መቅረዝ የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል
ቅድስት ይልማ የክብር እንግዳ የሆነችበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል።
አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ሀሙስ ግንቦት 8 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዕለቱም በእረኛዬ ፣ በታዛ ፣ ዶቃን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት ደራሲና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ የክብር እንግዳ ሆና የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

"ጉማ "ፊልም በዲጂታላይዝድ መልክ ተደራጅቶ ድጋሜ ለመድረክ እንዲበቃ ተጠየቀ
በሚሼል ፓፓቲከስ የተደረሰው የ"ጉማ"ፊልም ዳራ እና ሒሳዊ ዳሰሳን በሚመለከት በቴአትርና ጥበባት መምህር ያሬድ ዘኪሮስ ጥናታዊ ጽሁፍና ሒሳዊ ምልከታ ቀርቧል፡፡
እንደ መምህር ያሬድ በኢቲኖግራፊ የፊልም ዘውግ የተሰራና በኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ የሚያጠነጥነው"ጉማ" በግጭት አፈታት ላይ የሚያተኩር ቢሆንም ከሁሉም ማህበረሰብ ተነጥሎ የማይታየውን ባህል እምነትና አስተሳሰብ አጣምሮ የያዘ ድንቅ ኢትዮጵዊ ፊልም መሆኑን አንስተዋል፡፡
ፊልሙን ከሥነ ምግባራዊ ሒስ አተያይ ረገድ ባህልንና ዕሴትን ያዋቀረ በመሆኑ ችግርን በራስ የመፍታት ባህልና ጥበብን ይናገራል ነው ያሉት፡፡
ሚሼል ፓፓቲከስ ሃገርኛ ታሪክን በ"ጉማ" ፊልም ላይ የደረሱት ከማህበረሰቡ ተነጥሎ የማይታየውን ባህል ለማሳደግ እንደነበር መምህር ያሬድ አንስተዋል፡፡
ዛሬ ላይ እየተደረሱ ለህዝብ የሚበቁት ሃገርኛ ፊልሞች በአስተሳሰብና በፍልስፍና ከምዕራባዊያን የተቀዱ በመሆናቸውና፤ የበሰለ ምናባዊ አስተሳሰብ ስለሚጎድላቸው በታሪክ አወቃቀርና በአስተማሪነታቸው የጉማን የድርሰት መሰረት የያዙ አይደሉም ይላሉ፡፡
ፊልሙ ሀገር ዉስጥ እንደማይገኝና በሀገረ አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ተሰንዶ እንደተቀመጠ ተመላክቷል።
በዚሁ ምክንያት ዘመኑን በዋጀ መሳሪያና ባለሙያ ተሰንዶ ለእይታ እንዲቀርብ ቢሮው ጥረት እያደረገ ቢሆንም የኪነ-ጥበብ ተቋማትና ማህበራት የድርሻቸውን እንዲወጡ ሠርፀ ፍሬስብሃት ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሚዲያ ተቋማት የምስጋና ፕሮግራም አካሄድ
የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል የበጎ አድራጎት ሥራዎች ነፃ የማስታወቂያ ሰዓት በመስጠት እንዲተዋወቅ እንዲሁም ማዕከሉ ድጋፍ እንዲያገኝ ስለአበረከቱትና እያበረከቱ ስላለው ድጋፍ እውቅና የመስጠት እና ምስጋና የማቅረብ ዝግጅት ዛሬ ግንቦት 8 2016 ዓ.ም በማዕከሉ ተካሄዷል።
ባለፉት ጊዜያት ነፃ የአየር ሰዓት ፣ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ጨምሮ በሚሊዮን ብሮች የሚያወጣ የሚዲያ አገልግሎት ለማዕከሉ እንደተሰጠም ተገልጿል።
ለማዕከሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካበረከቱ የሚዲያ ተቋማት መካከል አርትስ ቲቪ፣ ኦቢኤን ፣ ኢቢሲ ፣ ኤፍቢሲ፣ኢቢኤስ፣አሻም ቲቪ ፣ ትርታ 97.6፣ ቲቪ 9 ፣ አሚኮ፣ አሐዱ ሬድዮ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
በፕሮግራሙ ላይም በኢትዮጵያ ከ 7ሺ በላይ የልብ ህሙማን ህፃናት ወረፋ እየጠበቁ እንደሆነ እና ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሹ ተገልጿል ።
የኢትዮጲያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል በሀገራችን የነጻ የልብ ቀዶ ሕክምና በመስጠት ላይ የሚገኝ ብቸኛ ተቋም ሲሆን ላለፉት 34 ዓመታት ከ8000 በላይ ለሚሆኑ ሕጻናት የልብ ቀዶ ሕክምና በማድረግ የነፍስ አድን ሥራዎችን እንዳከናወነ ተገልጿል።
ማዕከሉ ሁሉንም የሕክምና ወጪዎች ያለምንም ክፍያ በነጻ እንደሚያከናውን የገለፅ ሲሆን አስፈላጊ ወጪዎችንም በዋነኛነት ከማሕበረሰቡ በሚሰበሰብ ዕርዳታ በተጨማሪ ደግሞ ከሀገር በቀል እና የውጪ ድርጅቶች በሚደረግ ድጋፍ በመሸፈን ላይ እንደሚገኘ ተነግሯል።

