ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)
38.6K subscribers
3.54K photos
191 videos
7 files
3.98K links
Ethiopian Reporter (ሪፖርተር) በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሴንተር በሳምንት ሁለቴ እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ ነው፡፡ ጋዜጣው ለነጻ ፕሬስ፣ ለነጻ ሐሳብናና ለነጻ መንፈስ መስፈን ይተጋል፡፡ Facebook: https://www.facebook.com/EThReporter Twitter: @EthioReporter LinkedIn: linkedin.com/in/ሪፖርተር-ሪፖርተር-123415146
Download Telegram
የጤና ሚኒስትሯ ሊያ (ዶ/ር) ከሳዑዲ ዓረቢያ እንዲመለሱ እየተደረጉ ያሉት ስደተኞች ቅድመ ምርመራ ሳይደረግላቸው ተፋፍገው እየተላኩ መሆኑን ገልጸው፣ ቁጥሩን በትክልል ባያስታውሱትም የቫይረሱ ምልክት የታየባቸው ተመላሽ ስደተኞች መኖራቸውን ገልጸዋል።
https://www.ethiopianreporter.com/article/18618
በራሳቸው ወጪ ለ14 ቀናት በሆቴሎች እንዲቆዩ የሚደረጉ በእነዚህ ቀናት ውስጥ የምርመራ ውጤት ካልደረሳቸው፣ ከ14 ቀናት በኋላ ለሚኖረው ቆይታቸው የሚያስፈልገው ወጪ በመንግሥት እንደሚሸፈን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/article/18701
"ነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ" በሚለው መርሁ የሚታወቀው ሪፖርተር ጋዜጣ ዳግም ከሀያ ሁለት አመታት በኋላ ሪፖርተር መጽሔትን ይዞ ብቅ ብሏል።
ሊንኩን በመጫን ይከታተሉን።
Facebook: https://www.facebook.com/ethiopianreportermagazine/
Twitter: (@ethreporter_mag): https://t.co/ewk3dEyiCo
Telegram: http://t.me/ethioreportermagazine
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በህዳሴ ግድብ ላይ ለሚያደርጉት ድርድር በሁለት ሳምንታት ውስጥ ከስምምነት ለመድረስ ተስማሙ
---------------------
የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና የወደፊት አሠራርን በተመለከተ የሚያደርጉትን ድርድር አስመልክቶ በወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የተጠራው ስብሰባ ሦስቱ አገራት በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ከስምምነት እንዲደርሱ አግባባ፡፡
ኢትዮጵያ ከሁለት ሳምንታት በኋላ በዓባይ ወንዝ ላይ የምትገነባውን ግድብ ውኃ ለመሙላት ዕቅድ እንዳላት ይታወቃል፡፡
በሦስቱ አገራት የሚደረገው ድርድር የአፍሪካ ጉዳይ በመሆኑ በአፍሪካውያን መፈታት እንዳለበትና ይኼንንም አገሮቹ ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲያሳውቁ ከውሳኔ የተደረሰ ሲሆን፣ አገሮቹ ከቃላት መካረርና ከአላስፈላጊ መግለጫዎች እንዲቆጠቡ አቅጣጫ ተቀምጦ ልዩ የመሪዎች ስብሰባው መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ግብጽ ጉዳዩ በተባበሩት ድርጅት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እንዲታይ በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በሦስቱ አገሮች የሚደረገው ድርድር ውጤት እያስገኘ ነውና በዚሁ መንገድ መፍትሔ ይፈለግ ስትል በተደጋጋሚ አስታውቃለች፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤትም የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካውያን ይፈታ ሲል ጉዳዩን ሳይመለከተው ቀርቷል፡፡
ሦስቱ አገሮች በሁለት ሳምንታት ውስጥ ከስምምነት እንዲደርሱ የአፍሪካ ሕብረትና የጉባዔው አባላት ድጋፍ እንዲያደርጉም መመሪያ ተላልፏል፡፡
በስብሰባው የጉባዔው አባል የሆኑት የኬኒያ፣ የማሊና የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
‹‹ግብፅ በሶማሌላንድ የጀመረችው እንቅስቃሴ ምንም ይሁን ምን፣ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎቹ የኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች ላይ አሉታዊ ጉዳት እንደማያስከትል ተስፋ እናደርጋለን። ከዚህ ውጪ ከሆነ ሕጋዊነት አይኖረውም፡፡ ከሆነ ግን ሰብዓዊነትንም ሆነ ዓለም አቀፍ የሰላምና የደኅንነት መርህን ይቃረናል፤›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ (አምባሳደር)
https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/19480
የሪፖርተር ጋዜጣ የእሁድ ሐምሌ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. እትም ዋና ዋና ዜናዎች
1. ግብፅ የኢትዮጵያ ጎረቤት በሆነችውና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሕጋዊ ዕውቅና ባላገኘችው ሶማሌላንድ የጦር ሠፈር ለመመሥረት እያደረገች ያለውን ጥረት፣ ኢትዮጵያ በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን አስታወቀች።
