በ፳፻፲፪ የምህረት ዓመት በብዙ ውጥንቅጥ ውስጥ ብናልፍም የመንግስቱን ዕሴቶች ለመኖር ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩን! ጥያቄው ምን ያህል እነዚህን አጋጣሚዎች ተጠቅመንባቸዋል ነው? የአዲስ ዓመት መባቻው የማሰላሰያ ጊዜ እንዲሆንልን ጸሎታችን ነው።
፳፻፲፫ የምህረት ዓመት በግል እንደ ክርስቲያን፤ በጋራ እንደ አማኞች ስብስብ መንግስቱን የምናሰፋበት፣ ቃሉን የምንታዘዝበት እና ጎረቤቶቻችንን የምንወድበት ዓመት እንዲሆንልን ጸሎታችን እና ልመናችን ነው!
EvaSUE |ኢቫሱ
#EvaSUE

IFES World Student Day · Pray for students on Friday 16 October 2020
https://ifesworld.org/en/wsd/
https://ifesworld.org/en/wsd/
IFES
IFES · Pray for students on Friday 20 October 2023
Currently people will be praying on this year’s World Student Day. Go here to add yourself or your prayer group to the map below. Will you join us
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታዩን ብለዋል ፦
- በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በየደረጃው ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የሚያስችል #ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው።
⇛ በቅርቡ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በየተራ ተማሪዎቻቸውን ይቀበላሉ።
⇛ በሀገሪቱ ሁሉም ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ወደዩኒቨርሲቲ ለማምራት #ዝግጅት ማድረግ አለባቸው።
⇛ በ44 ዩኒቨርሲቲዎች በተደረገ ግምገማ አብዛኛዎቹ ኮሮና ቫይረስን በመከላከል የመማር ማስተማሩን ሂደት ማከናወን በሚችሉበት ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
⇛ የቀሩ ጥቂት ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ሳምንት ዝግጅታቸውን እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
⇛ የጤና ፕሮቶኮል እና የሰላም ሁኔታውን የሚያስጠብቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል።
⇛ በተጨማሪም በአመቱ ከክህሎት እና እውቀት በተጨማሪ የስብእና ግንባታ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን በስርአተ ትምህርቱ ይካተታል። (ኤፍ ቢ ሲ)
----- ----- ----
መረጃው የ@tikvahethiopia ነው።

ጥቅምት፣ 6 ⇒ ፀሎት
ነገ ጥቅምት 6 [October_16]፣ ዓርብ አለም አቀፋዊ የተማሪዎች የፀሎት ቀን ነው።
በዓለማችን በወንጌላውያን አማኞች መሰፋትና መበርታት ታሪክ ውስጥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃን ትልቁን ድርሻ እንደሚወስዱ የታወቀ ነው፡፡
ለምሣሌ፣ በአሜሪካ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በተነሳው "Student Volunteer Mission for Foreign" በተነሳው በአንድ ወቅት የሰላሣ ሰባት የኮሌጅ ተማሪዎች፣ ወንጌል ወደ አልደረሳቸው ሀገራት ለመሄድ እና እድሜአቸውን በሄዱበት ለማሳለፍ ፍቃደኛ ሆነው ቃል ገብተው ነበር፡፡ ወደ ብዙ ሃገሮች ወንጌልን የማድረስ ሀላፊነትም ወስደዋል፡፡
