Event Addis Media
9.62K subscribers
6.08K photos
12 videos
4 files
4.71K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌በዓለም ሲኒማ በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።

እሁድ በ12:00 "ከመጋረጃ ጀርባ" ተውኔትም ይቀርባል።

    መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!

https://t.me/EventAddis1/6236
❤2
📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።

    መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!

https://t.me/EventAddis1/6236
👍6❤1
📌የበጎ ሰው ሽልማት በበጀት እጥረት ሊቋረጥ ተባለ

ላለፉት 12 ዓመታት በዓመቱ መጨረሻ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች ላይ በጎ አስተዋፅኦ ላደርጉ ሰዎች የሚሰጠው ሽልማት ድርጅቱን በሚደግፉ ተቋማት የፋይናንስ እጥረት ሳቢያ የመቋረጥ አደጋ እንዳጋጠው ተነግሯል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማት ላለፉት 10 ዓመታት ስፖንሰር በማድረግ ሽልማቱን ሲደግፍ የቆየው ሄኒከን ኢትዮጵያ የቢራ ማስታውቂያ በብሮድካስት ሚዲያዎች እንዳይተላለፍ መታገዱን ምክንያት በማድረግ የበጎ ሰው ሽልማት መርሃ ግብር በቀጥታ ስርጭት በቴሌቪዥን በሚተላለፍበት ወቅት ሽልማቱን ስፖንስር ከሚያደርግበት በጀት ጋር የማይመጣጠን ማስታስታወቂያ ሽፋን በመሰጠቱ የተነሳ የስፖንሰር ድጋፉን ማቋረጡ ታውቋል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማትን እንደ ቴሌና ንግድ ባንክ ባሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ስፖንስር ለማስደረግና ለማስቀጠል የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ የዘንድሮ የበጎ ሰው ሽልማት ላይካሄድ እንደሚችል ታውቋል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የተመዘገበና በበጎ ፈቃደኛ የቦርድ አባላት የሚተዳደር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ዓመታዊ የሽልማት በጀቱን አሁንም በለጋሾች ድጋፍ ነው የሚያካሂደው፡፡

Via ቁምነገር  ሚዲያ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤6😁4🤔1💔1
📌"የበርበሬ አውሎንፋስ" የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

የደራሲ አበረ ሽፈራው"የበርበሬ አውሎንፋስ” የተሰኘ መጽሐፍ ትላንትና ሀሙስ ሀምሌ 3 2017 በዋልያ መጸሀፍት ቤት አዳራሽ ተመርቋል።

የደራሲ አበረ ሽፈራው “የበርበሬ አውሎንፋስ”፣ የመጀመሪያ መጽሐፉ ሲሆን፣ በስነጽሁፍ መንገድ ላይ ለረጅም ዓመታት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አሻራውን ያኖረ ሰው ነው።

በተጨማሪም ከደራሲ ህይወት እምሻው (ባለቤቱ ናት) ስራዎች ጀርባ የሚደግፋትና የሚያግዛት ቁልፍ ሰው እንደሆነ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍5❤3
📌"ቆይታ ከትዕግስት ዋልታንጉስ ጋራ"

"ቆይታ ከትዕግስት ዋልታንጉስ ጋራ" የተሰኘ በስነ-ልቦና ያተኮረ ልዩ የውይይት ዝግጅት ሊካሄድ ነው።

ይህ ውይይት á‹¨áˆšáŠŤáˆ„á‹°á‹ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሲሆን ጀምሮ የሚካሄድበት ቦታ ደግሞ አዲስ አበባ እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኘው ከቤት እስከ ከተማ ከተማ ማዕከል ውስጥ ነው።

ትዕግስትም ዋልተንጉሥ የስነ ልቦና ባለሙያ ስትሆን ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በአዕምሮ ቁስለት (trauma focused therapy) ላይ በማተኮር ንቁ አገልግሎት  እየሰጠች ያለች ባለሙያ ናት። በ2016 ዓ.ም ለንባብ የበቃው እና 10ኛ ዕትም ላይ የደረሰው  የ "ምን ሆኛለሁ?” መጽሐፍ ተባባሪ ጸሐፊም ናት።

