Event Addis Media
9.63K subscribers
6.09K photos
13 videos
4 files
4.71K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች “በሽብር ወንጀል” ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ

የፌደራል ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ” ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞችን፤ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት አቀረበ። ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

በሌላ በኩል የኢቢኤስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አማን ፍስሐፅዮን የብርቱካንን ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በመግለጫቸው በድርጅቱ ውስጥ እና በውጭ የተቀናጀ ሀይል ከጋዜጠኝነት መርህ ውጭ የሆነ ተግባር ተፈፅሟል ብለዋል።

የብርቱካን ጉዳይም አዘጋጆቹ ያለ በቂ መረጃ ማጣራት ያከናወኑት መሆኑን ገልጸዋል።

ዝግጅቱም ከማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ የወረደው በራሷ በብርቱካን ጥያቄ መሰረት መሆኑን ነው የተናገሩት መረጃዎችን ለማጣራት ባደረጉት ጥረትም ነገሩ ውሸት ሆኖ መገኘቱን ገልጸው፣ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በዶክመንተሪው ምክንያት ለፈጠረው ችግር መላ ኢትዮጵያውያንን ይቅርታ ጠይቀዋል።

ችግሩን በፈጠሩት አካላት ላይ ድርጅቱ አስተዳደራዊ እርምጃ ከመውሰድም በተጨማሪ አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚተባበር ገልጸዋል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌"የያዩ ትውስታ"የመታሰቢያ ዝግጅት እየተካሄደ ነው

የአንጋፋው ሙዚቀኛ ያየህይራድ አላምረው የመታሰቢያ ዶክመንተሪ ፊልም ምርቃትና ሊሰራው በውጥን ላይ የነበረው "አስርቱ ትዕዛዛት" የተሰኘው ስራው የሚቀርብበት "የያዩ ትውስታ" ተብሎ የተሰየመው ልዩ ዝግጅት ዛሬ መጋቢት 19/2017  ከ10:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል ሲል ባላገሩ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ታዋቂው የሙዚቃ ደራሲ፣ ፕሮዲውሰርና ፕሮሞተር ያየህይራድ አላምረው የጥላሁን "ቆሜ ልመርቅሽ" ፣ የአስቴር አወቀን "ሰበቡ" እና "የሠርጌ ትዝታ" ፣ የኩኩ "ይቺ ናት ሀገሬ" ፣ የቡድን ሥራዎች የኾኑት የነ ዘሪቱ "መኖርህን ሌሎች ይሻሉ" ፣ እና የነ ጸደኒያ "ሰው ነው ነው ለሰው መድሃኒቱ" የተሰኙ ሙዚቃዎች የግጥም ድርሰቶች ጀርባ የነበረ የሙዚቃ ፕሮዲውሰርና ፕሮሞተር ጭምር ነበር ።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:

1."The Big Art Sale" ዓወድርዕይ ለሃያኛ ጊዜ ሊካሄድ ነው።

2.ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ ከዓመታት በኃላ የሙዚቃ አልበሟን ለአድማጮች ልታደርስ ነው።

3.አርቲስት ቢኒያም ወርቁ ሊመሰገን ነው።

4.በእውነተኛ ታሪክ የተመሠረተው "ቀይ ባህር ሲቀላ" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/qYHu2jD5558?si=tqbzAKeyIuRkGBMQ

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌ግዙፉ አውድርዕይ ለሃያኛ ጊዜ ሊካሄድ ነው

በጥበብ አፍቃሪያኑና በጥበበኛው ዘንድ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀው ’The Big Art Sale’ ዓውደ ርዕይ በዚህ ዓመት ለሃያኛ ጊዜ  በሒልተን ሆቴል  የፊታችን ሚያዝያ 4 እና 5  2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

በአውደ ርዕዩ ከ100 በላይ ሰዓሊያንና ቀራፂያን አዳዲስ ሥራዎቻቸውን ለጎብኚዎችና ለገዢዎች ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

ከጥበብ ስራዎች በተጨማሪ ጥበብ አፍቃሪያኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚዝናኑባቸው የመጠጥና የምግብ ኮርነሮች ሲኖሩ፤ለልጆች ልዩ የመጫወቻ ሥፍራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

