Event Addis Media
9.6K subscribers
6.06K photos
12 videos
4 files
4.68K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ሁለቱ አርቲስቶች ጃፓን ገብተዋል

ተወዳጆቹ አርቲስቶች ኮሜዲያን ደረጀ ሀይሌ እና ተዋናይ መኮንን ላዕከ በጃፓን ዋና ከተማ ቶኪዮ ለሚኖሩ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን የጥበብ ስራዎቻቸውን ለማቅረብ ጃፓን ቶኪዮ ገብተዋል።

ሁለቱ አርቲስቶች የፊታችን እሁድ September 7 / 2025 ዓ ም በቶኪዮ ካቱሺካ ሂጋሺታቲሺ ሴንተር ዉስጥ በሙዚቃ የታጀበ ልዩ የኮሜዲ ምሽት ያቀርባሉ። በዚህ ደማቅ የኮሜዲ ምሽት ላይ መታደም የመግቢያ ዋጋዉ 3000 የጃፓን የን ሲሆን የመግቢያ ትኬቱም በሊትል ኢትዮጵያ በመሸጥ ላይ ነው።

©️ይትባረክ ዋለልኝ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
5🔥4🥰4👍3
ዛሬ የአመቱ የመጨረሻዋን ቅዳሜ በምስጋና!

አዲሱን አመት በምስጋና ልዩ የአዲስ አመት ፕሮግራም ዛሬ ቅዳሜ ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ

የሚቀርቡ ፕሮግራሞች?

የፍቅር፣የስኬት፣የስራ፣የበጎ ስራ እቅድዎን ለማሳካት ከምን እንጀምር የሚለውን ምላሽ ከመድረኩ ይዘው:-

~የስነልቦና ባለሙያዎች እና አማካሪዎች
~የትውልዱ ምልክት አትጊ የሆኑ ወጣቶች
~ስኬታማ የቢዝነስ ልምዶች
~የህይወት ጉዟቸውን በጣፋጭ ታሪክ እያዋዙ ከመድረኩ
~የግጥም ስራዎች
~ሙዚቃ
~ምስጋና

የ2017 አመቱን በምስጋና ሸኝተን 2018ን በምስጋና ልናስጀምር ተዘጋጅተናል።

እርሶም ተጋብዘዋል።

ለበለጠ መረጃ
ስልክ 0939504545/0922111330

አዘጋጅ:-ቲኤች ግሩፕ ከስዊት ላይፍ ፎር ኦል ጋር በመተባበር
9🔥1
የወጣቶች አግሮኢኮሎጂ ስታርትአፕ ውድድር ተካሄደ

‘’የወጣቶች አግሮኢኮሎጂ ስታርትአፕ ውድድር’’ (Youth in Agroecology Startup Competition) አሸናፊዎች የሽልማት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ።

የዚህ ውድድር አላማም፤ የምግብ ሉዓላዊነት፣ ዘላቂያዊነት፣ ለማኅበረሰብ ደህንነት ሀገር በቀል መፍትሔዎችን ማምጣት እና ጤናማ ሀገር በቀል ምግቦችን ማስተዋወቅ እንደሆነ ተገልጿል።

‘’የወጣቶች አግሮኢኮሎጂ ስታርትአፕ ውድድር’’ የፈጠራ ሀሳቦቻቸውን ካቀረቡ 54 ወጣቶች መካከል በዘርፉ ልምድ ባላቸው ዳኞች ተመዝነው ለተመረጡት ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

በዚህም መሠረት አንደኛ ለወጣው ኪሩቤል ኃይለሥላሴ 200,000 ብር፣ ሁለተኛ ለወጣው ዳግማዊ አመሃ 150,000 ብር እና ሦስተኛ ለወጡት ሕይወት ሲሳይ እና ኢማን ኢብራሂም 100,000 ብር ተሸልመዋል።

