ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)
38.7K subscribers
3.58K photos
197 videos
7 files
4.01K links
Ethiopian Reporter (ሪፖርተር) በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሴንተር በሳምንት ሁለቴ እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ ነው፡፡ ጋዜጣው ለነጻ ፕሬስ፣ ለነጻ ሐሳብናና ለነጻ መንፈስ መስፈን ይተጋል፡፡ Facebook: https://www.facebook.com/EThReporter Twitter: @EthioReporter LinkedIn: linkedin.com/in/ሪፖርተር-ሪፖርተር-123415146
Download Telegram
#ማስታወቂያ

ከሕብረት ባንክ - ይቀበሉ!

ለበዓል ከተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚላክልዎትን ገንዘብ ከሕብረት ባንክ ይቀበሉ!

ከባንኩ ጋር ከሚሰሩ አለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች ማለትም ዌስተርን ዪኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስፋስት፣ ሪያ ፣ዳሃብሺል እና ዩፔሲ በስዊፍት ኮድ - UNTDETAA አማካኝነት ይቀበሉ፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡

🌐 ትክክለኛውን የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡፡

Telegram | Facebook | Instagram | LinkedIn | X | YouTube | Website

#Remittances #MoneyTrasnfer #HibretBank #Swift #SwiftCode #Bank
የሁለቱ ኢትዮጵያዊያን የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ውይይት

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ.ኤም.ኤፍ. (IMF) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ጉባዔ ባለፈው ሳምንት ተካሂዷል። ከዚህ ስብሰባ ጎን ለጎንም በዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም አማካይነት የተሰናዳ የማዕከላዊ ባንክ ገዥዎች ውይይትም ተደርጓል።
በዚህ የውይይት መድረክ ላይም ሁለት በተለያዩ ተልዕኮና ኃላፊነት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ልሂቃን ተገናኝተዋል። አቶ አበበ አዕምሮ ሥላሴ እና አቶ ማሞ ምሕረቱ። አቶ አበበ አዕምሮ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአፍሪካ ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ አቶ ማሞ ምሕረቱ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ናቸው።
አቶ ማሞ ምሕረቱ አይኤምኤፍ ባሳናዳው የማዕከላዊ ባንክ ገዥዎች የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሪፎርም ተግባራት ለማስረዳት የተጋበዙ ሲሆን ይህንን መድረክ ለመምራትና ለማወያየት የተሰየሙት ደግሞ አቶ አበበ አዕምሮ ናቸው። 
ውይይቱን የሚመሩት አቶ አበበ አዕምሮ ለ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140623/
የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት አምራችና አቅራቢዎች ለሥራቸው አዳጋች የሆነባቸውን ችግሮች አቀረቡ

በአገር ውስጥ የሚገኙ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት አምራቾችና አቅራቢዎች፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትና የጉምሩክ አሠራር ሥራቸውን አዳጋች እንዳደረገባቸው ቅሬታ አቀረቡ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአገር በቀል የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ግብዓት አቅራቢዎች በተለይም ኬብል፣ ትራንስፎርመር፣ ኮንዳክተርና ሌሎች አምራቾች ጋር ዓርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ውይይት ሲያደርግ ነው ቅሬታቸው የቀረበው፡፡
በውይይቱ አቅራቢዎች፣ አምራቾችና  ማኅበራቶች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከውጭ አገር የሚገቡ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ግብዓቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት በሚደረገው ጥረት፣ አገር ውስጥ በርካታ መሰናክሎች እየገጠሟቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ትራንስፎርመር አምራቾች ማኅበር ፕሬዚዳንትና አድቫንቴጅ ኢንዱስትሪ ፒኤልሲ የተሰኘ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት በላይ በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ትራንስፎትመር ውድ የሆነው ጥሬ ዕቃው ከውጭ አገር ስ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140650/
#ማስታወቂያ

ጂካብ ትራንስፖርት

ለሾፌርም ለተጓዥም ዳጎስ ያለ ጥቅም የሚያስገኝ አገልግሎት ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ጂካብን ይጠቀሙ በትራንስፖርት ዘርፍ እስካሁን ያልነበሩ እና ያልተለመዱ ጥቅሞችን ያግኙ፡፡

