Event Addis Media
9.08K subscribers
5.26K photos
5 videos
3 files
3.97K links
Connect with Addis Ababa's artistic community! Find out about art exhibitions, music events, workshops, and cultural experiences. Contact: @Tmanaye
Download Telegram
"ለእናቴ" የሥነጽሑፍ ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት

ባሳለፍነው ዓመት ይፋ የተደረገው የእናት ባንክ "ለእናቴ" የጽሑፍ ውድድር  አሸናፊዎች የፊታችን ግንቦት 19 2016 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል በሚዘጋጀ ልዩ ፕሮግራም ሽልማት እንደሚበረክትላቸው እናት ባንክ አስታውቋል።

ለ"እናቴ" የጽሑፍ ውድድር ከአንድ ወር በላይ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በተደረገ ጥሪ መሰረት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ውስጥ የሚገኙ ከ1500 በላይ የሥነጽሑፍ ተዋዳዳሪዎች እንደተሳተፉ ተገልጿል።

ውድድሩ ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር ፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርው ጽሑፍ የሚገልጽበት ሲሆን በይዘት ደረጃም ተዋዳዳሪዎች "ለእናቴ" ብለው ስለእናታቸው የሚያጋሩበትን ፍቅርና ስሜት ዳኞች አወዳድረው የሚያበላልጡበት ሳይሆን ተወዳዳሪዎች ለእናታቸው ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት እንዴት  እንደገለጹ ፣ ስሜታቸውን ወደ ሌሎች ለማጋባት እንዴት እንደጣሩ የተዳኙበት አውደ እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።

የማወዳደሪያ መስፈርቱ በተመሳሳይ መንገድ የቀረበ ሲሆን የቅርጽ ጉዳዮች 50 በመቶ የይዘት ጉዳዮች 50 በመቶ በድምሩ ከ100 ነጥብ የተያዘ ሲሆን
በውድድሩ ከአንድ እስከ አምስት የወጡ አሸናፊዎች ሽልማት የሚሰጣቸው ሲሆን ሌሎች አስራ አንድ የተመረጡ ጽሑፎችም በውድድሩ በተዘጋጀው መጽሔት ላይ ጽሐፎቻቸው ይወጣል ተብሏል።

ግንቦት 19 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በሒልተን ሆቴል በተዘጋጅው የቀይ ምንጣፍ የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙበት ሲሆን የተወዳዳሪዎች ሥራዎች በራሳቸው አንደበት መድረክ ላይ ይቀርባል ተብሏል።

በተጨማሪም የተለያዩ የኪነጥበብና ሥነጽሑፍ ባለሞያዎች እንዲሁም አትሌቶች ስለእናቶቻቸው ለታዳሚያን ሀሳባቸውን እንደሚያጋሩ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ ሙሉ ለሙሉ ታድሶ በአዲስ መልክ ስራ መጀመሩን በአክብሮት ይገልፃል :: 

ውድ  የቶቶት ቤተሰቦቻችን  ከግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ  ልዩ ቁርጥ ቤታችንን  በክብር እንዲጎበኙልን ጠርተንዎታል :: 
ምርጥ ምርጡን  ሁሌም ለእናንተ እናቀርባለን ::

0116 46 07 18
09 09 00 44 00

ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ

አድራሻ ገርጂ መብራት ሀይል አንበሳ ጋራዥ ፊት ለፊት

#Ads
የድምጻዊ ደሳለኝ መርሻ"ኑድኒያ" የጉራጊኛ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት ይለቀቃል 

የድምጻዊ ደሳለኝ መርሻ "ኑድኒያ "የተሰኘ 7ኛ የጉራጊኛ የሙዚቃ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ይደርሳል።

ይህ የጉራጊኛ አልበም 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስለፍቅር፣ ስለሃገር፣ ስለማህበራዊ ህይወት የሚዳስስ ሁለገብ አልበም ነው ተብሏል።

አልበሙ ላይ በርካታ ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በግጥም እና ዜማ ራሱ ደሳለኝ መርሻ፣ ፈለቀ ማሩ፣ ናቲ ኃይሌ፣ ዘነበ መርሃባ፣ ሀብታሙ አብርሃም፣ አለማየሁ ወልዴ የተሳተፉ ሲሆን በቅንብር አሌክስ ይለፍ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፣ ሰማገኘው ሳሙኤል፣ ፋኑ ጊዳቦ፣ ቢኒአነዴ ርሆቦት (ሮባ) የተሳተፉ ሲሆን በሚክሲንግ ሰለሞን ሃ/ማርያም፣ ፍሬዘር ታዬ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፣ ቢኒአንዴ ተሳትፈዋል፡፡ በማስተሪንግ ሰለሞን ሃ/ማርያም በአልበሙ ተሳትፏል።

"ኑድኒያ" አልበም ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በአርቲስቱ ዩቲዩብ ቻናልና በሁሉም ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያ የሚገኝ ሲሆን ሲዲውን ኪነት ኢንተርቴይመንት አሳትሞ ያከፋፍለዋል፡፡

አርቲስት ደሳለኝ መርሻ አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ በትክክል የተመዘገበ 3.8 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ዛሬ በማርዮት ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጿል።

አርቲስት ደሳለኝ መርሻ በሙዚቃዎቹ የጉራጌ እሴቶችን፤ ታሪክ፤ ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና ማሕበራዊ ሕይወትን በተባ ኪናዊ ለዛ በመሰነድ እና በማስተዋወቅ የራሱን አሻራ አኑሯል፡፡

ባለፉት 20 አመታት ሙዚቃን ሕይወቱ በማድረግ ለበርካታ ድምፃውያንም ግጥም እና ዜማዎችን የሰጠው ደሳለኝ መርሻ የመጀመርያ አልበሙ ያሳተመው አዲስ አበባ ውስጥ የታክሲ ሹፌር እየሰራ ባለበት ወቅት ነበር።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
አፍሮ ኤዥያ ዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ "ድልድዮችን መገንባት ህይወትን ማዳን" በሚል መሪቃል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።

ኤፍ ዚ ማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር አፍሮ ኤዥያ ዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እያካሄደ ይገኛል።

ይህ አለም ዓቀፍ የጤና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከዛሬ ግንቦት 09 ቀን እስከ ግንቦት 11 2016 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህም ኤክስፖ ላይ ከ4 መቶ በላይ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ የጤና ተቋማት እንደሚሳተፉ የተገለጸ ሲሆን ማህበረሰቡ እየመጣ ሊጎበኘውና ሊጠቀምበት እንደሚገባ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የተለያዩ መጻሕፍትን በስስ ቅጂ( Soft Copy) ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ይህንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀላሉ።

https://t.me/kooblife

https://t.me/kooblife

https://t.me/kooblife

Ads

እናመሰግናለን መልካም ቀን !
ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን "ሙዚየሞች ለትምህርት እና ለምርምር”  በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።

አለም አቀፍ የሙዚየም ቀን  በአለም አቀፍ ደረጃ ለ47 ግዜ በሀገራችን ደግሞ ለ22ኛ ግዜ በዛሬው እለት ግንቦት 9 /2016 በኢትዮጵያ ቅርስ ባለ ስልጣን አዘጋጅነት በመከበር ላይ ይገኛል።

እለቱ ሲከበር ሙዚየሞች ትኩረት እንዲያገኙ እና ያልታዩት እንዲታዩ የማድረግ አንዱ አላማው መሆኑ ተነስቷል።

የሙዚየም ዋነኛው ስራ ማስተማር ሲሆን ለሀገር ግንባታ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም ተገልጿል።

ሙዚየሞች አንድነታችንን የሚያጠናክሩልን በመሆናቸው ልንንከባከባቸው እና ልንጎበኛቸው እንደሚገባም ተጠቁሟል።

ወደፊት ሙዚየሞች የሚጎበኙበት ሰአት የማሻሻል እና ከስራ ሰአት ውጪ ሰዎች መጎብኘት የሚችሉበት ሁኔታ በማመቻቸት ላይ እንደሆነም ሰምተናል።

