የፎቶግራፍ እና አጫጭር ፊልሞች ውድድር ይፋ ሆነ
የ5ኛውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የፎቶግራፍ እና አጫጭር ፊልሞች ውድድር በመሳተፍ ዛሬውኑ ይቀላቀሉ ይሸለሙ!
የፎቶግራፍ ውድድር፦ ትምህርት የማግኘት መብት
‘የትምህርት መብት’፦ ሰፊና በርካታ ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች የሚዳስስ ሲሆን ከመሠረታዊ ሰብአዊ መብቶች መካከል የሚመደብ ነው። ማንኛውም ሰው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት በነጻ እንዲያገኝ፤ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በአጠቃላይ ለሁሉም ክፍት፣ ተደራሽ እና በሂደትም በነጻ እንዲቀርብለት፤ እና የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ደግሞ ችሎታን መሠረት አድርጎ ለሁሉም ተደራሽ የሚያደርግ፣ በሂደትም ያለክፍያ ማስገኘት የሚያስችል መብት ነው። በአጭሩ የትምህርት የተጠበቀላቸውን እና ያልተጠበቀላቸውን ልጆችና ወጣቶችን ሁኔታ የሚያሳዩ ፎቶ ግራፎችን በካሜራዎ በማስቀረት ለውድድር ያቅርቡ!
የአጫጭር ፊልሞች ውድድር፦ (ጀማሪ፣ ባለሙያ) ዘርፍ ውድድር የነጻነት መብት
የነጻነት መብት ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ያለመያዝ ወይም ክስ ሳይቀርብበት ወይም ሳይፈረድበት ያለመታሰር መብትን የሚመለከት ነው፡፡ የነጻነት መብት የመጠበቅ እና የማጣት ሁኔታን የሚያስቃኙ አጫጭር ፊልሞችን በሞባይል እና በፕሮፌሽናል ካሜራ በመቅረጽ፣ አርትኦት በመሥራት ይወዳደሩ።
ተወዳዳሪዎች ለውድድር ያቀረቧቸውን ፎቶግራፎች እና አጫጭር ፊልሞች በመቀበል ላይ ነን።
ውድድሩ እስከ ኅዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ክፍት ሆኖ ይቆያል!
ለተጨማሪ መረጃ፦ https://filmfest.ehrc.org
0973149236
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

❤1
📌ሉሲና ሰላም ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ
በቼክ ሪፐብሊክ ለእይታ ቀርበው የነበሩት ሉሲና ሰላም ከሁለት ወር ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
ሁለቱ ቅሪተ አካላት በፕራግ ሙዚየም የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ዛሬ ንጋት ላይ አዲስ አበባ መግባታቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በቆይታቸው ከመላው አውሮፓ በጎረፉ ቱሪስቶች እንደተጎበኙ እና የኢትየጵያን የሰው ዘር መገኛነት በዓለም አደባባይ ማስተዋወቃቸውንም ጨምሮ ገልጿል፡፡
ሁለቱ ቅርሶች ከነሐሴ 19፣ 2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 13፣ 2018 ድረስ በፕራግ ሙዚየም ለሕዝብ እይታ ቀርበዋል፡፡