ይህ ልዩ ዓውደ ርዕይ ጠቢብያኑ ሥራቸውን እንዲሸጡ እድል የሚሰጣቸው ሲሆን፤ ገቢውም  ለበጎ አድራጎት ሥራዎች እንደሚውል ተጠቁሟል።

በዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው የጥበብ ዓውደርዕዩ ዋትስ አውት አዲስ ከሒልተን ሆቴል ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ነው።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌"የእግዜር ብቸኝነት" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የገጣሚ መኳንንት መንግስቱ ሦስተኛ መጽሐፍ የሆነው "የእግዜር ብቸኝነት" መጽሐፍ በዚህ ሳምንት ለንባብ በቅቷል።

መጽሐፍ በ138 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ300 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ገጣሚ መኳንንት መንግስቱ ከዚህ ቀደም "ክፍት የስራ ቦታ" እና "ስንፋታ እንደግስ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አቅርቧል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌አርቲስት ቢኒያም ወርቁ ሊመሰገን ነው

ደራሲ፣አዘጋጅና ተዋናይ ቢኒያም ወርቁ የሚመሰገንበት ልዩ ዝግጅት የፊታችን ሰኞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል።

መርሐግብሩ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በጥበቡ ዓለም የኖረው እና እየኖረ የሚገኘው፣ በርካቶችን ከህልምና ተሰጥኦዋቸው ያገናኘው ሁለገቡ ከያኒ ቢኒያም ወርቁ ለእስካሁን አበርክቶው፣ ትጋትና ብቃቱ በይፋ የሚመሰገንበት መሰናዶ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ይህ የምስጋና መርሐግብር የፊታችን ሰኞ መጋቢት 22 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር ከ11 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ይከናወናል።

አርቲስት ቢኒያም ወርቁ  ከ20 በላይ ፊልሞች እና ከ7 በላይ ትያትሮችን በደራሲነት፣ በአዘጋጅነት፣ በተዋናይነት እና በዳይሬክተርነት ሰርቷል፡፡

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
ቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ 2017

«ቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ 2017» በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከመጋቢት 19 ቀን እስከ ሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

ታሜሶል ኮሙዩኒኬሽን በዛሬው እለት በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጸው፥ ይህ ኤክስፖ ከዚህ ቀደም ከተደረጉ የንግድ ትርኢቶች የተለየ እና ልዩ የሚያደርጉት በርካታ ዝግጅቶች ማቀዱን ገልጿል።

በዚህ ኤክስፖ ጎብኚዎች የተለያዩ የፆም ምግቦች (በብፌ መልክ) በአንድ ቦታ በ150 ብር ከነፃ የስንቅ ማልት ጋር ያገኛሉ።

ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ የሆነውን የ50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ በኤክስፖ ላይ በልዩ ሁኔታ ይተዋወቃል።

2.8 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የኤሌክትሪክ መኪና እና የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል እንዲሁም አይቴል የሞባይል ቀፎ ለሽልማት ቀርቧል።

ከመደበኛው የንግድ ትርኢት ባለፈ የባህል፣ የትምህርት እና የመዝናኛ መድረክ የቀረበ ሲሆን የሀገራችንን ባህል እና እሴቶች የሚያንጸባርቁ ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች ይኖሩታል።

ታሜሶል ኮሙዩኒኬሽን ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን እና ከሊያን ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በመሆን አዘጋጅተውታል፡፡

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
"በመንገዴ ላይ" አውደርዕይ በእይታ ላይ ነው

በሠዓሊና ቀራጺ ሄኖክ ፀጋዬ የተዘጋጀውና "በመንገዴ ላይ" የሚል ርዕስ የተሰጠው የቅራጻቅርጽ የሥነጥበብ አውደ ርዕይ ባሳለፍነው ረቡዕ መጋቢት 17  2017 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው እንጦጦ ጋለሪ ውስጥ ለእይታ በቅቷል።ይህ የሥነጥበብ አውደርዕይ እስከ ሚያዝያ 7 2017 ዓ.ም ድረስ በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌በሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ስም የተሰየመው የሮያሊቲ ክፍያ ማስገኛ ሥርዓት ይፋ ሆነ

በተወዳጁ የሙዚቃ ባለሙያ ኤልያስ መልካ ስም የተዘጋጀው የሙዚቃ ሮያሊቲ መሰብሰቢያ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በይፋ ተዋውቋል።

ሥርዓቱ ኤልያስ መልካ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ሮያሊቲ መሰብሰቢያ ወይም (EMEMRC) የሚል መጠሪያ የተሰጠው ነው።

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር የሮያሊቲ ክፍያ አሰባሰብን አስመልክቶ በጋራ ያዘጋጁትን የሮያሊቲ ክፍያ ቀመር ለማፅደቅ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የቀረበለትን ቀመር ለማፅደቅ ከሚዲያ አመራሮችና ከፈጠራ ባለሙዎች ጋር እየተወያየ ሲሆን፥ ተቋማት የሚከፍሉት የሮያሊቲ ክፍያ የገቢ አቅማቸውን መሰረት በማድረግ 24 ሠአት የሙዚቃ ውጤቶችን ይጠቀማሉ ተብሏል።

የሙዚቃ ተጠቃሚዎች በዓመትና በጊዜያዊነት ክፍያ መፈፀም እንደሚችሉም ተሰምቷል።

ለአዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በቀረበው ቀመር መሰረት ተቋማቱ በ24 ሠአት ውስጥ 360 እነዲሁም በዓመት ደግሞ 131 ሺህ 400 ሙዚቃዎችን እንደሚያጫውቱ ተመላክቷል።

የሙዚቃ ባለሙያውም በተጫወተለት የሙዚቃ መጠን የሚከፈለው ሲሆን፥ ባለስልጣኑና ሁለቱ ማህበራት በዛሬው ዕለት የሮያሊቲ ክፍያ ቀመርን ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ዘግቧል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌ዳማሪዮስ ፋሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ዳማሪዮስ ፋሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋሽን፣ በስነ ዉበት (ሜካፕ)፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ሴኩሪቲ እና በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ሰልጣኞችን ለማሰልጠን ምዝገባ እንደጀመረ ይፋ አድርጓል።

ዳማሪዮስ ተግባር ተኮር የሆኑ ስልጠናዎች  የሚሰጥ ሲሆን  ከመስከረም ጀምሮ በLevel 2  ዓለም አቀፍ በሆኑ ባለሙያዎች ስልጠናዎች ይሰጣል ተብሏል በተጨማሪም ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ በተቋሙ አቅም መሰረት የፋይናንስ አገልግሎቶች እንደሚመቻችላቸው ተገልጿል።

አቅም ለሌላቸው ሰልጣኞች ከዳሽን ባንክ እና ከንብ ባንክ ጋር የዱቤ ብድር አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት ተፈፅሟል።

በሜካፕ ትምህርት ክፍል ከMario ሜካፕ ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ውል መፈፀማቸውን ገልፀው ከቆዳ ስፔሽሊስት ዶክተሮች ጋር በጥምረት አብሮ ለመስራት ውል መፈፀማቸው ተገልጿል።

አሁን ለ20 ቋሚ ሰራተኞች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን፣ ከRome Business School ጋር ለተማሪዎች የስኮላርሺፕ ስምምነት ተደርጓል።

ተቋሙ ቦሌ ብራስ የሚገኝ ሲሆን በ1200 ካሬ ሜትር ላይ አርፏል፣ 24 ከፍሎች ሲኖሩት፣ ዘጠኝ የመማርያ ከፍሎች፣ አንድ ቤተ መጽሐፍትን ያካተት ተቋም ነው።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌"ልጄስ" ድራማ ድጋሚ ለእይታ ሊቀርብ ነው

"ልጄስ" ተከታታይ ድራማ ከክፍል አምስት በኃላ ያለው ቀጣይ ክፍል ከሚያዝያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በቃና ቴሌቪዥን መታየት እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው ያመለክታል።

