📌ሞተረኛ ትራንስፖርት በይፋ ወደ ስራ ገባ
ሞተረኛ ትራንስፖርት በመዲናዋ በነዳጅ የሚሰሩትን ሞተሮች በኤሌክትሪክ ለመተካት ማሰቡን ገልጿል።
የሞተረኛ ትራንስፖርት የቦርድ ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ንጉሴ ባደረጉት ንግግር፣ የሞተረኛ ትራንስፖርት በአዲስ አበባ የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ሞተሮችን በኤሌክትሪክ ሞተሮች ለመተካት ማቀዱን ገልጸዋል።
ይህ ፕሮጀክት የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።
በንግግራቸው፣ አቶ ሮቤል በ2024 ዓ.ም. በተደረገ ጥናት መሰረት፣ በአዲስ አበባ ብቻ 23 ሺህ 854 የነዳጅ ሞተሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
እነዚህ ሞተሮች በዓመት 34 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ የሚጠቀሙ ሲሆን፣ ይህም 4.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ያስወጣል ሲሉ ገልጸዋል።
በነዳጅ የሚሰሩ ሞተሮችን ወደ ኤሌክትሪክ ሞተር በመቀየር በዓመት
48 ሺህ6 44 ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን መከላከል እንደሚቻልም አብራርተዋል።
ኩባንያው ሞተረኞችን ለመደገፍ፣ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክ ሞተር መግዣ ዋጋን 50 በመቶ የሚሸፍን የብድር አገልግሎት ማመቻቸቱን ገልጿል።
በተጨማሪም፣ ለኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ሞተሮችን ለማቅረብ ከቻይና አጋር ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተደርጓል።
አቶ ሮቤል አክለው እንደተናገሩት የሞተረኛ ትራንስፖርት አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ከመፍጠር ባሻገር፣ ቀልጣፋና ደህንነቱ የተጠበቀ የሎጅስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
የድርጅቱ ስራዎች በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያዎች በዝርዝር እንደሚገለጹም አስታውቀዋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

❤2👍1
የክብር ካባ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተበረከተ
መልህቅ ኪን ፕሮዳክሽን ያሰናዳው አምስተኛ ዙር የስነ-ጽሁፍ ምሽት ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ቃሊቲ በሚገኘው ካፍደም ሲኒማ ቤት የተካሄደ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን በመሸለም የክብር ካባ አልብሷቸዋል።
መልህቅ ኪን ፕሮዳክሽን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ኪነ-ጥበባዊ ፋይዳ ለመስጠት ከመንግስት እውቅና አግኝቶ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በተለይ በኪነ-ጥበቡ መስክ ለሀገራችን እና ለወገኖቻችን ታላቅ ስራ የሰሩ ባለሙያዎችን ሲዘክር ቆይቷል።
በዛሬው እለት በተከናወነው ለአምስተኛ ጊዜ በተሰናዳው የኪነጥበብ መርሐግብር ላይ
1. ጸሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ
2.ጸሐፌ ተውኔቱና ገጣሚው ጋሽ አያልነህ ሙላቱ
3. ዶክተር ተሻለ አሰፋ (ረ/ኘ)
4.አርቲስት ራሄል ተሾመ
በኢትዮጵያ ኪነጥበብ ላበረከቱት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተግባር የክብር ካባ እና የእውቅና
ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
በሌላ በኩል
1.ወይዘሮ አንጋቱ ኃይሌ በኢንቨስትመንት ዘርፍ
2. አርቲስት ግርማ ተሾመ በኪነጥበብ ዘርፍ
3. አትሌት ዮሐንስ ቢፋ (መኩ)በስፖርት ልማት ዘርፍ
4.ለአቃቂ ልጆች ህብረት በበጎ አድራጎት ዘርፍ
በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራ ላከናወኑ ተቋማት እና ግለሰቦች የክብር ካባ እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
ለአምስተኛ ጊዜ በተደረገው የኪነጥበብ እና የእውቅና መርሐግብር ላይ በርካታ አርቲስቶች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ኮሜዲያኖችና በሀገራችን ታዋቂ እንዲሁም ተጽኖ ፈጣሪዎች ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

