Event Addis Media
9.6K subscribers
6.06K photos
12 videos
4 files
4.68K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌"የኔ ቆንጆ ኑሪ" በሚለው ዘፈኑ የሚታወቀው አብርሃም አየለ ሙሉ የዘፈን አልበም ሊለቅ እንደሆነ ሀገር ይወቅልኝ አለ።

አብርሃም አየለ የሚለቀው አልበም ከ4 ሚሊየን ብር በላይ እንደፈጀ የተናገረ ሲሆን ይህ "ዱዳሌብ" የተሰኘ የዘፈን አልበም የፊታችን ማክሰኞ ህዳር 23 እንደሚለቀቅም አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣29😭9👍32😱1
📌ጣና ነሽ ፪ ጀልባ አገልግሎት መስጠት ጀመረች

በመጨረሻም ጣና ነሽ ፪ ጀልባ የመጀመሪያውን የመንገደኞች ማጓጓዝ ስራዋን ከባሕር ዳር ወደ ደልጊ እና ደቅ በማድረግ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀምራለች።

188 ተሳፋሪዎችን የማጓጓዝ አቅም ያላት ጣናነሽ ፪ በአስደማሚው የጣና ሐይቅ የተፈጥሮ ከባቢ የሚደረገውን ጉብኝት እና ወደ ጎርጎራ ኢኮ ሎጅ የሚደረገውን ጉዞ ይበልጥ ምቹ አድርጋው ሰንብታለች።

አሁን ደግሞ ጣና ነሽ ፪ ጀልባ የመጀመሪያውን የመንገደኞች ማጓጓዝ ከባሕር ዳር ወደ ደልጊ እና ደቅ በማድረግ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሯን የክልሉ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍62😁1🙏1
📌የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ ጭስ ቻይና ደረሰ

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአፋር ክልል የሚገኘው የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ድጋሚ ከፈነዳ በኋላ የፍንዳታው ጭስ ቀይ ባህርን ተሻግሮ ቻይና ደርሷል።

በፍንዳታው ወቅት ጭስ እና ሰልፈር ዳይኦክሳይድ እስከ 14 ኪሎሜትር ከፍታ ድረስ የወጣ ሲሆን ጭሱ ቀይ ባህርን ተሻግሮ ሰሜን ምዕራብ ህንድ ከደረሰ በኋላ የህንድን አየር ክልል በመልቀቅ ወደ ቻይና እያመራ ነው ተብሏል።

ጭሱ በሰዓት ከ120-130 ኪሎሜትር በሆነ ፍጥነት እየሄደ እንደሆነ የተገመተ ሲሆን ወትሮውንም በመጥፎ አየር ለምትታወቀው ዴሊህ ከተማም ስጋት ሆኗም ነበር።

የሜትሮዎሎጂ ባለሙያዎች ግን ጭሱ ከ25,000-45,000 ጫማ ከፍታ ውስጥ እየተጓዘ በመሆኑ መሬት ላይ የአየር ብክለት ተፅዕኖው እምብዛም አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።

የህንድ የሜትሮዎሎጂ ተቋምም የጭሱ ተፅዕኖ በዴሊህ ከተማ ላይ ብዙም አይቆይም ሲል አስታውቆም ነበር።

በዚህው የኤርታሌ ፍንዳታ ጭስ የተነሳም በርካታ በረራዎች ተሰርዘው የቆዩ ሲሆን ጭሱ የሳተላይት ተግባራትንና የበረራ ስራዎችን በጊዜያዊነት ተስተጓጉለዋል።

ኤይር ኢንዲያ፥ በጭሱ የተነሳ 11 በረራዎችን ሲሰርዝ የህንድ የሲቪል አቪየሽን ተቋምም አብራሪዎች ከጭሱ ጋር በተያያዘ የገጠማቸው ነገር ካለ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጠይቆ፤ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶም ነበር።

የፍንዳታው ጭስም የህንድ የአየር ክልልን ሙሉ ለሙሉ በመልቀቅ ወደ ቻይና እንዳመራ የህንድ የሜትሮዎሎጂ ተቋም ገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6😱5👍1
📌ቅዳሜ ከሰዓትን በቁም ነገር ያሳልፉ

ሱስ መዳን የሚችል በሽታ ነው!

