገልጿል።

ይህም አምራቾችና ነጋዴዎች የገበያ ፍላጎትን ተረድተው ምርታቸውን በብቃት እንዲያቀርቡ ይረዳቸዋል።

ዳንቴል ከአምራቾች እስከ ሸማቾች ያለውን ሰንሰለት ለማሳለጥ ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

ይህም ተጠቃሚዎች የሚያዝዟቸው ምርቶች ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲደርሷቸውና የት ደረጃ ላይ እንዳሉ እንዲከታተሉ  ያስችላቸዋል።

በተጨማሪም ድርጅቱ የደንበኞችን እምነት ለመጠበቅ "ምርቱ ካልተመቸ የመመለስ መብት" (Return Policy) ከአቅራቢዎች ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5👍1
📌"ቀለም" ዲጂታል መጽሔት ንባብ በቃ

ቀለም ዲጂታል መጽሔት ቅፅ 1/ ዕትም 6 ለአንባቢያን ቀርቧል።ለተከታታይ 6 ወራት በቴሌግራም ቻናል የተለያዩ ዓምዶችን አካቶ ለንባብ የበቃው ቀለም መጽሔት ስድስተኛ ዕትም ከሰሞኑ ንባብ በቅቷል።

ቀለም ዲጂታል መጽሔት በዚህ ዕትሙ ስለ ሠዓሊ እና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ታሪክ አንስቶ፣ በግጥም ተውቦ ከወጉ አካቶ በስነ-ጽሑፍ ቀለሞች አሸብርቋል።

በነፃ ያንብቡ:-

https://t.me/kelemofficial
👍72🙏2
📌የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 75ኛ ዓመት ክብረበዓል

75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፥ የቀድሞ ምሩቃንና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የቤተሰብ ቀንን ከነገ ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ያከብራል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 75ኛ የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን ከባለፈው ወር ጀምሮ በተለያዩ ፕሮግራሞች በማክበር ላይ ይገኛል።

የቀድሞ ተማሪዎች ሳምንት ከታህሳስ 18-24/2018 ዓ.ም እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

የቀድሞ ተማሪዎች እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቤተሰቦች በበዓሉ ማክበሪያ ሳምንት ታህሳስ 18-19/2018 ዓ.ም በ6 ኪሎ ዋናው ግቢ እና ከታህሳስ 20-24/2018 ዓ.ም በሁሉም ካምፓሶች በመገኘት እንዲያከብሩ ጥሪ አድርጓል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"ጊዜን መሸከም" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

በገጣሚ ዘውዱ አለልኝ የተዘጋጀው "ጊዜን መሸከም" መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ ታህሣሥ 18 ቀን ከቀኑ 10:00 ጀምሮ 24 አካባቢ በሚገኘው መሶብ የሙዚቃ ማዕከል ውስጥ ይመረቃል።

"ጊዜን መሸከም" መጽሐፍ 54 ግጥሞችን የያዘ ሲሆን  በ162 ገጽ የተቀነበበ ነው። የመጽሐፉ ቅርጽ በዋሽንት አውታረ ቅኝት የተሠራ ሆኖ በጥቁር፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ እና ነጭ ቀለማት የተከፋፈለ ነው። 

ቀለማቱ ከኢትዮጵያ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች  ዋሽንት፣ ክራር፣ ነጋሪት እና ሞረሽ ከምትባል ወፍ ጋር የተቀነባበረ ነው ተብሏል።

እያንዳዱ ክፍል ቀለማዊ እና ሙዚቃዊ ፍካሬ መግቢያ አለው። እንዲሁም ግላዊ መግቢያ እና ድኅረ ቃል በመጽሐፉ ውስጥ ተካቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1
📌 "ያልተመለሱ ዳናዎች" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

በደራሲ ካህሳይ አብርሃ ብስራት (አማኑኤል ማንጁስ) የተዘጋጀው «ያልተመለሱ ዳናዎች» የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ይመረቃል።