❤9👍2
📌ኒውማ ኢትዮጵያ አምባሳደር ሾመ
ኒውማ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት (የሱስ ማገገሚያ ማዕከል)፥ አቤ እና ልጆቿ በሚል መጠሪያ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚታወቁትን ወይዘሮ አበበች ቶላን ብራንድ አምባሳደሩ አድርጎ ሾሟል።
ወይዘሮ አበበች ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ልጆችን፣ በየሆስፒታሉ የሚገኙ ታማሚዎችን፣ በየቤቱ ጠያቂ አጥተው ያሉ በእድሜ የገፉ እናቶችና አባቶች በማገዝ እና በመሰለ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከፍተኛ ሱታፌ አላቸው።
ይህን ጥረታቸውን የተመለከቱ በርካታ ሰዎችና ተቋማትም ከጎናቸው ቆመዋል። በተለይም ከጤና ክብካቤ አገልግሎት ጋር በተያያዘ፥ የጤና መድኅን ዓመታዊ ክፍያን በመፈፀም፣ በመድኃኒት ግዢ፣ በጤና ምርመራ አገልግሎት ላይ፥ አቅመ ደካሞች የሚያስፈልጋቸው ሳያገኙ እንዳይቀሩ ብዙ ሠርተዋል። ከጤና ጣብያዎች፣ ከየካቲት 12 አጠቃላይ ሆስፒታል እና ጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ከተለያዩ ከጤና ምርመራ ተቋማት እንዲሁም ከፋርማሲዎች ብሎም በእነዚህ ተቋማት ከሚሠሩ ሐኪሞችና የጤና ባለሞያዎችም ጋር በመናበብ፥ ድጋፍ የሚፈልጉትን በማገዝ ከ 20 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል።
ለዚህና ለበርካታ አገልግሎታቸውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በመንግሥት እንዲሁም ከአለማቀፍ ተቋማት እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
“ይህ አገልግሎት ለብዙዎች አረአያ እና ምሳሌ የሚሆን ነው።” ያሉት የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ዘክርስቶስ ጸጋዬ በቢሮው በተካሄደ የስምምነት ፊርማ፥ ወይዘሮ አበበች ቶላ የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን አስታውቀዋል።
ብዙዎች ማሚ እያሉ የሚጠሯቸው ወይዘሮ አበበች ፣ የኒውማ ኢትዮጵያ’ን፥ በሱስ ውስጥ ያሉ ልጆችና ወጣቶችን ሕይወት የመታደግ ዓላማ ተጋርተዋል።

❤5👏2🔥1
📌ደራሲና ዳይሬክተር ብሩክ ሞላ በአሜሪካ ኤምባሲ ልዩ እንግዳ በመሆን ይቀርባል
(መግቢያው በነፃ ነው)
በሰባተኛው የ CREATOR LAB ዝግጅታችን ላይ የፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር የሆነውን እንዲሁም የሙዚቃ ፕሮዲዩሰር የሆነው ብሩክ ሞላን ይዘንላችሁ መተናል ።
ብሩክ ሞላ ከሰራቸው ፊልሞች ውስጥ ከዳመና በላይ ፣ ህዳር ፣ በቅርብ ግዜ በ DSTV ላይ ይታይ የነበረው ናፍውቆት የተሰኘውን የሚውዚክ ድራማ ተጠቃሾቹ ናቸው። እንዲሁም ከ 50 በላይ የ ሙዚቃ ክሊፖችን እና ከ 120 በላይ የሙዚቃ ድርሰቶችን ከሳውንድ ትራክ ጋር አንድላይ ሰርቷል ።
በዚህ ዝግጅት ላይ ሰለ ድርሰት እና ዝግጅት እንዲሁም የራሱን የሂዎት ተሞክሮ ለ እናንተ ያካፍለናል። ሰለሆነም በዚህ መድረክ ላይ እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
ደራሲ እና አዘጋጅ የመሆን ፍላጎት ያላችሁ፤ እንዲሁም በ ሙያው ላይ ልምድ ያላችሁ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛና ዕድል ለእናንተ ነው።
📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 ( ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )
📅 ቀን: ማክሰኞ - ጳጉሜ 4 ፣ 2017
🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00
🎟 መግቢያ : ነፃ
አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር
በ ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ኢንስታግራም ገፃችንን ፎሎ ማድረግ እንዳይረሱ
📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

