Event Addis Media
9.59K subscribers
6.04K photos
12 videos
4 files
4.67K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌አሜሪካ የ”ዲቪ” ሎተሪ እድልን አገደች!

የዩናይትድ ስቴትስ ብራውን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከተፈጸመ የተኩስ እሩምታ ግድያ በኋላ የ”ዲቪ” ሎተሪ እድልን ማገዷን አሳወቀች።

የሀገሪቱ የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ኃላፊ ክሪስቲ ኖዬም በብራውን ዩኒቨርሲቲ የተኩስ እሩምታ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ “አሁን በተቋረጠው የዲቪ መርኀ-ግብር ተጠቃሚ ከሆነ አገር የመጣ ነው” ብለዋል።

ለኃላፊዋ የዲቪ ሎተሪ እድል መርኀ-ግብሩን እንዲያቋርጡ “አቋርጪ” ሲሉ ትናንት ሐሙስ ታኅሣሥ 9 /2018 ዓ.ም ማምሻውን ትእዛዝ ያስተላለፉላት የአገሪቱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ብሏል ዶቸቬለ በዘገባው።

የዲቪ ሎተሪ መርኀ-ግብር በየዓመቱ 50,000 ፍልሰተኞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲገቡ የሚያስችል እድል እንደነበር ነው የተገለፀ ሲሆን በዚህ እድል በርካታ ኢትዮጵያውያንም ተጠቃሚ እንደነበሩ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
7🤔2
📌ተጠባቂው "ከርቤ" ፊልም ተለቀቀ

በሂስትሪ ፊልም ካምፓኒ ተሰርቶ የቀረበው "ከርቤ" ፊልም በNahom_Multimedia ዩቲዩብ ቻናል በኩል ተለቀቀ።

ፊልሙን ለመመልከት ይኸው ሊንክ:https://youtu.be/CWE3vgB29uE?si=IgA67qcgs5Kp2HYD

ከርቤ ፊልም ጭብጡን በጓደኛው ታላቅ በደልና ታላቅ ውለታ መሃል ገብቶ የተወጠረው አባት ነገሮችን ለመፍታት በሚከፍለው መስዋትነት እና በቀረው ቤተሰብ መካከል የተፈጠረውን ክስተት የሚያሳይ ልብ አንጠለጣይ ፊልም ነው።

በስዩም በላይ Produced የተደረገ ሲሆን ፊልሙን ዳይይሬክት ያደረገው አለባቸው አራጌ፣ ሲኒማቶግራፊውን  ዳንኤል ግርማ፣  በትወና ደግሞ በሄኖክ ወንድሙ፣ መዓዛ ገ/ሕይወት ፣ የአብሥራ ታደሠ፣ ከድር ሁሴን፣ ይሁኔ ምንዋጋው፣ ሰርካለም ደምሴና ሌሎችም ተሳትፈውበታል፡፡
8🔥1
📌የተደለዙ ገጾች መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል

በጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደዮሐንስ የተዘጋጀው "የተደለዙ ገጾች " መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።

የተደለዙ ገጾች ዐሥር አጫጭር እውነተኛ ታሪኮችን የያዘ መፅሐፍ ነው። ትኩረት የተነፈጉ ቁም ነገሮች፣ እንደዋዛ የታለፉ ውልብታዎች፣ የተኖሩ የሕይወት ገጽታዎች ናቸው።

ዐጭር ቢሆኑም በዝርዝር የሚታወሱን፣ ፈገግ የሚያደርጉን፣ የሚያሳዝኑን፣ የሚወቅሱን ግን ዘንግተን ያለፍናቸው የታሪካችን አካል ናቸው።

መጽሐፉ በጃዕፋርና ክብሩ መፅሐፍት መደብር ይገኛል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5👍2
📌የመጀመሪያዋ ሴት የረዥም ልቦለድ ደራሲ ፀሐይ መልአኩ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የደራሲዋ አዲስ መጽሐፍ ርዕስ "ዘባሲል" ይሰኛል።

"ዘባሲል” መጽሐፍ በ399 ገፆች የተቀነበበ ታሪክ ለበስ ልብ ወለድ ነው።

መፅሐፉ ዛሬ  ቅዳሜ ታኅሣሥ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትያና ቤተመጻፍት አገልግሎት (ወመዘክር( አዳራሽ ይመረቃል።

