ባይራ ዲጂታል መጽሄት ቅጽ 2 ቁጥር 4.pdf
8.9 MB
📌ባይራ ዲጂታል መጽሔት ለንባብ በቅቷል።
ቅጽ 2 ቁጥር 4
በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com

❤8
📌የአስቻለው "እመት ሸዋ" ቪዲዮ ዛሬ ይለቀቃል
የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ(አርዲ) "እመት ሸዋ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሙዚቃ ቪዲዮው በዛሬው ዕለት በብርቧክስ ሪከርድስ በኩል ይሰራጫል።
አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ከዚህ ቀደም በለቀቃቸው "እናትዋ ጎንደር" እና "ካሲናው ጎጃም" "አሞራው ካሞራው" በተሰኙ ሙዚቃዎች ከፍተኛ ተደማጭነትን አግኝቷል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

❤10👍1
📌ንጉሥ ማልት በምርት ጥራት ተሸለመ
በምርቱ ጣዕም እና ጥራት ተወዳጅነትን ያተረፈው ንጉስ ማልት ለሽልማት በቅቷል።
ሸላሚው ድርጅት በ1961 በብራስልስ፣ ቤልጂየም የተመሰረተው Monde Selection ሲሆን ግንባር ቀደም ራሱን የቻለ የጥራት ግምገማ ተቋም ነው።
በጠንካራ ግምገማዎቹ እና መስፈርቶቹ የሚታወቀው ሞንዴ ሰሌክሽን በየአመቱ ምርቶችን በምግብ፣ መጠጦች፣ መዋቢያዎች እና ሌሎችንም ከ3,000 በላይ የሆኑ የተለያዩ ምርቶች ገምግሞ እንደየ ጥራት ደረጃቸው ሽልማት ይሰጣል።
ይህ ተቋም የነሐስ፣ ሲልቨር፣ ወርቅ እና ግራንድ ወርቅን ጨምሮ የተከበሩ የጥራት መለያዎችን በመሸለም በአለም አቀፍ ደረጃ ይታወቃል።
ከ60 ዓመታት በላይ ባለው እውቀት፣ Monde Selection በተጠቃሚ ምርቶች ጥራት ላይ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያዘጋጃል።
በእዚህ ትልቅ ተቋም ከአልኮል ነፃ መጠጥ የሆነው ንጉስ ማልት የ2025 በምርት ጥራት የወርቅ ተሸላሚ ሆኗል።
ንጉስ ማልት ከሞድን ሰሌክሽ የጥራት ሽልማት ሲያገኝ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።
ባለፈው አመትም የብር ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል። በአገራችን ኢትዮጵያ ከንጉስ ተጨማሪም ሌሎች ምርቶችም እንደየ ጥራት ደረጃቸው እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ይህ ተደጋጋሚ ሽልማት ለንጉስ ማልት እና ለተጠቃሚዎቹ ብቻ ሳይሆን ለአገር የሚያበረክተው እውቅና ቀላል አይደለም።
ንጉስ ደረጃውን አስጠብቆ እንዲቆይ ለሌሎች ምርቶች ደግሞ አርአያ በመሆን በምርት ጥራታቸውን አስጠብቀው ከአመት አመት ለሽልማት እንዲበቁ መነቃቃትን ይፈጥራል ።

❤6👍2
📌ፈንድቃ አዲስ የሚያስገነባውን ህንፃ ይፋ አደረገ
ፈንድቃ ባህል ማዕከል በቀጣይ የሚያስገነባውን ዘመናዊ የባህል ማዕከል ህንፃ ንድፍ ይፋ አድርጓል።
ፈንድቃ የባህል ማዕከል ስራ አስኪያጅ መላኩ በላይ በማህበራዊ ትስስር ገጽ "በካርሎ ራቲ አሶሺያቲ - የሚመራው በዓለም አቀፍ ታዋቂ የሆነው የኢጣሊያ የስነ ሕንፃ ተቋም - ለአዲሱ የፈንድቃ ህንፃ ንድፍ የመጀመሪያውን ምዕራፍ እንዳጠናቀቀ በማካፈሌ በጣም ደስተኛ ነኝ" ብሏል።
ፈንድቃ የባህል ማዕከል በጥቅምት 2017 ዓ.ም ከፈረሰ በኋላ በቦታው የራሱን ህንጻ እንዲሰራ ቦታው ለፈንድቃ መሰጠቱ ይታወሳል።
ከታህሳስ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ፈንድቃ ከሀያት ሬጀንሲ ጋር በመተባበር ኮንሰርቶችንና እና አዝማሪ ፕሮግራሞችን እያቀረ ይገኛል።

❤8👍6👎2👌2
📌የአዲስ ለገሠ "ማስታወሻ" አልበም ተለቀቀ
“ማስታወሻ" የተባለ ስያሜ የያዘው ይህ የመጀመሪያ አልበሙ 14 የሙዚቃ ስራዎች የተካተተበት ነው።
አልበሙ ፍቅር የተቀነቀነበት መዋደድ የነገሠበት አዲስ ለገሠ የራሱን ቀለም እና አቀራረብ ያስተዋወቀበት ስራ ነው ተብሏል።
አልበሙ በርካታ የሙዚቃ ዘይቤዎችን እና ዘውጎችን ያካተተ ሲሆን በሀሳብ፥ በሙዚቃ ቅንብር፥ በድምፅ እና በአዘፋፈን አዲስ ጣዕም ይዞ መቅረብ ችሏል።
በማስታወሻ አልበሙ ላይ ይልማ ገ/አብ፣ ናትናኤል ግርማቸው፣ እሱባለው ይታየው (የየሺ ልጅ)፣ ሞገስ ተካ እና ሌሎች ዕውቅ የዜማና የግጥም ደራሲዎች፣ እንዲሁም እራሱ አዲስ ለገሠ በግጥም እና ዜማ የተሳተፉበት ነው፡፡
በሙዚቃ ቅንብሩም ሚካኤል ሃይሉ፥ ኪሩቤል ተስፋዬ፥ ብሩክ አፈወርቅ እንዲሁም ሌሎችም የተሳተፉብት ሲሆን ማስተሪንጉን ኪሩቤል ተስፋዬ ተጠቦበታል፡፡
የ “ማስታወሻ” አልበም ስራን ጀምሮ ለማጠናቀቅ ሶስት ዓመታትን እንደፈጀ የተነገረ ድምጻዊው ለዚህ የአልበም ሥራው ሲል በርክት ያለ ክፍያ ከሚከፈልበት ከሙዚቃ ክለብ ስራዎች ራሱን ከሁለት ዓመታት እንዳቀበም ተናግሯል።
ድምጻዊ አዲስ ለገሠ "ኮርቼ የሚናገርለት አልበም ነው" ሲሉ የገለጸውን የመጀመሪያ አልበሙን በአዲስ ለገሰ ይፋዊ ዩትዩብ ቻናልና በሁሉም ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች ለቋል።
አዲስ ለገሠ: YouTube:https://youtube.com/@addislegesseofficial?si=k2XXutbiqlcdVMcD

❤20😢1
📌አንዱ መጽሐፍ በ130 ሺህ ብር ተሸጠ
የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኀበር የተቋቋመበትን 27ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “ወባን በእኛ ሐብት፣ በእኛ እውቀትና ጉልበት እናጠፋለን!" በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በስዊስ ኢን ኔክሰስ ሆቴል በድምቀት ተከብሯል።
በዚህ የምስረታ ክብረ በዓል ላይ የማኅበሩን የሃያ ሰባት ዓመታት ታሪክ የሚያሳይ "ፈጥኖ ደራሹ ማኅበር" የተሰኘ መጽሐፍ ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።
በክብረ በዓሉ ላይ ይህ "ፈጥኖ ደራሹ ማኅበር" የተሰኘው መጽሐፍ በ130 ሺህ ብር ተሸጧል። መፅሐፉን ለጨረታ ያቀረበው የፕሮግራሙ መሪ ማናዬ እውነቱ ነው። ጨረታውን ሲሲ አር ዲኤ በ80ሺ ብር ያሸነፈ ሲሆን መፅሐፉን ለመግዛት ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርግ የነበረው ለወገኔ ማይክሮ ፋይናንስ ለጨረታ ያዘጋጀውን 50ሺ ብር ለማህበሩ ገቢ አድርጏል።
"ፈጥኖ ደራሹ ማኅበር" መጽሐፍ በአስር ሁለት ምዕራፎች የተዘጋጀ ሲሆን የመጽሐፉ ዓላማ የማኅበሩን አመሠራረት፣ ያከናወናቸውን ሥራዎች፣ የተገኙ ለውጦችን፣ እየተካሄዱ ያሉ ሥራዎችን፣ መልካም ጎኖችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣ የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎችን ዘርዝሮ በማቅረብ ለቀጣይ ትውልድ ብሎም ለመሰል ድርጅቶች ትምህርት ሆኖ እንዲያገለግል እንደሆነም ተገልጿል።
የጤና፣ልማትና ፀረ-ወባ ማኀበር ነሐሴ 17 ቀን 1990 ዓ.ም ተመሥርቶ ባለፉት 27 ዓመታት ሕብረተሰቡን የሚጠቅሙ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እንዳከናወነ አስታውቋል።
ፎቶ: Tekle Markon

👍8❤5🤣4👎2
📌አርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ ይቅርታ ጠየቀ
አርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን ይቅርታ ጠየቀ። አርቲስት ሸዋፈራው በሰይፉ ሾው ላይ ቀርቦ ይቅርታ መጠየቁን ተመልክተናል። አሁን የማምንበትን መፅሐፍ ቅዱስ የሰጠችኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ናት፣ እኔ ብሽሽቅ ውስጥ አልገባም፣ ወንጌል ብሽሽቅ አይደለም፣ "እዛ ሰፈር" እያልኩ ለነበረው ስብከት ይቅርታ እጠይቃለሁ። ሌላው አለ የተባለውን እኔ አላልኩም ማስረጃ መቅረብ አይቻልም። እዛ ሰፈር ላልኩት ይቅርታ እጠይቃለሁ ብሏል።
©️Fast Mereja

👎29👏11🍌3✍1❤1
📌የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጳጉሜ 4 ይመረቃል !
ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ከ11 ቀናት በኃላ ጳጉሜ 4 2017 ዓ.ም ይመረቃል ተብሏል።
በኬንያ የኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር ደመቀ አጥናፉን ምንጭ አድርጎ ቢቢሲ እንደዘገበው ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም የአፍሪካ መሪዎች እና ሌሎች የተጋበዙ እንግዶች በሚገኙበት ይመረቃል።
ከአምስት ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት በአፍሪካ ግዙፉ እንደሆነ የተነገረለት ሕዳሴ ግድብ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታው ሲካሄድ ቆይቷል።
በአምስት ዓመታት ውስጥ ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ ከአስር ዓመታት በላይ ፈጅቶ የኢትዮጵያ መንግሥት በመጪው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ በይፋ እንደሚመረቅ ማስታወቁ ይታወቃል።

❤15👎1
📌ፈለገ ኪን የኪነጥበብ መድረክ 1ኛ ዓመት
ከኢትዮጵያ ዓይነስውራን ማሕበር ጋር በመተባበር በየወሩ የሚዘጋጀው "ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ መድረክ የፊታችን ቅዳሜ አንደኛ ዓመቱን ያከብራል።
ወጣት ከያኒያንን በማበረታታትና አንጋፋ የኪነጥበብ ሰዎችን በመዘከር ፤ በኪነጥበቡ ዓለም የላቀ አበርክቶ ያላቸውን ሙያተኞችን በክብር እንግድነት ጋብዞ ልምዳቸውን እንዲያጋሩ በማድረግ ለተከታታይ 11 ወራት የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።
"ፈለገ ኪን" አንደኛ ዓመቱን በርካታ የኪነጥበባ ባለሞያዎች በተገኙበት ነሐሴ 24 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አሸናፊ ከበደ የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል ውስጥ ይከበራል።

❤5
📌ጉዞ ወደ ተወዳጁ እና የአለም ምርጥ የቱሪዝም
በሚያምረው ወንጪ ናሂሊ ትመረቃለች ፤ ምርቃት ብቻ ሳይሆን የጀልባ ሽርሽር ፣ ሀይኪንግ እና
የጭቃ ባዝ ከምንከውናቸው ነገሮች ናቸዉ ፤
በጉዞ መፅሀፍ መመረቅ አዲስ ፣ የሚያምር እና የተለየ ልማድ ነው ፤ ናሂሊን በደስታ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ እና እሁድ ( ነሀሴ 24 እና 25 ) እንመርቃት።
Date : August 30 & September 1 2025
Duration : 2 days & 1 night
Departure: Mexico, Wabi Shebelle Hotel
6:00 AM @ 12:00 LT
Price : 8000ETB For Locals
Package includes
ትራንስፖርት / Transport
ቁርስ / Breakfast /X2/
ምሳ / Lunch / X2 /
እራት / barbecue
የታሸገ ውሃ / Bottled Water
የመግቢያ ዋጋ / Entrance
የአስጎብኚ / Local Guide
ዋና / Swimming
የምሽት እሳት ዳር ጨዋታCampfire
የተፈጥሮ ፍል ውሀ / Hot Spring Water & bath
ማደሪያ ድንኳን (Tent)
📷ፎቶግራፍ /🌅 Photograph
For more info call 📞 0919874598

📌ሰውመሆን ይስማው እና ግሩም ኤርሚያስ እንግዳ የሆኑበት ልዩ ዝግጅት በአሜሪካ ኤምባሲ ተዘጋጅ
(መግቢያ በነፃ ነው)
በስድስተኛው የcreative lab ዝግጅታችን ሁለት ተወዳጅ እንግዶችን ይዘንላቹ የመጣን ሲሆን ተወዳጁን ተዋናይ ፣ ደራሲ እና ዳይሬክተር ግሩም ኤርሚያስን እና ሲኒማቶግራፈር እንዲሁም ደራሲ እና ዳይሬክተር የሆነው ሰውመሆን ይስማውን ይዘንላችሁ ቀርበናል።
በዚህ ዝግጅት ላይ ለእናንተ ልምዳቸውን እና የፊልም ተሞክሮዋቸውን የሚያካፍሉበት ዝግጅት ነው ።
እንዲሁም የግሩም ኤርሚያስ የሆነውን ወርቀዘቦ የተሰኘውን ፊልም ለዕይታ በማቅረብ በፊልሙ ላይ የውይይት መርሃግብር ይኖረናል። ሰለሆነም በዚህ መድረክ ላይ እንዲታደሙ ተጋብዘዋል።
ጀማሪ የፊልም እና የቴያርትር ፍላጎት ያላችሁ እና በሙያው ላይ መስራት የምትፈልጉ ይህ የመገናኛና ዕድል ለእናንተ ነው።
📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )
📅 ቀን: ነሃሴ 27 ፣ 2017
🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00
🎟 መግቢያ: ነፃ
አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር
በፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ቴሌግራም ገፃችንን ፎሎ ማድረግ እንዳይረሱ
📎 በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA
ለተጨማሪው:
https://t.me/EventAddis1

❤11👍1🔥1🥰1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
1.የዘጠናዎቹ ተወዳጅ ድምጻዊት ትዕግሥት በቀለ ከ20 ዓመታት በኃላ የሙዚቃ ኮንሰርቷን በኢትዮጵያ ልታቀርብ ነው። ኮንሰርቱ የሚካሄድበት ቀን ታውቋል።ድምጻዊቷም ወደ ኢትዮጵያ መጥታለች።በዝርዝር እንነግራችኋለን።
3.በተጠባቂው የመላው አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) ላይ አራት ሴት ድምጻዊያን ከኢትዮጵያ እጩ ሆነዋል። እጩ የሆኑት ድምጻዊያን እነማን ናቸው?።
3.በአዲስ አበባ ከተማ በስፋቱ እና በያዛቸው የመጻሕፍት ዓይነት ግዙፍ ነው የተባለለት ዘመናዊ የመፅሐፍ መደብር ነገ ይከፈታል።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/mKL83b3hC1I?si=pvxT82muNGPfdbJq
📌መልካም ምሽት

📌 የነዋይ ደበበ ነጠላ ሙዚቃ ተለቀቀ
የአንጋፋው ድምጻዊ ነዋይ ደበበ "የብርሃን ሉል" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ አመሻሹን በሆፕ ኢንተርቴይመንት የዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ቀርቧል።
በዚህ ነጠላ ሙዚቃ ላይ በግጥምና ዜማ ሞገስ ተካ የተሳተፈ ሲሆን የሙዚቃ ቅንብሩን ካሙዙ ካሣ ሰርቶታል።

❤10🔥2
📌ኃይሌ ሆቴል ሻሸመኔ ዳግም ስራ ጀመረ !
ኃይሌ ሆቴል ሻሸመኔ ታድሶና ሚሰጣቸውን አገልግሎቶች አሳድጎ የአስፍቶና ፤አዘምኖ በድጋሚ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።
የኃይሌ እና ዓለም ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር አካል የሆነው ኃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ግሩፐ ባለ ሶስት ኮኮብ ሆቴል በሻሸመኔ ከተማ ዳግም ግንባታውንና የማስፋፊያ ስራውን አጠናቆ ነሀሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ኃይሌ ሆቴል ሻሽመኔ ማስፋፊያውን ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን 84 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣የተለያዩ ባሮችና ዘመናዊ ሬስቶራንቶች የስፖ (የሳውና እና ስቲም) ፣ጂምናዚየም ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) አገልግሎቶች ላይ ማሻሻያዎችን ጨምሮ ስራ ጀመረ።
ሆቴሉ ለ 210 የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በቀጣይ አገልግሎቱን እያሰፋ 300 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ እድልን ይፈጥራል።
የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩኘ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ለግንባታውም ከ600 ሚሊዬን ብር በላይ እንደወጣና የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች መግለጫ የሆነውን በይቻላል መንፈስ የተገነባ የስራ ባህልንና የአገልግሎት ልህቀትን ደንበኞቻቸው በሻሸመኔም እንደሚያገኙ ተናግረዋል።

👍15❤1🔥1👏1
📌ብርሃንና ሰላም ከህትመት ገበያ ወጥቶ ወደ አዳዲስ ዘርፎች ላይ እንዲያተኩር ማሳሰቢያ ተሰጠ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ከመጣው የህትመት ገበያ በመውጣት፣ ትኩረቱን ወደ አዳዲስና ትርፋማ ዘርፎች ላይ እንዲያደርግ በኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንደተመከረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።
ምንም እንኳን ድርጅቱ ባለፉት ዓመታት ትርፋማ ሆኖ ቢቀጥልም፣ ለዘላቂነቱ ሲባል ከህትመት ባሻገር ያሉ አማራጮችን ማየት አስፈላጊ እንደሆነ ታምኖበታል።
ባለፉት ዓመታት ብርሃንና ሰላም ከ178.7 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ የንግድ እና የጸጥታ ሰነዶችን በማተም ከጠቅላላ አቅሙ 92% ተጠቅሟል። በተጨማሪም፣ ከኢንዱስትሪው ለውጦች እና ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎሎች ባሻገር፣ ከግብር በፊት 606 ሚሊዮን ብር ትርፍ በማስመዝገብ፣ ከዓመታዊ ዒላማው 98% ማሳካቱን ተገልጿል።
ይሁን እንጂ፣ ይህ ስኬት ቢኖርም፣ ኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ድርጅቱ በጊዜ ሂደት ሊቀንስ ከሚችለው የህትመት ገበያ ቀስ በቀስ እንዲወጣና ወደፊት ትርፋማ ሊሆኑ በሚችሉ ሌሎች የንግድ መስኮች ላይ እንዲያተኩር አሳስቧል። ይህ ስልታዊ ለውጥ የድርጅቱን ተወዳዳሪነትና ዘላቂነት እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።

❤12😢4👍2
📌 "የብሌን አንዳች" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል
የጋዜጠኛ ዋለልኝ አየለ "የብሌን አንዳች" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ አርብ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።
በ240 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ 24 ርዕስ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል በ400 ብር የጀርባ ዋጋም ለአንባቢያን ቀርቧል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የጋዜጠኛ ዋለልኝ አየለ "የብሌን አንዳች" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ አርብ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።
በ240 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ 24 ርዕስ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል በ400 ብር የጀርባ ዋጋም ለአንባቢያን ቀርቧል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4
📌መቅረዝ ሥነ ኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል
የመቅረዝ ሥነ ኪን የኪነጥበብ ዝግጅት የዓመቱ ማጠናቀቂያ መሰናዶ ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በአድዋ ሲኒማ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ ዝግጅት ላይ ሚካኤል ታምሬ፣ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል፣ ኤፍሬም ስዩም የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የመቅረዝ ሥነ ኪን የኪነጥበብ ዝግጅት የዓመቱ ማጠናቀቂያ መሰናዶ ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በአድዋ ሲኒማ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ ዝግጅት ላይ ሚካኤል ታምሬ፣ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል፣ ኤፍሬም ስዩም የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5
ግጥም ሲጥም በብሔራዊ ቤተመንግስት AHOC
ሀብታሙ ሃደራ በ2016 ዓመተ ምህረት ያደረሰን 'እንዲህ ያለም የለ!' የተሰኘ ጥዑም የግጥም ስብስብ መጽሐፉን እንዘክራለን።
በሰዓቱ ተገኙና በሀብታሙና በጓደኞቹ በሚቀርቡ ጥዑም ግጥሞች ሰላምን ሸምቱ፤ ጎበዝ ገጣሚያንን ተዋወቁ!
በፍል ውሃ በኩል ባለው የብሔራዊ ቤተመንግስት መግቢያ (5ኛ በር) ቢገቡ አዲስ ሃውስ ኦፍ ካልቸርን በቀላሉ ያገኙታል።

❤7
📌 ድባብ የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል
ድባብ የኪነጥበብ ዝግጅት ለመጀመሪያ ጊዜ ነገ አርብ ነሐሴ 30 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ 22 አካባቢ በሚገኘው ድባብ ሆቴል ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።
በዚህ የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ ደራሲ ዘነበ ወላ በክብር እንግድነት የሚቀርብ ሲሆን በተጨማሪም ምግባር ሲራጅ፣ ሀብታሙ ሀደራ፣ አስታወሰኝ ረጋሣ፣ኪሩቤል ዘርፉ፣ ታዲዮስ አዲሱ እና ሌሎችም የሥነጽሑፍ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

❤3
"ወይ አዲስ አበባ" መጽሔት በድጋሚ ወደ ህትመት
“ወይ አዲስ አበባ” መጽሔት በኅትመት ዋጋ መናር ምክንያት ከተቋረጠች በኋላ በአዲስ ዓመት ዋዜማ፣ የፊታችን ቅዳሜ ዳግም ለኅትመት በቅታ ከእጃችሁ ትገባለች።
"ወይ አዲስ አበባ" መጽሔት ከአሁን በኋላም በየሁለት ወሩ እየታተመች ለንባብ ትበቃለችም ተብሏል።
"ወይ አዲስ አበባ" ወደ ህትመት በድጋሚ ስትመለስ በመጀመሪያ እትሟ ደራሲ ስንዱ አበበ፣ሰሎሞን ወርቁ፣ሠዓሊ እሸቱ ጥሩነህ፣ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ፣ ደረጀ በላይነህ፣ መዓዛ ወርቁ፣ ጥሩነህ ካሳ፣ ኃይሉ ውድነህ፣ ብርሃኑ ሰሙ፣ መኮንን ወልደ አረጋይ፣ ዕዝራ እጅጉ፣ ሶስና አሸናፊና ገዛኸኝ መኮንን እና ሌሎችም የበኩላቸውን የሀሳብ ሰበዝ አዋጥተዋል።
በተጨማሪም የብርሃኑ ድጋፌን ምርጥ ፊልሞችና ሙዚቃዎችም ትጠቆማላችሁ።
ቅዳሜዎ በመዝናናት ላይ መዝናናት፣ በቁምነገር ላይም ቁምነገር ይታከልባት ዘንድ፣ “ወይ አዲስ አበባ” መጽሔትን ቀድመው ከእጅዎ ያስገቡ ተብላችኋል።
በጃዕፈር መጻሕፍት መደብር እና በቶሞካ ሁሉም ቅርንጫፎች ውስጥ ያገኟታል።
“ወይ አዲስ አበባ”ን ያንብቡ፣ በ“ወይ አዲስ አበባ” ላይም ይጻፉ ።

❤9👍4
📌"ወርቃማ ታሪኮች" አውደርዕይ ቅዳሜ ይከፈታል
የሠዓሊ ኢያሱ ሲሳይ የሥዕል ስራዎች የሚቀረቡበት "ወርቃማ ታሪኮች" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ የፊታችን ቅዳሜ ጷጉሜን 1 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ መስከረም 5 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

❤6