❤11👍3
📌ድምጻዊት ትዕግሥት በቀለ ከ20 ዓመታት በኃላ
ድምጻዊት ትዕግሥት በቀለ በ1990ዎች አጋማሽ በለቀቀችው "ሳቂታው" አልበም በበርካታ የሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ትታወቃለች።
ይህ አልበም ለአድማጮች ከቀረበ ከጥቂት ዓመታት በኃላ ድምጻዊት ትዕግሥት በቀለ ኑሮዋን በባህርዳር ማዶ አድርጋለች።
ከሰሞኑም ከ20 ዓመታት በኃላ የሙዚቃ ኮንሰርቷን ልታቀርብ ወደ ሀገሯ ኢትዮጵያ ተመለሳለች።
ከ20 ዓመታት በኃላ ቀጠሮ የተያዘለት ይህ የሙዚቃ ኮንሰርት በመጪው አዲስ ዓመት መስከረም 3 2018 በግዙፉ ሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
ድምጻዊት ትዕግሥት በቀለ ከዓመታት በምታቀርበው ኮንሰርት ላይ የመክፈቻ ሙዚቃዋ "ዓውደ ዓመቱ" የተሰኘው የበዓል ሙዚቃዋ እንደሆነም ሰምተናል።
በዚህ ሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ከትግዕስት በቀለ በተጨማሪም አለማየሁ ሄርጶ፣ ያሬድ ነጉ እና ኢሳይያስ ታምራትና ሌሎችም ድምጻዊያን አብረው የሙዚቃ ስራዎቻቸው እንደሚያቀርቡ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኮንሰርቱን ያዘጋጀው ደግሞ ሹር ጉድ ኢንተርቴይመንት ነው።

❤4🔥3
📌ድምጻዊ ኃይሉ አመርጋ ዛሬ ኮንሰርት ያቀርባል
ተወዳጁ ድምጻዊ ኃይሉ አመርጋ ከሙዚቃ አልበሙ አስቀድሞ የመጨረሻዬ ነው ያለውን የሙዚቃ ኮንሰርት ዛሬ ያቀርባል።
ኃይሉ የሚሳተፍበት ኮንሰርት "ፋንታ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ኮንሰርት " ይሰኛል።
የሙዚቃ ኮንሰርቱ ዛሬ ጳጉሜን 5 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ጊዮን ሆቴል ይካሄዳል።
በኮንሰርቱ ላይ ከኃይሉ አመርጋ በተጨማሪም ሚካኤል በላይነህ፣ ዳዊት መለሰ፣ ጆኒ ራጋ፣አኒስ ጋቢ፣ ኤደን አይሸሽም እና መስፍን ብርሃኑ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

❤5🔥1
📌መርካቶ ቴሌቪዥን ጣቢያ ስርጭት ጀመረ
"መርካቶ" የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ስርጭት እንደጀመረ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዛሬ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ዘርፍ የተቀላቀለው አዲሱ ጣቢያን የኢትዮሳት NSS 12 57°E ተጠቃሚዎች በ11545 Hor 45000 ሰርች በማድረግ መመልከት ይችላሉ ተብሏል።
መርካቶ ቴሌቪዥን ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣት ስራ ፈጣሪዎች የሚመራ አዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሆነም ሰምተናል።

