Event Addis Media
9.62K subscribers
6.1K photos
13 videos
4 files
4.72K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌የጠርሲዳ ከበደ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው።

በደራሲ ጠርሲዳ ከበደ የተዘጋጀው "ውሃዬን ሽጬ ኮዳ የገዛኹለት" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ በይፋ ተመርቆ ለንባብ ይበቃል ተብሏል።

መጽሐፉም በርካታ ልዩ ልዩ እንግዶች በተገኙበት የፊታችን ሰኞ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ይመረቃል።

በዕለቱም አርቲስት ተስፉ ብርሃኔ፣ አርቲስት ዋሲሁን በላይ ፣ ድምጻዊ አንተነህ ምናሉ፣ ገጣሚ ሒክማ ፋንቱ እና ሌሎችም በመድረኩ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌 ዋርካ ሬድዮ ወደ ስርጭት ሊመለስ ነው።

የዋርካ ሬዲዮ 104.1 ድጋሚ ወደ ሙከራ ስርጭት ተመልሶ በቅርቡ መደበኛ ፕሮግራሞችን ለመጀመር እንዳሰበ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከሬድዮ ባለቤቶቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮ ዋርካ የጠቅላላ ጉባኤውን መደበኛና ድንገተኛ ስብሰባዎቹን በጊዮን ሆቴል አካሂዶ ዋና ውሳኔዎቹን በቃለ ጉባኤ ማፀደቁን ተከትሎ የተለያዩ ለመጪ ጉዞው ወሳኝ የሆኑ አዳዲስ አመራሮችን አካቶ በአዲስ የተነቃቃ መንፈስ ወደስራ ገብቷል ተብሏል።

አዲሱ አመራር ስቱዲዮ ከማመቻቸት አንስቶ የታዳሚን ቀልብ ይዞ ለመዝለቅ የሚያስችለውን አዲስ የስትራቴጂ አቅጣጫ እየነደፈ በፍጥነት ወደአየር ተመልሶ ለመምጣት እየተንደረደረ እንደሆነ ተሰምቷል።

ጋዜጠኛ ስለሺ ተሰማ የኢትዮ ዋርካ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆኑም ተመርጠዋል።

ዋርካ ሬድዮ በመጪው አስርት አመታት በምስራቅ አፍሪካ የተለየ ምርጥ ሚዲያ ሆኖ ልቆ እንደሚወጣ የሚታመን እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ኩባንያው ከብዙሀን መገናኛው የሬዲዮ ስራዎች በትይዩ በጥናትና የማማከር አገልግሎት ተሰማርቶ የቢዝነስ ሞዴል ቅኝቱን እንዲያጠናክር ጉባኤው አሳሰቦ በጫረታ አሸንፎ የያዘውን ሞገድ ኤፍ ኤም 104.1 ሬዲዮን በፍጥነት ለአየር እንዲያበቃ አደራ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

ዘውትር ሐሙስ በኤቨንት አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሰራጭ የቆየው "የሐሙስ መረጃዎች" ልዩ ጣዕም ጨምሮ በቴሌቪዥን መስኮት መተላለፍ ጀምሯል።

የሐሙስ መረጃዎችን ዘውትር አርብ "አርትስ ስፔሻል" በሚል ርዕስ ምጥን ፕሮግራሙን ወደ እናንተ ያደርሳል።

"የአርትስ ስፔሻል" ምጥን ፕሮግራም ዘውትር አርብ ከምሽቱ 1:00 እና በድጋሚ ከምሽቱ 4:00 ላይ በአርትስ ቴሌቪዥን የዜና ሠዓት ይተላለፋል።

በተጨማሪም በሚሊዮኖች ተከታይ ባለው በ"Arts tv World" የዩቲዩብ ቻናል ይሰራጫል።

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ:

አርዕስት:

አርዕስት መረጃዎች:

1. "ታስፈልገኛለህ" ፊልም ለእይታ በቃ።

2."ዴጊያ" ትውፊታዊ ተውኔት ለመድረክ ሊበቃ ነው።

3.የተቃውሞ የገጠመው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ነገ በለንደን ከተማ ይካሄዳል።