የያኔው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ተማሪዎች እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት የሚሆኑበት እና ወንጌልን ለሌሎች ሃገሮች ለመውስድ የሚታጠቁበት ቦታ ተደርገው ይታሰቡ ነበር፡፡ ይህም የሆነው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሚገኙ የክርስቲያን ተማሪዎች ህብረቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና የተማሪዎች እውነተኛ ህብረት የተነሳ ነው፡፡
በእኛም አህጉር፣ አፍሪካ፣ ወንጌልን በ19ኛው ክፍለ ዘመን ይዘው ከመጡት ትልቁን ቦታ የሚወስደው SIM (Sudan Interior Mission) የተቋቋመው በአንድ የ23 ዓመት የኮሌጅ ምሩቅ፣ ዎልተር ጎዋን፣ የኮሌጅ ጓደኛው ቶማስ ኬንት እና በዎልተር እናት ተጋባዥ በሆነው የ21 ዓመቱ ሮውላንድ ቢንጋም ነበር፡፡ ወንጌልን የማድረስ እንቅስቃሴው ሃገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች ከ70 በላይ በሆኑ ሀገራት ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥሯል፡፡
በተጨማሪም፣ ድነትን ያገኙ አማኞች እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንዲሆኑ የሚረዱ ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራርያዎች እና ሌሎች መጻሕፍቶችን በአማርኛ ቋንቋ አበርክተዋል፡፡ ለምሳሌ፣ በቡዙዎቻችን ቤተክርስቲያን የመንጠቀማቸው በቲም ፌሎስ እና ስቲቭ ስትራውስ የተጻፉ ማብራርያዎች እና መሰረታዊ የክርስትና ትምህርት መጻሕፍቶች እኔን ጨምሮ ብዙ ክርስቲያኖችን የጠቀሙ እንደሆኑ ግልጽ ነው፡፡
ይኸን ሁሉ ያልኩት፣ በሁለቱ የኮሌጅ ተማሪ ጓደኛሞች ውስጥ እግዚአብሄር በልባቸው ባከበደውና በእነርሱ ታዛዥነት የብዙዎቻችን ቤተሰብ የክርስቶስ ተከታዮች ሆነዋል፡፡ በእኛም ሀገር ከጥቂት ዓስርት ዓመታት በፊት ስደት ሣይበግረው በዩኒቨርሲቲ የክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ውስጥ በተቀጣጠለው የወንጌል እንቅስቃሴ ብዙ ተማሪዎች የክርስቶስ ኢየሱስ ተከታይ መሆን ችለዋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፣ በተመረቁበት ሙያ መንግስት በመደባቸው ከተሞች እና ገጠሮች በአስተማሪነት፣በግብርና ባለሞያነት፣ በሐኪምነት እና በሌሎች ሙያዎች በሄዱቡት ስፍራ ሁሉ ቤተክርስቲያን ተክለዋል። ይህ ተግባር፣ ተማሪዎችን ተጠቅሞ ስላደረገው እግዚአብሄርን የምናመሰግንበት የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው።
የፊታችን ዓርብ ፣ጥቅምት 6 [ኦክቶበር 16] በዓለም አቀፍ ደርጃ በ #IFES [International Fellowship of Evangelical Students] አስተባባሪነት፣ የተማሪዎች የፀሎት ቀን ነው:: ክርስቲያን ተማሪዎች የሆንን እና ሌሎቻችንም በዚህ ቀን ተማሪዎችን እና የዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረቶችን #በፀሎት እንድናስብ #ጥሪ ለማቅረብ ነው።
የሚከተሉት ለፀሎት የሚሆኑ አርዕስቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ፣ መንፈስ ቅዱስ ባሳሰባችሁ አርዕስቶች ላይ መፀለይ ትችላላችሁ።
