በነፃ የቀረበ እድል !
የኢ-ኮሜርስ ድርጅትዎን በነፃ ያስተዋውቁ !
ኢ-ኮሜርስ ( E-Commerce) ላይ እየሰራችሁ ለምትገኙ ተቋማት አስደሳች መረጃ እንነግራችኋለሁ።
የኢ-ኮሜርስ ተቋማት አገልግሎቶቻችሁን ያለምንም ክፍያ በነፃ በተወዳጁ ትርታ ኤፍ ኤም 97.6 በኩል የምታስተዋውቁበት እድል ተዘጋጅቶላቸዋል።
ምርትና አገልገሎትዎን ለማስተዋወቅ ተከታዮቹን አድራሻዎች ይጠቀሙ፣ይደውሉ ፣በነፃ ያስተዋውቁ:-
ስልክ: 0983111555
0931268671
@Sara.m@tiritfm.com
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ 🙏

📌 የስብሐቲዝም አንድ መቶኛ መድረክ
ስብሐቲዝም የሐሳብ፣ የንባብ፣ የውይይት መሰናዶ አንድ መቶኛ መድረክ ነገ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት(ወመዘክር )ይካሄዳል።
በዚህ መሰናዶ ላይ ተከታዮቹ መርሐግብሮች ይቀርባሉ:-
ዶክተር ዓለማየሁ አረዳ ሰው ስለምን አመክንዮአዊ እንሰሳ (Rational Animal) ተባለ? ብለው አርስቶትላዊ ሐሳባቸውን ሊነግሩን ወጥነዋል
ጋሽ ዘነበ ወላ 'ሰው መሆን በጋሽ ስብሐትለአብ ውስጥ' ምን ይመስል ነበር ይለናል።
ቡርሃን አዲስ 'ኑ ሰውነት'ን እንገንባ' ብሎ ፍልስፍናዊ ሐሳቡን ይነግረናል።
ጋሽ ኃይለመለኮት ገጠመኞቻቸው ውስጥ እየተመላለሱ የሚያጫውቱን የሰው መሆን ልክ አለ።
ወጣቶቹ ጋሽ ስብሐት ለወጣቶች ስስ ዓይን አለውና እነሱም በሰሱ መንፈስ ውስጥ አለሁ እያሉ ያውሉናል።
አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት በመድረክ ላይ ይመደረካል/Monologue/
የወመዘክር አዲሱ ሕንጻ 13ኛው ፎቅ መቶኛውን የስብሐቲዝም መድረክ ለማሰናዳት ክፍት ነው።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

❤4🥰2
📌 "አልንበረከክም" መጽሐፍ ሰኞ ይመረቃል
የገጣሚ እና ተዋናይ ዋሲሁን በላይ 5ኛው የሥነ-ጽሑፍ ስራ "አልንበረከክም" በብሔራዊ ቴአትር ሊመረቅ ነው።
"አንበረከክም" በሚል ርዕስ በሁለገቡ ከያኒ ዋሲሁን በላይ የተዘጋጀው አዲስ መጽሃፍ የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 24 2018 ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትአቴር ቤት ይመረቃል።
በዕለቱም በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሀሳቦቻቸው ያጋራሉ ተብሏል።
የመፅሃፍ አፍቃሪዎች፣ የጥበብ ሰዎችና የመድረክ ታዳሚዎች በዚህ የመጽሐፍ ምረቃ ላይ በክብር ተጋብዛችኋል ተብላችኋል።

