Hilina Desalegn
1.37K subscribers
51 photos
1 video
5 links
Best incredible and Amazing Ethiopian Poem. ኢትዮጵያዊ ስነ ግጥም ማቅረብ።
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግፍን ፍሩ
የትም ይሁን የትም መቼም ይሁን መቼ ግፈኞች መጨረሻቸው ውድቀት ነው።
ዛሬ ላይ በሚደርስበት ግፍና መከራ ዝም ያለ የተነሳ ዕለት ምላሹ የከፋ ይሆናል።
ሰላም ፍቅር አንድነት ለሁላችን!!
#ሀዘን 😔😔😔

በኢትዮጵያ መሬት ገደል ተደርምሶ፣
ስንቱን ሸረሸረው ጀግንነቱን ምሶ፣
ሐበሻን ቆራርጦ በደም አበስብሶ።
ህሊና ደሳለኝ መጥታለች
ተቀበል ተቀበል እያለች
"… ተቀበል አንተው… 

አይችለው የለ እንጂ - የልባም ትከሻ፣
ከውርደቱ ደጃፍ - ነውሩን ማምለጥ ሲሻ፣
ገርፎ ማሳመን ነው፣ የፈሪ ሰው በትር፣ የሽንታም ሰው ጋሻ።

                 እንመን ግድ የለም…

ፍትሕ አይታለምም - ሐቁን እየሸሹ፣
የጠፋው እንዲገኝ፣ እስኪ መጀመርያ፣ ይፈተሽ ፈታሹ፤

አቀርቅራ ታዝግም፣ ትጎናበስ እንጂ፣ መሔድ እስኪያድላት፣
ሰብረህ ስታበቃ፣ 'ምርኩዝ እንቺ' ብለህ ደርሰህ አትደልላት፤

'በኔ ብቻ' በሽታ - ጥበት እየቀጣን፣
በ'ናታችን ርስት፣ ባባታችን መሬት፣ መደገፊያ እያጣን፤

ቁልቁል እያሰቡ - ምንድነው ከፍታ፣
መብት እየነጠቁ - ምንድነው ግዴታ?
እስከ መቼ ተረት - ግዴለም ይነጋል፣
መንገድ እየቀሙ - ምርኩዝ ምን ያደርጋል?

አንተ እንደሁ ልማድህ አለስልሶ መግደል አሳስቆ መግፋት፣
'ካብኩ' እያሉ 'ማቅለል' 'ሳምኩ' እያሉ 'መትፋት'፣
የበደል ላይ ጀግና - ሬሳ ላይ መዛት፣
መዋረድን ሽሽት - የአሽቃባጭ አፍ መግዛት፤

እየሸሹ ትግል - እየሮጡ ዛቻ፣
በጉንዳን ልቡና - የነብር ዘመቻ፤

የበላ እያሠረ - የቀማ ቢገፈው፣
የሳተ እያረመ - ያጠፋ ቢገርፈው፤

ጀግና ልማዱ ነው፣ ባርያ ሆኖ ታሽቶ፣ ንጉሥ ኾኖ መግዛት፣
እያነሰ ገዝፎ - እየሞተ መብዛት፤

ያ ሽንታም ላመሉ - በሬሳ ይፎክራል፣
ከፈሪ ገዳይ 'ድል' - የጀግና 'ሞት' ያምራል፤

                    ይልቅ……

በእኔ ልቅደም ትርክት- የዘር ደዌ አያጥቃን፣
ከጎጥ ቀንበር ፍቱን - ጠቦ መሞት በቃን፤

የጸደይ ወይን ኾኖ - የሐቅ እንባ ቢጥም፣
በድሎ መጀገን - ጀብድ ሆኖ ቢረግጥም፣
የትግላችን ልኩ - ያሳር ደም ቢያስምጥም፣
በሰፋ ሀገር ጠበን - ኢትዮጵያን አንሰጥም!!!

👏👏👏👏 
ጤነኛን መመረዝ የሞተን ሰው ማከም፤
ወዳጅን አጣልቶ ለማስታረቅ መድከም፤
ከበግ መሀል ቆሞ የቀበሮ ጸሎት፤
በእጅ አዙሪት ገድለዉ የአዞ እንባ ቢያነቡት፤
ማንም ከእዉነት ቢሸሽ ባድር ባይ ሆዱ፤
ይዘገያል እንጂ መቼ ይቀራል ፍርዱ!።
እናት ዶሮን ገድሎ ጭልፊት አባራሪ ፤
አባት ገደል ገፍቶ የሙት ልጆች ጧሪ፤
የማስመሰል ኑሮ የሞት መንገድ ይብቃን፤
ክፋትን ሞከርነዉ መልካም ነገር ይዉጣን።

