📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://t.me/EventAddis1/6236
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://t.me/EventAddis1/6236
👍8❤4
📌 "እንዳለሁ አበራለሁ" መጽሐፍ ሐሙስ ይመረቃል
በደራሲ ማክዳ አርሺ ተጽፎ፣ በታዋቂው ደራሲና ገጣሚ በውብ አማርኛ በግጥም የተቀናበረው፣ ስለ ኦቲዝም ግንዛቤን የሚያስጨብጠው "እንዳለሁ አበራለሁ" የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን ሐሙስ ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም በስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ግቢ ውስጥ ይመረቃል።
ስለ ኦቲዝም ያለንን ግንዛቤ በጋራ በምናሳድግበት በዚህ ልዩ መድረክ ላይ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

❤3
📌መቅረዝ ሥነኪን ሐሙስ ይካሄዳል
መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ሐሙስ ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ ዝግጅት ላይ አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ የክብር እንግዳ በመሆን የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

❤1🥰1
📌"የወዲያነሽ" መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል
በአንጋፋው ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል የተዘጋጀውና በቅርቡ በድጋሚ የታተመው "የወዲያነሽ"መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) ይመረቃል።
ወዳጆቹና አክባሪዎቹ በሚገኙበት በልዩ መርሐግብር ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
በአንጋፋው ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል የተዘጋጀውና በቅርቡ በድጋሚ የታተመው "የወዲያነሽ"መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) ይመረቃል።
ወዳጆቹና አክባሪዎቹ በሚገኙበት በልዩ መርሐግብር ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍12❤7
📌ደራሲ ደመወዝ ጎሽሜ እንግዳ የሆነበት መሰናዶ!
በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ሳምንት የተመረጠው መጽሐፍ "አዲስቱ እየሩሳሌም" የተሰኘ መጽሐፍ ሲሆን በክብር እንግዳነት የመጽሐፉ ጸሐፊ ደመወዝ ጎሽሜ ይገኛል ተብሏል። የዝግጅቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ሳምንት የተመረጠው መጽሐፍ "አዲስቱ እየሩሳሌም" የተሰኘ መጽሐፍ ሲሆን በክብር እንግዳነት የመጽሐፉ ጸሐፊ ደመወዝ ጎሽሜ ይገኛል ተብሏል። የዝግጅቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍9👏4🙏2❤1
📌አርቲስት ዘሪቱ ከበደ መጽሐፍ ጻፈች
በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ውስጥ በድምጻዊነቷ እንዲሁም በግጥምና ዜማ፣ በትወና ችሎታዋ ከፍተኛ ስምን ያተረፈችውና በኋላም ሙሉ ጊዜዋን ለመንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ወደ ዝማሬ ዓለም የገባችው አርቲስት ዘሪቱ ከበደ "ከልጅነት እስከ ልጁነት" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ ጽፋለች።
በግል ታሪኳ ላይ የሚያጠነጥነው ይህ መጽሐፏ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚቀርብ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአርቲስቷ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1

❤37👏7🔥4👎2
📌ጋዜጠኞቹ ደመወዝ እየተከፈላቸው አይደለም ተባለ
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ሠራተኞች ደመወዝ እየተከፈላቸው አለመሆኑንና መቸገራቸውን ተናገሩ።
በቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይተዳደር የነበረው ‹‹የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት››፣ ክልሉ ለአራት ከተከፋፈለ በኋላ፣ እያንዳንዳቸው ክልሎች የሚጠበቅባቸውን በጀት ባለመስጠታቸው፣ ቀናቶች ካለፉ በኋላ ይከፈላቸው የነበረው ደመወዝ ሙሉ በሙሉ መቆሙንና እየተቸገሩ መሆናቸውን የድርጅቱ ሠራተኞች ተናገሩ፡፡
ሪፖርተር ጋዜጣ ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የጣቢያው ሠራተኞች፣ ላለፉት ስድስት ወራት ደመወዛቸው በጊዜው እንደማይከፈላቸውና ወሩ ባለፈ በ15ኛው ቀን ይከፈላቸው የነበረ ቢሆንም፣ የሰኔ ወር ደመወዝም ግን ሙሉ በሙሉ እንዳልተከፈላቸው ተናግረዋል፡፡
ከ400 በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ፣ አብዛኞቹ ሠራተኞች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ በመሆናቸው፣ በተለይም ከቤተሰቦቻቸው ርቀው የሚኖሩ በደመወዝ መዘግየት ምክንያት ከፍተኛ ጫና ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡
‹‹የድርጅቱ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል›› የሚሉት ሠራተኞቹ፣ ለዚህም ወደ ሌሎች የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች እየሄዱ መሆኑን በማሳያነት ይጠቅሳሉ፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የድርጅቱ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚና የተቋሙ ተወካይ አቶ ዘለዓለም ገነሞ፣‹‹ድርጅቱ ችግር ውስጥም ሆኖ ቢዘገይም ሳይከፍል የቀረበት ጊዜ የለም››ሲሉ ተናግረዋል።
©️ሪፖርተር ጋዜጣ