😁10❤2
📌የድምፃዊ ሐይሉ አመርጋ አልበም ተመረቀ
(አልበሙ አርብ ጥቅምት 21 ይለቀቃል )
የድምፃዊ ሐይሉ አመርጋ “ አሁን“ የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአማራጭ የማሰቢያ ስፍራ በድምቀት ተመርቋል::
በአልበም ስራው ላይ ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ)፣ ብሩክ አፈወርቅ፣ በረከት ተስፋአፅቂ፣ ኤርሚያስ ሞላ እና ኢብራሂም በቅንብር፣ አበጋዝ ክብረወርቅ ሽዎታ እና ሮቤል ዳኜ በሚክሲንግና ማስሪንግ፣ ሀይሉ አመርጋ፣ አክሊሉ ገ/መድህንና ወንደሰን ይሁብ በግጥምና ዜማ ተሳትፈዋል፡፡
በዚህ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ፕሮግራም ላይ ከአዲሱ “ አሁን“ አልበሙ ላይ የሙዚቃ ስራዎቹ በዲጄ የቀረቡ ሲሆን በተጭማሪ ድምጻዊ ሐይሉ አመርጋ የተመረጡ ስራዎቹን በፒያኖ ታጅቦ በአስገራሚ አቀራረብ ለታዳሚው አቅርቧል::
እንዲሁም ስለ ስራዎቹ ከታዳሚው አስተያየት የተሰጠ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የጃኞ ባንድ አባላትን ጨምሮ ድምፃዊያን የሙዚቃ ባለሙያዎች ጋዜጠኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ ተገኝተዋል::
አልበሙ ውስጥ ካሉ ዘፈኖች ለሁለቱ የቪዲዮ ክሊፕ ተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን አልበሙ ከወጣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደሚለቀቁ እና ሶስት የሚሆኑ ዘፈኖቹ ደግሞ ገና እየተሰራላቸው እንደሚገኝ ድምጻዊው ገልጿል፡፡
አልበሙ ከጥቅምት 21 ጀምሮ በሀይሉ አመርጋ የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ መተግበሪያዎች ላይ ይገኛል ሲል ይትባረክ ዋለልኝ ዘግቧል።

❤15👍2🔥1
📌 ሙሴ ሰለሞን ታሰረ
ቲክቶከሩ ሙሴ ሰለሞን መታሰሩን ከታማኝ የመረጃ ምንጮቼ ላረጋግጥ ችያለሁ ሲል ጠበቃ አበባየሁ ጌታ በፌስቡክ ገፁ ጽፏል።
ሙሴ ሰለሞን በምን ምክንያት እንደታሰር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ማረጋገጥ አልቻለም።
ቲክቶከሩ ሙሴ ሰለሞን አጫጭር መረጃዎችን ለቲክቶክ ተከታታዮቹ ሲያቀርብ ይታወቃል።

🤣10❤2😁2😡2👍1
📌"የጨቀየ ጥለት” የተሰኘ የአጭር አጭር ልቦለድ የተካተተበት መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል ተባለ
በተለያዩ ቅርፆች የቀረቡ 20 ተረኮችን የያዘውና በደራሲና የኮሙኒኬሽን ባለሙያው አሸናፊ መለሠ የተፃፈው "የጨቀየ ጥለት" የተሠኘው መጽሐፍ በ200 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን ጥቅምት 24 2018 ዓ.ም ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።
"የጨቀየ ጥለት" መጽሐፍ በይዘት ደረጃ ማኅበራዊ ፣ ፍልስፍናዊና ስነልቡናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ተረኮችን የያዘ ሲሆን በቅርፅ ደረጃ ደግሞ በርከት ያሉ አጫጭር ልቦለዶችን ከመያዙም በላይ በሐገራችን የመጨረሻ ትንሹን የአጭር አጭር ልቦለድ ያካተተ መጽሐፍ እንደሆነም ከደራሲው ሠምተናል።
ደራሲ አሸናፊ መለሠ ከዚህ ቀደም “የዳግማዊ ገፆች” በተሠኘውና በዕለት ማስታወሻ ቅርፅ በቀረበ ልቦለዱ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን ከዚህም ባሻገር በስነፅሁፍ ሒስና ልዩ ልዩ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎቹን ሰርቷል።