❤17👍7
📌ሀይማኖት ግርማ ለልጇ የቤት ስጦታ ሰጠች
ድምፃዊት ሀይማኖት ግርማ "ልጄ አሜን አልበሜን ስሰራ ቀን እና ማታ ሳይል አብሮኝ ስለለፋ በአዲሱ አመት ስጦታ" በማለት የመኖሪያ ቤት ስጦታ ማበርከቷ ተሰምቷል።
ልጇ አሜንም "እኔ ግዴታዬን ነው የተወጣውት።ከዚህ በኋላ በህይወትሽ ላይ ለሚገጥምሽ ማንኛውም ነገር ከጎንሽ ነኝ" ብሏል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ድምፃዊት ሀይማኖት ግርማ "ልጄ አሜን አልበሜን ስሰራ ቀን እና ማታ ሳይል አብሮኝ ስለለፋ በአዲሱ አመት ስጦታ" በማለት የመኖሪያ ቤት ስጦታ ማበርከቷ ተሰምቷል።
ልጇ አሜንም "እኔ ግዴታዬን ነው የተወጣውት።ከዚህ በኋላ በህይወትሽ ላይ ለሚገጥምሽ ማንኛውም ነገር ከጎንሽ ነኝ" ብሏል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤13👎5🥰1👏1
📌የሜሮን ጌትነት አዲስ መጽሐፍ ታተመ
የሁለገቧ ከያኒ ሜሮን ጌትነት "ሌላ ዕውነት የለኝም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መፅሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል ተብሏል።
"ሌላ ዕውነት የለኝም" መጽሐፍ ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘና በ134 ገፆች የተቀነበበ ነው።
ሜሮን በተለያየ ጊዜ የጻፈቻቸውን ግጥሞች በአንድ ላይ አድርጋ ለሕትመት ያበቃች ሲሆን ግጥሞቹም በግላዊ ገጠመኝና ዕይታ ላይ ትኩረታቸውን ያደርጋሉ።
ገጣሚ ሜሮን ጌትነት ስለመጽሐፏ "ሌላ እውነት የለኝም በተለያየ ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ ውስጥ ሆኜ የፃፍኳቸው ግጥሞች ስብስብ ነው። ግላዊ ስሜቶች፣ እውነቶችና በህይወት መስመር ላይ ያስተዋልኳቸው ማህበራዊ ሁነቶች ከጫሩብኝ ሀሳቦች ተነስቼ የከተብኳቸው ናቸው ትወዷቸዋላችሁ"ስትል ሀሣቧን ለተወዳጅ ሚድያ ገልጻለች።
ለ10 ዓመታት መኖሪያዋን ባህር ማዶ አድርጋ የነበረችው የኪነ- ጥበብ ሰው ሜሮን ጌትነት ለጥቂት ዓመታት ከጥበቡ ዓለም ራቅ ብላ መቆየቷ ይታወቃል።

❤25👍3👏2🥰1
📌ለ1 ሚሊየን ዶላር አሸናፊነት ይወዳደራሉ
ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች በአሜሪካ ጎት ታለንት ለ1 ሚሊየን ዶላር አሸናፊነት ይወዳደራሉ።
በ2025 የአሜሪካ ጎት ታለንት እየተወዳደሩ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች ቶማስ አለሙ እና ታምራት አያሌው ቲቲ ቦይስ ወደ ፍጻሜ ማለፍ ችለዋል።
ቲቲ ቦይስ ከሌሎች 8 ተወዳዳሪዎች ጋር በመፋለም ነው 4 ተወዳዳሪዎች ብቻ ወዳለፉበት የፍጻሜ ውድድር የተቀላቀሉት፡፡
ኢትዮጵያውያኑ የሰርከስ አርቲስቶች ቲቲ ቦይስ በተመልካች እና በውድድሩ ዳኞች ከፍተኛ አድናቆት ተችሯቸዋል።
በዳኞች በተሰጣቸው አስተያየት ሥራቸው ድንቅ የሆነ ተሰጥኦና በዓመቱ ከታዩ ክስተቶች አንዱ ነው ተብሎላቸዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ማህበር ጥምረት ፕሬዚዳንት ተክሉ ተሻገር ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያውያን በዚህ ዓለም አቀፍ ግዙፍ የተሰጥኦ ውድድር መድረክ ለፍጻሜ ሲደርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
ይህም ለኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሁሌም የሚጠቀስ ትልቅ ስኬት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
የውድድሩ ሽልማት የሆነውን 1 ሚሊየን ዶላር ለማሸነፍ የሕዝብ ድምፅ ወሳኝ ሲሆን ÷ ለተወዳዳሪዎች ድምፅ በመስጠት ልንደግፋቸው ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል ሲል FMC ዘግቧል።

