Event Addis Media
9.63K subscribers
6.09K photos
12 videos
4 files
4.71K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ሁለት ግዙፉ አውደርዕዮች በአንድ ሳምንት

በአንድ ሳምንት á‰ á‰°áŠ¨á‰łá‰łá‹­ ቀናት የሚካሄዱት አውደርዕዮች አርት ኦፍ ኢትዮጵያ እና The Big Art Sale ናቸው።

በሸራተን አዲስ በየዓመቱ ይካሄድ የነበረውና በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ለአምስት አመታት ተቋርጦ የነበረው Art of Ethiopia  የሥነጥበብ አውደርዕይ ዘንድሮ ተመልሷል።

ከአምስት በኃላ በተዘጋጀው በዚህ አውደርዕይ ላይ 62 ሠዓልያን የሥዕል ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ሚያዚያ 2 እና 3 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ይካሄዳል።

በሌላ በኩል The Big Art Sale
በሒልተን ሆቴል ቅፅር ግቢ ውስጥ ሚያዚያ 4 እና 5 2017 ዓ.ም  የሚካሄደው ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ከ200 ሠዓሊያን የሥነጥበብ ሥራዎቻቸውን ለሽያጭ ይቀርባሉ።

ዝግጅቶቹን What's out Addis ከሸራተን አዲስ፣ ከሂልተን ሆቴልና ከካልቸር ክለብ ጋር በመጣመር አሰናድተውታል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌የአስቻለው ፈጠነ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው

በእናትዋ ጎንደር፣ካሲናው ጎጃም፣ አሞራው ካሞራ በተሰኙ áŠáŒ áˆ‹ ዜማዎች ተወዳጅነትን ያተረፈው "አስቻለ"የተሰኘው አልበም ከአንድ ዓመት በፊት ለሙዚቃ አፍቃሪው ያደረሰው ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ( አርዲ) የሙዚቃ ኮንሰርት በእስራኤል ሀገር  ሊያቀርብ እንደሆነ ገልጿል።

አርትስ ስፔሻል ከድምጻዊ እንዳገኘው መረጃ ከሆነ የሙዚቃ ዝግጅቱ ከፋሲካ በኃላ በፈረንጆቹ ሜይ 15 2025 በቴላቪብ  እንደሚካሄድ ተነግሯል።

ድምጻዊ አስቻው ፈጠነ የሙዚቃ ኮንሰርት በእስራኤል ካቀረበ በኃላ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት የሙዚቃ ዝግጅቱን እንደሚያቀርብ ድምጻዊው ለአርትስ ስፔሻል ገልጿል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌አምስተኛው የጣፋጭ ሕይወት ምስጋና

በጣፋጭ ህይወት መልቲሚዲያ በየዓመቱ የሚዘጋጅው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ዝግጅት ዘንድሮው ለአምስተኛ ጊዜ ይካሄዳል።

አምስተኛው ምን ምን አዲስ ነገር ይዟል?ምንስ ክንውኖች ይኖሩታል ?

በዚህ መርሐግብር የጣፋጭ ሕይወት የፓናል ውይይት ሚያዝያ 30፣የቤተሰብ ፌስቲቫል ግንቦት 17 ዋናው የምስጋናና የሽልማት ቀን ግንቦት 30 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዚህ መርሐግብር መምህራን ፣የህክምና ባለሞያዎች፣አሽከርካሪዎች እና የፅዳት ባለሞያዎች፣ቤተሰቦች ይመሰገናሉ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ግንቦት 30 የምስጋና ቀን እንዲሆንም እንቅስቃሴዎች ተጀምሯል።

በስካይ ላይት ሆቴል በሚካሄደው የማጠቃለያ ፕሮግራም áˆ‹á‹­áˆ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በህይወት ክህሎት ስልጠና ፣ በበጎ አድራጎት ፣ ዝናን ለመልካም ምግባር፣ሚዲያውን ለስነልቦና ግንባታ ፣ ማህበራዊ ሚዲያውን ለመልካምነት ለተጠቀሙት ግለሰቦች እና ተቋማት ሽልማት ይሰጣል።

በመርሃግብሩ ላይ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ንግግር እንደሚያደርጉም ተገልጿል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
👍1
📌"የተቀደሱ ማሚቶዎች" የሥዕል አውደርዕይ

የሠዓሊ አለባቸው ካሣ የሥዕል ስራዎች የሚቀረቡበት "የተቀደሱ ማሚቶዎች" የሥዕል አውደርዕይ አርብ ሚያዝያ 3 2017 ዓ.ም áŒ€áˆáˆŽ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሚያዝያ 17 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌"ሰተቴ" ተከታታይ ድራማ ለእይታ ሊበቃ ነው

በመንገደኛው ባለቅኔ ከድር ሰተቴ ላይ መሠረቱን ያደረገ "ሰተቴ" የተሰኘ አዲስ ተከታታይ አስቂኝ ድራማ በአርትስ ቴሌቪዥን በቅርቡ ለተመልካቾች መቅረብ እንደሚጀመር ተነግሯል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
❤3
📌የ"ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ቅዳሜ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሄራዊ ማህበር የሚዘጋጀው "የፈለገ ኪን" ስምንተኛ የኪነጥበብ ዝግጅት ቅዳሜ ሚያዝያ 4 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት  ይካሄዳል።

ባለፉት ሰባት መድረኮች እንደተደረገው ሁሉ ስድስተኛው መርሀግብር ዓይነ ስውራንና የዓይነ ስውራን ወዳጆች á‹¨áˆ†áŠ‘ ባለተሰጥዖዎች የሙዚቃ፣ የሥነግጥምና የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ችሎታዎቻቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ነው ተብሏል።

በዕለቱም ደራሲ ከበደ ሚካኤል የሚዘከር ሲሆን ኃይሉ ፀጋዬ የዕለቱ ተጋባዥ የክብር እንግዳ በመሆን እንደሚገኝ ተገልጿል።

አዘጋጆቹ "በመርሃግብሩ ላይ በመታደም ከአይነስውራን አእምሮ የፈለቁ  áŠĽáˆá‰…áŁ  ጥልቅ፣ ምጡቅ  የስነ ጽሁፍ፣ የሙዚቃና የፍልስፍና ጠለ በረከቶችን ይቋደሱ " ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌ሁለት አጫጭር ፊልሞች ለእይታ ሊበቁ ነው

"ገብረ ጉንዳን" እና "አልባትሮስ" የተሰኙ ርዕሶች የተሰጣቸው ሁለት አጫጭር ፊልሞች ነገ ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ለእይታ ይበቃሉ፡፡

ሁለቱም ፊልሞች አጭር ፊልም የመስራት ሀሳብ ላላቸው እንዲሁም አጭር ፊልም መታደም ለሚፈልጉ የፊልም አፍቃሪያን ጥሩ አጋጣሚ ነው ተብሏል፡፡

በዝግጅቱ ላይ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ወጣቱ የፊልም ባለሞያ ናትናኤል ማርቆስ ይታሰባል።

የመግቢያ ዋጋው 2ዐዐ ብር ሲሆን ትኬቱን ቀድማችሁ በሚከተለው 1000394090658 (CBE) 0919320448 (Telebirr)
Dawit nahusenay የቴሌብር አካውንት መቁረጥ ትችላላችሁ ወይንም ወይም በሚቀጥለው ሊንክ መመዝገብ ይቻላል።

https://forms.gle/hwduM3nEqmh31Rwh8
❤1
📌የግጥም ምሽት የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል

"Youth impact"  የግጥም ምሽት  አዘጋጅቷል።

ይህም የግጥም ምሽት ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው Youth impact ግቢ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌ልዑል ሲሳይ ተከታታይ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው

የድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ኮንሰርት የፊታችን ሚያዚያ 18 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 እስከ እኩለሌሊት 6:00 ድረስ በጊዮን ሆቴል ይካሄዳል።

በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የተዘጋጀው ኮንሰርት እንደተጠናቀቀ ግንቦት 2 በሀዋሳ፣ ግንቦት 23 በድሬደዋ ሌሎች ድምፃዊያንን በማካተት የኮንሰርት ቱር እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ከልዑል ሲሳይ በተጨማሪስካት ናቲ፣ ሃና ግርማ እና ዊሃ በዝግጅቱ ላይ በቶራ ባንድ ታጅበው ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

በሦስቱም የኮንሰርቶች ላይ በአጠቃላይ ከ22 ሺህ በላይ ተመልካች የሚጠበቅ ሲሆን ቀድሞ ለሚገዙ ውስን የሚሆኑ ትኬቶችን 400 ብር መደበኛ 600 በዕለቱ በር ላይ 800 ቪአይፒ 2500 ብር ሲሆን ትኬቱን መግዛት የሚቻለው በቴሌ ብር ብቻ ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በዘመናዊ ሙዚቃ በመጀመሪያ አልበም ከፍተኛ ተወዳጅነት እና ተቀባይነት ያገኘው ልዑል ሲሳይ በፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ እና ሸጋ ኤቬንትስ እና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት ሀገር አቀፍ የሙዚቃ ቱር "የልዑል ሙዚቃ ቱር" በሚል ስያሜ ያከናውናል።

ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ "ልዑል'' ሲል በሰየመው የመጀመሪያ አልበሙ ውሰጥ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ስልተ-ምቶችን ጨምሮ ሬጌና ፖፕ ስልቶችን አካቶ መምጣቱ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:

1.ከተማ በቃኝ ብሎ ጭልጥ ያለ ገጠር የገባው ኢትዮጵያዊ áˆ á‹“ሊ የሥዕል ሥራዎቹ በሸራተን አዲስ ሆቴል ለእይታ ቀረቡ።

2.ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ እና ድምጻዊ አለማየሁ ሂርጶ ከ20 ዓመታት በኃላ የሙዚቃ ዝግጅታቸውን በአንድ መድረክ ሊያቀርቡ ነው።

3.ወጣቱ ድምጻዊ ልዑል ሲሳይ በሶስት የኢትዮጵያ ከተሞች የሙዚቃ ኮንሰርቱን እንደሚያቀርብ አስታወቀ።

4.ግንቦት 30 ሀገር አቀፍ የምስጋና ቀን እንዲሆን ጥያቄ ቀረበ።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/PZ_0mMbltYk?si=xAPx2WFWhr-JJh4z

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ሰይፍ ፋንታሁን ህመም ገጥሞት áŠĽáŠ•á‹°áŠá‰ áˆ¨ ተናገረ

ዝነኛው የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ፕሮግራሞች አቅራቢ ሰይፉ ፋንታሁን ትንሽ ህመም ገጥሞት እንደነበረ  በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታወቀ።

ሰይፉ ፋንታሁን በማህበራዊ ትስስር ገፁ"ቀለል ያለውን አድርጎልኛል።እግዚአብሔር ይመስገን።በዚህ ሳምንት ወደ ስራ እመለሳለሁ" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"የደራው" መጽሔት አራተኛ እትም ለንባብ በቃ

"የደራው" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ዲጂታል መጽሔት አራተኛው እትም ለንባብ በቅቷል።

ዲጂታል መጽሔቱ በዚህኛው እትም ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ ይዟል።

ከእዚህም መካከል አንጋፋው ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ ከዝነኛው ቴድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ጋር የተጣመሩበት የ"ደጃዝማች" አልበም ጉዳይ ይገኝበታል።

የደራው መጽሔት በተወደደችው  ቅዳሜ  ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ በደጆ ነው!!

በደራው መጽሔት በርካታ ጉዳዮችን በነፃ ይኮምኩሙ!