ህዳር 20 ከቀኑ 8:30 ጀምሮ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

ጉድ ላክ የሱስ ማገገሚያ በጎ አድራጎት ድርጅት 4ኛ  አመት የምስረታ  በዓሉን  22 አካባቢ በሚገኘው ካፒታል  ሆቴል እና ስፖ ያከብራል።

በዕለቱም የተለያዩ ፕሮግራሞች ተዘጋጅቷል
እርሶም እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

ጉድ ላክ  የሱስ  ማገገሚያ  የበጎ አድራጎት ድርጅት የተመሰረተው  በድርጅቱ  መስራች ባለ ራእይና  ስራ  አስኪያጅ   በሆነው  እድለኛው ዮናታን ሊዮን  ሲሆን   እራሱም  ለ22 አመታት  በአልኮል  ሱስ  የነበረ በዓሁን ሰዓት ለብዙ  ወጣቶች ምሳሌ የሆነ ብርቱ ባለራዕይ ነው።

ለበለጠ መረጃ:- 0924881562 
8👍4👏1
📌የድምጻዊ ሮቤል ሚዲቅሳ አልበም ተለቀቀ

ድምጻዊ ሮቤል ሜዲቅሳ ለዓመታት ሲያዘጋጀው የቆየውና "ከበር-አፍ" የተሰኘ ርዕስ የሰጠውን ሙሉ የሙዚቃ አልበሙን  ህዳር 19 2018 አመሻሽ ላይ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ዩቲዩብ ቻናል ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች አቅርቧል።

"ከበር-አፍ" የተሰኘው የሙዚቃ አልበም ብዙ አዳዲስ ነገሮችን የሞከረበት እንደሆነም ድምጻዊው ተናግሯል።

አልበሙ በጣም ብዙ የተለፋበት አዳዲስ ድምፆች እና የአዘፋፍን ስልቶች አሉት። ወደ ቀድሞዋ ኢትዮጵያ በፍቅር እንመለስ ብለው በትዝታ ሊመልሱን ተዘጋጅተዋል።

የአልበሙ መጠሪያ "ከበር-አፍ" ይሰኛል።
በውስጡ 12 ወጥ ስራዎች አሉት። በሙዚቃ ስልቱ ዘመናዊውን ሙዚቃ ከጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ባህል ጋር ያዋሃደ ሲሆን አንጋፋ ሙዚቀኞችም ተሳትፈውበታል።

ቀረፃ፣ የድምፅ ውህደት እና ማስተሪንግ ፡ ኤርሚያስ ፍቃዱ (12 ሙዚቃዎች)

የዜማ ደራሲ፡ ኤርሚያስ ፍቃዱ (11 ሙዚቃዎች)

የግጥም ደራሲ ፡ ኤርሚያስ ፍቃዱ (10 ሙዚቃዎች)

የግጥም ደራሲ ፡ ፀጋዬ ደቦጭ (1 ሙዚቃ)

የግጥም ደራሲ ፡ ብሌን ዮሴፍ (1 ሙዚቃ)

የዜማ ደራሲ ፡ ሮቤል ሚደቅሳ (1 ሙዚቃ)

የዜማ ደራሲ ፡ ሮቤል ሚደቅሳ (1 ሙዚቃ)

ሮቤል ሚደቅሳ  ከዚህ ቀደም ትዝታችን ፣ ወዳኝ ፣ ክነፍ ክነፍ የተሰኘ ርዕሶች የተሰጣቸውን ሙዚቃዎች ጨምሮ በተለያዩ ነጠላ ሙዚቃዎች ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
10
📌ብሩክ ኒውስ አሸንፏል

የ2025 የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ የኢንፎርማቲቭ አሸናፊ ብሩክ ኒውስ (ብሩክ ጫላ) ሆኗል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏248👎7🤔4
📌አርቲስት ማስተዋል "ጌታን ተቀበሉ" አለች

በቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ ለመሸለም ወደ መድረክ የወጣችው የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት  አርቲስት ማስተዋል ወንድወሰን "በህይወታችሁ ለውጥ ማምጣት ከፈለጋችሁ ጌታን ተቀበሉ" ብላለች።

ይህም ንግግሯ በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁46👏12🤣107🔥3💯2
📌አዶናይ 'የማርያምን ስም ሁሌም እጠራለሁ' አለ

በ2025 የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ "ላይፍ ስታይል" በተሰኘው ዘርፍ በአንድ መድረክ ለሁለተኛ ጊዜ የተሸለመ አዶናይ "ሁሌም ስሟን እጠራለሁ ማርያም ማርያም ማርያም" ሲል በመድረኩ ላይ ንግግር አድርጓል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
65🤣11🔥3🤔3👌1
📌በአክሱም የሆቴልም ሆነ የእንግዳ ማረፊያ የመኝታ ዋጋ በሶስት እጥፍ መጨመሩ ተነገረ

ነገ የሚከበረውን የፅዮን ማርያም በዓል አስመልክቶ በመቶ ሺ የሚቆጠር እንግዳ የመጣባት አክሱም የመኝታ አልጋ ዋጋዋ ሰሞኑን በሶስት እጥፍ መጨመሩ ተነገረ።

በቀን 500 ብር በመክፈል ሲታደርባቸው የነበሩ እንግዳ ማረፊያዎች 2 ሺ ብር እያስከፈሉ ሲሆን ለቀን አዳር ከሁለት እስከ ሶስት ሺ ይጠይቁ የነበሩ ሆቴሎችም እስከ ሶስት እጥፍ ድረስ ዋጋ መጨመራቸውን ፊደል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ክርስትና በኢትዮጵያ የተጀመረባት የመጀመርያዋ ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቅድስት ማርያም ናት፡፡

ሕንፃዋ የተገነባው በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክርስትናን የአክሱም መንግሥት ሃይማኖት ብሎ ካወጀው በንጉሥ ኢዛና (አብርሃ) ነው።

ቀደምት ጽሑፎች እንደሚያስነብቡት አክሱም ጽዮን ማርያም ለኢትዮጵያም ሆነ ለኤርትራ አብያተ ክርስቲያን ሁሉ መሠረታቸው ናት፡፡

በየዓመቱ ኅዳር 21 ቀን የሚከበረው የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ታላላቅ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ ነው። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ከአገር ውስጥም ሆነ ከባህር ማዶ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ አክሱም በመምጣት ያከብሩታል፡፡ ቱሪስቶችም በበዓሉ አጋጣሚ አክሱምን ይጎበኟታል፡፡

©️ፊደል ፖስት

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
14🥰1
📌አዶናይ መኪናዋን ወሰደ አሸነፈ!

የ2025 የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ የዓመቱ ምርጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቲክቶከር አዶናይ ሆኗል።

አዶናይ ትልቁን 'የዓመቱ ምርጥ ቲክቶከር ሽልማት' (Best TikTok of the Year Award) ወስዷል።

የዚህን ትልቅ ሽልማት ክብደት የበለጠ የሚያጎላው ደግሞ አዶናይ ከዋንጫው በተጨማሪም የተዘጋጀለትን የአዲስ መኪና ሽልማት ማግኘቱ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
24👎9👍4👏3💩3🤔2😢2
📌ኮሜድያን ወንደወሰን አውራሪስ አረፈ

ኮሜድያን ወንደወሰን አውራሪስ በድንገተኛ የልብ ህመም በዳግማዊ ምንልክ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ሕይወቱ አልፏል።