❤2👍1
📌ዲጄዎች ድምጻዊያን ላይ ቅሬታ አቀረቡ
አዲስ አልበም የሚሰሩ ድምጻዊያን የአልበማቸው ቅድመ ቅምሻ ላይ ዲጄዎችን መጋበዝ ትተው "ቲክቶከሮችን" እየጋበዙ ነው ሲል የኢትዮጵያ ዲጄዎች ማህበር ቅሬታ አሰምቷል።
ማህበሩ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ እንደፃፈው ድሮ ድሮ አንድ አርቲስት አልበም ሊያወጣ ሲል ዲጄውን ሰብስቦ አልበሜን ስሙልኝ ይል ነበር ብሏል።
አሁን አሁን ግን የሙዚቃን አልበም የሚገመግሙት ቲክቶከሮች እየሆኑ መምጣታቸውን እና ምንም አይነት ዲጄ ተጠርቶ እንደሙያ ስማልኝ መባል ቀርቷል ሲል ተናግሯል።
ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ የወጡ ትልልቅ የአልበም ማድመጥ (ሊስኒንግ) ፓርቲዎች ላይ እንኳን ዲጄው አይጠራም ግን በየክለቡና በየዝግጅቱ "ዘፈኔን አጫውቱልኝ" ይባላል ሲል ማህበሩ ትዝብቱን ጠቅሷል።
"ለምን አልተጠራንም" እያልን ሳይሆን አሁንም ሙያው የተሳሰረ መሆኑን አትርሱት ዞሮ ዞሮ እዚሁ ናችሁ ለማለት ነው ሲልም ቅሬታውን ደምድሟል።
©️አሁናዊ መረጃ

😁36❤10
📌"በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት እሁድ ይመለሳል
በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፋ የተዘጋጀው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ከፊታችን እሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ዕሁድ በ8:00 ሰዓት በሀገር ፍቅር ቴአትር በድጋሚ መቅረብ እንደሚጀምርም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዘጋጁ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፋ የተዘጋጀው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ከፊታችን እሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ዕሁድ በ8:00 ሰዓት በሀገር ፍቅር ቴአትር በድጋሚ መቅረብ እንደሚጀምርም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዘጋጁ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤26
በነፃ የቀረበ እድል !
የኢ-ኮሜርስ ድርጅትዎት በነፃ ያስተዋውቁ !
ኢ-ኮሜርስ ( E-Commerce) ላይ እየሰራችሁ ለምትገኙ ተቋማት አስደሳች መረጃ እንነግራችኋለሁ።
የኢ-ኮሜርስ ተቋማት አገልግሎቶቻችሁን ያለምንም ክፍያ በነፃ በተወዳጁ ትርታ ኤፍ ኤም 97.6 በኩል የምታስተዋውቁበት እድል ተዘጋጅቶላቸዋል።
ምርትና አገልገሎትዎን ለማስተዋወቅ ተከታዮቹን አድራሻዎች ይጠቀሙ፣ይደውሉ ፣በነፃ ያስተዋውቁ:-
ስልክ: 0983111555
0931268671
@Sara.m@tiritfm.com
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ 🙏

👍6❤3
📌የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተጀመረ
የአፍሪካን የቆዳ፣ የጨርቃጨርቅ፣ የአልባሳትና የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪዎችን የሚመራው 11ኛው የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት (AFRICA SOURCING AND FASHION WEEK) ከጥቅምት 20 እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ በሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ማዕከል ይካሄዳል።
የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት ከጨርቃጨርቅ፣ ከአልባሳት፣ ከቆዳ፣ ከቴክኖሎጂ እና ከቤት ማስጌጫ ዘርፎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትን ያሳትፋል።
ከ30 በላይ አገሮችን የሚወክሉ ከ200 በላይ አምራቾች በሚሳተፉበት በዚህ ዝግጅት ላይ፣ ምርቶችና ፈጠራዎች ከ7ሺ ለሚበልጡ የንግድ ባለሙያዎችና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ተመልካች ፊት ቀርበው የሚታዩበት መድረክ ነው።
የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት ላለፉት ዓመታት ከ50ሺ በላይ አዳዲስ የስራ ዕድሎችን ለወጣቶች መፍጠር መቻሉን ተገልጿል።
በዚህ በ11ኛው የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት ላይ በዘርፉ ወሳኝ የሆኑ ርዕሶችን ማለትም የኢኮኖሚ፣ የአእምሯዊ ንብረት መብቶች (INTELLECTUAL PROPERTY RIGHTS) እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሚና ላይ ትኩረት ያደርጋል።

❤3👍2
📌የድምፃዊ ሐይሉ አመርጋ አልበም ተለቀቀ
በበርካቶች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የድምፃዊ ሐይሉ አመርጋ “ አሁን“ የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በሀይሉ አመርጋ የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል ለሙዚቃ አፍቃሪያን ቀርቧል።
በአልበም ስራው ላይ ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ)፣ ብሩክ አፈወርቅ፣ በረከት ተስፋአፅቂ፣ ኤርሚያስ ሞላ እና ኢብራሂም በቅንብር፣ አበጋዝ ክብረወርቅ ሽዎታ እና ሮቤል ዳኜ በሚክሲንግና ማስሪንግ፣ ሀይሉ አመርጋ፣ አክሊሉ ገ/መድህንና ወንደሰን ይሁብ በግጥምና ዜማ ተሳትፈዋል፡፡
አልበሙ ውስጥ ካሉ ዘፈኖች ለሁለቱ የቪዲዮ ክሊፕ ተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን አልበሙ ከወጣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደሚለቀቁ እና ሶስት የሚሆኑ ዘፈኖቹ ደግሞ ገና እየተሰራላቸው እንደሚገኝ ድምጻዊው ገልጿል፡፡
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
በበርካቶች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የድምፃዊ ሐይሉ አመርጋ “ አሁን“ የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በሀይሉ አመርጋ የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል ለሙዚቃ አፍቃሪያን ቀርቧል።
በአልበም ስራው ላይ ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ)፣ ብሩክ አፈወርቅ፣ በረከት ተስፋአፅቂ፣ ኤርሚያስ ሞላ እና ኢብራሂም በቅንብር፣ አበጋዝ ክብረወርቅ ሽዎታ እና ሮቤል ዳኜ በሚክሲንግና ማስሪንግ፣ ሀይሉ አመርጋ፣ አክሊሉ ገ/መድህንና ወንደሰን ይሁብ በግጥምና ዜማ ተሳትፈዋል፡፡
አልበሙ ውስጥ ካሉ ዘፈኖች ለሁለቱ የቪዲዮ ክሊፕ ተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን አልበሙ ከወጣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደሚለቀቁ እና ሶስት የሚሆኑ ዘፈኖቹ ደግሞ ገና እየተሰራላቸው እንደሚገኝ ድምጻዊው ገልጿል፡፡
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤14🔥1
በነፃ የቀረበ እድል !
የኢ-ኮሜርስ ድርጅትዎን በነፃ ያስተዋውቁ !
ኢ-ኮሜርስ ( E-Commerce) ላይ እየሰራችሁ ለምትገኙ ተቋማት አስደሳች መረጃ እንነግራችኋለሁ።
የኢ-ኮሜርስ ተቋማት አገልግሎቶቻችሁን ያለምንም ክፍያ በነፃ በተወዳጁ ትርታ ኤፍ ኤም 97.6 በኩል የምታስተዋውቁበት እድል ተዘጋጅቶላቸዋል።
ምርትና አገልገሎትዎን ለማስተዋወቅ ተከታዮቹን አድራሻዎች ይጠቀሙ፣ይደውሉ ፣በነፃ ያስተዋውቁ:-
ስልክ: 0983111555
0931268671
@Sara.m@tiritfm.com