❤7😢2
📌በርካቶች የተቀባበሉት ነጠላ ሙዚቃ
በድምጻዊት ሳምራት አዘነ የተቀነቀነው "አያ ጥራኝማ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ነሐሴ 2 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ከተለቀቀ በኃላ ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በርካቶች እየተቀባበሉ ስለ ሙዚቃው እየጻፉ ይገኛሉ።
"አያ ጥራኝማ" ሙዚቃ ላይ በዜማ ይልቃል አስፋው፣ በግጥም እስጢፋኖስ መስፍን እንዲሁም በቅንብር ታምሩ አማረ ተሳትፈውበታል።
የሙዚቃ ቪዲዮውን ዮናስ ይታየው ዳይሬክት ያደረገው ሲሆን በዋሽንት ጣሰው ወንድም ተሳትፏል።
ድምጻዊት ሳምራዊት አዘነ የሙዚቃ ባለሞያ ስትሆን የኢትዮጵያን አይዶል ዳኛ እና የመረዋ ኳየር የሙዚቃ ቡድን አባል ነች።

❤9👍3
📌አንጀሊና ጆሊ የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታልን ጎበኙ
ዝነኛዋ አሜሪካዊት ተዋናይት ፣ የፊልም ባለሙያ እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ የሆኑት አንጀሊና ጆሊ በዛሬው ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።
ተዋናይቷ ያደረጉት ጉብኝት በዋነኝነት ሆስፒታሉ እየሰጠ በሚገኘው መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ፣ የሚታዩ ለውጦችን እንዲሁም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎች መለየት ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።
በጉብኝቱ ላይ አንጀሊና የሆስፒታሉን የቲቢና መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና አገልግሎት መስጫ ዋርድ ፣ ላብራቶሪ እንዲሁም ታካሚዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
አንጀሊና ወደ ሆስፒታሉ ከረጅም ጊዜያት በፊት መጥተው እንደነበር ያስታወሱ ሲሆን በአሁኑ ጉብኝታቸው ላይ ሆስፒታሉ ዘርፈ ብዙ ለውጦች አምጥቶ በመመልከታቸው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አክለውም ሆስፒታሉ ድጋፍ ቢደረግለት በቀጣይ የተሻለ
አገልግሎት ለታካሚዎች መስጠት በሚያስችለው አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዳለ በጉብኝቱ ላይ መገንዘባቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪም በሆስፒታሉ በቲቢ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተገኘው እድገት በእጅጉ የሚደነቅ እና የሚያስተማምን ስለሆነ በቀጣይ በጂ.ኤች.ሲ (Global Health Committee (GHC)) በኩል ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም እሸቱ በበኩላቸው ቲቢን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተዋናይቱ ላሳዩት ዘላቂ ቁርጠኝነት ፣ ልግስና እና በቀጣይ ለሚያደርጉት ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
Via ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል

❤19🤣8🥰1
📌‘ኢመርጅ’ የሥነጥበብ አውደርዕይ ተከፈተ
አስር ሁለት ሠዓሊያ እና የፊልም ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን ያቀረቡበት "ኢመርጅ" ዘመናዊ የሥነጥበብ አውደርዕይ ነሐሴ 7 2017 ዓ.ም በገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ የሥነጥበብ ሙዚየም ውስጥ በይፋ ተከፍቷል።
ይህ ‘ኢመርጅ’ ዘመናዊ የሥነጥበብ አውደርዕይ ለሁለት ዓመት በድህረ ምረቃ መርሀግብር፥ ከአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት በሥነጥበብ እና በፊልም ጥበብ ዘርፍ ትምህርታቸውን ተከታትለው በሰኔ 2017 ዓ.ም ያጠናቀቁ ተማሪዎች መካከል የተመረጡ ስድስት ሠዓሊያንን እና ስድስት የፊልም ባለሙያዎችን የመመረቂያ ጥናታዊ የሥራ ውጤት ለሰፊው ህዝብ ለማሳየት በዘመናዊ የሥነጥበብ ሙዚየም - ገብረክርስቶስ ደስታ ማዕከል የተዘጋጀ ዐውደርዕይ ነው።
በዚህ ዐውደርእይ ላይ የቀረቡት ስራዎች ስለ: ማህበራዊ፣ ልማታዊ ለውጥና ተጽእኖው፣ ሥነጥበባዊ የአእምሮ ህክምና፣ ሶሻል ሚዲያና ተጽእኖው እንዲሁም ከሀገር እስከ ዓለም አቀፍ እየደረሰ ስላለው የተሳሰረ ኢፍትሀዊ ብዝሀ ችግሮች ዙሪያ የሚዳስሱ ርዕሰ ጉዳዮች በዘመናዊ የሥነጥበብ አውድ ቀርበዋል።
ተሳታፊ ሠዓሊዎች፦
አለማየሁ ዳርሰማ፣ ማስተዋል ጌታ፣ ሙሉአዳም አዳነ፣ ሰሎሜ ጌታቸው፣ ቴዎድሮስ ክፍሌ፣ ዮናስ ፍቃዱ
ተሳታፊ የፊልም ባለሙያዎች፦
አቢይ ጌታሁን፣ አብርሐም ባህሩ፣ ኤልሻዳይ ይልማ፣ ጌታሁን ግርማ፣ ሊዲያ ምትኩ፣ ታደሰ በቀለ
የማዕከሉ የእይታ ሰዓት፡ ከማክሰኞ - እሁድ ከጠዋት 4:00 ሰዓት - አመሻሽ 11:00 ሰዓት
ቦታ፡ 6 ኪሎ ምስካየ ሓዙናን መድሃኒያለም ገዳም ከፍተኛ ትምህርት ቤት ጎን በሚገኘው የንግድና ኢኮኖሚ ኮሌጅ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ጊቢ ውስጥ።

❤4
📌ግራንድ ጮሮርሳ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው
ግራንድ ጮሮርሳ ኮንሰርት የፊታችን ነሐሴ 17 2017 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል እንደሚካሄድ የፕሮግራሙ አዘጋጅ Nethor events አስታውቋል።
በግራንድ ጮሮርሳ ኮንሰርት ታዋቂዎቹ ድምጻዊያን ሄለን በርሄ ፣ዮሳን ጌታሁን፣ሌንጮ ገመቹ፣ጌታቸው ኃይለማርያም፣አኒስ ጋቢ - ጆርጂ አቡ እና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎቻቸው ያቀርባሉ ተብሏል።
በዝግጅቱ ላይ በአፍሪካ ረጅሙ የጮርሮሳ ምግብ በአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ይመዘገባል ተብሏል።
የመግቢያ ክፍያ ቪአይፒ: 10,000 ቪቪአይፒ: 15,000 ብር ነው ተብሏል።
የኮንሰርቱ አዘጋጆች Nethor events እና Kenakon events ሲሆኑ "ይምጡ ባህሎቻችንን ይደግፉ እና ይደሰቱ" ብለዋል።

❤5
📌የልጆች መጻሕፍት ላይ ውይይት ይካሄዳል
በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል የልጆች መጻሕፍት በኢትዮጵያ በተሰኘ ርዕስ የልምምድ ልውውጥና ሙያዊ ውይይት ይካሄዳል፡፡
ሙያዊ ውይይቱ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 10 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ይካሄዳል።
የዕለቱ ተጋባዥ ከ120 በላይ መጻሕፍትን ለሕትመት ያበቃው የልጆች መጽሐፍ ደራሲ፣ ተርጓሚና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ መምህር ዓለም እሸቱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ኑሮውን በሀገረ አሜሪካ አድርጓል፡፡
በዕለቱ የሥነ ጥበባት ማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ጌትነት በኢትዮጵያ የልጆች መጻሕፍት ታሪክና ተግዳሮት ዙሪያ የመነሻ ጽሑፍ ያቀርባሉ፡፡
ይህ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ትብብር በኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር አማካኝነት የሚሰናዳው የክረምት ወራት የሥነ ጽሑፍ ሥልጠና አንዱ አካል ሲሆን በዕለቱ በዘርፉ የተሰማሩ የልጆች መጽሐፍ ደራሲያንና ባለሙያዎችና ይሳተፋሉ፡፡