ዘገባው ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል እና የአፍሪካ ቀን ክብረ-በዓል ከግንቦት 16 እስከ 18 በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ በጋራ ሊካሄዱ ነው
 
"አዲስ ጃዝ" የዚህ ዓመት ፌስቲቫሉን ከግንቦት 16 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን የአፍሪካ ቀን ክብረ-በዓል አብረው ይከበራል ተብሏል።

ዝግጅቱ የሚካሄድበት ስፍራ አፍሪካን ጃዝ ቪሌጅ ሲሆን አፍሪጎ ባንድ ከዩጋንዳ፣ ድምጻዊ ሴልሞር ቱኩድዚ ከዚምባብዌ፣ ማቲው ቴምቦ ከዛምቢያ በዕለቱ የሙዚቃቸው ስራቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃ መልክ ከማስያዝ አንስቶ የሮሃ ባንድ ድምቀት እስከ መሆን የሚጠቀሰው አንጋፋው ዳዊት ይፍሩን እንዲሁም አንጋፋው ግርማ በየነ እና ሌሎች አዳዲስ አርቲስቶችም በመድረኩ ስራቸውን ያቀርባሉ።

ከላይ ከተዘረዘሩት አርቲስቶች ጋር በጋራ እንደ ጆርጋ መስፍን፣ ያሆ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ፣ መሐሪ ብራዘርስና ዮሃና ሳህሌ የፌስቲቫሉ ድምቀት እንደሚሆኑ ተነግሯል።

የዚህ ዓመት ፌስቲቫል በልዩ ሁኔታ ለእውቁ ሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን የአልበም ምርቃት ትኩረት በመስጠት አድማጮች ልዩ ምሽት እንዲያሳልፉ እድሉን ይፈጥራል፡፡  

በፌስቲቫሉ ሁለተኛ ቀን ማለትም ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰላም ፕሮጀክቶች አንዱ ከሆነው ከኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ፕሮጀክትና አፍሪካ ኅብረት ጋር በጋራ ከሚከበረው የአፍሪካ ቀን ጋር በጋራ ይከበራል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ቴክኖ አዲሱን እና በቅርቡ በባርሴሎናው ዓመታዊ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ ያደረገውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በይፋ በኢትዮጵያ አስተዋወቀ።

የሞባይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ አዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስተዋወቀ። አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ (SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው።

ቴክኖ በቅርቡ በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው አንጋፍው እና አመታዊው የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን (Mobile World Congress) ላይ ይህን አዲስ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴልን ጨምሮ የተለያዩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በይፋ እንዳስተዋቀ የሚታወቅ ነው፣ በዚሁ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ የሆነው ቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በማንኛውም አይነት ሁኔታ እና የብርሃን መጠን ሳይገድበው ቁልጭ ያሉ ፎቶዎችን የማንሳት አቅም እንዲኖረው በማሰብ በካሜራ ቴክኖሎጂ አንጋፋው ሶኒ (SONY) ምርት የሆነውን ዘመናዊ ሴንሰር (Sony IMX890) የተገጠመለት መሆኑ ለየት ሲያደርገው በኢንዱስትሪው የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ‘PolarAce’ ፖላርኤስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የቪድዮ ኢሜጂንግ ሲስተሙን በማዳበር እና እንከን የለሽ በማድረግ የካሜራ ቴክኖሎጂውን ሁለቱ ኩባንያዎች ወደ ላቀ ደረጃ አድርሰውታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የ"ክብር ሽልማት" አሸናፊዎች ዝርዝር

የመጀመሪያው "የክብር ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በግዮን ግሩቭ ጋርደን ውስጥ ተካሄዷል።

የክብር ሽልማት አሸናፊዎች ዝርዝር የሚከተለውን ይመስላል:

📍የዓመቱ ምርጥ ልብ ወለድ

ቤባንያ (ዓለማየሁ ገላጋይ)

📍የዓመቱ ምርጥ አጫጭር ልብወለድ

ናፍቆት (እስከዳር ግርማይ)

📍የዓመቱ ምርጥ ግለታሪክ መጽሐፍ

ኅብር ሕይወቴ (ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ)