4."ውሃዬን ሸጩ ኮዳ የገዛኹለት" መጽሐፍ የፊታችን ሰኞ ይመረቃል።

8. "ጥያቄ ፣ መልስ፣ መኖር" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ  ሰኞ ይከፈታል።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/aV6SWpQaSRE?si=XFpyvyyxFHRsDcQk

📌መልካም ምሽት


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1
📌"ማለዳ ደጃፍ ላይ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

ከዚህ ቀደም አነጋጋሪ በነበረው "ከአመጿ ጀርባ" በተባለው መጽሐፏ የምትታወቀው ደራሲ ኤደን ሀብታሙ "ማለዳ ደጃፍ ላይ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ እንደምታበቃ ይፋ አድርጋለች።

ደራሲ ኤደን ሀብታሙ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"ጥቂት የማትባሉ የፌስ ቡክ እንዲሁም የአካል ወዳጆቼ፡ “መቼ ነው ሁለተኛ መጽሐፍሽን የምታቀምሺን?” ባላችሁኝ መሰረት እነሆ በጣም በቅርቡ ላዳርስልችሁ ሽር ጉድ እያልኩ ነው"ብላለች።

በተጨማሪም ስለመጽሐፉ ይዘትም"ትንሽ ቆም ብሎ ላስተዋለው፣ ማለዳ ደጃፍ ላይ፣ ስስ ተስፋና አዳዲስ ህልሞች በመስኮታችን ቀዳዳ ሾልከው ይገባሉ። ህይወት ሁሌም ማለዳ ደጃፋችን ላይ ታንኳኳለች።በማለዳ በራችንን ወለል አድርጋን ከከፈትን ደግሞ የበረታ ጸሀይ ያልነካቸው፣ ብዙ ትኩስ የተስፋ ፍንጥቅጣቂዎች፣ በጸሀይ ጨረሮችን ተሳፍረው ከቤትችን ይዘልቃሉ፣ ከቀናን ከሞላልን" ብላለች።

መጽሐፉ በ277 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ500 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚቀርብ ኤቨንት አዲስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

መጽሐፍ በቅርቡ በታላቅ ሥነሥርዓት ተመርቆ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።

አስቀድሞ ለንባብ የበቃው የደራሲዋ "ከአመጿ ጀርባ" መጽሐፍ በዛጎል መጻሕፍት ባንክ "የ2013 የዓመቱ የልቦለድ መጽሐፍ" በሚል ተመርጦ እንደነበር ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የቴዲ አፍሮ የለንደኑ ኮንሰርት እንዴት ነበር?

ከሰሞኑ ውዝግብ መነሻ ይሁን ሌላ ምክንያት የኮንሰርቱ ስፍራ እስከመጨረሻዋ ቀን አልተገለፀም ነበር ሊቀር ይችላል በሚል የጎንዮሽ ወሬዎችም በርትተዉ ነበር።

በመጨረሻም ቴዲ ረፋድ ላይ በማህበራዊ ድህረገፁ የተጠባቂዉን ኮንሰርት ስፍራ ይፋ አደረገ እናም ከተለያዩ ከተሞች ጉዞ ወደ ለንደን ተጀመረ።

ሙዚቃን ሁሌ ሳይሆን በድንገት መርጠዉ ከሚሰሙት ዘንድ ብሆንም ባገኘሁት የተሳትፎ እድል ቴዲን መድረክ ላይ ለማየት በሠዓቴ dominion center ተገኘሁ።

ከሁለት መቶ አንበልጥም መጀመሪያ ወደ አዳራሹ የዘለቅነዉ በሂደት ግን የሰዉ ቁጥር እየጨመረ መጣ በዚህ መሀል በተደጋጋሚ ጌታቸዉ ማንጉዳይ የቴዲ ማናጀር ላይ አይኔ አርፏል።

ሁለት እጁን ኪሱ ላይ ከቶ የሰዉን መግባት ይጠባበቃል አዳራሹን ይቃኛል ከፊት ከጀርባ ይመላለሳል ደጋግሞ ይመጣል ይሄዳል በመጨረሻም በተሳታፊዎች ያለመገኘት ስጋት የተጀመረው ኮንሰርት የቤቱን አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበ።

ከ1ሺ በላይ ሰዉ በተለያዩ ፕሮግራሞች ያላስተናገደዉ ሴንተር መያዝ በሚገባው ልክ ከ2000 በላይ ታዳሚ በሁሉም ቦታ አስተናገደ።

በኮንሰርቱ መሀል 2ት ግዜ የአዳራሹ ማናጀር እባካችሁ ባልኮኒዉ ላይ ያላችሁ አትዝለሉ ፕሮግራሙን እናቋርጣለን እስኪል ድረስ።

ህዝቡ በኮርኩማ አፍሪካ ተጀምሮ በጥቁር ሰዉ ሙዚቃ እስከተጠናቀቀበት 11 ዘፈኖች ከተለያዩ ከልበሞቹ ተመርጠዉ በቀረቡበት ምሽት ተደስቷል።

ቴዲ አፍሮ አንድ ቦታ ላይ ስለ ሀገሩ ሲዘፍን በስሜት አልቅሷል።የመድረክ ዝግጅት lighting sound ምናምን አይጠየቅም አንደኛ የነበረዉ ዝግጅት ደስ በሚል ትዝታ  በሀገረ እንግሊዝ ሰዓት አቆጣጠር እኩለ ለሊት ላይ ተጠናቀቀ።

Via ጋዜጠኛ ሀብታሙ ገደቤ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የጠርሲዳ ከበደ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

“ውሃዬን ሸጬ ኮዳ የገዛኹለት” በሚል ርዕስ የተፃፈው የደራሲ ጠርሲዳ ከበደ መጽሐፍ ዛሬ ሰኞ የካቲት 10 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11፡00 ላይ በ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በይፋ ይመረቃል፡፡

የመጽሐፍ ምርቃት ኹነቱን ፤ ፊካ ሶሻል ኢንተርፕረነርስ ፤ ሲግናል ኤቨንትስ  እና ሄኖክ የ'ታገኝ ልጅ በጋራ በመኾን ሸጋ አድርገው አዘጋጅተውታል፡፡

ተዋናይ እና አዘጋጅ ተስፉ ብርሃኔ ፣ ገጣሚ እና ተዋናይ ዋስይሁን በላይ ፣ መምህርና ተዋናይ ፈቃዱ ከበደ ፣ መምህርና ተዋናይ ፉአድ መሐመድ ፣ ተዋናይት ሕሊና ሲሳይ ፣ ተዋናይ ሔኖክ ዘርአብሩክ  ፣ ድምጻዊ አንተነህ ምናሉ ፣ ተዋናይት ሕይወት ወንድወሰን ፣ ገጣሚ ሂክማ ፋንቱ  ፣ ገጣሚ በረከት ተስፋዬ ፣ ብርኩማ ባንድ  ፣ ዐራት ነጥብ የኪነጥበብ ቡድን  እና  ፊካ ኳየር የ 124 ደቂቃዎች የጥበብ ‘ብፌ’ ሰድረዋል።  በድምሩ 70 ገደማ በየዘርፉ ያሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እንደሚሳተፉበትም ሰምተናል።

አዘጋጆቹ “ሥነ፟-ጽሑፍን ሲሉ ዋጋ ለከፈሉ ኹሉ ክብር ስንል ለፍተንበታል!” ያሉት ይኽ ኹነት ከደራሲዋ መጽሐፍ የተወሰደ የአንዲት ሴት ተውኔት ፣ የቀጥታ መድረክ ሙዚቃ እና ኮንቴምፖራሪ ዳንስ፣ ሙዚቃዊ ተውኔት ፣ ማራኪ አንቀፆች እና ግጥምን ያካተተ ኹነት አዘጋጅተው  ሸጋ ምሽት ሊሰጡን ቀጠሮ አስይዘውናል፡፡

በምሽቱ ተጋባዝ እንግዶችም የሚኖሩ ሲኾን፤ በተጨማሪ ከደራሲዋ ጋር የሚኖር የመጽሐፍ ማስፈረም ዝግጅትንም ያካተተ ነው ብለዋል፡፡ ኹነቱ ሥነ፟-ጽሑፍን ለሚወዱ ኹሉ ክፍት መሆኑንም ሰምተናል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የሙዚቀኛ ተፈሪ አሰፋ የክብር ስንብት እና የሥርዓተ ቀብር ሥነሥርዓት በቀጣይ ረቡዕና ሐሙስ ይከናወናል
           
ተወዳጁ ሙዚቀኛ ተፈሪ አሰፋ በሀገረ አሜሪካ በሕክምና ላይ እንዳለ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

አስከሬኑ ረቡዕ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ወደ ሀገሩ የሚመጣ ሲኾን፣ በማግስቱ፥ ሐሙስ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ የክብር ስንብት መርኀ ግብር ይከናወናል።

ከክብር ስንብቱ መርኀግብር በኋላ፣ ከቀኑ 6:30 ላይ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ይፈጸማል።

በክብር ስንብት እና በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ተወዳጁን ጥበበኛ ተፈሪ አሰፋን እንድንሰናበተው ኮሚቴው የአክብሮት ጥሪውን አቅርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የሽርሽር ጉዞ ወደ ላንጋኖ እና አቢያታ-ሻላ ብሄራዊ ፓርክ ከገሊላ ትራቭል ጋር 👏

📅 Date: February 22 & 23 / 2025 /
የካቲት 15 እና 16 / 2017 E.C
Duration: 2 Days & 1 Night
🚌 Departure:
📍 mexico wabi shebele
⌚️ 6:00 AM / 12:00 LT

Price(💵): 6000 ETB for Locals

Package includes:
🚎 ትራንስፖርት / Transportation
🥪 ቁርስ / Breakfast /X2/
🍔 ምሳ / Lunch /X2/
🍖 እራት / Barbecue Dinner /X1/
🥤 የታሸገ ውሃ / Bottled Water
🎫 የመግቢያ ዋጋ / Entrance Fees
🗺 የአስጎብኚ / Local Guide
🔥 የምሽት እሳት ዳር ጨዋታ / Campfire
🏕 ማደሪያ ድንኳን / Tent
📸 የፎቶግራፍ / Photography

For more information call on ☎️ 0919874598

@gelilatravel are excited to invite you to a unique and exhilarating campaign trip to Langano. This is more than just a getaway; it’s an opportunity to explore, relax, and create lasting memories.

Tiktok link:

https://vm.tiktok.com/ZMkW6bXjK/
📌 አምፊ የጥበብ ዝግጅት "በአንድ ቲኬት ህይወት እናድን" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ልዩ ፕሮግራም ቅዳሜ ይካሄዳል።

አዳማ ዩኒቨርሲቲ የስነጽሑፍ እና ትያትር ክበብ እና አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ ታዋቂ የጥበብ ሰዎች የሚዘጋጅ "አምፊ ጥበባት" የተሰኘ የጥበብ ፕሮግራም ቅዳሜ የካቲት 15 ከ 9፥00 -11:30 አዲስ አበባ ከቦሌ ወደ 22 በሚወስደው መንገድ 24 ባለው መሶብ የባህል አዳራሽ  ተመርቆ ይጀመራል።

በዚህ ፕሮግራም ግጥሞች፣ ቀልዶች፣ ሙዚቃ እና ድራማ የሚቀርቡ ሲሆን፣ ይህን ፕሮግራም ለየት የሚያደርገው፣ ከዚህ ፕሮግራም የሚገኘው ገቢ በካንሰር በሽታ እየተሰቃዩ ለሚገኙ አንድ የክበባችን አባል እናት ማሳከምያነት የሚውል ነው።

በዕለቱ መገኘት ብንችልም ባንችልም የቲኬቱ ዋጋ 250 ብር ብቻ ስለሆነ አንድ ቲኬት በመግዛት መተባበር መልካም ነው።  ለመመዝገብ  https://forms.gle/niyxbMBzW7qcZBWm8
"ማለዳ ደጃፍ ላይ" መጽሐፍ የፊታችን አርብ ይመረቃል

በደራሲ ኤደን ሀብታሙ የተዘጋጀው "ማለዳ ደጃፍ ላይ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በመጪው አርብ የካቲት 14 ቀን 2017 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

"ማለዳ ደጃፍ ላይ" የድህረ ዘመናዊ ልቦለድ (post modernism writing style) የአጻጻፍ ቅርጽ የያዘ፣ በ277 ገጾች የተቀነበበ መጽሀፍ ሲሆን በቅርጹም ሆነ በአቀራረቡ ለየት ያለ መልክ ይዞ ለመምጣት የሞከረ የልቦለድ ስራ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በ13 ምዕራፎች (በ13 ወራት በተወከሉ) በሥነቃል እና በሥነሥዕል የተሰነደ የልቦለድ ስራ ነው። አስራ ሶስቱ ታሪኮች ለብቻቸውም ሆነ አንድ ላይ በህብረት መቀናጀት የሚችሉ የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ አንኳር ገጸባህርያትን አቅፎ የያዘ ነው።  

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በይዘቱ ከማህበራዊ፣ ጥበባዊ እና አሁናዊ (current affairs)፣ስነልቦናዊ እና ሰዋዊ (humanistic) ጉዳዮችን በጥልቅ የሚዳስስ ስራ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” አርብ የካቲት 14፣ ከቀኑ 10፡00 ሰአት ላይ የተለያዪ የክብር እንግዶች፣ የጥበብ ባለሞያዎች እና የመጽሐፍ አፍቃሪያን በተገኙበት በዋልያ መጽሐፍ መደብር ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌መቅረዝ ሥነኪን ዛሬ ይካሄዳል

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር ለሁለት ዓመታት የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ሐሙስ ዛሬ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ክብረ በዓል ኪነጥበባዊ ዝግጅት ላይ ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው የክብር እንግዳ በመሆን የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌አላቲኖስ የፊልም ውይይት ዛሬ ይካሄዳል

አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ዛሬ ሐሙስ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ የቀይ ካርድ ፊልም ላይ ውይይት ያካሄዳል።

በዕለቱም የቀይ ካርድ ፊልም አዘጋጅ የአብሥራ ዶጮ በክብር እንግድነት ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ’ መጽሐፍ ሦስተኛ ክፍል የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል

በጋዜጠኛ ገነት አየለ የተዘጋጀውና ‘በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታ’ የተሰኘው መጽሐፍ ሦስተኛ ክፍል የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ በዋልያ መጻሕፍት ይመረቃል።

የፈረንሳይ ተወላጅ የሆነው አርኖ ሚሼል ዳባዲ ከወንድሙ ጋር ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ጊዜ ያየውን፣ የተመለከተና የሰማውን ያኖረበት ይህ መጽሐፍ፥ በዋናነት በዘመነ መሳፍንት የነበረችውን ኢትዮጵያ የሚያመላክት ነው። ከዛም አልፎ መልክዓምድሩንና በዘመኑ የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን ባህል፣ ስርዓት፣ መልክ፣ ወግና ሥርዓት፣ አለባበስንም ጭምር በማራኪ ትረካ የሚያስቃኝ ነው። ይህን መጽሀፍ ለገነት ያሳተመላት ዋልያ መጽሀፍት ሲሆን ድርጅቱ በርካታ ድርሰቶች ለህትመት ማድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡

ገነት ይህን መጽሐፍ ከፈረንሳይኛ ወደ አማርኛ በመመለስ የመጀመሪያውን እትም በ2009 ዓ.ም ለንባብ አብቅታለች። በ2013 ዓ.ም ደግሞ ኹለተኛውን ክፍል ለተደራስያን ያደረሰች ሲሆን፥ መጽሐፉ አራት ክፍሎች ያሉት መሆኑን ጠቅሳ፥ አራተኛውና የመጨረሻው የመጽሐፉ ክፍል መተርጎም መጀመሯን አሳውቃለች።

በዚህ የምርቃት መርሀ ግብር ላይ ደራሲ አበራ ለማ፣የታሪክ ባለሙያ ዶክተር ዘካርያስ አምደብርሀን ፣የፍልስፍናው ሰው ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ እና ዶክተር አውግቸው አማረ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።

ጋዜጠኛ፣ ደራሲና ተርጓሚ ገነት አየለ ከዚህ ቀደመ ‘የመንግሥቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች’ እንዲሁም ‘ትንሿ ሀገር’ የተሰኙ መጽሐፎችንም ለአንባብያን አድርሳለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"የብሌን አንዳች" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በጋዜጠኛ እና ደራሲ ዋለልኝ አየለ የተዘጋጀው "የብሌን አንዳች" የተሰኘ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት ለአንባቢያን እንደቀረበ ከደራሲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በ240 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ 24 ርዕስ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል በ400 ብር የጀርባ ዋጋም ለአንባቢያን ቀርቧል።

ሁለት ጋዜጠኞችን እና አንድ የራሱን ነፃ ሕይወት የሚከተል ፍስሐ የሚባል ወጣት ዐቢይ ገጸ ባህሪያት ያደረገው ‹‹የብሌን አንዳች›› መጽሐፍ፤ በተለይም በፍስሐ በኩል የኢትዮጵያን ባህል፣ ወግ፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ ይሞግታል፡፡ በሁለቱ ጋዜጠኞች በኩል ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና የፍቅር ጉዳዮችን ያስቃኘናል፡፡ አረቄ ቤትም ካፌም በመገኘት ያስተዋላቸውን ነገሮች፣ የሰዎችን የሕይወት ገጠመኞች ያስቃኛል።

የደራሲ ዋለልኝ አየለ የመጀመሪያ ሥራ የሆነው ይህ መጽሐፍ በጃዕፋር መጽሐፍት (ሜክሲኮ) በኤዞፕ መጽሐፍት መደብር (ፒያሳ) ይገኛል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌በእይታ ላይ የሚገኝ የሥዕል አውደርዕይ !

ሠዓሊ ትዕማር ተገኝ እና ሠዓሊ ፈትለወርቅ ታደሰን “Question & Assured Existence “ በሚል ርዕስ ያዘጋጁት የሥዕል ዓውደ ርዕይ ከየካቲት 10 ቀን 2017 ጀምሮ በገብረ-ክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ሙዚየም በእይታ ላይ ይገኛል።

በዚህ ሳምንት የተከፈተው የሥዕል ዓውደ ርዕይ ከሰኞ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ/ም  እስከ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር ለተመልካቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል::

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"ማለዳ ደጃፍ ላይ" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

በደራሲ ኤደን ሀብታሙ የተዘጋጀው "ማለዳ ደጃፍ ላይ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ አርብ የካቲት 14 ቀን 2017 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

"ማለዳ ደጃፍ ላይ" የድህረ ዘመናዊ ልቦለድ (post modernism writing style) የአጻጻፍ ቅርጽ የያዘ፣ በ277 ገጾች የተቀነበበ መጽሀፍ ሲሆን በቅርጹም ሆነ በአቀራረቡ ለየት ያለ መልክ ይዞ ለመምጣት የሞከረ የልቦለድ ስራ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በ13 ምዕራፎች (በ13 ወራት በተወከሉ) በሥነቃል እና በሥነሥዕል የተሰነደ የልቦለድ ስራ ነው። አስራ ሶስቱ ታሪኮች ለብቻቸውም ሆነ አንድ ላይ በህብረት መቀናጀት የሚችሉ የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ አንኳር ገጸባህርያትን አቅፎ የያዘ ነው።  

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በይዘቱ ከማህበራዊ፣ ጥበባዊ እና አሁናዊ (current affairs)፣ስነልቦናዊ እና ሰዋዊ (humanistic) ጉዳዮችን በጥልቅ የሚዳስስ ስራ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” አርብ የካቲት 14፣ ከቀኑ 10፡00 ሰአት ላይ የተለያዪ የክብር እንግዶች፣ የጥበብ ባለሞያዎች እና የመጽሐፍ አፍቃሪያን በተገኙበት በዋልያ መጽሐፍ መደብር ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

ዘውትር ሐሙስ በኤቨንት አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሰራጭ የቆየው "የሐሙስ መረጃዎች" ልዩ ጣዕም ጨምሮ በቴሌቪዥን መስኮት መተላለፍ ጀምሯል።

የሐሙስ መረጃዎችን ዘውትር አርብ "አርትስ ስፔሻል" በሚል ርዕስ ምጥን ፕሮግራሙን ወደ እናንተ ያደርሳል።

"የአርትስ ስፔሻል" ምጥን ፕሮግራም ዘውትር አርብ ከምሽቱ 1:00 እና በድጋሚ ከምሽቱ 4:00 ላይ በአርትስ ቴሌቪዥን የዜና ሠዓት ይተላለፋል።

በተጨማሪም በሚሊዮኖች ተከታይ ባለው በ"Arts tv World" የዩቲዩብ ቻናል ይሰራጫል።

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ:

አርዕስት መረጃዎች:

1."እንጦጦ  ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" ወደ ቀድሞ ሰሙ  "ተፈሪ መኮንን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" ተብሎ ተመልሷል ።

2.በ13 ወራት የተወከሉ 13 ታሪኮችን የያዘው የደራሲ ኤደን ሀብታሙ "ማለዳ ደጃፍ ላይ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ።

3."በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ"  መጽሐፍ ሶስተኛ ክፍል ነገ ይመረቃል።

4.ከፍተኛ ውጪ እንደወጣበት የተነገረውና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የተዘጋጀው "አባ መልካ" ፊልም እይታ ሊበቃ ነው።

5."የ1966 ሕዝባዊ አብዮት እና መኢሶን አንዳንድ ማስታወሻ" የተሰኘ መጽሐፍ ላይ እሁድ ውይይት ይካሄዳል።

6.ዓለምአቀፉ የሬጌ አቀንቃኝ አልቦሮሲ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ዝግጅቱን ሊያቀርብ ነው።


"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/g7fKBrVde34?si=cj0ncJ24szpqAWFz

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"ማለዳ ደጃፍ ላይ" መጽሐፍ ተመረቀ

በደራሲ ኤደን ሀብታሙ የተዘጋጀው "ማለዳ ደጃፍ ላይ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ አርብ የካቲት 14 ቀን 2017 አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

በመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ በሕይወት እምሻው እና እሱባለው አበራ የመጽሐፍ ዳሰሳ የቀረበ ሲሆን አዜብ ወርቁ፣ ቸርነት ወ/ገብርኤል፣ ግሩም ተበጀ እና በሁሉም አለበል ከመጽሐፉ የውስጥ ገጾች ለታዳሚያን አንብበዋል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የደራሲ ኤደን ሀብታሙ የአስረኛ ክፍል የአማርኛ መምህሯ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። መጽሐፉንም በክብር መርቀዋል።

"ማለዳ ደጃፍ ላይ" የድህረ ዘመናዊ ልቦለድ የአጻጻፍ ቅርጽ የያዘ፣ በ277 ገጾች የተቀነበበ መጽሀፍ ሲሆን በቅርጹም ሆነ በአቀራረቡ ለየት ያለ መልክ ይዞ ለመምጣት የሞከረ የልቦለድ ስራ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በ13 ምዕራፎች (በ13 ወራት በተወከሉ) በሥነቃል እና በሥነሥዕል የተሰነደ የልቦለድ ስራ ነው። አስራ ሶስቱ ታሪኮች ለብቻቸውም ሆነ አንድ ላይ በህብረት መቀናጀት የሚችሉ የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ አንኳር ገጸባህርያትን አቅፎ የያዘ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በይዘቱ ከማህበራዊ፣ ጥበባዊ እና አሁናዊ ፣ስነልቦናዊ እና ሰዋዊ ጉዳዮችን በጥልቅ የሚዳስስ ስራ ነው።