📌 የሪፖርተር ጋዜጠኛ ታሰረ
የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አበበ ፍቅር ታሰረ፡፡ ጋዜጠኛ አበበ የታሰረው ትናንት ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት አካባቢ ነው፡፡
ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው ከልደታ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎች መረጃ በማሰባሰብ ላይ እያለ ሲሆን፣ የታሰረበት ምክንያት እስካሁን ግልጽ አልሆነም፡፡ ጋዜጠኛ አበበ በዕለቱ በፖሊሶች ተይዞ ከመወሰዱ በስተቀር በወቅቱ ወዴት እንደተወሰደና እንደታሰረ ባለመታወቁ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት በማድረግ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባደረገው ትብብር ጋዜጠኛው በልደታ ክፍል ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጌጃ ሰፈር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ ታውቋል፡፡
ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው እየሠራው ለነበረው ዘገባ ሚዛኑን ለመጠበቅ፣ የክፍለ ከተማውን ኃላፊዎች ለማነጋገር በሥፍራው በተገኘበት ወቅት ነበር፡፡
ዘገባው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1

👍2
📌"ነገረ መጻሕፍት" ውይይት ነገ ይካሄዳል
የነገረ መጻሕፍት አዘጋጆችና ታደሚያን ቅዳሜ "ቀይ ባህር ሲቀላ " በተሰኘ መጽሐፍ ላይ ይወያያሉ።በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት ነገ ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ሳምንት የተመረጠው መጽሐፍ "ቀይ ባህር ሲቀላ " የተሰኘ መጽሐፍ ሲሆን በክብር እንግዳነት የመጸሐፉ ፀሐፊ ዶ/ር ፍርድአወቀ ማሞ ይገኛሉ ተብሏል። የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

📌"ህልም እልም" የሥዕል አውደርዕይ ሰኞ ይከፈታል
የሠዓሊ ስዩም አያሌው የሥዕል ስራዎች የሚቀረቡበት "ህልም እልም " የሥዕል አውደርዕይ የፊታችን ሰኞ ሚያዝያ 20 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ግንቦት 4 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
የሠዓሊ ስዩም አያሌው የሥዕል ስራዎች የሚቀረቡበት "ህልም እልም " የሥዕል አውደርዕይ የፊታችን ሰኞ ሚያዝያ 20 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ግንቦት 4 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌አድማስ የሙዚቃ ባንድ ከአርባ አንድ ዓመት በኋላ ወደ መድረክ ላይ ሊወጣ እንደሆነ ተገለፀ
የፊታችን ሚያዚያ 25 እና 26 2017 ዓ.ም በሚከበረው የኢትዮጵያ የጃዝ ፌስቲቫል ላይ ከ41 ዓመታት በኋላ አበጋዝ ክብረወርቅን፣ ሔኖክ ተመስገን፣ ቴድሮስ አክሊሉን እና ግሩም መዝሙርን ያቀፈው አድማስ ባንድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራዎቹን ያቀርባል፡፡
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ፣ አ.አ ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ እና ሳይ ሪኮርድስ በጋራ የሚያዘጋጁት ሁለተኛው የዓለም የሥነጥበብ ቀን እና የኢትዮጵያ ጃዝ ፌስቲቫል ከሚያዚያ 21 2017 ጀምሮ ከአለ ሥነጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት የተሰባሰቡ የቆዩ ሥዕሎችና ከሠዓሊያን ማኅበር የተገኙ የዘመኑ ስዕሎች ተዋኅደው የሚታዩበት አውደርዕይ የሚከፈት ሲሆን የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ሚያዚያ 25 እና 26 ከ7፡00 ጀምሮ ደግሞ የሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር የሚመጡ የጃዝ ሙዚቀኞች ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ለሁለተኛ ጊዜ በሚዘጋጀው ታላቅ ዝግጅት ላይ ከአድማስ ባንድ በተጨማሪ ነጋሪት ባንድ፣ አስሊ ባንድ፣ መሐሪ ብራዘርስ ባንድ፣ ሳሙኤል ይርጋ እና ሌሎች ከሀገር ውስጥ ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ዘሯ ከኢትዮጵያ የሚመዘዘው ትውልደ እስራኤላዊት ሔዋን መሸሻ እና ዚምባቡዌያዊቷ ናሲቦ ሙቲዚ (ናንሲ) መድረኩን ያስውቡታል፡፡
ከሚያዚያ 21 2017 ጀምሮ ለሳምንታት ለዕይታ የሚቀርበውን የሥዕል ትርኢት በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ ለሁሉም ሰው ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ታዳጊ ህጻናት ራሳቸውን ከሥነጥበብ ጋር የሚያቆራኙበት መርሐግብርም የፌስቲቫሉ አካል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በዝግጅ ላይ ለመታደም ትኬቱ ቴሌ ብር ላይ የሚገኝ በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:
1.ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) በእስራኤል የነፃነት ቀን በቴሌቪብ የሙዚቃ ኮንሰርቱን እንደሚያቀርብ ይፋ ካደረገ በኃላ ተቃዋሞ እና ድጋፍ ገጠመው።
2.የአዲስ አበባው የጣይቱ የባህልና ትምህርት ማዕከል ነገ በድማቅ ሥነሥርዓት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው።
3.የዝነኛዋ ፎቶግራፍ አይደ ሙሉነህ የፎቶግራፍ አውደርዕይ በይፋ ተከፈተ።
4."በይው ተቀየረ እንጂ ትሪው አልተነሳም" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ነገ ይከፈታል።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/wLacEyqFBHY?si=J5xScqMLoLe-9xnF
📌መልካም ምሽት
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