📍የዓመቱ ምርጥ የወግና መጣጥፍ መጽሐፍ አሸናፊ

ችቦ (ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ )

📍የዓመቱ ምርጥ ተውኔት

በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ (ውድነህ ክፍሌ)

📍የዓመቱ ምርጥ ግጥም

እናርጅ እናውጋ (ጌራወርቅ ጥላዬ)

📍የዓመቱ ምርጥ የፊልም ድርሰት

ዶቃ (ቅድስት ይልማ እና ቤዛ ኃይሉ)

📍የዓመቱ ምርጥ የዘፈን ግጥም

ላይለ ኩሉ (ዳን አድማሱ)

📍የክብር ሽልማት በሥነጽሑፍ ዘርፍ የሕይወት ዘመን ሽልማት

ኃይለመለኮት መዋዕል

📍የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ የመዝናኛ ዩቲዩብ

ዶንኪ ቲዩብ

📍የዓመቱ ምርጥ የሚዲያ ሰው

መንሱር አብዱልቀኒ

📍የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ዝግጅት አቅራቢ

አስካለ ተስፋዬ

📍የዓመቱ በጋዜጠኝነት ዘርፍ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ

አማረ አረጋዊ

📍የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅት

ትዝታችን በኢቢኤስ

📍የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት

ለዛ

📍የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት አቅራቢ

ትዕግስት በጋሻው

ድረገፅ: https://eventaddis.com
የዕብነ ሐኪም "ብራና" ገሚስ አልበም ተመረቀ

ከዓለም አቀፉ ሶኒ ኢንተርቴይመንት አፍሪካ ጋር አብሮ በመስራት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሆነው ወጣቱ ሙዚቀኛ ዕብነ ሐኪም "ብራና” የተሰኘ ገሚስ የሙዚቃ አልበሙ በይፋ ተመርቋል።

አልበሙ በባና ሪከርድስ የቀረበ ሲሆን አቀናባሪ ኑሂ በአቀናባሪነት ፤ ሙዚቀኛ ዕብነ ሐኪም በሙዚቃ ዜማ እና ግጥም ጻሀፊነት እንዲሁም ሌሎች ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች እንደተሳተፉበት ተገልጿል።

ገሚስ አልበሙ ብራና ፣ የኔታ ፣ቃል ብቻ፣ ገላ ፣ይሁን ፣ ጉድ ነው የተሰኙ አንዱ ከአንዱ ጋር በሀሳብ የሚተሳሰሩ ስድስት የሙዚቃ ስብስቦችን ይዟል።

አልበሙ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ስልትን ከዘመናዊ ስልቶች ጋር በማጣመር የተዘጋጀ ሲሆን የኢትዮ-ፊዩዥን የሙዚቃ ስልትን የያዘ እንደሆነ ተገልጿል።

ለሁሉም ሙዚቃዎች ስድስት የሙዚቃ ቪዲዮዎች የተሰራላቸው ሲሆን አልበሙን ለማጠናቀቅ በአጠቃላይ አራት ዓመት ገደማ እንደፈጀም ተገልጿል።

ገሚስ አልበሙ በ"EBNE HAKIM" በተሰኘው የሙዚቀኛው የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል ተለቋል።

ከተመሰረተ ሶስት ዓመታት ያስቆጠረው "ባና ሪከርድስ" አዳዲስ ባለተሰጥኦ ሙዚቀኞችን እየመረጠ የማርኬቲንግ ፣ ስርጭት እና ፕሮዳክሽን ስራዎችን የሚሰራ ሲሆን ይህም "የብራና" አልበም የመጀመሪያ ፕሮጄክታቸው እንደሆነ የባና ሪከርድስ መስራችና ስራ አስኪያጅ ብሌን መኮንን ገልጻለች።

በተጨማሪም"ባና ሪከርድስ የተመሰረተው የኢትዮጵያን ሙዚቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ነው። በዚህም ታላቅ ኅላፊነት እንዲሁም ኩራት ይሰማናል” በማለት ተናግራለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ለአባቶች ቀን ልዩ ውድድር ተዘጋጀ

