Event Addis Media
9.59K subscribers
6.04K photos
12 videos
4 files
4.67K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ዶ/ር ተሻለ አሰፋ "ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል" ሲል ተናገረ

ታዋቂው የቴአትር ጥበባት መምህርና አዘጋጅ ዶ/ር ተሻለ አሰፋ "ሆቴሎችም ቲያትር ማሳያ ሆነው ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል" ሲል ትዝብቱን ተናግሯል።

የዶ/ር ተሻለ አሰፋ ሙሉ ሀሳቡ እንደሚከተለው ይቀርባል" ባለፈው ሐሙስ "የእራት ግብዣው" የተሰኘውን ቲያትር በዓለም ሲኒማ እየተመለከትኩ ሀሳቤ ለሁለት ተከፍሎ ነበር።

በአንድ ወገን በቲያትሩ ስደሰት በሌላ በኩል ደግሞ እስካሁን ድረስ አልላቀቅ ካለኝ ጥያቄ ጋር ስሟገት ነበር። ዓለም ሲኒማ ቲያትር ቤት አይደለምኮ።

ታዲያ ለምንድነው በርካታ ድንቅ ስራዎችና በሳል ባለሙያዎች ወደዚያ የሄዱት? (የተሰደዱት ብዬ ነገሩን ማጮህ አልፈለግኩም)። ይሄ ጥያቄ ከዚህ በፊት በሌሎች ባለሙያዎችም ሲጠየቅ ሰምቻለሁ። መልስ እጠብቅ ነበር።

በተለይ ዋና ስራችሁ ቲያትር መስራት ከሆነ ቲያትር ቤቶች። መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ደጃችሁ ድረስ መጥቼ ተሟግቻለሁ። መልስ  አላገኘሁም። እንዳይረፍድ እሰጋለሁ። በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ሲኒማዎች ብቻ ሳይሆኑ ሆቴሎችም ቲያትር ማሳያ ሆነው ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል። ሙያው ታላቅ ነው። ክብር ስጡት፤ ወይም ክብር ሰጥተውት ዋጋ እየከፈሉለት ያሉትን ባለሙያዎች አክብሯቸው። ይብቃኝ መሰለኝ። ለማንኛውም የ"የእራት ግብዣው" ቲያትር ተሳታፊዎች በሙሉ ድንቅ ሾል ሰርታችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤11🤔4👍2🙏1
📌"ነገረ ኢትዮጵያውያን" መጽሐፍ ይመረቃል

በላዕከ ወንጌል በኃይሉ በቀለ የተፃፈው "ነገረ ኢትዮጵያውያን " የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ ታህሳስ 11 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ 4ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በርካታ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🥰7❤6
📌ቲክቶከሮቹ በአፈንጋጭ አለባበሳቸው ታሰሩ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሀገራችን ባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎች ላይ  ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  በ3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥነ-ምግባር  ባፈነገጠ አኳሃን ሰውነታቸውን  የገላለጠ አለባበስ ለብሰው በአደባባይና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አባሮቻቸው ጋር በቁጥጥር ሼር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል።

‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን በሀገራችን አዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩ፣ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፋ እና ፕሮግራሙን ያቀነባበሩ ተጠርጣሪዎች:-

‎1ኛ. ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣
‎2ኛ. በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣
‎3ኛ. መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣
‎4ኛ. ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና
‎5ኛ. ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርየም ‎የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ አለባበሶችና መጤ ባህሎች ተስፋፍተው በትዉልዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያስከትሉ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።

©️ የፌዴራል ፖሊስ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍40❤10😁9👎5💯4🤝2
📌ሶፊ ሾው ከአሻም ቴሌቪዥን ታገደ

አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁን በኮንትራት ውል በዜና አቅራቢነት እንዲሁም በቅርቡ በጣቢያችን ‹‹ሶፊ ሾው›› ሲል በሰየመው የመዝናኛ ዝግጅቱ  በአሻም የቴሌቪዥን እና በዩትዩብ ገፅ እያዘጋጀ ሲያቀርብ እንደነበረ ይታወቃል፡፡

ይህ በሆነበት ከትላንት ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ስለ ጋዜጠኛው ከኢትዮጵያዊነት ባሕል፣ ወግ እንዲሁም ሃይማኖት ያፈነገጠ ተግባር ሲፈጽም የሚያሣይ መረጃ በድምጽ፣ በጽሁፍና በተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር ሲዘዋወር ተመልክተናል፡፡