ደራሲ ካህሳይ አብርሃ ከዚህ ቀደም "የአሲምባ ፍቅር" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍54
📌አርቲስት ሰብለ ተፈራ የክብር መታሰቢያ ተደረገላት

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት እየተከበረ በሚገኘው የቤቶች ድራማ 13ኛ ዓመት ልዩ ክብረ በዓል ላይ፣ ለቀድሞዋ የድራማው ተዋናይ አርቲስት ሰብለ ተፈራ (ትርፌ) የክብርና የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዷል።

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የሚተላለፈው የቤቶች ድራማ ተዋናዮች እና የዝግጅት ክፍሉ አባላት ለአርቲስቷ የክብር አበባ አኑረዋል።

"መቼም ከውስጣችን የማትጠፋዋ" በሚል የታወሰችው አርቲስት ሰብለ ተፈራ፣ በቤቶች ድራማ ትርፌ የተሰኘችውን ገጸ ባህሪ ወክላ በብቃት መጫወቷ ይታወሳል።

አርቲስት ሰብለ ተፈራ በ2008 ዓ.ም ሕይወቷ ማለፉ አይዘነጋም።

©️ኢቢሲ ዶትስትሪም

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
26👍7🕊1
የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ቅጥር ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ፥ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ገለልተኛ የምርጫ ጣቢያ ሠራተኞችን በጊዜያዊነት ለመቅጠር እንደሚፈልግ አስታውቋል።

መስፈርቱን የምታሟሉ በሁሉም ክልሎች ላይ “በምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚነት” ማገልገል የምትፈልጉ አመልካቾች ማመልከት ትችላላችሁ ብሏል።

ማመልከቻ ቀን፦

ከታኅሣሥ19  እስከ ታኅሣሥ 28  ቀን 2018 ዓ.ም  ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት

የምልመላ መሥፈርት፦

• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦ 12ኛ እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ ቦርዱ በሚያቋቁማቸው የምርጫ ጣቢያዎች፣
• የክልሉን የስራ ቋንቋ መናገር እና መጻፍ የሚችሉ
• የሥራ ቆይታ ፦ ለ2 ወር፣
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

ለማመልከት ፦

https://nebe-election.org/recruitment ላይ ማመልከት ትችላላችሁ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

https://t.me/EventAddis1

https://t.me/EventAddis1
5👎1
📌አነጋጋሪው የኢትዮ ቴሌኮም ዋጋ ጭማሪ

ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ አገልግሎቶቹ (ፓኬጆች) ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል። ይህም ጭማሪ በተለያዩ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ እንደመሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

ከዚህ ቀደም በ400 ብር ይሸጥ የነበረው ሳምንታዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት ፓኬጅ ወደ 550 ከፍ ብሏል። ይህም በአንድ አገልግሎቱ ላይ ብቻ ከ150 ብር በላይ ጭማሪ ማለት ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ ስለ ዋጋ ጭማሪው ተከታዩን ብሏል" እየታዩ ያሉትን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች፣ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች እየጨመሩ ያሉ የካፒታልና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት መጠነኛ የታሪፍ ማስተካከያ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👎289🥰1
📌"ግጥም ሲጥም በብሔራዊ ቤተመንግስት"

"ግጥም ሲጥም" ዝግጅት በብሔራዊ ቤተመንግስት በአዲስ ሐውስ ኦፍ ካልቸር ውስጥ ታህሳስ 25 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

በዕለቱም በገጣሚ ታዴዎስ አዲሱ "አያምንምና ቀድሞም ያልካደ" መጽሐፍ ዙሪያ ልዩ መሰናዶ ተዘጋጅቷል።

የግጥም ሲጥም አዘጋጆች ስለ መጽሐፉ ጸሐፊ ተከታዩን ብለዋል " ታዴዎስ አዲሱ በ2017 “አያምንምና ቀድሞም ያልካደ” ሲል የሰየማትን የግጥም ስብስብ ስራውን ካደረሰን ወዲህ በርካታ መድረኮች ላይ ተሰጥዖውን እያካፈለ ያለ ወጣት ነው።