❤21👍8
📌አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ በአሜሪካ ኤምባሲ ልዩ እንግዳ በመሆን ይቀርባል
(መግቢያው በነፃ ነው)
በስምንተኛው የCREATOR LAB ዝግጅት ላይ የፊልም ተዋናይ፣ ደራሲ እና ዳይሬክተር እንዲሁም ፕሮዲዩሰር የሆነውን ቸርነት ፍቃዱ እንግዳ ሆኖ ይቀርባል።
ቸርነት ፍቃዱ 13 ፊልሞች ላይ በትወና 6 ፊልሞች ላይ በ ፕሮዲዩሰርነት እና 5 ቴያትሮች ላይ ደግሞ በትወና ተሳትፏል።
በብዙዎች ዘንድም ተወዳጅነትን ያተረፈው እና የተመልካችን ቀልብ የሳበው "ኪያ" እና "ጥላዬ" ፊልም ላይ ሲሆን በድርሰትም በትወናም ተሳትፏል። ቸርነት በቀርቡ በሰራው ስራም ቀንጃ ፊልም ላይ በ ፕሮዲዩሰር እና በትወና መሳተፉ ይታወቃል ።
በዚህ ዝግጅት ላይም በቅርቡ በወጣው ቀንጃ ፊልም ላይ ስለ ፊልሙ አሰራር ፣ ገጠመኞች እንዲሁም የራሱን የሂዎት ተሞክሮ ለ እናንተ ለተሳታፊዊች ለማካፈል ቀጠሮ ይዘናል። ሰለሆነም በዚህ መድረክ ላይ እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
ተዋናይ ፤ ደራሲ እንዲሁም አዘጋጅ የመሆን ፍላጎት ያላችሁ እና በ ሙያው ላይ ልምድ ያላችሁ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛ ዕድል ለእናንተ ነው።
📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 ( ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )
📅 ቀን: ማክሰኞ - መስከረም 6 ፣ 2017
🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00
🎟 መግቢያ: ነፃ
አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር
📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡

❤17
📌የክቡር ዶክተር ሃዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ካስፈተናቸው 25 ተማሪዎች መካከል 24ቱ ከ529 በላይ ውጤት አምጥተዋል።
የክቡር ዶክተር ሃዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ደረጀ ከፈለኝ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩን አስረድተዋል።
አዳሪ ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ ለ3ኛ ጊዜ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በመስጠት በክልሉ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።
በአዳሪ ት/ቤቱ በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 25 ተማሪዎች መውሰደቸውን የተናገሩት አቶ ደረጀ ከ25 ተፈታኞች መካከል 24ቱ ከ529 በላይ፤ ማምጣታቸውንና 3 ተማሪዎች ደግሞ 573 ያመጡ ሲሆን፤ አንድ ተማሪ 407 ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል።
25ቱም ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህር ዘርፍ ፈተና መውሰዳቸውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አስረድተዋል።
Via tikvahuniversity

👏29❤16
📌አሻም ቴሌቪዥን የስራ ማስታወቂያ አውጥቷል
ቴሌቪዥን ጣቢያው 4 ሪፖርተሮችን ይፈልጋል።
በተጨማሪም ኤዲተር ፣ የፕሮግራም ክፍል ኃላፊ እና የሽያጭ ባለሞያም እፈልጋለሁ ብሏል።
የአሻም ቴሌቪዥን ባልደረባ መሆንን የምትሹ ተመዝገቡ። ተወዳደሩ ።ይቅናችሁ እንላለን።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ቴሌቪዥን ጣቢያው 4 ሪፖርተሮችን ይፈልጋል።
በተጨማሪም ኤዲተር ፣ የፕሮግራም ክፍል ኃላፊ እና የሽያጭ ባለሞያም እፈልጋለሁ ብሏል።
የአሻም ቴሌቪዥን ባልደረባ መሆንን የምትሹ ተመዝገቡ። ተወዳደሩ ።ይቅናችሁ እንላለን።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤13🥰4
📌ጋዜጠኛ አልዳ ግዛቸው ብራንድ አምባሳደር ሆነች
አስቀድሞ በሸገር 102.1 ሬድዮ አሁን ላይ በኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተለያዩ መሰናዶዎችን በማዘጋጀት እና በማቅረብ የምትታወቀው ጋዜጠኛ ኤልዳ ግዛቸው የ"ቢሃይንድ ዘ ሲን" ብራንድ አምባሳደር በመሆን እንደተሾመች ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኤልዳ ግዛቸው ብራንድ አምባሳደር ሆኖ የተሾመችበት"ቢሃይንድ ዘ ሲን" በሰባት የአፍሪካ ሀገራት እየተከወነ የሚገኝ የጥናት እና የምርምር ፕሮጀክት ነው ተብሏል።
መርሐግብሩ የኪነጥበብ ሙያ ላይ ያሉ ወጣት ሴቶች ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግም ተገልጿል።
ሙያተኞች ያላቸውን ሚና፣ ተግዳሮት እና ተስፋ በየሀገራቱ ማጥናት እና የጥናት ውጤቶቹን ለልዩ ልዩ አገልግሎት በተለይም ለፖሊሲ ግብአት እንዲውሉ ያደርጋል፡፡
በዚህ ፕሮጀክት ላይ OSSREA፣ ICRW ከMaster Card Foundation ጋር ተባብረው ይሰራሉም ተብሏል።
ጋዜጠኛ አልዳ ግዛቸው ከጋዜጠኝነቷ ባሻገር በተለያዩ መድረኮች እና ማህበራዊ ትስስር ገፆቿ በኩል በምታጋራቸው የሥነጽሑፍ ሥራዎቿም ትታወቃለች።
📲 TikTok:
https://www.tiktok.com/@eldagizachew?_t=ZM-8ycUyGgkmYC&_r=1
📸 Instagram: https://www.instagram.com/elda_gizachew?igsh=ZGFudHJvY3d0bzJ0
▶️ YouTube: http://www.youtube.com/@eldacorner369
#BehindTheScenesAfrica #CreativeEquity #YoungWomenInArts #NationalCreativeAmbassador

