Event Addis Media
9.63K subscribers
6.08K photos
12 videos
4 files
4.7K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌"ሰተቴ" ተከታታይ ድራማ ለእይታ ሊበቃ ነው

በመንገደኛው ባለቅኔ ከድር ሰተቴ ላይ መሠረቱን ያደረገ "ሰተቴ" የተሰኘ አዲስ ተከታታይ አስቂኝ ድራማ በአርትስ ቴሌቪዥን ከሐምሌ 20 ጀምሮ ለተመልካቾች መቅረብ እንደሚጀመር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

"ሰተቴ" ተከታታይ አስቂኝ ድራማ ከፍተኛ በጀት ወጥቶበት በከፍተኛ ጥራት የተዘጋጀ ሥራ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በተስፋዬ አየለ (ዶ/ር) ‘መንገደኛው ባለ ቅኔ ከድር ሰተቴ’ በተሰኘ መፅሐፍና በጦቢያ ግጥምን በጃዝ ሲቀርብ በነበረው የአንድ ሰው ቴአትር ላይ ተመርኩዞ በአንተነህ ኃይሌ ዳይሬክተርነት ተመርቶ የሀገራችንን ወጣትና አንጋፋ ተዋናዮችን በማሳተፍ የተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
11🔥2👍1😁1
📌“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ በድጋሚ ለንባብ በቃ

የኤልያስ መልካ ሕይወትና ሥራዎችን የሚተርከው “የከተማው መናኝ” መጽሐፍ በአንባቢያን ጥያቄ መሰረት በድጋሚ ታትሞ ለአንባቢያን ቀረበ።

“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ  ጃፋርን መጻሕፍት ቤትን ጨምሮ በሁሉም የመጻሕፍት መደብሮች ለአንባብያን ቀርቧል::

በደራሲና ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው (ማዕረግ) የተዘጋጀው መጽሐፉ ለንባብ ከበቃበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡

“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ የተናፋቂውን ኤልያስ መልካ አነጋጋሪ የግል ፍልስፍና እና የሕይወት ውጣ ውረድ የሚተርክ ሲሆን መጽሐፉ በወጣበት ዓመትም በኢ-ልብወለድ ዘርፍ ከዓመቱ አምስት ምርጥ መጽሐፍት አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡

ይነገር ጌታቸው (ማዕረግ) በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ላይ ምርምርን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን በ2015 ዓ.ም ሙዚቃ፣ታሪክና ፖለቲካ ላይ ያተኮረውን “ጠመንጃና ሙዚቃ” የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባብያን አድርሷል፡፡

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
9🔥3👍1
📌ሚሊኒየም አዳራሽ ፈርሶ በድጋሚ ሊገነባ ነው

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኘው እና በተለምዶ ሚሊኒየም አዳራሽ በመባል የሚታወቀው አዲስ ፓርክ እና ማኔጅመንት ከታህሳስ 2018 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ፈርሶ በአዲስ መልኩ እንደሚገነባ ተገለጸ።

በ2000 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት የጀመረው ይህ ግዙፍ አዳራሽ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ታላላቅ አዳራሾች ግንባር ቀደሙ ነው።

አዲሱ ግንባታ የአዳራሹን አቅም እና ዘመናዊነት ይበልጥ እንደሚያሳድግ ሲጠበቅ፣ ለግንባታው የሚወጣው ኢንቨስትመንት መጠን እና የስራ ተቋራጩ ማንነት በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል።

ሚሊኒየም አዳራሽ በ20 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ እስከ 25,000 ሰዎችን የማስተናገድ አቅም አለው።

ይህ አዳራሽ ከትልልቅ ብሔራዊ ፕሮግራሞች፣ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች፣ ኤግዚቢሽኖች፣ ኃይማኖታዊ ፕሮግራሞች፣ የምርቃት ስነስርዓቶች በተጨማሪ፣ ታላላቅ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ለሽኝት ስነስርዓቶች ጭምር ሚናውን ሲጫወት መቆየቱ ከካፒታል መግለጫው ተመልክቷል።

በሰኔ ወር 2017 ምሽት ላይ፣ ሚሊኒየም አዳራሽ የተለመደውን አገልግሎት እየሰጠ በነበረበት ወቅት ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንደገጠመው ታውቋል። የዚህ ችግር ምንጭ ለጊዜው በሚመለከተው አካል እየተጣራ በመሆኑ፣ ጊዜው ሲደርስ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከ 17 ዓመታት በኃላ አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ፈርሶ በአዲስ መልኩ መገንባት ለወደፊቱ ለተለያዩ ዝግጅቶች የተሻለ እና ዘመናዊ የመስተንግዶ አማራጭ እንደሚሰጥ ይጠበቃል ተብሏል።

Via ካፒታል ጋዜጣ

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
14👍1👏1
📌የዘሪቱ ከበደ የመዝሙር ዝግጅት ሊካሄድ ነው

በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ በድምጻዊነቷና በግጥም ችሎታዋ ከፍተኛ ስምን ያተረፈችውና በኋላም ሙሉ ጊዜዋን ለመንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ወደ ዝማሬ ዓለም የገባችው ዘሪቱ ከበደ፣ “ማጽናናትህ” በሚል ርዕስ አዲስ የመዝሙርና የምስክርነት ዝግጅት ማዘጋጀቷን አስታውቃለች።

ይህ ዝግጅት፣ አርቲስቷ በህይወቷ ካሳለፈቻቸው ከባድ ውጣ ውረዶች እና ከደረሰባት ጥልቅ ሐዘን በመነሳት፣ እግዚአብሔር እንዴት እንዳጽናናት የምትመሰክርበት ልዩ መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ዘሪቱ ከበደ በሙዚቃው ዓለም በከፍተኛ ዝና ላይ በነበረችበት ወቅት ከገጠማት የህይወት ለውጥ አንስቶ፣ በተለይም በቅርብ ዓመታት ውስጥ ህጻን ልጇን በሞት በማጣቷ ምክንያት የደረሰባትን ከባድ ሐዘን በይፋ መናገሯ ይታወሳል። የ"ማጽናናትህ" ዝግጅት ርዕስም በቀጥታ ከዚሁ የግል የህይወት ምዕራፍ ጋር የተያያዘ ነው።

ይህ የምስክርነት ምሽት ዘሪቱ ከደረሰባት ከባድ የሐዘን ስሜትና የህይወት ፈተና ውስጥ ያለፈችበትን መንገድ እና ያገኘችውን መንፈሳዊ መጽናናት ለሌሎች የምታካፍልበት መድረክ ይሆናል። ዝግጅቱ፣ የግል ስቃይን ወደ ህዝባዊ የተስፋ መልዕክት የመቀየር ጥልቅ መንፈሳዊ አንድምታ ያለው ሲሆን፣ በህይወታቸው ተመሳሳይ ፈተና ላለፈባቸው ብዙዎች መጽናናትንና መነቃቃትን ይሰጣል ተብሎ ይታመናል።

የዝግጅቱ ዝርዝር:

የዝግጅቱ ስም፦ ማጽናናትህ (የመዝሙርና የምስክርነት ምሽት)

ቀን፦ ነሐሴ 10, 2017 ዓ.ም. | August 16, 2025

ቦታ፦Beza International Church

©️ዘ-ሐበሻ

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
9👎5👍2🙏1
📌ነፃ የሞዴሊንግ እስኮላርሺፕ ዕድል

ሞዴል መሆን ይፈልጋሉ ?

ፕሪስቴጅ አዲስ ከሌጋሲ ሞዴሊንግ ኤጀንሲ ጋር በጋራ በመሆን ነፃ የሞዴሊንግ ስልጠና ለእናንተ ይዞላችሁ መጥቷል።

የዚህ እድል ተካፋይ መሆን የምትፈልጉ ከታች ያለውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባችኋል።

የፕሪስቴጅ አዲስ እና ሌጋሲ ሞዴሊንግ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ቻናል ፎሎ ያድርጉ ።

ይሄንን ፖስት የተደረገውን ሼር በማድረግ ኢንስታግራም ስቶሪ ላይ ያጋሩ ፣ ሁለቱንም ቻናሎች ታግ ያድርጉ ።

ኮሜንት ላይ ፍላጎት ያላቸውን ሶስት ሰዎችን ታግ ያድርጉ።

በኮሜንት ሃሳብ መስጫ ላይ ሌጋሲ ሞዴሊንግ መማር ለምን እንደምትፈልጉ እና ይሄንን እድል ላንቺ / ላንተ ለምን እድሉ መሰጠት እንዳለበት ግለፅ/ጪ ።

ይሄ እድል ከ 16 ዓመት እስከ 30 ዓመት ለሆኑት ክፍት ነው።

ምንም አይነት የሞዴሊንግ ልምድ አይጠይቅም - ለጀማሪዎች ክፍት ነው ።

#ፕሪስቴጅአዲስ እና #ሌጋሲሞዴኒንግ ሃሽታጎችን ይጠቀሙ ።

የዚህ እድል ተካፋይ ለመሆን የ @prestigeaddis ኢንስታግራም ገፅ ላይ በመግባት ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት በማሟላት መሳተፍ ይችላሉ።

መልካም ዕድል

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
1
📌ገጣሚና ሠዓሊ ከበደች ተክለአብ ልምዷን ታጋራለች

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል ገጣሚና ሠዓሊ ከበደች ተክለአብ በሥራዎቿና በሕይወቷ ዙሪያ ልምዷን ታጋራለች፡፡

በዕለቱ ስለገጣሚነቷ፣ ስለሠዓሊነቷ፣ በሶማሊያ ሐዋይ የ10 ዓመታት የእስር ቤት ቆይታዋ፣ በሀዋርድ ዩኒቨርስቲ በተማሪነትም በመምህርነትም ስላሳለፈቻቸው ዓመታት ታወጋናለች፡፡

ዝግጅቱ የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 19፣ 2017 ከ8 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይቀርባል፡፡

ይህ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ትብብር በኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር አማካኝነት የሚሰናዳው የክረምት ወራት የሥነ ጽሑፍ ሥልጠና አንዱ አካል ነው፡፡

የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል በዝግጅቱ እንዲታደሙ ግበዣውን ያቀርባል፡፡

የዝግጅቱ ቦታ:- በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ (በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ)፡፡ https://maps.app.goo.gl/yb1LFT7PDTwLUP217

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
12👍4🤔1
📌“አፄ ዘርዐ ያዕቆብ እና ሥራዎቹ” መጽሐፍ ተመረቀ

በዶ/ር አንዱአለም አባተ (የአጸደ ልጅ) እና በኢንጅነር ቴዎድሮስ ደመቀ የተጻፈ “አፄ ዘርዐ ያዕቆብ እና ሥራዎቹ” የተሰኘ መጽሐፍ ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል፡፡

በመርሀ- ግብሩ ላይ ገጣሚና አዘጋጅ ጌትነት እንየው  እና በዶ/ር ገዛኸኝ ጸጋው ከመጽሐፉ ውስጥ የተወሰኑ ቅንጭብ ታሪኮች ተነበዋል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማኀበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብእ ኮሌጅ ምክትል ዲን በዶ/ር ሲሳይ ሳህሌ አማካኝነት መጽሐፉን የሚዳስስ ጥልቅ ሀሳብ የያዘ ጽሑፍ ቀርቧል።

መጽሐፉ የመካከለኛውን ዘመን ታላቅ ንጉስ የአፄ ዘርዐ ያዕቆብን የሕይወት ታሪክና ሥራዎች የሚያስዳስስ ሲሆን 19 ምዕራፎች እና 542 ገጾች አሉት።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
6👍2
📌የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ ተመረቀ

የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ በሀገራችን የሙሉ ጊዜ የልጆች የቴሌቪዠን ቻናል በመጀመር ፈርቀዳጅ የሆነና በተለይም በልጆችና ቤተሰቦቻቸው ዘንድ ሠፊ ተቀባይነት በማግኘት በአወንታዊ የትውልድ ግንባታ ላይ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው ይህንን መተግበርያ ይፋ ያደረገው።