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ 🙏
የኢ-ኮሜርስ ድርጅትዎን በነፃ ያስተዋውቁ !
ኢ-ኮሜርስ ( E-Commerce) ላይ እየሰራችሁ ለምትገኙ ተቋማት አስደሳች መረጃ እንነግራችኋለሁ።
የኢ-ኮሜርስ ተቋማት አገልግሎቶቻችሁን ያለምንም ክፍያ በነፃ በተወዳጁ ትርታ ኤፍ ኤም 97.6 በኩል የምታስተዋውቁበት እድል ተዘጋጅቶላቸዋል።
ምርትና አገልገሎትዎን ለማስተዋወቅ ተከታዮቹን አድራሻዎች ይጠቀሙ፣ይደውሉ ፣በነፃ ያስተዋውቁ:-
ስልክ: 0983111555
0931268671
@Sara.m@tiritfm.com
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ 🙏
በነፃ የቀረበ እድል !
የኢ-ኮሜርስ ድርጅትዎን በነፃ ያስተዋውቁ !
ኢ-ኮሜርስ ( E-Commerce) ላይ እየሰራችሁ ለምትገኙ ተቋማት አስደሳች መረጃ እንነግራችኋለሁ።
የኢ-ኮሜርስ ተቋማት አገልግሎቶቻችሁን ያለምንም ክፍያ በነፃ በተወዳጁ ትርታ ኤፍ ኤም 97.6 በኩል የምታስተዋውቁበት እድል ተዘጋጅቶላቸዋል።
ምርትና አገልገሎትዎን ለማስተዋወቅ ተከታዮቹን አድራሻዎች ይጠቀሙ፣ይደውሉ ፣በነፃ ያስተዋውቁ:-
ስልክ: 0983111555
0931268671
@Sara.m@tiritfm.com
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ 🙏
የኢ-ኮሜርስ ድርጅትዎን በነፃ ያስተዋውቁ !
ኢ-ኮሜርስ ( E-Commerce) ላይ እየሰራችሁ ለምትገኙ ተቋማት አስደሳች መረጃ እንነግራችኋለሁ።
የኢ-ኮሜርስ ተቋማት አገልግሎቶቻችሁን ያለምንም ክፍያ በነፃ በተወዳጁ ትርታ ኤፍ ኤም 97.6 በኩል የምታስተዋውቁበት እድል ተዘጋጅቶላቸዋል።
ምርትና አገልገሎትዎን ለማስተዋወቅ ተከታዮቹን አድራሻዎች ይጠቀሙ፣ይደውሉ ፣በነፃ ያስተዋውቁ:-
ስልክ: 0983111555
0931268671
@Sara.m@tiritfm.com
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ 🙏
📌 የስብሐቲዝም አንድ መቶኛ መድረክ
ስብሐቲዝም የሐሳብ፣ የንባብ፣ የውይይት መሰናዶ አንድ መቶኛ መድረክ ነገ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት(ወመዘክር )ይካሄዳል።
በዚህ መሰናዶ ላይ ተከታዮቹ መርሐግብሮች ይቀርባሉ:-
ዶክተር ዓለማየሁ አረዳ ሰው ስለምን አመክንዮአዊ እንሰሳ (Rational Animal) ተባለ? ብለው አርስቶትላዊ ሐሳባቸውን ሊነግሩን ወጥነዋል
ጋሽ ዘነበ ወላ 'ሰው መሆን በጋሽ ስብሐትለአብ ውስጥ' ምን ይመስል ነበር ይለናል።
ቡርሃን አዲስ 'ኑ ሰውነት'ን እንገንባ' ብሎ ፍልስፍናዊ ሐሳቡን ይነግረናል።
ጋሽ ኃይለመለኮት ገጠመኞቻቸው ውስጥ እየተመላለሱ የሚያጫውቱን የሰው መሆን ልክ አለ።
ወጣቶቹ ጋሽ ስብሐት ለወጣቶች ስስ ዓይን አለውና እነሱም በሰሱ መንፈስ ውስጥ አለሁ እያሉ ያውሉናል።
አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት በመድረክ ላይ ይመደረካል/Monologue/
የወመዘክር አዲሱ ሕንጻ 13ኛው ፎቅ መቶኛውን የስብሐቲዝም መድረክ ለማሰናዳት ክፍት ነው።

