Event Addis Media
9.6K subscribers
6.06K photos
12 videos
4 files
4.68K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ዛሬ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ቀን ነው

የዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ቀን በየዓመቱ በጎርጎሮሳዊያኑ የጊዜ ቀመር November 19 ይከበራል።

ጋዜጠኝነት ዜና እና መረጃን የመሰብሰብ፣ የማጣራት፣ የመተንተን እና ለህዝብ የማቅረብ ተግባር ወይም ሙያ ነው።

ጋዜጠኞች በሥልጣን ላይ ያሉትን ተጠያቂ በማድረግ እና ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመስጠት በህብረተሰቡ ውስጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ በሃሳብ ደረጃ ይታመናል።

ጋዜጠኝነት እውነትን የማወቅ ፍላጎትና ጉጉት ነው። ጋዜጠኝነት ታማኝነትን የተላበሰ ሙያ ነው። በስራው ታማኝ እና ስነ ምግባር ያለው፥ ሁል ጊዜም እውነትን ለመናገር የሚጥር ነው ጋዜጠኛ የሚባል ጋዜጠኛ።

ጋዜጠኝነት ፅናት ነው። ጽኑ መሆንንና ቆራጥነትን ያዘለ፥ ከፍራቻ የፀዳ፤ ገለልተኛነትን የተላበሰ ነው ጋዜጠኝነት።

ከአድሎ መንፃት፤ የርህራሄ ተምሳሌት መሆን፤ ተጨባጭነት፤ አሳማኝና ምክንያታዊ መሆን ነው ጋዜጠኝነት።

ጋዜጠኝነት ነፃነት ነው። ራሱን የቻለ እና በውጫዊ ጫናዎች እና ፍላጎቶች ተጽእኖ ስር አለመውደቅ ነው ጋዜጠኝነት።

የመረጃ ምንጮችን ሚስጥራዊነት ማክበር፤ ለተጠያቂነት ራስን ማዘጋጀት፤ ለተሰራው ስራ ተጠያቂ መሆን፤ ስህተትን ለማረም እና ለስህተት ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ መሆን ነው ትክክለኛ ጋዜጠኝነት።

እናም ከላይ የተነሱ ሀሳቦችን በጥቂቱ የምታሟሉ ጋዜጠኞች፥ እንኳን ለቀናችሁ አደረሳችሁ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
26👍8🥰1
📌አሻም ቲቪ 22 በሚሆኑ ሰራተኞቹ ተከሰሰ

አሻም ቴሌቪዥን ብዛታቸው 22 በሚሆኑ ሰራተኞቹ አማካይነት ክስ የተመሰረተበት ሲሆን፣ በዚሁም ሂደት የድርጅቱ ንብረቶች ሙሉ በሙሉ እንዳይንቀሳቀሱ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ዕግድ እንደተላለፈበት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል። ምንጮቹ አክለውም፣ ለጣቢያው ጋዜጠኞች የሶስት ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈለ አመልክተዋል። በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁኑ ሰዓት ድረስ፣ አሻም ቲቪ የሰጠው ይፋዊ ማብራሪያ የለም።

ከዚህ ቀደም የጣቢያው ቢሮ መታሸጉ የሚታወስ ሲሆን፣ ጣቢያውን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው አሻም ትሬዲንግ የእሸጋ ተግባሩ "ጣቢያውን ወደ መደበኛ ስራው ለመመለስ ከሚደረጉ ጥረቶች" ጋር አስተሳስሮ ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

©️ሚኪያስ ጥላሁን

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4👍3😱3🤔1🕊1
📌‘Crazy Day’፣ ‘Valentine Day’ እና ሌሎች ‘መጤ ባህሎች’ በትምህርት ቤቶች የሚከለክል አዲስ ደንብ መዘጋጀቱ ተገለፀ

ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታውቋል።

ይህ ደንብ ከኢትዮጵያውያን ወግና ልማድ ጋር ይቃረናሉ ተብለው የተለዩ የውጭ ባህላዊ ልማዶችን ጨምሮ፣ እየጨመረ የመጣውን አዋኪ ጉዳዮች ለመግታት ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

የደንቡ ዋና ዓላማ በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ጉዳዮችን በመከላከል፣ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀና ግብረ-ገብነትን የተላበሰ ብቁ ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል ነው።