"መቅረዝ ሥነኪን" ፕሮግራም በድምቀት ተካሄደ
ደራሲና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ የክብር እንግዳ የሆነችበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ትላንት ግንቦት 8 2016 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ በድምቀት ተካሄዷል።
በዕለቱም በእረኛዬ ፣ በታዛ ፣ ዶቃን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት ደራሲና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ የክብር እንግዳ ሆና የተገኘች ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና የዳንስ ስራዎቻቸውን አቅረበዋል።
በዝክረ መቅረዝ ሥነኪን የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት መስራችና የረቂቅ ሙዚቃ ሊቁ ፕ/ር አሸናፊ ከበደ የልደት ቀናቸውን ምክንያት በማድረግ ተዘክረዋል።
ፍሬሕይት መላኩ ፣ጋሻው የኋላሸት ፣ጆኒ ሀብቴ ፣ታዲዮስ አዲሱ፣ ሲራክ ወንድሙ፣ ዳንኤል ሙሉጌታ የግጥም ስራዎቻቸውን አቅረበዋል።
የህግ ባለሞያ እና ደራሲ መሰረት ባህሩ "እሰሩኝ" ከተሰኘው መጽሐፏ አጭር ልቦለድ ያነበበች ሲሆን በኪዳኔ ግርማ ኮቴንቴፓራሪ ዳንስ ቀርቧል።በተጨማሪም ተስፋ እና ኮዜት እንዳለ የሙዚቃ ስራዎቻውን አቅረበዋል።
በዝግጅቱ ላይ ደራሲ ኃይለመኮለት መዋዕል "እረኛዬ" ድራማ ላይ ስለነበራቸው ገጠመኝ እና ስለ ቅድስት ይልማ ምስክርነት የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም ደራሲ እና ዳይሬክትር ቅድስት ይልማ የማሳረጊያ ንግግር አድርጋለች።

"መንታ መንገድ"ተውኔት እሁድ ከመድረክ ይሰናበታል
ከሁለት ዓመት በፊት ድጋሚ ወደ መድረክ የተመለሰው "መንታ መንገድ" ተውኔት የፊታችን እሁድ ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከመድረክ እንደሚሰናበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት አስታውቋል።
በቶፊቅ አልሃኪም የተደረሰው እና የአለማየሁ ገ/ሕይወት አዛማጅ ትርጉም የሆነው እንዲሁም ተክሌ ደስታ በአዘጋጅነት የተሳትፈበት ተውኔቱ በመድረክ ቆይታው እንደ ሚካኤል ታምሬ፣ እታፈራሁ መብራቱ፣ ተስፋዬ ገ/ሀና፣ ዳንኤል ተገኝ ፣ ሚኪ ተስፋን ጨምሮ በርካታ ባለሙያዎች እንደተሳተፉበት ይታወሳል።
ከቴአትር ቤቱም ይህን ቴአትር ያልተመለከታችው የቴአትር አፍቃሪያን፣ ከመድረክ ከመሰናበቱ በፊት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በመገኘት እንዲትመለከቱ ጥሪ ቀርቧል።

"ለእናቴ" የሥነጽሑፍ ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት
ባሳለፍነው ዓመት ይፋ የተደረገው የእናት ባንክ "ለእናቴ" የጽሑፍ ውድድር አሸናፊዎች የፊታችን ግንቦት 19 2016 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል በሚዘጋጀ ልዩ ፕሮግራም ሽልማት እንደሚበረክትላቸው እናት ባንክ አስታውቋል።
ለ"እናቴ" የጽሑፍ ውድድር ከአንድ ወር በላይ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በተደረገ ጥሪ መሰረት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ውስጥ የሚገኙ ከ1500 በላይ የሥነጽሑፍ ተዋዳዳሪዎች እንደተሳተፉ ተገልጿል።
ውድድሩ ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር ፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርው ጽሑፍ የሚገልጽበት ሲሆን በይዘት ደረጃም ተዋዳዳሪዎች "ለእናቴ" ብለው ስለእናታቸው የሚያጋሩበትን ፍቅርና ስሜት ዳኞች አወዳድረው የሚያበላልጡበት ሳይሆን ተወዳዳሪዎች ለእናታቸው ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት እንዴት እንደገለጹ ፣ ስሜታቸውን ወደ ሌሎች ለማጋባት እንዴት እንደጣሩ የተዳኙበት አውደ እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።
የማወዳደሪያ መስፈርቱ በተመሳሳይ መንገድ የቀረበ ሲሆን የቅርጽ ጉዳዮች 50 በመቶ የይዘት ጉዳዮች 50 በመቶ በድምሩ ከ100 ነጥብ የተያዘ ሲሆን
በውድድሩ ከአንድ እስከ አምስት የወጡ አሸናፊዎች ሽልማት የሚሰጣቸው ሲሆን ሌሎች አስራ አንድ የተመረጡ ጽሑፎችም በውድድሩ በተዘጋጀው መጽሔት ላይ ጽሐፎቻቸው ይወጣል ተብሏል።
ግንቦት 19 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በሒልተን ሆቴል በተዘጋጅው የቀይ ምንጣፍ የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙበት ሲሆን የተወዳዳሪዎች ሥራዎች በራሳቸው አንደበት መድረክ ላይ ይቀርባል ተብሏል።
በተጨማሪም የተለያዩ የኪነጥበብና ሥነጽሑፍ ባለሞያዎች እንዲሁም አትሌቶች ስለእናቶቻቸው ለታዳሚያን ሀሳባቸውን እንደሚያጋሩ ተገልጿል።

ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ ሙሉ ለሙሉ ታድሶ በአዲስ መልክ ስራ መጀመሩን በአክብሮት ይገልፃል ::
ውድ የቶቶት ቤተሰቦቻችን ከግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ ቁርጥ ቤታችንን በክብር እንዲጎበኙልን ጠርተንዎታል ::
ምርጥ ምርጡን ሁሌም ለእናንተ እናቀርባለን ::
0116 46 07 18
09 09 00 44 00
ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ
አድራሻ ገርጂ መብራት ሀይል አንበሳ ጋራዥ ፊት ለፊት
#Ads

የድምጻዊ ደሳለኝ መርሻ"ኑድኒያ" የጉራጊኛ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት ይለቀቃል
የድምጻዊ ደሳለኝ መርሻ "ኑድኒያ "የተሰኘ 7ኛ የጉራጊኛ የሙዚቃ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ይደርሳል።
ይህ የጉራጊኛ አልበም 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስለፍቅር፣ ስለሃገር፣ ስለማህበራዊ ህይወት የሚዳስስ ሁለገብ አልበም ነው ተብሏል።
አልበሙ ላይ በርካታ ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በግጥም እና ዜማ ራሱ ደሳለኝ መርሻ፣ ፈለቀ ማሩ፣ ናቲ ኃይሌ፣ ዘነበ መርሃባ፣ ሀብታሙ አብርሃም፣ አለማየሁ ወልዴ የተሳተፉ ሲሆን በቅንብር አሌክስ ይለፍ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፣ ሰማገኘው ሳሙኤል፣ ፋኑ ጊዳቦ፣ ቢኒአነዴ ርሆቦት (ሮባ) የተሳተፉ ሲሆን በሚክሲንግ ሰለሞን ሃ/ማርያም፣ ፍሬዘር ታዬ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፣ ቢኒአንዴ ተሳትፈዋል፡፡ በማስተሪንግ ሰለሞን ሃ/ማርያም በአልበሙ ተሳትፏል።
"ኑድኒያ" አልበም ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በአርቲስቱ ዩቲዩብ ቻናልና በሁሉም ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያ የሚገኝ ሲሆን ሲዲውን ኪነት ኢንተርቴይመንት አሳትሞ ያከፋፍለዋል፡፡
አርቲስት ደሳለኝ መርሻ አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ በትክክል የተመዘገበ 3.8 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ዛሬ በማርዮት ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጿል።
አርቲስት ደሳለኝ መርሻ በሙዚቃዎቹ የጉራጌ እሴቶችን፤ ታሪክ፤ ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና ማሕበራዊ ሕይወትን በተባ ኪናዊ ለዛ በመሰነድ እና በማስተዋወቅ የራሱን አሻራ አኑሯል፡፡
ባለፉት 20 አመታት ሙዚቃን ሕይወቱ በማድረግ ለበርካታ ድምፃውያንም ግጥም እና ዜማዎችን የሰጠው ደሳለኝ መርሻ የመጀመርያ አልበሙ ያሳተመው አዲስ አበባ ውስጥ የታክሲ ሹፌር እየሰራ ባለበት ወቅት ነበር።