📌 የአንጋፋው ደራሲ ሳህለ ሥላሴ ብርሃነማርያም ልደት በልዩ ዝግጅት ዛሬ ይከበራል
ጥበበ መድሎት የጋዜጠኝነትና የኪነ ጥበብ ሰልጣኞች አንጋፋ የኢትዮጵያ የስነ ጽሁፍ ባለውለታዎችን ለመዘከር ቀጠሮ ይዟል።
የ''መከረኞቹ'' ፣ ''ያገር ልጅ'' እና ''ባሻ ቅጣውን የመሰሉ ዘመን ተሻጋሪ የስነ ጽሑፍ ስራዎችን ያጋሩንን ጋሽ ሳሕለሥላሴን እናከብራቸው ዘንድ እንድታጅቡን በክብር ጋበዝናችሁ።
📖 ደራሲና አርታኢ ሀይለመለኮት መዋዕል
📖 ጋዜጠኛ ግርማ ፍሰሃን
📖 ደራሲና ተርጓሚ ሳህለስላሴ ብርሃነማርያም
📖 ገጣሚት ባንቻየሁ አሰፋ
⏰ ሰዓት :አርብ ነሐሴ 9 ከቀኑ - 10:30 ጀምሮ
📍 አድራሻ ካሳንችስ ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል
መግቢያ በነፃ

❤11🥰3👎1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
1.የአንጋፋው ሙዚቀኛ መላቱ አስታጥቄ አዲስ የሙዚቃ አልበም የሚለቀቅበት ቀን ይፋ ሆነ።
2."ቴአትር በየቤታችሁ ሊገባ ነው" ተብሏል።የአፍሪካን ሬነሳንስ ቴሌቪዥን "Arts Pluse" የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ ሊያደረግ ነው ።አዲሱ መተግበሪያ ምን ምን ጉዳዮች ይዟል እንነግራችኋለን።
3.መስከረም አበራ እና ቸርነት ፍቃዱ የተጣምሩበት አዲስ ሀገርኛ ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/9hJNQhiM_ow?si=Bt_BmTaEvpCymvlY
📌መልካም ምሽት

👍5❤3
"ቀለም" ዲጂታል መጽሔት ዛሬ ለንባብ ይበቃል
የቀለም ዲጂታል መጽሔት አዘጋጆች "የወር ሰው ይበለን! ተባብለን በተለያየን በ30 ቀናችን ይሄው በዛሬው ዕለት ቅፅ 1/ ዕትም 2 ነሐሴ 10 አመሻሽ 12:00 ላይ ለንባብ ይበቃል" ብለዋል።
የቀለም መጽሔት ቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ይሁኑ።
https://t.me/kelemofficial

🔥3❤1
📌 "ፓሌሮዳ" አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ
የሕክምና ባለሙያ በሆነው ዶ/ር ደሳለው ካሳሁን የተፃፈውና በስነጹሑፋ ባለሙያዎች የተመሰከረለት እንዲሁም በኢትዮጵያ ስነጽሑፍ በአዲስ አቀራረብ የተጻፈ መፅሐፍ ነዉ የተባለለት “ፓሌሮዳ” ኢትዮጽያ ለምን ? የተሰኘዉ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቅቷል።
“ ፓሌሮዳ “ መጽሐፍ መጽሐፈ ሄኖክን፣ ሜታፊዚክስን፣ የህክምና አብዮትን፣ ጂኦፖለቲካንና ሀገራዊ አብርሆትን አንድ ላይ አሰናስሎ፣ ያቀረበ መጽሐፍ ሲሆን ሀገራዊ ብሎም አለመአቀፋዊ ፋይዳ ያላቸውን ሀሳቦች የያዘ መጽሐፍ ነው።
በ “ ፓሌሮዳ “ በገሃዱ አለም ተጨባጭ ሁነቶች ላይ ተመስርቶ፣ በተለያየ መነሻ የተሰባሰቡ ምሁራን የመጽሐፈ ሄኖክን መፍቻ አትላሶችን ፍለጋ አብርሆት በተሰኘ ህቡዕ ማህበር ስር ታቅፈው ከኢትዮጵያ ገዳማት እስከ የአውሮፓ የምድር ውስጥ ቤተመጻሕፍት ድረስ የሚያደርጉትን እልህ አስጨራሽ ጉዞ የሚያሳይ ሳይንሳዊ፣ መንፈሳዊ፣ ፍልስፍና ቀመስ እንዲሁም ጂኦፖለቲካዊ ልቦለድ ነው።
መፅሐፉን በ ሀሁ መጻህፍት መደብር እና በሁሉም የመፅሐፍ መደብሮች ያገኙታል ሲል ይትባረክ ዋለልኝ ነግሮናል።

