Event Addis Media
9.6K subscribers
6.06K photos
12 videos
4 files
4.68K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ሀይማኖት ግርማ ለልጇ የቤት ስጦታ ሰጠች

ድምፃዊት ሀይማኖት ግርማ "ልጄ አሜን አልበሜን ስሰራ ቀን እና ማታ ሳይል አብሮኝ ስለለፋ በአዲሱ አመት ስጦታ" በማለት የመኖሪያ ቤት ስጦታ ማበርከቷ ተሰምቷል።

ልጇ አሜንም "እኔ ግዴታዬን ነው የተወጣውት።ከዚህ በኋላ በህይወትሽ ላይ ለሚገጥምሽ ማንኛውም ነገር ከጎንሽ ነኝ" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
13👎5🥰1👏1
📌የሜሮን ጌትነት አዲስ መጽሐፍ ታተመ

የሁለገቧ ከያኒ ሜሮን ጌትነት "ሌላ ዕውነት የለኝም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መፅሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል ተብሏል።

"ሌላ ዕውነት የለኝም" መጽሐፍ ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘና በ134 ገፆች የተቀነበበ ነው።

ሜሮን በተለያየ ጊዜ የጻፈቻቸውን ግጥሞች በአንድ ላይ አድርጋ ለሕትመት ያበቃች ሲሆን ግጥሞቹም በግላዊ ገጠመኝና ዕይታ ላይ ትኩረታቸውን ያደርጋሉ።

ገጣሚ ሜሮን ጌትነት ስለመጽሐፏ "ሌላ እውነት የለኝም በተለያየ ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ ውስጥ ሆኜ የፃፍኳቸው ግጥሞች ስብስብ ነው። ግላዊ ስሜቶች፣ እውነቶችና በህይወት መስመር ላይ ያስተዋልኳቸው ማህበራዊ ሁነቶች ከጫሩብኝ ሀሳቦች ተነስቼ የከተብኳቸው ናቸው ትወዷቸዋላችሁ"ስትል ሀሣቧን ለተወዳጅ ሚድያ ገልጻለች።

ለ10 ዓመታት መኖሪያዋን ባህር ማዶ አድርጋ የነበረችው የኪነ- ጥበብ ሰው ሜሮን ጌትነት  ለጥቂት ዓመታት ከጥበቡ ዓለም ራቅ ብላ መቆየቷ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
25👍3👏2🥰1
📌ለ1 ሚሊየን ዶላር አሸናፊነት ይወዳደራሉ

ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች በአሜሪካ ጎት ታለንት ለ1 ሚሊየን ዶላር አሸናፊነት ይወዳደራሉ።

በ2025 የአሜሪካ ጎት ታለንት እየተወዳደሩ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች ቶማስ አለሙ እና ታምራት አያሌው ቲቲ ቦይስ ወደ ፍጻሜ ማለፍ ችለዋል።

ቲቲ ቦይስ ከሌሎች 8 ተወዳዳሪዎች ጋር በመፋለም ነው 4 ተወዳዳሪዎች ብቻ ወዳለፉበት የፍጻሜ ውድድር የተቀላቀሉት፡፡

ኢትዮጵያውያኑ የሰርከስ አርቲስቶች ቲቲ ቦይስ በተመልካች እና በውድድሩ ዳኞች ከፍተኛ አድናቆት ተችሯቸዋል።

በዳኞች በተሰጣቸው አስተያየት ሥራቸው ድንቅ የሆነ ተሰጥኦና በዓመቱ ከታዩ ክስተቶች አንዱ ነው ተብሎላቸዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ማህበር ጥምረት ፕሬዚዳንት ተክሉ ተሻገር ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያውያን በዚህ ዓለም አቀፍ ግዙፍ የተሰጥኦ ውድድር መድረክ ለፍጻሜ ሲደርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ይህም ለኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሁሌም የሚጠቀስ ትልቅ ስኬት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

የውድድሩ ሽልማት የሆነውን 1 ሚሊየን ዶላር ለማሸነፍ የሕዝብ ድምፅ ወሳኝ ሲሆን ÷ ለተወዳዳሪዎች ድምፅ በመስጠት ልንደግፋቸው ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል ሲል FMC ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
21👍8
📌አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ በአሜሪካ ኤምባሲ ልዩ እንግዳ በመሆን ይቀርባል