2. ከአንድ ወር በፊት በድንገት ከተገደለው የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘውና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) በቅርቡ የተቀላቀው አቶ ጃዋር መሐመድ፣ የታዋቂ ሰዎች አድራሻ ተለይቶ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸውና ንፁኃን እንዲታፈኑ ትዕዛዝ ማስተላለፉን በምርመራው እንዳረጋገጠ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ለፍርድ ቤት ተናገረ፡፡
3. በመካሄድ ላይ ባለው የቴሌኮም ዘርፍ የለውጥ ትግበራ፣ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች እንዳይገቡ መንግሥት እንደወሰነ ታወቀ፡፡
4. በትግራይ ክልል ይካሄዳል የተባለው ምርጫ ተካሂዶ በአሁኑ ወቅት ሥልጣን ላይ የሚገኘው የክልሉ ገዥ ፓርቲ ሕወሓት ሥልጣኑን ለሌላ ፓርቲ ካስረከበ፣ የፌዴራል መንግሥት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ጣልቃ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።
5. የዳኞችን የመኖሪያ ቤት ችግር በተወሰነ ደረጃ ለመቅረፍ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ749 ሚሊዮን ብር ያስገነባቸውን አራት የጋራ መኖሪያ ሕንፃዎች፣ ቅዳሜ ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. አስረከበ፡፡
6. በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 ዓ.ም. በነበረ የአመፅ እንቅስቃሴ በደረሰ የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመት ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው፣ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡
7. የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አክሲዮን ማኅበር የነዳጅ ውጤቶችን ከውጭ ለማስገባት የሚያስችለው በቂ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በማጣቱ፣ ህልውናው አደጋ እንዳዣበበት አስታወቀ፡፡
‹‹ሰላም ለመፍጠር መንግሥት መግባት በማይችልባቸው ቦታዎችና አካባቢዎች በመግባት፣ ከአንድ ሺሕ በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎች ትጥቅ ያስፈታሁ እንጂ ነፍሰ ገዳይ አይደለሁም፤›› አቶ ጃዋር መሐመድ
https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/19479
የሪፖርተር ጋዜጣ የእሁድ ነሀሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. እትም ዋና ዋና ዜናዎች
1. የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መንግሥት የወላይታ ዞን የክልልነት ጥያቄን በንግግርና በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንዲያበጅለት ጥሪ አቀረቡ፡፡
2. መንግሥት ስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ለማዘዋወር የተያዘውን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ሲባል የሁሉም ፋብሪካዎች አጠቃላይ ሀብት ግመታን እንዲያከናውን የተቀጠረው የእንግሊዙ ቡከር ቴት የተባለው ኩባንያ ሥራውን አጠናቆ ለመንግሥት ባቀረበው ሪፖርት መሠረት፣ የፋብሪካዎቹ አጠቃላይ ሀብትና ንብረት 88 ቢሊዮን ብር መገመቱን ሪፖርተር ያገኘው መረጃ አመለከተ።
3. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለረዥም ጊዜ የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆን ያገለገሉትን አቶ ዳውድ ኢብሳን ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ጋር በትብብር ለመሥራት ፈቃደኛ አይደሉም በማለት አገዳቸው፡፡
4. ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው አቶ ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት የተገኘው የሳተላይት መሣሪያ በግለሰብ እጅ መያዝ የሌለበት ከመሆኑም በተጨማሪ ሕገወጥ መሆኑ እንደተረጋገጠ ዓቃቤ ሕግ ተናገረ፡፡
5. ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት በድርድር ለመፍታት ወደ ተቋረጠው ድርድር ለመመለስ መወሰኗ ተገለጸ። ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌትና አስተዳደር ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት በአፍሪካ ኅብረት መሪነት የተጀመረው ድርድር ለሦስት ተከታታይ ጊዜ የተቋረጠ ሲሆን፣ ለድርድሩ መቋረጥም ሱዳንና ግብፅ የተለያዩ ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ ማቅረባቸው ነው።
6. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በአዲስ አደረጃጀትና አወቃቀር ለማሻሻል የሚያስችል ሰፊ ዝግጅት መጀመሩንና ለዚህ ሥራ በጥናትና የምክር ሥራ ለሚያካሂዱ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጨረታ እንደሚወጣ ታወቀ፡፡
7. የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋ፣ ለሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮልና በወ/ሮ ቀለብ ስዩም ላይ ከቆጠራቸው ሰባት ምስክሮች ውስጥ አራቱን በቀዳሚ ምርመራ መዝገብ አስመዘገበ፡፡
አቶ ጃዋር መሐመድ በመታመማቸው ምስክርነት ተቋረጠ
በታምሩ ጽጌ
ዓቃቤ ሕግ አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ ዛሬ ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ሊያሰማ ሦስት ምስክሮችን ያቀረበና ጭብጥ ያስያዘ ቢሆንም አቶ ጃዋር መታመማቸውን በመግለጻቸውና ፍርድ ቤቱም ከሁኔታው ግንዛቤ በመውሰድ ምስክሮቹ ከመሰማታቸው በፊት እንዲቋረጥ አድርጓል።
ፍርድ ቤት የቀረቡት ስምንት ተጠርጣሪዎች ሲሆኑ ስድስቱ በኮረና ቫይረስ መያዛቸው በመረጋገጡ አልቀረቡም።
አቶ ጃዋር በጣም መታመማቸውንና በመንግስት ሐኪሞች ለመታየት ሥጋት ስላለባቸው በግል ሐኪማቸው እንዲታከሙ፣ ባለቤታቸውና ልጃቸው በውጭ አገር መሆናቸውን ገልጸው በቪዲዮ በራሱ ወጪ እንዲያነጋግራቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።
አቶ በቀለም ዓቃቤ ሕግ በቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ያቀረባቸውን ምስክሮች መንግስት በገንዘብ ገዝቶ ያቀረባቸው እንደመሰላቸው ጠቁመው፣ መሰማቱ አላግባብና ሕጉን ያልተከተለ መሆኑን፣ ጠበቆቻቸውን በነጻነት እንዳያነጋግሩ ፌደራል ፖሊስ ካሜራ ገጥሞ ሊያዳምጣቸው በመዘጋጀቱ እንዳላነጋገሯቸው በመናገር ምስክርነቱን እንደሚቃወሙ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ የሁሉንም መቃወሚያ ውድቅ አድርጎ ምስክሮቹ እንዲሰሙ ትዕዛዝ ቢሰጥም አቶ ጃዋር መቀመጥና መቆም እንዳልቻሉ በማመልከታቸው ተቋርጦ ለነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ተቀጥሯል።
አቶ ጃዋር መሐመድ <<በማላውቀው ሐኪም መነካት አልፈልግም>> በማለቱ በግል ሐኪም እንዲታከም ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጠ
- የዓቃቤ ሕግ ምስክርሮችን መሰማት ተጀመረ

በታምሩ ጽጌ

አቶ ጃዋር መሐመድ ከአራት ቀን በፊት ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደታመመ ለፍርድ ቤት በማስረዳት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሳይሰሙ ለዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በተቀጠረው መሠረት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች መሰማት ጀመሩ።
ምስክሮች ከመሰማታቸው በፊት ፍርድ ቤቱ ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. የሰጣቸው ትዕዛዞች መፈጸም አለመፈጸማቸውን አረጋግጧል። በዚህም መሠረት አቶ ጃዋር መንግሥት ሳይሆን በመንግሥት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሥጋት እንደሆኑበትና ለሕይወቱ ስለሚፈራ በግሉ ሐኪም ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን ቢስት እንኳን በመንግሥት ሐኪም መመርመር እንደማይፈልግ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በጣም መታመሙን፣ ምግብ ሲመገብ እንደሚያስመልሰውና አሁን ላይ ደግሞ እያስቀመጠው መሆኑን አስረድቷል።
ዓቃቤ ሕግ በሰጠው አስተያየት ለአቶ ጃዋር ሕክምና እንዲያገኙ ተጠይቀው በግል ሐኪሜ ከልሆነ አልታከምም እንዳሉ ገልጿል። አቅርቦቱ እያለ አልፈልግም እያሉ ወደሌላ ሐኪም ቤት መውሰድ ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም መሆኑን ጠቁሞ በሕግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌም የሚጥስ መሆኑን አክሏል። ወደ ግል ሐኪም ሪፈር ሊደረጉ የሚችሉት ከመንግሥት ሕክምና በላይ የሆነ ሕክምና ሲያስፈልግ ብቻ መሆኑንም ተናግሯል።
ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 21 ድንጋጌ መሠረት አቶ ጃዋር በግል ሐኪም እንዲታዪ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አቶ ለማ ላይ ዕርምጃ መውሰድ ያለበት የኦሮሚያ ብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ነው ወይስ አጠቃላይ የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ? በሚል የሚጠይቁ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የራስ የሆነ ማዕከላዊ ኮሚቴ ካለው እንዲሁም ሌሎቹም እንዲሁ የሚኖራቸው ከሆነ ከቀደመው የኢሕአዴግ አደረጃጀት የሚለየው በምንድነው? በማለት በርካቶች ይጠይቃሉ፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/article/19665
በሪፓርተር ጋዜጣ የሚወጡትን የሥራ ማስታወቂያዎች በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት (SMS) መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 7474 OK ብለው ይላኩ።
ለሥራ ለመመዝገብ በስልኮ OK ብቻ ብለው ወደ 7474 አሁኑኑ መልእክት ይላኩ!