ይህ ተከታታይ ድራማ በሰማኸኝ አይችሉሁም ዳይሬክት የተደረገ ሲሆን አርቲስት ዳንኤል አሸናፊ (ፂሞ) በመሪ ተዋናይነት ተውኖበታል፡፡

እስከ አምስተኛው ክፍል ድረስ በካናል ፕላስ እና በቃና ቲቪ ዩቲዩብ ቻናል እየተላለፈ የቆየው"ልጄስ" ተከታታይ ድራማ ከክፍል አምስት በኃላ ያለው ቀጣይ ክፍል በካናል ፕላስ ሲኒማ ብቻ ሲተላለፈ እንደነበር ይታወሳል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌EBS "አዲስ ምዕራፍ" ፕሮግራም በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ መሰረት ከስርጭት ታግዶ እንዲቆይ ተወሰነ

“አዲስ ምዕራፍ” የቴሌቪዥን ፕሮግራምን በተመለከተ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ "አዲስ ምዕራፍ" በተሰኘ ፕሮግራሙ እሑድ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ያሰራጨውን ፕሮግራም ከመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና ከዘርፉ ሕጎች አንጻር በመገምገም አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ብሏል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ ሪድስ አምስተኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

ለዓመታት የልጆች የንባብ ልምድ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ የሚገኘው ኢትዮጵያ ሪድስ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው አምስተኛ ጉባኤው ከትላንት መጋቢት 24 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

በዝግጅቱ ላይ ከተለያየ ዘርፍ የተወጣጡ ባለሙያዎች ስለ ልጆች ንባብ እና ተያያዥ ሀሳቦች ላይ መነሻ ጥናታዊ ፅሁፎች እያቀረቡ ሲሆን በፅሁፎቹም መነሻነት የሃሳብ ልውውጥ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ጉባኤ ላይ የልጆች ንባብ ባህልን ለማሳደግ አስተዋፅኦ ያደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና የመስጠት መርሃግብር ይካሄዳል ተብሏል።

ኢትዮጵያ ሪድስ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በሀገሪቱ በሁሉም ክልሎች ከ70 በላይ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ቤተመጽሐፍትን በማቋቋም ከመንግስት እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር አብሮ እየሰራም እንደሚገኝ አስታውቋል።

የ22 ዓመታት እድሜ ያስቆጠረው ኢትዮጵያ ሪድስ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች እና ልጆችን ባለፉት ዓመታት በንባብ አገልግሎት ተደራሽ ማድረጉን ገልጿል።

📸 ተክሌ ማርኮን

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌ሁለገቡ ባለሞያ ኢ/ር ጌታሁን ሄራሞ እንግዳ የሆነበት አላቲኖስ የፊልም ውይይት ዛሬ ይካሄዳል

አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ "ቀለም እና ሲኒማቶግራፊ"በሚል ርዕስ ውይይት  ያካሂዳል።

በዝግጅቱ ላይ የፊልም ባለሞያዎች ባለቀለም ፊልሞችን መሰራት ከጀመሩ ወዲህ ቀለም የፊልሙን ታሪክ (Story) ለታዳሚው በተሻለ መልኩ ከማስተላለፍ አኳያ የሚጫወተውን ሚና በተመለከተ የቀለም ባለሞያው ኢ/ር ጌታሁን ሔራሞ ሀሳቡን ያጋራል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:

1.አንጋፋው አርቲስት ኪሮስ ኃይለሥላሴ በማርች ባንድ ታጀቦ ምስጋና ሊቀርብለት ነው።

2.አርትስ ቴሌቪዥን በመንገደኛው ባለቅኔ ከድር ሰተቴ ላይ መሠረቱን ያደረገ አዲስ ድራማ ሊጀምር ነው።በሌላ "በሕግ አምላክ" ድራማ ምዕራፍ ሶስት የሚጀምርበት ቀን ታውቋል።

3. ተወዳጁ ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው።

4.ሁለቱ ግዙፍ የሥየጥበብ አውደርዕዮች በአንድ ሳምንት በተከታታይ ቀናት ሊካሄዱ ነው።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/3dymotNOWis?si=a9WgTbBvuj-m2cdP

