Event Addis Media
9.62K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌"የቀለም ጨዋታ" ፊልም ዛሬ ለእይታ ይበቃል

በብርሃኑ መብሬ ተደርሶ በኪሩቤል ስዩም የተዘጋጀው "የቀለም ጨዋታ" የተሰኘ አዲስ ፊልም ዛሬ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል።

"የቀለም ጨዋታ" ፊልም አንድ ዓመት ከ4 ወር በላይ ጊዜን የወሰደ ሲሆን  ደረጄ ሀይሌ፣ሙሉዓለም ጌታቸዉ፣ሱራፌል ብስራት፣አለምፀሀይ እሸቱ፣ተመስገን ሚካኤል፣ ሳባ ታደሰን ጨምሮ ከ85 ተዋናኒያን እንደተሳተፉበት ተገልጿል።

በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው "የቀለም ጨዋታ" ፊልም ታህሳስ 11፣12 ፣13 እና 18፣19፣20 በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የድምጻዊ ፍቃዱ ትዕዛዙ "ባለውለታዬ" የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ይለቀቃል

የቀደሞ ድምጻዊ ተፈራ ነጋሽ የሙዚቃ ስራዎችን በድጋሚ የተጫወተውና "ዘንድሮ" በሚል ርዕስ በአልበም መልክ ለአድማጮች ያደረሰው ድምጻዊ ፍቃዱ ትዕዛዙ "ባለውለታዬ" የሙዚቃ ቪዲዮውን ዛሬ ታህሥሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ያደርሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የሜላት ቀለመወርቅ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ይለቀቃል

የድምጻዊት ሜላት ቀለመወርቅ "ዜሮ" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በራሷ ዩቲዩብ ቻናል ለአድማጮች ይደርሳል።

ድምጻዊት ሜላት በማህበራዊ ትስስር ገጿ"አዲሱን የሙዚቃ ቪድዮ  ስራዬን በራሴ ዩትዩብ ቻናል ወደናንተ አደርሳለው። ሁሌም በስራዎቼ ስለምታበረታቱኝ በጣም አመሰግናለው" ብላለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ ነገ ይካሄዳል

52ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ዮናስ ታረቀኝ " ፍራንስ ካፋካንና ሥራዎቹን በጨረፍታ" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።

ይህም ውይይት እሁድ ታህሣሥ 13 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው:Tiktok:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rbUqppyscx&_r=1

Telegram: https://t.me/EventAddis1
📌በአርቲስት ዘነበች ታደሰ"ጭራ ቀረሽ" ህይወትና ሥራ ላይ ያተኮረ መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል።

በሀገራችን በቴያትርና ሙዚቃ ዘርፍ በሁለገብ ሙያተኛነት ደምቀው ሲያበሩ ከነበሩ ከያኒያኒን መካከል አንዷ የነበረችው አርቲስት ዘነበች ታደሰ (ጭራ ቀረሽ) ሕይወትና ስራዎች ላይ የሚያጠንጥን መጽሐፍ ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

በዶ/ር ጌታቸው ተድላ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ አርቲስት ዘነበች ታደሰ ማን ነች? ለምንስ ጭራ ቀረሽ የሚል ስያሜ ተሰጣት? ለጥበብ ምን አበረከተች? የሚሉ ጥያቄዎችን ሊመልስ የሚችል በፅሁፍና በምስል የተደራጀ መፅሐፍ  እንደሆነ ተገልጿል።

አርቲስት ዘነበች ታደሰ  'ሎሚ ብወረውር' በሚለው ዘፈኗና በመድረክ ላይ ውዝዋዜዋ ይበልጡን በህዝብ ልብ ውስጥ የምትታወስ ትሁን እንጂ ጥቂት በማይባሉ የመድረክ ቴያትሮችና የቴሌቪዥን ድራማ ብሎም ፊልም ላይ  በመሳተፍ አቅሟን አሳይታለች።

ለአብነት ያህል (Shaft in Africa) ላይ ከታዋቂው የሆሊዉድ ተዋናይ ሪቻርድ ራውንድትሪ ጋር የመተወን እድል ሲገጥማት በጥሩ ብቃት የተሰጣትን ሚና ለመወጣት የቻለች ብቁ ሙያተኛ ነበረች።

'ጭራ ቀረሽ' የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ መፅሀፍ  ዛሬ ታህሳስ 12 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመርቆ ለንባብ ይበቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"የለውጥ ሰበዞች" የፎቶግራፍ አውደርዕይ ተከፈተ

የአምስት ፎቶ ባለሞያዎች የፎቶግራፍ ስራዎች የሚቀርብበት "የለውጥ ሰበዞች" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የፎቶግራፍ አውደርዕይ á‰…á‹łáˆœ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ውስጥ ተከፍቷል።

ዝርዝሩን በድረገጻችን ያንብቡ: http://surl.li/egtnqg

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌"ብስክሌት በአዲስ" ፌስቲቫል

"ብስክሌት አዲስ" የተሰኘ የብስክሌት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ ነው።

ዝርዝሩን ያንብቡ:http://surl.li/egtnqg

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የሀዲንቆ የማሲንቆ አልበም ነገ ይለቀቃል

በመስንቆው ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቹ ሀዲስ አለማየሁ በመድረክ ስሙ (ሀዲንቆ) የተዘጋጀው የመስንቆ አልበም ነገ ታህሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።የሙዚቃ አልበሙ "Streets of haddis" የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቷል።

ተጨማሪውን ያንብቡ:http://surl.li/jsqasd

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የድምጻዊት ኢሪ ዲ "ሰላም ነው" ሙዚቃ ተለቀቀ

የወጣቷ ድምጻዊት ኢሪ ዲ "ሰላም ነው" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ሙዚቃ በተለያዩ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ለአድማጮች ደርሷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌በጋዜጠኛ ተስፋ ፈሩ የተፃፈው "አንሶላ ውስጥ ሟች እና ሌሎችም ወጎች" ለንባብ በቃ

መጽሐፉ 57 ወጎች እና ሽሙጦች የተካተቱበት ሲሆን በ207 ገፆች ተቀንብቧል። ደራሲው ጋዜጣ ላይ በሚጽፋቸው ቁምነገር አዘል አዝናኝ ጽሑፎች ይታወቃል።

የተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ  ጉዳዮችን የሚዳስሱ ወጎች በተካተቱበት መፅሐፍ ጀርባ ላይ አቶ ሙሼ ሰሙ፣ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን እና ዶክተር መስፍን ፈቃዴ አስተያየታቸውን አስፍረዋል።

መጽሐፉ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌6ኛው የወር ወንበር ዝግጅት ቅዳሜ ይካሄዳል

በዕለቱ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ይኩኖአምላክ መዝገቡ “ኪን እና ስየማ፡ ኢትዮጵያዊ የትምህርት ዘይቤ በለቀማ” በሚል ርእስ ሃሳባቸውን ያቀርባሉ። ከታዳሚዎች ጋርም ውይይት የሚደረግ ይሆናል።

በዝግጅቱ እንትትሳተፉ ሁላችሁም በአክብሮት ተጋብዛችኋል።


📌 በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ

⏰ ከ10፡00-12፡00

📝በዝግጅቱ ላይ የሚገኙ ከሆነ ይህንን ቅፅ በመሙላት ይመዝገቡ
https://bit.ly/3BFVvGS

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌አዲስ የቪዲዮ ሥነጥበብ ፌስቲቫል ዛሬ ይከፈታል።

ለአምስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የአዲስ ዓለም አቀፍ የቪዲዮ ስነ-ጥበብ ፌስቲቫል ዛሬ ሐሙስ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ስድስት ኪሎ በሚገኘው በገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ስነ-ጥበብ ማዕከል በምሽቱ 12:00 ጀምሮ  ይከፈታል።

ፌስቲቫሉም ለ 5ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ቦታዎች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ይህ አምስተኛው  ፌስቲቫልም በቅርቡም ህይወቱ ላለፈው ሠዓሊና የቪዲዮ ስነ-ጥበብ ሙያተኛ ሙሉጌታ ገ/ኪዳን መታሰቢያ እንዲሆን ተሰይሟል ተብሏል።

የዘንድሮው መሪ ቃልም "የማንሰራሪያ ተረኮች" ወይንን"Re(Cover) Story" ሆኗል።

ለዚህ ፌስቲቫል 350 ሠዓሊያን ከ 84 ሀገራት ያመለከቱ ሲሆን የመጨረሻወቹ 12 ስራዎች ተመርጠዋል ተብሏል።

በዚህ ፌስቲቫል እነዚህ የተመረጡ ስራዎችና የተጋበዙ 4 ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ፕሮግራሞች ለእይታ ይቀርባሉ።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 ጎዶ'ን ጥበቃ

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር


📍 ዋዋጎ

ድርሰት: ታረቀኝ ብርሃኑ
አዘጋጅ: ጥላሁን ዘውገ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍የሕይወት ታሪክ

ድርሰትና ዝግጅት ነብዩ ባዬ እና ቢንያም ወርቁ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1