❤12❤🔥1🔥1
📌አበረ አዳሙ ለብሪክስ የሥነጽሑፍ ሽልማት ታጩ
ደራሲ አበረ አዳሙ ለብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ላይ እጩ ሆነው እንደቀረቡ ተሰምቷል።
የብሪክስ የእጩ ዝርዝሩ በብራዚሊያ በተካሄደው ሁለተኛው የብሪክስ የባሕላዊ እሴቶች ጉባኤ ላይ ይፋ ተደርጓል።
በዝርዝሩ ከብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ግብፅ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ኢራንና ኢንዶኔዥያ ጨምሮ ከሌሎችም ሀገራት የተወጣጡ 27 ደራሲያን ተካተውበታል፡፡
በብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ዙሪያ በተካሄደው ውይይት ወቅት፤ የሥነ ጽሑፍ ምሁራንና አሳታሚዎችን የሚያካትት የብሪክስ ሀገራት የጸሐፊዎች ማኅበር ምሥረታም እውን ሆኗል፡፡ የማኅበሩ ዋነኛ ዓላማ ቀጣይነት ያለው የባሕል ልውውጥን ማሳደግ እና በሥነ ጽሑፍ መስክ የሚደረጉ ጥረቶችን ማስተባበር እንዲሁም የሽልማቱን አዘጋጅ ኮሚቴ መደገፍ ነው።

❤7👏7
📌ዋልያ የሀሳብና መጽሐፍ መድረክ ቅዳሜ ይጀምራል
በዋልያ መጻሕፍት መደብር አዘጋጅነት የሚሰናደው "ዋልያ የሀሳብና መጽሐፍ መድረክ" የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 8 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ መካሄድ ይጀምራል።
በመጀመሪያ መሰናዶው ላይ ዶ/ር ሀብቴ ጀቢሳ በእንግድነት ተጋብዘዋል የመወያያ ርዕሱም "የምንመገበው ምግብ የያዘው ደቂቅ ንጥረ ነገር የአእምሮ የማሰብ ጉልበትን እንዴት እንደሚነካ እና በማኅበራዊ የኑሮ መስተጋብራችን በሚያስከትለው አሉታዊ እና አዎንታዊ ተጽዕኖ ዙሪያ ይሆናል ተብሏል።
እንደ መነሻ "ቀንጨራነት እና ድኽነት በኢ/ያ” በተሰኘው መጽሐፍ ዙሪያ ላይ ታ'ከን ሀሳባችንን እያነሳን የምንጥል ይሆናል ብለዋል አዘጋጆቹ። መጽሐፉ የአዕምሮ እና የአካል መቀንጨር በሀገር እድገት ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ እያብራራ በዛውም የመፍትሄ ሀሳብ ይጠቁመናል ተብሏል።