አሻም ይህንኑ በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ጋዜጠኛው የተሰራጨውን መረጃ ተከትላ ስለ ተሰራጨበት መረጃ ሶፎኒያስን ማብራሪያ እንዲሰጥበት ጠይቃለች፡፡ በዚህም ሶፎኒያስ <<አሁን ራሴን ለማስተካከል፤ለማከም ፀበል ገብቻለሁ>> የሚል አጭር ምላሽ ከመስጠት ውጭ ተጨማሪ ያለው ነገር የለም።

ስለሆነም አሻም ሚድያ ትሬዲንግ አ.ማ. የኢትዮጵያን ባህል እና ወግ እንዲሁም የህብረተሰቡን እሴት እና ሃይማኖት ያከበረ የምትመራበት ኤዲቶሪያል አላት፡፡ ይሁን እንጂ ጋዜጠኛው የሚዲያውን ኤዲቶሪያልም ሆነ የማህበረሰቡን እምነት ፣ እሴት፣ ወግ፣ ባህልና ሃይማኖት የሚጻረር ተግባር ተሰራጭቶበት በመመልከቷ እጅጉን እያዘነች ድርጊቱ የሚዲያ ተቋሟን የማይወክል ይልቁንም በጽኑ የምታወግዘው መሆኑን ለውድ ተመልካቾቻችን እና ተከታታዮቻችን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አሻም ሚዲያ ትሬዲን አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ ዋሲሁን በፈጸመው ከባድ የማህበረሰባዊ እሴት እና ኤዲቶሪያል ጥሰት ጭምር የነበራትን የስራ ውል ከዛሬ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማቋረጡዋን ለመግለጽ ትወዳለች፡፡

©️አሻም ቴሌቪዥን

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤15👏12
📌 ዛሬ የኤልያስ መልካ ልደት ነው!

ኤልያስ መልካ በሕይወት ቢኖር ዛሬ የ48ተኛ ዓመት ልደቱን ያከብር ነበር።

በልደቱ ቀን ይህን ታላቅ የሙዚቃ ሰው ለኢትዮጵያችን የሙዚቃ ዘርፍ አበርክቶው እናመሰግናለን እንላለን።

42 ዓመት ኖሮ ከ50 በላይ አልበሞችን ያቀናበረው ሙዚቀኛ የዜማ እና ግጥም ደራሲ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ፕሮድዩሰር የሆነው ኤልያስ መልካ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ባለውለታ ነው።

በቅንብር ስራ ላይ በቆየባቸው 19 ዓመታት ተወዳጅነትን ያተረፉ ከ50 በላይ አልበሞችን አቀናብሯል።

የኢዮብ መኮንንን "እንደቃል" አልበም፣ የጌቴ አንለይን “መልክሽ አይበልጥሽም” አልበም፣ የቤሪን "ከምን ነፃ ልውጣ" አልበም እና ወዘተ... ደግሞ ከቅንብር ባሻገር በግጥም እና ዜማ በመሳተፍ ጭምር የሰራቸው አልበሞች ናቸው።

ኤልያስ ከአማርኛ በተጨማሪ በትግርኛ፣ ኩናምኛ፣ኦሮሚኛ የተዜሙ የሙዚቃ ስራዎችንም አቀናብሯል ነጠላ ዜማዎችን እና ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚውሉ ስራዎችንም በብዛት ሰርቷል።

ከአዳዲስ ሙዚቀኞች ጋር በመስራት ተስእጦ ያላቸውን ሙዚቀኞች ማውጣትም ሌላው መገለጫው ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ አብረውት ከሰሩ የወቅቱ ጀማሪ ሙዚቀኞች መካከል ዘሪቱ ከበደ፣ ሚካያ በኃይሉ፣ ኃይሌ ሩትስ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ኢዮብ መኮንን ይጠቀሳሉ።

ኤልያስ መልካ ከሙዚቀኛነቱ ባሻገር ለሙዚቀኛው መብት መከበር ከፍተኛ ትግል እና ወደር የለሽ አስተዋፅኦ ያበረከተ እንዲሁም ሙዚቀኛው የልፋቱን እንዲያገኝ ሙዚቃን በስልክ መተግበሪያ (App) እንዲገበያይ የመጀመሪያውን እርምጃ የተራመደ ታላቅ የሙዚቃ እና የፈጠራ ሰው ነበር።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤42🕊4🔥3
📌ቲክቶከር አዶናይ ታሰረ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ሼር ሊውል የቻለው ‎ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩት አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር በዋሉበት የወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ዕውቅና እና ገንዘብ ለማግኘት ብቻ በማሰብ ሚዲያዎችን ኃላፊነት በጎደለው አኳሃን እየተጠቀሙ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በመልካም ሥነ ምግባር ተቀርጾ ሀገርን የሚጠቅሙ ተግባራትን እንዳያከናውንና በተቃራኒው በትውልዱ ላይ ርካሽ ባህልን ለመጫ የሚደረገው ተግባር ለመከላከል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁18👏9😡9❤2
📌አሻም ቴሌቪዥን ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ

አሻም ቴሌቪዥን ስራውን ለመቀጠል አቅም ስለሌላው ሙሉ በሙሉ ስርጭቱን እንዳቋረጠ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ጣቢያው በቴሌቪዥንም ሆነ በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ከዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በይፋ ስርጭቱን ማቆሙን ገልጿል።

አሻም ቴሌቪዥን ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ የአሻም ሚዲያ መታወቂያ በመያዝ ወይም የሚዲያዋን ሎጎ በመጠቀም በየትኛውም ሁነት (Event) ፣ በእቅድ ዜና ወይም ፕሮግራም ፣ በስልጠና መድረክ ፣ ቃለ-መጠይቅ እና በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚገኙ (የሚሳተፉ) ባለሞያዎች የሚዲያ ተቋሙን እንደማይወክሉ ለሁሉም የግልና መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች  ጭምር በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን ብሏል።

አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር á‰Łáˆˆá‰á‰ľ 8 ዓመታት ጀምሮ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዜናና ወቅታዊ እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች መረጃዎችን በቴሌቪዥን እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😭42❤6😢3🔥2👍1
📌"ጎላ ጉህ"  ያሬድ ሹመቴ ነው

የድምጻዊት የማርያም ቸርነት "የደጋ ሰው" አልበም ላይ አብዛኞቹን ግጥሞች የጻፈውና ያስደመመን "ጎላ ጎህ"  የተባለው ባለ ብዕር ስም á‹ŤáˆŹá‹ľ ሹመቴ እንደሆነ ደጃፍ ፖድካስት ላይ ተናግሯል።

ይሄ  ጎላ ጎህ የሚባለው ሰው ማነው ስትሉ ለከረማችሁ ሙሉ መልሱን ልሹ ያሬድ ሹመቴ á‹­áŠáŒáˆŤá‰˝áŠ‹áˆá˘

ሊንክ:https://youtu.be/tm9PercKdUI?si=8rUTaybnEUjzQQKM

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍25🔥12❤6😱3
📌አንባቢያን መጽሐፍ የሚቀያየሩበት ልዩ ዝግጅት

የአዲስ የሥነጽሑፍ ፌስቲቫል አካል የሆነ  "ሥነ ጽሑፍ እና ነገረ ሐቲት" የተሰኘ መርሐግብር ተዘጋጅቷል።

ቅዳሜ ታህሳስ 4 ፣ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 – 12:00 ከቤት እስከ ከተማ ፡ የከተማ ማዕከል ውስጥ በተዘጋጀው በዚህ መሰናዶ የመጽሐፍ ወዳጆች አዳዲስ እና የቆዩ መጻሕፍትን የሚሸጡበት፣የመጻሕፍት ልውውጥ፣እንዲሁም ያነበቡትን መጽሐፍ  በሌላ የሚቀያየሩበት እና ሾለ ሥነ ጽሑፍ ጥልቅ ውይይት የሚያደርጉበት ይሆናል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ሰምቷል።

በውይይቱ ላይ ከኢትዮጵያ ቡክ ፎረም ዳዊት ብርሃኑ ፣ ከኢትዮጵያ ሳይንክ አካዳሚ ሐያሲ ቴዎድሮስ አጥላው፣ ጸሐፌ ተውኔት መዓዛ ወርቁ እንዲሁም ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ይገኙበታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍5❤4
📌 የሮማን ተወለደ "ዮዲታ" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

ሮማን ተወልደብርሃን የጻፈችውና የክርስትና እናቴ በሰጠችኝ ሁለተኛ ስሜ "ዮዲታ" የተሰኘ ርዕስ ሰጥቼዋለሁ ያለችውን መጽሐፏን በዚህ ሳምንት ለንባብ አብቅታለች።

"ዮዲታ" የተሰኘው መጽሐፏ በይዘት ግለታሪክ ሲሆን ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 4 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ገሐር በሚገኘው በአዲሱ ጃፋር የመጽሐፍት መደብር ውስጥ ይመረቃል።

