📌ሎጆችና ሬስቶራንቶች ደረጃ ሊሰጣቸው ነው
የቱሪዝም ሚኒስቴር ቀደም ሲል በሆቴሎችና ሪዞርቶች ላይ ብቻ ሲካሄድ የቆየውን የደረጃ ምዘና ሥራ፣ ሎጆችንና ሬስቶራንቶችን ጭምር እንዲያካትት የሚያስችል አዲስ ሀገራዊ መመዘኛ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
ይህ አዲስ የደረጃ አሰጣጥ ሥርዓት አገሪቱ ለቱሪዝም ዘርፍ የምትሰጠውን ትኩረት ከፍ የሚያደርግ ሲሆን፣ የዘርፉን ጥራትና አገልግሎት ለማሻሻል ያለመ ነው ተብሏል።
የተዘጋጀው መመዘኛ በረቂቅ ደረጃ ተጠናቅቆ፣ በቀጣይነት ለባለድርሻ አካላት ውይይት ቀርቦ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።
በሌላ በኩል፣ ከ2014 በጀት ዓመት ጀምሮ አዳዲስ ሆቴሎች በተገቢው ጊዜ የደረጃ ምደባ እንዲያደርጉ የታቀደ ቢሆንም፣ የደረጃ ምደባው ሂደት ላይ ችግሮች መፈጠራቸው ታውቋል።
የተፈጠሩት ችግሮች ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች እንዳሏቸው ተጠቁሟል። አንደኛው፣ ባለሀብቶች በተያዘው ጊዜ የኮከብ ደረጃ ለመመደብ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ አብዛኞቹ ተቋማት የኮከብ ደረጃ ለመመደብ ብቁ ሆነው አለመገኘታቸው ነው። ይህ ደግሞ የቱሪዝም ዘርፉን ጥራት ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ላይ ፈተና እንደሚሆን ተገልጿል ሲል ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

❤3
📌የአነጋጋሪው ሙዚቃ ቪዲዮ ነገ ማታ ይለቀቃል
የድምጻዊ ናቲ ኬር "ነገር ነገር " የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና በቲክቶክ የማህበራዊ ትስስር ገፅ መድረክ በርካቶች የተቀባበሉት ሙዚቃ ቪዲዮ ነገ አርብ ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በድምጻዊው የዩቲዩብ ቻናል ለአድማጮች ተመልካች ይቀርባል ተብሏል።
"ነገር ነገር ባይልሽ ነገር - ተሸክሜ አኖርሽ ነበረ"
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የድምጻዊ ናቲ ኬር "ነገር ነገር " የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና በቲክቶክ የማህበራዊ ትስስር ገፅ መድረክ በርካቶች የተቀባበሉት ሙዚቃ ቪዲዮ ነገ አርብ ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በድምጻዊው የዩቲዩብ ቻናል ለአድማጮች ተመልካች ይቀርባል ተብሏል።
"ነገር ነገር ባይልሽ ነገር - ተሸክሜ አኖርሽ ነበረ"
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤8👍2🔥2
📌 የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሹም ሽር
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን ከታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጌትነት ታደሠ ከኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኃላፊነታቸው ተነስተው የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እንደተሾሙ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
አቶ ጌትነት ታደሰ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሸን ኮሚሽነር ኃላፊ ሆኖ የተመደቡት በአምባሳደር ሽፍራው ሽጉጤ (ዶ/ር) ምትክ መሆኑንም ሰምተናል።
አቶ ጌትነት ታደሠ ከኢቢሲ ስራ አስፈፃሚነታቸው አስቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ እንደነበሩ ይታወሳል።