ደንቡ የኢትዮጵያውያንን ባህልና ወግ የሚቃረኑ ተብለው በግልጽ የተዘረዘሩ አሉታዊ መጤ ድርጊቶችንና ክብረ በዓላትን በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መፈጸም ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።

የሀገሪቷን ባህልና ወግ ይቃረናል ከተባሉት ድርጊቶች ዉስጥ Crazy Day፣ Gentle Day ፣ Olds Day፣  Valentine Day፣ Color Day፣ Pyjama Day የሚሉት ይገኙበታል።

የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እስከ 150,000 ብር ቅጣት በአዲሱ ደንብ ይጠብቃቸዋል ተብሏል።

©️ ዘገባው የካፒታል ጋዜጣ ነው

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍369👎5🤣5👏4🤡1
የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ ሰሎሞን ገብረስላሴ  አረፉ

ከብስራተ ወንጌል ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ሬድዮ በልጆች ፕሮግራም  አዘጋጅነታቸው የሚታወቁት ጋሽ ሰሎሞን ገብሥላሴ ዛሬ ህዳር 12 2018 በ83 ዓመታቸው  ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ለተወዳጅ ሚድያ ዝግጅት ክፍል ተናግረዋል።

አቶ ሰለሞን ከልጆች ፕሮግራም በተጨማሪ ሰዎችና ስራዎቻቸው ፤ ህብረተሰባችን እንዲሁም ባህላዊ ሙዚቃዎቻችን የተባሉ ፕሮግራሞችን በዋና አዘጋጅነት ሰርተዋል ፡፡

በኢትዮጵያ ሬዲዮ ከፕሮግራም አዘጋጅነት እስከ ዋና አዘጋጅነት በተጨማሪም የብሄራዊ ሬዲዮ የአማርኛ ፕሮግራም ተጠባባቂ ሃላፊ እንዲሁም የምስራች ድምጽ አለም አቀፍ አገልግሎት ሃላፊ ሆነው በ1986 በጡረታ እስከተሰናበቱበት ድረስ ለ40 ዓመታት ለሙያቸው ታማኝ ሆነው አገልግለዋል፡፡

በጡረታ ከተገለሉ  በኃላም እንደገና ወደ ሙያው ተመልሰው በምስራች ድምፅ ተዘጋጅቶ ከደቡብ አፍሪካ በሚተላለፈው ተመሳሳይ ይዘት ባለው ፕሮግራም በዋና አዘጋጅነት ሰርተዋል ።

የምስራች ድምፅን ደርግ ሲወርሰውና አንዳንድ ጋዜጠኞች ከስራ ሲሰናበቱ አቶ ሰለሞን በስራቸው እንዲቀጥሉ ተደርጎ ነበር ፡፡

በጋዜጠኝነት ሙያቸውም በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅ ከመሆናቸውም በላይ ታዋቂ ጋዜጠኞችንና በሚድያ እና በኪነ-ጥበቡ መስክ ተሰማርተው እናት ሀገራቸውን በማገልገል ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችንም ያፈሩ አንጋፋ ጋዜጠኛ ነበሩ።እመቤት ወ/ገብርኤል፣ ብርሃኑ ገ/ማርያም፣ አስካለ ተስፋዬ፣ ዓለም አታፋረደው፣ አማረች ሙሉ ይገኙበታል።

አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ ለሀገርና ለህዝብ ላከናወኑት ተግባር በሚዲያና ጋዜጠኝነት ዘርፍ የ10ኛውን የበጎ ሰው ሽልማት ተቀብለዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5😢5🙏2🫡2🤔1💔1
📌የውበት ሠሌዳ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ "የውበት ሰሌዳ" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ቅዳሜ ህዳር 13 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 10:00 ጀምሮ በጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

በዕለቱም ጸሐፌተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮተ መዋዕለ ፣ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል፣ መራሔ ተውኔት ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ፣ የዝና ወርቁ አርቲስት ስዩም ተፈራ በክብር እንግድነት ይገኛሉ ተብሏል።

ገጣሚያኑ ሰለሞን ሳህለ፣ዋሲሁን በላይ፣ ፌቤን ፋንጮ ሌሎችም የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