(መግቢያው በነፃ ነው)

በስምንተኛው የCREATOR LAB ዝግጅት  ላይ የፊልም ተዋናይ፣ ደራሲ እና ዳይሬክተር እንዲሁም ፕሮዲዩሰር የሆነውን ቸርነት ፍቃዱ እንግዳ ሆኖ ይቀርባል። 

ቸርነት ፍቃዱ 13 ፊልሞች ላይ በትወና 6 ፊልሞች ላይ በ ፕሮዲዩሰርነት እና 5 ቴያትሮች ላይ ደግሞ በትወና ተሳትፏል።

በብዙዎች ዘንድም ተወዳጅነትን ያተረፈው እና የተመልካችን ቀልብ የሳበው "ኪያ" እና "ጥላዬ" ፊልም ላይ ሲሆን በድርሰትም በትወናም ተሳትፏል። ቸርነት በቀርቡ በሰራው ስራም ቀንጃ ፊልም ላይ በ ፕሮዲዩሰር እና በትወና መሳተፉ ይታወቃል ።


በዚህ ዝግጅት ላይም በቅርቡ በወጣው ቀንጃ ፊልም ላይ ስለ ፊልሙ አሰራር ፣ ገጠመኞች እንዲሁም የራሱን የሂዎት ተሞክሮ ለ እናንተ ለተሳታፊዊች ለማካፈል ቀጠሮ ይዘናል። ሰለሆነም በዚህ መድረክ ላይ እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

ተዋናይ ፤ ደራሲ እንዲሁም አዘጋጅ የመሆን ፍላጎት ያላችሁ እና በ ሙያው ላይ ልምድ ያላችሁ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛ ዕድል ለእናንተ ነው።


📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 (  ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

📅 ቀን: ማክሰኞ - መስከረም 6 ፣ 2017

🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00 

🎟 መግቢያ: ነፃ

አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር

📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
17
📌‎የክቡር ዶክተር ሃዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ካስፈተናቸው 25 ተማሪዎች መካከል 24ቱ ከ529 በላይ ውጤት አምጥተዋል።

‎የክቡር ዶክተር ሃዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ደረጀ ከፈለኝ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ  ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩን አስረድተዋል።

‎አዳሪ ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ ለ3ኛ ጊዜ  የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በመስጠት በክልሉ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

በአዳሪ ት/ቤቱ በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 25 ተማሪዎች መውሰደቸውን የተናገሩት አቶ ደረጀ  ከ25 ተፈታኞች መካከል 24ቱ ከ529 በላይ፤ ማምጣታቸውንና 3 ተማሪዎች ደግሞ  573 ያመጡ ሲሆን፤  አንድ ተማሪ 407 ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል።

‎25ቱም ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህር ዘርፍ ፈተና መውሰዳቸውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አስረድተዋል።

Via tikvahuniversity

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
👏2916
📌አሻም ቴሌቪዥን የስራ ማስታወቂያ አውጥቷል

ቴሌቪዥን ጣቢያው 4 ሪፖርተሮችን ይፈልጋል።

በተጨማሪም ኤዲተር ፣ የፕሮግራም ክፍል ኃላፊ እና የሽያጭ ባለሞያም እፈልጋለሁ ብሏል።

የአሻም ቴሌቪዥን ባልደረባ መሆንን የምትሹ ተመዝገቡ። ተወዳደሩ ።ይቅናችሁ እንላለን።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
13🥰4
ይህ የዘናጭ ፍላወርስ መልዕክት ነው

ቆይ መቼ ነው ህይወቴ ለምትላት ሚስትህ እቅፍ አበባ አስታቅፈሀት ቀኗን የምታሳምርላት...

መቼስ ነው  ለፍቅረኛህ  የፈካ ፅጌረዳ ሰጥተህ ቀኗን የምታፈካው?

ኧ ?

