Event Addis Media
9.6K subscribers
6.06K photos
12 videos
4 files
4.68K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ኦዳ አዋርድ ሕዳር 30 ይካሄዳል

የዘንድሮው ኦዳ አዋርድ የሽልማት እና የእውቅና የመስጠት ሥነሥርዓት የፊታችን ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በድምቀት ይከናወናል፡፡

ኦዳ አዋርድ ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ በሚያዘጋጀው የሽልማት መርሃግብር ከቀደምት ዓመት ውድድሮች ለየት ባለ መልኩ በመቅረብ ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ በሙዚቃው ዘርፍ ላይ ብቻ በማተኮር የሽልማት ስነስርዓቱን እንደሚያከናውን ተነግሯል።

በመሆኑም በሙዚቃው ዘርፍ ብቻ ከሀገር ውስጥ 30 እጩዎችን በ6 የሽልማት ዘርፎች ለምርጫ ያቀረበ ሲሆን ከሀገር ውስጥ እጩዎች በተጨማሪ ከ12 አፍሪካ ሃገራት የተወጣጡ እጩዎችን ለህዝቡ ይፋ ያደርጋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም እጩዎች ለሽልማት የሚበቁት ሙሉ በሙሉ በህዝብ ምርጫ መሆኑ ተገልጿል።

ከአፍሪካ ሃገራት በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ በ"AFRICAN SUPER STAR” ዘርፍ ላይ ተሸላሚ ለመሆን የሚሳተፉት 12 የአፍሪካ ሃገራት፦ ሩዋንዳ፣ ማሊ፣ ሞሮኮ፣ አንጎላ፣ ማዳጋስካር፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሲሼልስ፣ ጋና፣ ቶጎ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ ናቸው።

በተጨማሪም 9ኛው ኦዳ አዋርድ ከሃገር ውስጥ የሙዚቃ ስራዎች ለሽልማት እጩዎችን የሚያቀርብበት ስድስት ዘርፎች ሲኖሩት እነሱም፡- የህይወት ዘመን ተሸላሚ፣የአመቱ ምርጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ አርቲስት፣የአመቱ ምርጥ ቪዲዮ ክሊፕ፣የአመቱ ምርጥ ሴት ድምፃዊት፣የአመቱ ምርጥ ወንድ ድምፃዊ፣የአመቱ ምርጥ ምርጥ ሀገርኛ ዘፋኝ ናቸው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3👍3
📌የደጃፍ ፖድካስት ምዕራፍ 4 በቅርቡ ይጀመራል

በዳዊት ተስፋዬ የሚዘጋጀውና በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው "ደጃፍ ከዳዊት ተስፋዬ ጋር" የፖድካስት ዝግጅት ምዕራፍ 4 በቅርቡ እንደሚጀምር የፖድካስቱ አዘጋጅ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
30👍10🔥5
📌ቤርሙዳ ተውኔት ዛሬ በነፃ ይቀርባል

በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፋ የተዘጋጀው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 16 2018 ዓ.ም ከ11:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ያለመግቢያ ክፍያ በነፃ እንደሚቀርብ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዘጋጁ ተሻለ አሰፍ(ዶ/ር) ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
18👍5
"ሺ ዊንስ" የተሰኘ በአይነቱ ልዩ የሆነ የእግር ኳስና የሴቶችን አቅም ማጎልበት ላይ ያተኮረ ፕሮግራም መካሄድ ጀመሯል፡፡

የኢንግሊዝ ኤምባሲ፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና ኤን ዜድ ኮምኒኬሽንስ ጋር በመሆን ለዚህ ፕሮጀክት እውንነት በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ለአምስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል በአዲስአበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ወጣት ሴቶችን በማሰባሰብ በእግር ኳስ ውድድሮች ፣በአመራርነት፣ራስን በማብቃት ላይ ስልጠና ይሰጣል በተያያዘም የስልጠና ሞጁል ለሰልጣኞች በአማርኛ ተዘጋጅቶ ተስጥቷል፡፡

አርአያ የሚሆኑ  ሴቶችም ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉ ይሆናል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ከ10ሺህ በላይ ሴቶችን ለመድረስ ታቅዷል፡፡
በዚህም የአመራር ብቃታቸው እንዲጎለብት፣ በራስ መተማመናቸው እንዲጨምር በማድረግ በግልና በስራ ህይወታቸው አዲስ በሮች እንዲከፈቱ የሚያደርግ ይሆናል።