👍5😁4❤2🤣1
📌በአዲስ አበባ የጋረዱ አሟሟት መነጋገሪያ ሆነ
ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ 22 አካባቢ በሚገኘው "ቪ.አይ.ፒ ላውንጅ" በተሰኘው ጭፍራ ቤት (ክለብ) ውስጥ በጠባቂነት(ጋረድ) ሆኖ ሲሰራ የቆየው ወጣት ልደቱ አየነው (አቢ) በድንገተኛ ጥቃት እንደተገደለ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በወቅቱም የሟች አስክሬን ለምርመራ የተወሰደ ሲሆን ውጤቱም ከ15 ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚሆን ተነግሯል።
ወጣት ልደቱ አየነው (አቢ) በሚሰራበት ቪ.አይ.ፒ ላውንጅ ውስጥ ስራ ላይ እያለ በጩቤ ተወግቶ መገደሉንም የቅርብ ቤተሰቦቹ በማህበራዊ ገፆቻቸው ሲናገሩ ተመልክተናል።
የሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች የሚሰራበት ሆቴል ሰራተኛው ተገደሎበት ለአንድ ቀን እንኳ ስራውን ሳያቆም እየሰራ እንዳለና የአዲስ አበባ ፖሊስ ገዳዮቹን ለህግ በማቅረብና ለጠፋው ህይወት ተመጣጣኝ ፍትህ ለመስጠት ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማድረጉንም ጭምር እየተናገሩ ይገኛሉ።
በዚህም ምክንያት "ፍትህ ለአቢ" እና "ሕጉ ይከበር፣ ፍትህ ይስፈን" በሚል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እያካሄዱ ነው።
በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻቸውም 1ኛ ግልጽና ፍጥነት ያለው ምርመራ እንዲፈጸም 2ኛ የተጠረጠረው አካል በህግ ፊት የሚገባውን ፍርድ እንዲያገኝ 3ኛ ፍትህ ሳይዘገይ በተግባር እንዲፈጸም በአጠቃላይ ለወጣት ልደቱ ፍትህ እንዲሰጠው ጥያቄዎችን እየቀረቡ ይገኛል።
ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዲስ አበባ ፖሊስና እና ከቪ.አይ.ፒ ላውንጅ ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ቢሞክርም አልተሳካም።

❤11😭11🤔2
Event Addis Media
📌በአዲስ አበባ የጋረዱ አሟሟት መነጋገሪያ ሆነ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ 22 አካባቢ በሚገኘው "ቪ.አይ.ፒ ላውንጅ" በተሰኘው ጭፍራ ቤት (ክለብ) ውስጥ በጠባቂነት(ጋረድ) ሆኖ ሲሰራ የቆየው ወጣት ልደቱ አየነው (አቢ) በድንገተኛ ጥቃት እንደተገደለ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በወቅቱም የሟች አስክሬን ለምርመራ የተወሰደ ሲሆን ውጤቱም ከ15 ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚሆን…
📌የፖሊስ መግለጫ ስለ ጋረዱ አሟሟት
ቪ አይ ፒ ላውንጅ በሚባል ሆቴል በሁለት ግለሰቦች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የሰው ህይወት ማለፉን ተከትሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
ድርጊቱ የተከሰተው ነሀሴ 07 ቀን 2017 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 7 ሰዓት ከሩብ ገደማ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሃያ ሁለት አካባቢ በሚገኘው" ቪ አይ ፒ ላውንጅ" በተባለ ሆቴል ውስጥ ነው።
በዕለቱ በድርጅቱ በጋርድነትና በዲጄ ሰራተኝነት ተቀጥረው በሚሰሩ ልደቱ አያኖ እና ናትናኤል ልዑል በተባሉ ግለሰቦች መካከል ምክንያቱ ባልታወቀ አለመግባባት በተፈጠረ ጸብ ምክንያት ናትናኤል ልዑል የተባለው ግለሰብ ጭንቅላቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረስበት መሆኑን ፖሊስ በስፍራው ደርሶ ካሰባሰበው መረጃ ማረጋገጥ ተችሏል።
በቅርብ ርቀት የነበሩ ሰዎች ተጎጂውን ወደ ህክምና በመወሰድ ልደቱ አያኖ የተባለው ግለስብ ከአካባቢው እንዳይሸሽ እየጠበቁት በነበረበት አጋጣሚ ድብደባው በተፈፀመበት አልጋ ክፍል ቁጥሩ 505 አምስተኛ ፎቅ ላይ ባለ ክፍል ውስጥ ገብቶ በሩን ከውስጥ በመዝጋት ከክፍሉ ባለ መስኮት ወደ መሬት ወድቆ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እርዳታ እየተደረገለት ህይወቱ ያለፈ ሲሆን ትክክለኛ የአሟሟቱን ሁኔታ ለማወቅ ምርመራው ቀጥሏል።
ከባድ ጉዳት የደረሰበት ናትናኤል ልዑል የተባለው ግለሰብ አሁንም በህክምና ተቋም ውስጥ ተኝቶ ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማስረጃ የማሰባሰብ ስራዎችን በመስራት እና የአስክሬን ምርመራ ውጤት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል የምርመራ ስራው እንደተጠናቀቀ ሙሉ መረጃውን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
@EventAddis1

❤8😭2
📌 የተሰወሩት ጋዜጠኞች መፈታታቸው ተሰማ
ከሰሞኑ መነጋገርያ ሆኖ የሰነበተው የሶስት ጋዜጠኞች በሀይል ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ ደብዛቸው መጥፋቱ ነበር። ድርጊቱ በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጭ ያሉ ጋዜጠኞችን እና እንደ ሲፒጄ ያሉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ቡድኖችን ትኩረት ስቦ ቆይቷል።
መሠረት ሚድያ እንደዘገበው ከሆነ ትላንት ማምሻውን (ነሐሴ 16 2017 ዓ.ም) ታፍነው ተወስደው የነበሩት ጋዜጠኞች አብዱልሰመድ መሐመድ፣ ዮናስ አማረ እና ሐሰን ሰይድ ከታፈኑበት ተለቀው በተለያዩ የአዲስ አበባ ስፍራዎች ተበትነው ተገኝተዋል።
ትላንትና ምሽት ሶስት ሰዓት ገደማ ጋዜጠኞቹ ከአዲስ አበባ ወጣ ባሉ ስፍራዎች ተለቀው መገኘታቸው ታውቋል።
©️ዘገባው የመሠረት ሚዲያ ነው።

👏3🤬3✍1😨1
📌ድምፃዊ ኢሳያስ ታምራት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ
ድምፃዊ ኢሳያስ ታምራት በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ኢትዮፒካሊንክ ዘግቧል።
ፖሊስ ድምጻዊ ኢሳያስን ከነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሲሆን ፤ነሀሴ 07 በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የቀጠሮ ችሎት ቀርቧል ።
ፖሊስ ተጠርጣሪውን በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል እንደጠረጠረውና ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
ፍርድ ቤትም ስምንት የምርመራ ቀናት ፈቅዷል። በዚህ መሰረት ቀጣዩ ችሎት ሀሙስ ነሀሴ 15 ታይቶ ፖሊስ በድጋሜ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲሰጡት ጠይቋል።
የኢሳያስ ጠበቃም ድምፃዊው ከቀናት በኋላ አልበምን እንደሚያወጣ እና ለዚያም ዝግጅት እያደረግ እንደሆነ እንዲሁም በተመሳሳይ ወንጀል የተጠረጠረው ጓደኛው በዋስ መለቀቁን በማስረዳት የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ጠይቋል።
ኢሳያስ በበኩሉ "የተያዝኩት ከፀበል ቦታ ነው ፤ ደካማ እናቴን እና የስድስት ወር ልጄን ጥዬ ነው እዚህ ያለሁት በመሆኑም ዋስትናዬ ተከብሮ በውጪ ሆኜ ጉዳይን ልከታተል" ሲል ጠይቋል።
መርማሪ ፖሊስ ደግሞ ተከሳሹ ያቀረበውን የዋስትና ጥያቄ እንደሚቃወም እና ሌሎች አባሪዎቹን ለመያዝ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ከተለያዩ ተቋማት ለማምጣት እንዲችል ተጨማሪ የምርመራ ቀን እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አድምጦ ለፖሊስ ስምንት ተጨማሪ ቀናትን ፈቅዶ የችሎቱ ሂደት መጠናቀቁ ተነግሯል።

😱9❤4
📌በኢትዮጵያ የቴምር ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል ከነሃሴ 20 እስከ 22 2017 ዓ.ም በአፋር ሰመራ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል።
ፌስቲቫሉ ከዘጠኝ ሃገራት የተውጣጡ የቴምር አምራቾች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎች እና የፈጠራ ባለቤቶች የሚገኙበት ነው።
በፌስቲቫሉም የልምድ ለውውጥ ይደረጋል፣ ዘመናዊ የቴምር አመራረት ዘዴ ይዳሰሳል፣ እንዲሁም የተሻሻሉ የቴምር ዝርያዎች ይተዋወቃሉ።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል ከነሃሴ 20 እስከ 22 2017 ዓ.ም በአፋር ሰመራ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል።
ፌስቲቫሉ ከዘጠኝ ሃገራት የተውጣጡ የቴምር አምራቾች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎች እና የፈጠራ ባለቤቶች የሚገኙበት ነው።
በፌስቲቫሉም የልምድ ለውውጥ ይደረጋል፣ ዘመናዊ የቴምር አመራረት ዘዴ ይዳሰሳል፣ እንዲሁም የተሻሻሉ የቴምር ዝርያዎች ይተዋወቃሉ።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4👏1
ባይራ ዲጂታል መጽሄት ቅጽ 2 ቁጥር 4.pdf
8.9 MB
📌ባይራ ዲጂታል መጽሔት ለንባብ በቅቷል።
ቅጽ 2 ቁጥር 4
በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- bayradigital2016@gmail.com

❤8
📌የአስቻለው "እመት ሸዋ" ቪዲዮ ዛሬ ይለቀቃል
የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ(አርዲ) "እመት ሸዋ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሙዚቃ ቪዲዮው በዛሬው ዕለት በብርቧክስ ሪከርድስ በኩል ይሰራጫል።
አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ከዚህ ቀደም በለቀቃቸው "እናትዋ ጎንደር" እና "ካሲናው ጎጃም" "አሞራው ካሞራው" በተሰኙ ሙዚቃዎች ከፍተኛ ተደማጭነትን አግኝቷል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ(አርዲ) "እመት ሸዋ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሙዚቃ ቪዲዮው በዛሬው ዕለት በብርቧክስ ሪከርድስ በኩል ይሰራጫል።
አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ከዚህ ቀደም በለቀቃቸው "እናትዋ ጎንደር" እና "ካሲናው ጎጃም" "አሞራው ካሞራው" በተሰኙ ሙዚቃዎች ከፍተኛ ተደማጭነትን አግኝቷል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤10👍1
📌ንጉሥ ማልት በምርት ጥራት ተሸለመ
በምርቱ ጣዕም እና ጥራት ተወዳጅነትን ያተረፈው ንጉስ ማልት ለሽልማት በቅቷል።
ሸላሚው ድርጅት በ1961 በብራስልስ፣ ቤልጂየም የተመሰረተው Monde Selection ሲሆን ግንባር ቀደም ራሱን የቻለ የጥራት ግምገማ ተቋም ነው።
በጠንካራ ግምገማዎቹ እና መስፈርቶቹ የሚታወቀው ሞንዴ ሰሌክሽን በየአመቱ ምርቶችን በምግብ፣ መጠጦች፣ መዋቢያዎች እና ሌሎችንም ከ3,000 በላይ የሆኑ የተለያዩ ምርቶች ገምግሞ እንደየ ጥራት ደረጃቸው ሽልማት ይሰጣል።
ይህ ተቋም የነሐስ፣ ሲልቨር፣ ወርቅ እና ግራንድ ወርቅን ጨምሮ የተከበሩ የጥራት መለያዎችን በመሸለም በአለም አቀፍ ደረጃ ይታወቃል።
ከ60 ዓመታት በላይ ባለው እውቀት፣ Monde Selection በተጠቃሚ ምርቶች ጥራት ላይ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያዘጋጃል።
በእዚህ ትልቅ ተቋም ከአልኮል ነፃ መጠጥ የሆነው ንጉስ ማልት የ2025 በምርት ጥራት የወርቅ ተሸላሚ ሆኗል።
ንጉስ ማልት ከሞድን ሰሌክሽ የጥራት ሽልማት ሲያገኝ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።
ባለፈው አመትም የብር ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል። በአገራችን ኢትዮጵያ ከንጉስ ተጨማሪም ሌሎች ምርቶችም እንደየ ጥራት ደረጃቸው እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ይህ ተደጋጋሚ ሽልማት ለንጉስ ማልት እና ለተጠቃሚዎቹ ብቻ ሳይሆን ለአገር የሚያበረክተው እውቅና ቀላል አይደለም።
ንጉስ ደረጃውን አስጠብቆ እንዲቆይ ለሌሎች ምርቶች ደግሞ አርአያ በመሆን በምርት ጥራታቸውን አስጠብቀው ከአመት አመት ለሽልማት እንዲበቁ መነቃቃትን ይፈጥራል ።

❤6👍2
📌ፈንድቃ አዲስ የሚያስገነባውን ህንፃ ይፋ አደረገ
ፈንድቃ ባህል ማዕከል በቀጣይ የሚያስገነባውን ዘመናዊ የባህል ማዕከል ህንፃ ንድፍ ይፋ አድርጓል።
ፈንድቃ የባህል ማዕከል ስራ አስኪያጅ መላኩ በላይ በማህበራዊ ትስስር ገጽ "በካርሎ ራቲ አሶሺያቲ - የሚመራው በዓለም አቀፍ ታዋቂ የሆነው የኢጣሊያ የስነ ሕንፃ ተቋም - ለአዲሱ የፈንድቃ ህንፃ ንድፍ የመጀመሪያውን ምዕራፍ እንዳጠናቀቀ በማካፈሌ በጣም ደስተኛ ነኝ" ብሏል።
ፈንድቃ የባህል ማዕከል በጥቅምት 2017 ዓ.ም ከፈረሰ በኋላ በቦታው የራሱን ህንጻ እንዲሰራ ቦታው ለፈንድቃ መሰጠቱ ይታወሳል።
ከታህሳስ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ፈንድቃ ከሀያት ሬጀንሲ ጋር በመተባበር ኮንሰርቶችንና እና አዝማሪ ፕሮግራሞችን እያቀረ ይገኛል።

❤8👍6👎2👌2
📌የአዲስ ለገሠ "ማስታወሻ" አልበም ተለቀቀ
“ማስታወሻ" የተባለ ስያሜ የያዘው ይህ የመጀመሪያ አልበሙ 14 የሙዚቃ ስራዎች የተካተተበት ነው።
አልበሙ ፍቅር የተቀነቀነበት መዋደድ የነገሠበት አዲስ ለገሠ የራሱን ቀለም እና አቀራረብ ያስተዋወቀበት ስራ ነው ተብሏል።
አልበሙ በርካታ የሙዚቃ ዘይቤዎችን እና ዘውጎችን ያካተተ ሲሆን በሀሳብ፥ በሙዚቃ ቅንብር፥ በድምፅ እና በአዘፋፈን አዲስ ጣዕም ይዞ መቅረብ ችሏል።
በማስታወሻ አልበሙ ላይ ይልማ ገ/አብ፣ ናትናኤል ግርማቸው፣ እሱባለው ይታየው (የየሺ ልጅ)፣ ሞገስ ተካ እና ሌሎች ዕውቅ የዜማና የግጥም ደራሲዎች፣ እንዲሁም እራሱ አዲስ ለገሠ በግጥም እና ዜማ የተሳተፉበት ነው፡፡
በሙዚቃ ቅንብሩም ሚካኤል ሃይሉ፥ ኪሩቤል ተስፋዬ፥ ብሩክ አፈወርቅ እንዲሁም ሌሎችም የተሳተፉብት ሲሆን ማስተሪንጉን ኪሩቤል ተስፋዬ ተጠቦበታል፡፡
የ “ማስታወሻ” አልበም ስራን ጀምሮ ለማጠናቀቅ ሶስት ዓመታትን እንደፈጀ የተነገረ ድምጻዊው ለዚህ የአልበም ሥራው ሲል በርክት ያለ ክፍያ ከሚከፈልበት ከሙዚቃ ክለብ ስራዎች ራሱን ከሁለት ዓመታት እንዳቀበም ተናግሯል።
ድምጻዊ አዲስ ለገሠ "ኮርቼ የሚናገርለት አልበም ነው" ሲሉ የገለጸውን የመጀመሪያ አልበሙን በአዲስ ለገሰ ይፋዊ ዩትዩብ ቻናልና በሁሉም ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች ለቋል።
አዲስ ለገሠ: YouTube:https://youtube.com/@addislegesseofficial?si=k2XXutbiqlcdVMcD

❤20😢1
📌አንዱ መጽሐፍ በ130 ሺህ ብር ተሸጠ
የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኀበር የተቋቋመበትን 27ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “ወባን በእኛ ሐብት፣ በእኛ እውቀትና ጉልበት እናጠፋለን!" በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በስዊስ ኢን ኔክሰስ ሆቴል በድምቀት ተከብሯል።
በዚህ የምስረታ ክብረ በዓል ላይ የማኅበሩን የሃያ ሰባት ዓመታት ታሪክ የሚያሳይ "ፈጥኖ ደራሹ ማኅበር" የተሰኘ መጽሐፍ ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።
በክብረ በዓሉ ላይ ይህ "ፈጥኖ ደራሹ ማኅበር" የተሰኘው መጽሐፍ በ130 ሺህ ብር ተሸጧል። መፅሐፉን ለጨረታ ያቀረበው የፕሮግራሙ መሪ ማናዬ እውነቱ ነው። ጨረታውን ሲሲ አር ዲኤ በ80ሺ ብር ያሸነፈ ሲሆን መፅሐፉን ለመግዛት ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርግ የነበረው ለወገኔ ማይክሮ ፋይናንስ ለጨረታ ያዘጋጀውን 50ሺ ብር ለማህበሩ ገቢ አድርጏል።
"ፈጥኖ ደራሹ ማኅበር" መጽሐፍ በአስር ሁለት ምዕራፎች የተዘጋጀ ሲሆን የመጽሐፉ ዓላማ የማኅበሩን አመሠራረት፣ ያከናወናቸውን ሥራዎች፣ የተገኙ ለውጦችን፣ እየተካሄዱ ያሉ ሥራዎችን፣ መልካም ጎኖችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣ የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎችን ዘርዝሮ በማቅረብ ለቀጣይ ትውልድ ብሎም ለመሰል ድርጅቶች ትምህርት ሆኖ እንዲያገለግል እንደሆነም ተገልጿል።
የጤና፣ልማትና ፀረ-ወባ ማኀበር ነሐሴ 17 ቀን 1990 ዓ.ም ተመሥርቶ ባለፉት 27 ዓመታት ሕብረተሰቡን የሚጠቅሙ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እንዳከናወነ አስታውቋል።
ፎቶ: Tekle Markon

👍8❤5🤣4👎2
📌አርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ ይቅርታ ጠየቀ
አርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን ይቅርታ ጠየቀ። አርቲስት ሸዋፈራው በሰይፉ ሾው ላይ ቀርቦ ይቅርታ መጠየቁን ተመልክተናል። አሁን የማምንበትን መፅሐፍ ቅዱስ የሰጠችኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ናት፣ እኔ ብሽሽቅ ውስጥ አልገባም፣ ወንጌል ብሽሽቅ አይደለም፣ "እዛ ሰፈር" እያልኩ ለነበረው ስብከት ይቅርታ እጠይቃለሁ። ሌላው አለ የተባለውን እኔ አላልኩም ማስረጃ መቅረብ አይቻልም። እዛ ሰፈር ላልኩት ይቅርታ እጠይቃለሁ ብሏል።
©️Fast Mereja

👎29👏11🍌3✍1❤1
📌የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጳጉሜ 4 ይመረቃል !
ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ከ11 ቀናት በኃላ ጳጉሜ 4 2017 ዓ.ም ይመረቃል ተብሏል።
በኬንያ የኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር ደመቀ አጥናፉን ምንጭ አድርጎ ቢቢሲ እንደዘገበው ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም የአፍሪካ መሪዎች እና ሌሎች የተጋበዙ እንግዶች በሚገኙበት ይመረቃል።
ከአምስት ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት በአፍሪካ ግዙፉ እንደሆነ የተነገረለት ሕዳሴ ግድብ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታው ሲካሄድ ቆይቷል።
በአምስት ዓመታት ውስጥ ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ ከአስር ዓመታት በላይ ፈጅቶ የኢትዮጵያ መንግሥት በመጪው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ በይፋ እንደሚመረቅ ማስታወቁ ይታወቃል።

❤15👎1
📌ፈለገ ኪን የኪነጥበብ መድረክ 1ኛ ዓመት
ከኢትዮጵያ ዓይነስውራን ማሕበር ጋር በመተባበር በየወሩ የሚዘጋጀው "ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ መድረክ የፊታችን ቅዳሜ አንደኛ ዓመቱን ያከብራል።
ወጣት ከያኒያንን በማበረታታትና አንጋፋ የኪነጥበብ ሰዎችን በመዘከር ፤ በኪነጥበቡ ዓለም የላቀ አበርክቶ ያላቸውን ሙያተኞችን በክብር እንግድነት ጋብዞ ልምዳቸውን እንዲያጋሩ በማድረግ ለተከታታይ 11 ወራት የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።
"ፈለገ ኪን" አንደኛ ዓመቱን በርካታ የኪነጥበባ ባለሞያዎች በተገኙበት ነሐሴ 24 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አሸናፊ ከበደ የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል ውስጥ ይከበራል።

❤5
📌ጉዞ ወደ ተወዳጁ እና የአለም ምርጥ የቱሪዝም
በሚያምረው ወንጪ ናሂሊ ትመረቃለች ፤ ምርቃት ብቻ ሳይሆን የጀልባ ሽርሽር ፣ ሀይኪንግ እና
የጭቃ ባዝ ከምንከውናቸው ነገሮች ናቸዉ ፤
በጉዞ መፅሀፍ መመረቅ አዲስ ፣ የሚያምር እና የተለየ ልማድ ነው ፤ ናሂሊን በደስታ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ እና እሁድ ( ነሀሴ 24 እና 25 ) እንመርቃት።
Date : August 30 & September 1 2025
Duration : 2 days & 1 night
Departure: Mexico, Wabi Shebelle Hotel
6:00 AM @ 12:00 LT
Price : 8000ETB For Locals
Package includes
ትራንስፖርት / Transport
ቁርስ / Breakfast /X2/
ምሳ / Lunch / X2 /
እራት / barbecue
የታሸገ ውሃ / Bottled Water
የመግቢያ ዋጋ / Entrance
የአስጎብኚ / Local Guide
ዋና / Swimming
የምሽት እሳት ዳር ጨዋታCampfire
የተፈጥሮ ፍል ውሀ / Hot Spring Water & bath
ማደሪያ ድንኳን (Tent)
📷ፎቶግራፍ /🌅 Photograph
For more info call 📞 0919874598

📌ሰውመሆን ይስማው እና ግሩም ኤርሚያስ እንግዳ የሆኑበት ልዩ ዝግጅት በአሜሪካ ኤምባሲ ተዘጋጅ
(መግቢያ በነፃ ነው)
በስድስተኛው የcreative lab ዝግጅታችን ሁለት ተወዳጅ እንግዶችን ይዘንላቹ የመጣን ሲሆን ተወዳጁን ተዋናይ ፣ ደራሲ እና ዳይሬክተር ግሩም ኤርሚያስን እና ሲኒማቶግራፈር እንዲሁም ደራሲ እና ዳይሬክተር የሆነው ሰውመሆን ይስማውን ይዘንላችሁ ቀርበናል።
በዚህ ዝግጅት ላይ ለእናንተ ልምዳቸውን እና የፊልም ተሞክሮዋቸውን የሚያካፍሉበት ዝግጅት ነው ።
እንዲሁም የግሩም ኤርሚያስ የሆነውን ወርቀዘቦ የተሰኘውን ፊልም ለዕይታ በማቅረብ በፊልሙ ላይ የውይይት መርሃግብር ይኖረናል። ሰለሆነም በዚህ መድረክ ላይ እንዲታደሙ ተጋብዘዋል።
ጀማሪ የፊልም እና የቴያርትር ፍላጎት ያላችሁ እና በሙያው ላይ መስራት የምትፈልጉ ይህ የመገናኛና ዕድል ለእናንተ ነው።
📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )
📅 ቀን: ነሃሴ 27 ፣ 2017
🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00
🎟 መግቢያ: ነፃ
አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር
በፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ቴሌግራም ገፃችንን ፎሎ ማድረግ እንዳይረሱ
📎 በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA
ለተጨማሪው:
https://t.me/EventAddis1

❤11👍1🔥1🥰1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
1.የዘጠናዎቹ ተወዳጅ ድምጻዊት ትዕግሥት በቀለ ከ20 ዓመታት በኃላ የሙዚቃ ኮንሰርቷን በኢትዮጵያ ልታቀርብ ነው። ኮንሰርቱ የሚካሄድበት ቀን ታውቋል።ድምጻዊቷም ወደ ኢትዮጵያ መጥታለች።በዝርዝር እንነግራችኋለን።
3.በተጠባቂው የመላው አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) ላይ አራት ሴት ድምጻዊያን ከኢትዮጵያ እጩ ሆነዋል። እጩ የሆኑት ድምጻዊያን እነማን ናቸው?።
3.በአዲስ አበባ ከተማ በስፋቱ እና በያዛቸው የመጻሕፍት ዓይነት ግዙፍ ነው የተባለለት ዘመናዊ የመፅሐፍ መደብር ነገ ይከፈታል።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/mKL83b3hC1I?si=pvxT82muNGPfdbJq
📌መልካም ምሽት

📌 የነዋይ ደበበ ነጠላ ሙዚቃ ተለቀቀ
የአንጋፋው ድምጻዊ ነዋይ ደበበ "የብርሃን ሉል" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ አመሻሹን በሆፕ ኢንተርቴይመንት የዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ቀርቧል።
በዚህ ነጠላ ሙዚቃ ላይ በግጥምና ዜማ ሞገስ ተካ የተሳተፈ ሲሆን የሙዚቃ ቅንብሩን ካሙዙ ካሣ ሰርቶታል።

❤10🔥2