መጽሔቱን የግሎ ለማድረግ
👇👇👇
https://t.me/yederaw
📌የፊልም ባለሞያ አንተነህ ኃይሌ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ይቀርባል

(መግቢያው በነፃ ነው)

የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር አንተነህ ኃይሌን ጋብዟል::

የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች"ከአንተነህ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን áˆ˛áˆ†áŠ• ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን áˆ›áŠ­áˆ°áŠž ሚያዚያ 7 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ ገለጸዋል።

በዕለቱ ከፊልም ባለሞያው ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::

ፕሪስቴጅ አዲስ ከአንተነህ ኃይሌ ጋር  የሚያደረገው አዝናኝ áŠĽáŠ“ አስተማሪ ቆይታ  ማክሰኞ ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:

📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱

  https://jazzio.land/register

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌ቫይደም ሄልዝ በአዲስ አበባ ቢሮ ከፈተ

በህንድ ሀገር መሰረቱን ያደረገው ቫይደም ሄልዝ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮውን ከፈተ

በውጭ ሀገራት ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን በማማከርና የጉዞ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የሚታወቀውና በህንድ  ሀገር መሰረቱን ያደረገው ቫይደም ሄልዝ በአዲስ አበባ ቅርንጫፉን በይፋ እንደከፈተ አስታውቋል።

"ቫይደም ሄልዝ አለም አቀፍ ልምዱን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ከህክምና ጉዞ ጋር ተያይዘው የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ለታካሚዎችና ለቤተሰቦቻቸው እፎይታን ለመስጠት ያለመ" መሆኑን የቫይደም ሄልዝ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ፓንኬጅ ቻንድራ ተናግረዋል።

ቫይደም ሄልዝ በህንድ፣ ቱርክ፣ ታይላንድ፣ ዱባይ፣ ጀርመን፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ሲንጋፖር፣ ማሌዥያ እና ደቡብ ኮሪያ ከሚገኙ ከ 8,000 በላይ ዶክተሮች ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን እስካሁን ድረስም በዓለም ዙሪያ ከ 100,000 በላይ ታካሚዎች ህክምና እንዲያገኙ አስተዋጽኦ እንዳደረገም ተገልጿል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌 የዘሪቱ ከበደ የመድረክ አልበም

የዘማሪት ዘሪቱ ከበደ "ማዕናናትህ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና መድረክ (Live) ላይ እንደተቀረጸ የተነገረለት የመዝሙር አልበም የፋሲካ ዕለት እንደሚለቀቅ ዘማሪዋ በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
👍1
📌ሰራዊት ፍቅሬ በሲትኮም ድራማ እየመጣ ነው

ከበርካታ ዓመታት በኃላ ዝነኛው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ "ማረፊያ" በተሰኘ አዲስ አስቂኝ ድራማ ላይ ሊተውን እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የድራማው ፕሮዲዩሰር አርቲስት አሸናፊ ማህሌት በማህበራዊ ትስስር ገፁ"ይህ ቀን እንደሚመጣ አውቅ ነበር። እንዲህ ይፈጥናል ብዬ ግን አላሰብኩም ።ሁለገቡ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ በተከፈተው የሚያዚያ ወር የአርቲስቶች የዝውውር መስኮት ሪከርድ በሆነ ዋጋ "ማረፊያ" የተሰኘውን ሲትኮም ድራማ ተቀላቅሏል" ብሏል።

በተጨማሪም አርቲስት አሸናፊ ማህሌት " ከወጣበት ከፍተኛ ዋጋ አንፃር በርካታ የሳቅ አና የቁምነገር ጎሎችን በማስቆጠር ተመልካቾቻችንን አርክቶ ለሲትኮማችን ብዙ ዋንጫዎችን ያመጣል ብለን እናምናለን" ሲል ተናግሯል።

አያይዘውም "ያለብንን የሳቅ ጫሪ አጥቂ ቦታ ስለሸፈንን በዚህ አመት ከንፈር የሚባለውን በረኛ አስከፍተን ጥርስን ነፃ በማውጣት ውጭ እንደምናሳድረው ለተመልካቾቻችን ቃል እንገባለን" ሲል ተናግሯል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ እና ድምጻዊ አለማየሁ ሂርጶ ከ20 ዓመታት በኃላ የሙዚቃ ስራዎችን በአንድ መድረክ ሊያቀርቡ ነው።

በ1990ዎቹ ለሙዚቃ አፍቃሪያን ከደረሱ የሙዚቃ አልበሞች መካከል "ኢቫንጋዲ" የተሰኘው አልበም ተጠቃሽ ነው።

በዚህ አልበም ጎሳዬ ተስፋዬ እና አለማየሁ ሂርጶ በርካቶች የማይረሷቸው ተወዳጅ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች ያቀርቡበት ነበር።

በ"ኢቫንጋዲ" አልበም የተጣመሩት ሁለቱ ድምጻዊያውን ከ20 ዓመታት በኃላ የሙዚቃ ስራዎችን በአንድ መድረክ ሊያቀርቡ እንደሆነ አርትስ ስፔሻል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ የሙዚቃ ዝግጅትም ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል ተብሏል።

በሙዚቃው ዝግጅቱ ላይ ከጎሳዬ ተስፋዬ እና አለማየሁ ሂርጶ ባሻገር አንጋፋው ድምጻዊ ኤፍሬም ታምሩ እና ወጣቷ ድምጻዊት ሜላት ቀለመወርቅም ያቀነቅኗል።

ለዓመታት በኖርዌይ በስደት አስቸጋሪ ጊዜ ሲመል ቆይቶ በቅርቡ ወደ ሃገር ቤት የተመለሰው  ድምፃዊ አለማየሁ ሄርጶ ከዓመታት በኃላ ወደ ሙዚቃ መመለሱን ይፋ ያደረገበት የሙዚቃ ሥራውን ከወራት በፊት ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌የድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ የችሎት ሂደትን የሚዲያ ባለሙያዎች እንዳይታደሙ በፍርድ ቤት ታገዱ

ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ያስቻለው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በፍቅረኛው ወጣት ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ህልፈት ተጠርጥሮ በምርመራ ሂደት ላይ የሚገኘው የአርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ጉዳይ በታየበት ችሎት ነው ፍርድ ቤቱ መገናኛ ብዙሃን ችሎቱን እንዳይታደሙ ያገደው፡፡

በዛሬው ችሎት ፖሊስ የመገናኛ ብዙሃን በተለያዩ ጊዜያት “የችሎቱን ውሎ በተደጋጋሚ አዛብተው ዘግበውታል” በሚል የምርመራ ሂደቱ ላይ እክል በመፍጠራቸው በችሎቱ እንዳይታደሙ ጠይቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ በችሎቱ የተጠየቁት የተከሳሽ ጠበቃ በፊናቸው ፖሊስ ያቀረበውን አቤቱታ እንደሚደግፉ ገልጸዋል፡፡

ችሎቱም ግራ ቀኙን ካደመጠ በኋላ “መገናኛ ብዙሃን ካሁን በፊት አንድ ጊዜ ተከሳሽ ለፋሲካ በዓል ወጥቶ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ጠይቋል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሟች የግል ማህደር (ዳይሪ) በተከሳሽ ጠበቃ እጅ ነው የሚገኘው የሚሉ የተዛቡና ሀሰተኛ ዘገባዎች ማቅረባቸው በችሎቱና በምርመራ ሂደቱ ላይ እክል እንደሚፈጥር በመታመኑ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች (ጋዜጠኞች) ችሎቱን እንዳይታደሙ” በሚል ብይን ሰጥቷል።

በዛሬው ችሎት በዚህ አይነት መልኩ ትክክለኛውን የችሎት ውሎ ከመዘገብ ይልቅ እውነትን አዛብተው የዘገቡ መገናኛ ብዙሃን የትኞቹ ናቸው የሚለው ሳይለይ፤ ችሎቱ ላይ የታደሙ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ለቀው እንዲወጡ በዳኛው በታዘዘው መሰረት የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ እና የሌሎችም መገናኛ ብዙሃን ዘጋቢዎች በዚሁ ትዕዛዝ ከችሎቱ ለቀው ወጥተዋል ሲል ዶቼቬሌ ዘግቧል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌የፈረጃ ፊልም ቀረፃ ሚያዝያ 20 ይጀምራል

በህዝብ መዋጮ የሚሰራዉና በኢትዮጵያ የመጀመርያው (Crowdfunding) ፊልም የሆነው ፈረጃ የተሰኘዉ የቦክስ ፊልም ከብዙ ዝግጅትና አድካሚ ጉዞ በኋላ የታሰበዉ በጀት ባይሞላም ቀረፃዉ ሚያዝያ 20 ሊጀመር ነዉ።

አርቲስት ሄኖክ ወንድሙ ሂደቱ ከባድ እንደነበር ተናግሮ የቦክስ ፊልም እንደመሆኑ ለቀረፃዉ ብዙ ሰው እንደሚያስፈልግና በተሳትፎ እንዲያግዙት ወጣቱን ኃይል ጠይቋል።

በገንዘብና በሀሳብ ላገዙት ሰዎች በሙሉ ትልቅ ክብርና ምስጋናዉንም አቅርቧል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ሕይወት አጭር ናት" ያለው ሰለሞን ተካልኝ አረፈ

ከሳምንታት በፊት "ሕይወት አጭር" ሲል የተናገረው ሰለሞን ተካልኝ ዛሬ ማረፉ ተሰማ።

አነጋጋሪ እና አወዛጋቢ የፖለቲካ ዘፈኖችን በመስራት የሚታወቅው ሰለሞን ተካልኝ ከሳምንታት በፊት በፍሎረዳ ግዛት ክሊር ዋተር በተባለ ቢች ላይ ሆኖ በራሱ የቲክቶክ ገፅ ላይ ይሄን ቪዲዮ ለተከታዮቹ አጋርቶ ነበር በቪዲዮው ላይ "ሕይወት አጭር ናት" ሲል የተናገረው ሰለሞን ዛሬ ማረፉ ተሰምቷል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የመጻሕፍት ድጋፍ አደረገ

ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል  200 የሚደርሱ ልዩ ልዩ የህክምና መጻሕፍት ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የተረከቡት የዲላ ዩኒቨርሲቲ  ቤተ መጻሕፍትና ኢንፎርሜሽን ዳይሬክተር አስናቀ ሙልዬ(ዶ/ር)፣ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፤ ከዛጎል የመጻሕፍት ባንክ  ለዩኒቨርሲቲው የተበረከቱት መጻሕፍት በቁጥር  200 የሚደርሱ የህክምናና ልዩ ልዩ መጻሕፍት እንደሆኑ ገልጸው፤  እነዚህ መጻሕፍት በተለይ በዚህ ወቅት ተማሪውን ወደ ንባብ ለመመለስም ይሁን ላይብረሪውን በተሟላ ሁኔታ  ለማደራጀት አስተዋጽኦቸው  የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል።

ዶ/ር አስናቀ አያይዘውም፤ ይህ በመጻሕፍት ባንኩ የተደረገው á‹ľáŒ‹á ለአሁኑ እንደ ጅምር ይታይ እንጂ በቀጣይ ከዛጎልም ይሁን áŠ¨áˆŒáˆŽá‰˝ ተቋማት ጋር ግንኙነቶችን በማጠናከር ሌሎች ላይብረሪዎችንም የማደራጀቱ ሾል ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ዛጎል የመጻሕፍት ባንክን ወክለው መጻሕፍቱን ያስረከቡት ወ/ሪት ፍፁም áˆ›áˆŠ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ፤ ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ከ2013 ጀምሮ መጻሕፍትና አንባቢ ለማገናኘት የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ድርጅት እንደሆነ አውስተው፣ድርጅቱ ይህን አላማውን ለማሳካት áŠ¨á‹¨áŒáˆˆáˆ°á‰Śá‰˝áŠ“ ተቋማት መጻሕፍትን እያሰባሰበ እስካሁን ወደ 40 ሺህ የሚደርሱ መጻሕፍትን እንዳሰራጨ በመግለጽ  ለዲላ ዩኒቨርሲቲ 200 ልዩ ልዩ መጻሕፍትን እንዳስረከበ ተናግረዋል።

ወ/ሪት ፍፁም  አክለውም፥ á‰ á‰€áŒŁá‹­áˆ ይህንኑ ድጋፍ በሌሎች መስኮች ላይም አጠናክሮ ለማስቀጥል ከዩኒቨርሲቲው ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ገልጸው ፤  በዩኒቨርሲቲው ለተደረገላቸው መልካም አቀባባል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
👍1