የዚህ ዘግጅት መግቢያው 300 ብር ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤8👍4👎2
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:

1.ጀግና አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ "የኃይሌ ኃይሎች" የተሰኘ መጽሐፍ በልጁ ተጽፎለታል።የኃይሌን ብዙውን የሕይወት ታሪክ ሕዝብ የሚያውቀው ቢሆንም ይሄን መጽሐፍ ምን ለየት ያደርገዋል ? ከልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረስላሴ ያገኘውን መልስ እንነግራችኋለን።

2. ተወዳጁ ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስ በትወና የተሳተፈባቸው ሁለት የተለያዩ ፊልሞች በአንድ ሳምንት ውስጥ ለእይታ ሊበቁ ነው።

3. ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ"ለካ ሰርቻለሁ፣የሀገሬ ሥነጽሑፍ ውስጥ አለሁበት" ሲል የተናገረበትና ሶስት ተከታታይ ድርሰቶቹ በአንድ የተሰበሰቡበት "ዝይን" መጽሐፍ ለአንባቢያን ሊቀርብ ነው።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/D96pVJBAZuY?si=GaREQolLqIOpDB3L

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
❤7👍2👏1
📌ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ነገ ይካሄዳል።

ልዑልሰገድ በየነ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 92ተኛ መድረክ "ፍለጋችን በዘመናችን ውስጥ" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ ነገ ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤1
📌የገጣሚ መላክ ማሩ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

የገጣሚ መላክ ማሩ "መንታ ነፍስ"የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ ነገ ሐምሌ 6 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ታኦስ የባህል አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዕለቱም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በመጽሐፉ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
❤1
📌የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "እንደ አመሌ" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ትላንት አመሻሹን በናሆም ሪከርድስ የዩቲዩብ በኩል ለአድማጮች ቀርቧል።

በ"እንደ አመሌ" ሙዚቃ ላይ በግጥምና ዜማ አብዲ እንዲሁም በቅንብር ብሩክ ተቀባ ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
👍3❤2
📌የአለማየሁ ገላጋይ ሦስት ድርሰቶች ተሰበሰቡ

የደራሲ አለማየሁ ገላጋይ ሦስትያ ድርሰቶች በአንድ የተካተቱበት መጽሐፍ ለአንባቢያን ቀረበ።

በፍቅር ስም ፣ ታለ በእውቀት ስም፣ ሀሰተኛው በእምነት ስም  የተሰኙ ሶስት ተከታታይ ድርሰቶች "ዝይን" በተሰኘ ርዕስ ውስጥ በአንድ እንደተሰባሰቡም ተነግሯል።

የመጽሐፍ አሳታሚ ዋልያ መጽሐፍ ሲሆን በጠንካራ ወረቀት፣ ለማንበብ በሚያመች መልኩ እንደተዘጋጀም ተገልጿል። በተጨማሪም በሀርድ ከቨር 200 መጻሕፍት ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።

ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ በማህበራዊ ትስስር ገፁም “ዝይን" ን ዳጎስ ብላ ስመለከት " ለካ ሰርቻለሁ፣ የሀገሬ ሥነ ጽሁፍ ውስጥ አለሁበት" የሚል ምስክርነት ለራሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰማኝ። አይጣበቅብኝ ፣ ለእብሪት አይዳርገኝ እንጂ አንዳንዴ ይሁን" ሲሉ ተናግሯል።

መጽሐፉ በቅርቡ በተለይ ዝግጅት እንደሚመረቅም አርትስ ስፔሻል ከዋልያ መጻሕፍት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🔥8❤5👍3
📌ኢቫንጋዲ የኢንቴርየር ዲዛይን ስልጠና ጀመረ

ከተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ የሚገኘውና በሁለት ወጣት  ሴት ባለሞያዎች ሜሮን መኮንን እና ህብረወርቅ ገለታ የሚመራው ኢቫንጋዲ ኮንስትራክሽንና ቤተ-ውበት በዚህ ክረምት የኢንቴርየር ዲዛይን ስልጠና በይፋ ጀምሯል።

በተጨማሪም ኢቫንጋዲ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች -

ኢንቴርየር ዲዛይን እስከ ግንባታው

ላንድስኬፕ/የገፀ ምድር/ ዲዛይን

አርክቴክቸራል ዲዛይን

3D Rendering & Modeling

Physical modeling እና ሌሎችም አገልግሎቶች ይገኙበታል።

አድራሻቸው: ሾላ ገበያ ቡና ባንክ ያለበት ህንፃ  አንደኛ ፎቅ ላይ ነው።

ስልኩ ቀጥራቸው ደግሞ

0915416410
0938218123

በቴሌግራም አድራሻቸው @Evangadiconstruction ሊያገኟቸውም ይችላሉ።

የቲክቶክ ቻናል: merryevangadi_interiors

የቴሌግራም ቻናል:https://t.me/Evangadiconstruction1
❤1👍1
📌ከጋዜጦችን ጀርባ ያለ ያልተነገረለት ታታሪ ሰው

የሕትመት ዋጋ መናር ብዙ ጋዜጦችና መፅሔቶችን ከሕትመት ውጪ አድርጓል። እጅግ ተወዳጅ የነበረው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከወር በፊት ሹልክ ብሎ ከገበያ ብዙ ሰው አላስተዋለም።

ያሉትም ጋዜጦች አዲስዘመን፣ ሄራልድ፣ ፎርቹን፣ ካፒታል በገበያ ውስጥ እየተንገዳገዱ ቢቀጥሉም ኮፒያቸውን በመጨመር ተደራሽነታቸውን ለማሳደግ የሕትመት ዋጋ ንረቱ አስሮ አስቀምጧቸዋል።

አንድ ጋዜጠኛ ወዳጄ ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች ለታይታ ያህል እንጂ ኮፒ ጨምሮ ማሳተም ገንዘብን አትሞ ሜዳ ላይ የመርጨት ያህል እንደሚቆጠር አጫውቶኛል።

እንደብርሐኑ ዮሐንስ ዓይነቱ ጋዜጣ አከፋፍሎ ሕይወቱን ለሚገፋ ሰው ይኸ ጉዳይ ይበልጥ አሳሳቢ ነው።

ብርሐኑ የሕመት ኢንደስትሪው በከባድ ወጀብ ውስጥ ባለበትም በዚህ ወቅት ተስፋ ባለመቁረጥ ጋዜጦችን ተሸክሞ ከመነሻው 4 ኪሎ፣ በ 22 ፣በ መገናኛ፣ በቦሌ በእግሩ አቆራርጦ ደንበኞቹ ጋር ያደርሳል።

ጠዋት ማልዶ ተነስቶ እስከ ቀኑ 10:00 አንዳንዴም 11:00 ሰዓት ድረስ መጓዝ የዕለት ተዕለት ሥራው ነው። በዚህ መንገድ ከሚያገኛት በወር 5 ሺህ ብር ገደማ ገቢ ሁለት ልጆቹን እያስተማረ ይገኛል።

ሥራ እንዴት ነው አልኩት።
መጥፎ ነው ብሎ ማማረር አልፈለገም። በአጭሩ "ቀዝቅዟል" አለኝ።
"መቀዝቀዙ ገቢህን ጎድቶታል?"
"አዎን እንደበፊቱ አይደለም" የሚል አጭር ምላሽ ሰጠኝ።

አዎ ብርሐኑ ለዓመታት ከእጅ ወደአፍ በሆነ የጋዜጣ ማዞርና ማከፋፈል ሥራ ውስጥ ቆይቷል። ዛሬም ግን አልደከመውም። ዛሬም ሥራውን ስለማሳደግ አብዝቶ ያስባል።