⇉ እንደ ሀገር በገጠመን የፖለቲካ ቀውስና እሱን ተገን አድርጎ በሚፈጠረው የዘርኝነት ችግር ዩኒቨርሲቲዎች የግጭት መናሃርያ ሲሆኑ ቆይተዋል፡፡ ተማሪዎችም በብዙ ተቸግረዋል፤ ትምህርታቸውን ተረጋግተው ሣይማሩ፣ የፌሎሽፕ ህብረታቸውንም ማድረግ እየተሳናቸው ቆይተዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲ ህብረቶች በተጨማሪ ተማሪዎች ህብረት የሚያደርጉባቸው በአቅራቢያ የሚገኙ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት በብዙ ተቸግረዋል፡፡ በግጭት ወቅት ተማሪዎችን ቤተክርስትያናቸው በማሳደር እና በሌሎች አሰፈላጊ ነገሮች በመተባበር የተቸገሩት ችግር ቀላል አልነበረም፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ዓይነቶቹን ችግሮች እንዲያስወግድልን፣ ተማሪዎች በተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ያለምንም ፍርሃት ትምህርታቸውን እንዲማሩ፤ ህብረታቸውንም እንዲያካሂዱ እግዚአብሄር እንዲረዳን/ እንዲረዳቸው በፀሎታችን እናስባቸው።
⇉ እንደሚታወቀው ዩኒቨርሲቲ ወስጥ ያለው የካምፓስ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት እራሱን የቻለ ቤተክርስቲያን አይደለም፤ ይልቁን ተማሪዎች ግቢ በሚቆዩበት ጊዜ የክርስቶስ እውነተኛ ደቀመዝሙር ለመሆን ቃሉን የሚያጠኑበት፣ የሚማሩበት፣ አብረው የሚጸልዩበት፣ ለሌሎች ወንጌል የሚናገሩበት ሕብረት ነው፡፡ ሕብረቱ፣ በተለይም ወንጌል ካልደረሰባቸ (unreached) አካባቢ ለመጡ ተማሪዎች ወንጌልን በመናገር እነርሱም ወደመጡበት አካባቢ ሲመለሱ ለሕዝባቸው የምስራቹን እንዲናገሩ በማድረግ የእግዚአብሄርን መንግስት የማስፋት ስራን ይሰራል፡፡
ክርስቲያን ተማሪዎች፣ በህብረት ውስጥ የሚገኙትን በረከቶች የሚካፈሉበት ቦታ እንዲሆንላቸው፣ከግቢ ሲወጡ የቤተክርስቲያናቸው የአገልግሎት ተረካቢ እንዲሆኑ፣ በተሰጣቸው ሀላፊነት ለሌሎች በእውነተኛ ህይወታቸውና በውሳኔያቸው ክርስቶስን የሚገልጡ እንዲሆኑ፣ በተመደቡበት ቦታና ሙያ እንደ እግዚአብሄር መንግስት ወኪል እንዲመላለሱ እግዚአብሄር እንዲረዳን / እንዲረዳቸው እንፀልይ።
⇉ በተማሪዎች ህብረት ውስጥ ለሚያገልግሉ የተማሪ መሪዎች እና ተማሪዎችን በማገልገለ የሚድክሙ አገልጋዩችን (EvaSUE Staff's) እግዚአብሄር እንዲረዳቸውና የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ እንዲሞላብን/እንዲሞላባቸው በጸሎታችን እናስባቸው።
⇉ በዘመናት ሁሉ እውነተኛው ወንጌል እንደሚነገር ሁሉ ስሁት የሆነውም አስተምህሮ ከሐዋርያት ጊዜ ጀምሮ ያው ስህተት መልኩን እየቀያየረ ይኖራል፡፡ በዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች በእነዚህ ትምህርቶች ተጠቂ የመሆናቸው አድል ከፍ ያለ ነው፡፡ ስሁት ትምህርቶች ለእግዚአብሄር የሚኖረንን እውነተኛ እውቀት ያጎድፋሉ፤ ከእውነት መንገድም ፈቀቅ ያደርጋሉ (Sound life always Follow Sound Doctrine)፡፡ ሰለዚህ፣ ስሁት ከሆነ አስተምህሮ ተማሪዎች እንዲተርፉ ይልቁን በእውነተኛው ወንጌል ጸንተው በመቆም ሀሰትን እንዲቃወሙ፣ ለእውነተኛው ወንጌል እንደሚገባ እንዲኖሩ እግዚአብሄር እንዲረዳን/ እንዲረዳቸው በጸሎታችን ማሰብ።
⇉ ልክ እንደ እኛው ሀገር በሌሎች ሀገራት የሚገኙትን የከፍተኛ ደረጃ የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረቶች እናስብ፡፡ በተለይም ሰደት በሚበዛባቸው የአረብ ሀገራትና በሌሎች የዓለም ክፍሎች ለሚኖሩ ክርስቲያን ተማሪዎች እንፀልይ። በአካል ባናውቃቸውም በክርስቶስ መንግስት ያሉ ወንድሞችና እህቶቻችን ስለሆኑ በጸሎቶቻችን እናስባቸዋለን።
እግዚአብሔር የዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎችን ይባርክ!! ለሀገራችንም ሰላምን ይስጠን።
በረከት ኢያሱ፣ በኢቫሱየተማሪዎች መማክርት።
ማጣቀሻዎች:—
1) Rowland Bingham, May 1943, " Seven sevens of Years" pg 9&14
2) https://campusministry.org/ from Mobilization Category
3)https://www.sim.org/where From SIM Website.