ለበለጠ መረጃ፦ በ 📞 8993 ይደውሉ፡፡ አልያም ቦሌ አለምነሽ ፕላዛ 6ተኛ ፎቅ ላይ በመምጣት ተጨማሪ መረጃ ያግኙ፡፡

ጂካብ እየተከፈልዎ ይጓዙ!
https://t.me/GCabreg
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በባንክ ዋስትና ክርክር ለሰበር ችሎት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ብርሃን ባንክ ለአፍሮ ጽዮን ኮንስትራክሽን ኩባንያ የገባውን የ76.2 ሚሊዮን ብር ዋስትና በሚመለከት፣ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ የሕግ ጥሰት እንዳለበት ገልጾ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርቦት የነበረው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ፡፡
አየር መንገዱ ታኅሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ባቀረበው አቤቱታ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ እንደቅደም ተከተላቸው በተለያዩ ጊዜያት በጉዳዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ የሕግ ስህተት እንዳለበት ገልጾ ውሳኔውን በመቃወም፣ ለሰበር ችሎት አቤቱታ አቅርቦ ነበር።
ለሰበር ሰሚ ችሎቱ የቀረበው አቤቱታ እንደሚያስረዳው፣ በአመልካችነት የቀረበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅድመ ሁኔታ የሌለውና በቀረበ ጊዜ የሚከፈል ዋስትና ላይ ተመሥርቶ፣ ብርሃን ባንክ ላይ የ76.26 ሚሊዮን ብር ክስ በተፋጠነ ሥነ ሥርዓት አቅርቧል፡፡ የሥር ፍርድ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140644/
‹‹በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ዋነኛ የሚባሉ የፖለቲካ ኃይሎችን ያካተተ ጊዜያዊ አስተዳደር ያስፈልጋል›› ደጀን መዝገበ (ዶ/ር)፣ የውድብ ናፅናት ትግራይ (ውናት) ሊቀመንበር

ደጀን መዝገበ (ዶ/ር) በ2012 ዓ.ም. ተመሥርቶ ከአራት ዓመታት በኋላ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔ በማካሄድ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሙሉ የፖለቲካ ፓርቲነት ዕውቅና የተሰጠው ውድብ ናፅነት ትግራይ (ውናት) በሚል መጠሪያ የሚታወቀው፣ እንቅስቃሴውን በትግራይ ክልል ውስጥ ያደረገ ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው። የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በፌዴራሊዝምና በመንግሥት አስተዳደር (Federalism and Governance) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ፋኩልቲ ውስጥም በመምህርነት አገልግለዋል። ‎ደጀን (ዶ/ር) የፖለቲካውን ዓለም እንቅስቃሴ በይፋ የተቀላቀሉት የሚመሩት ፓርቲ በተመሠረተበት ተመሳሳይ ዓመት በ2012 ዓ.ም. ሲሆን፣ ፓርቲው ትግራይ ክልልን በሪፈረንደም ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሥርዓት የማስወጣት ዓላማ ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው። ‎ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምሥረታ ጀምሮ በአስተዳደሩ አመራር የሃምሳ ሲደመር ድምፅ ባለ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140620/
ኢትዮ ቴሌኮም ያልተሸጡ ቀሪ አክሲዮኖችን እንደገና ለገበያ እንደሚያቀርብ አስታወቀ

በሳሙኤል አባተ
ኢትዮ ቴሌኮም ያልተሸጡ ቀሪ አክሲዮኖችን እንደገና ለገበያ እንደሚቀርብ አስታወቀ፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የአሥር በመቶ ድርሻ በ121 ቀናት ውስጥ 47,377 ኢትዮጵያውያን 10.7 ሚሊዮን አክሲዮኖችን መግዛታቸውን ገልጿል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ዓርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ 712 ግለሰቦች የ900,000 ብርና ከዚያ በላይ አክሲዮን ገዝተዋል። የአክሲዮን ሽያጩ እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ባሉት 121 ቀናት 47,377 ኢትዮጵያውያን 10.7 ሚሊዮን አክሲዮኖችን መግዛታቸውን፣ ከአክሲዮን ሽያጩ 3.2 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አሠራር መሠረት ግለሰቦች በገዙት መጠን የአክሲዮን ድልድል ይደረጋል ተብሏል። የኢትዮ ቴሌኮምን የአሥር በመቶ ድር...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140633/
ለአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጀ


ፖሊሲው በነዳጅና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል

በሳሙኤል አባተ
ለአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ረቂቅ ፖሊሲ ማዘጋጀቱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ። ከዚህ በፊት ራሱን የቻለ የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ባለመኖሩ፣ አዲስ ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለውይይት ቀርቧል። የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ከድልማግሥት ኢብራሒም ለሪፖርተር እንደነገሩት፣ ረቂቅ የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ተዘጋጅቷል፡፡
እንደ አማካሪው ገለጻ፣ ረቂቅ ፖሊሲው የተዘጋጀው የአገሪቱን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ መነሻ በማድረግ ነው፡፡ ፖሊሲው የኢትዮጵያ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ምን እንደሚመስል፣ ቀጣይ ዕቅዶችንና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ፖሊሲው ነዳጅና ኤሌክትሪክ (ታዳሽ ኃይል) የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀቱን፣ ተሽከርካሪዎች ከውጭ እንዴት እንደሚገቡ፣ ተሽከርካሪዎቹ ማሟላ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140656/
በጀት የተመደበላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ አለመፈጸማቸው በፓርላማ አባላት ጥያቄ አስነሳ 

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ቃል ተገብቶላቸው፣ ታቅደው፣ በጀት ተመድቦላቸው፣  ዲዛይን ወጥቶላቸውና ተጀምረው በተለያዩ የአፈጻጸም ደረጃዎች የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች አለመከናወንና አለመጠናቀቅ ለምን? በሚል በርካታ የፓርላማ አባላት ጥያቄ አቀረቡ፡፡
ጥያቄ የተነሳው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ሲገመግም ነው፡፡
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በሪፖርታቸው፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በከተሞች የተለያየ ደረጃ ያላቸው 4,658 ኪሎ ሜትር መንገዶች ለመገንባት ታቅዶ፣ የ4,869 ኪሎ ሜትር መንገዶች ግንባታ ተከናውኗል ብለዋል፡፡  
የመንገድ ግንባታው 199 ኪሉ ሜትር የጌጠኛ ድንጋይ መንገድ፣ 1,574 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ፣ 2,980 ኪሎ ሜትር የጥርጊያ መንገድና 111 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ መሆናቸውንና አ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140653/
#ማስታወቂያ

ነዳጅዎን በሲቢኢ ብር ፕላስ  በቀላሉ ቀድተው
በሰላም ይጓዙ!
****
የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ተጠቅመው
ከሲቢኢ ብር ሂሳብዎ ወይም ከባንክ ሂሳብዎ ጋር በማገናኘት በቀላሉ የነዳጅ ክፍያዎን መፈፀም ይችላሉ፡፡
****
አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ይጫኑ/ያዘምኑ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች : https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች : https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

#cbe #cbebirr #ethiopia #digitalbanking #banking #business #fuel #payment
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ማስታወቂያ

💫ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ቴምር ሪልስቴት ለበአል ልዩ ቅናሽ ይዘልዎ መቷል!
📍ሳር ቤት
2B +G +21 አፓርትመንት
ባለ 2 እና 3 መኝታ
ካሬ 64 200 ብር ብቻ
10 ፐርሰንት ቅድመ ክፍያ
የ 40 ፐርሰንት ቅናሽ አድርገን ሽያጭ ጀምረናል፡፡
እንዲሁም
📍ፒያሳ  ከምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት 3ኛውንና የመጨረሻውን የንግድ ሱቅ በመሸጥ ላይ እንገኛለን።
2B+G+5 የሆነ
በ3.9ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ
በ1 አመት ተኩል የሚረከቡት
በቂ የመኪና ማቆሚያ ያለው

🔔በተጨማሪም
📍  በአያት አደባባይ ግንባታው ከ80% በላይ የደረሰ ሳይት ጨምሮ
በፒያሳ-ሊሴ እና
በሱማሌ ተራ
አፓርትመንቶችን እስከ 35% በሚደርስ ቅናሽ ይዘንልዎት መተናል

💫 ዋና ዋና መለያዎች
እየኖሩበት የሚከፍሉበት አማራጭ ያላቸው
ከ10% ጀምሮ መክፈል መቻልዎ
በተለያዬ ቦታ የሳይት አማራጭ መኖሩ
በኢትዮጵያ ብር ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ መዋዋል መቻልዎ
👌ከባለ 1- ባለ 3 መኝታ

ለተጨማሪ መረጃ
🤳 09 50 28 56 66/ 09 48 86 37 38
#ማስታወቂያ

ከሕብረት ባንክ - ይቀበሉ!

ለበዓል ከተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚላክልዎትን ገንዘብ ከሕብረት ባንክ ይቀበሉ!

ከባንኩ ጋር ከሚሰሩ አለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች ማለትም ዌስተርን ዪኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስፋስት፣ ሪያ ፣ዳሃብሺል እና ዩፔሲ በስዊፍት ኮድ - UNTDETAA አማካኝነት ይቀበሉ፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡

🌐 ትክክለኛውን የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡፡

Telegram | Facebook | Instagram | LinkedIn | X | YouTube | Website

#Remittances #MoneyTrasnfer #HibretBank #Swift #SwiftCode #Bank
ዘወትር ዕረቡ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ከዓመት በፊት ላነሷቸው አንገብጋቢ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ እንዲሰጡ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ሠራተኞች አንገብጋቢ ለተባሉ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በድጋሚ እንዲያነጋግሯቸው የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ጠየቀ፡፡ ከሠራተኛው ደመወዝ በቀጥታ ተቆርጦ ለአደጋ ሥጋት መከላከል ገቢ ይደረግ በሚል የሚያስገድደው ረቂቅ አዋጅ ሠራተኛው ላይ ተፈጻሚ እንዳይሆን ጥያቄ አቀረበ፡፡
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ነገ የሚከበረውን የሜይዴይን በዓል አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ በተከታታይ መንግሥት ምላሽ እንዲሰጥባቸው የቀረቡ ዋና ዋና ጥያቄዎች እስካሁን ምላሽ ባለማግኘታቸው ሠራተኞች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው፡፡
ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ አወንታዊ ምላሽ ይሰጥባቸዋል ተብሎ ቃል ተገብቶባቸው የነበሩ ጥያቄዎች እስካሁን ምላሽ አለማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ፕሬ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140732/
የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች በሙሉ የሒሳብ መዝገብ ካላቀረቡ እንዳይስተናገዱ ተወሰነ


በዘጠኝ ወራት 160.9 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገልጿል

ከመጪው በጀት ዓመት ጀምሮ የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች በሙሉ የሒሳብ መዝገብ ካላቀረቡ እንዳይስተናገዱ የሚያስገድድ ውሳኔ መተላለፉን፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገለጸ።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሁሉም የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች ሥርዓት ያለው የሒሳብ መዝገብ ካላቀረቡ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ አይስተናገዱም፡፡
የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋይ ነጋዴዎች በታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 መሠረት የሒሳብ መዝገብ እንዲይዙ በሕግ እንደሚገደዱ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት የወጪ ገቢ ሰነዳቸውን ባግባቡ አዘጋጅተው የሚስተናገዱ እንዳሉም ጠቁመዋል። ሆኖም በደረሰኝ ግብይት ካለመፈጸምና በሌሎች ምክንያቶች የሒሳብ መዝገብ ይዞ ለመገኘት ችግር አለ ያሉት አቶ ሰውነት፣ ‹‹አብዛኞቹ በተለይ የደረጃ ለ ግብር ከፋዮች በግም...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140722/
አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የፋይናንስና የቦታ አቅርቦት ተግዳሮት እንደሆነባቸው ተነገረ

አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የፋይናንስና የቦታ አቅርቦት ተግዳሮት እንደሆነባቸው፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታወቀ፡፡
ኢንዱስትሪዎቹ ለባንክ የብድር ዋስትና ማስያዣ የአቅም ውስንነት ስላለባቸው፣ በቂ የፋይናንስ አቅርቦት ስለሚያገኙ የመሥራት ፍላጎት እያላቸው በገንዘብ ዕጦት ወደ ሥራ መግባት ያቃተቸው መኖራቸውን፣ የኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ ዮሱፍ፣ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
የመሥሪያ ቦታ ዕጦት ሌላኛው ተግዳሮት መሆኑን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ በማስፈጸም አቅም ውስንነትና ተቀናጅቶ መሥራት ባለመቻል ምክንያት የተስተጓጎሉ ሥራዎች ብዙ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ኢንዱስትሪዎቹ በመቋቋም ላይ ሳሉ ብቻ ሳይሆን ከተቋቋሙ በኋላም በርካታ ፈተናዎች እየገጠሟቸው መሆኑን ጠቅሰው፣ ለአብነትም የመነሻ ካፒ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140715/
የሕግ አወጣጥ የጥራት ጥያቄ የተነሳበት የእንስሳት ጤና ደኅንንት አዋጅ ፀደቀ

በምክር ቤት አባላት የሕግ አወጣጥ ጥያቄ የተነሳበትን የእንስሳት ጤና ደኅንነት አዋጅ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ሚያዝያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ባካሄደው ስበሰባ በሙሉ ድምፅ ፀደቀ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ቀድሞ ቀርቦ ከነበረው ረቂቅ በሰፊው ልዩነት ተሻሽሎ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ከጅምሩ እንዴት ተገምግሞ ሊቀርብ ቻለ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ወደ ፓርላማ የተላከ ሕግ በዚህ መጠን በሰፊ ልዩነት የሚቀየር ከሆነ፣ ቀድሞ ሲመጣ የራሱ የሆነ ችግር ያለበት በመሆኑ መታየት አለበት በማለትም ትኩረት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከ93 በላይ ማሻሻያዎችን ይዞ የመጣው ረቂቅ አዋጁ፣ ‹‹የዕርድ እንስሳት›› የሚለውን ትርጉም እንደ ኢትዮጵያ ባህልና ልማድ ወይም የውጭ ሥጋ ተቀባይ አገሮች ፍላጎት፣ ለሰው ልጅ ምግብነት የሚውሉ አጥቢ እንስሳት፣ ዓሳ፣ ዶሮና ሌሎች አዕዋፋትን እንደሚያካትት ደንግጓል፡፡
ከዋናው ሥጋ በስተቀር ያሉ የእንስሳት ዕርድ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140719/
የሰላም ሚኒስቴር ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዳይመለሱ የፖለቲካ ማስያዣ ሆነዋል አለ


ከሁለት ሚሊዮን ተፈናቃዮች በዘጠኝ ወራት የተመለሱት 380 ሺሕ ናቸው ተብሏል

ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ወደ ቀድሞ ሕይወታቸውና መኖሪያቸው እንዳይመለሱ፣ የፖለቲካ ማስያዣና የኢኮኖሚ መጠቀሚያ ተደርገዋል ሲል የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. የተቋማቸውን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርቡ ነው ይህንን የተናገሩት፡፡
የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ ባቀረቡት ሪፖርት፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ የፈረሰባቸውን ቤት ገንብቶ ወይም ትራንስፖርት አመቻችቶ ማጓጓዝ ቢሆን ኖሮ ያን ያህል  እንደማያስቸግር፣ ነገር ግን እነሱን መያዣ አድርጎ የመጫወት ፖለቲካ እንዳለ ገልጸዋል፡፡
ለአብነት በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከተደረገ በኋላ፣ በትግራይ ክል...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140740/
#ማስታወቂያ

Baankii Siinqee
Tokkummaan gara milkaa’inaatti!

ሲንቄ ባንክ
በአንድነት ወደ ስኬት!

#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ
#EMPOWERED_TOGETHER
መንግሥት ለፕሬስ ነፃነት መከበር ኃላፊነቱን ይወጣ!

የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም. (ሜይ 3 ቀን 2025) ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ይዘከራል፡፡ የፕሬስ ነፃነት ቀን በኢትዮጵያ መከበር ከጀመረ ከሦስት አሠርት ዓመታት በላይ ቢሆኑትም፣ አፍን ሞልቶ ነፃነቱ በሚፈለገው ደረጃ ላይ ነው ከማለት ይልቅ በበርካታ ችግሮች መከበቡ ነው የሚታወቀው፡፡ ቀደም ሲል የነበሩ ማዋከቦች፣ ማስፈራራቶች፣ እስሮችና የመረጃ ክልከላ ሊቀረፉ ያልቻሉ ችግሮች እንደሆኑ ማስተባበል አይቻልም፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፕሬስ ነፃነት ቀን ሲደነገግ ታሳቢ የተደረገው፣ መንግሥታት ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን አክብረው እንዲያስከብሩ ነው፡፡ ይህም መነሻ የሚያደርገው እ.ኤ.አ. በ1948 በተመድ የተወሰነውንና አገሮች ተቀብለው የሕጎቻቸው አካል ያደረጉትን ሁለንተናዊ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ (Universal Declaration of Human Rights) ነው፡፡ ኢትዮጵያም የእዚህ ድንጋ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140729/