Event Addis Media
9.59K subscribers
6.04K photos
12 videos
4 files
4.67K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ኮሜዲያን ደረጀ ሀይሌ ተሸለመ

ኮሜዲያን ደረጀ ሀይሌ መቶ ሺህ ብር፣ካባ ዋንጫና ሰአት ተሸለመ።

ዛሬ ማምሻውን በእቴጌ ፊልም ኘሮዳክሽን ተዘጋጅቶ የቀረበው የመዝሙረ ዳዊት  አዲስ ሮማንስ ኮሜዲ ፊልም "በቃ ፍቅር" የተሰኘ ፊልም በአዲሱ ህጻናት እና ወጣቶች ቴአትር ቤት ተመርቋል።

በዚህ የፊልም ምረቃ ላይ በፊልሙ ተዋናይ ለሆነው ታላቁ ኮሜዲ ደረጀ ሀይሌ   የክብር ካባ፣ ዋንጫ  እንዲሁም ከቴምር ፕሮፖርቲስ  የአንድ መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል ።በተጨማሪ  ደረጀ ሀይሌ አይዛክ ሰዓት ተሸልሟል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
25👍6
📌ዶ/ር አንተነህ ፀጋዬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የሥነ ተግባቦት መምህር የሆኑት አንተነህ ፀጋዬ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በዩኒቨርሲቲው ለበርካታ ዓመታት  በማስተማር እና በምርምር ሥራዎች ያገለገሉት ዶ/ር አንተነህ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ኅዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም  ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ጀርመንን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እና በአሜሪካ በተለያዩ  የትምህርት መስኮች ዕውቀት የቀሰሙት ዶ/ር አንተነህ፤ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በብሔራዊ ጥቅም እና አጀንዳ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ትንታኔዎችን በመስጠት ይታወቃሉ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢164
📌በዳሞ መንግሥቱ የተጻፈው “ያልተሻገርነው ድልድይ” የተሰኘ መጽሐፍ ለህትመት በቃ

ደራሲው በዚህ መጽሐፉ ከጥልቅ የህይወት ልምዱ በመነሳት ስለ ሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ህይወት የሚመለከቱ ጉዳዮች ከአዝናኝ እና አስተማሪ ከሆኑ ዓለም አቀፍ ገጠመኞቹ ጋር በማዋሀድ ትዝብቱን እና ያልተሻገርናቸውን ድልድዮች ለመሻገር ምን ብናደርግ እንደሚሻል የግል ምልከታውን ከመፍትሔ ሃሳቦች ጋር ያጋራል።

በእርግጠኝነት የምንነግሮ መፅሀፉን አንብበው ይወዱታል ኪስን በማይጎዳ ዋጋ አትርፋችሁ ትዝናኑበት ዘንድ እየጋበዘ የመጽሐፉን በጃፋር መደብር፣ በሀሁ የመጽሐፍ መደብር እና በኤዞፕ የመጽሐፍ መደብር እንደሚገኝ ስንጠቁም በደስታ ነው፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏61👍1
📌የነፃነት ላቀው "ደጋ አምባ" ድራማ ዛሬ ይጀምራል

በጋዜጠኛ ነፃነት ላቀው ተደርሶ በአንተነህ ኃይሌ የተዘጋጀው "ደጋ አምባ" ተከታታይ ድራማ ዛሬ ሐሙስ ህዳር 4 ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ በአቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል።

በድራማው ላይ የሥነልቦና ባለሞያና የቡና ፖድካስት አዘጋጅ  የሆነችው ሰላም አታላይ በመሪ ተዋናይነት ትሳተፋለች ተብሏል።

ደጋ አምባ ድራማ በህይወትዎ እጅግ አጥብቀው ለዓመታት ሲፈልጉት የነበረን ነገር ለማግኘት ከጫፍ ደርሰው ነገር ግን የመጨረሻ ውሳኔዎ የአንድ መንደር ሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ እልቂት ቢያመጣ  ምን ያደርጋሉ? በማለት ይጠይቃል።