ተቋሙ አላማና ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማስፋት በማሰብ መተግበርያውን ማበልጸጉን ይፋ አድርጓል።

በባለፉት አስርት አመታት በልጆች ዙርያ የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ የቆየው ተቋሙ በባለፉት ሰባት አመታት ደግሞ በኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን የልጆች ፕሮግራሞችን በማቅረብ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን ያስመረቀው ይህ መተግበርያ በውስጡ 10 የሚሆኑ ይዘቶችን ማካተቱን ነው የተገለጸው።

መተግበርያው ያበለጸገው መሁቡብ ቴክኖሎጂስ መተግበርያው ለልጆች አመቺ የሆነና አጠቃቀም ተብሎ ቀለል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን ስራ አስኪያጅ ህብስት አሰፋ እንደተናገሩት በተመደቡበት የስራ ዘርፍ ተሰልፈው ከመጋረጃ ጀርባ ያሉ የተቋሙ ሰራተኞች እና ባለሙያዎች ምስጋና ይግባና ዛሬ ለዚህ በቅተናል ብለዋል።

ተቋማችን እዚህ ለመድረሱ ሚስጥር የልጆቻችን ወላጆች ናቸው ያሉት ስራ አስኪያጇ ስላደረጋችሁት ሁሉ ነገር እናመሰግናለን ብለዋል።

©️ድሬቲዩብ

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
👍4
📌ከአንድ መቶ በላይ ተዋንያን የሚሳተፉበት "ንጉሥ አርማህ" ተውኔት ነገ ለመድረክ ይበቃል

በደራሲ መልካሙ ዘሪሁን ተጽፎ በተሻለ አሰፋ (ዶ/ር) የተዘጋጀውና መሠረት ሕይወት ረዳት አዘጋጅ የሆነችበት "ንጉሥ አርማህ" ተውኔት ከበርካታ ዓመታት በኃላ በድጋሚ ነገ ሐምሌ 20 2017 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ከቀኑ 8፡30 ላይ ወደ መድረክ ይመለሳል።

"ንጉሥ አርማህ" ወደ መድረክ ሲመለስ ከመቶ በላይ አንጋፋና ወጣት ተዋንያን እንደሚሳተፉበት ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የቴአትሩ ደራሲ አቶ መልካሙ ዘሪሁን ቴአትሩ ከተጻፈ 24 ዓመት እንደሆነ አስታውሶ ዛሬ ላይ ግን ትውልዱንና ያለንበትን ዘመንን በሚዋጅ ሁኔታ አብሮነት፣አንድነትን በንጉሥ አርማህ ታሪክና አስተዋይነት ውስጥ ቴአትሩ መዘጋጀቱን ገልጿል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
👍42
📌ጋዜጠኛ የኃላሸት ዘሪሁን በትወና የመጣበት "ወደ ማዶ" የተሰኘው ትያትር በ30 የዓለም ሀገራት መድረኮች ለዕይታ ሊቀርብ ነው።

የኪነ-ብስራት እና የነገረ ኪን የሬድዮ ፕሮግራሞች አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ የኃላሸት ዘሪሁን በትወና የመጣበትና "ወደ ማዶ" የተሰኘ ተውኔት ዓለም አቀፍ የቲያትር ጉዞ ሊጀመር መሆኑ ተነግሯል።

በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ተደርሶ በሴም አማኑኤል የተዘጋጀው "ወደ ማዶ" ትያትር የኮሜዲ ዘውግ ያለው ማህበራዊ ጉዳዮችን እያነሳ የሚሄድ፣ ሲሆን በሕይወታችን የሚገጥሙን ችግሮች ለማውጣት የሚደረግን ትንቅንቅ የሚያሳይ ነው።

በትያትሩ ላይ ሃረገወይን አሰፋ፣ ሽዋፈራው ደሳለኝ እና የኋላእሸት ዘሪሁን ይተውኑብታል ተብሏል።

"ወደ ማዶ" ዓለም አቀፍ የትያትር ጉዞ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሚገኙባቸው በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ አህጉራት በሚገኙ ሀገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ከ30 በላይ መድረኮች እንደሚታይ ተገልጿል።