------------
Join @EvaSUE58

EvaSUE |ኢቫሱ pinned «ጥቅምት፣ 6 ⇒ ፀሎት ነገ ጥቅምት 6 [October_16]፣ ዓርብ አለም አቀፋዊ የተማሪዎች የፀሎት ቀን ነው። በዓለማችን በወንጌላውያን አማኞች መሰፋትና መበርታት ታሪክ ውስጥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃን ትልቁን ድርሻ እንደሚወስዱ የታወቀ ነው፡፡ ለምሣሌ፣ በአሜሪካ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በተነሳው "Student Volunteer Mission for Foreign" በተነሳው በአንድ ወቅት የሰላሣ…»
#UPDATE
ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 እስከ ጥቅምት 30/2013 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ ተመራቂ ተማሪዎችን ብቻ መቀበል እንደሚችሉ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሀዋሳ በተጀመረው የማጠቃላይ መድረክ ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
👉🏿 ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጁነታቸውን በሥራ አመራር ቦርድ ገምግመው ከጥቅምት 23/2013 በፊት ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቅ አለባቸው፡፡
👉🏿 ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጁነታቸው ሳይረጋገጥ ጥሪ የሚያቀርብ ዩኒቨርሲቲ አይኖርም፡፡
በተካሄደው ግምገማ መሰረት ቢጫ እንዲሁም ቀይ የተሰጣቸው ዩኒቨርሲቲዎች በአስቸኳይ ማስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች አስተካክለው ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
👉🏿 የዩኒቨርስቲዎችን ጥሪ በሚመለከት መርኃ ግብሩ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡
👉🏿 የትራንስፖርት አቅርቦትን በተመለከትም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ (MoSHE) የማመቻቸት ሥራ የሚሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
▪️መረጃው የ @tikvahethiopia ነው።
---- ---- ---- -----
@EvaSUE58
#WolaitaSodoUniversity
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች ብቻ የምዝገባ (Registration) ጊዜ ከጥቅምት 23-24/2013 ዓ.ም ሆኖ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን (Day-One-Class-One) ደግሞ ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳሬክቶሬት አሳውቋል፡፡
👉🏿 መረጃው የ @tikvahethmagazine ነው።
------
👉🏿 @EvaSUE58

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎቹን ጠርቷል!
በ2012ዓ.ም በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ለነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ብቻ ዩኒቨርሲቲው የምዝገባ ቀን ከጥቅምት 25- 26/2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሚሻሻል ወይም የሚቀየር ነገር ካለ ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል፡፡
መረጃው የ @tikvahethmagazine ነው።
------ ---- -------

የመጀመሪያ ዙር የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ !
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የሚቀበሉትን የቅበላ መርሃ ግብር አውጥቷል።
በዚህም መሰረት፦
👉🏿 ከጥቅምት 23-24
አዲስ አበባ፣ አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ሐዋሳ፣ ቡሌ ሆራ፣ መቐሌ፣ ራያ፣ ወሎ፣ መቅደላ አምባ፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች፤
👉🏿 ከጥቅምት 25-26
አርሲ፣ ኮተቤ፣ ሰላሌ፣ ደብረ ብርሃን፣ ዲላ፣ መደወላቡ፣ አርባምንጭ፣ ዋቻሞ፣ ጂንካ፣ አምቦ ዩኒቨርሲቲዎች፤
👉🏿 ከጥቅምት 25-27
አክሱም፣ አዲግራት፣ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች፤
👉🏿 ከጥቅምት 27-28
ጅማ፣ ወልቂጤ፣ ቦንጋ፣ ሐረማያ፣ ኦዳ ቡልቱም፣ ቀብሪ ደሐር፣ ወላይታ ሶዶ፣ ወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች፤
👉🏿 ከጥቅምት 27-29
ባህርዳር፣ ደባርቅ፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲዎች፤
👉🏿 ከጥቅምት 28-30
ጎንደር፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች፤
👉🏿 ከጥቅምት 29-30
ሚዛን ቴፒ፣ መቱ፣ ጋምቤላ፣ ድሬዳዋ፣ ጅጅጋ፣ ወለጋ፣ ደምቢዶሎ፣ አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ይቀበላሉ ተብሏል።
----- ----- ----- -----

Christianity is a God-given, Bible-based, Christ-centered #worldview that gives us a coherent and comprehensive view of reality. This worldview begins with the infinite, personal, truine God who is there and is not silent, who was living in love before anyone or anything else ever existed. This loving God has revealed himself in the world that he made, in the inspired Word of the Bible, and in the incarnate Word of his Son. All meaning and purpose -including our own meaning and purpose are defined in relationship to him.
Thus the #Christian_worldview is not merely a set of propositions but a perspective on life that flows out of our friendship with a personal God, whose love writes our story.
-------
Excerpt from Philip Graham Ryken, Christian worldview: A Student's Guide, Ed.Davids Dockery, Wheaton IL: Crossway,2013.
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#በጣም_አስቸኳይ
ጥሪ የተደረገላችሁ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች አሁን ካለው ሀገራዊ ሁኔታ አንፃር ለደህንነታችሁ ባላችሁበት እንድትቆዩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ለወደፊት የመግቢያ ቀናችሁ በሚወጣ ተለዋጭ ማስታወቂያ ይገለፃል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE (Bereket Gudisa)

#MoSHE
በወቅታዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎች ወደ የግቢቸው የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያቆሙና ተለዋጭ ጥሪ እስኪደርሳቸው በየቤታቸው እንዲቆዩ እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች ስብሰባ ላይ ሲሆኑ ጥሪዎችን በጊዜያዊነት የሚቆሙበትን ውሳኔ ይፋ እንደሚያደርጉ አሐዱ ቴሌቪዥን ከሚኒስቴሩ ኃላፊዎች መስማቱን ዘግቧል፡፡
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot

#ለዩኒቨርሲቲ_ተማሪዎች
ከኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት :
በሀገሪቱ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ ለጊዜዉ መግታት አስፈልጓል፡፡
በዚሁ መሰረት:-
1. እስካሁን ዩኒቨርሲቲወቻችሁ ላይ የደረሳችሁ ተማሪዎች በግቢያችሁ እንድትቆዩ እና በየግቢያችሁ የሚሰጣችሁን ማሳሰቢያ እየተከታተላችሁ እንድትንቀሳቀሱ ፤ አካባቢያችሁ ያለ የትኛውም የተለየ ጉዳይ ለተቋሞቻችሁ ሃላፊዎች እንድታሳውቁ ፤
2. እስካሁን ከወላጆቻችሁ አካባቢ ያልተነሳችሁ በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ ከወላጆቻችሁ ጋር እንድትቆዩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም
@tikvahethiopia