📌የገጣሚ መላክ ማሩ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል
የገጣሚ መላክ ማሩ "መንታ ነፍስ"የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ ነገ ሐምሌ 6 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ታኦስ የባህል አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።
በዕለቱም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በመጽሐፉ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1

❤1
📌የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል ሙዚቃ ተለቀቀ
የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "እንደ አመሌ" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ትላንት አመሻሹን በናሆም ሪከርድስ የዩቲዩብ በኩል ለአድማጮች ቀርቧል።
በ"እንደ አመሌ" ሙዚቃ ላይ በግጥምና ዜማ አብዲ እንዲሁም በቅንብር ብሩክ ተቀባ ተሳትፈውበታል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

👍3❤2
📌የአለማየሁ ገላጋይ ሦስት ድርሰቶች ተሰበሰቡ
የደራሲ አለማየሁ ገላጋይ ሦስትያ ድርሰቶች በአንድ የተካተቱበት መጽሐፍ ለአንባቢያን ቀረበ።
በፍቅር ስም ፣ ታለ በእውቀት ስም፣ ሀሰተኛው በእምነት ስም የተሰኙ ሶስት ተከታታይ ድርሰቶች "ዝይን" በተሰኘ ርዕስ ውስጥ በአንድ እንደተሰባሰቡም ተነግሯል።
የመጽሐፍ አሳታሚ ዋልያ መጽሐፍ ሲሆን በጠንካራ ወረቀት፣ ለማንበብ በሚያመች መልኩ እንደተዘጋጀም ተገልጿል። በተጨማሪም በሀርድ ከቨር 200 መጻሕፍት ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።
ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ በማህበራዊ ትስስር ገፁም “ዝይን" ን ዳጎስ ብላ ስመለከት " ለካ ሰርቻለሁ፣ የሀገሬ ሥነ ጽሁፍ ውስጥ አለሁበት" የሚል ምስክርነት ለራሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰማኝ። አይጣበቅብኝ ፣ ለእብሪት አይዳርገኝ እንጂ አንዳንዴ ይሁን" ሲሉ ተናግሯል።
መጽሐፉ በቅርቡ በተለይ ዝግጅት እንደሚመረቅም አርትስ ስፔሻል ከዋልያ መጻሕፍት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

🔥8❤5👍3
📌ኢቫንጋዲ የኢንቴርየር ዲዛይን ስልጠና ጀመረ
ከተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ የሚገኘውና በሁለት ወጣት ሴት ባለሞያዎች ሜሮን መኮንን እና ህብረወርቅ ገለታ የሚመራው ኢቫንጋዲ ኮንስትራክሽንና ቤተ-ውበት በዚህ ክረምት የኢንቴርየር ዲዛይን ስልጠና በይፋ ጀምሯል።
በተጨማሪም ኢቫንጋዲ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች -
ኢንቴርየር ዲዛይን እስከ ግንባታው
ላንድስኬፕ/የገፀ ምድር/ ዲዛይን
አርክቴክቸራል ዲዛይን
3D Rendering & Modeling
Physical modeling እና ሌሎችም አገልግሎቶች ይገኙበታል።
አድራሻቸው: ሾላ ገበያ ቡና ባንክ ያለበት ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ ነው።
ስልኩ ቀጥራቸው ደግሞ
0915416410
0938218123
በቴሌግራም አድራሻቸው @Evangadiconstruction ሊያገኟቸውም ይችላሉ።
የቲክቶክ ቻናል: merryevangadi_interiors
የቴሌግራም ቻናል:https://t.me/Evangadiconstruction1