ታዴዎስ በኢትዮጵያ የግጥም ግጥሚያ ሻምፒዮናም ብርቱ ተፎካካሪ ሆኖ ከመቅረቡም ባሻገር በምሽቱ ብቸኛውን ሙሉ ነጥብ ማግኘት ችሎም ነበር"

የዝግጅቱ መግቢያ የግቢውን ጉብኝት ጨምሮ 300 ብር እንደሆነም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
9😁1
📌 የከተማችን ውዱ ኮንሰርት ዛሬ ምሽት ይካሄዳል

መግቢያው 25 ሺ ብር ነው

የፈረንጆች አዲስ ዓመት ሲመጣ ሁሌም ልዩ የሙዚቃ በማሰናዳት የሚታወቀው ሸራተን አዲስ ነው፡፡

ሸራተን ዘንድሮ ከአሜሪካ ታዋቂውን የአር ኤንድቢ አቀንቃኝ ትሬይ ሶንግዝን የሚያስመጣ ሲሆን አብረውትም ድምፃዊ ብዙአየሁ ደምሴና ናቲ ማን ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ አስታውቋል፡፡

ዛሬ አመሻሽ ላይ ለሚካሄደው ለዚህ ኮንሰርት ሆቴሉ ያስቀመጠው የአንድ ሰው መግቢያ 25 ሺህ ብር ነው፡፡

ይህ ክፍያ ምንም እንኳ ምግብና መጠጥን የሚያካትት ቢሆንም ካለፈው አመት ጋር ሲተያይ ግን ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣224👎3
📌ዛሬ እኩለ ሌሊት ላይ ርችት ይተኮሳል

ፈረንጆቹ ዛሬ እኩለ ሌሊት ላይ አዲስ ዓመታቸውን ይቀበላሉ። የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት (2026) መግባት ምክንያት በማድረግ፣ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ በሸራተን አዲስ ሆቴል የርችት ተኩስ እንደሚከናወን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ የርችት ዝግጅቱ ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ለ15 ደቂቃ ያህል የሚቆይ ይሆናል ተብሏል።

ህብረተሰቡ ድንገተኛ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንዳይደናገጥ እና ዝግጅቱ ለበዓል አከባበር ብቻ መሆኑን ተገንዝቦ በተለመደው ሰላማዊ ሁኔታ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣175🤔1🤡1
📌ለያየህይራድ አላመራው ቤተመጽሐፍት ተከፈተ

የግጥምና የዜማ ደራሲ፣አቀናባሪና ኢንተርፕነር ያየህ ይዕራድ አላመራው በስሙ ቤተ-መጻህፍት የተከፈተለት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ነው።

ያየህ ይራድ ከጥበብ ሰውነቱ እኩል አንባቢ እና የተለያዩ ስነ-ጽሐፎችን በመሰብሰብ የሚታወቅ ሲሆን በህይወት እያለ የሰበሰባቸው ከ5000 በላይ መጻህፍትም ለቤተ-መጻህፍቱ ተበርክቷል።

ከመጻህፍቱ ባሻገርም በተለያዩ ጊዜአት ለንባብ የበቁ መጽሔቶች እና ጋዜጦችም ለቤተ-መጻህፍት አገልግሎት በስጦታ ተበርክተዋል።

በእህቱ ሀሳብ አመነጪነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መጻህፍትና ቤተ-መዛግብት አገልግሎት ጋ በተመሰረተ ግንኙነት ስጦታዎቹም ሆኑ በስሙ የተከፈተው ቤተ-መጻህፍት እውን ሊሆን እንደቻለ ተገልጧል። በዚህም መሰረት ለንባብ እንዲሁም ለጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲውሉ ለስሙ መዘከሪያ የሚሆን አንድ ክፍል በቤተ-መጻህፍት መልክ ተደራጅቶ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

በዛሬው መርሐ-ግብር ላይም የያራድ ቤተሰቦች፣የስራ ባልደረቦች እና አድናቂዎችን ጨምሮ አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ፣ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በባህልና ስፖርት ሚኒስትር የባህልና ጥበባት ምኒስትር ዴኤታ፣የሙዚቃ ባለሙያው ሰርጸ ፍሬ ስብሐት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተገኝተዋል ሲል ብራና ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
9👏5
📌በአንዱዓለም ጎሳ እና በቀነኒ ቤተሰቦች መካከል የተጀመረው የዕርቅ ሂደት ተቋረጠ

በወጣት ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረውና በኋላም በዋስ የተፈታው ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ፣ ጉዳዩ በኦሮሞ ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት (በአባ ገዳዎች) እንዲያልቅ ጥረት ሲደረግ ቢቆይም ሂደቱ ሳይሳካ መቅረቱ ተገለጸ።

​የዕርቁ መቋረጥ ዋና ምክንያቶች፡-
የቤተሰብ ቅሬታ፡- የሟች ቀነኒ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ፣ ድምጻዊው በዋስ መፈታቱ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፣ "የልጄን ደምም ሆነ እውነት እስካሁን አላገኘንም" ብለዋል።

የሥርዓቱ አካሄድ፡- የአባ ገዳዎች ስብሰባ (ጋዲሳ) ለሦስት ጊዜያት የተካሄደ ቢሆንም፣ በአራተኛው ቀጠሮ ላይ የሟች አባት ሳይገኙ ቀርተዋል። አባ ገዳ ጎበና ሆላ እንደገለጹት፣ ቤተሰቡ ለዕርቁ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሂደቱ ተቋርጧል።

የእውነት ፍለጋ ልዩነት፡- አቶ አዱኛ "ገዳዮች ሳይለዩና ድርጊቱ ሳይታመን 'ጉማ' (የደም ካሳ) አንቀበልም" በሚል ሂደቱን ተችተዋል። አንዱዓለም በበኩሉ ድርጊቱን እንዳልፈጸመውና እውነቱ እንዲወጣ እንደሚፈልግ ለአባ ገዳዎቹ ሲገልጽ ቆይቷል።

ቤተሰቦቿ ቀናኒ በሰው እጅ እንደተገደለች ሲያምኑ፣ አንዱዓለም ግን ራሷን እንዳጠፋች በመግለጽ መከራከሩ በሁለቱ ወገኖች መካከል መግባባት እንዳይፈጠር አድርጓል።

©️Fastmereja

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😭1110👏8🤔3
📌ታዋቂው የሙዚቃ ጣቢያ MTV ስርጭት አቆመ

ለተከታታይ አራት አስርት ዓመታት የዓለምን የሙዚቃ ኢንዱስትሪና የፖፕ ባሕል (Pop Culture) ሲመራ የቆየው ታዋቂው MTV፣ የቴሌቪዥን ስርጭቱን ስለማቆሙ መረጃዎች እየወጡ ነው።

ጣቢያው በተለይም በፈረንጆቹ 1980ዎቹ እና 90ዎቹ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለዓለም በማስተዋወቅና የበርካታ ታዋቂ አርቲስቶችን ስም በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና ነበረው።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተመልካቾች ወደ ዲጂታል አማራጮች እንደ YouTube እና TikTok መዞራቸው ለጣቢያው መዳከም ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል።

የስርጭቱ መቋረጥ ምክንያቶች፡-

* የዲጂታል አማራጮች መስፋፋት፡ ተመልካቾች የሙዚቃ ቪዲዮዎችን በቴሌቪዥን ከመጠበቅ ይልቅ በማንኛውም ሰዓት በኢንተርኔት ማግኘታቸው።

* የተመልካች ቁጥር መቀነስ፡ የወጣቱ ትውልድ ትኩረት ከባህላዊ የኬብል ቴሌቪዥን ወደ ማህበራዊ ሚዲያዎችናየቀጥታ ስሬጭቶች አገልግሎቶች መሸጋገሩ።