ትናንት "ልቤን" ብሎ ወደ ህክምና አምርቶ ነበር።

ለሊቱን ሁሉ ሕክምና እየወሰደ ከአንድም ሁለት ጊዜ አሰቸጋሪ ደረጃ እየደረሰ በሕክምና ህይወቱ ተመልሷል።

ይሁንና የአንዲት ሴት ልጅ አባት የሆነው ኮሜድያን ወንደወሰን አውራሪስ ዛሬ ማለዳ ላይ አርፏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😭22🕊4😢32
📌ዝነኛው የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን የ30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው ሪፖርተር ጋዜጣ ቢሮ በድንገት በመገኘት ለሪፖርተር መስራችና ባለቤት አቶ አማረ አረጋዊ የእንኳን አደረሰዎ መልካም ምኞቱን ገልጿል።

በኢትዮጵያ የመዝናኛ ኢንደስትሪ ውስጥ ስመ ጥር የሆነው ሰይፉ ፋንታሁን ፣ ወደዚህ ከፍታ ከመድረሱ በፊት አቶ አማረ አረጋዊ ላደረጉለት ድጋፍም ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
13🙏3
📌የአእላፋት ሳምንት ዐውደርዕይ

የአእላፋት ሳምንት የተሰኘ ዐውደ ርእይ ሊካሔድ ነው

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ከታኅሣሥ 16 - 24 2018 ዓ.ም. የሚካሔድ "የአእላፋት ሳምንት" የተሰኘ ዓመታዊ ልዩ ዐውደርዕይ ማዘጋጀቱ ተገለጸ::

በዚህ ዐውደ ርዕይ ላይ ከዐሥር በላይ ገዳማት ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችና ማኅበራት የሚሳተፉ ሲሆን የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የሚሠራባቸው ዐሥራ ስምንት ፕሮጀክቶች ኤግዚቢሽንም ይካሔዳል::

በግዮን ሆቴል ግራውንድስ በሚካሔደው በዚህ ዝግጅት ላይ ጃን ፎረም የተሰኘ የሀገር ውስጥና የውጪ ምሁራን የሚሳተፉበት በምዝገባ ታዳሚዎችን የሚያስተናግድ በልዩ ልዩ ርእሶች ዐውደ ጥናት ፣ መጽሐፍ ምርቃት ፣ ለሳምንት የሚቆይ የሕፃናት ልዩ የገና በዓል ዝግጅት እና በርካታ ክንውኖችን ያካተተ መሆኑን የኢጃት ፕሮጀክት ማናጀር  ወ/ሪት ቃልኪዳን ገልጻለች::

በአእላፋት ሳምንት ላይ ከደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና አባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ጋር በመተባበር "ኢትዮጵያዊው ነባቤ መለኮት" የተሰኘ የቅዱስ አባ ጊዮርጊስ 600ኛ የዕረፍቱ በዓል አካል የሆነ ልዩ ዐውደ ጥናትና መዘክር ይካሔዳል::

በዐውደ ርዕዩ ላይ የሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን "መድሎተ ዕቅበተ እምነት" የሆኑት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬን የሚዘክር ልዩ ጉባኤ የሚኖር ሲሆን በዕቅበተ እምነት ዙሪያም የጥናት ወረቀቶች ይቀርባሉ:: 

በዐውደ ርእዩ ዐሥራ ዐራት አርእስት ዐውደ ጥናት ፣ ትምህርታዊ ውድድሮች ፣ የቢዝነስ ኔትወርክ ሁነቶች፣ የሽልማት መርሐ ግብሮችና ልዩ ልዩ ክስተቶችም ታቅደዋል:: 

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
29🙏7👎1
📌ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ተሸለመች

ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ (ሸገር ኤፍ ኤም 102.1) የኢጋድ የህይወት ዘመን የሚዲያ ሽልማት አሸናፊ እንደሆነች ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ መስራችና ስራ አስኪያጅ መዓዛ ብሩ ሽልማቱ የተሰጣቸው የኢጋድ(IGAD) ዓመታዊ የሚዲያ ሽልማት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደበት ወቅት ነው።

ሽልማቱንም ከኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስና ከኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር ) ተቀብለዋል።