👍7❤1
📌አርቲስት ተስፋዬ አበበ የግጥም እና የዜማ ሥራቸውን ለአብነት የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች አስረከቡ
አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) በኢትዮጵያ ቀዳሚ ለሆነው ለአብነት የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች፤ የግጥምና የዜማ ሥራዎቻቸውን በዛሬው ዕለት በይፋ አስረክበዋል፡፡
አርቲስቱ በሥማቸው በተሰየመው የኪነ-ጥበብ ማዕከል ውስጥ የአብነት የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ነው ሥራዎችቸውን ያስረከቡት፡፡
የልዩ ፍላጎት ትምህርት መርሃ ግብርን ጨምሮ በሁሉም ዕድሜ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች፤ ያላቸውን ምቹና ተስማሚ እምቅ አቅምና በዋጋ ሊተመን የማይችል አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ ለተቋቋመው አብነት የማህበረሰብ ት/ቤቶች አርቲስቱ ሥራቸውን ማስረከባቸው ተገልጿል።
በኪነ ጥበብ ማዕከሉ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ወርቅነህ፤ የአብነት አካዳሚ ለአርቲስት ተስፋዬ አበበ እስከ ሕይወት ዘመናቸው ድረስ በተለያየ መንገድ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።
ስለ አርቲስቱ ሥራ እና ለትምህርት ቤታቸው ስለተበረከተው ሥራም ምስጋና አቅርበዋል።
በመድረኩ በማዕከሉ ተማሪዎች የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ሥራዎች ለታዳሚዎች ቀርበዋል።
©️አሐዱ ሬድዮ

❤14👏5
📌የደራሲ ናትናኤል ቀረዓለም መጽሐፍት!
“…ሕይወት ቀላል ነበረች፣ ቀላልም ትሆን ነበር፡፡ ሞታችንን እንደሞታችን እንጂ እንደሞታቸው ላንሞት… ሕይወትን እንደ ሕይወታችን ከመኖር ይልቅ እንደ ሕይወታቸው ለመኖር መረጥን!... ለምን?” "ዛሬ ቅዳሜ አይደለም” ከተሰኘው መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡
“…በመጀመሪያ ልቧ ባዶ ነበር። ሐረጓ በቅጥር ላይ ያድግ እንዲሆን የሚታሰብ በምንጭ አጠገብ ያፈራ እንደሚሆን የፍሬ ዛፍ ያልተዘነጋች። የተዘነጋች የመሰላት።
የፍቅር አምላክ ይጎበኛት ዘንድ ጥቂት መጠበቅ ይጠበቅባት እንደነበር የዘነጋች። መጠበቋን ሳትጠብቅ ትኖር የነበረች አንዲት ባዶ ልብ ነበረች። ክፋትና ተንኮልን፣ አመጽና እብሪትን፣ ትዕቢትና ትምክህትን ታውቅ ያልነበረች፣ አታውቅ ያልነበረች ልብ ነበረች።
በመጀመሪያ ልቧ ባዶ ነበር? ባዶነት በልቧ ሰፍፎ አልነበረም? ባዶነት የሞላው ልብ እንዴት ባዶ ይባላል? ባዶነት የሞላውን ልቧን እንደታቀፈች ትኖር ነበር። ማታም ሳይሆን፣ጠዋትም ሳይሆን በፊት። “ትናንት እመጣለሁ” ከተሰኘው መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡
“…ከማይነጋው ሌሊት፤ ከማይጨልመው ቀን አጋማሽ… ምርጫ በእጅህ አልነበረችም… ያደለችህን ትቀበል እንጂ ትጠይቅም ሆነ መሻትህ ይፈጸም ዘንድ ትማልድ… ብትማልድም ከቀኝህ በሚሆን አልታደልክም… ፍርሃትና ድንዛዜ በሞላው… ምናልባትም በሚሞላው ቆይታህ ከሐሴት ትጎራበትም ሆነ… ከነፍስ እስራት ነፃ ትወጣ ዘንድ ስለመታደልህ እርግጠኛ አይደለህም… እውነት ከአንተ ዘንድ ነች… ብትነግረን አናምንም… ብትጠይቀን አንመልስም፡፡…” “እውነት / አዛምድ” ከተሰኘው መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡
ሁሉንም መጻሕፍት በጃፋር መጻሕፍት መደብሮች ማግኘት ይችላሉ፡፡
አሳታሚ እና አከፋፋይ - ጃፋር መጻሕፍት
ደራሲውን ለመወዳጀት: https://www.facebook.com/natnael.kerealem

❤9
📌የሁለት ሀገራት የሙዚቃና ባህል ድግስ
ወደ እንግሊዝ ሳይጓዙ እዚሁ አዲስ አበባ ላይ በአንድ መድረክ የሁለት ሀገራት የሙዚቃ ባህል ተደግሷል!
ዩኬ ኢትዮ ሚዮዚክ ኮንሰርት
ለማይረሳው ውብ ምሽት ይዘጋጁ!
ከእንግሊዝ የተውጣጡ The sassenachs Ceilidh Band
ከኢትዮጵያ ድምፃዊት ጠረፍ ካሳሁን ከኪዩ ጃምስ ባንድ ጋር በተወዳጅ ዲጄዎች ዘና እያሉ ውብ ቅዳሜ አመሻሽን ከኛ ጋር ያሳልፉ
ይህ ውብ የሙዚቃ ባህል እና የሁለቱን ሀገራት የሙዚቃ ምሽት ባለን ጥቂት ቦታ በነፃ ተመዝግበው ብቻ ይሳተፋ!
👉https://nz-events.vercel.app/
ቅዳሜ ጥቅምት 29 ጃክሮስ በሚገኘው በቬኑ ዌር ሀውስ በሮች ከ9:00 ጀምሮ ይከፈታሉ።
ብሪቲሽ ካውንስል ከብሪቲሽ ኢንባሲ እና ከ ኤን ዜድ ኮሚዮኒኬሽን ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል
አሁን ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ!
👉https://nz-events.vercel.app/
@nzcommunications @britishcouncilet @ukandethiopia @abbay.tv @marathon_spirits @thesassenachs @kiya.kassahun @milupresents @youbel.music @blackstarboy01 @venuewh @natnaelzer

❤3
“ትናንት እመጣለሁ” መጽሐፍ ዙሪያ የተሰጠ ዳሠሣ
በሥነ ጽሁፍ ውስጥ የተለመዱ አሠራሮችን እና ሕጎችን በተወሰነ መልኩ በማሻሻል (modify) በማድረግ ሙከራዎችን ወይም (experiments) በጥቂት መጽሐፍት አማካኝነት መመልከት ከጀመርን ጥቂት ሳንሰነባብት አልቀረንም፡፡
“ትናንት እመጣለሁ” በተሰኘው ድርሰት ውስጥ የተመለከትናቸው ሙከራዎች ወይም (experiments) ለሥነ ጽሁፋችን ምን ጨመሩ? ወይም ከሥነ ጽሁፋችን ምን አጎደሉ? መጽሀፉንስ Experimental ነው ብዬ ከብያኔ ላይ ለመድረስ ምን አነሳሳኝ?
እንደሚታወቀው ከexperimental ሥነ ጽሁፍ መገለጫዎች መካከል የተወሰኑትን ለመመልከት ብንሞክር አንዱ የምናገኘው መገለጫ የጽሁፉ ከማሕበረሰባዊው ልምድ ወይም (norm) መነጠል መቻሉ ነው፡፡ ልምድ ስንል ከአኗኗል ዘይቤያችን ጋር ብቻም ሳይሆን ሥነ ጽሁፋችን የተቀረጸበትንና እየተላለፈበት ያለበትን መንገድም ማስተዋል ልብ ይሏል፡፡
ተጨማሪውን ያንብቡ:https://shorturl.at/KF969