* የይዘት ለውጥ፡ MTV ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሙዚቃ ይልቅ በሪያሊቲ ሾው (Reality Shows) ላይ ማተኮሩ የነበረውን ተቀባይነት እንዲቀንስ አድርጎታል።

MTV እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1 ቀን 1981 ስርጭቱን ሲጀምር የመጀመሪያው የቪዲዮ ሙዚቃ "Video Killed the Radio Star" እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይ ደግሞ የኢንተርኔት ዓለም በቴሌቪዥን ስርጭቱ ላይ ተመሳሳይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

ምንም እንኳን ቴሌቪዥን ስርጭቱ ቢቆምም፣ ብራንዱ በዲጂታል መድረኮች እና በተለያዩ ዝግጅቶች (እንደ MTV VMAs ሽልማት) ህልውናውን ሊቀጥል እንደሚችል ይገመታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6😭4👍1
📌በebs የቴክኖሎጂ ፕሮግራም አቅራቢ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሣ ሁለተኛ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

የሰለሞን ሙሉጌታ ካሣ አዲስ መጽሐፍ “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፦ የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ?” የተሰኘ ስያሜ እንዳለውም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የመጽሐፉ ይዘት ኤአይ ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን ከሁለት ዓመታት ጥልቅ ጥናትና የጽሁፍ ድካም በኋላ ለንባብ እንደሚቀርብም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
12👍4👏2
📌የአቢ ላቀው ሙዚቃ 100 ሚሊዮን እይታ አገኘ

ድምፃዊት አቢ ላቀው በ"የኔ ሀበሻ" በሚለው የሙዚቃ ቪዲዮዋ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛውን የዩቲዩብ የእይታ ቁጥር በማስመዝገብ ቀዳሚ ሆናለች።

​ይህ ተወዳጅ ሙዚቃዋ 100 ሚሊዮን እይታዎችን በዩቲዩብ በማስመዝገብ ታሪክ ሰርቷል። ይህም እስካሁን በዩቲዩብ ፕላትፎርም ላይ ለአንድ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቪዲዮ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

"የኔ ሀበሻ" ከተለቀቀበት ጊዜ ጀምሮ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ባሉ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሙዚቃ ሆኗል።

​አቢ ላቀው ለዚህ ታላቅ ስኬት ላበቋት አድናቂዎቿ "አመሰግናለሁ" በማለት ምስጋናዋን ገልጻለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
37👏17
📌ታላቅ የሲንፎኒ ኦኬስትር ኮንሰርት ቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመትን እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት ምሥረታ የአልማዝ ኢዩቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የስትሪንግ ኦርኬስትራ በጋራ ታላቅ ሲነፎኒ ኦኬስትራ ኮንሰርት አቀረቡ፡፡

ሲንፎኒ ስትሪንግ ኦኬስትራው ካቀረበው ኮንሰርት ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ኮንዳክተር ሰለሞን ሉሉ፤" እረኛው ባለዋሽንት" (ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ ፡አክሊሉ ዘውዴ) ‹‹የልቤ ጉዞ›› ኮንዳክተር (አማኑኤል ቡሌ ፤ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ) የአስቴር አወቀ ‹‹ጠይም ዘለግ ያለ›› ‹‹ የክቡር ዶ/ር የጥላሁን ገሠሠ ‹‹እንኳን ቆሜ ብቀበርም..›› ኮንዳክተር ዶ/ር ዕዝራ አባተ ‹‹የተነቃቃ ስሜት›› በረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ የተቀመሩ ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን የዕለቱን ሲነፎኒ ኦኬስትራ ኮንሰርት በ ረ/ፕ አክሊሉ ዘውዴ መራሒ ሙዚቃ መሪነት ቀርቧል፡፡
                                
በዕለቱ የሙዚቃ ተመራማሪና ባለሞያ የኢትዮጵያ ቤተመጽሐፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት ዋና ዳይሬክትር አቶ ሰርጸፍሬ ስብሀት እና ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ የሙዚቃ አፍቃሪያን ተገኝተዋል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
14👏2👍1