“ዘባሲል” መፅሐፍ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ደምና አጥንት ተከፍሎባት የተረከባትን ሃገር ባለአደራ ሆኖ ለቀጣዩ ትውልድ እንዴት ማስተላለፍ እንዳለበት እንደሚጠቁም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
7🙏6👍2
📌ትውልደ ኢትዮጵያዊው ደራሲ በአሜሪካ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ደራሲና ፀሀፊ ዲናው መንግስቱ በኒውዮርክ የሚገኘውን ፔን አሜሪካን በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ተመረጡ።

ከትናንት በስቲያ ረቡዕ የፔን አሜሪካ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ በተደረገ ምርጫ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዲናው መንግስቱ ድርጅቱን በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

የ103 ዓመት እድሜ ያለው ታዋቂው ተቋም "ፔን አሜሪካ" ዋና መቀመጫውን በኒውዮርክ ያደረገና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

ተግባሩም ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን መደገፍ ፣ ለስነ ፅሁፍ እድገትና ነፃነት መታገል፣እንዲሁም በአጠቃላይ በአለም ዙሪያ ሰብአዊ መብት እንዲከበር መስራት መሆኑ ይነገራል፡፡

ይህንን ግዙፍ ተቋም በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ነው ትውልድ ኢትዮጵያዊው ፀሐፊና ደራሲ ዲናው መንግስቱ የተመረጡት።

ዲናው መንግስቱ በኒውዮርክ የሚገኘውና የኪነ ጥበብ ኮሌጅ የሆነው ባርድ ኮሌጅ የሪትን አርት ፕሮግራም ዳይሬክተር ሆነውም ይሰራሉ።

ኢትዮጵያ አሜሪካዊው ደራሲ ዲናው መንግስቱ ትውልዳቸው በአዲስ አበባ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ መፅሐፍትን ለንባብ አብቅተዋል።

©️ሸገር 102.1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
14👏4
📌ቤቲንግ ቢከለከልም ብሔራዊ ሎተሪ ግን የቤቲንግ ቁማር እያጫወተ መሆኑ ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በሀገሪቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ (Betting) ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙ ይታወሳል።ራሱ ተቋሙ በድረ-ገጽ አማካኝነት የ"ቨርችዋል" ጨዋታዎችን ማጫወት መጀመሩን ካፒታል ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁18👍2🥱1
📌በስንቱ ድራማ የኢቤኤስ ቆይታው ተጠናቀቀ

ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የነበረው ተወዳጁ በስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ፕሮዲዩሰር የሆነው አብሪኮም መልቲሚዲያ፤ ከጣቢያው ጋር የነበረውን የሥራ ውል ማጠናቀቁን መልቲሚዲያው አሳውቋል።

አብሪኮም መልቲሚዲያ ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር የነበረው የሥራ ቆይታ መጠናቀቁን ተከትሎ፤ ተወዳጁ በስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ድራማ ከታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን እንደማይተላለፍ እና በበስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ዙሪያ የሚኖሩ ተጨማሪ መረጃዎችን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ መልቲሚዲያው ገልጿል።

ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር ሰላማዊ እና ጥሩ የሥራ ቆይታ እንደነበራቸው የገለጸው አብሪኮም፤ ለጣቢያው ባለቤቶች እና ሠራተኞች የቀና ምሥጋና አቅርበዋል።

©️ይትባረክ ዋለልኝ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢197👍5🔥3👏3
📌ደራሲ አዳም ረታን በአካል የምታገኙበት እድል

ደራሲ አዳም ረታን በአካል የምታገኙበት እድል በጃፋር መጽሐፍት መደብር በኩል ተዘጋጅቷል።

ደራሲ አዳም ረታ ከነገ በስቲያ ሐሙስ ታህሥሣ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በአዲሱ የጃዕፋር መፅሐፍት መደብር የመጽሐፍት የፊርማ ሥነሥርዓት ያከናውናል።

በተጨማሪም ከአድናቂዎቹ ጋር ስለ ስራዎች በተናጥል ይጨዋወታል። የፎቶግራፍ መርሐግብርም እንደሚያካሂድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
37🔥10
📌ደራሲ አዳም ረታን የምታገኙት ዛሬ ነው

ደራሲ አዳም ረታን በአካል የምታገኙበት እድል !