ይህን ውድድር የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ሥርዓትና ሥነ-ምሕዳራዊ ግብርና ሕብረት (Ethiopian Sustainable Food Systems and Agroecology Consortium - ESFSAC) ከየአፍሪካ ምግብ ሉዓላዊነት ሕብረት (Alliance for Food Sovereignty in Africa - AFSA) በጋራ ያዘጋጁት እንደሆነ ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
4
📌ጂ አር (JR) ፔትሮልዬም ያስገነባው ግዙፍ የአውሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ ዲፖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ኩባንያው በአሁኑ ጊዜ ፤ እየጨመረ የመጣው የሀገሪቱን የሀይል ፍላጎት ለማሟላት ራዕይ ሰንቆ ፤ ከሃምሳ ስምንት በላይ ማድያዎችን በመገንባት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የጄ አር ፔትሮሊየም ስራ አስኪያጅ ወ/ት ፀጋ ሀይሉ ተቋማችን ከእህት ኩባንያው ደስታ ካሴ የግል ፈሳሽ ትራንስፖርት ጋር በመሆን ፤ ከአንድ መቶ ሃምሳ በላይ የነዳጅ ቦቴዎችን በማሰማራት በመላው የሃገራችን ክፍል በትጋት፣ በላቀ ዝግጁነትና በታማኝነት አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ፤ በሃገራችን ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ላሉ እንደእነ ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የመሳሰሉ እና ለሌሎች አዳዲስና አንጋፋ ተቋማት ሃይል በማቅረብ ፤ በሃገሪቱ ለሚከናወኑ ሜጋ ፕሮጀክቶች የሃይል ደጀን መሆን ችሏል ብለዋል።

አሁን ደግሞ ኩባንያው ጄ አር ፔትሮልዬም 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት በማድረግ በሃገራችን ብሎም በአሀጉራችን ብቸኛና የሁላችንም ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ራዕይ ለማሳካት ዲፖ መግንባት መቻሉን ተናግረዋል።

ዲፖው ዘጠኝ ሚሊዬን ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ ነው ገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ያደረገው።

ይህ ግዙፍ የአውሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ ዲፖ ዛሬ ጷግሜ 01 ቀን 2017ዓም ፤ የኩባንያው የማኔጅመንት አባላት፣ የኩባንያው አጋር አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይፋ ተደርጓል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
6
📌ሞተረኛ ትራንስፖርት በይፋ ወደ ስራ ገባ

ሞተረኛ ትራንስፖርት በመዲናዋ በነዳጅ የሚሰሩትን ሞተሮች በኤሌክትሪክ ለመተካት ማሰቡን ገልጿል።

የሞተረኛ ትራንስፖርት የቦርድ ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ንጉሴ ባደረጉት ንግግር፣ የሞተረኛ ትራንስፖርት በአዲስ አበባ የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ሞተሮችን በኤሌክትሪክ ሞተሮች ለመተካት ማቀዱን ገልጸዋል።

ይህ ፕሮጀክት የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

በንግግራቸው፣ አቶ ሮቤል በ2024 ዓ.ም. በተደረገ ጥናት መሰረት፣ በአዲስ አበባ ብቻ 23 ሺህ 854 የነዳጅ ሞተሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ ሞተሮች በዓመት 34 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ የሚጠቀሙ ሲሆን፣ ይህም 4.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ያስወጣል ሲሉ ገልጸዋል።

በነዳጅ የሚሰሩ ሞተሮችን ወደ ኤሌክትሪክ ሞተር በመቀየር በዓመት
48 ሺህ6 44 ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን መከላከል እንደሚቻልም አብራርተዋል።

ኩባንያው ሞተረኞችን ለመደገፍ፣ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክ ሞተር መግዣ ዋጋን 50 በመቶ የሚሸፍን የብድር አገልግሎት ማመቻቸቱን ገልጿል።

በተጨማሪም፣ ለኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ሞተሮችን ለማቅረብ ከቻይና አጋር ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተደርጓል።

አቶ ሮቤል አክለው እንደተናገሩት የሞተረኛ ትራንስፖርት አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ከመፍጠር ባሻገር፣ ቀልጣፋና ደህንነቱ የተጠበቀ የሎጅስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።

የድርጅቱ ስራዎች በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያዎች በዝርዝር እንደሚገለጹም አስታውቀዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
2👍1
የክብር ካባ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተበረከተ

መልህቅ ኪን ፕሮዳክሽን ያሰናዳው አምስተኛ ዙር የስነ-ጽሁፍ ምሽት ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ቃሊቲ በሚገኘው ካፍደም ሲኒማ ቤት  የተካሄደ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ  የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን በመሸለም የክብር ካባ አልብሷቸዋል።

መልህቅ ኪን ፕሮዳክሽን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ኪነ-ጥበባዊ ፋይዳ ለመስጠት ከመንግስት እውቅና አግኝቶ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በተለይ በኪነ-ጥበቡ መስክ ለሀገራችን እና ለወገኖቻችን ታላቅ ስራ የሰሩ ባለሙያዎችን ሲዘክር ቆይቷል።

በዛሬው እለት በተከናወነው ለአምስተኛ ጊዜ በተሰናዳው የኪነጥበብ መርሐግብር ላይ

1. ጸሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ
2.ጸሐፌ ተውኔቱና ገጣሚው ጋሽ አያልነህ ሙላቱ
3. ዶክተር ተሻለ አሰፋ (ረ/ኘ)

4.አርቲስት ራሄል ተሾመ

በኢትዮጵያ ኪነጥበብ ላበረከቱት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተግባር የክብር ካባ እና የእውቅና
ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

በሌላ በኩል

1.ወይዘሮ አንጋቱ ኃይሌ በኢንቨስትመንት ዘርፍ
2. አርቲስት ግርማ ተሾመ በኪነጥበብ ዘርፍ
3. አትሌት ዮሐንስ ቢፋ (መኩ)በስፖርት ልማት ዘርፍ
4.ለአቃቂ ልጆች ህብረት በበጎ አድራጎት ዘርፍ

በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራ ላከናወኑ ተቋማት እና ግለሰቦች የክብር ካባ እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

ለአምስተኛ ጊዜ በተደረገው የኪነጥበብ እና የእውቅና መርሐግብር ላይ በርካታ አርቲስቶች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ኮሜዲያኖችና በሀገራችን ታዋቂ እንዲሁም ተጽኖ ፈጣሪዎች ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
9👍2
📌ኒውማ ኢትዮጵያ አምባሳደር ሾመ

ኒውማ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት (የሱስ ማገገሚያ ማዕከል)፥ አቤ እና ልጆቿ በሚል መጠሪያ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚታወቁትን ወይዘሮ አበበች ቶላን ብራንድ አምባሳደሩ አድርጎ ሾሟል።

ወይዘሮ አበበች ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ልጆችን፣ በየሆስፒታሉ የሚገኙ ታማሚዎችን፣ በየቤቱ ጠያቂ አጥተው ያሉ በእድሜ የገፉ እናቶችና አባቶች በማገዝ እና በመሰለ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከፍተኛ ሱታፌ አላቸው።

ይህን ጥረታቸውን የተመለከቱ በርካታ ሰዎችና ተቋማትም ከጎናቸው ቆመዋል። በተለይም ከጤና ክብካቤ አገልግሎት ጋር በተያያዘ፥ የጤና መድኅን ዓመታዊ ክፍያን በመፈፀም፣ በመድኃኒት ግዢ፣ በጤና ምርመራ አገልግሎት ላይ፥ አቅመ ደካሞች የሚያስፈልጋቸው ሳያገኙ እንዳይቀሩ ብዙ ሠርተዋል። ከጤና ጣብያዎች፣ ከየካቲት 12 አጠቃላይ ሆስፒታል እና ጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ከተለያዩ ከጤና ምርመራ ተቋማት እንዲሁም ከፋርማሲዎች ብሎም በእነዚህ ተቋማት ከሚሠሩ ሐኪሞችና የጤና ባለሞያዎችም ጋር በመናበብ፥ ድጋፍ የሚፈልጉትን በማገዝ ከ 20 ዓመታት  በላይ  አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል።

ለዚህና ለበርካታ አገልግሎታቸውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በመንግሥት እንዲሁም ከአለማቀፍ ተቋማት እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