የእግኳስ ውድድሩ ስምንት ቡድኖችን የሚያካትት ሲሆን በዚህ አሰልጣኞች ባለተሰጠኦችን እንዲለዩ የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡ ቡድኖቹ የአስፈላጊ ቁሳቁስ ልገሳ የሚደረግላቸውም ይሆናል፡፡

ለዚህም ዓላማ  ከሀገረ እንግሊዝ በ2013 ከዊጋን አትሌቲክ ጋር የኤፍ.ኤ ካፕ ሻምፒዮን በሆነው ኤመርሰን ቦይሴ የተመራ 3 ኢንተርናሽናል የአሰልጣኞች ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።

የአሰልጣኝነት ስልጠናዎችን ይካሄዳሉ፣ ከ17 አመት በታች ያሉ ወጣት ሴት ባለተሰጥኦዎችን የመለየት ስራም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ሺ ዊንስ እሷ ስታሸንፍ እኛም እናሸንፋለን በማለት በኢትዮጵያ የጾታ እኩልነት ፣ የወጣቶች አቅም መጎልበትና የሴቶች ስፖርት እድገት ቁርጠኝነት ላይ አበክሮ ይሰራል፡፡
 
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
2👍1
📌 በ50 ብር 50 ፊልሞችን ይመልከቱ

የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል መካሄድ ጀምሯል።

በዚህ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የፌስቲቫሉ ዳይሬክተር ይርጋሸዋ ተሾመ ባስተላለፉት መልዕክት የዘንድሮው ፌስቲቫል"50 ፊልም፣በ50 ብር" በሚል መርሐግብር የሚሰናዳ ሲሆን፣ አንድ ሰው በ50 ብር ከቴሌ ብርና ዳሽን ሱፐር አፕ በሚቆርጠው አንድ ቲኬት ብቻ 50 ፊልሞችን መመልከት የሚችልበት ምቹ የጥበብ ድግስ ነው፡፡

በፌስቲቫሉ ላይ ከሚሳተፉ ፊልሞች መካከል ቀንጃ፣ጀቢና፣ ማንዘንድ፣ዳናሽ ፣እንዴት ልሁን ገመሀልያ ፣ ታስፈልገኛለህ ፣ጭረት ፣አለሁ፣የቀለም ጨዋታ፣ከባድ ማፍያ ፣ሣማ
እና ቀያይ ቀምበጦች ናቸው ።

ፊልሞችን መመልከት የሚፈልጉ ተመልካቾች ፍላሚጎ በሚገኘው አዲሱ የህፃናትና ወጣቶች አርት ኮምፕሌክስ በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
7👍2
📌የልጆች ንባብ ፌስቲቫል በድሬድዋ!

ኢትዮጵያ ሪድስ ከፈረንሳይ ኤምባሲና ከአሊያንስ ኢትዮ- ፍራንሲስ ጋር በመተባበር እንደ ከ ዚህ በፊቱ  የልጆች ንባብ ፌስቲቫል በድሬደዋ ከተማ አካሄደ ፡፡

"የልጆች ንባብ ላይ እና ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ በማተኮር የተሻለ ትውልድ እንፍጠር " በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀናት አሊያንስ-ኢትዮ ፍራንሲስ ድሬደዋ ግቢ ዉስጥ የተካሄደው የልጆች ንባብ ፌስቲቫል በልዩ ልዩ ሁነቶች የደመቀ ሲሆን ልጆች በታዋቂዋ አለም ጸሃይ ወዳጆ የተጻፈዉን ጣይቱ ብጡል የተሰኘውን መጽሃፍ ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ መጥሃፍትን በማንበብ ፣ ያነበቡትን መልሶ በመተረክ እና በመወያየት፣ሥዕል በመሳል ፣ ተረት እን የተለያዩ ታሪኮችን በማድመጥ ፣ ግጥም በማንበብ ፣ የጥያቄ እና መልስ ውድድር በማድረግ እና በተለያዩ ንባብን በሚያበረታቱ እና በሚያዝናኑ ክንዋኔዎች አሳልፈዋል፡፡

አሸናፊ ተማሪዎች የተለያዩ መጽሃፍቶችን በአሊያንስ ድሬዳዋ እና በኢተዮጵያ ሪድስ ተሸልመዋል፡፡

በቦታው ከ10 የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የልጆች ካራክተር የሰራው ታዋቂው ኮሜዲያን አስረስ በቀለ ልጆችን እንዲያነቡ የሚመክር እና የሚያዝናኑ ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን አቅርቧል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5
📌"ላለመኖር መወለድ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በደራሲ ጥበቡ አወቀ የተጻፈው "ላለመኖር መወለድ" የተሰኘ ልቦለድ መጽሐፍ ዛሬ ሕዳር 17 2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ለአንባቢያን ቀርቧል።