ደራሲ አዳም ረታን በአካል የምታገኙበት እድል በጃፋር መጽሐፍት መደብር በኩል ተዘጋጅቷል።

ደራሲ አዳም ረታ ዛሬ ሐሙስ ታህሥሣ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በአዲሱ የጃዕፋር መፅሐፍት መደብር የመጽሐፍት የፊርማ ሥነሥርዓት ያከናውናል።

በተጨማሪም ከአድናቂዎቹ ጋር ስለ ስራዎች በተናጥል ይጨዋወታል። የፎቶግራፍ መርሐግብርም እንደሚያካሂድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
11👍8
📌የአእላፋት ሳምንት አውደርዕይ ዛሬ ይጀምራል

የመጀመሪያው የአእላፋት ሳምንት አውደርዕይ እና ፎረም ዛሬ አርብ ታህሥሣ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 በጊዮን ሆቴል ግራውንድስ በይፋ ይጀምራል።

ከታህሣሥ 18 እስከ ታህሣሥ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከጠዋት 4:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 2፡00 ሰዓት ድረስ ዐውደ ርዕዩ ለምዕመናን በአጠቃላይ ክፍት ይሆናል፡፡

ሃይማኖታዊ ትምህርቶች ይሰጣሉ፣መጽሐፍት ይመረቃሉ፣ጥናታዊ ፅሁፎችም ይቀርባሉ፡፡

በኢትዮጵያ ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማህበር የሚዘጋጀው ይሄ ዝግጅት በግዮን ሆቴል ግራውንድስ ይደረጋል።

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በአዲስ አበባና በድሬደዋ ከተማ የሚያዘጋጀው የ2018 የ3ኛው የአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር ታህሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይና በድሬ ለገሀር አደባባይከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ማህበሩ አስታውሷል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏118👍2
"ዳንቴል" የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ስራ ጀመረ

በዳንቴል ሶፍትዌር ኃ.የተ.የግ.ማኀበር የተዘጋጀው "ዳንቴል" የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ስራ ጀምሯል።

"ዳንቴል" መተግበሪያ ተጠቃሚዎች በመተግበሪያው ላይ የሚገኙ ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው እንደ ቴሌግራም፣ ፌስቡክና ቲክቶክ በማጋራትና ሽያጭ እንዲከናወን በማድረግ የኮሚሽን ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

ይህ አሰራር በተለይ የስራ ልምድ ያላቸው ነገር ግን ወደ ስራው ዓለም ለመግባት በካፒታል እጥረት ለተቸገሩ ወጣቶች እንደ ትልቅ ድልድይ ያገለግላል ተብሏል።

መተግበሪያው ተጠቃሚዎች የትኛውን ምርት፣ በምን አይነት የገበያ ሁኔታ እና በምን ያህል ካፒታል መጀመር እንዳለባቸው የሚያማክር የራሱ የሆነ የAI ስርዓት እንዳለውም ተገልጿል።

ይህም አምራቾችና ነጋዴዎች የገበያ ፍላጎትን ተረድተው ምርታቸውን በብቃት እንዲያቀርቡ ይረዳቸዋል።

ዳንቴል ከአምራቾች እስከ ሸማቾች ያለውን ሰንሰለት ለማሳለጥ ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

ይህም ተጠቃሚዎች የሚያዝዟቸው ምርቶች ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲደርሷቸውና የት ደረጃ ላይ እንዳሉ እንዲከታተሉ  ያስችላቸዋል።

በተጨማሪም ድርጅቱ የደንበኞችን እምነት ለመጠበቅ "ምርቱ ካልተመቸ የመመለስ መብት" (Return Policy) ከአቅራቢዎች ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4👍1
📌"ቀለም" ዲጂታል መጽሔት ንባብ በቃ

ቀለም ዲጂታል መጽሔት ቅፅ 1/ ዕትም 6 ለአንባቢያን ቀርቧል።ለተከታታይ 6 ወራት በቴሌግራም ቻናል የተለያዩ ዓምዶችን አካቶ ለንባብ የበቃው ቀለም መጽሔት ስድስተኛ ዕትም ከሰሞኑ ንባብ በቅቷል።

ቀለም ዲጂታል መጽሔት በዚህ ዕትሙ ስለ ሠዓሊ እና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ታሪክ አንስቶ፣ በግጥም ተውቦ ከወጉ አካቶ በስነ-ጽሑፍ ቀለሞች አሸብርቋል።