❤1
📌"የተመለሱ እይታዎች" አውደርዕይ ተከፈተ
የሠዓሊ ኪሩቤል ተፈሪ የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "የተመለሱ እይታዎች" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ትላንትና ረቡዕ መስከረም 7 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል።
ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ጥቅምት 3 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የሠዓሊ ኪሩቤል ተፈሪ የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "የተመለሱ እይታዎች" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ትላንትና ረቡዕ መስከረም 7 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል።
ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ጥቅምት 3 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤7
📌ሸገር ጋዜጠኞቼ ከታሰሩ 17 ቀናት ሆናቸው አለ
የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጋዜጠኞች፣ አርታኢ ትዕግስት ዘሪሁን እና ሪፖርተር ምንታምር ፀጋው፣ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቁጥጥር ስር ከዋሉ 17 ቀን ሆናቸው።
የፌዴራል ፖሊስ፣ ጋዜጠኞቹን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው፣ ያሰራጩት ዘገባ በሕግ የተከለከለ ይዘት ያለውና የሽብር ድርጊት ነው ብሎ እንደሆነ፣ ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቅድለት፣ ባቀረበው ማመልከቻ ጠቁሟል፡፡
የሕክምና ባለሞያዎች፣ ለመንግስት ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ፣ የጤና ሚኒስቴር በሰርኩላር ያስተላለፈውን መፍትሄ፣ እንዴት እንደሚመለከቱት፣ የሕክምና ባለሞያ ቃለ መጠይቅ በማድረግ፣ ነሐሴ 24 በሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ፣ ዜናው ተላልፎ ነበር፡፡
በዚሁ ዜና ምክንያት የፌዴራል ፖሊስ፣ ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁን እና ምንታምር ፀጋውን፣ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ፣ ምክንያቱን ዘርዝሮ፣ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው በመጠየቁ፣ ፍርድ ቤቱ ዘጠኝ ቀን ፈቅዶለት ነበር፡፡
በቀጣዩ ቀጠሮ፣ የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ፣ የገንዘብ ዝውውራቸውን እና ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል፡፡
የፌዴራል ፖሊስን ምክንያትና ከጋዜጠኞቹ የቀረበውን መከራከሪያ ያዳመጠው፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ፣ ጋዜጠኞቹ በ50,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
በትዕዛዙ መሰረት፣ መስከረም 7/2018 ከሰዓት በኋላ፣ አስፈላጊው ፎርማሊቲ ተሟልቶ፣ ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ደርሶታል፡፡
ይሁንና፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ውሳኔ በይግባኝ፣ ወደ ፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመወሰዱ፣ ለመስከረም 12/2018 ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

❤9🤬3👍1👎1🤔1😢1
📌 አዳብና ፌስቲቫል በሁለት ከተሞች ይከበራል
የ2018 የክስታኔ አዳብና ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እና ኬላ ከተሞች በድምቀት እንደሚከበር ተነገረ።
አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማኀበር እና አክራሚ የሴቶች በጎ አድራጎት ማህበር በጥምረት አዳብና በፌስቲቫል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ይካሄዳል።
ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አዳብና በአዲስ አበባ ጥቅምት 02 2018 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን ቀደም ብሎ መስከረም 24 2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን በኬላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እንደተደረገ ተነግሯል።
የአዳብና ባህል የልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ጨዋታና መተጫጫ ሥነሥርዓት ሲሆን 800 ዓመታት በፊት በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ አካባቢ ለዘመናት ሲከበር ኖሯል።
አዳብና በከስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ይህ ድንቅ የሆነ የአዳብና ባህል በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት በUNESCO እንዲመዘገብ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጿል።
መላው ኢትዮጵያውያን መስከረም 24 ኬላ እና ጥቅምት 02 በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ የሚከበረውን ፌስቲቫል ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርበዋል።

❤9
የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
1. አንጋፋዋ ድምጻዊት አስቴር አወቀ ከዓመታት በኃላ በልዩ የሙዚቃ ድግስ በአዲስ አበባ ከአድናቂዎቹ ልትገናኝ ነው።
2.ሙዚቀኛ ጆኒ ራጋ "ቁልፉን ስጪኝ" የተሰኘው አልበሙን በለቀቀ በ20 ዓመቱ በተመሳሳይ ቀን ሁለተኛ አልበሙን ለአድማጮች ሊያቀርብ ነው።
3.ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መጻሕፍትን በማዘጋጀትና በማሳተም ለማሰራጨት የሚያስችለውን “ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ” የተሰኘ አሳታሚ ድርጅት ማቋቋሙን አስታወቀ።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/pwk3_pkRRns?si=gvLwt3jpjJ05Kjhm
📌መልካም ምሽት

❤9👏7