"የውበት "በ115 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን
43 ግጥሞችን በውስጡ ይዟል በ350 የጀርባ ዋጋም ለአንባቢያን ቀርቧል።

ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም "የቃል ሠሌዳ" እና "የጊዜ ሰሌዳ"  የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3👍2🔥2🥰1
📌አጫጭር ፊልሞች ላይ ያተኮረ ሙያዊ ውይይት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል አጫጭር ፊልሞች ላይ ያተኮረ ሙያዊ ውይይት አሰናድቷል፡፡

ውይይቱ ቅዳሜ ህዳር 13/2018 ዓ.ም ከ8 ሰዓት ጀምሮ በአካዳሚው ቅጥር ግቢ ይካሄዳል፡፡

አንጋፋው የፊልም ባለሙያ ብርሃኑ ሽብሩ በቀረቡት ፊልሞች ላይ ሙያዊ ዳሰሳውን ያቀርባል፡፡

ዝግጅቱ የአለ ስነጥበብና ዲዛይን ትምሕርት ቤት እና የልቀት ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች በሰሯቸው አጫጭር ፊልሞች ያተኩራል፡፡

በተጨማሪም ህዳር 11 እና 12 ከ8፡00– 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከ3፡00 – 8፡00 በአካዳሚው አዳራሽ ለዕይታ ይቀርባሉም ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5🔥1
📌የያንጎ ኢትዮጵያ የመንገድ ደኅንነት ሥልጠና

ያንጎ ኢትዮጵያ የመንገድ ደኅንነት ሥልጠና እና የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና መስጠት ጀመረ

የዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ ያንጎ ግሩፕ አካል የሆነውና በጂቱጂ አይቲ ሶሊውሽን አ.ማ. እና በኤለጋንስ ኢምፖርት ኤንድ ኤክስፖርት ፒኤልሲ ሥር የሚተዳደረው ያንጎ ኢትዮጵያ፣ ለደኅንነት፣ ለአገልግሎት ልህቀት እና ቅልጥፍና እንዲሁም ለማኅበረሰብ ተሳትፎ ያለውንቁርጠኝነት በማጠናከር የመንገድ ደኅንነት ፕሮግራም እና የመጀመሪያ እርዳታ እና የአገልግሎት ልህቀት ሥልጠና መርሐግብር ለአጋር አሽከርካሪዎች መስጠት ጀምሯል፡፡

“ያንጎ ኬርስ”በተሰኘው የማኅበራዊ ድጋፍ አገልግሎት ስር የተጀመረው ይህተነሣሽነት፣ የኩባንያው ትኩረት ይበልጥ ደኅንነታቸው በተጠበቁ መንገዶች፣ በጠንካራ ማኅበረሰቦች እና ለተሳፋሪዎች ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡

የሥልጠናው ክፍለ ጊዜ፣ አጋር አሽከርካሪዎች የመንገድደኅንነት ግንዛቤ እና ተግባራዊ የመጀመሪያ ህክምናክህሎቶችን እንዲታጠቁ በማድረግና የተሳፋሪዎችን ልምድበማጎልበት- በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰፊው ሕዝባዊደኅንነት አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።

ተጨማሪውን ያንብቡ:https://sl1nk.com/m4IWs
2
📌 "ማስተዋል"  ኮንሰርት ዛሬ ይካሄዳል

የድምጻዊ ማስተዋል እያዩ "ማስተዋል" የሙዚቃ ኮንሰርት ዛሬ ህዳር 13 2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

በዚህ ኮንሰርት ላይ ከማስተዋል እያዩ ባሻገር ድምጻዊት ሔዋን ገብረወልድ የሙዚቃ ስራዋን ታቀርባለች ተብሏል።

የራሱን ነጠላ ዜማዎች ጨምሮ የተለያዩ ድምፃዊያን ሙዚቃዎችን ማለፊያ በሚባል ሁኔታ ሲጫወተው የቆየው ድምጻዊ ማስተዋል በ2016 ዓ.ም የካቲት 1 ነበር "እንዚራ" ሲል የሰየወመውን የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጮች ያቀረበው። ይህም አልበሙም በበርካቶች ዘንድ ተወዶለታል።