❤1👍1
📌ከጋዜጦችን ጀርባ ያለ ያልተነገረለት ታታሪ ሰው
የሕትመት ዋጋ መናር ብዙ ጋዜጦችና መፅሔቶችን ከሕትመት ውጪ አድርጓል። እጅግ ተወዳጅ የነበረው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከወር በፊት ሹልክ ብሎ ከገበያ ብዙ ሰው አላስተዋለም።
ያሉትም ጋዜጦች አዲስዘመን፣ ሄራልድ፣ ፎርቹን፣ ካፒታል በገበያ ውስጥ እየተንገዳገዱ ቢቀጥሉም ኮፒያቸውን በመጨመር ተደራሽነታቸውን ለማሳደግ የሕትመት ዋጋ ንረቱ አስሮ አስቀምጧቸዋል።
አንድ ጋዜጠኛ ወዳጄ ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች ለታይታ ያህል እንጂ ኮፒ ጨምሮ ማሳተም ገንዘብን አትሞ ሜዳ ላይ የመርጨት ያህል እንደሚቆጠር አጫውቶኛል።
እንደብርሐኑ ዮሐንስ ዓይነቱ ጋዜጣ አከፋፍሎ ሕይወቱን ለሚገፋ ሰው ይኸ ጉዳይ ይበልጥ አሳሳቢ ነው።
ብርሐኑ የሕመት ኢንደስትሪው በከባድ ወጀብ ውስጥ ባለበትም በዚህ ወቅት ተስፋ ባለመቁረጥ ጋዜጦችን ተሸክሞ ከመነሻው 4 ኪሎ፣ በ 22 ፣በ መገናኛ፣ በቦሌ በእግሩ አቆራርጦ ደንበኞቹ ጋር ያደርሳል።
ጠዋት ማልዶ ተነስቶ እስከ ቀኑ 10:00 አንዳንዴም 11:00 ሰዓት ድረስ መጓዝ የዕለት ተዕለት ሥራው ነው። በዚህ መንገድ ከሚያገኛት በወር 5 ሺህ ብር ገደማ ገቢ ሁለት ልጆቹን እያስተማረ ይገኛል።
ሥራ እንዴት ነው አልኩት።
መጥፎ ነው ብሎ ማማረር አልፈለገም። በአጭሩ "ቀዝቅዟል" አለኝ።
"መቀዝቀዙ ገቢህን ጎድቶታል?"
"አዎን እንደበፊቱ አይደለም" የሚል አጭር ምላሽ ሰጠኝ።
አዎ ብርሐኑ ለዓመታት ከእጅ ወደአፍ በሆነ የጋዜጣ ማዞርና ማከፋፈል ሥራ ውስጥ ቆይቷል። ዛሬም ግን አልደከመውም። ዛሬም ሥራውን ስለማሳደግ አብዝቶ ያስባል።
"ሳይክል ወይንም ሞተር ሳይክል ባገኝ ሥራዬን ለማስፋትና ገቢዬን ለማሳደግ እችላለሁ" አለኝ።
(ፍሬው አበበ)

❤16😢5👍2
📌ድምጻዊ አዲስ ለገሠ አዲስ ሙዚቃ ሊለቅ ነው
የድምጻዊ አዲስ ለገሠ "እቱ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ሐምሌ 5 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በራሱ የዩቲዩብ ቻናል ለሙዚቃ አድማጮች ይደርሳል።
በዚህ የድምጻዊ አዲስ ለገሠ ነጠላ ሙዚቃ ላይ በግጥም ናትናኤል ግርማቸው በዜማ እሱባለው ይታየው (የሺ) እንዲሁም በሙዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ተሳትፈዋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የድምጻዊ አዲስ ለገሠ "እቱ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ሐምሌ 5 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በራሱ የዩቲዩብ ቻናል ለሙዚቃ አድማጮች ይደርሳል።
በዚህ የድምጻዊ አዲስ ለገሠ ነጠላ ሙዚቃ ላይ በግጥም ናትናኤል ግርማቸው በዜማ እሱባለው ይታየው (የሺ) እንዲሁም በሙዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ተሳትፈዋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍3❤1
📌ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን ስራ ተሰጠው
ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) በተመቸው ሰዓት ስራ መጀመር እንደሚችል የእሁድ ቤት አዘጋጆች አብስርውታል።
ድንገት ከሚዲያ የጠፋው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን በቅርቡ ፈተና ውስጥ እንደሆነ የሚገልጽ አሳዛኝ ቪዲዮ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ከአሰራጫ በኃላ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።
ከሰሞኑም ለ40 ቀናት በገዳም የቆየበትን የመታደስና የፈውስ ጉዞ አጠናቆ በሰላም ወደ ቤተሰቡና ልጆቹ መመለሱ ይታወሳል።