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"የደራው" መጽሔት ለንባብ በቃ

"የደራው" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ዲጂታል መጽሔት ሶስተኛ እትም ለንባብ በቅቷል።

ዲጂታል መጽሔቱ በዚህኛው እትም ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ ይዟል።

ከእዚህም መካከል በአዲስ አበባ በሰማይ በራሪ ታክሲዎች ፣የአሜሪካው ታሪፍ፣የቲክቶክ ውለታ፣ወደብ ማግኘት፣መርካቶ እንሂድ፣በBig Habesha የሙዚቃው ዓለም ጦርነት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን በነፃ ይኮምኩሙ ተብላችኋል።

መጽሔቱን የግሎ ለማድረግ
👇👇👇
https://t.me/yederaw
👍1
የጠይም ፈረንጅ  50,000 ብር ሊሸልም ነው!!

ሙዚቀኛ ብስራት ሱራፌል ስድስት የሙዚቃ ስራዎችን የያዘው ተወዳጅ ሙዚቀኞች እና ደራሲዎች ያሳተፈው የጠይም ፈረንጅ አልበም በቅርብ ቀን ለአድማጭ ሊያደርስ ዝግጅቱን አጠናቋል!

ሙዚቀኛውም ከዚህ በፊት ተወዳጅ ሁለት አልበሞችን ቃል በ ቃል እና ማለፊያ በተጨማሪም ነጠላ ዜማዎቹ በአድማጭ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙ ናቸው::

ታዲያ የጠይም ፈረንጅን የአልበም ገፅ (Cover) ምስል የፈጠራ አቅም ላላቸው ሰዎች እድሉን ሰጥታል! ከአልበሙ መጠሪያ እና ከቀደሙት ስራዎቹ በመነሳት ይገልፃል ብላችሁ  የምታስቡትን ስራ ከታች በተቀመጡት አድራሻዎች መሳተፍ ትችላላችሁ!!

ታዲያ ከሁሉም ተወዳዳሪዎች አንድ ብቻ አሸናፊ ሲኖር ሽልማቱም ሃምሳ ሺ ብር  ጨምሮ በጠይም ፈረንጅ አልበም ገፅ ላይ ይሄው ምስል ይውላል!

በቴሌግራም @YeteyimFerej                 
                     (0972236767)
በኢሜል Yeteyim.Ferenj@gmail.com
በመላክ መሳተፍ ትችላላችሁ!

ለተወዳዳሪዎች በሙሉ መልካም እድል!

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
'የትዝታዬ ማሕደር' ሚያዝያ 5 2017 ዓ.ም ይመረቃል

"ዳግላስ ጴጥሮስ "በሚለው የብዕር ስሙ የሚታወቀው፣ በርካታ መፅሀፎችን እና መጣጥፎችን ያስነበበው ደራሲ ጌታቸው በለጠ 'የትዝታዬ ማሕደር' በሚል ርዕስ የሕይወት ታሪኩን  ፅፎ በቅርቡ ያስመርቃል፡፡

ደራሲ ጌታቸው  በለጠ፣ የደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገለ ሲሆን በየጊዜው በሚሰጣቸው የማህበራዊ እና የኪነ ጥበባት ሂሶችም ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ሚድያዎች ላይ በመቅረብ ቃለ- መጠይቆች በመስጠት ከበሬታን ያገኘ ደራሲ ነው።
ደራሲ ጌታቸው በለጠ፣ ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ  በጋዜጦች ላይ በመፃፍ አቅሙን ያሳየ የብዕር ሰው ነው።

ደራሲ ጌታቸው በለጠ የሚያስመርቀው መፅሀፍ፣448 ገፆች ያሉት ሲሆን ከልጅነት እስከ አዋቂነት ዕድሜ ያሳለፈውን ሕይወት በመፅሀፉ ላይ አካቷል፡፡

