Event Addis Media
9.62K subscribers
6.09K photos
12 videos
4 files
4.71K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሽልማቱን ተነጠቀ

ሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ለአርቲስት አንዱአለም ጎሳ የሰጠውን ሽልማት እንደነጠቀ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

ፋውንዴሽኔ ሽልማቱን እንዲያነሳ የሚጠይቅ ድምጽ ከሰሞኑ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲስተጋባ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከቀድሞው ባለቤቱ ከሞዴል ቀነኒ ህልፈት ጋር ተያይዞ ስሙ እየተነሳ ያለው ድምጻዊ  አንዷለም እስካሁን  በጉዳዩ ላይ ያለው የሰጠው ምላሽ  የለም፡፡

ድምጻዊው በሞዴል ቀነኒ  ድንገተኛ ህልፈት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ ቢሆንም፣ በፍ/ቤት ጥፋተኛነቱ አለመረጋገጡ ይታወቃል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
19🔥3👎2🤣2
📌"ከመጋረጃው ጀርባ" ተውኔት ነገ ይመለሳል

የቶፊቅ ኑሪ ድርሰት የሆነውና በዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ተዘጋጅቶ ለህዝብ ሲታይ የቆየው “ከመጋረጃ ጀርባ” ኮሜዲ ተውኔት ከአንድ ዓመት በኃላ ነገ እሁድ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በ12:00 ሰዓት አለም ሲኒማ ዳግም ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

ወቅታዊ ጉዳዮችን እያዋዛ በማቅረብ የሚታወቀው "ከመጋረጃ ጀርባ" ቴአትር ቀድሞ የነበረውን ይዘት ሳይለቅ እንዲሁም ከገሊላ ርዕሶም በስተቀር የነበሩትን ተዋናዮች በሙሉ ይዞ ዳግም ወደ ተመልካች ይደርሳል ተብሏል።

ተዋናይት ገሊላ ርዕሶም  የምትጫወታትን ገፀባህሪ የምስራች ግርማ  ተክታ እንደምትጫወትም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6🥰1
📌 ሁሉ ስፖርት መኪና ሸለመ!

"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል"ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ የቆይታ ጊዜው ከሰኔ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ አዲስ አበባን ጨምሮ በተመረጡ አራት የክልል ከተሞች ይካሄዳል።

እንዲሁም የተለያዩ የስፖርት ሁነቶችን ለማከናወን ከፍተኛ በጀት መመደቡ ታወቀ። በዛሬው እለትም ሁለገብ online solution በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተዘጋጀውን መተግበሪያ ይፋ ሆኗል ፣ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ልዩ የሁለገብ ቤተሰብ ለሆኑ ተሳታፊዎች ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በተሰጠው ፍቃድ መሰረት ይፋ ተደርጓል።

1- አቶ ለአለም ገብረኪዳን ገብረ መስቀል የBYD SEAGULLየኤሌክትሪክ መኪና
ከመቀሌ
2- አቶ ይብራህ ፈተዊ የኤሌክትሪክ ሳይክል
ከአድዋ
3- አቶ ጫላ ኦላኒ የስማርት ስልክ
ከጋንቤላ
4- አቶ አማኑኤል እዮብ ፕሌይ ስቴሽን
ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ

5- አቶ ምናየው ንጉሴ የስማርት ቴሌቪዥን ሽልማት
ከአርባምንጭ(ጎፋ ወረዳ) ተበርክቶላቸዋል።

የዘንድሮው የ"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል" ሲጀመር በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ሚድያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሲሆን፤ ለደንበኞቹ ይበልጥ ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ የሆነው አዲስ ዌብሳይትም ተዋውቋል።

ዌብሳይታችንን ይጎብኙ
ሁሉ ስፖርት ቤተሰብ ይሁኑ!

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🔥21
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በልጁ መጽሐፍ ተጻፈለት

ከጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተና በልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

ይኸ በሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተዘጋጀው መጽሐፍ በአማርኛ "የኃይሌ ኃይሎች"በእንግሊዝኛ "Dissecting Haile" የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቶታል።

መጽሐፉ የኢትዮጵያዊውን የረጅም ርቀት አትሌት እና ስራ ፈጣሪ የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከእረኝነት ዘመኑ አንስቶ ያለውን ድንቅ ሕይወት፣መርሆች እና ዘላቂ ትሩፋት የሚዳስስ ከመሆኑ ባሻገር ከኃይሌ ገብረሥላሴ ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተ መጽሐፍ መሆኑን ደራሲዋ ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናግራለች።

አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መጽሐፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነም ተነግሯል።

ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ኃይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ገብረሥላሴ ገልጻለች።

በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ለማሰናዳት አንድ ዓመት እንደፈጀ ተነግሯል።

መጽሐፉ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እንዲሁም በብሬል የተሰናዳ እንደሆነም ተገልጿል።