📌የጉማ ሽልማት ሥነሥርዓት ለ3ኛ ጊዜ ተራዘመ
የመዲናዋ አድማቂ ከሆኑ ዝግጅቶች መካከል አንደኛው የሆነው የጉማ ሽልማት ሥነሥርዓት ዘንድሮ ለ11ኛ ጊዜ ይካሄዳል።
የሽልማት ሥነሥርዓቱን አስቀድሞ ቅዳሜ ጥቅምት 22 2018 ለማካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች የቀን ለውጥ ተደርጎ ወደ ጥቅምት 29 2018 ዓ.ም እንደተዛወር አዘጋጆቹ መግለጻቸው ይታወሳል።
ዛሬ ጥቅምት 26 የሽልማቱ አዘጋጆች ወደ ሕዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ለሶስተኛ ጊዜ የሽልማት ሥነሥርዓቱ እንደተራዘመ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል ።
በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በሚካሄደው የሽልማት ሥነሥርዓት ላይም በርካታ ያሉ አዳዲስ ነገሮች ይስተናገዱበታል።
11ኛውን የጉማ ፊልም ተዋናይት ወለላ አሰፋ እና ተዋናይት ፍቅርተ ጌታሁን የሕይወት ዘመን ተሸላሚ አድርጎ እንደሚሸልም እንዲሁም የዛሬ 50 ዓመት ወ/ት አዲስ አበባ ተብላ የተሸለመችው ወሰኔ ኃይሉ የጉማ ሔርሜላ ተሸላሚ እንደሆኑ ተገልጿል።
በዕለቱ አለባበስ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠውና የሀገር ባህል አልባሳት እንጂ እርቃንን የሚያሳይ አለባበስ እንደማይፈቀድም ተገልጿል።
በተጨማሪም ኀብረተሰቡን ለማሳተፍ የተወሰነ ቲኬት በሽያጭ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚቀርብ ተነግሯል።
የሽልማት ካታጎሪው ዘንድሮ ቀንሶ ወደ 20 እንዲወርድ መደረጉን የተገለፀ ሲሆን የዘንድሮ ሽልማት በአድዋ 130ኛ ዓመት የሚከበርበት ዓመት መሰጠቱ ልዩ እንደሚያደርገው አዘጋጆቹ አስታውቋል።

❤10
📌የባሕል ማዕከል እና ዲኤስቲቪ ጥምረት
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል እና ዲኤስቲቪ በመተባበር ያዘጋጁት የጥበብ ምሽት ተካሄደ
"የአንድ ግጥም አንድ ወግ” ኪነ ጥበባዊ ዝግጅት በድምቀት የተከናወነ ሲሆን በዲኤስቲቪ አቦል ቴሌቪዥን የሚተላለፉ ተወዳጅ ድራማዎችን እያቀረቡ ያሉት ተዋናዮችና ፕሮዲዩሰሮች የዝግጅቱ ልዩ እንግዶች በመሆን ልምዳቸውን አካፍለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ "በሀገራችን የኪነጥበብና በተለይም በቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም ስራዎች ጉልህ አበርክቶ እያከናወነ ካለው ዲኤስቲቪ አቦል ቴሌቪዥን ጋር በትብብር የጥበብ መድረክ ማዘጋጀታችን ወደፊትም ይቀጥላል። ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋርም በትብብር ለመስራት ባሕል ማዕከላችን ክፍት ነው” ሲሉ በመክፈቻ ዝግጅቱ ወቅት ተናግረዋል።
ተጨማሪውን ያንብቡ:https://url-shortener.me/8V83

❤6🔥1
"ዛሬ ቅዳሜ አይደለም" መጽሐፍ የተሰጠ አስተያየት
ከነባር የሥነ ጽሑፍ ሥርዓት ጋር በመዛመድ የራሳቸውን ቅርጽ እና ማንነት የማንፀባረቅ ኃይልን የሚታደሉ. በጊዜ ሂደትም ራሳቸው ከነባር የሥነ ጽሑፍ ሥርዓት ጋር በመመደብ እርስ በእርሳቸው መዛመድ የሚችሉ ነገር ግን የራሳቸውን ቅርጽ እና ማንነት የማንፀባረቅ ኃይልን የሚታደሉ ሌሎችን መፍጠር የሚችሉ መጽሐፍትን በየጊዜዉ ለማየት አንታደልም።
ይህን በቀደመ ሥርዓት ውስጥ መፈጠር የሚችል ነገር ግን ከተፈጠረበት አኗኗር በማፈንገጥ የራሱን ሁለንተና የሚፈጥር "ዛሬ ቅዳሜ አይደለም" የተሰኘ መጽሐፍ ለማንበብ ታደልኩ!
ፈጠራ በተሞላበት "Innovative storytelling technique" የለመድናቸውን የሥነ ጽሑፍ ሰበዞች ያልዳሰሰ ሊያስብል በሚቃጣ ነገርግን በተለየ መንገድ ስለዳሰሰ ፣ ጨርቁን በጣለ "ዕብድ" ይነገራሉ ወይም ይነሳሉ ተብለው የሚታሰቡ ስል ሀሳቦችን እጅግ በተዋዛ አንዳንዴም በፈጠጠ መንገድ በማቅረብ የተደራሲውን ልብ ሰቅዞ በመያዝ ስሙን እንኳን ከማናውቀው ገፀ ባህርይ እስከ መኖሩ የማይታወቅ "ጊዜ" ያለ ውስን "time frame" ነፃነቱን አውጆ ነፃነታችንን የሚያጎናጽፈንን ሥራ በተመለከትኩ ጊዜ እንደ መምህር ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ መጽሐፍ ወዳድ ግለሰብ ተደስቻለሁ።
"የኢትዮጵያን ሥነ ጽሑፍ አንድ እርምጃ..." ፣ "የሀገራችን ሥነ ጽሁፍ ከፍ እያለ ስለመምጣቱ" የሚሉ እና የመሳሰሉ ሀሳቦችን የዘነጋን መስለን በጊዜ ውስጥ እንዳሻን ወደፊት እና ወደኋላ እንዲሁም ወደታች እና ወደላይ እየተረማመድን የፈጠራ አጥር ይገፋ ስላልተሳነው መጽሐፍ ብቻዬን መስካሪ አልሆን ዘንድ ጠይቄያለሁ!
መልካም ንባብ!
"ዛሬ ቅዳሜ አይደለም"
ዮሴፍ ተመስገን (የቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ መምህር)
በድረገፅ ያንብቡ:https://url-shortener.me/92B0

❤4
📌የአዲስ ለገሰ ማስታወሻ ኮንሰርት ዛሬ ይካሄዳል
ድምጻዊ አዲስ ለገሠ "ማስታወሻ" የተሰኘ የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጮች ካደረሰ በኃላ ዛሬ የመጀመሪያ የሙዚቃ ዝግጅቱ ያቀርባል።
ቅዳሜ ጥቅምት 29 2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በሚካሄደው በዚህ ሙዚቃ ዝግጅት ከአዲስ ለገሰ በተጨማሪም መሳይ ተፈራ ካሣና ተዓምር ግዛው የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ያቀረቡበት ተብሏል።
ካዛንቺስ የሚገኘው ኢንተርሌግዤሪ ሆቴል የማስታወሻ የሙዚቃ ድግስ የሚቀርብበት ቦታ ነው።
አዲስ ለገስ ከዚህ የሙዚቃ ድግስ መልስ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የተለያዩ የሙዚቃ መሰናዶዎችን እንደሚያዘጋጅም ተገልጿል።

❤1👍1
📌ዘሪቱ ከበደ ማብራሪያ ልትሰጥ ነው
በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ውስጥ በድምጻዊነቷ እንዲሁም በግጥምና ዜማ፣ በትወና ችሎታዋ ከፍተኛ ስምን ያተረፈችውና በኋላም ሙሉ ጊዜዋን ለመንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ወደ ዝማሬ ዓለም የገባችው አርቲስት ዘሪቱ ከበደ "ከልጅነት እስከ ልጁነት" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ ጽፋ በቅርቡ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።
በግል ታሪኳ ላይ የሚያጠነጥነው ይህ መጽሐፏ በርካታ አነጋጋሪ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል።
ከሰሞኑም የመጽሐፏ ጉዳይ በሁለት ጉራ ከፍሎ ሲያወያይ፣ ሲያከራከርም ተመልክተናል።
አርቲስት ዘሪቱ ከበደ በዚህ መጽሐፏ ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠት ዛሬ ቀጠሮ ይዛለች።
ይህ ቀጠሮ በነገረ መጽሃፍት አዘጋጆች በኩል የተሰናዶ ሲሆን ቅዳሜ ጥቅምት 29 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቀበና በሚገኘው Fss አዳራሽ ውስጥም ይከናወናልም ተብሏል።
የዝግጅቱ አቅራቢና አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ እንደሆነም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

❤18👎3
📌የዳዊት መለሰ አልበም የሚለቀቅበት ቀን ታወቀ
ድምጻዊ ዳዊት መለሰ የመጨረሻ አልበሙን በ1995 ዓ.ም ለአድማጮች ያቀረበ ሲሆን ለዓመታት ተጨማሪ አልበም ሳይሰራ ቆይቷል።
ከሰሞኑም ድምጻዊ ዳዊት መለሰ አዲስ አልበሙን እንዳጠናቀቀ እንዲሁም የሚለቀቅበት ቀን እንደተቆረጠለትም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህ ከሁለት አስርት ዓመታት በኃላ ለአድማጮች የሚቀረበው አልበም "ምስጢር" የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቷል።
ከቀናትም በፊት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የአልበም ማድመጫ ሥነሥርዓት ተከናውኗል።
ከአልበም ማድመጫ ሥነሥርዓት በኃላም ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስርና ገፁ" ሚስጢር የተሰኘውን መጪውን አልበሜን በማካፈል ክብር አግኝቻለሁ።ሚስጢር የዘፈን ስብስብ ብቻ አይደለም። ታሪክ ነው። በመሥራት ላይ 20 ዓመታት ያለፈው። ለሁላችሁም በጣም በቅርቡ እስከ ማካፍላችሁ አጅግ ጓጉቻለሁ" ሲል ጽፏል።
ይህ የዳዊት መለሰ አልበም የፊታችን...
ቀኑን ለማወቅ ተጨማሪውን ያንብቡ: https://url-shortener.me/92H2

❤15
📌ጌትነት እንየው የመኪና ሽልማት ተበረከተለት !
ሁለገቡ ከያኒ ጌትነት እንየው ከሐበሻ ቢራ የBYD መኪና ሽልማት ተበርክቶለታል።
በተጨማሪም ከአቢሲኒያ ባንክ የአምስት ሚሊዮን ብር ስጦታ እነሆ በረከት ተብሏል።
ይህ ሽልማት የተበረከተለት ጌትነት እንየው በኪነጥበቡ ላሳለፋቸው 43 ዓመታት እና ለ68ኛ ዓመት የልደት በዓሉ እውቅና ለመስጠት በተዘጋጀው መርሃግብር ላይ ነው።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ሁለገቡ ከያኒ ጌትነት እንየው ከሐበሻ ቢራ የBYD መኪና ሽልማት ተበርክቶለታል።
በተጨማሪም ከአቢሲኒያ ባንክ የአምስት ሚሊዮን ብር ስጦታ እነሆ በረከት ተብሏል።
ይህ ሽልማት የተበረከተለት ጌትነት እንየው በኪነጥበቡ ላሳለፋቸው 43 ዓመታት እና ለ68ኛ ዓመት የልደት በዓሉ እውቅና ለመስጠት በተዘጋጀው መርሃግብር ላይ ነው።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤44👍24👏5
📌ኮሜዲያን ደረጀ ሀይሌ ተሸለመ
ኮሜዲያን ደረጀ ሀይሌ መቶ ሺህ ብር፣ካባ ዋንጫና ሰአት ተሸለመ።
ዛሬ ማምሻውን በእቴጌ ፊልም ኘሮዳክሽን ተዘጋጅቶ የቀረበው የመዝሙረ ዳዊት አዲስ ሮማንስ ኮሜዲ ፊልም "በቃ ፍቅር" የተሰኘ ፊልም በአዲሱ ህጻናት እና ወጣቶች ቴአትር ቤት ተመርቋል።
በዚህ የፊልም ምረቃ ላይ በፊልሙ ተዋናይ ለሆነው ታላቁ ኮሜዲ ደረጀ ሀይሌ የክብር ካባ፣ ዋንጫ እንዲሁም ከቴምር ፕሮፖርቲስ የአንድ መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል ።በተጨማሪ ደረጀ ሀይሌ አይዛክ ሰዓት ተሸልሟል።

❤25👍6
📌ዶ/ር አንተነህ ፀጋዬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የሥነ ተግባቦት መምህር የሆኑት አንተነህ ፀጋዬ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
በዩኒቨርሲቲው ለበርካታ ዓመታት በማስተማር እና በምርምር ሥራዎች ያገለገሉት ዶ/ር አንተነህ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ኅዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ጀርመንን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እና በአሜሪካ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ዕውቀት የቀሰሙት ዶ/ር አንተነህ፤ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በብሔራዊ ጥቅም እና አጀንዳ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ትንታኔዎችን በመስጠት ይታወቃሉ።

😢16❤4