❤44👏8👍4
ተፈራረሙ !
ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቨንትስ ከኪንግስ እግር ኳስ ቡድን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ሐምሌ 7 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል።
በዚህ ስምምነት መሠረት ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቨንትስ ለኪንግስ እግርኳስ ቡድን ብቸኛ ስፖንሰር በመሆን በጋራ ይሰራሉ ተብሏል።
የኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቨንትስ መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሩት ሐይሉ በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ በስምምነታቸው ደስተኛ መሆናቸውን አስረድተው ውላቸውም ለ6 ወር ያህል እንደሚቆየም ተናግረዋል።
በተጨማሪም በነዚህም ጊዜያቶች በሚደረጉ በየትኛውም ዝግጅቶች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት እንደሆነም ገልጸዋል።
የኪንግስ እግር ኳስ ቡድን ፕሬዘዳንት አቶ አቤኔዘር ሰብስቤ በበኩላቸው ስምምነቱ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል በመጠቆም፤ ከኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቨንትስ ጋር በጋራ መስራታቸው ይበልጥ ጠንክረው እንዲሰሩ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።
ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቨንትስ የተለያዩ ዝግጅቶችን በብቃት የሚያዘጋጅ ድርጅት ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህም መንፈሳዊ የመዝሙር ድግሶችን ከማዘጋጀት ባሻገር፤ከተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ዝግጅቶችን ጨምሮ ትላልቅ ሠርጎችን፣ ስብሰባዎችን፣ ምርቃቶችን እና የተለያዩ ኢቨንቶችን በብቃት በመወጣት የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘ ድርጅት ነው።
#ruthailupomi #ሩት_ሀይሉ #elvezetinternationalevents #viralchallenge #fyp

❤3🤔2
📌የ"ልጄስ ?" ድራማ ደራሲና አዘጋጅ ሰማኝጌታ አይችሉህም የክብር እንግዳ የሆነበት ዝግጅት ነገ ይካሄዳል።
ሁለተኛው Creative lab ዝግጅት ደራሲ እና ዳይሬክተር ሰማኝጌታ አይችሉህምን ይዞላችሁ ቀርቧል።
በዚህ ዝግጅት ሰማኝጌታ ስለ "ልጄስ?" ተከታታይ ድራማ አፃፃፍ እንዲሁም ዳይሬክቲንግ ጥበብን ያካፍላል።
ጀማሪ የስክሪፕት ፀሀፊዎች ዳይሬክተሮች በፊልሙ ዓለም ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ወጣት ጀማሪ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛና ዕድል ለእናንተ ነው ተብላችኋል።
በዕለቱ እጅግ ተወዳጅነት ያተረፈውን የተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ "ልጄስ?" ፓይለት ኤፒሶድ ይቀርባል። በዚህም ከፊልሙ ጀርባ ያለውን ራዕይ እንዲሁም የስራ ሂደት
በተመለከተ ውይይት ይኖራል ።
📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )
📅 ቀን: ሃምሌ 8 ፣ 2017
🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00
🎟 መግቢያ: ነፃ
አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር
📎 በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

❤10👍1👎1
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ህልውና አሳሳቢ ሆነ
ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አጠቃላይ እንቅስቃሴ በመዳከሙና ህልውናው አሳሳቢ በመሆኑ ቀጣይ ዕጣ ፈንታቸው እንዳስጨነቃቸው የድርጅቱ ጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡
ማንነታቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የድርጅቱ ጋዜጠኞች ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ በተቋሙ ውስጥ በርካታ ችግሮች እንዳሉ ገልፀው፣ ለአብነትም ደመወዝ በሰዓቱ እንደማይከፈላቸው፣ ይህም ተደጋግሞ የሚስተዋል እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ላለፉት ሦስት አመታት የተቋሙ ፊዚካልና ፋይናንሻል የስራ አፈጻጻም፣ እንዲሁም የሰራተኛውም ሆነ የአመራሩ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዶ እንደማያውቅ የገለፁት ጋዜጠኞቹ "በይፋ ፈርሷል ለመባል ጫፍ ላይ ነው ያለው" በማለት ድርጅቱ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡
የድርጅቱ ባለቤት የነበረው የቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከፈረሰና አራት የተለያዩ ክልሎች ከተዋቀሩ በኋላ ክልሎቹ እንደየ ድርሻቸው ለተቋሙ በጀት የሚመድቡበት አሰራር የተዘረጋ ቢሆንም ተግባራዊ ባለመሆኑ ችግሮቹ መፈጠራቸውን ተናግረዋል፡፡
የሲዳማ ክልል የራሱን ብዙሃን መገናኛ በመመስረቱ በጀት ለመመደብ ፍቃደኛ አለመሆኑን፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሚጠበቅበትን እያዋጣ እንዳለሆነ የሚናገሩት ጋዜጠኞቹ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግን ከሚጠበቅበት በላይ በማዋጣት ለማገዝ እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡
የደቡብ ኢትየጵያ ክልል በበኩሉ ከተመደበለት ኮታ በታች ቢሆንም በጀት እያዋጣ እንደሆነ ጋዜጠኞቹ ተናግረዋል፡፡
በእነዚህና በሌሎችም ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ምክንያት ድርጅቱ ህልውናው እንደሚያሰጋና ቀጣይ ዕጣ ፈንታቸው አሳሳቢ መሆኑን ነው ጋዜጠኞቹ የገለፁት፡፡
Via ኢትዮ ኤፍኤም

❤5
📌በአለልኝ አዘነ ገዳዮች ላይ ተፈረደ
የእግር ኳስ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ ግድያ የተከሰሱት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው።
በአለልኝ አዘነ ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት ዛሬ የተሰየመዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት አደይ ጌታቸዉና በእህቷ ባል ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ይህንን ዉሳኔ ያስተላለፈው መጋቢት 17/2016 ዓ/ም በተጋቡ በ15ኛ ቀን አለልኝ አዘነን ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል መግደላቸውን በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች ካረጋገጠ በኋላ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ

❤2
📌የወጣቷ ድምፃዊ ማህሌት ወንድሙ “እድለኛ” አልበም በሰዋሰው በኩል የሚለቀቅበት ቀን ይፋ ሆነ
‘’እሺ አትለኝም ወይ’’ እና ‘’ዝም’’ በሚሉት ሁለት ነጠላ ዜማዎች በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን እና ተቀባይነትን ያገኘችዉ የወጣቷ ድምፃዊ ማህሌት ወንድሙ (ማሂ) የመጀመሪያ አልበም ሀምሌ 18/2017 ዓ.ም ይለቀቃል።
‘’እድለኛ’’ የተሰኘዉ የወጣቷ ድምፃዊ አልበም በሰዋሰዉ መልቲሚዲያ ፕሮዲዩስ የተደረገ ሲሆን የሬከርዲንግ ፕሮዲዩሰሩ ደግሞ ወንዶሰን ይሁብ እንደሆነ ተነግሯል።
በጥቂት ወራት ልዩነት በተከታታይ ሁለት ነጠላ ዜማዎችን በመልቀቅ ከ13 ሚሊየን በላይ ተመልካች በዩቲዩብ ማግኘት የቻለችዉ ድምፃዊ ማህሌት ወንድሙ(ማሂ) በአልበሟም ልዩ ነገር ይዛ ብቅ ስለማለቷ ሰምተናል።
10 ያህል ሙዚቃዎችን የያዘዉ ‘’እድለኛ’’ አልበም የፊታችን አርብ በሰዋሰዉ መተግበሪያ እና የዩቲዩብ ገጽ ይለቀቃል።

❤10👍3🥰1
📌የሙዚቃ አቀናባሪው የራሱን የሙዚቃ አልበም ሰራ
በድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ "አስቻለ" አልበም ላይ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ያቀናበረው ቢንአንዴ የራሱን "ነጭ ጤፍ" የተሰኘ አልበም ለአድማጮች ሊያቀርብ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
"ነጭ ጤፍ" የተለያዩ አንጋፋ እና ጀማሪ ድምፃዊያንን፣ ደራሲዎችን እንዲሁም ሙዚቀኞች እንደተሳተፉበት ተገልጿል።
የሙዚቃ ስራው ብዙ የተደከመበትና እንዲሁም ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ ያልተለመዱ ፕሮፌሽናል የሙዚቃ ድምፆችን፣ የሙዚቃ ቅንብሮችን እንዲሁም ዜማዎችንና አዛዜሞችን ይዞ እንደቀረበ ተነግሯል።
ይህ የሙዚቃ አልበም በቅርቡ በተለያዩ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ለአድማጮች ይቀርባል ተብሏል።

❤11👍1
📌"ሰተቴ" ተከታታይ ድራማ ለእይታ ሊበቃ ነው
በመንገደኛው ባለቅኔ ከድር ሰተቴ ላይ መሠረቱን ያደረገ "ሰተቴ" የተሰኘ አዲስ ተከታታይ አስቂኝ ድራማ በአርትስ ቴሌቪዥን ከሐምሌ 20 ጀምሮ ለተመልካቾች መቅረብ እንደሚጀመር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።
"ሰተቴ" ተከታታይ አስቂኝ ድራማ ከፍተኛ በጀት ወጥቶበት በከፍተኛ ጥራት የተዘጋጀ ሥራ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በተስፋዬ አየለ (ዶ/ር) ‘መንገደኛው ባለ ቅኔ ከድር ሰተቴ’ በተሰኘ መፅሐፍና በጦቢያ ግጥምን በጃዝ ሲቀርብ በነበረው የአንድ ሰው ቴአትር ላይ ተመርኩዞ በአንተነህ ኃይሌ ዳይሬክተርነት ተመርቶ የሀገራችንን ወጣትና አንጋፋ ተዋናዮችን በማሳተፍ የተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

❤11🔥2👍1😁1
📌“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ በድጋሚ ለንባብ በቃ
የኤልያስ መልካ ሕይወትና ሥራዎችን የሚተርከው “የከተማው መናኝ” መጽሐፍ በአንባቢያን ጥያቄ መሰረት በድጋሚ ታትሞ ለአንባቢያን ቀረበ።
“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ ጃፋርን መጻሕፍት ቤትን ጨምሮ በሁሉም የመጻሕፍት መደብሮች ለአንባብያን ቀርቧል::
በደራሲና ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው (ማዕረግ) የተዘጋጀው መጽሐፉ ለንባብ ከበቃበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡
“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ የተናፋቂውን ኤልያስ መልካ አነጋጋሪ የግል ፍልስፍና እና የሕይወት ውጣ ውረድ የሚተርክ ሲሆን መጽሐፉ በወጣበት ዓመትም በኢ-ልብወለድ ዘርፍ ከዓመቱ አምስት ምርጥ መጽሐፍት አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡
ይነገር ጌታቸው (ማዕረግ) በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ላይ ምርምርን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን በ2015 ዓ.ም ሙዚቃ፣ታሪክና ፖለቲካ ላይ ያተኮረውን “ጠመንጃና ሙዚቃ” የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባብያን አድርሷል፡፡

❤9🔥3👍1
📌ሚሊኒየም አዳራሽ ፈርሶ በድጋሚ ሊገነባ ነው
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኘው እና በተለምዶ ሚሊኒየም አዳራሽ በመባል የሚታወቀው አዲስ ፓርክ እና ማኔጅመንት ከታህሳስ 2018 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ፈርሶ በአዲስ መልኩ እንደሚገነባ ተገለጸ።
በ2000 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት የጀመረው ይህ ግዙፍ አዳራሽ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ታላላቅ አዳራሾች ግንባር ቀደሙ ነው።
አዲሱ ግንባታ የአዳራሹን አቅም እና ዘመናዊነት ይበልጥ እንደሚያሳድግ ሲጠበቅ፣ ለግንባታው የሚወጣው ኢንቨስትመንት መጠን እና የስራ ተቋራጩ ማንነት በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል።
ሚሊኒየም አዳራሽ በ20 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ እስከ 25,000 ሰዎችን የማስተናገድ አቅም አለው።
ይህ አዳራሽ ከትልልቅ ብሔራዊ ፕሮግራሞች፣ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች፣ ኤግዚቢሽኖች፣ ኃይማኖታዊ ፕሮግራሞች፣ የምርቃት ስነስርዓቶች በተጨማሪ፣ ታላላቅ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ለሽኝት ስነስርዓቶች ጭምር ሚናውን ሲጫወት መቆየቱ ከካፒታል መግለጫው ተመልክቷል።
በሰኔ ወር 2017 ምሽት ላይ፣ ሚሊኒየም አዳራሽ የተለመደውን አገልግሎት እየሰጠ በነበረበት ወቅት ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንደገጠመው ታውቋል። የዚህ ችግር ምንጭ ለጊዜው በሚመለከተው አካል እየተጣራ በመሆኑ፣ ጊዜው ሲደርስ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከ 17 ዓመታት በኃላ አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ፈርሶ በአዲስ መልኩ መገንባት ለወደፊቱ ለተለያዩ ዝግጅቶች የተሻለ እና ዘመናዊ የመስተንግዶ አማራጭ እንደሚሰጥ ይጠበቃል ተብሏል።
Via ካፒታል ጋዜጣ

❤14👍1👏1
📌የዘሪቱ ከበደ የመዝሙር ዝግጅት ሊካሄድ ነው
በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ በድምጻዊነቷና በግጥም ችሎታዋ ከፍተኛ ስምን ያተረፈችውና በኋላም ሙሉ ጊዜዋን ለመንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ወደ ዝማሬ ዓለም የገባችው ዘሪቱ ከበደ፣ “ማጽናናትህ” በሚል ርዕስ አዲስ የመዝሙርና የምስክርነት ዝግጅት ማዘጋጀቷን አስታውቃለች።
ይህ ዝግጅት፣ አርቲስቷ በህይወቷ ካሳለፈቻቸው ከባድ ውጣ ውረዶች እና ከደረሰባት ጥልቅ ሐዘን በመነሳት፣ እግዚአብሔር እንዴት እንዳጽናናት የምትመሰክርበት ልዩ መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ዘሪቱ ከበደ በሙዚቃው ዓለም በከፍተኛ ዝና ላይ በነበረችበት ወቅት ከገጠማት የህይወት ለውጥ አንስቶ፣ በተለይም በቅርብ ዓመታት ውስጥ ህጻን ልጇን በሞት በማጣቷ ምክንያት የደረሰባትን ከባድ ሐዘን በይፋ መናገሯ ይታወሳል። የ"ማጽናናትህ" ዝግጅት ርዕስም በቀጥታ ከዚሁ የግል የህይወት ምዕራፍ ጋር የተያያዘ ነው።
ይህ የምስክርነት ምሽት ዘሪቱ ከደረሰባት ከባድ የሐዘን ስሜትና የህይወት ፈተና ውስጥ ያለፈችበትን መንገድ እና ያገኘችውን መንፈሳዊ መጽናናት ለሌሎች የምታካፍልበት መድረክ ይሆናል። ዝግጅቱ፣ የግል ስቃይን ወደ ህዝባዊ የተስፋ መልዕክት የመቀየር ጥልቅ መንፈሳዊ አንድምታ ያለው ሲሆን፣ በህይወታቸው ተመሳሳይ ፈተና ላለፈባቸው ብዙዎች መጽናናትንና መነቃቃትን ይሰጣል ተብሎ ይታመናል።
የዝግጅቱ ዝርዝር:
የዝግጅቱ ስም፦ ማጽናናትህ (የመዝሙርና የምስክርነት ምሽት)
ቀን፦ ነሐሴ 10, 2017 ዓ.ም. | August 16, 2025
ቦታ፦Beza International Church
©️ዘ-ሐበሻ

❤9👎5👍2🙏1
📌ነፃ የሞዴሊንግ እስኮላርሺፕ ዕድል
ሞዴል መሆን ይፈልጋሉ ?
ፕሪስቴጅ አዲስ ከሌጋሲ ሞዴሊንግ ኤጀንሲ ጋር በጋራ በመሆን ነፃ የሞዴሊንግ ስልጠና ለእናንተ ይዞላችሁ መጥቷል።
የዚህ እድል ተካፋይ መሆን የምትፈልጉ ከታች ያለውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባችኋል።
✅የፕሪስቴጅ አዲስ እና ሌጋሲ ሞዴሊንግ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ቻናል ፎሎ ያድርጉ ።
✅ይሄንን ፖስት የተደረገውን ሼር በማድረግ ኢንስታግራም ስቶሪ ላይ ያጋሩ ፣ ሁለቱንም ቻናሎች ታግ ያድርጉ ።
✅ ኮሜንት ላይ ፍላጎት ያላቸውን ሶስት ሰዎችን ታግ ያድርጉ።
✅በኮሜንት ሃሳብ መስጫ ላይ ሌጋሲ ሞዴሊንግ መማር ለምን እንደምትፈልጉ እና ይሄንን እድል ላንቺ / ላንተ ለምን እድሉ መሰጠት እንዳለበት ግለፅ/ጪ ።
✅ ይሄ እድል ከ 16 ዓመት እስከ 30 ዓመት ለሆኑት ክፍት ነው።
✅ ምንም አይነት የሞዴሊንግ ልምድ አይጠይቅም - ለጀማሪዎች ክፍት ነው ።
✅ #ፕሪስቴጅአዲስ እና #ሌጋሲሞዴኒንግ ሃሽታጎችን ይጠቀሙ ።
የዚህ እድል ተካፋይ ለመሆን የ @prestigeaddis ኢንስታግራም ገፅ ላይ በመግባት ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት በማሟላት መሳተፍ ይችላሉ።
መልካም ዕድል

📌ገጣሚና ሠዓሊ ከበደች ተክለአብ ልምዷን ታጋራለች
በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል ገጣሚና ሠዓሊ ከበደች ተክለአብ በሥራዎቿና በሕይወቷ ዙሪያ ልምዷን ታጋራለች፡፡
በዕለቱ ስለገጣሚነቷ፣ ስለሠዓሊነቷ፣ በሶማሊያ ሐዋይ የ10 ዓመታት የእስር ቤት ቆይታዋ፣ በሀዋርድ ዩኒቨርስቲ በተማሪነትም በመምህርነትም ስላሳለፈቻቸው ዓመታት ታወጋናለች፡፡
ዝግጅቱ የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 19፣ 2017 ከ8 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይቀርባል፡፡
ይህ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ትብብር በኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር አማካኝነት የሚሰናዳው የክረምት ወራት የሥነ ጽሑፍ ሥልጠና አንዱ አካል ነው፡፡
የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል በዝግጅቱ እንዲታደሙ ግበዣውን ያቀርባል፡፡
የዝግጅቱ ቦታ:- በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ (በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ)፡፡ https://maps.app.goo.gl/yb1LFT7PDTwLUP217

❤12👍4🤔1
📌“አፄ ዘርዐ ያዕቆብ እና ሥራዎቹ” መጽሐፍ ተመረቀ
በዶ/ር አንዱአለም አባተ (የአጸደ ልጅ) እና በኢንጅነር ቴዎድሮስ ደመቀ የተጻፈ “አፄ ዘርዐ ያዕቆብ እና ሥራዎቹ” የተሰኘ መጽሐፍ ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል፡፡
በመርሀ- ግብሩ ላይ ገጣሚና አዘጋጅ ጌትነት እንየው እና በዶ/ር ገዛኸኝ ጸጋው ከመጽሐፉ ውስጥ የተወሰኑ ቅንጭብ ታሪኮች ተነበዋል።
ከዚህ በተጨማሪም፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማኀበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብእ ኮሌጅ ምክትል ዲን በዶ/ር ሲሳይ ሳህሌ አማካኝነት መጽሐፉን የሚዳስስ ጥልቅ ሀሳብ የያዘ ጽሑፍ ቀርቧል።
መጽሐፉ የመካከለኛውን ዘመን ታላቅ ንጉስ የአፄ ዘርዐ ያዕቆብን የሕይወት ታሪክና ሥራዎች የሚያስዳስስ ሲሆን 19 ምዕራፎች እና 542 ገጾች አሉት።

❤6👍2
📌የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ ተመረቀ
የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ በሀገራችን የሙሉ ጊዜ የልጆች የቴሌቪዠን ቻናል በመጀመር ፈርቀዳጅ የሆነና በተለይም በልጆችና ቤተሰቦቻቸው ዘንድ ሠፊ ተቀባይነት በማግኘት በአወንታዊ የትውልድ ግንባታ ላይ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው ይህንን መተግበርያ ይፋ ያደረገው።
ተቋሙ አላማና ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማስፋት በማሰብ መተግበርያውን ማበልጸጉን ይፋ አድርጓል።
በባለፉት አስርት አመታት በልጆች ዙርያ የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ የቆየው ተቋሙ በባለፉት ሰባት አመታት ደግሞ በኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን የልጆች ፕሮግራሞችን በማቅረብ ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን ያስመረቀው ይህ መተግበርያ በውስጡ 10 የሚሆኑ ይዘቶችን ማካተቱን ነው የተገለጸው።
መተግበርያው ያበለጸገው መሁቡብ ቴክኖሎጂስ መተግበርያው ለልጆች አመቺ የሆነና አጠቃቀም ተብሎ ቀለል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዠን ስራ አስኪያጅ ህብስት አሰፋ እንደተናገሩት በተመደቡበት የስራ ዘርፍ ተሰልፈው ከመጋረጃ ጀርባ ያሉ የተቋሙ ሰራተኞች እና ባለሙያዎች ምስጋና ይግባና ዛሬ ለዚህ በቅተናል ብለዋል።
ተቋማችን እዚህ ለመድረሱ ሚስጥር የልጆቻችን ወላጆች ናቸው ያሉት ስራ አስኪያጇ ስላደረጋችሁት ሁሉ ነገር እናመሰግናለን ብለዋል።
©️ድሬቲዩብ

👍4