አልበሙ ለአድማጮች ከቀረበ 1 ዓመት ከስምንት ወር የቆየው ሲሆን የሙዚቃ ኮንሰርትም ሳይዘጋጅለት ቆይቷል።

የድምጻዊው አድናቂዎቹም የማስተዋል እያዩ ኮንሰርት መቼ ነው የሚል ጥያቄዎች ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3👍1🥰1
📌የግመል ስጋ በአዲስ አበባ

በአዲስ አበባ ከተማ ሕገ-ወጥ የግመል እርድ መበራከቱንና ድርጊቱ ከወትሮው የተለየና አዲስ ፈተና እንደሆነበት የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታውቋል።

የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ግመሎች ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ታርደው ለሽያጭ እየቀረቡ መሆኑን ገልጸው፣ "በተለይም ወደ ቦሌ ሚካኤል ባሉ አካባቢዎች የግመል ስጋ በድብቅ አስገብተው የሚሸጡ መኖራቸውን" አስረድተዋል።

ሕገ-ወጥ እርድ የሚፈጸመው አስፈላጊው ምርመራ ባልተካሄደበትና ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ሲሆን እንደሆነ፣ ይህ የህብረተሰቡን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ድርጅቱ ለማስተካከል እየሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

"ሕብረተሰቡ ጥራቱን የጠበቀ ስጋ መውሰድ እንደሚፈልግ እናውቃለን" ያሉት ሥራ አስኪያጁ፣ ለዚህም ሲባል ማኅበረሰቡ ሕገ-ወጥ የግመል እርድን ሲመለከት ወዲያውኑ ጥቆማ መስጠት እንደሚገባው አሳስበዋል።

ሕጋዊው የግመል እርድ በቄራዎች ድርጅት በተለይም በአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ በስፋት እንደሚከናወንና፣ ስጋውን በስፋት ለሚጠቀሙት የሶማሌና የአፋር ህዝብ ተደራሽ እንደሚሆን ተገልጿል።

የቄራዎች ድርጅት በአማካኝ በቀን ከ7 እስከ 10 የሚደርሱ ግመሎችን እርድ እንደሚያከናውን ጭምር ተዘግቧል።

©️አሐዱ ሬድዮ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4🕊1
📌 "ቢራቢሮ "የተሰኘ ተውኔት ለእይታ ሊበቃ ነው

በደራሲ ኤልያስ ቤተማርያም ተጽፎ በዘካርያስ ረታ የተዘጋጀው "ቢራቢሮ" የተሰኘ ተውኔት የፊታችን ረቡዕ ህዳር 17 ከ11:30 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር ይቀርባል።

በተውኔቱ ላይ ሩሐማ ኃ/ሚካኤል ፣ ዮናታን መኮንን፣ እየሩሳሌም ገ/ስላሴና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።

የተወኔቱ ሚውዚክ ዳይሬክተር ዮሐንስ አማረ ሲሆን የፕሮዳክሽን ማናጀሮች ሀና ታዬ(እርጎዬ) እና ሔኖክ ተሾመ ናቸው።

ተውኔቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራተኛ አመት የቴአትር ጥበባት ተማሪዎች የተዘጋጀ ነው።

"ቢራቢሮ" ተውኔት ባለፈው ዓመት ሰኔ 23 ብሔራዊ ቴአትር ቤት ለተመልካች ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5🥰1
📌"ውብ አዲስ" የሥነጥበብ አውደርዕይ ተከፈተ

"ውብ አዲስ" የተሰኘ የሥነጥበብ አውደርዕይ በዚህ ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ጎላ የሥነጥበብ ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል።

"ውብ አዲስ" በሚል ርዕስ ፣ትኩረቱን በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያደረገው ይህ አውደርዕይ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓመት ውስጥ ሶስት ተከታታይ (ከህዳር-2018 እስከ ህዳር-2019) የሚቀረብ የግል የሥዕል ትርዒት ነው።

ይህ በዓመቱ ውስጥ በተከታታይ የሚቀርብ የሥዕል አውደርዕይ በሠዓሊ ሀሮን የተዘጋጀ ነው።

አውደርዕው ከህዳር 11 እስከ ህዳር 22 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5👍1
📌የኤፍ.ኤ ካፕ ዋንጫ ወደ ኢትዮጵያ መጣ !

የብሪትሽ ኤንባሲ ከአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና ኤን ዜድ ኮምኒኬሽንስ ጋር በጋራ በመሆን "ሺ ዊንስ" በሚለው ፕሮጀክቱ በቀጣይ ሳምንት ለእግር ኳስ አሰልጣኞች(ሴቶች) ስልጠና ለመስጠት ቀጠሮ ተይዟል።

"ሺ ዊንስ" ወጣት ሴቶችን በስፖርት ለማብቃት የተነደፈ ተነሳሽነት ነው። በዚህ መርሃግብር መሰረት ታዋቂ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ጨምሮ የበጎ ፍቃደኛ አሰልጣኞች የልዑካን ቡድን አዲስ አበባን በመጎብኘት የአሰልጣኝነት ስልጠናዎችን በማካሄድ፣ ከዓለም አቀፍ አሰልጣኞች ጋር የእግር ኳስ ውድድርን በመምራት፣ ከ17 አመት በታች ያሉ ወጣት ሴት ተሰጥኦዎችን በመለየት እና የስፖርት ትጥቅ ለሚፈልጉ ሴቶች ያስረክባል፣ ስልጠናም ይሰጣል።

ለዚህም ዓላማ  ከሀገረ እንግሊዝ በ2013 ከዊጋን አትሌቲክ ጋር የኤፍ.ኤ ካፕ ሻምፒዮን በሆነው ኤመርሰን ቦይሴ የተመራ 3 ኢንተርናሽናል የአሰልጣኞች ቡድን ዛሬ እሁድ ህዳር 14 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ወደ አዲስ አበባ ገብቷል።

ከእንግሊዝ ሀገር የሚመጡት ባለሙያዎች ተወዳጁን የኤፍ.ኤ ካፕ ዋንጫን ይዘውም ገብተዋል።

በዚህ መርሐግብር ላይ ለመሳተፍ
👉https://nz-events.vercel.app/rsvp
7😁6
በኮሪደር ልማቱ ወንበሮች ላይ ልብስ ያሰጡ ተቀጡ

በኮሪደር ልማት ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም ላይ እርምጃ ተወሰደ

ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም  በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13  በኮሪደር ልማት በተሰሩ የህዝብ ማረፊያ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ።

ድርጊቱን ፈጽመው የተገኙ  የኮሪደር ልማቱ  የመዝናኛ ካፌ እና ሰራተኞቹን ወደ ህግ በማቅረብ ተጠያቂ በማድረግ ካፌው ተገቢው ቅጣት አስኪቀጣ መታሸጉ ተገልጿል።

ህብረተሰቡ በከተማዋ ውስጥ  በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ የኮሪደር ልማቶችና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ መገልገልና መጠቀም እንደሚገባም አስታውቋል፡፡

ደንብ ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለስልጣኑ አስታውቋል ሲል ኤኤምኤን ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣465👏4
📌ኦዳ አዋርድ ሕዳር 30 ይካሄዳል

የዘንድሮው ኦዳ አዋርድ የሽልማት እና የእውቅና የመስጠት ሥነሥርዓት የፊታችን ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በድምቀት ይከናወናል፡፡

ኦዳ አዋርድ ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ በሚያዘጋጀው የሽልማት መርሃግብር ከቀደምት ዓመት ውድድሮች ለየት ባለ መልኩ በመቅረብ ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ በሙዚቃው ዘርፍ ላይ ብቻ በማተኮር የሽልማት ስነስርዓቱን እንደሚያከናውን ተነግሯል።

በመሆኑም በሙዚቃው ዘርፍ ብቻ ከሀገር ውስጥ 30 እጩዎችን በ6 የሽልማት ዘርፎች ለምርጫ ያቀረበ ሲሆን ከሀገር ውስጥ እጩዎች በተጨማሪ ከ12 አፍሪካ ሃገራት የተወጣጡ እጩዎችን ለህዝቡ ይፋ ያደርጋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም እጩዎች ለሽልማት የሚበቁት ሙሉ በሙሉ በህዝብ ምርጫ መሆኑ ተገልጿል።

