Event Addis Media
9.62K subscribers
6.09K photos
12 videos
4 files
4.71K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌 ሁሉ ስፖርት መኪና ሸለመ!

"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል"ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ የቆይታ ጊዜው ከሰኔ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ አዲስ አበባን ጨምሮ በተመረጡ አራት የክልል ከተሞች ይካሄዳል።

እንዲሁም የተለያዩ የስፖርት ሁነቶችን ለማከናወን ከፍተኛ በጀት መመደቡ ታወቀ። በዛሬው እለትም ሁለገብ online solution በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተዘጋጀውን መተግበሪያ ይፋ ሆኗል ፣ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ልዩ የሁለገብ ቤተሰብ ለሆኑ ተሳታፊዎች ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በተሰጠው ፍቃድ መሰረት ይፋ ተደርጓል።

1- አቶ ለአለም ገብረኪዳን ገብረ መስቀል የBYD SEAGULLየኤሌክትሪክ መኪና
ከመቀሌ
2- አቶ ይብራህ ፈተዊ የኤሌክትሪክ ሳይክል
ከአድዋ
3- አቶ ጫላ ኦላኒ የስማርት ስልክ
ከጋንቤላ
4- አቶ አማኑኤል እዮብ ፕሌይ ስቴሽን
ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ

5- አቶ ምናየው ንጉሴ የስማርት ቴሌቪዥን ሽልማት
ከአርባምንጭ(ጎፋ ወረዳ) ተበርክቶላቸዋል።

የዘንድሮው የ"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል" ሲጀመር በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ሚድያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሲሆን፤ ለደንበኞቹ ይበልጥ ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ የሆነው አዲስ ዌብሳይትም ተዋውቋል።

ዌብሳይታችንን ይጎብኙ
ሁሉ ስፖርት ቤተሰብ ይሁኑ!

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🔥21
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በልጁ መጽሐፍ ተጻፈለት

ከጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተና በልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

ይኸ በሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀው መጽሐፍ በአማርኛ "የኃይሌ ኃይሎች"በእንግሊዝኛ "Dissecting Haile" የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቶታል።

መጽሐፉ የኢትዮጵያዊውን የረጅም ርቀት አትሌት እና ስራ ፈጣሪ የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከእረኝነት ዘመኑ አንስቶ ያለውን ድንቅ ሕይወት፣መርሆች እና ዘላቂ ትሩፋት የሚዳስስ ከመሆኑ ባሻገር ከኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተ መጽሐፍ መሆኑን ደራሲዋ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናግራለች።

አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መጽሐፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነም ተነግሯል።

ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ኃይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ ገልጻለች።

በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ለማሰናዳት አንድ ዓመት እንደፈጀ ተነግሯል።

መጽሐፉ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እንዲሁም በብሬል የተሰናዳ እንደሆነም ተገልጿል።

"የኃይሌ ኃይሎች" ወይም "Dissecting Haile" መጽሐፍ የፊታችን ነሐሴ 2017 ዓ.ም በይፋ ለአንባቢያን የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ማስጀመሪያ ዝግጅት፣ በመቀጠልም ዓለም አቀፍ ደረጃ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

በአማዞን፣ በቴሌብር፣ በተለያዩ የኦንላይን አማራጮችና እንዲሁም መጽሐፍት መሸጫ መደብሮች መፅሀፉ በኤሌክትሮኒክ አማራጮችና በሀርድ ኮፒ ከነሐሴ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በትዕዛዝ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
20👏4🔥3
📌በልጄስ ተከታታይ ድራማ ላይ ባሳየው የትወና ብቃት በርካቶች እያደንቁት የሚገኙት ዳንኤል አሸናፊ የሚተውንበት "ማዘንድ" ፊልም ዛሬ ይመረቃል።

በባሮክ ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ የቀረበው "ማ-ዘንድ" የተሰኘው ፊልም ዛሬ ሰኞ ሰኔ 30 በዓለም ሲኒማ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ታዋቂ የፊልም ባለሞያዎች በተገኙበት በቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርዓት ድምቀት ይመረቃል።

በአንድ የተሳሳተ የአፈና  ወንጀል ታሪክ ውስጥ የፍቅር እና የማህበራዊ ግንኙነቶች መፈራረስን ጭብጡ አድርጎ የተሰራው ፊልም ነው።

የ"ማ ዘንድ" ፊልም አዘጋጅ ብሩክ ተፈራ ሲሆን በፊልሙ ላይ በልጄስ ተከታታይ ድራማ ላይ ባሳየው የትወና ብቃት በርካቶች እያደንቁት የሚገኙት ዳንኤል አሸናፊ (ዳኒ ጺም) ይተውነበታል። በተጨማሪም ቸርነት ፍቃዱ፣ ኑሃሚን መሠረትን ጨምሮ ሌሎችም ተውነውበታል።

ማዘንድ ልብ አንጠልጣይ የወንጀል ፊልም ከተመረቀ በኃላ ሃምሌ 4 5 6 እና 11 12 13 በሁሉም የመንግስት እና የግል ሲኒማ ቤቶች ለእይታ በቃ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
11🔥3👏2👍1
📌የተለያዩ ስልጠናዎች ለስልጠና ፈላጊዎች

(ያልተከፈለበት ማስታወቂያ )