በጃፋር መጽሐፍት መደብር በኩል ለንባብ የበቃ መጽሐፏ በቀጣይ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንደሚሰራጭም ደራሲዋ ገልጻለች።

ደራሲ ሮማን ተወለደብርሃን አስቀድማ ጉራማይሌና የነፍስ እኩያዎች የተሰኙ መጽሐፍትን በቡድን እንዲህም ለታዳጊዎች ደናደን የተሰኙ መጽሐፍትን ለንባብ አብቅለታች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤25
📌ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ

ኢትዮጵያዊው የፊልም ባለሙያ ቤዛ ኃይሉ 'አላዛር' በተሰኘ ፊልም ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ::

በፊልም ጽሁፍ አዘጋጁና ዳይሬክተሩ የተሠራው ፊልም፤ የ "ዳካር ኮርት የ2025 ዓለም አቀፍ የአጭር ፊልም ፌስቲቫል ግራንድ ፕሪ ሽልማት አሸናፊ ለመሆን በቅቷል፡፡

ለ36 ደቂቃዎች የሚዘልቀው “አላዛር” ፊልም፣ ለምርጥ ዳይሬክተር የሚሰጠውን “አባባካር ሳም ማክሃራም” የተሰኘውን ሽልማት መቀዳጀቱንም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

ፊልሙ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የገበሬ ማህበረሰብ ሐይማኖት፣ አመክንዮና አምልኮ ዙሪያ በማጠንጠን ተመልካቾችን ስሜታዊ መዋዥቅ ውስጥ ሰቅዞ እንደሚይዝ ዳኞቹ ለምርጫቸው በሰጡት ማብራሪያ መናገራቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤42👍8👏3🔥1
📌"ከርቤ" ፊልም አርብ ይለቀቃል !

በሂስትሪ ፊልም ካምፓኒ ተሰርቶ የቀረበው "ከርቤ" ፊልም አርብ ታህሳስ 10 ልክ 12:00 ሲል በNahom_Multimedia ዩቲዩብ ቻናል በኩል  ይለቀቃል።

ጭብጡን በጓደኛው ታላቅ በደልና ታላቅ ውለታ መሃል ገብቶ የተወጠረው አባት ነገሮችን ለመፍታት በሚከፍለው መስዋትነት እና በቀረው ቤተሰብ መካከል የተፈጠረውን ክስተት የሚያሳይ ልብ አንጠለጣይ ፊልም ነው።

በስዩም በላይ Produced የተደረገ ሲሆን ፊልሙን ዳይይሬክት ያደረገው አለባቸው አራጌ፣ áˆ˛áŠ’áˆ›á‰śáŒáˆŤáŠá‹áŠ•  ዳንኤል ግርማ፣  በትወና ደግሞ በሄኖክ ወንድሙ፣ መዓዛ ገ/ሕይወት ፣ የአብሥራ ታደሠ፣ ከድር ሁሴን፣ ይሁኔ ምንዋጋው፣ ሰርካለም ደምሴና ሌሎችም ተሳትፈውበታል፡፡

ፊልሙ አርብ ታህሳስ 10 ምሽት በNahom_Multimedia ዩቲዩብ በኩል ለተመልካች ይደርሳል።

ፊልሙ የሚለቀቅበት ቻናል ሊንክ ይኸው

https://youtube.com/@nahommultimedia?si=YqGl8THSPt1GIv7D
👍9❤8
📌የያንጎ ፌሎውሺፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት ተጀመረ

ይህም የቀጣዩን ትውልድ ዐቅም በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ለማጎልበት የሚያስችል ነው::

ዓለም አቀፋዊ የቴክኖሎጂ ተቋም የሆነው ያንጎ ግሩፕ፣ የያንጎ ፌሎውሺፕ ቀጣይ ምዕራፍ - በመላው አፍሪካ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ችሎታን ለማጎልበት ዓልሞ እንደተነደፈ አስታውቋል። 

ያንጎ ፌሎውሺፕ፣ ወጣቶችን በማማከር እና አቅጣጫ በመጠቆም እንዲሁም ግብዓቶችን እና የግንኙነት መረቦችን በመዘርጋት፣ ተሳታፊዎች ማኅበረሰባቸውን የሚጠቅሙ ሐሳቦችን እንዲያመነጩ ብሎም ወደ ተግባር እንዲቀይሩ እገዛ ያደርጋል።

በዛምቢያ እና በአይቮሪኮስት በተሳካ ሁኔታ የተጀመረው የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም አድማሱን በማስፋት ወደ አራት ተጨማሪ ሀገራት፣ ማለትም ኢትዮጵያ፣ ሞዛምቢክ፣ ጋና እና ሴኔጋል ደርሷል።

መዳረሻዎቹን እያሰፋ የመጣው የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም፣ የገንዘብ ድጋፍን እና የባለሙያዎችን ሰፊ እገዛ ያካተተ ከመሆኑም ባሻገር፣ በድንበር ያልተገደበ ሰፊ የፌሎው ተጠቃሚ ማኅበረሰብ ግንኙነቶችን በማመቻቸት ተሳታፊዎች ለኅብረተሰባቸው መፍትሔ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ: https://url-shortener.me/460W
❤4👍1👎1
📌የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ

የ2018 ዓ.ም 3ኛው የአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ (ኢጃት) "የአእላፋት ሳምንት" የዝማሬ መርሐግብር ታኅሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይና በድሬ ለገሀር አደባባይ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ አሳውቋል።

በተጨማሪም የአእላፋት ሳምንት የተሰኘ ዐውደ ርዕይና የፎረም መድረክ ከታኅሣሥ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በግዮን ሆቴል ግራውንድስ ለማከናወን ዝግጅቱን መጨረሱን አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤52👎8👍3👏2
📌አሜሪካ የ”ዲቪ” ሎተሪ እድልን አገደች!

የዩናይትድ ስቴትስ ብራውን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከተፈጸመ የተኩስ እሩምታ ግድያ በኋላ የ”ዲቪ” ሎተሪ እድልን ማገዷን አሳወቀች።

የሀገሪቱ የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ኃላፊ ክሪስቲ ኖዬም በብራውን ዩኒቨርሲቲ የተኩስ እሩምታ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ “አሁን በተቋረጠው የዲቪ መርኀ-ግብር ተጠቃሚ ከሆነ አገር የመጣ ነው” ብለዋል።

ለኃላፊዋ የዲቪ ሎተሪ እድል መርኀ-ግብሩን እንዲያቋርጡ “አቋርጪ” ሲሉ ትናንት ሐሙስ ታኅሣሥ 9 /2018 ዓ.ም ማምሻውን ትእዛዝ ያስተላለፉላት የአገሪቱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ብሏል ዶቸቬለ በዘገባው።

የዲቪ ሎተሪ መርኀ-ግብር በየዓመቱ 50,000 ፍልሰተኞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲገቡ የሚያስችል እድል እንደነበር ነው የተገለፀ ሲሆን በዚህ እድል በርካታ ኢትዮጵያውያንም ተጠቃሚ እንደነበሩ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤7🤔2
📌ተጠባቂው "ከርቤ" ፊልም ተለቀቀ

በሂስትሪ ፊልም ካምፓኒ ተሰርቶ የቀረበው "ከርቤ" ፊልም በNahom_Multimedia ዩቲዩብ ቻናል በኩል á‰°áˆˆá‰€á‰€á˘

ፊልሙን ለመመልከት ይኸው ሊንክ:https://youtu.be/CWE3vgB29uE?si=IgA67qcgs5Kp2HYD

ከርቤ ፊልም ጭብጡን በጓደኛው ታላቅ በደልና ታላቅ ውለታ መሃል ገብቶ የተወጠረው አባት ነገሮችን ለመፍታት በሚከፍለው መስዋትነት እና በቀረው ቤተሰብ መካከል የተፈጠረውን ክስተት የሚያሳይ ልብ አንጠለጣይ ፊልም ነው።

በስዩም በላይ Produced የተደረገ ሲሆን ፊልሙን ዳይይሬክት ያደረገው አለባቸው አራጌ፣ áˆ˛áŠ’áˆ›á‰śáŒáˆŤáŠá‹áŠ•  ዳንኤል ግርማ፣  በትወና ደግሞ በሄኖክ ወንድሙ፣ መዓዛ ገ/ሕይወት ፣ የአብሥራ ታደሠ፣ ከድር ሁሴን፣ ይሁኔ ምንዋጋው፣ ሰርካለም ደምሴና ሌሎችም ተሳትፈውበታል፡፡
❤8🔥1
📌የተደለዙ ገጾች መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል

በጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደዮሐንስ የተዘጋጀው "የተደለዙ ገጾች " መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።

የተደለዙ ገጾች ዐሥር አጫጭር እውነተኛ ታሪኮችን የያዘ መፅሐፍ ነው። ትኩረት የተነፈጉ ቁም ነገሮች፣ እንደዋዛ የታለፉ ውልብታዎች፣ የተኖሩ የሕይወት ገጽታዎች ናቸው።