በደጋ አምባ ድራማ ጥበብ ከተፈጥሮ፣ራስ ወዳድነት ከፅናት፣ፍቅር ከታማኝነት አፈታሪክ ከእውነታ ጋር ተፋጠው ይቀርቡበታል።

ደጋ አምባ አዲስ ልብ አንጠልጣይ ድራማ በአቦል ቲቪ ዛሬ መቅረብ ይጀምራል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
19🔥2
📌ያንጎ ኢትዮጵያ ከቀይ መስቀል ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ዘመቻ አካሄደ

የዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ያንጎ ግሩፕ አካል የሆነው ያንጎ ኢትዮጵያ (በፍራንቻይዝ ጂ2ጂ አይቲ ሶሉሽንስ አ.ማ. እና ኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ኃ.የተ.የግ.ማ. የሚተዳደር) ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ዘመቻ ጀምሯል። ዘመቻው ያንጎ የአካባቢውን ማህበረሰብ ለመደገፍ ያለውን ተነሳሽነትን ያማከለ ነው።
 
የያንጎ ኢትዮጵያ የፍራንቻይዝ አጋሮች እና አጋር አሽከርካሪዎች በበጎ ፍቃደኝነት ደም በመለገስ ላይ ሲሆኑ ይህም የደም ተፈላጊነት ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻር ኩባንያው ህብረተሰቡን ለማገልገል ያለው ቁርጠኝነትን አጉልቶ ያሳያል፡፡
 
"ያንጎ እውነተኛ እድገት ከማህበረሰቡ ደህንነት ጋር አብሮ የተሳሰረ ነው ብሎ ያምናል። ይህ ዘመቻ የመተሳሰብ፣የኃላፊነት እና የትብብር እሴቶቻችንን ያሳያል። ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጎን በመቆማችን ኩራት ይሰማናል፤ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ለሌሎችም ጥሪ ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡" በማለት በኢትዮጵያ የያንጎ ተወካይ ዶ/ር ይቅናለም አበበ ተናግረዋል።
 
የደም ልገሳ ዘመቻው የበጎ ፈቃደኝነትን እና የማኅበረሰብ መንፈስን አስፈላጊነት የሚያጎላ ሲሆን፣ ትናንሽ የግለሰብ ተግባራት ተባብረው ትርጉም ያለው ማኅበራዊ ተፅእኖ መፍጠር እንደሚችሉ የያንጎን እምነት የሚያጠናክር ነው።
 
ያንጎ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤቱን በዱባይ ያደረገ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገኙ ቴክኖሎጂዎችን ለአካባቢው ማኅበረሰቦች ተስማሚ በሆነ መልኩ የዕለት ተዕለት አገልግሎቶች የሚያቀርብ ኩባንያ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1👍1
📌በፎሊክ አሲድ በቀላሉ መከላከል የሚቻል በሽታ ሕጻናትን ለእድሜ ልክ የአካል ጉዳትና ለሞት ተጋላጭ እየዳረጋቸው ነው ተባለ

ሆፕ ኤስ ቢ ኤች በዓለም አቀፍ ደረጃ "የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውስጥ ከመጠን በላይ የፈሳሽ ክምችት ሕመም ጋር ለሚወለዱ ሕፃናት የሚደረገውን ጥረት ማፋጠን" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን አለም አቀፍ ክብረበዓል በማስመልከት ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ አካሄደ።

በዚህ መድረክ ላይ ስለ ነርቭ ዘንግ አፈጣጠር ችግር እና የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ ከመጠን በላይ ክምችት ወይም "የስፖይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ" በሽታ ምንነት እንዲሁም የበሽታውን መንስዔ እና መፍትሔ በባለሙያዎች የታገዘ ግንዛቤን የመፍጠር ስራን ጨምሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ስራዎች እንደተሰራም የሆፕ ኤስ ቢ ኤች መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቤዛ በሻህ ገልጸዋል።