ላለፉት 15 አመታት የኢትዮጵያ የአባቶች ቀንን በየዓመቱ ሲያከብር የቆየው ኢትዮጵያ አባቶች ቀን በጎ አድራጎት ድርጅት ዘንድሮም ለ16ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ የአባቶች ቀንን ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በልዩ ሁኔታ ለማክበር ተዘጋጅቷል።

የበጎ አድራጎት ድርጅቱ በዘንድሮው የኢትዮጵያ አባቶች ቀን በተለየ መልኩ ልጆች ለአባታቸው ስሜትና ፍቅራቸውን በመግለፅ የሚሳተፉበት ውድድርም አዘጋጅቷል፡፡

ውድድሩም ለደጉ አባብዬ ያላችሁን ክብርና ምስጋና በምን መልኩ እንደምትገልፁ የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ በመቅረጽና "በኢትዮጵያ አባቶች ቀን በጎ አድራጎት ድርጅት" ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ መልዕክት መላኪያ ላይ በማስቀመጥ የሚከናወን ነው።

በዚህም የሚላኩ ቪዲዮዎች በተቋሙ ገፆች ላይ ተለጥፈው እስከ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሚያገኙት የእይታና የላይክ መጠን ተመርጠው

1ኛ ለሚወጣ የምስክር ወረቀት፣ ጋቢና ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ፡፡

2ኛ ለሚወጣ ጋቢና ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ፡፡

እንዲሁም 3ኛ ለሚወጣ ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ ላይ የሚታደሙ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ታሪካዊ ፎቶና ምስል በመላክ መወዳደር ትችላላችሁ ተብላችኋል።

በአባቶች ቀን ለአባቶቻችሁ ፍቅራችሁን እና ክብራችሁን ለመግለፅ አስባችሁ ነገር ግን አቅማችሁ የማይፈቅድላችሁ፤
እንዲሁም "አባቴ ፍፁም የተለየ ሊነገር የሚገባው ታሪክ አለው" የምትሉ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጻቸው በውስጥ መስመር መልዕክታችሁን ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

ድርጅቱ የተመረጠ ታሪክ ያላቸውን አባቶች ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በዮድ አቢሲያ የባህል አዳራሽ ለአባቶቻችሁ ተገቢውን ክብርና ምስጋና ይሰጣል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ነጻ የቤተመዘክር( ሙዚየም ) ጉብኝት

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀንን ዘንድሮ  በሀገራችን  ለ22ኛ ግዜ «ሙዚየሞች ለትምህርት እና ምርምር»  "Museum for Education and Research" በሚል መሪ ቃል ያከብራል::

ዛሬ ግንቦት 10 2016 ዓ.ም ሁሉም ነዋሪ ያለምንም  ክፍያ በነፃ እየመጣ እንዲጎበኝ ይጋብዛል።

የሙዚየሙ አድራሻ:- መስቀል አደበባይ ከአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በስተቀኝ በኩል።

ምንጭ። አዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የአብርሆት ቤተመጽሀፍት ከ18 ዓመት በላይ በሆናቸው ወጣቶች የተሰሩ የሰው ሰራሽ  አስተውሎት ዘርፍ  ውጤቶችን  በሞሮኮ ራባት በሚካሄድ ኤግዚቢሽን ላይ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ፡፡

23 ታዳጊዎችን ያካተተ ቡድን ለሮቦ ፌስት ውድድር ወደ አሜሪካን ማቅናቱ  የሚታወስ ነው፡፡

ይህ በከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንዲሁም በአብርሆት ቤተመጽሀፍት እና በአቡጊዳ ሮቦቲክስ ማእከል በተደረገ ስምምነት ወደ አሜሪካ ያቀናው  የታዳጊዎች ቡድን በሚቺጋን ሎውረንስ ዩኑቨርስቲ በተካሄደ ውድድር በሶስት የሮቦ ፌስት የውድድር ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ከግብጽ እና ጋና ውጪ አፍሪካንም ጭምር ወክለው እንደተሳተፉ የተናገሩት ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአብርሆት ቤተመጽሀፍትና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዳይሬክተር ኢንጂነር ውባየሁ ማሞ በቴክኖሎጂ ሰለጠኑ ከሚባሉ አገራት ጋር የነበረው ፉክክር በስተመጨረሻ ድል የተቀዳጀንበትም ነው ብለዋል፡፡

