Event Addis Media
9.08K subscribers
5.26K photos
5 videos
3 files
3.97K links
Connect with Addis Ababa's artistic community! Find out about art exhibitions, music events, workshops, and cultural experiences. Contact: @Tmanaye
Download Telegram
“የስዕል ደብተሬ” የልጆች ቀለም ማቅለሚያ እና አጭር ታሪክ ያካተተ መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ይመረቃል

በምዕራፍ ግሩም የተዘጋጀው “የስዕል ደብተሬ” የተሰኘ የልጆች ቀለም ማቅለሚያ እና አጭር ታሪክ ያካተተ የህፃናት መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ግንቦት 11 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ይመረቃል።

መፅሃፉ ለኢትዮጵያውያን ልጆች የተዘጋጀ ሃብታም ከሆነው ባህላቸውና ታሪካቸው የሚያቀራርባቸው፣ የሚያጭውት፣ የሚያዝናና እንዲሁም የታዳጊዎችን የመፍጠር ችሎታ የሚያሳድግና እውቀት የሚሰጣቸው ብቻ ሳይሆን ስነምግባር የሚያስተምር ፣መረዳዳትንና መዋደድን የሚመክር ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን አዘጋጇ ለሸገር ታይምስ ሚዲያ ገልጻለች፡፡

የመጽሐፉ ምርቃት እሁድ ግንቦት 11 ቀን ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል እንደሚደረግና ወላጆች በምርቃት ቦታ ከልጆቻቻው ጋር በመገኘት ልጆቻቻውን እያስተማሩና እያዝናኑ ለኢትዮጵያ ልጆች ጠቃሚና ገንቢ ተደርገው የተዘጋጁትን መጻሕፍት እንዲመርቁም አዘጋጆቹ ምዕራፍ ግሩምና ፈንድቃ የባህል ማእከል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ አዲስ ከሚመረቀው "የስዕል ደብተሬ" በተጨማሪ በአዘጋጇ ከዚህ ቀደም የተዘጋጀውን በኢትዮጵያን ባህላዊ አልባሳት የማቅለሚያ መጽሐፍ ቁጥር 1 መጽሐፍ ም የማግኘት እድልም ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"ትዝታ"ፊልም ዛሬ ይመረቃል

የዳንኤል አንማው "ትዝታ"ፊልም ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 7 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፒያሳ በሚገኛው ኤልያና ሆቴል አዳራሽ ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቀይ ምንጣፍ ሥነሥርዓት ይመረቃል::

እንግዳሰው ሀብቴ(ቴዲ) ፣ቃልኪዳን ጥበቡ ፣ይመር አባተ፣ፋንታ ስንታየሁ ፣ዳግም ተዘራ ፣በሀይሉ እንግዳ እና ሌሎችም በተዋይነት ተሳተፈውበታል።

የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ዳንኤል አንማው ሲሆን በኤላዳን ፊልምስ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

የትዝታ ፊልም ምርቃት ግንቦት 9 10 11 እና ግንቦት 16 17 18 በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል::

ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1
የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል «ዕፅዋትን ይመልከቱ ንፁህ አየር ይተንፍሱ »ልዩ የመዝናኛ መርሐግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል «ዕፅዋትን ይመልከቱ ! ንፁህ አየር ይተንፍሱ !» በሚል መሪ ቃል ግንቦት 10 እና 11 ቀን 2016 ዓ.ም በማዕከሉ ውስጥ ልዩ የመዝናኛ መርሐግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ሁለት ቀናት በሚቆየው መርሐግብር ላይ የአዋቂዎች የተራራ ላይ የእግር ጉዞ፣  አዝናኝ የሙዚቃ ዝግጅት፣ የህፃናት መዝናኛ መጫዎቻዎች፣ የፈረስ እና ግመል ግልቢያ ፣ የማዕከሉ ሳቢና ማራኪ መልክአ-ምድራዊ አቀማመጥ ጉብኝት ፣ የመፅሀፍ ዓውደ-ርዕይ  እንዲሁም የተለያየ የዕደ-ጥበብ ስራዎች በተግባር የሚሞከሩበት
መሠናዶዎች ያለምንም  የመግቢያ ክፍያ በነጻ እንደተዘጋጁ የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የደንበኛች ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ አቶ ክንፈ ገብረማርያም ገልጸዋል።