📌የዘቢብ መልኬ አዲስ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው
የደራሲ ዘቢብ መልኬ "ፉካ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ የፊታችን ረቡዕ ነሐሴ 14 2017 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት አዳራሽ ውስጥ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይመረቃል።
"ፉካ" የደራሲ ዘቢብ መልኬ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ መጽሐፍ ነው።
ደራሲዋ ከዚህ ቀደም “ስብጥር “ግጥም እና የወግ ስብስብ መፅሐፍ፣ “ኮላዥ “ የአጭር ልቦለዶች ስብስብ መጻሕፍትን ለንባብ ማብቃቷ ይታወቃል።

📌ሁለቱም ጋዜጠኞች የገቡበት አልታወቀም
አንጋፋው ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ከቀናት በፊት በደኅንነት አካላት ተይዘው መወሰዳቸው እና እስካሁንም የደረሱበት እንደማይታወቅ እና ፍርድ ቤትም እንዳልቀረቡ ተሰማ።
ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ ሰኞ ነሐሴ 5/2017 ቀን ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍኖ መወሰዱ የታወቀ ሲሆን ከቆይታ በኋላ ግን በመንግስት የደኅንነት ኃይሎች እንደተያዘ ታውቋል፡፡
በተመሳሳይም የሪፖርተር ጋዜጣ ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ዮናስ አማረም ሐሙስ ነሐሴ 8/2017 ከቢሮ እንደወጣ በመንግስት የደኅንነት ኃይሎች ተይዞ መወሰዱ ተነግሯል።
ምንም እንኳን ጋዜጠኞች በመንግስት የደኅንነት አካላት ተይዘው ቢወሰዱም ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ድረስ ያሉበት ስፍራ እንደማይታወቅ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ቤተሰቦቻቸውም በጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ደግሞ የአብዱልሰመድ ባለቤት ልጇን ከተገላገለች ጥቂት ቀናት በመሆኑ በአራስ አቅም በየፖሊስ ጣቢያው ለመዞር እንደተገደደች ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ በሪፖርተር ጋዜጣ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ዘገባዎችን እንዲሁም ቃለ ምልልሶችን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን ጋዜጠኛ አብዱልሰመድም በአሐዱ ራዲዮ ቀዳሜ ገበያ የተሰኘ ፕሮግራም በማዘጋጀት ለአድማጭ ሲደርስ ቆይቷል፡፡
ጋዜጠኞች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለዘፈቀደ እስር፣ ገድያ እና እንገልት መዳረጋቸው የተለመደ ጉዳይ መሆኑ በርካታ ዓለም አቀፍ ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡
©️መረጃው የሆርን ፍሪኩዌንሲ ነው።