❤4🥰2
📌 "አልንበረከክም" መጽሐፍ ሰኞ ይመረቃል
የገጣሚ እና ተዋናይ ዋሲሁን በላይ 5ኛው የሥነ-ጽሑፍ ስራ "አልንበረከክም" በብሔራዊ ቴአትር ሊመረቅ ነው።
"አንበረከክም" በሚል ርዕስ በሁለገቡ ከያኒ ዋሲሁን በላይ የተዘጋጀው አዲስ መጽሃፍ የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 24 2018 ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትአቴር ቤት ይመረቃል።
በዕለቱም በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሀሳቦቻቸው ያጋራሉ ተብሏል።
የመፅሃፍ አፍቃሪዎች፣ የጥበብ ሰዎችና የመድረክ ታዳሚዎች በዚህ የመጽሐፍ ምረቃ ላይ በክብር ተጋብዛችኋል ተብላችኋል።

👍7❤1
📌አርቲስት ተስፋዬ አበበ የግጥም እና የዜማ ሥራቸውን ለአብነት የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች አስረከቡ
አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) በኢትዮጵያ ቀዳሚ ለሆነው ለአብነት የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች፤ የግጥምና የዜማ ሥራዎቻቸውን በዛሬው ዕለት በይፋ አስረክበዋል፡፡
አርቲስቱ በሥማቸው በተሰየመው የኪነ-ጥበብ ማዕከል ውስጥ የአብነት የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ነው ሥራዎችቸውን ያስረከቡት፡፡
የልዩ ፍላጎት ትምህርት መርሃ ግብርን ጨምሮ በሁሉም ዕድሜ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች፤ ያላቸውን ምቹና ተስማሚ እምቅ አቅምና በዋጋ ሊተመን የማይችል አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ ለተቋቋመው አብነት የማህበረሰብ ት/ቤቶች አርቲስቱ ሥራቸውን ማስረከባቸው ተገልጿል።
በኪነ ጥበብ ማዕከሉ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ወርቅነህ፤ የአብነት አካዳሚ ለአርቲስት ተስፋዬ አበበ እስከ ሕይወት ዘመናቸው ድረስ በተለያየ መንገድ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።
ስለ አርቲስቱ ሥራ እና ለትምህርት ቤታቸው ስለተበረከተው ሥራም ምስጋና አቅርበዋል።
በመድረኩ በማዕከሉ ተማሪዎች የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ሥራዎች ለታዳሚዎች ቀርበዋል።
©️አሐዱ ሬድዮ

❤14👏5
📌የደራሲ ናትናኤል ቀረዓለም መጽሐፍት!
“…ሕይወት ቀላል ነበረች፣ ቀላልም ትሆን ነበር፡፡ ሞታችንን እንደሞታችን እንጂ እንደሞታቸው ላንሞት… ሕይወትን እንደ ሕይወታችን ከመኖር ይልቅ እንደ ሕይወታቸው ለመኖር መረጥን!... ለምን?” "ዛሬ ቅዳሜ አይደለም” ከተሰኘው መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡
“…በመጀመሪያ ልቧ ባዶ ነበር። ሐረጓ በቅጥር ላይ ያድግ እንዲሆን የሚታሰብ በምንጭ አጠገብ ያፈራ እንደሚሆን የፍሬ ዛፍ ያልተዘነጋች። የተዘነጋች የመሰላት።
የፍቅር አምላክ ይጎበኛት ዘንድ ጥቂት መጠበቅ ይጠበቅባት እንደነበር የዘነጋች። መጠበቋን ሳትጠብቅ ትኖር የነበረች አንዲት ባዶ ልብ ነበረች። ክፋትና ተንኮልን፣ አመጽና እብሪትን፣ ትዕቢትና ትምክህትን ታውቅ ያልነበረች፣ አታውቅ ያልነበረች ልብ ነበረች።
በመጀመሪያ ልቧ ባዶ ነበር? ባዶነት በልቧ ሰፍፎ አልነበረም? ባዶነት የሞላው ልብ እንዴት ባዶ ይባላል? ባዶነት የሞላውን ልቧን እንደታቀፈች ትኖር ነበር። ማታም ሳይሆን፣ጠዋትም ሳይሆን በፊት። “ትናንት እመጣለሁ” ከተሰኘው መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡
“…ከማይነጋው ሌሊት፤ ከማይጨልመው ቀን አጋማሽ… ምርጫ በእጅህ አልነበረችም… ያደለችህን ትቀበል እንጂ ትጠይቅም ሆነ መሻትህ ይፈጸም ዘንድ ትማልድ… ብትማልድም ከቀኝህ በሚሆን አልታደልክም… ፍርሃትና ድንዛዜ በሞላው… ምናልባትም በሚሞላው ቆይታህ ከሐሴት ትጎራበትም ሆነ… ከነፍስ እስራት ነፃ ትወጣ ዘንድ ስለመታደልህ እርግጠኛ አይደለህም… እውነት ከአንተ ዘንድ ነች… ብትነግረን አናምንም… ብትጠይቀን አንመልስም፡፡…” “እውነት / አዛምድ” ከተሰኘው መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡
ሁሉንም መጻሕፍት በጃፋር መጻሕፍት መደብሮች ማግኘት ይችላሉ፡፡
አሳታሚ እና አከፋፋይ - ጃፋር መጻሕፍት
ደራሲውን ለመወዳጀት: https://www.facebook.com/natnael.kerealem