መቼ አሰብክ

ነገ አይባልም።

ፍቅርን ፣ደስታን ፣ለመግለፅ  ቆይ ነገ፣ከነገ ወዲያ አይባልም።

ለዚህ ደግሞ ዘናጭ ፍላወርስ አሉልህ ።

📍 አድራሻቸው ሰሚት ፍየል ቤት 20 ሜተር ላይ ተገኘዋለህ።

ከደወልክም ያለህበት ይልኩልሃል ።

☎️09 22 74 04 75 
6🥰3😁1
📌ጋዜጠኛ አልዳ ግዛቸው ብራንድ አምባሳደር ሆነች

አስቀድሞ በሸገር 102.1 ሬድዮ አሁን ላይ በኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተለያዩ መሰናዶዎችን በማዘጋጀት እና በማቅረብ የምትታወቀው ጋዜጠኛ ኤልዳ ግዛቸው የ"ቢሃይንድ ዘ ሲን" ብራንድ አምባሳደር በመሆን እንደተሾመች ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኤልዳ ግዛቸው ብራንድ አምባሳደር ሆኖ የተሾመችበት"ቢሃይንድ ዘ ሲን" በሰባት የአፍሪካ ሀገራት እየተከወነ የሚገኝ የጥናት እና የምርምር ፕሮጀክት ነው ተብሏል።

መርሐግብሩ የኪነጥበብ ሙያ ላይ ያሉ ወጣት ሴቶች ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግም ተገልጿል።

ሙያተኞች ያላቸውን ሚና፣ ተግዳሮት እና ተስፋ በየሀገራቱ ማጥናት እና የጥናት ውጤቶቹን ለልዩ ልዩ አገልግሎት በተለይም ለፖሊሲ ግብአት እንዲውሉ ያደርጋል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት ላይ OSSREA፣ ICRW ከMaster Card Foundation ጋር ተባብረው ይሰራሉም ተብሏል።

ጋዜጠኛ አልዳ ግዛቸው ከጋዜጠኝነቷ ባሻገር በተለያዩ መድረኮች እና ማህበራዊ ትስስር ገፆቿ በኩል በምታጋራቸው የሥነጽሑፍ ሥራዎቿም ትታወቃለች።

📲 TikTok:

https://www.tiktok.com/@eldagizachew?_t=ZM-8ycUyGgkmYC&_r=1

📸 Instagram: https://www.instagram.com/elda_gizachew?igsh=ZGFudHJvY3d0bzJ0

▶️ YouTube: http://www.youtube.com/@eldacorner369

#BehindTheScenesAfrica #CreativeEquity #YoungWomenInArts #NationalCreativeAmbassador
12❤‍🔥1🔥1
📌አበረ አዳሙ ለብሪክስ የሥነጽሑፍ ሽልማት ታጩ

ደራሲ አበረ አዳሙ ለብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ላይ እጩ ሆነው እንደቀረቡ ተሰምቷል።

የብሪክስ የእጩ ዝርዝሩ በብራዚሊያ በተካሄደው ሁለተኛው የብሪክስ የባሕላዊ እሴቶች ጉባኤ ላይ ይፋ ተደርጓል።

በዝርዝሩ ከብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ግብፅ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ኢራንና ኢንዶኔዥያ ጨምሮ ከሌሎችም ሀገራት የተወጣጡ 27 ደራሲያን ተካተውበታል፡፡

በብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ዙሪያ በተካሄደው ውይይት ወቅት፤ የሥነ ጽሑፍ ምሁራንና አሳታሚዎችን የሚያካትት የብሪክስ ሀገራት የጸሐፊዎች ማኅበር ምሥረታም እውን ሆኗል፡፡ የማኅበሩ ዋነኛ ዓላማ ቀጣይነት ያለው የባሕል ልውውጥን ማሳደግ እና በሥነ ጽሑፍ መስክ የሚደረጉ ጥረቶችን ማስተባበር እንዲሁም የሽልማቱን አዘጋጅ ኮሚቴ መደገፍ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
7👏7
📌ዋልያ የሀሳብና መጽሐፍ መድረክ ቅዳሜ ይጀምራል

በዋልያ መጻሕፍት መደብር አዘጋጅነት የሚሰናደው  "ዋልያ የሀሳብና መጽሐፍ መድረክ" የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 8 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ  መካሄድ ይጀምራል።