በተጨማሪም እስካሁን ባልተለመደ መልኩ ትያትሩ በሚታይባቸው ሀገራትና መድረኮች ከትያትሩ ጎን ለጎን ለየኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል የገቢ ማሰባሰቢያ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ይህንንም በጎ አላማ ለማሳካት ከማዕከሉ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
5👍2
📌የታገል ሰይፉ "የእኔ ደማቅ ሠዎች" ለንባብ በቃ

ገጣሚና ደራሲ ታገል ሰይፉ "የእኔ ደማቅ ሠዎች" ሲል የሰየመውን አዲስ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት ለንባብ እንዳቀረበ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከጃፋር መጽሐፍ መደብር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

መጽሐፉ ስለ ከያኒያኑ ሙሉጌታ ተስፋዬ፣ሐዲስ አለማየሁ፣ስብሐት ገ/እግዚአብሔር፣ደበበ ሰይፉ እና ስለ ሌሎችም ሰዎች ያልተሰሙ መረጃዎችን የያዘ እንደሆነ ተነግሯል።

ታገል ሰይፉ ''የእኔ ደማቅ ሰዎች'' በሚል ርዕስ አስቀድሞ ተከታታይ ቪዲዮዎችን በዩቱብ ቻነሉ ሲለቅ እንደቆየ ይታወሳል።

"የእኔ ደማቅ ሰዎች" መጽሐፍ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
8
📌ስብሐቲዝም ስለመንግሥቱ ኃይለማርያም

ደራሲና ገጣሚ ይታገሡ ጌትነት የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 93ተኛ መድረክ "መንግሥቱ ኃይለማርያም 'ከፖለቲካ ባሻገር" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

የስብሐቲዝም አዘጋጆች ተከታዩን ብለዋል" ይታገሡ ጌትነት ነው የ93ኛ መድረክ እንግዳ። ስለ ሊቀ መንበር መንግስቱ ከፖለቲካ ገጽታቸው እስከ ግለሰባዊ ማንነታቸው የሚያወጋን እርሳቸውን አግኝቶ በበቃ ብዕር የተከተበልን ይታገሡ ነው።

ደራሲው ስለጻፈ ብቻ ሳይሆን ከልጅነት ጀምሮ እርሳቸውን ያውቃል። ስለሆነም ከሌላው በተለየ የሚነግረንን ሙሉ ያደርገዋል" ።

ውይይቱ ነገ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3
📌በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባው ባለ 11 ወለል ግዙፍ የሲኒማና ቴአትር አዳራሽ እየተጠናቀቀ ይገኛል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ አካባቢ እያስገነባው ያለው ባለ 11ወለል የህጻናት ቴአትርና ሲኒማ አዳራሽ ህንጻ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል ።

ዋንኛው የቴአትር አዳራሹ 1300 ሰዎች መያዝ የሚችል ሲሆን ፣ ሌሎች ሁለት መካከለኛ የሲኒማ አዳራሾችም በህንጻው ግንባታ ውስጥ ተካትተዋል።  የዋንኛው ቲያትር አዳራሽ መድረክ በሀይድሬሊክ ሲስተም 360 ዲግሪ መሽከርከር እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው።

©️Samson michailovich

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🔥7👍31👏1
📌የደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል "የወዲያነሽ" የልቦለድ መጽሐፍ ዳግም ሊታተም ነው።

የተወዳጁ ደራሲ፣ አርታኢ እና መምህር ኃ/መለኮት መዋዕል "የወዲያነሽ" መጽሐፍ ከአስር ዓመታት በኋላ ዳግም በቅድም ክፍያ ሽያጭ ለሕትመት ይበቃል ተብሏል።

መፅሐፉ ከ39 ዓመታት በፊት በ1978 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ለአንባቢያን ሲደርስ በ5.50 ዋጋ እንደነበር ደራሲ ኃ/መለኮት መዋዕል ከእዚያ በኋላ በተለያዩ አጋጣሚዎች መታተሙን አስታውሷል።

ከአስር ዓመታት በፊት በ2007 ዓ.ም ለመጨረሻ ጊዜ መታተሙን በመጥቀስ የመፅሀፉ ፈላጊዎች ቁጥር መበራከት ለዳግም ሕትመቱ ምክንያት እንደሆነ ጠቅሷል።

"የወዲያነሽ" መጽሐፍ ድጋሚ ሲታተም የጀርባ ዋጋው 400 ብር ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000571154319(ኃይለመለኮት መዋዕል ) ብር በማስገባት መጽሐፉን ቀድማችሁ መግዛት ትችላላችሁ ተብላችኋል።

የቀድመ ሽያጭ አስተባባሪዎች "መጽሐፍ ስትገዙ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ  በውስጥ ላኩልን https://shorturl.at/F7POF መጽሐፏ ከህትመት ሲወጣ በምረቃዋ ዕለት ወይም በሌላም መንገዶች ሁሉ ይደርሷችኋል" ሲሉ ተናግረዋል።

"የወዲያነሽ"ን ተከትሎ ሌላኛው የደራሲው ተወዳጅ ስራ "ጉንጉን" ዳግም እንደሚታተም በመግለፅ "የአዕምሮ ማህፀን ጤና ካለ አይመክንም፣ ከሰራህበት ሁል ጊዜ እየፋፋ እያደገ ነው የሚሄደው" ያለው ደራሲ ኃ/መለኮት መዋዕል ከእዚህ በኋላ ባለው ጊዜ አዳዲስ ሥራዎችን ለማበርከት እንደጥር ጠቁሟል።

ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል "የአርትኦት ሥራዎችን አቁሜያለሁ" ያለ ሲሆን "ከፈጣሪ  ፍቃድ ጋር"በቀጣዩ ዓመት አዲስ ስራ ሊኖር እንደሚችል ተናግሯል።

©️FM Addis 97.1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
10
📌 DStv ሙሉ በሙሉ ለካናል ፕላስ ተሸጠ

የፈረንሳዩ ተቋም ካናል ፕላስ  የደቡብ አፍሪካውን መልቲቾይዝ ግሩፕ (DStv) በ3 ቢሊየን ዶላር ገዝቶታል።

ካናል ፕላስ መጀመሪያውንም ቢሆን የመልቲቾይዝ 45 በመቶ ባለድርሻ የነበረ ሲሆን አሁን ሙሉ ለሙሉ ድርሻውን ገዝቶታል።

መልቲቾይዝ ለ40 አመታት የቆየ ስም የገነባ መሆኑ ሲገለፅ በአፍሪካ ከ50 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት ይገለፃል።

መልቲቾይዝ በክፍያ ከሚሰሩ የቴሌቪዥን ገበያዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዲ ኤስ ቲቪ እና ጎቲቪ በኩል የተለያዩ የስፖርት እና የመዝናኛ ፕሮግራሞችን በክፍያ ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

ግዢው ሙሉ ለሙሉ በመጪው ጥቅምት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ ካናል+ የደቡብ አፍሪካን ፕሮዳክሽን በአዲስ ገበያዎች የማስተዋወቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል።

ደቡብ አፍሪካ በህጓ የደቡብ አፍሪካን የስርጭት መብት የያዘ ድርጅት ባለቤትነቱ ከ20 በመቶ በላይ በውጪ ዜጋ መያዝን ስለምትከለክል መልቲቾይዝ የስርጭት መብቱን ላይሰንስኮ በተሰኘ ድርጅት ማድረጉ ተሰምቷል።

መልቲቾይዝ ሃገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በዲ ኤስ ቲቪ በኩል የእግር ኳስ እና የመዝናኛ ፕሮግራሞችንም ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ካናል+ በበኩሉ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ከገባ በኋላ የክፍያ ቴሌቪዥኑን በመዝጋት ወደ ሌላ አማራጮች ማዞሩን ከወራት በፊት መግለፁ ይታወሳል።

©️TikvahethMagazine

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4😱2
📌ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን ከህልፈቱ 17 ቀናት በኃላ ዛሬ ስርዓተ ቀብሩ በቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ተፈፀመ

ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን ሀምሌ 2 ቀን 2017 ዓ/ም በአሜሪካ ሲያትል ከተማ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ ይታወሳል።ዛሬ ሀምሌ 19 ቀን 2017 ከህልፈቱ 17 ቀናት በኃላ ስርዓተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ተፈጽሟል።

ጋዜጠኛው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከጋዜጠኝነት እስከ የዜናና ወቅታዊ መረጃ ዳይሬክተር በመሆን አገልግሏል።

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን "የሚዲያ_ዳሰሳ " በሚል ርዕስ ሲያቀርበው በነበረው ትንታኔ በአድማጭ ተመልካቾች ዘንድ ይታወሳል።

ወደ አሜሪካ በመሄድም በPhD ተመርቋል።ከትምህርቱ ጎን ለጎንም እስከ ህልፈቱ ድረስ TBS በተባለው የትግርኛ ቴሌቪዥን በአማርኛና በትግርኛ ቋንቋዎች ወቅታዊና የመዝናኛ ፕሮግራሞች ሲያቀርብ ነበር። 

በ1963 ዓ/ም በትግራይ ውቕሮ ከተማ የተወለደው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ  የጋዜጠኝነትን ኮሙዩኒኬሽንን ክፍል በዲግሪ ተመርቋል። በጋዜጠኝነት ሙያ ለረጅም አመታት ሰርቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
8😢3😭3
📌በቻይና ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ተሸለመች

ጋዜጠኛ ሰላም ተሾመ ከሰሞኑ በቻይና በተካሄደው የ"Road and Belt journalist forum" ላይ ኢትዮጵያን ወክላ ተገኝታ ነበር።

በፎረሙ ከ30 በላይ ሃገራት ከተወከሉ የሚዲያ ባለሙያዎች መካከል ጋዜጠኛ ሰላም ተሾመ ባቀረበችው ስራ ከፍ ያለ ዕውቅና ተሰጥቷት።

በዚህም ስራዋ ተሸላሚ ሆና የሀገራችንን ስም አስጠርታለች።

©️ጋዜጠኛ ያልፋል አሻግር

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
11
📌ድምጻዊ ብስራት ጋረደው "ከእንግዲህ በኃላ በመዝሙር ጠብቁኝ" ሲል ተናገረ

ድምጻዊ የግጥምና ዜማ ደራሲው ብስራት ጋረደው በአርትስ ቴሌቪዥን በኩል በሚተላለፈው 'ዘጠናዎቹ' የቴሌቪዥን ዝግጅት ላይ እንግዳ ሆኖ ቀርቦ ነበር በዚህም ዝግጅት ላይ "ከእንግዲህ በኃላ በመዝሙር ጠብቁኝ" ሲል ተናግሯል።

ብስራት ጋረደው በተጨማሪም "ከሞትኩበት ያነሳኝን አምላኬን ዘፍኜ አላሳዝነውም" ብሏል።

ድምጻዊ ብስራት ጋረደው በዘጠናዎቹ በለቀቀው "ሳላምንበት" በተሰኘው ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሙ ከበርካታ የሙዚቃ አድማጮች ጋር ተዋውቋል።

በተጨማሪም ለበርካታ ድምጻዊያን የግጥምና ዜማ ስራዎችን አበርክቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3
📌የጋዜጠኛው የስለት ጥቃት ሀሰት ሆኖ ተገኘ

የስፖርት ጋዜጠኛው አሉላ ፍሬው "በጩቤ ተወጋሁ" ያለው ጉዳይ በመረጃና ማስረጃ ሀሰት ሆኖ ተገኘ

የCD ስፖርትና የNBC ኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኛው አሉላ ፍሬው በስለት የመወጋት አደጋ እንደደረሰበት ከ51 ቀናት በፊት በራሱ የፌስቡክ ገፅ አስታውቆ ነበር።ይህም አስነዋሪ ድርጊት በወቅቱ መነጋገሪያ እንደነበረ ይታወሳል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ታምሩ አለሙ እና ባልደረቦቹ ጥልቅ ምርመራ አድርገው ፣መረጃዎችን አጣርተው ነበር።

ይህ "ጋዜጠኛው ላይ ጉዳት ያደረሰው ማነው?" በሚል ርዕስ የቀረበው ሰፋ ያለ ዘገባ "የፖሊስ፣ የክሊኒክ፣ የማህበሩና የፌዴሬሽኑን ምላሽ" ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

በምርመራቸውም የስፖርት ጋዜጠኛው የሰጣቸው መረጃና በምርመራ ያገኙት መረጃ ፍፁም የማይገናኝ በመረጃና ማስረጃ ሀሰት እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከዘገባቸው ላይ ተመልክቷል።

የምርምር ቡድኑ "የዚህ ዘገባ አላማ የሙያ ባልደረባችን ያጋጠመውን ጉዳት መነሻ በማድረግ በሙያተኞች ላይ የሚደርሰውን በደልና ጥቃት ማውገዝ ብሎም ማጋለጥ ነበር፤ ሆኖም መረጃውን ስናጣራ ውጤቱ ይህ ሆኗል" ሲል አስታውቋል።

ሙሉ መረጃውን ከጋዜጠኛ ታምሩ አለሙ የፌስቡክ ገፅ ያንብቡ: https://www.facebook.com/1812918430/posts/pfbid02E2uAome5LTwaR9YZbYBQsLwiQX93kyqysRYPSpC5SpC9U3FiekbqriQpGjDAQxVpl/

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4😁4🔥2🤔1
📌የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ይቅርታ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ከ" ንጉሥ አርማህ" ተውኔት የመክፈቻ ሥነሥርዓት ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው የታዳሚያን መጉላላት በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

ቴአትር ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ"በትናንትናው ዕለት ማለትም ሐምሌ  20 ቀን 2017 ዓ.ም  ‹‹ንጉሥ አርማህ›› ቴአትር በይፋ መከፈቱ ይታወቃል፡፡ በዕለቱ የተመልካቹ ብዛት ከቴአትር ቤቱ አዳራሽ አቅም በላይ በመሆኑ በቦታ ጥበት ምክንያት የተመለሳችሁ ክቡራን ተመልካቾቻችንን ከፍተኛ ይቅርታ በቴአትር ቤቱ ሥም እንጠይቃለን" ስለማለቱ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

በሌላ በኩል "ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8፡30 ይቀርብ የነበረው ‹‹12ቱ እንግዶች›› ቴአትር  ወደ ቅዳሜ 8፡30 የተዘዋወር ሲሆን  ‹‹ንጉሥ አርማህ›› ቴአትር ዘወትር እሁድ በ8፡30 ለክቡራን ተመልካቾች እንደሚቀርብ በአክብሮት እንገልጻለን" ሲል የመርሐግብር ለወጥ እንዳደረገም ቴአትር ቤቱ አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🙏173
📌"ሣማ ፊልም" ተመረቀ

በደራሲና አዘጋጅ ሞገስ አስራት ተዘጋጅቶ በአድዋ ፊልምስ የቀረበው "ሳማ" ፊልም ትላንት ሰኞ ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዓለም ሲኒማ ተመርቋል።

በፊልሙ ላይም በመሪ ተዋናይነት ሽዋፈራሁ ደሳለኝ ፣ ሙላለም ጌታቸው ፣ ቤዛነሽ አያሌው እንዲሁም ሌሎች አዳዲስ ተዋንያን ተሳትፈውበታል ።

ከዚህ ቀደም በተመልካች ተወዳጅነትንና አድናቆትን እንዲሁም በተለያዩ አዋርዶች ላይ በበርካታ ዘርፎች በመታጨትና በመሸለም የሚታወቀውን "ክሱት" የተሰኘ ፊልም በመስራት ለዕይታ ያበቃው አድዋ ፊልምስ ፕሮዳክሽን አሁን ደሞ ሙሉ ቀረፃውን በጉራጌ ዞን ያደረገ "ሣማ" የተሰኘ ፊልምን ለእይታ አብቅቷል።

ፊልሙ በቅርቡ በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይቀርባል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1