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን እነዚህ አገልግሎቶችን በተሻለ ደረጃ ለማስተዋወቅ ዓላማ አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ አቶ ክንፈ ገብረማርያም ጨምረው  ገልጸዋል።

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በ705 ሄክታር ቦታ ላይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ይገኛል። የዕፅዋት ማዕከሉ ከባህር ጠለል ከ2600- 2950 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን  ከ950 በላይ ሀገር በቀል የዕፅዋት ዝርያዎችን ይዟል።

Via ጌች ሀበሻ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ዛሬ ሐሙስ ነው

እነሆ የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥለው ይቀርባሉ

ይህችን ሊንክ https://rb.gy/9fmwu6 በመነካት ብቻ የሐሙስ መረጃዎችን በድረገጻችን በጥሩ አቀራረብ ማንበብ ትችላላችሁ።

ማሳሰቢያ: የኤቨንት አዲስ ድረገጽ መረጃዎችን በእርሶዎ ሚዲያ ላይ ሲጠቀሙ እባክዎ በተገቢው መንገድ ምንጭ ይጠቀሱ። በተገቢው መንገድ ምንጭ መጥቀስ የጋዜጠኝነት ብቃት አንዱ መለኪያ ነው።

የEventAddis/ሁነት አዲስ ማህበራዊ ገፆቻችን:

Telegram:https://t.me/EventAddis1

Website: https://eventaddis.com

Facebook:https://facebook.com/groups/2009372275938661/

Facebook Page:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851&mibextid=ZbWKwL
መቅረዝ የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል

ቅድስት ይልማ የክብር እንግዳ የሆነችበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ዛሬ ሀሙስ ግንቦት 8 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዕለቱም በእረኛዬ ፣ በታዛ ፣ ዶቃን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት ደራሲና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ የክብር እንግዳ ሆና የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"ጉማ "ፊልም በዲጂታላይዝድ መልክ ተደራጅቶ ድጋሜ ለመድረክ እንዲበቃ ተጠየቀ

በሚሼል ፓፓቲከስ የተደረሰው የ"ጉማ"ፊልም ዳራ እና ሒሳዊ ዳሰሳን በሚመለከት በቴአትርና ጥበባት መምህር ያሬድ ዘኪሮስ ጥናታዊ ጽሁፍና ሒሳዊ ምልከታ ቀርቧል፡፡

እንደ መምህር ያሬድ በኢቲኖግራፊ የፊልም ዘውግ የተሰራና በኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ የሚያጠነጥነው"ጉማ" በግጭት አፈታት ላይ የሚያተኩር ቢሆንም ከሁሉም ማህበረሰብ ተነጥሎ የማይታየውን ባህል እምነትና አስተሳሰብ አጣምሮ የያዘ ድንቅ ኢትዮጵዊ ፊልም መሆኑን አንስተዋል፡፡

ፊልሙን ከሥነ ምግባራዊ ሒስ አተያይ ረገድ ባህልንና ዕሴትን ያዋቀረ በመሆኑ ችግርን በራስ የመፍታት ባህልና ጥበብን ይናገራል ነው ያሉት፡፡

ሚሼል ፓፓቲከስ ሃገርኛ ታሪክን በ"ጉማ" ፊልም ላይ የደረሱት ከማህበረሰቡ ተነጥሎ የማይታየውን ባህል ለማሳደግ እንደነበር መምህር ያሬድ አንስተዋል፡፡

ዛሬ ላይ እየተደረሱ ለህዝብ የሚበቁት ሃገርኛ ፊልሞች በአስተሳሰብና በፍልስፍና ከምዕራባዊያን የተቀዱ በመሆናቸውና፤ የበሰለ ምናባዊ አስተሳሰብ ስለሚጎድላቸው በታሪክ አወቃቀርና በአስተማሪነታቸው የጉማን የድርሰት መሰረት የያዙ አይደሉም ይላሉ፡፡

ፊልሙ ሀገር ዉስጥ  እንደማይገኝና በሀገረ አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ተሰንዶ እንደተቀመጠ ተመላክቷል።

