Event Addis Media
9.61K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌 ኃይሌ ሪዞርት ጅማ ሥራ ጀመረ

ኃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ግሩፕ አሥረኛውን መዳረሻ እና ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል በጅማ ከተማ  አገልግሎት አስጀምሯል።

ዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ስራ የጀመረው ኃይሌ ሪዞርት ጅማ 105 የእንግዶች ማረፊያ ክፍሎች፣የምግብ አዳራሾች፣የተለያዩ ባሮች፣ የመዋኛ ገንዳ፣ ስፓ፣ ጂምናዚየም፣ ከ30 እስከ 500 ሰዎችን የሚይዙ 5 የስብሰባ አዳራሾች፣ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) አገልግሎት ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

የመሰብሰቢያና የምግብ አዳራሾች በአካባቢያው በሚነገሩ ታሪካዊ ስያሜዎች እንደተሰየመም ተገልጿል።

ኃይሌ ሪዞርት ጅማ ከ210 በላይ ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ እድል የፈጠረ ሲሆን በቀጣይ በሙሉ አቅም ሥራ ሲጀምር 400 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል ከመፍጠርም ባሻገር ከፍተኛ ጥራት ባለው የአገልግሎት ባህል ህብረተሰቡን ለማገልገል በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አቶ ተስፋዬ አስራት አስረድተዋል።

በሐዋሳ ከተማ አንድ ተብሎ የተጀመረው የኃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ግሩፕ ዘንድሮ አስራ አምስት ሆኖታል።

ሐይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች በቀጣይ የሻሸመኔውን እና የደብረብርሃን ከተማ መዳረሻውን በቅርቡ ለማስመረቅና ስራ ለማስጀመር ቀን ከሌት እየሰራ መሆኑን የሐይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩፕ  ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ ተናግረዋል።

ለተጨማሪው: @EventAddis1
📌"ጊዜን መሸከም" መጽሐፍ ለንባብ በቃ።

የገጣሚ ዘውዴ አለልኝ  ‹‹ጊዜን መሸከም›› የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ከሰሞኑ ለአንባቢያን ቀርቧል።

መጽሐፍ 54 ግጥሞችን የያዘ ሲሆን  በ162 ገጽ የተቀነበበ ነው።የመጽሐፉ ቅርጽ በዋሽንት አውታረ ቅኝት የተሠራ ሆኖ በጥቁር፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ እና ነጭ ቀለማት የተከፋፈለ ነው። 

ቀለማቱ ከኢትዮጵያ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች  ዋሽንት፣ ክራር፣ ነጋሪት እና ሞረሽ ከምትባል ወፍ ጋር የተቀነባበረ ነው ተብሏል።

እያንዳዱ ክፍል ቀለማዊ እና ሙዚቃዊ ፍካሬ መግቢያ አለው። እንዲሁም ግላዊ መግቢያ እና ድኅረ ቃል በመጽሐፉ ውስጥ ተካቷል።

መጽሐፉን ለመግዛት የምትፈልጉ በኦንላይን online ማዘዝ ትችላላችሁ ተብላችኋል።

የመግዣ ዋጋው በኢትዮጵያ ብር 350 ሲሆን፣ በውጭ ሀገር መገበያያ $20  ዶላር ተተምኗል።

አካውንት ቁጥር...
አቢሲኒያ ባንክ ( bank of abyssinia) 200869327  ዘውዱ አለልኝ አራገው ( zewdu alelgn aragaw)

ዳሽን ባንክ (Dashen bank)  5472769396011 ዘውዱ አለልኝ  አራጋው ( zewdu alelgn aragaw)

ንግድ ባንክ (CBE ) 1000298476936 (Daniel abreha) ዳንኤል አብርሃ

ቴሌ ብር / tellebirr፦ 0913240885 zewdu alelgn

ክፍያ የፈጸሙን የባንክ ደረሰኝ Screenshot  አድርገው፣ ወይም ፎቶ አንስተው በዚህ የቴሌግራም ሊንክ ይላኩልን @Gizienmeshekem2424 ይላኩልን ተብላችኋል።
🥰1
📌በድምጻዊት ዲባን በኢሮብ አካባቢ በሚነገረው ሳሆ ቋንቋ የተሰራ የሙዚቃ አልበም ተለቀቀ ።

ድምጻዊት ዲባን በሳሆ ቋንቋ የሰራችው "Kokam liyo" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በDIBAAN የዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ደርሷል።

እዚህ አልበም ውስጥ ከተካተቱ 11 የሙዚቃ ስራዎች አስሩ ላይ በሙዚቃ ቅንብር የተሳተፈው ሙሳ ማቲ ነው።

የሙዚቃ አልበሙን በዚህ ቻናል በኩል https://youtube.com/playlist?list=PLQZbkiZabnHwu_BSzbOYPMtNm7dcs6iNl&si=a41zArVDFNDA1ybg ማግኘት ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ድምጻዊት ዲባን ወደ ጥበቡ አለም የተሳበችው ገና በልጅነቷ ነው በተለይ ለሞዴልንግ እና ሙዚቃ ልዩ ፍቅር አላት። ተሰጦዋን በትምህር ለማሳደግም የሞዴልንግ ትምህርት ተምራለች። ዲባን አሁን ላይ ወደ ሙዚቃው እያደላች ቢመስልም የሞዴሊንግ ስራንም እየሰራች ትገኛለች። ከዚህ ቀደም "ይባንድራ" የተሰኘ ነጠላ ዜማ ለአድማጮች ያደረሰች ሲሆን በመቀጠልም በ" ጋሆ"(GAHO) የተሰኘ የሙዚቃ ስራዋን ደረጃውን ከጠበቀ ቪዲዮ ጋ አዋዳ ዳግም ለአድማጮች ተመልካቾች አቅርባለች።

ኢሮብ በትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ስቶን በሰሜን ከኤርትራ በምሥራቅ ከአፋር ክልል ትዋሰናለች።  የብሔረሰቡ ቋንቋ ሳሆ በመባል ይታወቃል፡፡

ማኅበረሰቡ የሚገለገልባቸው የትንፋሽ፣ የክርና የምት የሙዚቃ መሣሪያዎች በአብነት ከሚጠቀሱት ናቸው፡፡ ሙዚቃ በማኅበረሰቡ ዘንድ ያለው ቦታም ከፍተኛ የሚባል ነው፡፡ ውድድር በሚደረግባቸው ባህላዊ የሙዚቃ ሥርዓቶች ማሸነፍ፣ በኅብረተሰቡ መካከል የሚሰጠውን ዋጋ ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡

ለተጨማሪው: @EventAddis1
📌አራተኛው አርኪ የሪል ስቴት ኤክስፖ በስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ

የቤት ሻጮችና ገዢዎች፣ እንዲሁም ገንቢዎች የተለያዩ ተቋማትን ለማገናኘትና ለማስተሳስር ዕድል ይሰጣል የተባለለት አራተኛው አርኪ ሆምስ ኤክስፖ በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በይፋ ተከፍቷል።

ከዛሬ ታህሳስ 25 እስከ ታህሳስ 27/2017 በሚካሄደው በዚህ ኤክስፖ በርካታ የቤት አልሚዎች እየገነቡት ስላለው ቤት ግንባታዉ ያለበት ደረጃ፣ ሊገነቡት ስላቀዱት ቤት፣ ቤቶቹን ዋጋ፣ ስለሚፈልጉት እቃ እና አገልግሎት ከኤክስፖ ተሳታፊዎችና ከጎብኚዎች ጋር መረጃና ልምድ ይለዋወጣሉ ተብሏል።

ወቅቱ የበዓል እንደመሆኑ በርካታ ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ በመሆኑ የኤክስፖውን ሳይጎበኙ ቤት እንዳይገዙ በሚል ሙሉ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት ልዩ የገና በዓል ቅናሽ መኖሩም ተገልገልፃል።

አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ያዘጋጀው ይሄ ኤክስፖ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ የቤት አልሚ ድርጅቶች እና አጋር አካላት እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ኤክስፖው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ፤ አንድ ላይ በማቀናጀት በከተማ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊሰሩ የታሰቡ መዋቅራዊ ቅንጅቶችን ለመፍጠር ምቹ ዕድል የሚፈጥር ገዥና ሻጭን በአንድ ላይ በማገናኘት በቀጥታ የሚፈልጉትን የቤት ዓይነት የሚመርጡበት ስለአጠቃላይ ሂደት በግልፅ መረጃ የሚለዋወጡበት በርካታ አማራጮች ያሉበት ለተረጋጋና ምክንያታዊ የቤት ግዥ ዉሳኔ ምቹና ዓይነተኛ አጋጣሚ እንደሚፈጥር የዝግጅት ክፍሉ ያስታወቀ ሲሆን ሁሉም ቤት ገዥ እና አልሚ ይህ ዕድል ሳያመልጠዉ ኤክስፖዉን እንዲሳተፍ ጥሪ አቅረቧል፡፡

ለተጨማሪው: @EventAddis1
📌የ"ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሄራዊ ማህበር የሚዘጋጀው "የፈለገ ኪን" አምስተኛ የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት  ይካሄዳል።

ባለፉት አራት መድረኮች እንደተደረገው ሁሉ አምስተኛው መርሀግብር ዓይነ ስውራንና የዓይነ ስውራን ወዳጆች የሆኑ ባለተሰጥዖዎች የሙዚቃ፣ የሥነግጥምና የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ችሎታዎቻቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ነው ተብሏል።

በዕለቱም አብዬ መንግስቱ ለማ  ይዘከራሉ፤ አንጋፋው ደራሲ አበራ ለማ ደግሞ የዕለቱ ተጋባዥ እንግዳ ሆነው እንደሚገኙ ተገልጿል።

አዘጋጆቹ "በመርሃግብሩ ላይ በመታደም ከአይነስውራን አእምሮ የፈለቁ  እምቅ፣  ጥልቅ፣ ምጡቅ  የስነ ጽሁፍ፣ የሙዚቃና የፍልስፍና ጠለ በረከቶችን ይቋደሱ " ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"ያልተወጋ ፍቅር "መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል።

በመምህርትና ገጣሚ ይሳለም አዳሙ የተዘጋጀው "ያልተወጋ ፍቅር" የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ይመረቃል።

በዕለቱም አርቲስት ስዩም ተፈራ፣ደራሲ የዝና ወርቁ፣ደራሲ አበራ ለማ፣ገጣሚ ፍሬሕይወት መላኩ እና ሌሎችም በክብር እንግድነት ይገኙበታል።

መምህርትና ገጣሚ ይሳለም አዳሙ ለ4 ዓመታት በመምህርነት፣ ለ12 ዓመታት በምክትል ር/መምህርነት ሠርታለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌ሀገራችን ኢትዮጵያ በሉሰበርግ ልትመሰገን ነው

‎የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የአውሮፓ ጉብኝትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት በሉክሰምበርግ ከተማ ማዘጋጃ ቤት  የማስታወሻና የምስጋና ዝግጅት የፊታችን ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም  ይካሄዳል።

‎በዕለቱ የኢትዮጵያና የሉክሰምበርግ ሠዓሊያን  ወቅቱን የሚያስታውስና ነጻ የፈጠራ ሥራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን የሥዕል ትርዒት ይከፈታል ተብሏል።

‎በመርሃግብሩ ላይ አስር የሀገራችን ሠዓሊዎች ሥራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ሠዐሊና መምህር ኃይሉ ክፍሌ ሀገሩን ወክሎ ንግግር እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።

‎የንጉሱ የሉከሰምቦርግ ጉብኝትለየት  የሚያደርገው በወቅቱ በነበረው የአንደኛው  የዓለም ጦርነት ጉዳት ምክንያት የገንዘብ  ልግስና ማድረጋቸው ሲሆን ፣በዚህ ዝግጅት  ላይም የከተማዋ ከንቲባና ንጉሳዊያን ቤተሰቦችንጨምሮ  ታላላቅ  እንግዶች  በመገኘትንግግር  እንደሚያደርጉ፣ ኢትዮጵያንም እንደሚያመሰግኑ ይጠበቃል ።

‎ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ከዚህ የአውሮፓ ጉብኝት  በኋላ መከፈቱን ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የመቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓል ልዩ ፕሮግራም ነገ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር ለሁለት ዓመታት የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ነገ ሐሙስ ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓል ልዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅት ላይ አርቲስት እታፈራሁ መብራቱ የክብር እንግዳ በመሆን የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"ቃልና ሙዚቃ" የተሰኘ ውይይት ነገ ይካሄዳል። ይህ ልዩ ውይይት ነገ ጥር 1 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ውይይት ላይ የሙዚቃ ባለሞያዋ ትሬዛ ዮሴፍ ዳሰሳ ታቀርባለች ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"ጀቢና"ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው።

በደራሲና ዳይሬክተር ሳሙኤል ተሻገር የተዘጋጀውና "ጀቢና" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ለእይታ ይበቃል። "ጀቢና" በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ ፊልም እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በአሁን ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በለታሪክ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበ ነው።

በፊልሙ ላይ ቤተልሔም ሸረፈዲን፣እታፈራሁ መብራቱ፣ ካሣሁን ፍስሃ(ማንዴላ)፣ ናትናኤል መኮንን፣አስራት ታደስ እና ሌሎችም ተውነውበታል።

ይህ ፊልም ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የድምፃዊ አህመድ ሁሴን(ማንጁስ) አልበም

የድምፃዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) "አልጣሽ" ሲል የሰየመውን የመጀመሪያ አልበሙን በዚህ ወር ለአድማጮች እንደሚያደርስ ተገልጿል።

በዚህ አልበም ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን በግጥም ይልማ ገብረዓብ ፣ ናትናኤል ግርማቸው ፣ መሰለ ጌታሁን ፣ ተስፋ ብርሀን በዜማው አበበ ብርሀኔ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ አህመድ ተሾመ(ዲንቢ)) በቅንብር አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሽዎታ አብዛኛውን ያቀናበረ ሲሆን ቀሪውን ከአቤል ጳውሎስ በጋራ ሰርተውታል፡፡

ይህ የድምጻዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) አዲስ አልበም ጥር 16 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለሙዚቃ አድማጮች ይደርሳል፡፡

ድምጻዊው "ደሴ ላይ" ፣ "ልቤ አቃተው" እና ሌሎችም ነጠላ ሙዚቃዎች ከዚህ ቀደም ለአድማጮች አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1