በነፃ ያንብቡ:-

https://t.me/kelemofficial
👍72🙏2
📌የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 75ኛ ዓመት ክብረበዓል

75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፥ የቀድሞ ምሩቃንና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የቤተሰብ ቀንን ከነገ ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ያከብራል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 75ኛ የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን ከባለፈው ወር ጀምሮ በተለያዩ ፕሮግራሞች በማክበር ላይ ይገኛል።

የቀድሞ ተማሪዎች ሳምንት ከታህሳስ 18-24/2018 ዓ.ም እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

የቀድሞ ተማሪዎች እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቤተሰቦች በበዓሉ ማክበሪያ ሳምንት ታህሳስ 18-19/2018 ዓ.ም በ6 ኪሎ ዋናው ግቢ እና ከታህሳስ 20-24/2018 ዓ.ም በሁሉም ካምፓሶች በመገኘት እንዲያከብሩ ጥሪ አድርጓል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"ጊዜን መሸከም" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

በገጣሚ ዘውዱ አለልኝ የተዘጋጀው "ጊዜን መሸከም" መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ ታህሣሥ 18 ቀን ከቀኑ 10:00 ጀምሮ 24 አካባቢ በሚገኘው መሶብ የሙዚቃ ማዕከል ውስጥ ይመረቃል።

"ጊዜን መሸከም" መጽሐፍ 54 ግጥሞችን የያዘ ሲሆን  በ162 ገጽ የተቀነበበ ነው። የመጽሐፉ ቅርጽ በዋሽንት አውታረ ቅኝት የተሠራ ሆኖ በጥቁር፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ እና ነጭ ቀለማት የተከፋፈለ ነው። 

ቀለማቱ ከኢትዮጵያ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች  ዋሽንት፣ ክራር፣ ነጋሪት እና ሞረሽ ከምትባል ወፍ ጋር የተቀነባበረ ነው ተብሏል።

እያንዳዱ ክፍል ቀለማዊ እና ሙዚቃዊ ፍካሬ መግቢያ አለው። እንዲሁም ግላዊ መግቢያ እና ድኅረ ቃል በመጽሐፉ ውስጥ ተካቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1
📌 "ያልተመለሱ ዳናዎች" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

በደራሲ ካህሳይ አብርሃ ብስራት (አማኑኤል ማንጁስ) የተዘጋጀው «ያልተመለሱ ዳናዎች» የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ይመረቃል።

ደራሲ ካህሳይ አብርሃ ከዚህ ቀደም "የአሲምባ ፍቅር" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍54
📌አርቲስት ሰብለ ተፈራ የክብር መታሰቢያ ተደረገላት

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት እየተከበረ በሚገኘው የቤቶች ድራማ 13ኛ ዓመት ልዩ ክብረ በዓል ላይ፣ ለቀድሞዋ የድራማው ተዋናይ አርቲስት ሰብለ ተፈራ (ትርፌ) የክብርና የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዷል።

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የሚተላለፈው የቤቶች ድራማ ተዋናዮች እና የዝግጅት ክፍሉ አባላት ለአርቲስቷ የክብር አበባ አኑረዋል።

"መቼም ከውስጣችን የማትጠፋዋ" በሚል የታወሰችው አርቲስት ሰብለ ተፈራ፣ በቤቶች ድራማ ትርፌ የተሰኘችውን ገጸ ባህሪ ወክላ በብቃት መጫወቷ ይታወሳል።

አርቲስት ሰብለ ተፈራ በ2008 ዓ.ም ሕይወቷ ማለፉ አይዘነጋም።

©️ኢቢሲ ዶትስትሪም

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
26👍7🕊1
የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ቅጥር ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ፥ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ገለልተኛ የምርጫ ጣቢያ ሠራተኞችን በጊዜያዊነት ለመቅጠር እንደሚፈልግ አስታውቋል።

መስፈርቱን የምታሟሉ በሁሉም ክልሎች ላይ “በምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚነት” ማገልገል የምትፈልጉ አመልካቾች ማመልከት ትችላላችሁ ብሏል።

ማመልከቻ ቀን፦

ከታኅሣሥ19  እስከ ታኅሣሥ 28  ቀን 2018 ዓ.ም  ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት

የምልመላ መሥፈርት፦

• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦ 12ኛ እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ ቦርዱ በሚያቋቁማቸው የምርጫ ጣቢያዎች፣
• የክልሉን የስራ ቋንቋ መናገር እና መጻፍ የሚችሉ
• የሥራ ቆይታ ፦ ለ2 ወር፣
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