ኢዜማ በአዲስ አበባ ከተማ ከመሬት አጠቃቀምና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማስተላለፍ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች ላይ ያደረገውን ምርመራ ውጤት ይፋ አደርግበታለሁ ያለበት ጋዜጣዊ መግለጫ አርብ ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ·ም. አምስት ሰዓት ላይ በራስ ሆቴል የተዘጋጀ ቢሆንም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ፈቃድ የላችሁም በሚል እንደከለከላቸውና መግለጫው እንደ ቀረ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ተናግረዋል።
በሪፓርተር ጋዜጣ የሚወጡትን የሥራ ማስታወቂያዎች በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት (SMS) መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 7474 OK ብለው ይላኩ።
ለሥራ ለመመዝገብ በስልኮ OK ብቻ ብለው ወደ 7474 አሁኑኑ መልእክት ይላኩ!
በአገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች የሚወስዱት ዕርምጃዎችን የሚገዙ የሕግ ማዕቀፎች እየተዘጋጁ የነበረ ቢሆንም፣ ይኼንን የተመለከተ የሕግ ማዕቀፍ ከረቂቅነት አልፎ ወደ ተግባር አልገባም፡፡ ስለዚህም የተለያዩ የመብት ተሟጋቾች ያለፉ ጊዜያት በፖሊሶች የተወሰዱ ዕርምጃዎችን ተከትለው በሕገ አግባብ የመጡ ተጠያቂነቶች አለመኖር እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/19719
የሪፖርተር ጋዜጣ የእሁድ ነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. እትም ዋና ዋና ዜናዎች
1. መንግሥት የቴሌኮሙዩኒኬሽን ገበያውን ለውጭ ኩባንያዎች ለመክፈት መወሰኑን ተከትሎ ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ውድድር ራሱን እያዘጋጀ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ ኩባንያው የሦስት ዓመት የዕድገት መርሐ ግብሩንና የ2013 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅዱን ይፋ አድርጓል፡፡ ረቡዕ ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ፣ ድርጅቱ ባለፈው በጀት ዓመት መተግበር የጀመረውን ‹‹ብሪጅ›› የተሰኘውን የሦስት ዓመት የዕድገት ስትራቴጂ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ከልሶ እንዳዘጋጀው ተናግረዋል፡፡
2. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚካሄደውን የመሬት ወረራና ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ማስተላለፍ ሒደት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን አስመልክቶ ያዘጋጀውን ጥናት ይፋ ለማድረግ በኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ በፖሊስ ታገደ፡፡
3. አሜሪካ ታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ኢትዮጵያ በያዘችው አቋም ላይ ጫና ለማሳደር በማሰብ፣ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የገንዘብ ድጋፍ በከፊል ለማቋረጥ መወሰኗ ተሰማ።
4. የኮሮና ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳይራዘም፣ በዚህ አዋጅ ምትክም ነባር አዋጆችንና እነሱን መሠረት አድርገው የሚወጡ አዳዲስ መመርያዎችን በመጠቀም የቫይረሱ ሥርጭትን ለመቆጣጠር መታቀዱ ተጠቆመ።
5. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2013 በጀት ዓመት ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ አንድ ሚሊዮን ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱን ጠቁሞ፣ ከኤሌክትሪክ ፍጆታ 16.5 ቢሊዮን ብር፣ ከልዩ ልዩ ገቢዎች ስምንት ቢሊዮን ብርና ከአገልግሎት ክፍያ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ለማግኘት በድምሩ 25 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱግ ግልጽ አድርጓል፡፡
6. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እንደሚነገረው ‹‹በሽግግር ወቅት የሚያጋጥሙ›› ተብለው ብቻ የሚታለፉ ሳይሆኑ፣ የተሳሳቱ ርዕዮተ ዓለማዊ ትርክቶችንና ጂኦ ፖለቲካዊ ዳራዎችን መነሻ በማድረግ በተቀነባበረና በተደራጀ ሥልት የሚፈጸሙ ኦርቶዶክሳውያንን የማፅዳት እንቅስቃሴዎች መሆናቸውን ቤተ ክህነት ገለጸች፡፡
7. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን የበሰለ ዳኝነትና የበሰለ ተቋም ያስፈልጉናል›› ሲሉ ተናገሩ፡፡ የበሰለ ዳኝነት ወይም ተቋም ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ያብራሩት ወ/ሮ መዓዛ፣ ሕግን ማዕከል አድርጎ የሚሠራ፣ ከየትኛውም አቅጣጫ ለሚመጣ ግፊት እጅ የማይሰጥ ዳኛና ተቋም ለኢትዮጵያ እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