“ይህ አገልግሎት ለብዙዎች አረአያ እና ምሳሌ የሚሆን ነው።” ያሉት የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ዘክርስቶስ ጸጋዬ  በቢሮው በተካሄደ የስምምነት ፊርማ፥ ወይዘሮ አበበች ቶላ የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን አስታውቀዋል።

ብዙዎች ማሚ እያሉ የሚጠሯቸው ወይዘሮ አበበች ፣ የኒውማ ኢትዮጵያ’ን፥ በሱስ ውስጥ ያሉ ልጆችና ወጣቶችን ሕይወት የመታደግ ዓላማ ተጋርተዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5👏2🔥1
📌ደራሲና ዳይሬክተር ብሩክ ሞላ በአሜሪካ ኤምባሲ ልዩ እንግዳ በመሆን ይቀርባል

(መግቢያው በነፃ ነው)

በሰባተኛው የ CREATOR LAB ዝግጅታችን ላይ የፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር የሆነውን እንዲሁም የሙዚቃ ፕሮዲዩሰር የሆነው  ብሩክ ሞላን  ይዘንላችሁ መተናል ። 

ብሩክ ሞላ ከሰራቸው ፊልሞች ውስጥ ከዳመና በላይ ፣  ህዳር ፣  በቅርብ ግዜ በ DSTV  ላይ ይታይ የነበረው  ናፍውቆት  የተሰኘውን  የሚውዚክ ድራማ ተጠቃሾቹ ናቸው።  እንዲሁም  ከ 50 በላይ የ ሙዚቃ ክሊፖችን እና  ከ 120 በላይ የሙዚቃ ድርሰቶችን ከሳውንድ ትራክ  ጋር አንድላይ ሰርቷል ።


በዚህ ዝግጅት ላይ ሰለ ድርሰት እና ዝግጅት እንዲሁም የራሱን የሂዎት ተሞክሮ ለ እናንተ ያካፍለናል።  ሰለሆነም በዚህ መድረክ ላይ እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

ደራሲ እና አዘጋጅ  የመሆን ፍላጎት ያላችሁ፤ እንዲሁም በ ሙያው ላይ ልምድ ያላችሁ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛና ዕድል ለእናንተ ነው።


📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 (  ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

📅 ቀን: ማክሰኞ - ጳጉሜ 4  ፣ 2017

🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00 

🎟 መግቢያ : ነፃ

አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር

በ ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ኢንስታግራም ገፃችንን ፎሎ ማድረግ እንዳይረሱ


📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
11👍3
📌ድምጻዊት ትዕግሥት በቀለ ከ20 ዓመታት በኃላ

ድምጻዊት ትዕግሥት በቀለ በ1990ዎች አጋማሽ በለቀቀችው "ሳቂታው" አልበም በበርካታ የሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ትታወቃለች።

ይህ አልበም ለአድማጮች ከቀረበ ከጥቂት ዓመታት በኃላ ድምጻዊት ትዕግሥት በቀለ ኑሮዋን በባህርዳር ማዶ አድርጋለች።

ከሰሞኑም ከ20 ዓመታት በኃላ የሙዚቃ ኮንሰርቷን ልታቀርብ ወደ ሀገሯ ኢትዮጵያ ተመለሳለች።

ከ20 ዓመታት በኃላ ቀጠሮ የተያዘለት ይህ የሙዚቃ ኮንሰርት በመጪው አዲስ ዓመት መስከረም 3 2018 በግዙፉ ሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ድምጻዊት ትዕግሥት በቀለ ከዓመታት በምታቀርበው ኮንሰርት ላይ የመክፈቻ ሙዚቃዋ "ዓውደ ዓመቱ" የተሰኘው የበዓል ሙዚቃዋ እንደሆነም ሰምተናል።

በዚህ ሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ከትግዕስት በቀለ በተጨማሪም አለማየሁ ሄርጶ፣ ያሬድ ነጉ እና ኢሳይያስ ታምራትና ሌሎችም ድምጻዊያን አብረው የሙዚቃ ስራዎቻቸው እንደሚያቀርቡ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኮንሰርቱን ያዘጋጀው ደግሞ ሹር ጉድ ኢንተርቴይመንት ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
4🔥3
📌ድምጻዊ ኃይሉ አመርጋ ዛሬ ኮንሰርት ያቀርባል