ለማመልከት ፦

https://nebe-election.org/recruitment ላይ ማመልከት ትችላላችሁ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

https://t.me/EventAddis1

https://t.me/EventAddis1
5👎1
📌አነጋጋሪው የኢትዮ ቴሌኮም ዋጋ ጭማሪ

ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ አገልግሎቶቹ (ፓኬጆች) ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል። ይህም ጭማሪ በተለያዩ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ እንደመሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

ከዚህ ቀደም በ400 ብር ይሸጥ የነበረው ሳምንታዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት ፓኬጅ ወደ 550 ከፍ ብሏል። ይህም በአንድ አገልግሎቱ ላይ ብቻ ከ150 ብር በላይ ጭማሪ ማለት ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ ስለ ዋጋ ጭማሪው ተከታዩን ብሏል" እየታዩ ያሉትን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች፣ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች እየጨመሩ ያሉ የካፒታልና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት መጠነኛ የታሪፍ ማስተካከያ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👎289🥰1
📌"ግጥም ሲጥም በብሔራዊ ቤተመንግስት"

"ግጥም ሲጥም" ዝግጅት በብሔራዊ ቤተመንግስት በአዲስ ሐውስ ኦፍ ካልቸር ውስጥ ታህሳስ 25 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

በዕለቱም በገጣሚ ታዴዎስ አዲሱ "አያምንምና ቀድሞም ያልካደ" መጽሐፍ ዙሪያ ልዩ መሰናዶ ተዘጋጅቷል።

የግጥም ሲጥም አዘጋጆች ስለ መጽሐፉ ጸሐፊ ተከታዩን ብለዋል " ታዴዎስ አዲሱ በ2017 “አያምንምና ቀድሞም ያልካደ” ሲል የሰየማትን የግጥም ስብስብ ስራውን ካደረሰን ወዲህ በርካታ መድረኮች ላይ ተሰጥዖውን እያካፈለ ያለ ወጣት ነው።

ታዴዎስ በኢትዮጵያ የግጥም ግጥሚያ ሻምፒዮናም ብርቱ ተፎካካሪ ሆኖ ከመቅረቡም ባሻገር በምሽቱ ብቸኛውን ሙሉ ነጥብ ማግኘት ችሎም ነበር"

የዝግጅቱ መግቢያ የግቢውን ጉብኝት ጨምሮ 300 ብር እንደሆነም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
9😁1
📌 የከተማችን ውዱ ኮንሰርት ዛሬ ምሽት ይካሄዳል

መግቢያው 25 ሺ ብር ነው

የፈረንጆች አዲስ ዓመት ሲመጣ ሁሌም ልዩ የሙዚቃ በማሰናዳት የሚታወቀው ሸራተን አዲስ ነው፡፡

ሸራተን ዘንድሮ ከአሜሪካ ታዋቂውን የአር ኤንድቢ አቀንቃኝ ትሬይ ሶንግዝን የሚያስመጣ ሲሆን አብረውትም ድምፃዊ ብዙአየሁ ደምሴና ናቲ ማን ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ አስታውቋል፡፡

ዛሬ አመሻሽ ላይ ለሚካሄደው ለዚህ ኮንሰርት ሆቴሉ ያስቀመጠው የአንድ ሰው መግቢያ 25 ሺህ ብር ነው፡፡

ይህ ክፍያ ምንም እንኳ ምግብና መጠጥን የሚያካትት ቢሆንም ካለፈው አመት ጋር ሲተያይ ግን ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣224👎3
📌ዛሬ እኩለ ሌሊት ላይ ርችት ይተኮሳል

ፈረንጆቹ ዛሬ እኩለ ሌሊት ላይ አዲስ ዓመታቸውን ይቀበላሉ። የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት (2026) መግባት ምክንያት በማድረግ፣ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ በሸራተን አዲስ ሆቴል የርችት ተኩስ እንደሚከናወን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ የርችት ዝግጅቱ ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ለ15 ደቂቃ ያህል የሚቆይ ይሆናል ተብሏል።

ህብረተሰቡ ድንገተኛ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንዳይደናገጥ እና ዝግጅቱ ለበዓል አከባበር ብቻ መሆኑን ተገንዝቦ በተለመደው ሰላማዊ ሁኔታ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣175🤔1🤡1