በዚሁ ምክንያት ዘመኑን በዋጀ መሳሪያና ባለሙያ ተሰንዶ ለእይታ እንዲቀርብ ቢሮው ጥረት እያደረገ ቢሆንም የኪነ-ጥበብ ተቋማትና ማህበራት የድርሻቸውን እንዲወጡ ሠርፀ ፍሬስብሃት ጥሪ አቅርበዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሚዲያ ተቋማት የምስጋና ፕሮግራም አካሄድ

የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል የበጎ አድራጎት ሥራዎች ነፃ የማስታወቂያ ሰዓት በመስጠት እንዲተዋወቅ እንዲሁም ማዕከሉ ድጋፍ እንዲያገኝ ስለአበረከቱትና እያበረከቱ ስላለው ድጋፍ እውቅና የመስጠት እና ምስጋና የማቅረብ ዝግጅት ዛሬ ግንቦት 8 2016 ዓ.ም በማዕከሉ ተካሄዷል።

ባለፉት ጊዜያት ነፃ የአየር ሰዓት ፣ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ጨምሮ በሚሊዮን ብሮች የሚያወጣ የሚዲያ አገልግሎት ለማዕከሉ እንደተሰጠም ተገልጿል።

ለማዕከሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካበረከቱ የሚዲያ ተቋማት መካከል አርትስ ቲቪ፣ ኦቢኤን ፣ ኢቢሲ ፣ ኤፍቢሲ፣ኢቢኤስ፣አሻም ቲቪ ፣ ትርታ 97.6፣ ቲቪ 9 ፣ አሚኮ፣ አሐዱ ሬድዮ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

በፕሮግራሙ ላይም በኢትዮጵያ ከ 7ሺ በላይ የልብ ህሙማን ህፃናት ወረፋ እየጠበቁ እንደሆነ እና ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሹ ተገልጿል ።

የኢትዮጲያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል በሀገራችን የነጻ የልብ ቀዶ ሕክምና በመስጠት ላይ የሚገኝ ብቸኛ ተቋም ሲሆን ላለፉት 34 ዓመታት ከ8000 በላይ ለሚሆኑ ሕጻናት የልብ ቀዶ ሕክምና በማድረግ የነፍስ አድን ሥራዎችን እንዳከናወነ ተገልጿል።

ማዕከሉ ሁሉንም የሕክምና ወጪዎች ያለምንም ክፍያ በነጻ እንደሚያከናውን የገለፅ ሲሆን አስፈላጊ ወጪዎችንም በዋነኛነት ከማሕበረሰቡ በሚሰበሰብ ዕርዳታ በተጨማሪ ደግሞ ከሀገር በቀል እና የውጪ ድርጅቶች በሚደረግ ድጋፍ በመሸፈን ላይ እንደሚገኘ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"መቅረዝ ሥነኪን" ፕሮግራም በድምቀት  ተካሄደ

ደራሲና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ የክብር እንግዳ የሆነችበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ትላንት ግንቦት 8 2016 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ በድምቀት ተካሄዷል።

በዕለቱም በእረኛዬ ፣ በታዛ ፣ ዶቃን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት ደራሲና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ የክብር እንግዳ ሆና የተገኘች ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና  የዳንስ ስራዎቻቸውን አቅረበዋል።

በዝክረ መቅረዝ ሥነኪን  የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት መስራችና የረቂቅ ሙዚቃ ሊቁ ፕ/ር አሸናፊ ከበደ የልደት ቀናቸውን ምክንያት በማድረግ ተዘክረዋል።

ፍሬሕይት መላኩ ፣ጋሻው የኋላሸት ፣ጆኒ ሀብቴ ፣ታዲዮስ አዲሱ፣ ሲራክ ወንድሙ፣ ዳንኤል ሙሉጌታ የግጥም ስራዎቻቸውን አቅረበዋል።

የህግ ባለሞያ እና ደራሲ መሰረት ባህሩ "እሰሩኝ" ከተሰኘው መጽሐፏ አጭር ልቦለድ ያነበበች ሲሆን በኪዳኔ ግርማ  ኮቴንቴፓራሪ ዳንስ ቀርቧል።በተጨማሪም ተስፋ እና ኮዜት እንዳለ የሙዚቃ ስራዎቻውን አቅረበዋል።

በዝግጅቱ ላይ ደራሲ ኃይለመኮለት መዋዕል "እረኛዬ" ድራማ ላይ ስለነበራቸው ገጠመኝ እና ስለ ቅድስት ይልማ ምስክርነት የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም ደራሲ እና ዳይሬክትር ቅድስት ይልማ የማሳረጊያ ንግግር አድርጋለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"መንታ መንገድ"ተውኔት እሁድ ከመድረክ ይሰናበታል

ከሁለት ዓመት በፊት ድጋሚ ወደ መድረክ የተመለሰው "መንታ መንገድ" ተውኔት የፊታችን እሁድ ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከመድረክ እንደሚሰናበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት አስታውቋል።

በቶፊቅ አልሃኪም የተደረሰው እና የአለማየሁ ገ/ሕይወት አዛማጅ ትርጉም የሆነው እንዲሁም ተክሌ ደስታ በአዘጋጅነት የተሳትፈበት ተውኔቱ በመድረክ ቆይታው እንደ ሚካኤል ታምሬ፣ እታፈራሁ መብራቱ፣ ተስፋዬ ገ/ሀና፣ ዳንኤል ተገኝ ፣ ሚኪ ተስፋን ጨምሮ በርካታ ባለሙያዎች እንደተሳተፉበት ይታወሳል።

ከቴአትር ቤቱም ይህን ቴአትር ያልተመለከታችው የቴአትር አፍቃሪያን፣ ከመድረክ ከመሰናበቱ በፊት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በመገኘት እንዲትመለከቱ ጥሪ ቀርቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"ለእናቴ" የሥነጽሑፍ ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት

ባሳለፍነው ዓመት ይፋ የተደረገው የእናት ባንክ "ለእናቴ" የጽሑፍ ውድድር  አሸናፊዎች የፊታችን ግንቦት 19 2016 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል በሚዘጋጀ ልዩ ፕሮግራም ሽልማት እንደሚበረክትላቸው እናት ባንክ አስታውቋል።

ለ"እናቴ" የጽሑፍ ውድድር ከአንድ ወር በላይ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በተደረገ ጥሪ መሰረት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ውስጥ የሚገኙ ከ1500 በላይ የሥነጽሑፍ ተዋዳዳሪዎች እንደተሳተፉ ተገልጿል።

ውድድሩ ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር ፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርው ጽሑፍ የሚገልጽበት ሲሆን በይዘት ደረጃም ተዋዳዳሪዎች "ለእናቴ" ብለው ስለእናታቸው የሚያጋሩበትን ፍቅርና ስሜት ዳኞች አወዳድረው የሚያበላልጡበት ሳይሆን ተወዳዳሪዎች ለእናታቸው ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት እንዴት  እንደገለጹ ፣ ስሜታቸውን ወደ ሌሎች ለማጋባት እንዴት እንደጣሩ የተዳኙበት አውደ እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።

የማወዳደሪያ መስፈርቱ በተመሳሳይ መንገድ የቀረበ ሲሆን የቅርጽ ጉዳዮች 50 በመቶ የይዘት ጉዳዮች 50 በመቶ በድምሩ ከ100 ነጥብ የተያዘ ሲሆን
በውድድሩ ከአንድ እስከ አምስት የወጡ አሸናፊዎች ሽልማት የሚሰጣቸው ሲሆን ሌሎች አስራ አንድ የተመረጡ ጽሑፎችም በውድድሩ በተዘጋጀው መጽሔት ላይ ጽሐፎቻቸው ይወጣል ተብሏል።

ግንቦት 19 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በሒልተን ሆቴል በተዘጋጅው የቀይ ምንጣፍ የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙበት ሲሆን የተወዳዳሪዎች ሥራዎች በራሳቸው አንደበት መድረክ ላይ ይቀርባል ተብሏል።