ተወዳጁ ድምጻዊ ኃይሉ አመርጋ ከሙዚቃ አልበሙ አስቀድሞ የመጨረሻዬ ነው ያለውን የሙዚቃ ኮንሰርት ዛሬ ያቀርባል።

ኃይሉ የሚሳተፍበት ኮንሰርት "ፋንታ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ኮንሰርት " ይሰኛል።

የሙዚቃ ኮንሰርቱ ዛሬ ጳጉሜን 5 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ጊዮን ሆቴል ይካሄዳል።

በኮንሰርቱ ላይ ከኃይሉ አመርጋ በተጨማሪም ሚካኤል በላይነህ፣ ዳዊት መለሰ፣ ጆኒ ራጋ፣አኒስ ጋቢ፣ ኤደን አይሸሽም እና መስፍን ብርሃኑ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
5🔥1
📌መርካቶ ቴሌቪዥን ጣቢያ ስርጭት ጀመረ

"መርካቶ" የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ስርጭት እንደጀመረ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ዛሬ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ዘርፍ  የተቀላቀለው አዲሱ ጣቢያን የኢትዮሳት NSS 12 57°E ተጠቃሚዎች በ11545 Hor 45000 ሰርች በማድረግ መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

መርካቶ ቴሌቪዥን ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣት ስራ ፈጣሪዎች የሚመራ አዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሆነም ሰምተናል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
17👍7
📌ሀይማኖት ግርማ ለልጇ የቤት ስጦታ ሰጠች

ድምፃዊት ሀይማኖት ግርማ "ልጄ አሜን አልበሜን ስሰራ ቀን እና ማታ ሳይል አብሮኝ ስለለፋ በአዲሱ አመት ስጦታ" በማለት የመኖሪያ ቤት ስጦታ ማበርከቷ ተሰምቷል።

ልጇ አሜንም "እኔ ግዴታዬን ነው የተወጣውት።ከዚህ በኋላ በህይወትሽ ላይ ለሚገጥምሽ ማንኛውም ነገር ከጎንሽ ነኝ" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
13👎5🥰1👏1
📌የሜሮን ጌትነት አዲስ መጽሐፍ ታተመ

የሁለገቧ ከያኒ ሜሮን ጌትነት "ሌላ ዕውነት የለኝም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መፅሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል ተብሏል።

"ሌላ ዕውነት የለኝም" መጽሐፍ ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘና በ134 ገፆች የተቀነበበ ነው።

ሜሮን በተለያየ ጊዜ የጻፈቻቸውን ግጥሞች በአንድ ላይ አድርጋ ለሕትመት ያበቃች ሲሆን ግጥሞቹም በግላዊ ገጠመኝና ዕይታ ላይ ትኩረታቸውን ያደርጋሉ።

ገጣሚ ሜሮን ጌትነት ስለመጽሐፏ "ሌላ እውነት የለኝም በተለያየ ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ ውስጥ ሆኜ የፃፍኳቸው ግጥሞች ስብስብ ነው። ግላዊ ስሜቶች፣ እውነቶችና በህይወት መስመር ላይ ያስተዋልኳቸው ማህበራዊ ሁነቶች ከጫሩብኝ ሀሳቦች ተነስቼ የከተብኳቸው ናቸው ትወዷቸዋላችሁ"ስትል ሀሣቧን ለተወዳጅ ሚድያ ገልጻለች።

ለ10 ዓመታት መኖሪያዋን ባህር ማዶ አድርጋ የነበረችው የኪነ- ጥበብ ሰው ሜሮን ጌትነት  ለጥቂት ዓመታት ከጥበቡ ዓለም ራቅ ብላ መቆየቷ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
25👍3👏2🥰1
📌ለ1 ሚሊየን ዶላር አሸናፊነት ይወዳደራሉ

ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች በአሜሪካ ጎት ታለንት ለ1 ሚሊየን ዶላር አሸናፊነት ይወዳደራሉ።