❤1
📌የ50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ በአዲስ አበባ ኮንሰርቶች
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በሀገሪቱ ውስጥ የመዝናኛ እና የዕድል ፍላጎትን ለማጣጣም በሚያስችል አዲስ እና ትኩረት የሚስብ አካሄድ ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በመተባበር በነገው እለት በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄዱ ሶስት ታዋቂ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ተከትሎ የፊታችን ግንቦት ወር የሚወጣውን 50 ሚሊዮን ሎተሪ እንደሚያስተዋውቅ ገለጸ።
በሙዚቃ ኮንሰርት ታዳሚዎች በመዝናናታቸው ጎን ለጎን የ50 ሚሊዮን ብር ግዙፍ ሎተሪ የመቁረጥ ዕድል ይኖራቸዋል ተብሏል።
ዛሬ በሚደረጉ ሶስቱም ኮንሰርቶች ላይ ለሚሳተፋ በነፃ ለሚመዘገቡ ባለዕድለኞች የ50,000 (የሃምሳ ሺህ ብር) ሽልማትም ቀርቧል።
ይህ ልዩ ዕድል ሽልማት ዛሬ በሚካሄዱት በሚሊኒየም አዳራሽ ሽርጉድ ኮንሰርት ፣ በግዮን ሆቴል ልዑል ኮንሰርት እና በማርዮት ሆቴል በሚካሄደው ኤሌጋንስ ኮንሰርቶች ላይ የሚሳተፉትን ተሳታፊዎች ሎተሪ በመቁረጥ በEthiolottery.et ድረ ገጽ ላይ በመመዝገብ በቀላሉ እድለኛ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አሳውቋል።