ኢጋድ በየዓመቱ በተለያዩ ዘርፎች የአባል ሀገራን የተመለከቱ ዘገባ የሰሩ ጋዜጠኞችን የሚሸልም ሲሆን ዘንድሮም የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከቱ ዘገባዎች የሰሩ ጋዜጠኞች ስራ አወዳድሮ ሸልሟል።

ሶስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (IGAD) የሚዲያ ሽልማት በስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
30👏24
📌️️ከአርቲስቶች ጋር ስራ የምትሰሩበት መድረክ ተዘጋጀ

ለስድስት ዓመታት ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ወጣቶችን ከታዋቂ አርቲስቶች ጋር እያገናኘ ሲሰራ የቆየው ፕሪስቴጅ አዲስ አሁን ደግሞ "ሲንካፕ ቻት" የተባለ ከምትወዱት እና ከምታደንቁት ታዋቂ አርቲስት ጋር ቡና እየጠጣችሁ ቆይታ የምታደርጉበትና ስለምትሰሩት ስራ የተለያዩ ምክሮችን የምታገኙበት፤የምታወሩበትን መድረክ ሊጀመር መሆኑን ኤቨንት አዲስ መረጃ ያገኘ ያመለክታል።

በመድረኩ ከምትወዱት አርቲስት ጋር መስራት አሰባችሁ ነገር ግን መንገዱን ያላገኛችሁ ሰዎች አንድ ላይ እንድትሰሩ የሚያመቻች ነውም ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
13👍3👎1
📌በአዲስ አበባ ግዙፍ የሥነጽሑፍ ፌስቲቫል ተዘጋጅ

ይህ ግዙፍ የሥነጽሑፍ ፌስቲቫል “አዲስ የስነጽሁፍ ፌስቲቫል” የተሰኘ ስያሜ ተሰጥቷል።

ዝግጅቱ ማክሰኞ ሕዳር 23 የሚጀምር ሲሆን እስከ ታህሳስ 5 2018 ዓ.ም ድረስ በከተማችን በተለያዩ ቦታዎች ይካሄዳል።

በፌስቱቫሉ የመጽሐፍ ውይይቶች ፣ የመጽሐፍ አውደርዕይ በርካታ ከመጻሕፍት ጋር የተያያዘ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ ተብሏል።

ከእነዚህ ዝግጅቶች መካከል ዝክሬ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ፣የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ እና ህትመት በሃያኛው መቶ ክፍለዘመን፣ሥነጽሑፍ እና ነገረ ሀቲታ፣አንድ ግጥም አንድ ወግ የተሰኙ ዝግጅቶች ይገኙበታል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
10
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📌2ኛው አላይቭ ማስ ስፖርት የቤተሰብ ፌስት

2ኛው Alive mass sport አብሮነት የቤተሰብ ፌስት የፊታችን ህዳር 28 ወሎ ሰፈር በሚገኘው ቃና ስቱድዮ ውስጥ በደምቀት ይካሄዳል።

ፌስቱን N4ED ከ Hawi Mass Dance ጋር አዘጋጅተውታል።

በፌስቱ ላይ አስደሳች የቤተሰብ ጨዋታዎች
ሁሉን የሚያካትት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ይኖራሉ ተብሏል።

ጤናማ ምግቦች ከጤና ምክር ጋር  በርካታ አዝናኝ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል።

እርሶም ከቤተሰብዎ ጋር ይህን ውብ ቀን ህዳር 28 ጠዋት 2:00 በቃና ስቱድዮ ይገኙ ተብለዋል።

ቲሸርቱን በቴሌብር እና በዳሽን ሱፐር አፐ ያገኙታል።በተጨማሪም ቦሌ በሚገኘው በሀርመኒ ሆቴልም እንገኛለን።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4👍1
📌በአዲስ አበባ የጣሊያን የምግብ ሣምንት ተካሄደ

የጣሊያን የንግድ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ከሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት አስረኛው የጣሊያን የምግብ ሳምንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በኢትዮጵያ የተካሄደው የጣሊያን  የምግብ ሣምንት የሁለቱን ሀገራት ወደጅነት በሚያጣናክር መልኩ ተካሂዶ እንደተጠናቀቀም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