በ2025 የአሜሪካ ጎት ታለንት እየተወዳደሩ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች ቶማስ አለሙ እና ታምራት አያሌው ቲቲ ቦይስ ወደ ፍጻሜ ማለፍ ችለዋል።

ቲቲ ቦይስ ከሌሎች 8 ተወዳዳሪዎች ጋር በመፋለም ነው 4 ተወዳዳሪዎች ብቻ ወዳለፉበት የፍጻሜ ውድድር የተቀላቀሉት፡፡

ኢትዮጵያውያኑ የሰርከስ አርቲስቶች ቲቲ ቦይስ በተመልካች እና በውድድሩ ዳኞች ከፍተኛ አድናቆት ተችሯቸዋል።

በዳኞች በተሰጣቸው አስተያየት ሥራቸው ድንቅ የሆነ ተሰጥኦና በዓመቱ ከታዩ ክስተቶች አንዱ ነው ተብሎላቸዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ማህበር ጥምረት ፕሬዚዳንት ተክሉ ተሻገር ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያውያን በዚህ ዓለም አቀፍ ግዙፍ የተሰጥኦ ውድድር መድረክ ለፍጻሜ ሲደርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ይህም ለኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሁሌም የሚጠቀስ ትልቅ ስኬት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

የውድድሩ ሽልማት የሆነውን 1 ሚሊየን ዶላር ለማሸነፍ የሕዝብ ድምፅ ወሳኝ ሲሆን ÷ ለተወዳዳሪዎች ድምፅ በመስጠት ልንደግፋቸው ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል ሲል FMC ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
21👍8
📌አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ በአሜሪካ ኤምባሲ ልዩ እንግዳ በመሆን ይቀርባል

(መግቢያው በነፃ ነው)

በስምንተኛው የCREATOR LAB ዝግጅት  ላይ የፊልም ተዋናይ፣ ደራሲ እና ዳይሬክተር እንዲሁም ፕሮዲዩሰር የሆነውን ቸርነት ፍቃዱ እንግዳ ሆኖ ይቀርባል። 

ቸርነት ፍቃዱ 13 ፊልሞች ላይ በትወና 6 ፊልሞች ላይ በ ፕሮዲዩሰርነት እና 5 ቴያትሮች ላይ ደግሞ በትወና ተሳትፏል።

በብዙዎች ዘንድም ተወዳጅነትን ያተረፈው እና የተመልካችን ቀልብ የሳበው "ኪያ" እና "ጥላዬ" ፊልም ላይ ሲሆን በድርሰትም በትወናም ተሳትፏል። ቸርነት በቀርቡ በሰራው ስራም ቀንጃ ፊልም ላይ በ ፕሮዲዩሰር እና በትወና መሳተፉ ይታወቃል ።


በዚህ ዝግጅት ላይም በቅርቡ በወጣው ቀንጃ ፊልም ላይ ስለ ፊልሙ አሰራር ፣ ገጠመኞች እንዲሁም የራሱን የሂዎት ተሞክሮ ለ እናንተ ለተሳታፊዊች ለማካፈል ቀጠሮ ይዘናል። ሰለሆነም በዚህ መድረክ ላይ እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

ተዋናይ ፤ ደራሲ እንዲሁም አዘጋጅ የመሆን ፍላጎት ያላችሁ እና በ ሙያው ላይ ልምድ ያላችሁ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛ ዕድል ለእናንተ ነው።


📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 (  ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

📅 ቀን: ማክሰኞ - መስከረም 6 ፣ 2017

🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00 

🎟 መግቢያ: ነፃ

አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር

📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
17
📌‎የክቡር ዶክተር ሃዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ካስፈተናቸው 25 ተማሪዎች መካከል 24ቱ ከ529 በላይ ውጤት አምጥተዋል።

‎የክቡር ዶክተር ሃዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ደረጀ ከፈለኝ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ  ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩን አስረድተዋል።

‎አዳሪ ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ ለ3ኛ ጊዜ  የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በመስጠት በክልሉ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