በመጀመሪያ መሰናዶው ላይ ዶ/ር ሀብቴ ጀቢሳ በእንግድነት ተጋብዘዋል የመወያያ ርዕሱም "የምንመገበው ምግብ የያዘው ደቂቅ ንጥረ ነገር የአእምሮ የማሰብ ጉልበትን እንዴት እንደሚነካ እና በማኅበራዊ የኑሮ መስተጋብራችን በሚያስከትለው አሉታዊ እና አዎንታዊ ተጽዕኖ ዙሪያ ይሆናል ተብሏል።

እንደ መነሻ "ቀንጨራነት እና ድኽነት በኢ/ያ” በተሰኘው መጽሐፍ ዙሪያ ላይ ታ'ከን ሀሳባችንን እያነሳን የምንጥል ይሆናል ብለዋል አዘጋጆቹ። መጽሐፉ የአዕምሮ እና የአካል መቀንጨር በሀገር እድገት ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ እያብራራ በዛውም የመፍትሄ ሀሳብ  ይጠቁመናል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1
📌"የተመለሱ እይታዎች" አውደርዕይ ተከፈተ

የሠዓሊ ኪሩቤል ተፈሪ የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "የተመለሱ እይታዎች" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ትላንትና ረቡዕ መስከረም 7 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል።

ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ጥቅምት 3 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
7
📌ሸገር ጋዜጠኞቼ ከታሰሩ 17 ቀናት ሆናቸው አለ

የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጋዜጠኞች፣ አርታኢ ትዕግስት ዘሪሁን እና ሪፖርተር ምንታምር ፀጋው፣ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቁጥጥር ስር ከዋሉ 17 ቀን ሆናቸው።

የፌዴራል ፖሊስ፣ ጋዜጠኞቹን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው፣ ያሰራጩት ዘገባ በሕግ የተከለከለ ይዘት ያለውና የሽብር ድርጊት ነው ብሎ እንደሆነ፣ ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት  የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቅድለት፣ ባቀረበው ማመልከቻ ጠቁሟል፡፡

የሕክምና ባለሞያዎች፣ ለመንግስት ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ፣ የጤና ሚኒስቴር በሰርኩላር ያስተላለፈውን መፍትሄ፣ እንዴት እንደሚመለከቱት፣ የሕክምና ባለሞያ ቃለ መጠይቅ በማድረግ፣ ነሐሴ 24 በሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ፣ ዜናው ተላልፎ ነበር፡፡

በዚሁ ዜና ምክንያት የፌዴራል ፖሊስ፣ ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁን እና ምንታምር ፀጋውን፣ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ፣ ምክንያቱን ዘርዝሮ፣ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው በመጠየቁ፣ ፍርድ ቤቱ ዘጠኝ ቀን ፈቅዶለት ነበር፡፡

በቀጣዩ ቀጠሮ፣ የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ፣ የገንዘብ ዝውውራቸውን እና ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስን ምክንያትና ከጋዜጠኞቹ የቀረበውን መከራከሪያ ያዳመጠው፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ፣ ጋዜጠኞቹ በ50,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በትዕዛዙ መሰረት፣ መስከረም 7/2018 ከሰዓት በኋላ፣ አስፈላጊው ፎርማሊቲ ተሟልቶ፣ ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ደርሶታል፡፡

ይሁንና፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ውሳኔ በይግባኝ፣ ወደ ፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመወሰዱ፣ ለመስከረም 12/2018 ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
9🤬3👍1👎1🤔1😢1
📌 አዳብና ፌስቲቫል በሁለት ከተሞች ይከበራል

የ2018 የክስታኔ አዳብና ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እና ኬላ ከተሞች በድምቀት እንደሚከበር ተነገረ።

አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማኀበር እና አክራሚ የሴቶች በጎ አድራጎት ማህበር በጥምረት አዳብና በፌስቲቫል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ይካሄዳል።

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አዳብና በአዲስ አበባ ጥቅምት 02 2018 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን ቀደም ብሎ መስከረም 24 2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን በኬላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እንደተደረገ ተነግሯል።

የአዳብና ባህል የልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ጨዋታና መተጫጫ ሥነሥርዓት ሲሆን 800 ዓመታት በፊት በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ አካባቢ ለዘመናት ሲከበር ኖሯል።

አዳብና በከስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ይህ ድንቅ የሆነ የአዳብና ባህል በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት በUNESCO እንዲመዘገብ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