❤9
📌የሁለት ሀገራት የሙዚቃና ባህል ድግስ
ወደ እንግሊዝ ሳይጓዙ እዚሁ አዲስ አበባ ላይ በአንድ መድረክ የሁለት ሀገራት የሙዚቃ ባህል ተደግሷል!
ዩኬ ኢትዮ ሚዮዚክ ኮንሰርት
ለማይረሳው ውብ ምሽት ይዘጋጁ!
ከእንግሊዝ የተውጣጡ The sassenachs Ceilidh Band
ከኢትዮጵያ ድምፃዊት ጠረፍ ካሳሁን ከኪዩ ጃምስ ባንድ ጋር በተወዳጅ ዲጄዎች ዘና እያሉ ውብ ቅዳሜ አመሻሽን ከኛ ጋር ያሳልፉ
ይህ ውብ የሙዚቃ ባህል እና የሁለቱን ሀገራት የሙዚቃ ምሽት ባለን ጥቂት ቦታ በነፃ ተመዝግበው ብቻ ይሳተፋ!
👉https://nz-events.vercel.app/
ቅዳሜ ጥቅምት 29 ጃክሮስ በሚገኘው በቬኑ ዌር ሀውስ በሮች ከ9:00 ጀምሮ ይከፈታሉ።
ብሪቲሽ ካውንስል ከብሪቲሽ ኢንባሲ እና ከ ኤን ዜድ ኮሚዮኒኬሽን ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል
አሁን ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ!
👉https://nz-events.vercel.app/
@nzcommunications @britishcouncilet @ukandethiopia @abbay.tv @marathon_spirits @thesassenachs @kiya.kassahun @milupresents @youbel.music @blackstarboy01 @venuewh @natnaelzer

❤3
“ትናንት እመጣለሁ” መጽሐፍ ዙሪያ የተሰጠ ዳሠሣ
በሥነ ጽሁፍ ውስጥ የተለመዱ አሠራሮችን እና ሕጎችን በተወሰነ መልኩ በማሻሻል (modify) በማድረግ ሙከራዎችን ወይም (experiments) በጥቂት መጽሐፍት አማካኝነት መመልከት ከጀመርን ጥቂት ሳንሰነባብት አልቀረንም፡፡
“ትናንት እመጣለሁ” በተሰኘው ድርሰት ውስጥ የተመለከትናቸው ሙከራዎች ወይም (experiments) ለሥነ ጽሁፋችን ምን ጨመሩ? ወይም ከሥነ ጽሁፋችን ምን አጎደሉ? መጽሀፉንስ Experimental ነው ብዬ ከብያኔ ላይ ለመድረስ ምን አነሳሳኝ?
እንደሚታወቀው ከexperimental ሥነ ጽሁፍ መገለጫዎች መካከል የተወሰኑትን ለመመልከት ብንሞክር አንዱ የምናገኘው መገለጫ የጽሁፉ ከማሕበረሰባዊው ልምድ ወይም (norm) መነጠል መቻሉ ነው፡፡ ልምድ ስንል ከአኗኗል ዘይቤያችን ጋር ብቻም ሳይሆን ሥነ ጽሁፋችን የተቀረጸበትንና እየተላለፈበት ያለበትን መንገድም ማስተዋል ልብ ይሏል፡፡
ተጨማሪውን ያንብቡ:https://shorturl.at/KF969