"ሳይክል ወይንም ሞተር ሳይክል ባገኝ ሥራዬን ለማስፋትና ገቢዬን ለማሳደግ እችላለሁ" አለኝ።

(ፍሬው አበበ)

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤16😢5👍2
📌ድምጻዊ አዲስ ለገሠ አዲስ ሙዚቃ ሊለቅ ነው

የድምጻዊ አዲስ ለገሠ "እቱ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ሐምሌ 5 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በራሱ የዩቲዩብ ቻናል ለሙዚቃ አድማጮች ይደርሳል።

በዚህ የድምጻዊ አዲስ ለገሠ ነጠላ ሙዚቃ ላይ በግጥም ናትናኤል ግርማቸው በዜማ እሱባለው ይታየው (የሺ) እንዲሁም በሙዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ተሳትፈዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
👍3❤1
📌ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን ስራ ተሰጠው

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) በተመቸው ሰዓት ስራ መጀመር እንደሚችል የእሁድ ቤት አዘጋጆች አብስርውታል።

ድንገት ከሚዲያ የጠፋው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን በቅርቡ ፈተና ውስጥ እንደሆነ የሚገልጽ አሳዛኝ ቪዲዮ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ከአሰራጫ በኃላ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ከሰሞኑም ለ40 ቀናት በገዳም የቆየበትን የመታደስና የፈውስ ጉዞ አጠናቆ በሰላም ወደ ቤተሰቡና ልጆቹ መመለሱ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
❤44👏8👍4
ተፈራረሙ !

ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቨንትስ ከኪንግስ እግር ኳስ ቡድን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ሐምሌ 7 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል።

በዚህ ስምምነት መሠረት ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቨንትስ ለኪንግስ እግርኳስ ቡድን á‰Ľá‰¸áŠ› ስፖንሰር በመሆን በጋራ ይሰራሉ ተብሏል።

የኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቨንትስ መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሩት ሐይሉ በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ በስምምነታቸው ደስተኛ መሆናቸውን አስረድተው ውላቸውም ለ6 ወር ያህል እንደሚቆየም ተናግረዋል።

በተጨማሪም በነዚህም ጊዜያቶች በሚደረጉ በየትኛውም ዝግጅቶች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት እንደሆነም ገልጸዋል።

የኪንግስ እግር ኳስ ቡድን ፕሬዘዳንት አቶ አቤኔዘር ሰብስቤ በበኩላቸው ስምምነቱ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል በመጠቆም፤ ከኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቨንትስ ጋር በጋራ መስራታቸው ይበልጥ ጠንክረው እንዲሰሩ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቨንትስ የተለያዩ ዝግጅቶችን በብቃት የሚያዘጋጅ ድርጅት ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህም መንፈሳዊ የመዝሙር ድግሶችን ከማዘጋጀት ባሻገር፤ከተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ዝግጅቶችን ጨምሮ ትላልቅ ሠርጎችን፣ ስብሰባዎችን፣ ምርቃቶችን እና የተለያዩ ኢቨንቶችን በብቃት በመወጣት የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘ ድርጅት ነው።

#ruthailupomi #ሩት_ሀይሉ #elvezetinternationalevents #viralchallenge #fyp
❤3🤔2
📌የ"ልጄስ ?" ድራማ ደራሲና አዘጋጅ ሰማኝጌታ አይችሉህም የክብር እንግዳ የሆነበት ዝግጅት ነገ ይካሄዳል።

ሁለተኛው Creative lab ዝግጅት ደራሲ እና ዳይሬክተር ሰማኝጌታ አይችሉህምን ይዞላችሁ ቀርቧል።

በዚህ ዝግጅት ሰማኝጌታ áˆľáˆˆ "ልጄስ?" ተከታታይ ድራማ አፃፃፍ እንዲሁም ዳይሬክቲንግ ጥበብን ያካፍላል።

ጀማሪ የስክሪፕት ፀሀፊዎች ዳይሬክተሮች በፊልሙ ዓለም ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ወጣት ጀማሪ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛና ዕድል ለእናንተ ነው ተብላችኋል።

በዕለቱ እጅግ ተወዳጅነት ያተረፈውን  የተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ   "ልጄስ?" ፓይለት ኤፒሶድ ይቀርባል። በዚህም ከፊልሙ ጀርባ ያለውን ራዕይ እንዲሁም የስራ ሂደት
በተመለከተ ውይይት ይኖራል ።

📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ( áŠ¨áˆľá‹ľáˆľá‰ľ ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

📅 ቀን: ሃምሌ 8 ፣ 2017

🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00 

🎟 መግቢያ: ነፃ

አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር

📎 በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤10👍1👎1
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ህልውና አሳሳቢ ሆነ

ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አጠቃላይ  እንቅስቃሴ በመዳከሙና ህልውናው አሳሳቢ በመሆኑ ቀጣይ ዕጣ ፈንታቸው እንዳስጨነቃቸው የድርጅቱ ጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡

ማንነታቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የድርጅቱ ጋዜጠኞች ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ በተቋሙ ውስጥ በርካታ ችግሮች እንዳሉ ገልፀው፣ ለአብነትም ደመወዝ በሰዓቱ እንደማይከፈላቸው፣ ይህም ተደጋግሞ የሚስተዋል እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ላለፉት ሦስት አመታት የተቋሙ ፊዚካልና ፋይናንሻል የስራ አፈጻጻም፣ እንዲሁም የሰራተኛውም ሆነ የአመራሩ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዶ እንደማያውቅ የገለፁት ጋዜጠኞቹ "በይፋ ፈርሷል ለመባል ጫፍ ላይ ነው ያለው" በማለት ድርጅቱ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡

የድርጅቱ ባለቤት የነበረው የቀድሞው የደቡብ  ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከፈረሰና አራት የተለያዩ ክልሎች ከተዋቀሩ በኋላ ክልሎቹ እንደየ ድርሻቸው ለተቋሙ በጀት የሚመድቡበት አሰራር የተዘረጋ ቢሆንም ተግባራዊ ባለመሆኑ ችግሮቹ መፈጠራቸውን ተናግረዋል፡፡ 

የሲዳማ ክልል የራሱን ብዙሃን መገናኛ በመመስረቱ በጀት ለመመደብ ፍቃደኛ አለመሆኑን፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሚጠበቅበትን እያዋጣ እንዳለሆነ የሚናገሩት ጋዜጠኞቹ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግን ከሚጠበቅበት በላይ በማዋጣት ለማገዝ እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡

የደቡብ ኢትየጵያ ክልል በበኩሉ ከተመደበለት ኮታ በታች ቢሆንም በጀት እያዋጣ እንደሆነ ጋዜጠኞቹ ተናግረዋል፡፡

በእነዚህና በሌሎችም ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች  ምክንያት ድርጅቱ ህልውናው እንደሚያሰጋና ቀጣይ ዕጣ ፈንታቸው አሳሳቢ መሆኑን ነው ጋዜጠኞቹ የገለፁት፡፡

Via ኢትዮ ኤፍኤም

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5
📌በአለልኝ አዘነ ገዳዮች ላይ ተፈረደ

የእግር ኳስ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ ግድያ የተከሰሱት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል የ16 እና 15  ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው።

በአለልኝ አዘነ ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት ዛሬ የተሰየመዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት አደይ ጌታቸዉና በእህቷ ባል ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ ይህንን ዉሳኔ ያስተላለፈው መጋቢት 17/2016 ዓ/ም በተጋቡ በ15ኛ ቀን አለልኝ አዘነን ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል መግደላቸውን በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች ካረጋገጠ በኋላ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤2
📌የወጣቷ ድምፃዊ ማህሌት ወንድሙ “እድለኛ” አልበም በሰዋሰው በኩል የሚለቀቅበት ቀን ይፋ ሆነ

‘’እሺ አትለኝም ወይ’’ እና ‘’ዝም’’ በሚሉት ሁለት ነጠላ ዜማዎች በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን እና ተቀባይነትን ያገኘችዉ የወጣቷ ድምፃዊ ማህሌት ወንድሙ (ማሂ) የመጀመሪያ አልበም ሀምሌ 18/2017 ዓ.ም ይለቀቃል።

‘’እድለኛ’’ የተሰኘዉ የወጣቷ ድምፃዊ አልበም በሰዋሰዉ መልቲሚዲያ ፕሮዲዩስ የተደረገ ሲሆን የሬከርዲንግ ፕሮዲዩሰሩ ደግሞ ወንዶሰን ይሁብ እንደሆነ ተነግሯል።

በጥቂት ወራት ልዩነት በተከታታይ ሁለት ነጠላ ዜማዎችን በመልቀቅ ከ13 ሚሊየን በላይ ተመልካች በዩቲዩብ ማግኘት የቻለችዉ ድምፃዊ ማህሌት ወንድሙ(ማሂ) በአልበሟም ልዩ ነገር ይዛ ብቅ ስለማለቷ ሰምተናል።

10 ያህል ሙዚቃዎችን የያዘዉ ‘’እድለኛ’’ አልበም የፊታችን አርብ በሰዋሰዉ መተግበሪያ እና የዩቲዩብ ገጽ ይለቀቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤10👍3🥰1
📌የሙዚቃ አቀናባሪው የራሱን የሙዚቃ አልበም ሰራ

በድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ "አስቻለ" አልበም ላይ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ያቀናበረው ቢንአንዴ የራሱን "ነጭ ጤፍ" የተሰኘ አልበም ለአድማጮች ሊያቀርብ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

"ነጭ ጤፍ" የተለያዩ አንጋፋ እና ጀማሪ ድምፃዊያንን፣ ደራሲዎችን እንዲሁም ሙዚቀኞች እንደተሳተፉበት ተገልጿል።

‎የሙዚቃ ስራው ብዙ የተደከመበትና እንዲሁም ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ ያልተለመዱ ፕሮፌሽናል የሙዚቃ ድምፆችን፣ የሙዚቃ ቅንብሮችን እንዲሁም ዜማዎችንና አዛዜሞችን ይዞ እንደቀረበ ተነግሯል።

‎ይህ የሙዚቃ አልበም በቅርቡ በተለያዩ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ለአድማጮች ይቀርባል ተብሏል።

‎ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
❤11👍1
📌"ሰተቴ" ተከታታይ ድራማ ለእይታ ሊበቃ ነው

በመንገደኛው ባለቅኔ ከድር ሰተቴ ላይ መሠረቱን ያደረገ "ሰተቴ" የተሰኘ አዲስ ተከታታይ አስቂኝ ድራማ በአርትስ ቴሌቪዥን ከሐምሌ 20 ጀምሮ ለተመልካቾች መቅረብ እንደሚጀመር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

"ሰተቴ" ተከታታይ አስቂኝ ድራማ ከፍተኛ በጀት ወጥቶበት በከፍተኛ ጥራት የተዘጋጀ ሥራ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በተስፋዬ አየለ (ዶ/ር) ‘መንገደኛው ባለ ቅኔ ከድር ሰተቴ’ በተሰኘ መፅሐፍና በጦቢያ ግጥምን በጃዝ ሲቀርብ በነበረው የአንድ ሰው ቴአትር ላይ ተመርኩዞ በአንተነህ ኃይሌ ዳይሬክተርነት ተመርቶ የሀገራችንን ወጣትና አንጋፋ ተዋናዮችን በማሳተፍ የተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
❤11🔥2👍1😁1