መላው ኢትዮጵያውያን መስከረም 24 ኬላ እና ጥቅምት 02 በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ የሚከበረውን ፌስቲቫል ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርበዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
9
የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

1. አንጋፋዋ ድምጻዊት አስቴር አወቀ ከዓመታት በኃላ በልዩ የሙዚቃ ድግስ በአዲስ አበባ ከአድናቂዎቹ ልትገናኝ ነው።

2.ሙዚቀኛ ጆኒ ራጋ "ቁልፉን ስጪኝ" የተሰኘው አልበሙን በለቀቀ በ20 ዓመቱ በተመሳሳይ ቀን ሁለተኛ አልበሙን ለአድማጮች ሊያቀርብ ነው።

3.ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መጻሕፍትን በማዘጋጀትና በማሳተም ለማሰራጨት የሚያስችለውን “ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ” የተሰኘ አሳታሚ ድርጅት ማቋቋሙን አስታወቀ።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/pwk3_pkRRns?si=gvLwt3jpjJ05Kjhm

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
9👏7
📌ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት ሊደረግ ነው

የሕዳሴ ግድብ ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት ሊደረግ እንደሆነ ተሰምቷል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከሰኞ መስከረም 12 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምዝገባ በማድረግ መጎብኘት ይቻላል አሉ።

ሚኒስትሯ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪስት መስህቦችን ጎብኝተዋል።

በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ጎብኝዎች ሕዳሴ ግድብን በአንድ ጊዜ 50 በመሆን መጎብኘት ይችላሉ።

ምዝገባው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል እንደሚሆን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል ሲል FMC ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
7👍3🥰2👎1
📌ሶፊ ዛሬ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውድድር ይዳኛል

ኢትዮጵያን ጨምሮ 23 ሀገሮች የሚሳተፉበት "ኢንተርቪዥን ሶንግ ኮንቴስት 2025" ላይ ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ባለሙያ ሱልጣን ኑሪ (ሶፊ) ኢትዮጵያን ወክሎ በዳኝነት ይሳተፋል::

በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የወከለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊም መሆን ችሏል::

ይህ ውድድር ዛሬ ማታ በቀጥታ ስርጭት በባላገሩ ቲቪ፣ ፌስቡክ እና ዩትዩብ ቻናል ይተላለፋል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
14👍2
📌አሰፋ ጫቦን የሚዘክር ቤተ-መጽሐፍት ተመረቀ

"ጋሞነቴ ከኢትዮጵያዊነቴ ጋር ተጋጭቶብኝ አያውቅም " በሚለው ንግግራቸው የምናውቃቸው የህግ ባለሙያ፣ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ፣ ደራሲና ፖለቲከኛ  ጋሽ አሰፋ ጫቦን የሚዘክር ቤተ-መጽሐፍት በጋሞ ባሕል ማዕከል ተመርቆ ተከፍቷል።

በመርሃግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የጋሽ አሰፋ ጫቦ ቤተሰቦች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
12🙏5🔥1🥰1
አዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አውጥቷል

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (አዲስ ዘመን፣ ጋዜጣ+፣ በሪሳ ) ለስራ ተወዳደሩ ማስታወቂያ አውጥቷል። የዚህ ተቋም ባልደረባ መሆን የምትፈልጉ ተወዳደሩ፣ ይቅናችሁ እንላለን።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
5👍1
📌የሸገር ጋዜጠኞች ከእስር ተፈተዋል

የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት ዛሬ ከእስር ተለቀዋል።

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛው ችሎት የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው በዋስ እንዲለቀቁ የስር
ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቷል።

ጋዜጠኞቹ በዋስ እንዲለቀቁ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ ዛሬ ከሰዓት በ21ኛ ቀናቸው ከእስር ተለቀዋል።

የፌዴራሉ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ፣ጋዜጠኞቹን ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት፣ ለፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ነበር፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ነገሩን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ መስከረም 14 ቀን 2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡

ጋዜጠኞችቹ ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው በቁጥጥር ስር በዋሉ 21ኛው ቀን በተለዋጩ ቀጠሮ ቀን ፣ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የስር ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ የሰጠው ውሳኔ አፅድቆ መዝገቡን ዘግቷል፡፡

በውሳኔው መሰረት ዛሬ ከሰዓት ከእስር ተለቀዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
14👏6🤔1