የጣሊያን የምግብ ዝግጅት ሣምንት የጣሊያን የምግብ ባህል ያስተዋወቀ እንዲሁም ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ወዳጅነት ያሳየ እንደሆነም ተገልጿል።

ለአራት ቀናት የቆየውና በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ለአራት ቀናት የተካሄደው መርሃግብሩ  ሼፎችን፣ ተማሪዎችን፣ የመንግስት እና  የቢዝነስ ሃላፊዎችን  እንዲሁም  ዓለም አቀፍ ተወካዮችን አገናኝቷል፡፡

በአዲስ አበባ የጣሊያን ንግድ ኤጀንሲ የንግድ ኮሚሽነር ክላውዲዮ ፓስኳሉቺ "የዘንድሮው የኢጣሊያ የምግብ ዝግጅት ሳምንት የወዳጅነት እና የጋራ እሴቶች ክፍ ብለው እንዲታዩ ያስቻለ" ነው ሲሉ ተናገረዋል፡፡

የጣሊያን ሼፎችን ከኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እና ተማሪዎች ጋር በማገናኘት የባህል ዲፕሎማሲውን እንዲጠናከር አድርገናል እንዲሁም  በምግብ ጥናት እና ዝግጅት ዘርፍ አዳዲስ የትብብር ዕድሎችን ከፍተናል" ሲሉም አክለዋል፡፡ 

በኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ውስጥ፣ ተጋባዥ እንግዶች ፣ተማሪዎች  በተገኙበት የጣሊያንን ባህላዊ እና ዘመናዊ ምግቦችን የማጣጣም ዝግጅት ተካሂዷል፡፡

ታዋቂው ጣሊያናዊው ሼፍ ኤልያ ግሪሎቲ ኢትዮጵያውያን ሼፎች እና የምግብ ዝግጅት ተማሪዎች ስለ ምግብ ዝግጀት የተግባር ስልጠናዎችን እና ማሳያዎችን አቅርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
8
📌እነ ጆን ዳንኤል ከእስር ይፈቱ ተባለ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) በእስራት እንዲቀጡ ወስኖ  የታሰሩት በቂ ስለሆነ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጠ።

ተከሳሾቹ በተከሰሱበት የህግ አንቀፅ ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን ችሎቱ በዛሬው ዕለት የዐቃቤ ሕግን የቅጣት ማክበጃ እና የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ተከሶሾቹ የተከሱበት የህግ አንቀፅ ቀላል እስራትን የሚያስከትል በመሆኑ 1ኛ ተከሳሽ በአንድ አመት ከአራት ወር፤ 2ኛ፣ 3ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በስምንት ወር እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ በ10 ወር እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

በመሆኑም ተከሳሾቹ በእስር ላይ የቆዩበት ጊዜ ተሰልቶ ተከሳሾቹ እንዲፈቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ውሳኔ አሳልፏል።

©️ FBC

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
23👍5🎉5👎2
📌የደራሲ አልሳ ሙሉጌታ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

በደራሲ ኤልሳ ሙሉጌታ የተዘጋጀው "ዋናተኛ ፀሐይ" የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ አርብ ሕዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በርካታ እንግዶች በተገኙበት ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ  ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር ) ይመረቃል።

በመጽሐፉ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይ በልዩነት ወላጅ አባቷን በክብር እንግዳነት ይገኛሉ ተብሏል።

ደራሲ ኤልሳ ሙለጌታ ከዚህ ቀደም "ሐምራዊ ተረኮች" የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባቢያን ማቅረቧ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4👍4
📌ሜንታል ሄልዝ አዲስ የሥነልቦና ውይይት

ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃግብር ቅዳሜ ሕዳር 27 ቀን 2016 ዓም 6ኪሎ በሚገኘው ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ የሥነጥበብ ሙዚየም ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ  ይካሄዳል::

የዚህ ወር ርዕስም፡- “Embracing for mental health” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳ የሥነልቦና ባለሞያ ናፍቆት ወ/ጻዲቅ ናቸው፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍6