📌"ዛኘ" ነጠላ ሙዚቃ ተለቀቀ
የድምፃዊ ፈለቀ ማሩ ''ዛኘ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የጉራጊኛ ነጠላ ሙዚቃ በሪቦ አዲስ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ደርሷል።
የሙዚቃው ግጥም በፈለቀ ማሩ የተሰራ ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር በኩል በኃይሉ ዘርይሁን ተሳትፏል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

📌"የሕይወት ታሪክ" ተውኔት በልዩ ፕሮግራም ዛሬ ይቀርባል።
ድርሰቱ እና ዝግጅቱ የነብዩ ባዬ እና የቢንያም ወርቁ የሆነው "የሕይወት ታሪክ" አዲስ ተውኔት ዛሬ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በልዩ ዝግጅት ይቀርባል።
ይህ ተውኔት ከዚህ ቀደም በሸገር ራዲዮ በሬድዮ ድራማ መልክ ቀረቡ የነበረ ሲሆን አሁን በመድረክ ተውኔት ቅርጽ ተሰርቷል ተብሏል።
በ"ሕይወት ታሪክ" በተውኔት ላይ ቢንያም ወርቁ እና ፀደይ ፋንታሁን ለሁለት ይተውናሉ።
ተውኔቱ በነባ ጥበባት እና ኮምኒኬሽን የቀረበ ነው።

📌አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ አረፈ
አንጋፋው አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
አርቲስት እንቁስላሴ 30 በሚሆኑ ፊልሞች እና ቴአትሮች ላይ በትወና በመሳተፍ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አገኝቷል፡፡

📌በፎቶግራፍ ጥበብ ላይ ሙያዊ ውይይት ተከናወነ
በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል ከአዲስ አበባ ፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማኅበር ጋር በመተባበር "በፎቶግራፍ ጥበብና በለውጥ ሰበዞች" ዙሪያ ሙያዊ ውይይት ጥር 9 2017 ዓ.ም በአካዳሚው ውስጥ አከናውኗል።
በሙያዊ ውይይቱ ላይ የሥነጥበብ ባለሙያና ኲሬተር ቆንጅት ሥዩም፣ ማኅደረ ኃይለሥላሴ፣ ሙሉጌታ አየነ፣ አንቶኒዮ ፊዮሬንቴ እና ሚካኤል ፀጋዬ የተሳተፉ ሲሆን፣ ወ/ሮ ቆንጅት የውይይት ሐሳቦችን በማንሳትና ጥያቄዎችን በማጫር ውይይቱን አጋፍራለች።
ከታኅሳስ 12 2017 ዓ.ም አንስቶ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ በቆየው "የለውጥ ሰበዞች" የተሰኘውን የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ መነሻ በማድረግ አራቱም ፎቶግራፈሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ስላገኟቸው ዕውቅናዎችና በሙያቸው ስላጋጠሟቸው ፈተናዎች በማንሳት ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
አካዳሚውና ማኅበሩ ከታህሳስ 12 እስከ ጥር 9-2017 ድረስ ያሰናዱት ዐውደ ርዕይና ውይይት የፎቶግራፍ ጥበብ በሀገሪቱ እንዲጎለብት መሰል ዝግጅቶች እንዲቀጥሉ የሚያበረታታ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎችና ተወያዮች ሰፊና ጥልቅ ሙያዊ ሀሳቦችን በማንሳት ደማቅ ተዋስዖ አድርገዋል።
Via የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

📌የኢትዮ ጃዝ ፈጣሪ የሆነው ሙላቱ አስታጥቄ ‹‹ሙዚቃ ሳይንስ ነው ስለዚህም ሳይንቲስቶቹን ማክበር ይገባናል›› ሲል ተናገረ፡፡
ሙላቱ ከፎርቹን ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደገለፀው ሙዚቃ ልክ እንደኬሚስትሪ ሁሉ የተለያዩ ድምፆች ተደባልቀውና ተዋህደው ጣእመ ዜማን ይፈጥራሉ፡፡
ሲናገርም ‹‹አውሮፓዊያን ሙዚቃን እንደሳይንስ ይመለከቱታል፡፡ አስፕሪንን ለመፍጠር የተለያዩ ኬሜካሎችን እንደሚያዋህዱት ሁሉ ሙዚቃንም እንደሳይንስ ቆጥረው ጥልቅ ምርምር በማድረግ ሙዚቃን ያመርታሉ፡፡ ስለዚህም በሳይንስና በሙዚቃ መካከል ምንም ልዩነት የለም፡፡›› ብሏል፡፡ ጨምሮም አፍሪካዊያን ደግሞ ለሙዚቃ ግብአት የሚሆኑትን ለአውሮፓ እንደሚያበረክቱ አስረድቷል፡፡
በአንድ ወቅት የድሮው አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ከፍቶ እንደነበር ያወሳው ሙላቱ በተለያዩ ምክንያቶች መቀጠል እንዳልቻለ ጠቅሷል፡፡ ይሁንና በርካታ ልጆች በትክክለኛው መንገድ ላይ መሄድ አለመቻላቸው እንደሚያሳዝነው አስረድቶ ‹‹ሙዚቃ ሳይንስ ቢሆንም አፍሪካዊያን ግን እንደጊዜ ማሳለፊያና ለዳንስ ብቻ ይጠቀሙበታል›› ካለ በኋላ ሙዚቃ እንደማንኛውም ጥበብ የትምህርት ስርአቱ ውስጥ መካተት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ሙዚቃ በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ቢካተት ወጣቶች የሙዚቃን ሳይንስነት እንደሚረዱትም አስታውቋል፡፡
Via ዘሀበሻ

📌ተወዳጁ ጋዜጠኛና ደራሲ ገነነ መኩሪያ ሊብሮ በሞት ከተለየ ዛሬ አንድ አመት ሆነው ።
ጋዜጠኛ ፥ ፀሀፊ ፥ ደራሲ ፥ ታሪክ አሻጋሪና ፥ የተራማጅ ሀሳብ ባለቤት ፥ እንዲሁም የአዲስ ሀሳቦች አፍላቂ የሆነው ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) በሞት ከተለየን ዛሬ አንድ ዓመት ሆነው።
የገነነ ቤተሰቦቹም " የገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ሞት ለታሪክ አድማጭና ፥ ለታሪክ አንባቢው ፥ ለታሪክ ነጋሪና ለታሪክ ተረካቢው እንዲሁም ሁሌም አዲስ ሀሳብና መንገድን ለሚናፍቀው ለሀገራችን የእግር ኳስ ስፖርት ትልቅ ሞት ሲሆን ከሁሉ በላይ ደግሞ ለእኛ ለቤተሰቦቹ ሀዘኑ በቃል የማይገለፅ እጅግ ከባድ ሀዘን ነው" ብለዋል።
የጋዜጠኛና ደራሲ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የአንደኛ የሙት ዓመት መታሰቢያንም ነፍሱ ባረፈችበት በዛሬዋ ዕለት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ አካሄድ መሠረት በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በፀሎት እንደታሰበ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ቤተሰቡ በተጨማሪ " እኛ ቤተሰቦቹ እርሱን ለማሰብም በቁስቋም ጌርጌሴኖን የመርጃና ማገገሚያ ማዕከል የሚገኙ ወገኖቻችንን በመመገብም እንዘክረዋለን" ብለዋል።
"የገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) እልፈት ከተሰማ ጀምሮ ሀዘናችንን ሀዘናችሁ አድርጋችሁ ከሀገር ውስጥም ይሁን ከውጪ ሀገር ያፅናናችሁን ወዳጆቹ በሙሉ ስለሁሉም ነገር በፈጣሪ ስም እጅግ አድርገን ዛሬም እናመሰግናችኋለን" ሲሉም ምስጋናቸውን አቅረበዋል።

📌የአርቲስት እንቁስላሴ የቀብር ሥነሥርዓት ተፈፀመ
የአርቲስት እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ የቀብር ሥነሥርዓት ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም በቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እንደተፈጸመ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአርቲስት እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ በተወለደ በ71 ዓመቱ ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 11/2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡
አርቲስት እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ ከአባታቸው ከአቶ ወ/አገኘሁ ኃይሌ እና ከእናታቸው ወይዘሮ ዘውድነሽ ብሩ በጥቅምት 27/1946 በአዲስ አበባ ከተማ መወለዱን የህይወት ታሪኩ ያትታል።
ከባለቤቱ ወይዘሮ አይናለም ወርቁ 3 ሴቶች እና 3 ወንድ ልጆች ያፈራ ሲሆን እንዲሁም 12 የልጅ ልጆችን አፍርቷል፡፡

📌የአስትሮ ፎቶግራፊና የከዋክብት ምልከታ ተካሄደ
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሥነ - ጥበብና የሳይንስ ማዕከላት ጋር በመተባበር የአስትሮ ፎቶግራፊና የከዋክብት ምልከታ አከናውኗል፡፡
በፀሐይ ምልከታ መርሐግብር ቴሌስኮፕን በመጠቀም የፀሐይን ፎቶስፊር እንዲሁም የፀሀይን ስፖቶች ታዳሚያን መመልከት ችለዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም አስትሮ ፎቶግራፈር ክብረት አፅባሓ በቴሌስኮፕ ታግዘው የተነሱ የሰማይ አካላት ፎቶግራፎችን ያሳዩ ሲሆን ስለአስትሮ ፎቶግራፊ ሙያ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በማታው መርሐግብር በሶሳይቲው ባለሙያ ሊዲያ ዲንሳ አስተባባሪነት ተሳታፊዎች ቬነስን እና ጁፒተርን ከአራት ጨረቃዎችዋ ጋር መመልከት እንዲሁም ሌዘር ፖይንተር/ የብርሃን መጠቆሚያ በመጠቀም ስለተለያዩ የሰማይ አካላት አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።
ይህም ተሳታፊዎችን የሚያስተምር እንዲሁም የተማሩትን በተግባር ለማስደገፍ ያገዘ መርሐግብር ሆኖ አልፏል፡፡
ጥር 9/2017 በተካሄደው በዚህ ፕሮግራም በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎችና ታዳሚያን ተገኝተዋል፡፡
©️መረጃው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ነው።

📌"የሎሚ ጭማቂ ትዝታ" አርብ ይመረቃል
በደራሲ አህመድ ሁስ የተዘጋጀው "የሎሚ ጭማቂ ትዝታ" የተሰኘ የረጅም ልቦለድ መጽሐፍ አርብ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።
በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ላይ አርቲስት ሚካኤል ታምሬ፣ደራሲ ህይወት እምሻው፣ ገጣሚ ሚካኤል ምናሴ፣ ገጣሚ ኪሩቤል ዘርፉ ፣ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋና ሌሎችም ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 ጎዶ'ን ጥበቃ
ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ዋዋጎ
ድርሰት: ታረቀኝ ብርሃኑ
አዘጋጅ: ጥላሁን ዘውገ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍የሕይወት ታሪክ
ድርሰትና ዝግጅት ነብዩ ባዬ እና ቢንያም ወርቁ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

📌የሙዚቃ ባለሞያ ተፈሪ አሰፋ አረፈ
የድራም የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቹ እና የነጋሪት ባንድ መስራች የሆነው ተፈሪ አሰፋ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ ተሰምቷል።
ተፈሪ አሰፋ የኢትዮጵይ ሙዚቃ ካለበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ የያዘውን ሞያ በውጭ ሃገር ተምሮ እና በሚገባ አጠናቆ ወደ ሃገሩ ኢትዮጵያ በመመለስ የድራም አጨዋወት ሞያ በሃገራችን በብዙ ሰው እንዲወደድ ያደረገ ታታሪ የሙዚቃ ሰው ነበር።
የሃገራችንን ሙዚቃ ድምበር ተሻጋሪ እንዲሆን እና በመላው ዓለም ተድማጭ እንዲሆን ጥናት አድርጎ የሙዚቃ አልበም በማስቀረፅ በዓለም ገበያ ላይ እንዲውል ያስቻለ ፣የድርሻውን የተወጣ እና እየተውጣ የሚገኝ ትጉህ፣ ታታሪ፣እውቀቱን ለሌሎች አሳልፎ መስጠትን የማይሰስት፣ ብዙ የድራም ተጫዋቾችን ያፈራ፣የድራም አጨዋወት ጥበብን በሚገባ በተማሪዋቹ አዕምሮ ውስጥ ያፅነሰ፣ ቀና ፣ልበ እሩሩህ እና ከሁሉም ሰው ጋር ተግባቢ እና መልካም ሰው ነበር።
Via አክሊሉ ወልደዮሀንስ

📌"ነገረ መጻሕፍት" ዛሬ ይካሄዳል
በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት ዛሬ ቅዳሜ ጥር 17 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዚህ መሰናዶ ላይ ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ እና ዶ/ር አንዱዓለም አባተ ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ አብይ ርዕሰ ጉዳይ "የተደበቁ እውነቶች የተጋረዱ ሀቆች" ይሰኛል።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

Event Addis Media
Photo
📌«ማህሙድ መዝፈን አልነበረበትም፤የሙዚቃው ድግስም ዓላማውን ስቷል» የጣዕም ልኬት አዘጋጆች
የሙዚቃ ባለሙያዎቹን ሰርፀ ፍሬ ስብሃት እና ምዕራፍ ተክሌን ያጣመረው በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 6 እስከ 8 ሰዓት የሚቀርበው "የጣዕም ልኬት" መሰናዶ በጥር 17 / 2017 ዓ.ም ቆይታው ሳምንታዊ ዳሰሳውን ያደረገው ለአንጋፋው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ የተዘጋጀውን የሙዚቃ ድግስ በተመለከተ ነው።
የሙዚቃ መርሃግብሩ በቀረበበት ሳምንት በከተራና ጥምቀት በዓል ልዩ ዝግጅት ምክንያት በወቅቱስለ ኮንሰርቱ ማንሳት እንዳልተቻለ አዘጋጆቹ ጠቁመዋል።
አዘጋጆቹ 'የሳምንቱ የሙዚቃ አምባ' ላይ ዳሰሳ ባደረጉበት የአንጋፋው ድምፃዊ መሀሙድ አህመድ የሙዚቃ ዝግጅት መልካም ጎኖች ቢኖሩትም ሊስተካከሉ ይገባቸው የነበሩ መሰረታዊ ነጥቦችን አስቀምጠዋል።
ድምፃዊ መሀሙድ አህመድ የኢትዮጵያ የሙዚቃ መልክ ተደርጎ የሚቆጠር እና የሚወደስ ታላቅ ድምፃዊ ከመሆኑ አንፃር እርሱን አክብሮ የተሰናዳ ዝግጅት መሆኑ ከመርሃ ግብሩ ጀርባ ያሉትን እንደሚያስመሰግን አዘጋጆቹ ገልፀው ከድምፃዊው የቀደሙና ዛሬ ላይ በህይወት ያጣናቸው ታላላቅ ሥራን የሰሩ ድምፃውያንን እንዲህ ባለ መልኩ ሳናከብራቸው እንደማለፋቸው ይህ ዝግጅት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠውም አንስተዋል።
መሀሙድ አህመድ በሙዚቃ ሕይወቱ የደረሰበት ደረጃ እና ከፍታ «ለዚህ ክብር የሚመጥን የጥበበ ሰው እንዲሆን ያደርገዋል» ያሉት አዘጋጆቹ ከእሱ በተጨማሪ በሥራቸው የላቀ ከፍታ ላይ ደርሰው ልክ እንደ እሱ አክብረን ላልሸኘናቸው ሁሉ 'የመንፈስ ውክልናን የሚወስድ ነው።" ሲሉ ገልፀዋል።
ከዚህ አንፃር ለመርሃ ግብሩ መሳካት ከውጥን ጀምሮ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ የደከሙት በጠቅላላ ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
ያም ሆኖ ግን ከታለመለት አላማ አንፃር ሲታይ ትልቅ ክፍተት የነበረበት ከመሆኑ ባለፈ በታሰበው ልክ መሬት ላይ ወርዷል ማለት እንደሚያዳግት የጣዕም ልኬት አዘጋጆች አንስተዋል።
ክፍተቱ የሚጀምረው መርሃ ግብሩ "የስንብት" የሚለውን ቃል መጠሪያ ከማድረጉ እንደሆነ አንስተዋል። መጠሪያው ትልቅ ክፍተት የሚፈጥር እና ከሥነ ልቦና አንፃር ሲታይ አሉታዊ ተፅዕኖው እንደሚያጋድል አዘጋጆቹ ገልፀዋል።