"የኃይሌ ኃይሎች" ወይም "Dissecting Haile" መጽሐፍ የፊታችን ነሐሴ 2017 ዓ.ም በይፋ ለአንባቢያን የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ማስጀመሪያ ዝግጅት፣ በመቀጠልም ዓለም አቀፍ ደረጃ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

በአማዞን፣ በቴሌብር፣ በተለያዩ የኦንላይን አማራጮችና እንዲሁም መጽሐፍት መሸጫ መደብሮች መፅሀፉ በኤሌክትሮኒክ አማራጮችና በሀርድ ኮፒ ከነሐሴ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በትዕዛዝ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
20👏4🔥3
📌በልጄስ ተከታታይ ድራማ ላይ ባሳየው የትወና ብቃት በርካቶች እያደንቁት የሚገኙት ዳንኤል አሸናፊ የሚተውንበት "ማዘንድ" ፊልም ዛሬ ይመረቃል።

በባሮክ ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ የቀረበው "ማ-ዘንድ" የተሰኘው ፊልም ዛሬ ሰኞ ሰኔ 30 በዓለም ሲኒማ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ታዋቂ የፊልም ባለሞያዎች በተገኙበት በቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርዓት ድምቀት ይመረቃል።

በአንድ የተሳሳተ የአፈና  ወንጀል ታሪክ ውስጥ የፍቅር እና የማህበራዊ ግንኙነቶች መፈራረስን ጭብጡ አድርጎ የተሰራው ፊልም ነው።

የ"ማ ዘንድ" ፊልም አዘጋጅ ብሩክ ተፈራ ሲሆን በፊልሙ ላይ በልጄስ ተከታታይ ድራማ ላይ ባሳየው የትወና ብቃት በርካቶች እያደንቁት የሚገኙት ዳንኤል አሸናፊ (ዳኒ ጺም) ይተውነበታል። በተጨማሪም ቸርነት ፍቃዱ፣ ኑሃሚን መሠረትን ጨምሮ ሌሎችም ተውነውበታል።

ማዘንድ ልብ አንጠልጣይ የወንጀል ፊልም ከተመረቀ በኃላ ሃምሌ 4 5 6 እና 11 12 13 በሁሉም የመንግስት እና የግል ሲኒማ ቤቶች ለእይታ በቃ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
11🔥3👏2👍1
📌የተለያዩ ስልጠናዎች ለስልጠና ፈላጊዎች

(ያልተከፈለበት ማስታወቂያ )

በዚህ ክረምት በጋዜጠኝነት፣ በፊልም፣ በሥነጽሑፍ፣ በግራፊክስና ዲዛይን፣ በስብዕና ግንባታ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች አጫጭር ስልጠናዎችን መውሰድ ከፈለጋችሁ በእዚህ ተቋማት መሰልጠን ትችላላችሁ።

ኤቨንት አዲስ ሚዲያ መልካም የክረምት ስልጠና ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኝላችዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🙏134🔥1👏1
📌ድምጻዊ ምስክር አወል "አዲሱ አልበሜ ያለፈቃዴ ነው የተለቀቀው" ሲል እንባ እየተናነቀው ተናገረ

የድምጻዊ ምስክር አወል አስር የሙዚቃ ስብስቦችን የያዘና "ልቻለው"  የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሙዚቃ አልበም ከወራት በፊት ሀርመኒ መልቲሚዲያ በተባለ የዩቲዩብ ቻናል እንደተለቀቀ ይታወሳል።

ትላንት ሰይፉ ሾው ላይ የቀረበው ድምጻዊ ምስክር አወል "አዲሱ አልበሜ ያለፈቃዴ ነው የተለቀቀው" በማለት እንባ እየተናነቀው ሲናገር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

በተጨማሪ ከዓመታት በኋላ ብዙ ለፍቶ ሙሉ አልበም ቢሰራም ድምጻዊው "ፕሮውዲሰሮቹ" ሲል የሚጠራቸው አካላት ግጥሙን ቆረጠው፣ ጥራት በጎደለው ቅንብር ፣ ያለምንም ማስታወቂያ (ፕሮሞሽን) በአጠቃላይ አልበሙ ሳያልቅ እንደለቀቁበትም ገልጿል።

ድምጻዊ ምስክር አወል ኢትዮጵያ ፣ እያመነሽ ፣ መንታዎቹ በሚሉት ዘፈኖቹ በበርካታ የሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢179💔3👍1
📌የሰርፀ ፍሬስብሐት አዲስ ሹመት

የሙዚቃ ባለሙያ ሰርፀ ፍሬስብሐት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆኖ እንደተሾመ ታወቀ።

ሰርፀ ፍሬስብሐት ከሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾመ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ይፋዊ ትውውቅ ማድረጉን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በፌስቡክ ገጹ ያሰራጨውን መረጃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

ሰርፀ ፍሬስብሐት አስቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ የባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ማገልገሉ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
10👏6🔥3👍2😁2