በዓለማችን በዓመት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህፃናት የዚህ በሽታ ተጠቂ ይሆናሉ፡፡

በአፍሪካ ይህ በሽታ በብዛት ከሚከሰትባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች።

ስፓይና ቢፊዳ ማለት ደግሞ የነርቭ ዘንግ ክፍተት ወይም የህብለሰረሰር በትክክል አለማደግ ሲሆን የሚከሰተውም የመጀመሪያዎቹ አራት የእርግዝና ሳምንታት ውስጥ ነው፡፡

ምልክቶቹም የውጭኛው የጀርባ ክፍል ላይ የሚታይ እብጠት ወይንም ክፍት ቁስል መታየት ነው፡፡

ይህ የጤና ችግር ያለባቸው ህፃናት የቀዶ ጥገና ህክምና የሚደረግላቸው ሲሆን ይህም የነርቭ ህዋሳቶችን የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለማድረግ የሚረዳ ይሆናል፡፡

በዚህም ምክንያት እነዚህ ሕጻናት ለእድሜ ልክ የአካል ጉዳት ብሎም ለሞት ተጋላጭ እንደሆኑም ተገልጿል።

ሆፕ ኤስ ቢ ኤች ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት በአሁን ሰዓት ከ5,700 በላይ ቤተሰቦችን በተለያዩ መንገዶች እያገለገለ ይገኛል።
2
📌የሕይወት እምሻው አዲስ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

47 ታሪኮችን የያዘውና "ዥዋዥዌ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የደራሲ ሕይወት እምሻው ስድስተኛ መጽሐፍ ቅዳሜ ሕዳር 6 2018 ዓ.ም ተመርቆ ለንባብ ይበቃል ተብሏል።

ደራሲዋ ስለ አዲሱ መጽሐፏ<< ዥዋዥዌ አርባ ሰባት የዘመን ማስታወሻ ታሪኮችን የያዘ ሲሆን የተስተካከለና የተመሰቃቀለው፤ የተሳካና የተሰናከለው፤ የሚያምርና የሚያስቀይመው፤ የሚያስደስትና የሚያማርረው፤ የሚያኮራና የሚያሳፍረው ዘመነኛ ኢትዮጵያዊ ሕይወታችንን እንደ ወረደ የሰነድኩበት ነው››  ስትል ተናግራለች።

የ "ዥዋዥዌ" መጽሐፍ  ምርቃት ቅዳሜ ህዳር 6 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ለገሃር በሚገኘው አዲሱ የጃፋር መጽሐፍት መደብር ውስጥ ይከናወናል።

ሕይወት እምሻው ከዚህ በፊት አምስት መፅሐፍትን ማለትም ባርቾ፣ ፍቅፋቂ፣ ማታ ማታ፣ ለእርቃን ሩብ ጉዳይ እና የቡና ቁርስ ለአንባቢያን ያደረሰች ደራሲ ነች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
17🔥1
📌የሀገራችን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሁሉ ተቋርጠዋል

የሳተላይት አቅራቢ ድርጅት በሆነው SES የቴሌ ፖርት ላይ እስራኤል አካባቢ ባጋጠመው ከፍተኛ የአየር ፀባይ ለውጥ ምክንያት የኃይል መቋረጥ ተፈጥሯል፡፡

በዚሁ ምክንያ የሀገራችን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭት እንደተቋረጠ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁8👍62
📌የክብር ዶክትሬት የተሠጣቸውን ግለሰቦች "በመጠሪያነት መጠቀም" እንደማይቻል ተገለፀ

የክብር ዶክትሬት የተሠጣቸውን ግለሰቦች "በመጠሪያነት መጠቀም" የማይቻል መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።

ሚኒስትሩ ይህን የገለፁት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ዘርፉን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም በትናንትው ዕለት በገመገመበት ወቅት ነው።

በዚሁ ወቅት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን በተመለከተ ችግር የነበረበት መሆኑን ያስታወሱት ሚኒስትሩ ወጥ አሰራር መከተል በማስፈለጉ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መደረጉን ገልፀዋል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ማድረግ ያለበት መሆኑን ጠቅሰው የክብር ዶክትሬት ማዕረግ የሚያገኙ ሰዎች ዶክተር ወይንም የክብር ዶክተር በሚል መጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አሳስበዋል።

ሚኒስትሩ በሙያው የተለየ ስራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዓረግ ማግኘት እንደሚችል ገልፀው ሆኖም ግን የተሠጠውን የክብር ዶክትሬት ለመጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አመልክተዋል።

በተጨማሪም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት ሀገራዊ እና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Via አዲስ ስታንዳርድ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
2🤣177👎1
📌ቤቶች ድራማ 13ኛ ዓመቱን ሊያከብር ነው

በቴሊቪዥን መስኮት የመጀመሪያው ሀገረኛ ሲትኮም የቤተሰብ ድራማ የሆነው ቤቶች 13ኛ ዓመት ክበረ በዓሉን እንደሚያከብር ይፋ አድርጓል።

ቤቶች ድራማ ሳይቆራረጥ ለተከታታይ 13 ዓመታት በ525 ክፍሎች ወደ ተመልካችመድረሱን ተዋናይ ጥላሁን ጉግሳ ተናግሯል።

ለተመልካች በደረሱት 525 ክፍሎች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችንማንሳት መቻሉ ነው የተገለፀው።

ሲትኮም ተከታታይ ድራማው አዲስና አቅም ያላቸውን ተዋንያን ማፍራትን አላማድረጉን የገለፀው ተዋናይ ጥላሁን ጉግሳ በዚህ ረገድ ቤቶች ድራማ አዲስ ፊቶችን ለተመልካች ማስተዋወቅ መቻሉ ሌላው ስኬቱ ነውብሏል።

የፊታችን ኅዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድራማው የተጀመረበት 13ኛ ዓመትበዓል በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ እንደሚከበር አራዳ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

በክብረ በዓሉ ላይ የመድረክ ቴአትር፣ ጭውውቶችና ሌሎች ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ይቀርባሉ።

በክብረ በዓሉ ላይ የቤቶች ድራማ አባል የነበረችው በድንገተኛ የመኪና አደጋህይወቷ ያለፈው ተዋናይ ሰብለ ተፈራ እንደምትዘከር ተገልጿል።

Via አራዳ Fm

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤮109🤷‍♂1👍1
የ11ኛው ጉማ አዋርድ አሸናፊዎች ዝርዝር

1.ምርጥ ተዋናይት፦ ቃልኪዳን ጥበብ (ትዝታ)
2. ምርጥ ተዋናይ:- ናታይ ጌታቸው ( ጥቁር አደይ)
3.ምርጥ ረ/ተዋናይ፦ አማኑኤል ሀብታሙ (አፊኒ)
4. የተመልካች ምርጫ፦( ባለ ክራር)
5.ምርጥ ዳይሬክተር፦  ፍፁም ካሳሁን (ጥቁር አደይ)
6.ምርጥ ፊልም፦ (ጥቁር አደይ)
7. ምርጥ ድምፅ፦ ሐብታም አዲስ (አፊኒ )
8. ምርጥ ኤዲተር፦ ዳንኤል አንማው (ትዝታ)
9.ምርጥ ስኮር፦  ስምአገኘኹ ሳሙኤል (አፊኒ)
10. ምርጥ ማጀቢያ ሙዚቃ፦ ኤደን አይሸሹ፣ ፍፁም ካሳሁን እና አብነት አጎናፍር (ጥቁር አደይ)
11. ምርጥ ሲኒማቶግራፈር፦ ኤልያስ ተስፋዬ 6 ሰዓት ከለሊቱ
12. ምርጥ ሜካአፕ፦ ዝናዊት ዘርጋባቸው (አፊኒ )
13.ምርጥ የፊልም ፅሁፍ፦ ፍፁም ካሳሁን (ጥቁር አደይ)
14.ተስፋ የተጣለባት ተዋናይት፦ ክላራ ሙሉጌት (ሁለት ቅጣት)
15. ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ፦ ሳሊም አብዱራህማን (ለፍትህ )
16.ምርጥ ረ/ተዋናይት፦  ማርታ ጎይቶም( 6 ሰዓት ከለሊቱ )

☑️. የሕይወት ዘመን ተሸላሚ፦ ፍቅርተ ጌታሁን እና ወለላ አሰፋ
☑️ የሐርሜላ ተሸላሚ፦ ወይዘሮ ወሰኔ ሀይሉ

☑️ ምርጥ አጭር ፊልም፦ በማን ዓይን አሸናፊ መስፍን

ከ16ቱ 5ቱን አዋርድ በመውሰድ ጥቁር አደይ ፊልም ከፊት ይገኛል፣ አፊኒ 4ት በመውሰድ ይከተላል፤ ትዝታ እና 6 ሰዓት ከለሊት ደሞ ሁለት ሁለት አዋርድ በማሸነፍ 3ተኛን ይዘዋል።

ስለ ተከታታይ ድራማ ከወራት በኃላ ጉማ "ሉሲ አዋርድ" ብሎ ተከታታይ ድራማዎችን ብቻ እንደሚሸልም ገልጿል።

ይህ መረጃ በፅዮን ታምራት የተዘጋጀ ነው!

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍146🔥1
📌ተፈራረሙ !

ሲግማ ምስራቅ አፍሪካ እና ስዊት ላይፍ ፎር ኦል በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ::

ሲግማ ምስራቅ አፍሪካ በጎ አድራጎት ድርጅት እና ስዊት ላይፍ ፎር ኦል በጎ አድራጎት ድርጅት በኢትዮጵያ ህገወጥ የሰውን ዝውውር ለመከላከል ፣ አስተማማኝ ፍልሰትን ለማስተዋወቅ እና ለተመላሾች ዳግም የመዋሃድ ድጋፍን ለማጠናከር የተቀናጀ ጥምረት ለመጀመር የመግባቢያ ሰነድ (MoU) በይፋ ተፈራርመዋል።

"ዲጂታል ድምጾች፣ እውነተኛ ተጽዕኖ፡ የፍልሰት አስተዳደር የሚዲያ ንቅናቄ በኢትዮጵያ"  ይህ ዘላቂ የሶስት ወራት ዘመቻ ከዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ቀን ( Dec18) በፊት የሚዲያ ቅስቀሳን እና የማኅበረሰብ ግንዛቤን ያጠናክራል የተባለውን ዘመቻ ያድጀምራሉ።

ዘመቻው በተጎጂዎች ላይ ያተኮሩ ምስክርነቶችን፣ አስተማማኝ እና ህጋዊ ፍልሰት ላይ የባለሙያ መመሪያዎችን እና በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ማህበረሰቦች የታለሙ የግንዛቤ መልዕክቶችን ያስተላልፋል።

"ጣፋጭ ህይወት" የሬዲዮ ፕሮግራምን ጨምሮ በተለያዩ የሚድያ አማራጮች ተከታታይነት ያለው ፕሮግራም በማድረግ አቅጣጫዎችን ከአላማው ለማሳካት  መሰረት ያደርጋል።

ሁለቱ ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታሰበውን የፍልሰተኞች ቀን Dec18/ 2025 በተለያዩ ተግባራት ይከውናሉ።

ሲግማ ምስራቅ አፍሪካ እና ስዊት ላይፍ ፎር ኦል ለጋሾች እና ባለድርሻ አካላት በብሔራዊ የመከላከያ ዘመቻዎች ላይ ኢንቨስትመንትን እንዲያሰፉ እና ለተጎጂዎች የስነልቦና፣ የትምህርት ስልጠና እና የኑሮ ድጋፍንም አቅደዋል።

ሲግማ ምስራቅ አፍሪካ ትኩረቱን በስደት ላይ በማድረግ የሚሰራ ሲሆን በተመሳሳይ ስዊት ላይፍ ፎር ኦል ወጣቶችን  ሁለገብ አቅም ለማሳደግ ትኩረት በማድረግም ይሰራል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6
📌 ሁለት የሥዕል አውደርዕዮች በዕይታ ላይ ይገኛሉ

የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሥነጥበብ ትምህርት ክፍል ተመራቂ ተማሪዎች ያዘጋጁት የሥነጥበብ ዓውደርዕይ በዚህ ሳምንት በይፋ ተከፍቷል።

የሥዕል አውደርዕይውም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ እስከ ታኅሣሥ 2 2018 ዓ.ም ድረስ በኮሌጁ የሥዕል ማሳያ ውስጥ በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

በሌላ በኩል "አብሮነት" የተሰኘው በብሩ ወርቁ ፣ያሬድ ወንደሰን እና ዘውዱ ገ/ሚካኤል የተዘጋጁ የሥዕል ሥራዎች የቀረቡበት አውደርዕይ ባሳለፍነው ረቡዕ ህዳር 3 2018 ዓ.ም በፈንድቃ የባህል ማዕከል ለእይታ ክፍት ሆኗል። እስከ ህዳር 29 2018 ዓ.ም እንደሚቀይም ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6
📌 "መልቲ" ተውኔት በይፋ ተመረቀ

በስንታየሁ ታዬ (ፋቡላ) የተዘጋጀው "መልቲ" አዲስ ኮሜዲ ቴአትር በትናንትናው ዕለት በቀይ ምንጣፍ ስነ ስርዓት በድምቀት ተመርቋል።

በአዶት ሲኒማ በተመረቀው ትያትር ታላላቅ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ትያትር አፍቃሪያን፣ እና በርካታ ተመልካቾች ተገኝተዋል።

በከፍተኛ የተመልካች ሳቅ የታጀበው  የ"መልቲ" ትያትር የመጀመሪያ የምርቃት መድረክ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ማግኘት ችሏል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢፌድሪ የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ትያትሩ እንዲሳካ ላደረጉ የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።

ትያትሩ ዘወትር አርብ በ11:30 በአዶት ሲኒማ በቋሚነት መታየት ይጀምራል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
2
📌"ውብ አዲስ ፩" የሥዕል ትርዒት ሊከፈት ነው

"ውብ አዲስ" በሚል ርዕስ ፣ትኩረቱን በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያደረገ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓመት ውስጥ ሶስት ተከታታይ (ከህዳር-2018 እስከ ህዳር-2019) የግል የሥዕል ትርዒት (Solo Art Exhibition) ለማቅረብ ሠዓሊ ሀሮን ዝግጅቱን ጨርሷል።

የመጀመሪያውን "ውብ አዲስ ፩" የሥዕል ትርዒትም ከአርብ ህዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ጎላ ሚካኤል አካባቢ በሚገኘው ጎላ ሥነ ጥበብ ማዕከልለህዝብ ዕይታ ክፍት ይሆናል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6
📌የ"ቁንጅና" ሙዚቃ ግጥም የዓለምፀሐይ ወዳጆ አይደለም ሲል ዳዊት መለሰ ተናገረ