ከአፍሪካ ሃገራት በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ በ"AFRICAN SUPER STAR” ዘርፍ ላይ ተሸላሚ ለመሆን የሚሳተፉት 12 የአፍሪካ ሃገራት፦ ሩዋንዳ፣ ማሊ፣ ሞሮኮ፣ አንጎላ፣ ማዳጋስካር፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሲሼልስ፣ ጋና፣ ቶጎ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ ናቸው።

በተጨማሪም 9ኛው ኦዳ አዋርድ ከሃገር ውስጥ የሙዚቃ ስራዎች ለሽልማት እጩዎችን የሚያቀርብበት ስድስት ዘርፎች ሲኖሩት እነሱም፡- የህይወት ዘመን ተሸላሚ፣የአመቱ ምርጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ አርቲስት፣የአመቱ ምርጥ ቪዲዮ ክሊፕ፣የአመቱ ምርጥ ሴት ድምፃዊት፣የአመቱ ምርጥ ወንድ ድምፃዊ፣የአመቱ ምርጥ ምርጥ ሀገርኛ ዘፋኝ ናቸው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3👍3
📌የደጃፍ ፖድካስት ምዕራፍ 4 በቅርቡ ይጀመራል

በዳዊት ተስፋዬ የሚዘጋጀውና በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው "ደጃፍ ከዳዊት ተስፋዬ ጋር" የፖድካስት ዝግጅት ምዕራፍ 4 በቅርቡ እንደሚጀምር የፖድካስቱ አዘጋጅ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
30👍10🔥5
📌ቤርሙዳ ተውኔት ዛሬ በነፃ ይቀርባል

በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፋ የተዘጋጀው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 16 2018 ዓ.ም ከ11:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ያለመግቢያ ክፍያ በነፃ እንደሚቀርብ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዘጋጁ ተሻለ አሰፍ(ዶ/ር) ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
18👍5
"ሺ ዊንስ" የተሰኘ በአይነቱ ልዩ የሆነ የእግር ኳስና የሴቶችን አቅም ማጎልበት ላይ ያተኮረ ፕሮግራም መካሄድ ጀመሯል፡፡

የኢንግሊዝ ኤምባሲ፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና ኤን ዜድ ኮምኒኬሽንስ ጋር በመሆን ለዚህ ፕሮጀክት እውንነት በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ለአምስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል በአዲስአበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ወጣት ሴቶችን በማሰባሰብ በእግር ኳስ ውድድሮች ፣በአመራርነት፣ራስን በማብቃት ላይ ስልጠና ይሰጣል በተያያዘም የስልጠና ሞጁል ለሰልጣኞች በአማርኛ ተዘጋጅቶ ተስጥቷል፡፡

አርአያ የሚሆኑ  ሴቶችም ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉ ይሆናል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ከ10ሺህ በላይ ሴቶችን ለመድረስ ታቅዷል፡፡
በዚህም የአመራር ብቃታቸው እንዲጎለብት፣ በራስ መተማመናቸው እንዲጨምር በማድረግ በግልና በስራ ህይወታቸው አዲስ በሮች እንዲከፈቱ የሚያደርግ ይሆናል።

የእግኳስ ውድድሩ ስምንት ቡድኖችን የሚያካትት ሲሆን በዚህ አሰልጣኞች ባለተሰጠኦችን እንዲለዩ የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡ ቡድኖቹ የአስፈላጊ ቁሳቁስ ልገሳ የሚደረግላቸውም ይሆናል፡፡

ለዚህም ዓላማ  ከሀገረ እንግሊዝ በ2013 ከዊጋን አትሌቲክ ጋር የኤፍ.ኤ ካፕ ሻምፒዮን በሆነው ኤመርሰን ቦይሴ የተመራ 3 ኢንተርናሽናል የአሰልጣኞች ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።

የአሰልጣኝነት ስልጠናዎችን ይካሄዳሉ፣ ከ17 አመት በታች ያሉ ወጣት ሴት ባለተሰጥኦዎችን የመለየት ስራም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ሺ ዊንስ እሷ ስታሸንፍ እኛም እናሸንፋለን በማለት በኢትዮጵያ የጾታ እኩልነት ፣ የወጣቶች አቅም መጎልበትና የሴቶች ስፖርት እድገት ቁርጠኝነት ላይ አበክሮ ይሰራል፡፡
 
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
2👍1