👍3
📌"በይው ተቀየረ እንጂ ትሪው አልተነሳም"
የሠዓሊ አሸናፊ መስቲካ የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "በይው ተቀየረ እንጂ ትሪው አልተነሳም" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ባሳፍነው ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ ብራስ አካባቢ በሚገኘው አርታዊ የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ በቅቷል።
ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድርስ እንደሚቆይ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የሠዓሊ አሸናፊ መስቲካ የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "በይው ተቀየረ እንጂ ትሪው አልተነሳም" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ባሳፍነው ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ ብራስ አካባቢ በሚገኘው አርታዊ የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ በቅቷል።
ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድርስ እንደሚቆይ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏5👍2❤1
📌የአይዳ ሙሉነህ የፎቶግራፍ ዓውደርዕይ
በአይዳ ሙሉነህ ተዘጋጅቶ በ ዘ-ኢንድ ፈንድ አዘጋጅነት እና በሪቺንግ ዘ-ላስት ማይል ድጋፍ ለህዝብ የቀረበው ሪፍሬሚንግ ኔግሌክት የተሰኘ የፎቶ ዓውደ-ርዕይ ተከፈተ፡፡
በዓውደ-ርዕዩ አይዳ ሙሉነህን ጨምሮ የሰባት አፍሪካዊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ስራ ስብስብ የቀረበ ሲሆን በዋነኝነትም ደሀ ከሚባሉ አገራት ውስጥ ከሚከሰቱ በሽታዎች ያላቸውን ማህበራዊ እና ኢኮሚያዊ ጫና ለተመልካች ለማቅረብና የአፍሪካዊያንን ድምፅ ለአለም ለማሰማት የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በስራዎቻቸው ጠንካራ ታሪክን በፎቶ የማስቀረት እና ማህረሰቡ የሚያልፍበትን እውነታ የማንፀባረቅ ድንቅ ችሎታ ያላቸው የስድስት አፍሪካዊ ባለሙያዎች 54 የስነጥበብ ስራዎችና ዘጋቢ‐ፎቶዎች የተካተተበት ዓውደ-ርዕይ ስነ-ጥበብ ምን ያህል ወሳኝ ጉዳዮችን የማጉላት ትልቅ አቅም እንዳለው ያሳያሉ ተብሏል፡፡
እ.ኤ.አ በ2022 ተጀምሮ በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በአፍሪካ 2.8 ሚሊዮን ሰዎችን ተደራሽ ያደረገው ይሄው ዓውደ-ርዕይ በታላቅ ክብረበአል ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰአት ጀምሮ እስከ ግንቦት 19 2017ዓ.ም በገብረክርስቶስ ደስታ ማዕከል ለተመልካች ክፍት ይሆናል፡፡

❤7👍7
📌ቴዲ አፍሮ በስምንት ሙዚቃዎች ላይ በግጥምና ዜማ የተሳተፈበት የአንጋፋዋ ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ "ደጃዝማች" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም የፊታችን አርብ ይለቀቃል
ይህ የአንጋፋዋ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ "ደጃዝማች" የተሰኘ ስምንተኛ አዲስ የሙዚቃ አልበም ላይ አስራ ሶስት ሙዚቃዎችን ይዟል።
ከእነዚህ አስራ ሶስት ሙዚቃዎች ውስጥ የስምንቱ ሙዚቃዎች ግጥምና ዜማ የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ / ሲሆን ሌሎቹን ሙዚቃዎች ደግሞ በግጥም ገጣሚ ይልማ ገብረአብ፣ገጣሚ መሰለ አስማማው፣ ገጣሚ ናትናኤል ግርማቸው የሰሩ ሲሆኑ ሞገስ ተካ እና ምስክር አወል ግጥምና ዜማ በመስራት በአልበሙ ላይ ተሳትፈዋል።
ከተቀሩት ስራዎች ውስጥ "ወለላዬ" የተሰኘው ሙዚቃ ደግሞ የኩኩ የድሮ ሙዚቃ ሲሆን ቴዲ ማክ እንደገና ሪአሬንጅ /Re Arrange/ አድርጎ የሰራው ሙዚቃ ነው።
የድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ " ደጃዝማች" በተሰኘው አዲስ አልበም ላይ ስመጥር የሆነ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት ሲሆን የሙዚቃ አቀናባሪው አቤል ጳውሎስ ዘጠኙን ሙዚቃዎች በማቀናበር እንዲሁም አስራ አንዱን ሙዚቃዎች ሚክስ በማድረግ ተሳትፏል።
ሁለቱን ሙዚቃዎች አሬንጅ ያደረገው ማሩ ዓለማየሁ ሲሆን ሙዚቀኛ ያሬድ ተፈራ፣ ሙዚቀኛ አክሊሉ ወ/ዩሐንስ (ጆኒ ሳክስ) እና ሙዚቀኛ ዘሪሁን በለጠ በሳክስፎን፣ግሩም መዝሙር እና ሳሙኤል አሰፋ በጊታር ተሳትፈዋል።
"ደጃዝማች"ን ሙሉውን አልበም ማስተር ሳውንዱን /Sound Mastering/የሰራው ኪሩቤል ተስፋዬ ነው።
"ደጃዝማች" የተሰኘ ስምንተኛ አልበም የፊታችን አርብ ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በራሷ ዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል።

❤14👍9👏1
📌ድምጻዊ ልዑል ሲሳይ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ይቀርባል
(መግቢያው በነፃ ነው)
የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር ልዑል ሲሳይን ጋብዟል::
የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች"ከልዑል ጋር በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን ማክሰኞ ሚያዚያ 28, 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ ገለጸዋል።
በዕለቱ ከድምጻዊ ልዑል ሲሳይ ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::
ፕሪስቴጅ አዲስ ከልዑል ሲሳይ ጋር የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ ማክሰኞ ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:
📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

👍7❤3
📌የድምጻዊት ዘቢባ ግርማ "እንደምንም" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነው
አንጋፋውና ወጣት የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት “እንደምንም" የሙዚቃ አልበም 13 ሙዚቃዎችን በውስጡ የያዘ ሲሆን አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አምስት ዓመት እንዲወሰድባትም ተነግሯል።
ለአልበሙ ላይ የሦስት የሙዚቃ ቪዲዮዎች ተሰርቶ የተጠናቀቁ ሲሆን ይህ አልበም ሙሉ በሙሉ በድምጻዊት ዘቢባ ግርማ ፕሮዲዩስ ተደርጓል፡፡
የሙዚቃ አልበሙ ስለ ፍቅር፤ ስለ ምስጋና እና ስለ እናት እና የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል።
የድምጻዊት ዘቢባ ግርሓጨ"እንደምንም" የተሰኘው አልበም የፊታችን አርብ ግንቦት አንድ በዘቢባ ግርማ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች አማካኝነት ለአድማጮች ይቀርባል።

👍1
📌የአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ አውደርዕይ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ 17ኛውን ዓመታዊ የመጽሐፍ አውደ-ርዕይ ከሚያዚያ 28 እስከ ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ስድስት ኪሎ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ውስጥ ያካሂዳል።
በነዚህ ቀናት በዩኒቨርሲቲው በመገኘት አውደርዕዩን ጎብኙ፣መጽሐፍት ግዙ፣ስለ ንባብ ተወያዩ ተብላችኋል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ 17ኛውን ዓመታዊ የመጽሐፍ አውደ-ርዕይ ከሚያዚያ 28 እስከ ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ስድስት ኪሎ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ውስጥ ያካሂዳል።
በነዚህ ቀናት በዩኒቨርሲቲው በመገኘት አውደርዕዩን ጎብኙ፣መጽሐፍት ግዙ፣ስለ ንባብ ተወያዩ ተብላችኋል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
❤7👍2👏1
📌ፈስቲቫሉን ላይ በነፃ ይታደሙ
ቅዳሜ እና እሁድ ሚያዝያ 25 እና 26 2017 ዓ.ም የሚደረገው የዓለም የጥበብ ቀን እና የኢትዮጵያ ጃዝ ፌስቲቫል መግቢያ በነፃ ሆኗል።
የዓለም አቀፍ የሥነጥበብ ቀን እና የኢትዮጵያ ጃዝ ፌስቲቫል ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሚያዚያ 25 እና 26 2017 ይከናወናል፡፡ የዘንድሮው ፌስቲቫል ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ታዋቂና ተወዳጅ የሆኑ ሙዚቀኞችን ያሳተፈ እንደሆነ ተነግሯል።
በዚህ ዓመት ፌስቲቫል ላይ ለኢትዮ-ጃዝ አባት ለታዋቂው ሙላቱ አስታጥቄ በዘርፉ ላበረከቱት ፈር ቀዳጅ ሥራቸውና እና በዓለም የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ላኖሩት ሙዚቃዊ ትሩፋት ክብር የሚሰጥበት እንደሆነም ተገልጿል።
በተጨማሪም በፌስቲቫሉ ላይ ከ41 ዓመታት በኃላ አድማስ ባንድ የሙዚቃ ዝግጅቱን ያቀርባል ተብሏል።
ዝግጅቱ ቅዳሜ ሚያዚያ 25 እና እሁድ ሚያዚያ 26 2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ከቀኑ 7፡00 እስከ ምሽት 1፡00 በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ውስጥ ይካሄዳል።
አዘጋጆቹ የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚና SAY Records ናቸው።

