Event Addis Media
9.6K subscribers
6.06K photos
12 videos
4 files
4.68K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌 "ቢራቢሮ "የተሰኘ ተውኔት ለእይታ ሊበቃ ነው

በደራሲ ኤልያስ ቤተማርያም ተጽፎ በዘካርያስ ረታ የተዘጋጀው "ቢራቢሮ" የተሰኘ ተውኔት የፊታችን ረቡዕ ህዳር 17 ከ11:30 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር ይቀርባል።

በተውኔቱ ላይ ሩሐማ ኃ/ሚካኤል ፣ ዮናታን መኮንን፣ እየሩሳሌም ገ/ስላሴና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።

የተወኔቱ ሚውዚክ ዳይሬክተር ዮሐንስ አማረ ሲሆን የፕሮዳክሽን ማናጀሮች ሀና ታዬ(እርጎዬ) እና ሔኖክ ተሾመ ናቸው።

ተውኔቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራተኛ አመት የቴአትር ጥበባት ተማሪዎች የተዘጋጀ ነው።

"ቢራቢሮ" ተውኔት ባለፈው ዓመት ሰኔ 23 ብሔራዊ ቴአትር ቤት ለተመልካች ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5🥰1
📌"ውብ አዲስ" የሥነጥበብ አውደርዕይ ተከፈተ

"ውብ አዲስ" የተሰኘ የሥነጥበብ አውደርዕይ በዚህ ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ጎላ የሥነጥበብ ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል።

"ውብ አዲስ" በሚል ርዕስ ፣ትኩረቱን በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያደረገው ይህ አውደርዕይ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓመት ውስጥ ሶስት ተከታታይ (ከህዳር-2018 እስከ ህዳር-2019) የሚቀረብ የግል የሥዕል ትርዒት ነው።

ይህ በዓመቱ ውስጥ በተከታታይ የሚቀርብ የሥዕል አውደርዕይ በሠዓሊ ሀሮን የተዘጋጀ ነው።

አውደርዕው ከህዳር 11 እስከ ህዳር 22 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5👍1
📌የኤፍ.ኤ ካፕ ዋንጫ ወደ ኢትዮጵያ መጣ !

የብሪትሽ ኤንባሲ ከአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና ኤን ዜድ ኮምኒኬሽንስ ጋር በጋራ በመሆን "ሺ ዊንስ" በሚለው ፕሮጀክቱ በቀጣይ ሳምንት ለእግር ኳስ አሰልጣኞች(ሴቶች) ስልጠና ለመስጠት ቀጠሮ ተይዟል።

"ሺ ዊንስ" ወጣት ሴቶችን በስፖርት ለማብቃት የተነደፈ ተነሳሽነት ነው። በዚህ መርሃግብር መሰረት ታዋቂ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ጨምሮ የበጎ ፍቃደኛ አሰልጣኞች የልዑካን ቡድን አዲስ አበባን በመጎብኘት የአሰልጣኝነት ስልጠናዎችን በማካሄድ፣ ከዓለም አቀፍ አሰልጣኞች ጋር የእግር ኳስ ውድድርን በመምራት፣ ከ17 አመት በታች ያሉ ወጣት ሴት ተሰጥኦዎችን በመለየት እና የስፖርት ትጥቅ ለሚፈልጉ ሴቶች ያስረክባል፣ ስልጠናም ይሰጣል።

ለዚህም ዓላማ  ከሀገረ እንግሊዝ በ2013 ከዊጋን አትሌቲክ ጋር የኤፍ.ኤ ካፕ ሻምፒዮን በሆነው ኤመርሰን ቦይሴ የተመራ 3 ኢንተርናሽናል የአሰልጣኞች ቡድን ዛሬ እሁድ ህዳር 14 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ወደ አዲስ አበባ ገብቷል።

ከእንግሊዝ ሀገር የሚመጡት ባለሙያዎች ተወዳጁን የኤፍ.ኤ ካፕ ዋንጫን ይዘውም ገብተዋል።

በዚህ መርሐግብር ላይ ለመሳተፍ
👉https://nz-events.vercel.app/rsvp
7😁6
በኮሪደር ልማቱ ወንበሮች ላይ ልብስ ያሰጡ ተቀጡ

በኮሪደር ልማት ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም ላይ እርምጃ ተወሰደ

ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም  በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13  በኮሪደር ልማት በተሰሩ የህዝብ ማረፊያ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ።

ድርጊቱን ፈጽመው የተገኙ  የኮሪደር ልማቱ  የመዝናኛ ካፌ እና ሰራተኞቹን ወደ ህግ በማቅረብ ተጠያቂ በማድረግ ካፌው ተገቢው ቅጣት አስኪቀጣ መታሸጉ ተገልጿል።

ህብረተሰቡ በከተማዋ ውስጥ  በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ የኮሪደር ልማቶችና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ መገልገልና መጠቀም እንደሚገባም አስታውቋል፡፡

ደንብ ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለስልጣኑ አስታውቋል ሲል ኤኤምኤን ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣465👏4
📌ኦዳ አዋርድ ሕዳር 30 ይካሄዳል