በአዳሪ ት/ቤቱ በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 25 ተማሪዎች መውሰደቸውን የተናገሩት አቶ ደረጀ  ከ25 ተፈታኞች መካከል 24ቱ ከ529 በላይ፤ ማምጣታቸውንና 3 ተማሪዎች ደግሞ  573 ያመጡ ሲሆን፤  አንድ ተማሪ 407 ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል።

‎25ቱም ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህር ዘርፍ ፈተና መውሰዳቸውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አስረድተዋል።

Via tikvahuniversity

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
👏2916
📌አሻም ቴሌቪዥን የስራ ማስታወቂያ አውጥቷል

ቴሌቪዥን ጣቢያው 4 ሪፖርተሮችን ይፈልጋል።

በተጨማሪም ኤዲተር ፣ የፕሮግራም ክፍል ኃላፊ እና የሽያጭ ባለሞያም እፈልጋለሁ ብሏል።

የአሻም ቴሌቪዥን ባልደረባ መሆንን የምትሹ ተመዝገቡ። ተወዳደሩ ።ይቅናችሁ እንላለን።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
13🥰4
ይህ የዘናጭ ፍላወርስ መልዕክት ነው

ቆይ መቼ ነው ህይወቴ ለምትላት ሚስትህ እቅፍ አበባ አስታቅፈሀት ቀኗን የምታሳምርላት...

መቼስ ነው  ለፍቅረኛህ  የፈካ ፅጌረዳ ሰጥተህ ቀኗን የምታፈካው?

ኧ ?

መቼ አሰብክ

ነገ አይባልም።

ፍቅርን ፣ደስታን ፣ለመግለፅ  ቆይ ነገ፣ከነገ ወዲያ አይባልም።

ለዚህ ደግሞ ዘናጭ ፍላወርስ አሉልህ ።

📍 አድራሻቸው ሰሚት ፍየል ቤት 20 ሜተር ላይ ተገኘዋለህ።

ከደወልክም ያለህበት ይልኩልሃል ።

☎️09 22 74 04 75 
6🥰3😁1
📌ጋዜጠኛ አልዳ ግዛቸው ብራንድ አምባሳደር ሆነች

አስቀድሞ በሸገር 102.1 ሬድዮ አሁን ላይ በኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተለያዩ መሰናዶዎችን በማዘጋጀት እና በማቅረብ የምትታወቀው ጋዜጠኛ ኤልዳ ግዛቸው የ"ቢሃይንድ ዘ ሲን" ብራንድ አምባሳደር በመሆን እንደተሾመች ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኤልዳ ግዛቸው ብራንድ አምባሳደር ሆኖ የተሾመችበት"ቢሃይንድ ዘ ሲን" በሰባት የአፍሪካ ሀገራት እየተከወነ የሚገኝ የጥናት እና የምርምር ፕሮጀክት ነው ተብሏል።

መርሐግብሩ የኪነጥበብ ሙያ ላይ ያሉ ወጣት ሴቶች ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግም ተገልጿል።

ሙያተኞች ያላቸውን ሚና፣ ተግዳሮት እና ተስፋ በየሀገራቱ ማጥናት እና የጥናት ውጤቶቹን ለልዩ ልዩ አገልግሎት በተለይም ለፖሊሲ ግብአት እንዲውሉ ያደርጋል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት ላይ OSSREA፣ ICRW ከMaster Card Foundation ጋር ተባብረው ይሰራሉም ተብሏል።

ጋዜጠኛ አልዳ ግዛቸው ከጋዜጠኝነቷ ባሻገር በተለያዩ መድረኮች እና ማህበራዊ ትስስር ገፆቿ በኩል በምታጋራቸው የሥነጽሑፍ ሥራዎቿም ትታወቃለች።

📲 TikTok:

https://www.tiktok.com/@eldagizachew?_t=ZM-8ycUyGgkmYC&_r=1

📸 Instagram: https://www.instagram.com/elda_gizachew?igsh=ZGFudHJvY3d0bzJ0

▶️ YouTube: http://www.youtube.com/@eldacorner369

#BehindTheScenesAfrica #CreativeEquity #YoungWomenInArts #NationalCreativeAmbassador
12❤‍🔥1🔥1