የደራሲ ጌታቸው መፅሀፍ 1000ብር የሚሸጥ ሲሆን በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ ታዋቂ ደራሲያን፣ እና የቅርብ ወዳጆቹ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌ሁለት ግዙፉ አውደርዕዮች በአንድ ሳምንት

በአንድ ሳምንት በተከታታይ ቀናት የሚካሄዱት አውደርዕዮች አርት ኦፍ ኢትዮጵያ እና The Big Art Sale ናቸው።

በሸራተን አዲስ በየዓመቱ ይካሄድ የነበረውና በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ለአምስት አመታት ተቋርጦ የነበረው Art of Ethiopia  የሥነጥበብ አውደርዕይ ዘንድሮ ተመልሷል።

ከአምስት በኃላ በተዘጋጀው በዚህ አውደርዕይ ላይ 62 ሠዓልያን የሥዕል ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ሚያዚያ 2 እና 3 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ይካሄዳል።

በሌላ በኩል The Big Art Sale
በሒልተን ሆቴል ቅፅር ግቢ ውስጥ ሚያዚያ 4 እና 5 2017 ዓ.ም  የሚካሄደው ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ከ200 ሠዓሊያን የሥነጥበብ ሥራዎቻቸውን ለሽያጭ ይቀርባሉ።

ዝግጅቶቹን What's out Addis ከሸራተን አዲስ፣ ከሂልተን ሆቴልና ከካልቸር ክለብ ጋር በመጣመር አሰናድተውታል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌የአስቻለው ፈጠነ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው

በእናትዋ ጎንደር፣ካሲናው ጎጃም፣ አሞራው ካሞራ በተሰኙ ነጠላ ዜማዎች ተወዳጅነትን ያተረፈው "አስቻለ"የተሰኘው አልበም ከአንድ ዓመት በፊት ለሙዚቃ አፍቃሪው ያደረሰው ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ( አርዲ) የሙዚቃ ኮንሰርት በእስራኤል ሀገር  ሊያቀርብ እንደሆነ ገልጿል።

አርትስ ስፔሻል ከድምጻዊ እንዳገኘው መረጃ ከሆነ የሙዚቃ ዝግጅቱ ከፋሲካ በኃላ በፈረንጆቹ ሜይ 15 2025 በቴላቪብ  እንደሚካሄድ ተነግሯል።

ድምጻዊ አስቻው ፈጠነ የሙዚቃ ኮንሰርት በእስራኤል ካቀረበ በኃላ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት የሙዚቃ ዝግጅቱን እንደሚያቀርብ ድምጻዊው ለአርትስ ስፔሻል ገልጿል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
📌አምስተኛው የጣፋጭ ሕይወት ምስጋና

በጣፋጭ ህይወት መልቲሚዲያ በየዓመቱ የሚዘጋጅው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ዝግጅት ዘንድሮው ለአምስተኛ ጊዜ ይካሄዳል።

አምስተኛው ምን ምን አዲስ ነገር ይዟል?ምንስ ክንውኖች ይኖሩታል ?

በዚህ መርሐግብር የጣፋጭ ሕይወት የፓናል ውይይት ሚያዝያ 30፣የቤተሰብ ፌስቲቫል ግንቦት 17 ዋናው የምስጋናና የሽልማት ቀን ግንቦት 30 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዚህ መርሐግብር መምህራን ፣የህክምና ባለሞያዎች፣አሽከርካሪዎች እና የፅዳት ባለሞያዎች፣ቤተሰቦች ይመሰገናሉ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ግንቦት 30 የምስጋና ቀን እንዲሆንም እንቅስቃሴዎች ተጀምሯል።

በስካይ ላይት ሆቴል በሚካሄደው የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይም በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በህይወት ክህሎት ስልጠና ፣ በበጎ አድራጎት ፣ ዝናን ለመልካም ምግባር፣ሚዲያውን ለስነልቦና ግንባታ ፣ ማህበራዊ ሚዲያውን ለመልካምነት ለተጠቀሙት ግለሰቦች እና ተቋማት ሽልማት ይሰጣል።

በመርሃግብሩ ላይ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ንግግር እንደሚያደርጉም ተገልጿል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
👍1