ከዚያ ይልቅ ማክበር እንደመሆኑ መጠን ስያሜው ያንን ተንተርሶ ሊሰጥ ይገባው እንደነበር በማንሳት መድረኩ ግቡን መቷል የሚል አመኔታ እንደሌላቸው ተናግረዋል። በጣዕም ልኬት አዘጋጆች ዕይታ በሙዚቃ ድግሱ ላይ የታዩ ክፍተቶች እንደሚከተለው ተቀምጠዋል።
👉« የመድረኩ ይዘት የተቃኘበት መንገድ ትልቅ ስህተት ነበረው፤ይህንን ያለ ይሉኝታ ማስቀመጥ ይገባል።» ብለዋል
👉ከሰዓት አከባበር ጋር በተገናኘ ትልቅ ክፍተት መፈጠሩን ተከትሎ በርካቶች ዝግጅቱን አቋርጠው ለመውጣት ከመገደዳቸው ባለፈ ጥቂት ታዳሚያን ብቻ መሀሙድ ሥራውን ሲያቀርብ መመልከታቸው ቀዳሚው ክፍተት እንደነበር ተጠቅሷል።
👉«መሀሙድን ለማክበር የተገኙት ድምፃውያን የራሳቸውን የቀደሙ ሥራዎች እና በየምሽት ክበቡ የሚቀርቡ ሙዚቃዎችን ደግመው ማቅረባቸው ከመድረኩ አላማ ጋር የሚጋጭ ነበር። በተጨማሪም የመድረኩ ዝግጅት ላይ ምን አይነት ሥራ ይቅረብ በሚለው ዙሪያ ምንም ግንዛቤ አልነበራቸውም።»
« ከዚያ ይልቅ በእለቱ ተዋጣላቸውም አልተዋጣላቸውም ከሁሉም ድምፃውያን አንደበት የመሀሙድን ስራ ልናደምጥ ይገባ ነበር» ሲሉ አዘጋጆቹ ገልፀዋል።
👉 «መሀሙድ በወቅቱ ከነበረበት የጤና እክል አንፃር አዘጋጆቹ ብቻ ሳይሆኑ ሙዚቀኞችም ጭምር እንዲዘፍን ፈፅሞ ማድረግ አልነበረባቸውም።»
ከእዚያ ይልቅ በመድረኩ የክብር ሥፍራ ላይ ሆኖ ቢከታተል መልካም እንደነበር አንስተዋል።
👉 የዝግጅቱ "እጥር ምጥን" ማለት አለመቻሉ ክፍተት መፍጠሩን ያነሱት የጣዕም ልኬቶች መርሃ ግብሩ ሚሊኒየም አዳራሽ የግድ እንዲሆን ከማድረግ ይልቅ ሌላ ስፍራ በመምረጥ የሙያ ምስክርነት፣ ዘጋቢ ፊልሞች፣ ስጦታዎችና ሌሎችም ጉዳዮች በተናበበ መልኩ ማድረግ ይቻል ነበር ሲሉ አንስተዋል። የምሽት ክለብ የመሰለ መርሃ ግብር መሆኑን ተከትሎ አዘጋጆቹ ሳይቀሩ ለመቆጣጠር ተቸግረው እንደነበር ገልፀዋል።
👉«ፕሮግራሙ ኮንሰርት የሚሰሩ ሰዎች እጅ ላይ መውደቁ ክፍተት ፈጥሯል ያሉት አዘጋጆቹ ኮንሰርት መሆኑ እና ገንዘብ ላይ ማተኮሩ የቀረቡት ድምፃውያን ከመሀሙድ አርቋቸዋል። » ሲሉ ሁኔታውን የገለፁ ሲሆን የመሀሙድን ስራ በተደጋጋሚ የተጫወቱ እንዲሁም የመሀሙድ ሙዚቃ ዘመን ተጋሪ ሆነው የሰሩ ባለሙያዎች ቢመረጡ መልካም ነበር ሲሉ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል።
ከእዚህ እና ከሌሎች ክፍተቶች እንፃር ዝግጅቱ ሀሳቡ እና መነሻው ትልቅ ተግባር ግን አጨራረሱ ዝቅተኛ እንደሆነ አንስተዋል።
Via ናትናኤል ሀብታሙ( Fm Addis 97.)
ለተጨማሪው: @EventAddis1

📌ሜንታል ሄልዝ አዲስ ውይይት ቅዳሜ ይካሄዳል
የአእምሮ ጤና ላይ ትኩረቱን አድርጎ በየወሩ የሚካሄደው ሜንታል ሄልዝ አዲስ የሥነልቦና ውይይት ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ይካሄዳል::
የዚህ ወር ርዕስም፡-“Understanding narcissistic presonality Disorder ” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳ በመሆን የሥነልቦና ባለሞያው የሆኑት ጴጥሮስ ሀጎስ የውይይት መነሻ ሀሳብ ያቀርባሉ ተብሏል።

📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል
54ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ዶ/ር ጋሻው አይፈራም "የትውልዶች ቅራኔ በዘመነ ብዙሃ ቀውስ" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
54ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ዶ/ር ጋሻው አይፈራም "የትውልዶች ቅራኔ በዘመነ ብዙሃ ቀውስ" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የመሠረት አዛገ መጽሐፍ አርብ ይመረቃል
የመሰረት የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራች በሆኑት ወ/ሮ መሰረት አዛገ የተጻፈው "ሺ ጊዜ እንዳፈቅር" የተሰኘ የግጥም መጽሔት ከሰሞኑ ለአንባቢያን ቀርቧል።ይህም መጽሐፍ ከነገ በስቲያ አርብ ጥር 23 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።በምርቃት ሥነሥርዓት ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ይገኙበታል ተብሏል።

📌 የሎሬቱ ቤት "ቪላ አልፋ" በድጋሚ ሊከፈት ነው
የዓለም ሎሬት ሜተር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ እና ስቲዲዮ የነበረው ቪላ አልፋ ከአራት ወራት ብኋላ ለህዝብ ክፍት ሊደረግ ነው።
በአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች አካባቢ የሚገኘው ቪላ አልፋ ከጣሪያው ጀምሮ ወደ ምድር የሚዘልቀው ፍሳሽ የእድሳት ጉዞውን ረጅም እና እድካሚ እንዳደረገው ታውቋል።
ነገር ግን በሁለት ወር ውስጥ ቀሪው ስራ እና የሙዚየም ስራው ተጠናቆ በአራት ወር ውስጥ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባ አያሌው ነግረውናል።
ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የአርቲስቱ መኖሪያ ቪላ አልፋ ከዛሬ ነገ በቅርቡ ክፍት ይሆናል ሲባል ቆይቷል።
ለመሆኑ ከወሰን ማካለል እና አካባቢው መኖሪያ መሃል እንደመሆኑ መጠን በዚህ ሐሳብ መንገድ ምን ተሰራ ብለን የጠየቅናቸው ኃላፊው የሙዚየሙ አጎራባች እንደተለየና ለጉብኝት አመቺ ተደርጎ እንደታደሰ ነግረውናል።
የአለም ሊቀ ሊቃውንት የኪነ ጥበብ ባለሙያው ሰአሊ አፈወርቅ ተክሌ የእጅ ስራዎች መካከል መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የግድግዳና ጣሪያ ስዕሎች፣ የሞዛይክ ስራዎች፣ የመስኮትና መስታወት ስዕሎች፣ የዳግማዊ የምፅአት ፍርድ፣ የደመራ ስእል፣ የራስ መኮንን ሀውልት፣ የአፍሪካ ድል አፍሪካ አጠቃላይ ነጻነት፣ የመስቀል አበባ እንዲሁም እናት ኢትዮጵያ ይገኙበታል።
መረጃው የሸገር ሬድዮ ነው።

📌የድምጻዊ ማሚላ ሉቃስ ‘እንደ ጊዜው’ የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል።
አስራ ሶስት ትራኮችን የያዘዉ የድምፃዊ ማሚላ ሉቃስ ‘’እንደ ጊዜው’’ አልበም ጥር 30 2017 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።
በሰዋሰው መልቲሚዲያ በኩል እንደሚለቀቁ ሲነገሩ ከነበሩ አልበሞች መካከል አንዱ የሆነው ‘’እንደ ጊዜው’’ የተሰኘዉ የድምፃዊ ማሚላ ሉቃስ አልበም ለስድስት ዓመታት የተለፋበት ሲሆን አንጋፋ እና ወጣት ባለሞያዎች ተሳትፈውበታል ።
በአልበሙ ላይ በግጥምና ዜማ ይልማ ገ/አብ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ፣ አለማየሁ ደመቀ እንዲሁም እራሱ ድምፃዊ ማሚላ ሉቃስን ጨምሮ ሌሎችም ባለሙያዎች አሻራቸዉን አሳርፈዉበታል።
አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ፣ካሙዙ ካሳ፣ ሚኪ ጃኖ፣ስማገኘዉ ሳሙኤል፣ፋኑ ጊዳቦ፣ሱራፌል የሺጥላ እና ጊልዶ ካሳ በሙዚቃ ቅንብሩ ተሳትፈዉበታል።
አልበሙ የፊታችን ጥር 30 ጀምሮ በሰዋሰው አፕ እና በሰዋሰዉ የዩቲዩብ ገፅ ላይ ይለቀቃል።