"ላለመኖር መወለድ" መጽሐፍ ረጅም ልቦለድ ሲሆን በ162 ገፆች ተቀንብቦ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለገበያ ቀርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍13🥰1
📌"በያይነት" የኪነጥበብ ዝግጅት

"በያይነት" የተሰኘ የኪነጥበብ ዝግጅት የፊታችን ሐሙስ ሕዳር 18 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ  ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አሸናፊ ከበደ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዝግጅቱ ላይ ግጥም፣ ወግ፣ሙዚቃ፣ ሞኖሎግ፣መልቲሚዲያ ቴአትር፣ ላይቭ ፔንቲንግ ይቀርባሉ።

ድምፃዊ አረጋኸኝ ወራሽ፣ አርቲስት ዳንኤል ተገኝ እንዲሁም ሰአሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን የክብር እንግዳ በመሆን ተገኝተው ልምዳቸውን ያካፍላሉ። 

ዝግጅቱ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቴአትር እና ፊልም ጥበባት ፣ የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት እና የአለ ስነ የጥበብ እና ዲዛይን ተማሪዎች የተዘጋጀ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
10👍3
📌የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን "ያለፈውን በማክበር የተሻለ ነገን ማለም" በሚል መሪ ቃል እያከበረ ነው።

ባለ ብዙ ታሪኩ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 75 አመታት በብዙ ዘርፎች በርካታ ምሁራንን አበርክቷል::

ዩኒቨርስቲው የሚያከብረውን የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን የስፖርት ውድድር፣ የአካዳሚክ ሴሚናሮች፤ የፓናል ውይይቶች፣ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች፣ የቤተሰብና የአጋሮች ቀንን ጨምሮ በተለያዩ ሁነቶች እንደሚያከበር ተጠቁሟል።

ዩኒቨርሲቲው በዓለም ውስጥ ላሉት የዕውቀት ልጆች 75ኛ አመት የአልማዝ እዮቤልዩ በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ ጥሪ ቀርቧል::

ተማሪዎቹ ከታህሳስ 18-24 ወደ እውቀት ቤታቸው እንዲመጡ ተጋብዘዋል::

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
14
📌አዶናይ ከአየር ኃይል ማስጠንቀቂያ ተሰጠው

ቲክቶከር አዶናይ ከሰሞኑ የአየር ሀይል አባላትን ሰግጡ በማለት ቦታዉ ድረስ ሔዶ ንግግር ማድረጉን ተከትሎ በጋበዙት አመራሮች ላይ ምርመራ ተጀምሯል።

ቲክቶከሩም ከአየር ሀይሎች ጋር ያደረገውን የንግግር ቪዲዮና ምስል ከማህበራዊ ገጾቹ እንዲያወርድም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁40👏117🤣6🤔4🕊1
📌"የኔ ቆንጆ ኑሪ" በሚለው ዘፈኑ የሚታወቀው አብርሃም አየለ ሙሉ የዘፈን አልበም ሊለቅ እንደሆነ ሀገር ይወቅልኝ አለ።

አብርሃም አየለ የሚለቀው አልበም ከ4 ሚሊየን ብር በላይ እንደፈጀ የተናገረ ሲሆን ይህ "ዱዳሌብ" የተሰኘ የዘፈን አልበም የፊታችን ማክሰኞ ህዳር 23 እንደሚለቀቅም አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣29😭9👍32😱1
📌ጣና ነሽ ፪ ጀልባ አገልግሎት መስጠት ጀመረች

በመጨረሻም ጣና ነሽ ፪ ጀልባ የመጀመሪያውን የመንገደኞች ማጓጓዝ ስራዋን ከባሕር ዳር ወደ ደልጊ እና ደቅ በማድረግ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀምራለች።

188 ተሳፋሪዎችን የማጓጓዝ አቅም ያላት ጣናነሽ ፪ በአስደማሚው የጣና ሐይቅ የተፈጥሮ ከባቢ የሚደረገውን ጉብኝት እና ወደ ጎርጎራ ኢኮ ሎጅ የሚደረገውን ጉዞ ይበልጥ ምቹ አድርጋው ሰንብታለች።

አሁን ደግሞ ጣና ነሽ ፪ ጀልባ የመጀመሪያውን የመንገደኞች ማጓጓዝ ከባሕር ዳር ወደ ደልጊ እና ደቅ በማድረግ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሯን የክልሉ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍62😁1🙏1