ዐጭር ቢሆኑም በዝርዝር የሚታወሱን፣ ፈገግ የሚያደርጉን፣ የሚያሳዝኑን፣ የሚወቅሱን ግን ዘንግተን ያለፍናቸው የታሪካችን አካል ናቸው።

መጽሐፉ በጃዕፋርና ክብሩ መፅሐፍት መደብር ይገኛል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5👍2
📌የመጀመሪያዋ ሴት የረዥም ልቦለድ ደራሲ ፀሐይ መልአኩ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የደራሲዋ አዲስ መጽሐፍ ርዕስ "ዘባሲል" ይሰኛል።

"ዘባሲል” መጽሐፍ በ399 ገፆች የተቀነበበ ታሪክ ለበስ ልብ ወለድ ነው።

መፅሐፉ ዛሬ  ቅዳሜ ታኅሣሥ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትያና ቤተመጻፍት አገልግሎት (ወመዘክር( አዳራሽ ይመረቃል።

“ዘባሲል” መፅሐፍ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ደምና አጥንት ተከፍሎባት የተረከባትን ሃገር ባለአደራ ሆኖ ለቀጣዩ ትውልድ እንዴት ማስተላለፍ እንዳለበት እንደሚጠቁም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤7🙏6👍2
📌ትውልደ ኢትዮጵያዊው ደራሲ በአሜሪካ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ደራሲና ፀሀፊ ዲናው መንግስቱ በኒውዮርክ የሚገኘውን ፔን አሜሪካን በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ተመረጡ።

ከትናንት በስቲያ ረቡዕ የፔን አሜሪካ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ በተደረገ ምርጫ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዲናው መንግስቱ ድርጅቱን በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

የ103 ዓመት እድሜ ያለው ታዋቂው ተቋም "ፔን አሜሪካ" ዋና መቀመጫውን በኒውዮርክ ያደረገና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

ተግባሩም ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን መደገፍ ፣ ለስነ ፅሁፍ እድገትና ነፃነት መታገል፣እንዲሁም በአጠቃላይ በአለም ዙሪያ ሰብአዊ መብት እንዲከበር መስራት መሆኑ ይነገራል፡፡

ይህንን ግዙፍ ተቋም በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ነው ትውልድ ኢትዮጵያዊው ፀሐፊና ደራሲ ዲናው መንግስቱ የተመረጡት።

ዲናው መንግስቱ በኒውዮርክ የሚገኘውና የኪነ ጥበብ ኮሌጅ የሆነው ባርድ ኮሌጅ የሪትን አርት ፕሮግራም ዳይሬክተር ሆነውም ይሰራሉ።

ኢትዮጵያ አሜሪካዊው ደራሲ ዲናው መንግስቱ ትውልዳቸው በአዲስ አበባ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ መፅሐፍትን ለንባብ አብቅተዋል።

©️ሸገር 102.1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤14👏4
📌ቤቲንግ ቢከለከልም ብሔራዊ ሎተሪ ግን የቤቲንግ ቁማር እያጫወተ መሆኑ ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በሀገሪቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ (Betting) ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙ ይታወሳል።ራሱ ተቋሙ በድረ-ገጽ አማካኝነት የ"ቨርችዋል" ጨዋታዎችን ማጫወት መጀመሩን ካፒታል ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁18👍2🥱1
📌በስንቱ ድራማ የኢቤኤስ ቆይታው ተጠናቀቀ

ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የነበረው ተወዳጁ በስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ፕሮዲዩሰር የሆነው አብሪኮም መልቲሚዲያ፤ ከጣቢያው ጋር የነበረውን የሥራ ውል ማጠናቀቁን መልቲሚዲያው አሳውቋል።

አብሪኮም መልቲሚዲያ ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር የነበረው የሥራ ቆይታ መጠናቀቁን ተከትሎ፤ ተወዳጁ በስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ድራማ ከታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን እንደማይተላለፍ እና በበስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ዙሪያ የሚኖሩ ተጨማሪ መረጃዎችን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ መልቲሚዲያው ገልጿል።

ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር ሰላማዊ እና ጥሩ የሥራ ቆይታ እንደነበራቸው የገለጸው አብሪኮም፤ ለጣቢያው ባለቤቶች እና ሠራተኞች የቀና ምሥጋና አቅርበዋል።

©️ይትባረክ ዋለልኝ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢19❤7👍5🔥3👏3