በተጨማሪም የተለያዩ የኪነጥበብና ሥነጽሑፍ ባለሞያዎች እንዲሁም አትሌቶች ስለእናቶቻቸው ለታዳሚያን ሀሳባቸውን እንደሚያጋሩ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ ሙሉ ለሙሉ ታድሶ በአዲስ መልክ ስራ መጀመሩን በአክብሮት ይገልፃል :: 

ውድ  የቶቶት ቤተሰቦቻችን  ከግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ  ልዩ ቁርጥ ቤታችንን  በክብር እንዲጎበኙልን ጠርተንዎታል :: 
ምርጥ ምርጡን  ሁሌም ለእናንተ እናቀርባለን ::

0116 46 07 18
09 09 00 44 00

ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ

አድራሻ ገርጂ መብራት ሀይል አንበሳ ጋራዥ ፊት ለፊት

#Ads
የድምጻዊ ደሳለኝ መርሻ"ኑድኒያ" የጉራጊኛ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት ይለቀቃል 

የድምጻዊ ደሳለኝ መርሻ "ኑድኒያ "የተሰኘ 7ኛ የጉራጊኛ የሙዚቃ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ይደርሳል።

ይህ የጉራጊኛ አልበም 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስለፍቅር፣ ስለሃገር፣ ስለማህበራዊ ህይወት የሚዳስስ ሁለገብ አልበም ነው ተብሏል።

አልበሙ ላይ በርካታ ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በግጥም እና ዜማ ራሱ ደሳለኝ መርሻ፣ ፈለቀ ማሩ፣ ናቲ ኃይሌ፣ ዘነበ መርሃባ፣ ሀብታሙ አብርሃም፣ አለማየሁ ወልዴ የተሳተፉ ሲሆን በቅንብር አሌክስ ይለፍ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፣ ሰማገኘው ሳሙኤል፣ ፋኑ ጊዳቦ፣ ቢኒአነዴ ርሆቦት (ሮባ) የተሳተፉ ሲሆን በሚክሲንግ ሰለሞን ሃ/ማርያም፣ ፍሬዘር ታዬ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፣ ቢኒአንዴ ተሳትፈዋል፡፡ በማስተሪንግ ሰለሞን ሃ/ማርያም በአልበሙ ተሳትፏል።

"ኑድኒያ" አልበም ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በአርቲስቱ ዩቲዩብ ቻናልና በሁሉም ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያ የሚገኝ ሲሆን ሲዲውን ኪነት ኢንተርቴይመንት አሳትሞ ያከፋፍለዋል፡፡

አርቲስት ደሳለኝ መርሻ አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ በትክክል የተመዘገበ 3.8 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ዛሬ በማርዮት ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጿል።

አርቲስት ደሳለኝ መርሻ በሙዚቃዎቹ የጉራጌ እሴቶችን፤ ታሪክ፤ ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና ማሕበራዊ ሕይወትን በተባ ኪናዊ ለዛ በመሰነድ እና በማስተዋወቅ የራሱን አሻራ አኑሯል፡፡

ባለፉት 20 አመታት ሙዚቃን ሕይወቱ በማድረግ ለበርካታ ድምፃውያንም ግጥም እና ዜማዎችን የሰጠው ደሳለኝ መርሻ የመጀመርያ አልበሙ ያሳተመው አዲስ አበባ ውስጥ የታክሲ ሹፌር እየሰራ ባለበት ወቅት ነበር።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
አፍሮ ኤዥያ ዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ "ድልድዮችን መገንባት ህይወትን ማዳን" በሚል መሪቃል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።

ኤፍ ዚ ማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር አፍሮ ኤዥያ ዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እያካሄደ ይገኛል።

ይህ አለም ዓቀፍ የጤና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከዛሬ ግንቦት 09 ቀን እስከ ግንቦት 11 2016 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህም ኤክስፖ ላይ ከ4 መቶ በላይ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ የጤና ተቋማት እንደሚሳተፉ የተገለጸ ሲሆን ማህበረሰቡ እየመጣ ሊጎበኘውና ሊጠቀምበት እንደሚገባ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የተለያዩ መጻሕፍትን በስስ ቅጂ( Soft Copy) ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ይህንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀላሉ።

https://t.me/kooblife

https://t.me/kooblife

https://t.me/kooblife

Ads

እናመሰግናለን መልካም ቀን !