የዘንድሮው ኦዳ አዋርድ የሽልማት እና የእውቅና የመስጠት ሥነሥርዓት የፊታችን ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በድምቀት ይከናወናል፡፡

ኦዳ አዋርድ ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ በሚያዘጋጀው የሽልማት መርሃግብር ከቀደምት ዓመት ውድድሮች ለየት ባለ መልኩ በመቅረብ ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ በሙዚቃው ዘርፍ ላይ ብቻ በማተኮር የሽልማት ስነስርዓቱን እንደሚያከናውን ተነግሯል።

በመሆኑም በሙዚቃው ዘርፍ ብቻ ከሀገር ውስጥ 30 እጩዎችን በ6 የሽልማት ዘርፎች ለምርጫ ያቀረበ ሲሆን ከሀገር ውስጥ እጩዎች በተጨማሪ ከ12 አፍሪካ ሃገራት የተወጣጡ እጩዎችን ለህዝቡ ይፋ ያደርጋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም እጩዎች ለሽልማት የሚበቁት ሙሉ በሙሉ በህዝብ ምርጫ መሆኑ ተገልጿል።

ከአፍሪካ ሃገራት በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ በ"AFRICAN SUPER STAR” ዘርፍ ላይ ተሸላሚ ለመሆን የሚሳተፉት 12 የአፍሪካ ሃገራት፦ ሩዋንዳ፣ ማሊ፣ ሞሮኮ፣ አንጎላ፣ ማዳጋስካር፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሲሼልስ፣ ጋና፣ ቶጎ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ ናቸው።

በተጨማሪም 9ኛው ኦዳ አዋርድ ከሃገር ውስጥ የሙዚቃ ስራዎች ለሽልማት እጩዎችን የሚያቀርብበት ስድስት ዘርፎች ሲኖሩት እነሱም፡- የህይወት ዘመን ተሸላሚ፣የአመቱ ምርጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ አርቲስት፣የአመቱ ምርጥ ቪዲዮ ክሊፕ፣የአመቱ ምርጥ ሴት ድምፃዊት፣የአመቱ ምርጥ ወንድ ድምፃዊ፣የአመቱ ምርጥ ምርጥ ሀገርኛ ዘፋኝ ናቸው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3👍3
📌የደጃፍ ፖድካስት ምዕራፍ 4 በቅርቡ ይጀመራል

በዳዊት ተስፋዬ የሚዘጋጀውና በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው "ደጃፍ ከዳዊት ተስፋዬ ጋር" የፖድካስት ዝግጅት ምዕራፍ 4 በቅርቡ እንደሚጀምር የፖድካስቱ አዘጋጅ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
30👍10🔥5
📌ቤርሙዳ ተውኔት ዛሬ በነፃ ይቀርባል

በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፋ የተዘጋጀው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 16 2018 ዓ.ም ከ11:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ያለመግቢያ ክፍያ በነፃ እንደሚቀርብ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዘጋጁ ተሻለ አሰፍ(ዶ/ር) ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
18👍5
"ሺ ዊንስ" የተሰኘ በአይነቱ ልዩ የሆነ የእግር ኳስና የሴቶችን አቅም ማጎልበት ላይ ያተኮረ ፕሮግራም መካሄድ ጀመሯል፡፡

የኢንግሊዝ ኤምባሲ፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና ኤን ዜድ ኮምኒኬሽንስ ጋር በመሆን ለዚህ ፕሮጀክት እውንነት በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ለአምስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል በአዲስአበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ወጣት ሴቶችን በማሰባሰብ በእግር ኳስ ውድድሮች ፣በአመራርነት፣ራስን በማብቃት ላይ ስልጠና ይሰጣል በተያያዘም የስልጠና ሞጁል ለሰልጣኞች በአማርኛ ተዘጋጅቶ ተስጥቷል፡፡

አርአያ የሚሆኑ  ሴቶችም ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉ ይሆናል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ከ10ሺህ በላይ ሴቶችን ለመድረስ ታቅዷል፡፡
በዚህም የአመራር ብቃታቸው እንዲጎለብት፣ በራስ መተማመናቸው እንዲጨምር በማድረግ በግልና በስራ ህይወታቸው አዲስ በሮች እንዲከፈቱ የሚያደርግ ይሆናል።

የእግኳስ ውድድሩ ስምንት ቡድኖችን የሚያካትት ሲሆን በዚህ አሰልጣኞች ባለተሰጠኦችን እንዲለዩ የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡ ቡድኖቹ የአስፈላጊ ቁሳቁስ ልገሳ የሚደረግላቸውም ይሆናል፡፡

ለዚህም ዓላማ  ከሀገረ እንግሊዝ በ2013 ከዊጋን አትሌቲክ ጋር የኤፍ.ኤ ካፕ ሻምፒዮን በሆነው ኤመርሰን ቦይሴ የተመራ 3 ኢንተርናሽናል የአሰልጣኞች ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።