😢12❤10😱3🤬3
📌“በሆቴሎች ውስጥ የሚደረግ ስብሰባ አይኖርም"
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በሚቀጥለው በጀት ዓመት ሁሉም ክፍለከተማዎች እና ተጠሪ ተቋማት “የሆቴል አገልግሎት ግዢ” እንዳይፈጽሙ አሳስቧል። ቢሮ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው የተመደበው በጀት “የታለመለትን ዓላማ ለማሳካት እንዲችል” መሆኑን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 350 ቢሊዮን ብር ማፅደቁ ይታወሳል። ከዚህ በጀት ወስጥ 70 በመቶ የሚሆነው ለካፒታል ሥራዎች የተመደበ ነው። ቀሪው ደግሞ ለመደበኛ ሥራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው። ከተማዋ በዚህ በጀቷ “ውጤታማ የሆኑ ሥራዎችን በቁጠባ ለማከናወን” እና “የታለመለትን ዓላማ ለማሳካት” እንድትችል ተጠሪ ተቋማት እና ክፍለ ከተማዎች በሆቴሎች ውስጥ የሚደረጉትን “ስብሰባዎች” እና “ሥልጠናዎች በመንግሥት መሰብሰቢያ አዳራሽ ብቻ” እንዲያከናውኑ በደብዳቤ ተገልጾላቸዋል።
በከተማዋ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ተፈርሞ ለተቋማቱ የተላከው ደብዳቤ “ለልዩ ልዩ ስብሰባዎች፣ ሥልጠናዎችና ግምገማዎች የሆቴል ግዢ አገልግሎት መፈጸም እንደማይችሉ” ይገልጻል። ተቋማቱ ስብሰባ እና ሥልጠና ማካሔድ ካለባቸው በራሳቸው የመሰብሰቢያ አዳራሽ መሆን እንደሚገባው ቢሮ አስታውቋል። ለዚህ እንዲያገለግል “የመንግሥት መሰብሰቢያ አዳራሾችና ካፍቴሪያዎችን በማጠናከር መገልገል” እንዳለባቸው አሳስቧል።
©️ኢትዮ ቲዩብ

❤6👍3👏2
📌የደበበ እሸቱ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ይፈፀማል
የአርቲስት ደበበ እሸቱ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
የአርቲስት ደበበ እሸቱ ሥርዓተ ቀብር በተመለከተ በብሔራዊ ቴአትር የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ መግለጫ ሰጥቷል።
አርቲስት ደበበ እሸቱ /ጋሽ ደቤ/ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ታሪክ ታላቅ ዐሻራ ያኖረ አርቲስት እንደነበር ተገልጿል።
የአርቲስት ስርዓተ ቀብር ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል።
ከዚያ በፊት አምስት ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የክብር ሽኝት እንደሚደረግለትም ታውቋል።

❤7😭5🖕2
📌ስፑትኒክ በኢትዮጵያ የሬዲዮ ሥርጭት ጀመረ
የስፑትኒክ አፍሪካ ፕሮግራም በአዲስ አበባና አካባቢዋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማሕበረሰብ ሬዲዮ 99.4 ኤፍ ኤም ለአድማጮች መቅረብ ጀምሯል።
ስፑትኒክ በሀገሪቱ አንጋፋ በሆነው ዩኒቨርሲቲ የሬዲዮ ጣቢያ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተዘጋጁ የትንታኔ ፕሮግራሞችን ለ6 ሚሊየን አድማጮች ማቅረብ መጀመሩ ተመላክቷል፡፡
ስፑትኒክ ዓለም አቀፍ የዜና ወኪል እና የሬዲዮ ማሰራጫ በ36 ቋንቋዎች ፕሮግራሞቹን የሚያቀርብ ሲሆን÷ በዓለም ዙሪያ 15 የይዘት ማዕከላት አሉት፡፡
በአማርኛ ቋንቋ የሚሠራ ብቸኛው የሩሲያ ሚዲያ የሆነው ስፑትኒክ ዘርፈ ብዙ የይዘት ማዕከሉን በፈረንጆቹ 2025 በአዲስ አበባ ከፍቷል፡፡
በተጨማሪም በ7 የአፍሪካ ሀገራት ማለትም በናይጄሪያ፣ ጊኒ፣ ዛምቢያ፣ ካሜሩን፣ ማሊ፣ ኒጀር እና ቦትስዋና ፕሮግራሞቹን እያስተላለፈ ይገኛል፡፡
በአፍሪካ ባሕል ዙሪያ በሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞቹ በምርጥ የሬዲዮ መጽሄት እና በምርጥ የሬዲዮ ፕሮግራም ምድቦች የሕብረቱን ሽልማት አግኝቷል፡፡
ስፑትኒክ አፍሪካ የአፍሪካ ብሮድካስቲንግ ሕብረት አባል እና ተሸላሚ እንዲሁም ሰሜናዊ አፍሪካን በሚሸፍነው የዓረብ ብሮድካስቲንግ ሕብረት አባል ነው ሲል FMC ዘግቧል።

❤15👎2👏2🥰1