በዚህ ክረምት በጋዜጠኝነት፣ በፊልም፣ በሥነጽሑፍ፣ በግራፊክስና ዲዛይን፣ በስብዕና ግንባታ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች አጫጭር ስልጠናዎችን መውሰድ ከፈለጋችሁ በእዚህ ተቋማት መሰልጠን ትችላላችሁ።

ኤቨንት አዲስ ሚዲያ መልካም የክረምት ስልጠና ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኝላችዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🙏134🔥1👏1
📌ድምጻዊ ምስክር አወል "አዲሱ አልበሜ ያለፈቃዴ ነው የተለቀቀው" ሲል እንባ እየተናነቀው ተናገረ

የድምጻዊ ምስክር አወል አስር የሙዚቃ ስብስቦችን የያዘና "ልቻለው"  የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሙዚቃ አልበም ከወራት በፊት ሀርመኒ መልቲሚዲያ በተባለ የዩቲዩብ ቻናል እንደተለቀቀ ይታወሳል።

ትላንት ሰይፉ ሾው ላይ የቀረበው ድምጻዊ ምስክር አወል "አዲሱ አልበሜ ያለፈቃዴ ነው የተለቀቀው" በማለት እንባ እየተናነቀው ሲናገር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

በተጨማሪ ከዓመታት በኋላ ብዙ ለፍቶ ሙሉ አልበም ቢሰራም ድምጻዊው "ፕሮውዲሰሮቹ" ሲል የሚጠራቸው አካላት ግጥሙን ቆረጠው፣ ጥራት በጎደለው ቅንብር ፣ ያለምንም ማስታወቂያ (ፕሮሞሽን) በአጠቃላይ አልበሙ ሳያልቅ እንደለቀቁበትም ገልጿል።

ድምጻዊ ምስክር አወል ኢትዮጵያ ፣ እያመነሽ ፣ መንታዎቹ በሚሉት ዘፈኖቹ በበርካታ የሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢179💔3👍1
📌የሰርፀ ፍሬስብሐት አዲስ ሹመት

የሙዚቃ ባለሙያ ሰርፀ ፍሬስብሐት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆኖ እንደተሾመ ታወቀ።

ሰርፀ ፍሬስብሐት ከሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾመ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ይፋዊ ትውውቅ ማድረጉን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በፌስቡክ ገጹ ያሰራጨውን መረጃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

ሰርፀ ፍሬስብሐት አስቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ የባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ማገልገሉ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
10👏6🔥3👍2😁2
📌በዓለም ሲኒማ በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።

እሁድ በ12:00 "ከመጋረጃ ጀርባ" ተውኔትም ይቀርባል።

    መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!

https://t.me/EventAddis1/6236
2
📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።

    መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!

https://t.me/EventAddis1/6236
👍61
📌የበጎ ሰው ሽልማት በበጀት እጥረት ሊቋረጥ ተባለ

ላለፉት 12 ዓመታት በዓመቱ መጨረሻ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች ላይ በጎ አስተዋፅኦ ላደርጉ ሰዎች የሚሰጠው ሽልማት ድርጅቱን በሚደግፉ ተቋማት የፋይናንስ እጥረት ሳቢያ የመቋረጥ አደጋ እንዳጋጠው ተነግሯል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማት ላለፉት 10 ዓመታት ስፖንሰር በማድረግ ሽልማቱን ሲደግፍ የቆየው ሄኒከን ኢትዮጵያ የቢራ ማስታውቂያ በብሮድካስት ሚዲያዎች እንዳይተላለፍ መታገዱን ምክንያት በማድረግ የበጎ ሰው ሽልማት መርሃ ግብር በቀጥታ ስርጭት በቴሌቪዥን በሚተላለፍበት ወቅት ሽልማቱን ስፖንስር ከሚያደርግበት በጀት ጋር የማይመጣጠን ማስታስታወቂያ ሽፋን በመሰጠቱ የተነሳ የስፖንሰር ድጋፉን ማቋረጡ ታውቋል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማትን እንደ ቴሌና ንግድ ባንክ ባሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ስፖንስር ለማስደረግና ለማስቀጠል የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ የዘንድሮ የበጎ ሰው ሽልማት ላይካሄድ እንደሚችል ታውቋል፡፡

የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የተመዘገበና በበጎ ፈቃደኛ የቦርድ አባላት የሚተዳደር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ዓመታዊ የሽልማት በጀቱን አሁንም በለጋሾች ድጋፍ ነው የሚያካሂደው፡፡

Via ቁምነገር  ሚዲያ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6😁4🤔1💔1
📌"የበርበሬ አውሎንፋስ" የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

የደራሲ አበረ ሽፈራው"የበርበሬ አውሎንፋስ” የተሰኘ መጽሐፍ ትላንትና ሀሙስ ሀምሌ 3 2017 በዋልያ መጸሀፍት ቤት አዳራሽ ተመርቋል።

የደራሲ አበረ ሽፈራው “የበርበሬ አውሎንፋስ”፣ የመጀመሪያ መጽሐፉ ሲሆን፣ በስነጽሁፍ መንገድ ላይ ለረጅም ዓመታት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አሻራውን ያኖረ ሰው ነው።

በተጨማሪም ከደራሲ ህይወት እምሻው (ባለቤቱ ናት) ስራዎች ጀርባ የሚደግፋትና የሚያግዛት ቁልፍ ሰው እንደሆነ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍53