ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)
38.6K subscribers
3.55K photos
192 videos
7 files
3.98K links
Ethiopian Reporter (ሪፖርተር) በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሴንተር በሳምንት ሁለቴ እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ ነው፡፡ ጋዜጣው ለነጻ ፕሬስ፣ ለነጻ ሐሳብናና ለነጻ መንፈስ መስፈን ይተጋል፡፡ Facebook: https://www.facebook.com/EThReporter Twitter: @EthioReporter LinkedIn: linkedin.com/in/ሪፖርተር-ሪፖርተር-123415146
Download Telegram
የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው የዶላር ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲፈቀድላቸው ጠየቁ


ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ፖሊሲው አይፈቅድም ብሏል

በሳሙአል አባተ
ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሥራ የጀመሩ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ ማውጣት በጀመረው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ እንዲፈቀድላቸው ጠየቁ።
ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝተው የውጭ ምንዛሪ ግብይት በማካሄድ ላይ የሚገኙ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች፣ ብሔራዊ ባንክ ማካሄድ በጀመረው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ከሰጣቸው 12 የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች አንዱ የሆነው ዮጋ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ የቅርንጫፍና የማርኬቲንግ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፋሲል ዓለሙ፣ ሥራ ከጀመሩ ስድስተኛ ወራቸውን እንደያዙ ገልጸው፣ ካለፉት አራት ሳምንታት ወዲህ በውጭ ምንዛሪ ገበያው ውስጥ የተወሰነ መቀዛቀዝ እየታየ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተለይ የውጭ ምንዛሪ የሚሸጡ ሰዎች ቁጥር እ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140456/
የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ረቂቅ ሕግ አለመፅደቅ ጥቃቶች እንዲስፋፉ ማድረጉን ኢሰመኮ ገለጸ

የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ረቂቅ ሕግ በፍጥነት አለመፅደቅ ጥቃቶች እንዲስፋፉ ምክንያት ሆኗል ሲል፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን የገለጸው፣ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት መብቶች አያያዝን በተመለከተ በ2016 ዓ.ም. ለሕዝብ ይፋ ባደረገው የክትትል ሪፖርት የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አተገባበር ላይ ባከናወነው ምልከታ፣ የተለዩ ግኝቶች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት ባካሄደበት ወቅት መሆኑን፣ የሰብዓዊ መብት ተቋሙ ሐሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ያወጣው የክትትል ግኝት መረጃ ያሳያል።
የኢሰመኮ የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረ ሐዋርያ፣ አብዛኛው የጥቃት ወንጀሎች ሪፖርት እንደማይደረጉ ጠቁመው፣ ፍትሕ ፍለጋ ሪፖርት ያደረጉ ውስን የጥቃት ተጎጂዎች በወንጀል ፍትሕ ሥርዓ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140468/
ጥራታቸው አጠራጣሪ የሆኑ የግብርና መሣሪያዎችን ማገድ የሚያስችል ረቂቅ መመርያ ወጣ

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የብቃት ማረጋገጫን በተመለከተ ያወጣው ረቂቅ መመርያ፣ ማንኛውም የግብርና መሣሪያ ጥራትና የደ
ኅንነት ጉድለትን አስመልክቶ አጠራጣሪ ሁኔታ ከተገኘ ወይም በፍተሻ ወቅት ችግር መኖሩ ሲረጋገጥ ማገድ የሚያስችል ድንጋጌ ይዞ ቀረበ፡፡
‹‹የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥ ቁጥጥር ረቂቅ መመርያ›› የሚል ርዕስ የተሰጠው ረቂቁ ከያዛቸው ዋና ዋና ድንጋጌዎች መካከል፣ የግብር መሣሪያ ስለማገድ፣ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ስለመመለስ፣ የግብርና ሜካናይዜሽን የኪራይ አገልግሎትና ግብርና መሣሪያ ጥገና የሚሰጡ ግለሰቦች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን የብቃት ማረጋገጫ መሥፈርቶች ይገኙበታል፡፡
በረቂቅ መመርያው ክፍል 6 አንቀጽ 19 ሥር የግብርና መሣሪያ ስለማገድ በሚል የቀረበው ድንጋጌ፣ ባለሥልጣኑ ከመሣሪያ ጥራትና ጉድለትን በተያያዘ ችግር መኖሩን ሲያረጋግጥ ማገድ እንደሚችል ሲገልጽ፣ በዚህ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140454/
ሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ የሚገኘውና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የፈሰሰበት የመሮጫ መም እየተበላሸ መሆኑ ተገለጸ

ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ በሞጆ ደረቅ ወደብ አንድ ዓመት ከአራት ወራት መቆየቱ የሚነገርለት የመሮጫ መም (ትራክ)፣ በጊዜው ለታለመለት ጥቅም ባለመዋሉ ምክንያት በቆይታ ብዛት እየተበላሸ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ለአዲስ አበባ ስታዲየም ተብሎ የተገዛው ይህ የመሮጫ መም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ለሚፈለገው አገልግሎት እንዳይውል ምክንያት ተብሎ እየተጠቀሰ የሚገኘው የስታዲየሙ የሳር ተከላ ሥራ በታቀደለት ጊዜና ወቅት ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ ነው፡፡
አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲየም ከአራት ዓመታት በፊት የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ‹‹ዝቅተኛውን መሥፈርት አያሟልም›› በሚል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች ማናቸውንም አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን እንዳያስተናግድ ማገዱ ይታወሳል፡፡ መንግሥት የደረጃ ማሻሻያ ግንባታው የዓለም አቀዱ የዕገዳ ውሳኔ ዕውን በሆነ ማግሥት ቢጀምረውም፣ እስካሁን ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ ስታዲየሙ ከአገልግሎት ውጪ እንደሆነ ይገኛል፡፡
ዕ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140408/
#ማስታወቂያ

ገደብ የለውም!
****
በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ
የአየር ጉዞ ትኬት ለመግዛት
የክፍያ ገደብ የለውም!
#cbe #digitalbanking #mobilebanking #banking #ethiopia #ethiopian #airticket
****
የሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን ለማግኘት፡
• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.mobilebanking
• IOS: https://apps.apple.com/us/app/cbe-mobile-banking-new/id1534203410#?platform=iphone
#ማስታወቂያ

ከሕብረት ባንክ - ይቀበሉ!

ለበዓል ከተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚላክልዎትን ገንዘብ ከሕብረት ባንክ ይቀበሉ!

ከባንኩ ጋር ከሚሰሩ አለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች ማለትም ዌስተርን ዪኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስፋስት፣ ሪያ ፣ዳሃብሺል እና ዩፔሲ በስዊፍት ኮድ - UNTDETAA አማካኝነት ይቀበሉ፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡

🌐 ትክክለኛውን የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡፡

Telegram | Facebook | Instagram | LinkedIn | X | YouTube | Website

#Remittances #MoneyTrasnfer #HibretBank #Swift #SwiftCode #Bank
የሪፖርተር ስራዎችን በእነዚህ አማራጮች ማግኘት ይችላሉ፦
💯 Website: www.EthiopianReporterJobs.com
💯 Facebook: http://bit.ly/2mPD7EG
💯 Telegram: https://bit.ly/3exwhdn
💯 Linkedin: https://bit.ly/2XJzm45
💯 Twitter: https://bit.ly/3cuJTnF
💯 Instagram: https://bit.ly/3fCE5j1
ይጎብኙን፤ ይከተሉን፤ ላይክ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን።
ዘወትር ዕረቡ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
አይሻሻል የሚል ሙግት የገጠመው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ማሻሻያ መፅደቅ አንድምታ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ አዋጁ ቢሻሻል፣ ሕጉ ቢከለስና ቢለወጥ የሚል ጥያቄ ተደጋግሞ ሲሰማ እንጂ አዋጁ ባይሻሻል ይሻላል የሚል ሙግት መስማት ብዙም አልተለመደም፡፡ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. በስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለውይይት ቀርቦ በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ የፀደቀው የተሻሻለው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1374/2017 ግን፣ ባልተለመደ ሁኔታ በባለድርሻ አካላት ‹‹ባይሻሻል ይበጃል›› የሚል ተቃውሞ ሲቀርብበት ነው የታየው፡፡

ማሻሻያ አዋጁ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ነበር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ቀርቦ ለዝርዝር ዕይታ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመራው፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ኅዳር ወር ላይ የአስረጂዎች መድረክ በማዘጋጀትና ለሕዝብ ውይይት በማቅረብ በአዋጁ ላይ ምክክር አድርጎ ነበር፡፡ ለጥቂት ዓመታት ብቻ በሥራ ላይ በቆየውን...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140582/
የበዓላት መተሳሰብና መደጋገፍ በአዘቦቱም ይቀጥል!

ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳን ፆም አብቅቶ በኢድ አል ፈጥር፣ እንዲሁም ሕዝበ ክርስቲያኑ የሁዳዴ ፆም ተጠናቆ በትንሳዔ በዓል በማኅበረሰቡ ውስጥ በስፋት ሲስተዋሉ የነበሩ የመተሳሰብና የመደጋገፍ መልካም እሴቶች ተስፋ ሰጪ ነበሩ፡፡ የሁለቱ ታላላቅ እምነቶች ምዕመናን ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው አዛውንቶችን፣ ወላጅ አልባ ሕፃናትን፣ አቅመ ደካሞችንና ኑሮ የከበዳቸው ወገኖችን ለመደገፍ ያሳዩት ርብርብ አስደሳች ነበር፡፡ በመንግሥት፣ በግብረ ሰናይ ማኅበራትና ሰብዓዊነት በሚሰማቸው ግለሰቦች ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች ለተደረገላቸው ዕገዛ ምሥጋና ሲያቀርቡ ሁሉም ሊባል በሚችል ሁኔታ ለአገር ሰላም መሆን ምኞታቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል፡፡ ሰጪና ተቀባይ በእንዲህ ዓይነቱ አስደሳች ስሜት ውስጥ ሆነው ለአገር ሰላምና መረጋጋት የሚረዳ ሐሳብ የተንፀባረቀበት ዓውድ ሲፈጥሩ፣ ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ብታልፍም ተስፋ እንደማይቆረጥባት እንደ ማሳያ ይቆጠራል፡፡ ይህ ስሜት ተጠናክሮ ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140507/
ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪውሪቲስ ወደ ኢንቨስትመንት ባንክ የማደግ ዕቅድ እንዳለው አስታወቀ

በያሬድ ንጉሤ
በቅርቡ በሙዓለ ንዋይ ገበያ ሰነድ አከናዋኝነት (Securities Dealer) ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ያገኘው ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪውሪቲስ አክሲዮን ማኅበር፣ ወደ ኢንቨስትመንት ባንክ የማደግ ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡
የባለሥልጣኑ መመርያ በተለይም በሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሰነድ አከናዋኝ ወይም (Securities Dealer) በ25 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ባንክ በማቋቋም መሥራት እንደሚቻል እንደሚፈቅድ የተቋሙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበባው ዘውዴ አስታውሰዋል፡፡
ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪውሪቲስ አክሲዮን ማኅበር ይህንን ዕቅዱን ያስታወቀው ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን ባካሄደው የመጀመሪያው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ላይ፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሴኪውሪቲስ ዲለር (የሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሰነድ አከናዋኝ ፈቃድ) ማግኘቱንም ገልጿል፡፡
ኢትዮ ፊደሊቲ በፋይናንስ ዘርፍ ልምድና...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140574/
የኢትዮጵያን የዋጋ ግሸበት ወደ ነጠላ አኃዝ የማውረድ ትልም ከ2028 በፊት አይሳካም ተባለ


የበጀት ድጋፍ መቀነስ ተግዳሮት ይኖረዋል ተብሏል

የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት በተያዘው እ.ኤ.አ. 2025 ሃያ በመቶ ሆኖ እንደሚቀጥልና ወደ ነጠላ አኃዝ የመውረድ ዕድሉ እ.ኤ.አ. በ2028 ሊሆን እንደሚችል፣ የዓለም የገንዘብ ድርጅትን ጠቅሶ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የልማት ድርጅት አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ የኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የ2025 የሦስት ወራት የኢኮኖሚ ሁኔታ በተመለከተ ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ የውጭ ምንዛሪ ክምችት 3.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱንና ለአንድ ወር ከ18 ቀናት ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች ወጪ መሸፈኛ ይሆናል ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ከጎረቤት አገሮች በተለይም ከኬንያ፣ ከታንዛኒያና ከኡጋንዳ ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑን የሚያብራራው ሪፖርቱ፣ በብሔራዊ ባንክ የባንኮች የብድር ጣሪያ ከተወነ በኋላ ወደ ኢኮኖሚው እየገባ ያለው ብድር እየቀነሰ መሆኑን ገልጿል፡፡ ለአብነት እ.ኤ.አ. በ2023 በየወ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140515/
‹‹አሥር ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ረሃብ ተጋርጦባቸዋል›› የዓለም የምግብ ፕሮግራም

በአዲስ ጌታቸው
አሥር ሚሊዮን ኢትዮጵያን ረሃብ እንደተጋረጠባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ በመላው ኢትዮጵያ ለከፋ ረሃብ ከተጋለጡት ውስጥ ሦስት ሚሊዮን ያህሉ በግጭትና በአየር ፀባይ መለዋወጥ (Extreme Weather) ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በየመጠለያው ሲረዱ የነበሩ ናቸው ብሏል፡፡
የድርጅቱ ነፍስ የማዳን ተግባራት አቅም በመዋዕለ ንዋይ እጥረት የተነሳ እጅግ መዳከሙን ያወሳው የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ከአሥር ሚሊዮን ረሃብተኞች 3.5 ሚሊዮን ያህሉ እጅግ ተጠቂ ተብለው የተያዙና ዕርዳታ ከእነ አካቴው ሊቋረጥባቸው እንደሚችል አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ ከፈረሰ በኋላ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርዳታ የማድረስ አቅሙ በእጅጉ እንደተጎዳ በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140520/
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከማዕድን ኢንቨስትመንት በነፃ አክሲዮን እንዲኖረው የሚያስገድድ ደንብ ሥራ ላይ አዋለ


የክልሉን መሬት ለማዕድን ሥራዎች ክፍት የማድረግ ሥልጣን ለአስተዳደሩ ይሰጣል

ከሦስት ሳምንታት በፊት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆነው በተሾሙት ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደ ተፈርሞ፣ በክልሉ ሥራ ላይ የዋለው የማዕድን አስተዳደርና የተለያዩ የማዕድን ሥራዎች ክፍያና ፈቃድን ለመወሰን የወጣ ደንብ፣ ከማንኛውም ባለፈቃድ አነስተኛና ከፍተኛ ደረጃ የማዕድን ኢንቨስትመንት ሥራ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አምስት በመቶ (5%) የአክሲዮን ድርሻ ያለ ምንም ክፍያ በነፃ መያዝ የሚያስችለውን አስገዳጅ ድንጋጌ ሥራ ላይ አዋለ።
በፕሬዚዳንቱ ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ተፈርሞ የጸደቀውን ደንብ ሪፖርተር የተመለከተው ሲሆን፣ ለክልሉ መሬትና ማዕድን ቢሮ ከተጻፈ ደብዳቤ ጋር ተያይዞ የቀረበው ደንብ፣ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ለአስተዳደሩ ካቢኔ ቀርቦ መፅደቁን የሚገልጽ ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከፈረሙበት ዕለትም ጀምሮ በሥራ ላይ መዋሉን ይገልጻል።
ከዚሁ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140517/
#ማስታወቂያ

Appilikeeshinii Dijiitaal Baankiingii Baankii Siinqee 'Play Store' irraa  buufachuun ammuma galmaa'aa, tajaajila isaa jalqabsisaa.

የሲንቄ ባንክ የዲጅታል ባንኪንግ መተግበሪያን ከplay store በማውረድ አሁኑኑ ይመዝገቡ፣ አገልግሎቱን ያስጀምሩ!

#Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan
#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ
#EMPOWERED_TOGETHER
የፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ቅዳሜ ይፈጸማል


በአዲስ አበባ ዓርብና ቅዳሜ የጸሎት መርሐ ግብር ይካሄዳል

የፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. እንደሚፈጸም የቫቲካን የቅድስት መንበር ፕሬስ ክፍል አስታውቋል፡፡
ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ካቶሊካውያን መሪ የነበሩት ፖፕ ፍራንሲስ ባደረባቸው ሕማም ምክንያት በ88 ዓመታቸው ያረፉት ሚያዝያ 13 ቀን ነበር፡፡
‹‹ክርስቶስ የሚወዳቸውን ታላቅ አባታችንን በትንሣኤው ማግስት ወደ ዘለዓለማዊ ማረፊያው ወስዷቸዋል፤›› በማለት የሐዘን መልዕክት ያስተላለፈችው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡



የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ የፖፑን ዜና ዕረፍት ተከትሎ በሰጡት መግለጫ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የትንሣኤ በዓል መልካም ምኞታቸውንና ለዓለም ሰላም ያላቸውን ፍላጎት በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በመገኘት ለመላው ምዕመናን ማስተላለፋቸውን አስታውሰው፣ ሰኞ ጧት በሮም ሰ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140562/
የሪፖርተር ጋዜጠኛ ታሰረ

የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አበበ ፍቅር ታሰረ፡፡ ጋዜጠኛ አበበ የታሰረው ትናንት ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት አካባቢ ነው፡፡

ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው ከልደታ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎች መረጃ በማሰባሰብ ላይ እያለ ሲሆን፣ የታሰረበት ምክንያት እስካሁን ግልጽ አልሆነም፡፡ ጋዜጠኛ አበበ በዕለቱ በፖሊሶች ተይዞ ከመወሰዱ በስተቀር በወቅቱ ወዴት እንደተወሰደና እንደታሰረ ባለመታወቁ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት በማድረግ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባደረገው ትብብር ጋዜጠኛው በልደታ ክፍል ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጌጃ ሰፈር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ ታውቋል፡፡

ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው እየሠራው ለነበረው ዘገባ ሚዛኑን ለመጠበቅ፣ የክፍለ ከተማውን ኃላፊዎች ለማነጋገር በሥፍራው በተገኘበት ወቅት ነበር፡፡
የጤና ባለሙያዎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ አለመሆኑ ተነገረ

የጤና ባለሙያዎች ያሉባቸው ችግሮች እንዲቀረፉ፣ ኑሯቸው እንዲሻሻልና ፍላጎታቸው ተሟልቶ ኅብረተሰቡን በሚፈለገው ልክ እንዲያገለግሉ ማድረግ ከመንግሥት የሚጠበቅ ኃላፊነት ብቻ አለመሆኑ ተነገረ፡፡
ይህ የተነገረው፣ ድሮጋ ፋርማ የተባለ ድርጅት የጤና ባለሙያዎችን ችግር ያቃልላል ያለውን የብድርና ቁጠባ ተቋም መመሥረቱን ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡
በጤና ሚኒስቴር የሕክምና አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኢሉባቦር ቡኖ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ የጤና ባለሙያዎች ከክፍያ ማነስ የተነሳ አገራቸውን ጥለው እንዳይሄዱና ኅብረተሰቡንም በቅንነት እንዲያገለግሉ የሚያስፈልጓቸው ነገሮች ሊሟሉላቸው ይገባል፡፡ የጤና ባለሙያዎች ፍላጎቶቻቸው እንዲሟሉና ኑሯቸው እንዲሻሻል ማድረግ የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ አለመሆኑንም ገልጸዋል፡፡
‹‹አብዛኛዎቹ የጤና ባለሙያዎች ትምህርታቸውን የተከታተሉት ብዙ ችግርና ውጣ ውረዶችን አልፈው ነው፡፡›› ያሉት ሥራ አስፈ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140512/