የአሰልጣኝነት ስልጠናዎችን ይካሄዳሉ፣ ከ17 አመት በታች ያሉ ወጣት ሴት ባለተሰጥኦዎችን የመለየት ስራም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ሺ ዊንስ እሷ ስታሸንፍ እኛም እናሸንፋለን በማለት በኢትዮጵያ የጾታ እኩልነት ፣ የወጣቶች አቅም መጎልበትና የሴቶች ስፖርት እድገት ቁርጠኝነት ላይ አበክሮ ይሰራል፡፡
 
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
2👍1
📌 በ50 ብር 50 ፊልሞችን ይመልከቱ

የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል መካሄድ ጀምሯል።

በዚህ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የፌስቲቫሉ ዳይሬክተር ይርጋሸዋ ተሾመ ባስተላለፉት መልዕክት የዘንድሮው ፌስቲቫል"50 ፊልም፣በ50 ብር" በሚል መርሐግብር የሚሰናዳ ሲሆን፣ አንድ ሰው በ50 ብር ከቴሌ ብርና ዳሽን ሱፐር አፕ በሚቆርጠው አንድ ቲኬት ብቻ 50 ፊልሞችን መመልከት የሚችልበት ምቹ የጥበብ ድግስ ነው፡፡

በፌስቲቫሉ ላይ ከሚሳተፉ ፊልሞች መካከል ቀንጃ፣ጀቢና፣ ማንዘንድ፣ዳናሽ ፣እንዴት ልሁን ገመሀልያ ፣ ታስፈልገኛለህ ፣ጭረት ፣አለሁ፣የቀለም ጨዋታ፣ከባድ ማፍያ ፣ሣማ
እና ቀያይ ቀምበጦች ናቸው ።

ፊልሞችን መመልከት የሚፈልጉ ተመልካቾች ፍላሚጎ በሚገኘው አዲሱ የህፃናትና ወጣቶች አርት ኮምፕሌክስ በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
7👍2
📌የልጆች ንባብ ፌስቲቫል በድሬድዋ!

ኢትዮጵያ ሪድስ ከፈረንሳይ ኤምባሲና ከአሊያንስ ኢትዮ- ፍራንሲስ ጋር በመተባበር እንደ ከ ዚህ በፊቱ  የልጆች ንባብ ፌስቲቫል በድሬደዋ ከተማ አካሄደ ፡፡

"የልጆች ንባብ ላይ እና ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ በማተኮር የተሻለ ትውልድ እንፍጠር " በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀናት አሊያንስ-ኢትዮ ፍራንሲስ ድሬደዋ ግቢ ዉስጥ የተካሄደው የልጆች ንባብ ፌስቲቫል በልዩ ልዩ ሁነቶች የደመቀ ሲሆን ልጆች በታዋቂዋ አለም ጸሃይ ወዳጆ የተጻፈዉን ጣይቱ ብጡል የተሰኘውን መጽሃፍ ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ መጥሃፍትን በማንበብ ፣ ያነበቡትን መልሶ በመተረክ እና በመወያየት፣ሥዕል በመሳል ፣ ተረት እን የተለያዩ ታሪኮችን በማድመጥ ፣ ግጥም በማንበብ ፣ የጥያቄ እና መልስ ውድድር በማድረግ እና በተለያዩ ንባብን በሚያበረታቱ እና በሚያዝናኑ ክንዋኔዎች አሳልፈዋል፡፡

አሸናፊ ተማሪዎች የተለያዩ መጽሃፍቶችን በአሊያንስ ድሬዳዋ እና በኢተዮጵያ ሪድስ ተሸልመዋል፡፡

በቦታው ከ10 የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የልጆች ካራክተር የሰራው ታዋቂው ኮሜዲያን አስረስ በቀለ ልጆችን እንዲያነቡ የሚመክር እና የሚያዝናኑ ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን አቅርቧል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5
📌"ላለመኖር መወለድ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በደራሲ ጥበቡ አወቀ የተጻፈው "ላለመኖር መወለድ" የተሰኘ ልቦለድ መጽሐፍ ዛሬ ሕዳር 17 2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ለአንባቢያን ቀርቧል።

"ላለመኖር መወለድ" መጽሐፍ ረጅም ልቦለድ ሲሆን በ162 ገፆች ተቀንብቦ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለገበያ ቀርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍13🥰1
📌"በያይነት" የኪነጥበብ ዝግጅት

"በያይነት" የተሰኘ የኪነጥበብ ዝግጅት የፊታችን ሐሙስ ሕዳር 18 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ  ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አሸናፊ ከበደ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዝግጅቱ ላይ ግጥም፣ ወግ፣ሙዚቃ፣ ሞኖሎግ፣መልቲሚዲያ ቴአትር፣ ላይቭ ፔንቲንግ ይቀርባሉ።

ድምፃዊ አረጋኸኝ ወራሽ፣ አርቲስት ዳንኤል ተገኝ እንዲሁም ሰአሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን የክብር እንግዳ በመሆን ተገኝተው ልምዳቸውን ያካፍላሉ። 

ዝግጅቱ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቴአትር እና ፊልም ጥበባት ፣ የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት እና የአለ ስነ የጥበብ እና ዲዛይን ተማሪዎች የተዘጋጀ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
10👍3