በሰው ሰራሽ የአስተውሎት ዘርፍ የአብርሆት ቤተመጽሀፍት ከጎግል ኩባንያ ጋር በመተባባር እየሰራ ነው ያሉት ኢንጂነር ውባየሁ ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው ወጣቶች ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ የሮቦቲክ ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በእንግሊዝና በሞሮኮ ራባት በሚካሄድ ኤግዚቢሽን ላይ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጋቸውንም አንስተዋል፡፡

በጥንቃቄ ታይተው ተፈትሸው ለውድድር የሚቀረቡት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተማሪዎች ያለአስተማሪ እውቀት መገብየት እንዲችሉ የሚያግዝ፤የነፍሰጡር እናቶችን የእርግዝና ክትትል ጊዜን የሚከታተል እንዲሁም አሰሪና ሰራተኛን ማገናኘት የሚችሉ መተግበሪያዎች ናቸው ያሉት ኢንጂነር ውባየሁ በሁለት ሳምንት ጊዜም ለህዝብ ይፋ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡

Via AMN

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
እሺ ሚዲያ እና የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በጋር ለመስራት ተፈራረሙ 

እሺ ሚዲያ እና የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የፕሮሞሽን እና የኮምኒኬሽን ስራዎችን በጋር ለመስራት ዛሬ ግንቦት 10 2016 ዓ.ም ተፈራርመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በአሁን ወቅት አሥር የሚደርሱ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች በማስተዳደር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ኮርፖሬሽኑ እነዚህን የሕዝብ መዝናኛና ፓርኮችን በማልማትና በማስተዋወቅ በከተማዎ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ልማትና ገፅታ የመገንባት ስራ አንድ አካል በማድረግ ሰፊ የህብረተሰብ ንቅናቄ  መድረክ ለማዘጋጀት አቅዷል፡፡

በዚህ የማነቃቂያ መድረክ መዝናኛ ቦታዎቹና ፓርኮቹን በሚሊዮን በሚቆጠሩ ነዋሪዎች እንዲጎበኙ እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብም ፓርኮቹን ለሕብረተሰብ አገልግሎት ለሚውሉ ተግባራት እንዲያለሙ ለማነቃቃት ብሎም ከፓርኮቹ የተሻለ ገቢ በማመንጨት ከተማ አስተዳደሩ ለወጠናቸው የልማት ተግባራትን እንዲደግፉ የማስቻል ዓላማ ተይዟል ተብሏል።

በዚህ የማነቃቂያ መርሐግብር ላይ የሰርግና ልደት ትዝታዎች የፎቶግራፍ አውደርዕይ፣ የዲፕሎማቶች እና አምባሳደሮች እንዲሁም የሚዲያ ባለሞያዎች ጉብኝት ፣ የሰርከስ ትርዒት ፣ የልጆች ጨዋታ ዝግጅቶችን ጨምሮ በርካታ መሰናዶዎች እንደተዘጋጀ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ፋና ላምሮት እና ብሌን ዮሴፍ ተለያዩ

ለዓመታት በፋና ቴሌቪዥን እየተላለፈ በሚገኘው በ"ፋና ላምሮት" የድምጻዊውን ውድድር ላይ በመሐል ዳኝነት ስትዳኝ የቆየችው የሙዚቃ ባለሞያው ብሌን ዮሴፍ ከፋና ላምሮት ጋር የነበራትን ቆይታ መጨረሷን በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።

ብሌን ዮሴፍ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"የፋና ላምሮት የዳኝነት ቆይታዬን ጨርሻለሁ።ሲያበረታኝ የነበረዉ ልብን የሚያሞቅ ፍቅራችሁ እንደነበር ታዉቁ ይሆን እግዚአብሔር ያክብርልኝ እወዳችኋለሁ" ብላለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የታሪክ ተመራማሪ ፣ ደራሲ ፣ግራፊክስ ዲዛይነርና ሠዓሊ በሁሉም አለበል በሙያዋ ላበረከተችው በርካታ ስራዎች የምስጋና ዝግጅት ተከናወነ

ደራሲ፣ገጣሚ፣ሠዓሊ እና በጎ ፍቃደኛ በሁሉም አለበል ለስራቻቸው ስራዎች ዛሬ ግንቦት 10 2016 ዓ.ም በፈንድቃ ባህል ማዕከል በተዘጋጀ የምስጋና ሥነሥርዓት ላይ በወዳጆቿ ተመስግናለች።

ደራሲ በሁሉም አለበል "የተዳፈነው ታሪክ :ራስ ጉግሣ ወሌ" ፣ "ታሪክን በቅኔ" ፣ የተዋጡ ድምጾች ፣ውስብስብ ውሎዎች ፣ሣምራዊ ፣የሸንበቶ ባህር የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሳለች።

"ኢትዮጵያዊ ሀገሩ የት ነው?" ፣ "የተቆለፈበት ቁልፍ" ፣ "ወድቆ የተገኘ ሀገር " ፣"ናፍቆት" የተሰኙ መጻሕፍትን ጨምሮ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ መጻሕፍት የሽፋን ገፅ (Cover) ሰርታለች።

በዚህ የምስጋና ሥነሥርዓቱ ላይ ዶ/ር ፀደይ ወንድሙ ስለ በሁሉም አለበል የታሪክ መጻሕፍት ዳሰሳ አቅርባለች።

ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ አርቲስት ደሳለኝ ኃይሉ ፣ ደራሲና የፊልም ባለሞያ እስከዳር ግርማይ ፣ ገጣሚ ይታገሱ ጌትነት ዶ/ር ተዋበች ቢሻው ፣ ዘላለም አለበል እና ሌሎችም ስለደራሲ ለሁሉም አለበል  ንግግር አድርገዋል።

በጉንጉን ባንድ ታጅበው ድምጻዊ ኤልያስ ተባባል ፣ ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ የሙዚቃ እና ግጥም ስራዎችን አቅርበዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ አዲስ አልበም

የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ አዲስ አልበም እንደተጠናቀቀ እና በቅርቡ ለአድማጮች እንደሚቀርብ ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ከዚህ ቀደም "አንተ ጎዳና" እና "ናፍቆት እና ፍቅር"የተሰኙ የሙዚቃ አልበሞችን ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል።

ለብዙ ፈጣን የኪነጥበብ መረጃዎች ይህን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ:

https://t.me/EventAddis1
"ብርሃን ኮንሰርት" የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል

ገቢው ለሰበታ መርሐ የዓይነስውራን ት/ቤት እንዲውል የተዘጋጀው "ብርሃን ኮንሰርት " የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም በግዮን ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ላይ ድምጻዊያኑ አብዱ ኪያር ፣ ቀመር የሱፍ ፣ ይርዳው ጤና ፣ባልከው አለሙ፣ ኃይማኖት ግርማና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎችን ያቀርባሉ ተብሏል።

የኮንሰርቱ መግቢያ መደበኛ መግቢያ 500 ሲሆን ቪአይፒ 1500 ብር እንደሆነ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
በእይታ ላይ ያሉ የሥዕል አውደርዕዮች

📍የሠዓሊ ሳምሶን ከበደ የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "ወይን ጠጅ" የሥዕል አውደርዕይ ከግንቦት 5 2016 ዓ.ም  ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ እይታ ይገኛል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ግንቦት 19 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል።

📍የሠዓሊ ሱራፌል አማረ “ድፍድፍ ” የተሰኘው የሥነጥበብ አውደርዕይ ከግንቦት 9 2016 ዓ.ም ጀምሮ ቦሌ ዓለም ሲኒማ ጀርባ በሚገኘው አትሞስፌር ጋለሪ ውስጥ በእይታ ላይ ይገኛል።ይህ አውደርዕይ እስከ ግንቦት 22 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1