ከሁለት አስርት ዓመታት በኃላ 'ምስጢር" የተሰኘ አልበሙን ለአድማጮች ያቀረበው ዳዊት መለሠ ሰይፉ ሾው ላይ ቀርቦ ነበር።

በዚህ ቃለመጠየቁ ዳዊት መለሠ በርካታ የእሱ ሙዚቃ ወዳጆች ስለሚወዱለት "ቁንጅና" ሙዚቃው ተከታዩን ብሏል"ቁንጅና የተሰኘው ዘፈኔን ዓለምፀሐይ ወዳጆ የፃፈችው የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ።ዘፈኑን የፃፈው ዮናስ ሙላቱ የተባለ ኪቦርድ ተጫዋች አለ።ቁንጅና እና ብቻሽን የተሰኘ ሁለት ዘፈን ሰጠኝ።ዓለምፀሐይ የፃፈችው ፍረጂኝ የተሰኘውን ዘፈን ነው"

በሌላ በኩል ከራሱ ሕይወት ጋር የሚገኘው ሙዚቃው "እህል ውሃ" የተሰኘው እንደሆነም ተናግሯል"ከራሴ ሕይወት ጋር የሚገናኝ ዘፈን የዘፈንኩት እህል ውሃ የተሰኘውን ዘፈን ነው።ቴዲ አፍሮ የቀድሞ ፍቅረኛዬን ያውቃት ነበር። አሜሪካ ሀገር ሲመጣ ደህና ነች ወይ? ሲለኝ አዎ ደህና ነች ሞክረን ነበር አልሆነም አልሰራም አልኩት።እህል ውሃ የሚለውን ዘፈን ሰርቶ ሰጠኝ። ቴዲን የማደንቀው ትልቅ ጭንቅላት ያለው ልጅ ነው።በዜማም በግጥምም የበሰለ ልጅ ነው"

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍65
📌የአበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ አባት አረፉ

የታዋቂው የሙዚቃ ሰው አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ወላጅ አባት ማረፋቸው ተሰምቷል።

አበጋዝ ከወላጅ አባቱ አቶ ክብረወርቅ ጋር ከወራት በፊት በታዋቂዋ ሞዴልና ፋሽን ዲዛይነር አና ጌታነህ ፕሮውዲስ በሚደረገው ፕሮግራም ( በአቦል ቲቪ ) ላይ ቀርቦ እንደነበር ይታወቃል።

ምናልባትም ከቅርብ ሰዎቹ ውጭ ብዙ አድናቂዎቹ አባቱን በመልክ ያዩዋቸው በዚያ ፕሮግራም ነው። የሙዚቀኛ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ አባት አቶ ክብረወርቅ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢6💔3
📌ለሚዲያ በሰጡት መረጃ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር በአካባቢው ስለተከሰተው “የሔሞሬጂክ ፊቨር” እንደሆነ በተገመተው ተላላፊ በሽታ ሰዎች መሞታቸውን ገልፀው ለመገናኛ ብዙሀን መረጃ መስጠታቸውን ተከትሎ ከሀላፊነታቸው ተነሱ።

የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ቢንያም አስራት ለአንድ ዓለማቀፍ ሚዲያ “የሔሞሬጂክ ፊቨር” እንደሆነ በተገመተው በሽታ ሳቢያ ሀኪሞችን ጨምሮ ሰዎች መሞታቸውን ገልፀው መረጃ በመስጠታቸው ከሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ምስጢሩ ሐምደኪ በተጻፈ ደብዳቤ ከሕዳር 5 ቀን 2028 ዓ.ም ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ተነግሯቸዋል። 

ዳይሬክተሩ ከሃላፊነት ከመነሳታቸው በፊት ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ከታከሙት አራት በሽተኞች አንዱ በህይወት እንዳለ እና የተሻለ የሚባል የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ሁለት የሆስፒታላቸው የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ እስካሁን ስድስት ሰዎች ተመሳሳይ ምልክቶችን በማሳየት ህይወታቸው ማለፉን ለዶቸ ቨለ ራዲዮ በይፋ ገልፀው ነበር።

የበሽታው ክስተትና ምንነት ዓለማቀፍ ትኩረት የሳበ ሲሆን የዓለም የጤና ድርጅትም ከመንግስት ጋር በመቀናጀት አስቸኳይ የመስክ ቡድን ወደ ስፍራው ልኳል። 

የጤና ሚኒስቴር እስከአሁን ድረስ ስምንት ሰዎች  በበሽታው የተጠረጠሩ መሆኑን ባወጣው መግለጫ ይፋ ያደረገ ሲሆን ስለ ሞቱ ሰዎች  ያለው ነገር የለም።
ዶክተር ቢንያም አስራት በበሽታው ሞት መመዝገቡን ይፋ ካደረጉ በኋላ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ የቅርብ የስራ ባልደረቦቻቸው ነግረውናል ሲል ዋዜማ ሬድዮ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😡315😁2🤯2🤬2🤨2🤔1
📌እንጀራ በሸቀጣ ሸቀጦች ሱቅ መሸጥ መከልከሉ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣንን የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች ውስጥ እንጀራ መሸጥ መከልከሉን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።

የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ የተለያዩ መርዛማ ነገሮች ሳሙና እና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች በቀጥታ ለምግብነት የሚውሉትን እንጀራ እና ዳቦን መሸጥ ልክ ባለመሆኑ ለመከልከል መገደዳቸውን ተናግረዋል ሲል ነው ዘገባው የጠቀሰው።

እንጀራ እና ዳቦ መሸጥ ያለባቸው በምግብ ቤቶች፣ በዳቦ ቤተች እና በባልትና ወይም ለዚሁ መሻጫነት በተፈቀደ ቦታ ብቻ መሆኑንም በማንሳትም ያልተፈቀደላቸው ነጋዴዎችም ሲሸጡ ከተገኙ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስገንዝበዋል ሲል ገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😱9😁84👍3
📌የሙዚቀኛ መሐመድ ራጅኡ አልበም ሊለቀቅ ነው

የሙዚቀኛ መሐመድ ራጅኡ "ብርሃን" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው በመሳሪያ የተቀነባበረ የሙዚቃ አልበም የፊታችን አርብ ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ለሙዚቃ አፍቃሪያን ይደርሳል ተብሏል። 

ለማዘጋጀት አንድ ዓመት እንደወሰደ የተነገረው "ብርሃን" የሙዚቃ አልበም አስር አንድ የሙዚቃ ስብስቦችን ይዟል።

"ብርሀን" በተሰኘው ሁለተኛ አልበሙ በኪቦርድ፣ ቤዝ፣አኮስቲክ ጊታር፣ክራር፣ የሙዚቃ መሳሪያዎች የተሰሩ የሙዚቃ ስራዎች ተካተዋል።

አልበሙ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በትሪፕል ሆቴልና ስፓ የሚመረቅ ይሆናልም ተብሏል።

የፊታችን ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በDeamat records ዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃልም ተብሏል።https://youtube.com/@deamatrecords?si=91IxewcK1ZdGshgL

ሙዚቀኛ መሐመድ ከዚህ ቀደሞ "ሰላምታ " የተሰኘው የመጀመሪያ አልበሙን በ2010 ዓ.ም ለአድማጭ አድርሷል።

ሙዚቀኛ መሐመድ የሙዚቃ ኪቦርድ መጫወት የጀመረው 1998 ዓ.ም ሲሆን ሶስት ዓመት አፍሪካ ጃዝ ስኩል ( ጃዝ አምባ ) ተምሯል።

ሙዚቀኛው ከትግርኛ ዘፋኞች መሐል ለረጅም ጊዜ  የአብርሃም ገብረመድህን ፣ የማህሌት ገብረጊዮርጊስ ፣ የሸዊት መዝገቦ ኪቦርዲስት በመሆን በብዙ አገራት ቱር አድርጓል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
8👍7🔥1