❤6👍3
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
1. ድምጻዊ ብስራት ሱራፌል ለአንደኛ ደረጃ ት/ቤት መምህሩ ያዜመበትን ሙዚቃ ጨምሮ 6 የሙዚቃ ስብስቦችን የያዘው "የጠይም ፈረንጅ" የሙዚቃ አልበምን ለአድማጮች አቀረበ።
2.ሁለት ጎራ ክፍሎ ሲያነጋገር የቆየው የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት ከትላንትና በስቲያ በእስራኤል ቴላቪቭ ተካሄደ። በሌላ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በ8 ሙዚቃዎች ላይ በግጥምና የተሳተፈበት የአንጋፋዋ ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ አልበም ዛሬ አመሻሹን ለአድማጮች ቀረበ።
3.በመድረክ መሪና ጋዜጠኛ ወንድወሰን ከበደ የተዘጋጀው "የመድረክ ማስታወሻ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።
4.ኢትዮጵያዊቷ በአሜሪካ ትልቅ የሥነጽሑፍ ሽልማት ተሸለመች።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/c6JUGt_BOl0?si=M28Ec0VbDN6xYOBs

👍6
📌የኢትዮፒካር እና አሚጎስ ጥምረት
ኢትዮፒካር መኪና አስመጪ ከአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ጋር በመተባበር፣ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዘመናዊ መኪኖችን ለ15 ደንበኞች ማስረከባቸውን ዛሬ ሚያዝያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮፒካር ዋና መ/ቤት በተካሄደ ሥነሥርዓት ላይ አስታውቀዋል።
በኢትዮፒካር በቀጥታ ግዢ እንዲሁም በባንክ ብድር አማራጭ እየቀረቡ የሚገኙት እነዚህ የኤሌክትሪክ መኪኖች የፋብሪካ ዋስትና እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፤እስካሁንም ከ1000 በላይ ለሚሆኑ ፈላጊዎች ከባንክ እንዲሁም ከብድርና ቁጠባ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ውል በመግባት መኪኖቹን ማስረከቡን የኢትዮፒካር ማርኬቲንግ ኃላፊ ወወይዘሪት አቤኔዘር ደበበ ገለጸዋል።
ኢትዮፒካር መኪኖቹን የሚሸጠው ከባትሪና መለዋወጫ ዕቃዎች ዋስትና ጋር መሆኑን የጠቆሙት የማርኬቲንግ ኃላፊዋ፤ በቻይና በ3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሞዴል መኪኖችን እንደሚያስመጣ ተናገረዋል።
አሚጎስ ከኢትዮፒካር ጋር ስምምነት ከፈጸመ ወዲህ ቅድመ ቁጠባውን ላሟሉ 100 ደንበኞቻቸው የኤሌክትሪክ መኪኖችን ያስረከቡ ሲሆን፤ እስከ መጪው ሰኔ 30 ባለው ጊዜም 50 ለሚደርሱ ደንበኞች መኪኖችን ለማስረከብ መታቀዱም ተነግሯል።

👍5🔥1
📌የሮፍናን ኮንሰርት ጋምቤላ ሊካሄድ ነው
የሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ"የኔ ትውልድ " የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 2 2017 ዓ.ም በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።
ይህ የሮፍናን የሙዚቃ ኮንሰርት በጋምቤላ ስታዲየም እንደሚካሄድም ሙዚቀኛው በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ"የኔ ትውልድ " የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 2 2017 ዓ.ም በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።
ይህ የሮፍናን የሙዚቃ ኮንሰርት በጋምቤላ ስታዲየም እንደሚካሄድም ሙዚቀኛው በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🔥6👍2❤1🥰1
📌"ቍናማት" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
በገጣሚ ሐዋዝ የሻነህ የተዘጋጀው "ቍናማት" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት ለንባብ በቅቷል።
መጽሐፉ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ205 ገፆች ተቀንብቦ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።
ገጣሚና ደራሲ ሐዋዝ የሻነህ ከዚህ መጽሐፍ አስቀድሞ "ኢካቦድ"የግጥም ስብስብ)፣ "የአዳም ፊርማ" እና "ሰውነት" የተሰኘ ረጅም ልቦለድ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቷል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
በገጣሚ ሐዋዝ የሻነህ የተዘጋጀው "ቍናማት" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት ለንባብ በቅቷል።
መጽሐፉ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ205 ገፆች ተቀንብቦ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።
ገጣሚና ደራሲ ሐዋዝ የሻነህ ከዚህ መጽሐፍ አስቀድሞ "ኢካቦድ"የግጥም ስብስብ)፣ "የአዳም ፊርማ" እና "ሰውነት" የተሰኘ ረጅም ልቦለድ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቷል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5🔥2
📌"ለጋስ አድማስ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው
በገጣሚ ወልደገብርኤል ደሳለኝ(ወገደ) የተዘጋጀው "ለጋስ አድማስ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ በቅርቡ ንባብ ይበቃል ተብሏል።
"ለጋስ አድማስ" የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ350 ብር በቅደመ ሽያጭ ለአንባቢያን ይቀርባል።
መጽሐፉን መግዛት ለሚፈልጉ የባንክ ቁጥር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፦ 1000530618661
ወልደገብርኤል ደሳለኝ
ቴሌ ብር ፦0992269755
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
በገጣሚ ወልደገብርኤል ደሳለኝ(ወገደ) የተዘጋጀው "ለጋስ አድማስ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ በቅርቡ ንባብ ይበቃል ተብሏል።
"ለጋስ አድማስ" የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ350 ብር በቅደመ ሽያጭ ለአንባቢያን ይቀርባል።
መጽሐፉን መግዛት ለሚፈልጉ የባንክ ቁጥር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፦ 1000530618661
ወልደገብርኤል ደሳለኝ
ቴሌ ብር ፦0992269755
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤3👍3
“የአፍሪካ ቀንድ” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው
“የአፍሪካ ቀንድ” የተሰኘው መጽሐፍ በመጪው አርብ ገበያ ላይ ይውላል ተብሏል።
በታዋቂው የአፍሪካ ቀንድ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ተመራማሪ በሆኑት ፕሮፌሰር ክርስቶፈር ክላፋም ተጽፎ፣ በጋዜጠኛ ኅይለመስቀል በሸዋምየለህ ወደ አማርኛ የተመለሰው ይኽ መጽሐፍ፣ በ231 ገጾች ተቀንብቦ በ450 ብር እንደሚሸጥ ሰምተናል።
መጽሐፉ፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ ባሏቸው ፖለቲካዊ ግንኙነቶች ላይ አተኩሮ፣ የመጪውን የቀንዱን ዕጣ ፈንታም ይዳስሳል ተብሏል።
መጽሐፉ በኹሉም የጃፋር መጽሐፍት ቤቶች እንደሚገኝም ተነግሯል።

👍13❤1🔥1