አፍሮ ኤዥያ ዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ "ድልድዮችን መገንባት ህይወትን ማዳን" በሚል መሪቃል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።
ኤፍ ዚ ማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር አፍሮ ኤዥያ ዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እያካሄደ ይገኛል።
ይህ አለም ዓቀፍ የጤና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከዛሬ ግንቦት 09 ቀን እስከ ግንቦት 11 2016 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል ተብሏል።
በዚህም ኤክስፖ ላይ ከ4 መቶ በላይ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ የጤና ተቋማት እንደሚሳተፉ የተገለጸ ሲሆን ማህበረሰቡ እየመጣ ሊጎበኘውና ሊጠቀምበት እንደሚገባ ተገልጿል።

የተለያዩ መጻሕፍትን በስስ ቅጂ( Soft Copy) ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ይህንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀላሉ።
https://t.me/kooblife
https://t.me/kooblife
https://t.me/kooblife
Ads
እናመሰግናለን መልካም ቀን !
https://t.me/kooblife
https://t.me/kooblife
https://t.me/kooblife
Ads
እናመሰግናለን መልካም ቀን !
ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን "ሙዚየሞች ለትምህርት እና ለምርምር” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።
አለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ47 ግዜ በሀገራችን ደግሞ ለ22ኛ ግዜ በዛሬው እለት ግንቦት 9 /2016 በኢትዮጵያ ቅርስ ባለ ስልጣን አዘጋጅነት በመከበር ላይ ይገኛል።
እለቱ ሲከበር ሙዚየሞች ትኩረት እንዲያገኙ እና ያልታዩት እንዲታዩ የማድረግ አንዱ አላማው መሆኑ ተነስቷል።
የሙዚየም ዋነኛው ስራ ማስተማር ሲሆን ለሀገር ግንባታ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም ተገልጿል።
ሙዚየሞች አንድነታችንን የሚያጠናክሩልን በመሆናቸው ልንንከባከባቸው እና ልንጎበኛቸው እንደሚገባም ተጠቁሟል።
ወደፊት ሙዚየሞች የሚጎበኙበት ሰአት የማሻሻል እና ከስራ ሰአት ውጪ ሰዎች መጎብኘት የሚችሉበት ሁኔታ በማመቻቸት ላይ እንደሆነም ሰምተናል።
ዘገባው ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው።

አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል እና የአፍሪካ ቀን ክብረ-በዓል ከግንቦት 16 እስከ 18 በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ በጋራ ሊካሄዱ ነው
"አዲስ ጃዝ" የዚህ ዓመት ፌስቲቫሉን ከግንቦት 16 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን የአፍሪካ ቀን ክብረ-በዓል አብረው ይከበራል ተብሏል።
ዝግጅቱ የሚካሄድበት ስፍራ አፍሪካን ጃዝ ቪሌጅ ሲሆን አፍሪጎ ባንድ ከዩጋንዳ፣ ድምጻዊ ሴልሞር ቱኩድዚ ከዚምባብዌ፣ ማቲው ቴምቦ ከዛምቢያ በዕለቱ የሙዚቃቸው ስራቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃ መልክ ከማስያዝ አንስቶ የሮሃ ባንድ ድምቀት እስከ መሆን የሚጠቀሰው አንጋፋው ዳዊት ይፍሩን እንዲሁም አንጋፋው ግርማ በየነ እና ሌሎች አዳዲስ አርቲስቶችም በመድረኩ ስራቸውን ያቀርባሉ።
ከላይ ከተዘረዘሩት አርቲስቶች ጋር በጋራ እንደ ጆርጋ መስፍን፣ ያሆ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ፣ መሐሪ ብራዘርስና ዮሃና ሳህሌ የፌስቲቫሉ ድምቀት እንደሚሆኑ ተነግሯል።
የዚህ ዓመት ፌስቲቫል በልዩ ሁኔታ ለእውቁ ሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን የአልበም ምርቃት ትኩረት በመስጠት አድማጮች ልዩ ምሽት እንዲያሳልፉ እድሉን ይፈጥራል፡፡
በፌስቲቫሉ ሁለተኛ ቀን ማለትም ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰላም ፕሮጀክቶች አንዱ ከሆነው ከኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ፕሮጀክትና አፍሪካ ኅብረት ጋር በጋራ ከሚከበረው የአፍሪካ ቀን ጋር በጋራ ይከበራል።

ቴክኖ አዲሱን እና በቅርቡ በባርሴሎናው ዓመታዊ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ ያደረገውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በይፋ በኢትዮጵያ አስተዋወቀ።
የሞባይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ አዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስተዋወቀ። አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ (SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው።
ቴክኖ በቅርቡ በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው አንጋፍው እና አመታዊው የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን (Mobile World Congress) ላይ ይህን አዲስ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴልን ጨምሮ የተለያዩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በይፋ እንዳስተዋቀ የሚታወቅ ነው፣ በዚሁ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ የሆነው ቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በማንኛውም አይነት ሁኔታ እና የብርሃን መጠን ሳይገድበው ቁልጭ ያሉ ፎቶዎችን የማንሳት አቅም እንዲኖረው በማሰብ በካሜራ ቴክኖሎጂ አንጋፋው ሶኒ (SONY) ምርት የሆነውን ዘመናዊ ሴንሰር (Sony IMX890) የተገጠመለት መሆኑ ለየት ሲያደርገው በኢንዱስትሪው የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ‘PolarAce’ ፖላርኤስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የቪድዮ ኢሜጂንግ ሲስተሙን በማዳበር እና እንከን የለሽ በማድረግ የካሜራ ቴክኖሎጂውን ሁለቱ ኩባንያዎች ወደ ላቀ ደረጃ አድርሰውታል።

የ"ክብር ሽልማት" አሸናፊዎች ዝርዝር
የመጀመሪያው "የክብር ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በግዮን ግሩቭ ጋርደን ውስጥ ተካሄዷል።
የክብር ሽልማት አሸናፊዎች ዝርዝር የሚከተለውን ይመስላል:
📍የዓመቱ ምርጥ ልብ ወለድ
ቤባንያ (ዓለማየሁ ገላጋይ)
📍የዓመቱ ምርጥ አጫጭር ልብወለድ
ናፍቆት (እስከዳር ግርማይ)
📍የዓመቱ ምርጥ ግለታሪክ መጽሐፍ
ኅብር ሕይወቴ (ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ)
📍የዓመቱ ምርጥ የወግና መጣጥፍ መጽሐፍ አሸናፊ
ችቦ (ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ )
📍የዓመቱ ምርጥ ተውኔት
በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ (ውድነህ ክፍሌ)
📍የዓመቱ ምርጥ ግጥም
እናርጅ እናውጋ (ጌራወርቅ ጥላዬ)
📍የዓመቱ ምርጥ የፊልም ድርሰት
ዶቃ (ቅድስት ይልማ እና ቤዛ ኃይሉ)
📍የዓመቱ ምርጥ የዘፈን ግጥም
ላይለ ኩሉ (ዳን አድማሱ)
📍የክብር ሽልማት በሥነጽሑፍ ዘርፍ የሕይወት ዘመን ሽልማት
ኃይለመለኮት መዋዕል
📍የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ የመዝናኛ ዩቲዩብ
ዶንኪ ቲዩብ
📍የዓመቱ ምርጥ የሚዲያ ሰው
መንሱር አብዱልቀኒ
📍የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ዝግጅት አቅራቢ
አስካለ ተስፋዬ
📍የዓመቱ በጋዜጠኝነት ዘርፍ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ
አማረ አረጋዊ
📍የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅት
ትዝታችን በኢቢኤስ
📍የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት
ለዛ
📍የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት አቅራቢ
ትዕግስት በጋሻው
ድረገፅ: https://eventaddis.com