#ገጣሚ_ህሊና_ደሳለኝ
ኦ'ፋ
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
እድሜዬን በሉብኝ
ስጋትና ተስፋ
እንደኛው ሲቀደኝ
አንዱ አይቶኝ ሲሰፋ
አይዞህ ሲሉ ስሰንፍ
ሳይሉኝም ስለፋ
ጠጎ ሳላይ አለሁ
ቁስሌ እንደከረፋ!!!
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ሕሌና ደሳለኝ
#ሰው_እኮ
እንኳን ሊከተልህ፣ ሄዶ መቃብርህ
ገና ቆመህ ሳለህ፣ እየሳቀ ገሎህ
የክፋት አረንቋ ፣ በተከማቸበት
በዛ መጥፎ ልቡ ፣ ነው ቀድሞ ሚቀብርህ።
✍️ሕሌና ደሳለኝ
ይሄው ደግሞ ነጋ
ተደብቆ ማንባት የለመዱ አይኖችሽ ሳቅ ቢለማመጡ፣
እምባ የጠገቡት አንሶላና ትራስ ፀሃይ ላይ ሊሰጡ፣

ይሄው ደግሞ ነጋ
ሽፍንፍንሽ ክፉ የሌሊት እህህህሽን ከጉያው ደብቆ፣
ስንቱን አሳሳተ ቀርቦ እንዳይጠይቅ ጥርስሽ ለሁሉም ስቆ፣

የፈግታሽ ፀዳል ውብ ስም ቢያሰጥሽም ፣
የቀኑብሽ ሁሉም አንችን አያውቁሽም፣

የሚወድሽ ሁሉ ቀኑን ቢያደላድል በፈገግታሽ ቤት ላይ፣
ማንም አያውቅሽም ከትራስሽና ከመሃረብሽ በላይ።

✍️ሕሌና ደሳለኝ
Hilina Desalegn
ይሄው ደግሞ ነጋ ተደብቆ ማንባት የለመዱ አይኖችሽ ሳቅ ቢለማመጡ፣ እምባ የጠገቡት አንሶላና ትራስ ፀሃይ ላይ ሊሰጡ፣ ይሄው ደግሞ ነጋ ሽፍንፍንሽ ክፉ የሌሊት እህህህሽን ከጉያው ደብቆ፣ ስንቱን አሳሳተ ቀርቦ እንዳይጠይቅ ጥርስሽ ለሁሉም ስቆ፣ የፈግታሽ ፀዳል ውብ ስም ቢያሰጥሽም ፣ የቀኑብሽ ሁሉም አንችን አያውቁሽም፣ የሚወድሽ ሁሉ ቀኑን ቢያደላድል በፈገግታሽ ቤት ላይ፣ ማንም አያውቅሽም…
ባለፎይ ጎንደር ላይ በተዘጋጀ አንድ የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ ካቀረብኩት ግጥም ላይ የተቀነጨበች ናት። ሙሉ ግጥሜ በቅርቡ በቪዲዮ አዘጋጆቹ ይለቁታል ተመልከቱት አዳምጡልኝ። አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቴ ትምህርቴ ላይ ነው። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በዚህ ዓመት በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪዬን የምጨርስ ይሆናል። ሰላም ለሁላችን፣ ሰላም ለአገራችን ይሁን። 🙏🙏🙏
አለም
አንደኛው ቸግሮት የሚቀምሰው አጥቶ ጎዳና ይወጣል
ሌላው ተንደላቆ የሶስት መቶ ሺህ ረብጣ ውሻ ይሸምታል፤
ሠብዓዊነት ጎድሎን ውሻ እያረባን ሠው ማዳን ጠፍቶናል።
አለም
አለም አስመሳይ ናት ያጣን እያሳጣች
ሞልቶ ለተረፈው ሚዛን ትደፋለች።
🕊ልቦና ይስጠን🙏
✍️ሕሌና ደሳለኝ
"መሸነፍ ፈልጌ"

መሸነፍ ፈልጌ፣
           ትቼ መጠንቀቁን፣
ውርደትን ናፍቄ፣
       እግር ስር መውደቁን፣
ሁሉ እንዲስቅብኝ፣
ከአቦል እስከ ክትሚያ፣
             በስሜ እንዲጠጣ፣
ደሜን አቀዝቅዤ፣
ለሽንፈት ፈዝዤ፣
                የሚያሸንፍ ታጣ፣
ሁሉም ከየቤቱ፣
                 ለድል እየወጣ!!!
ቸር ጊዜ 🙏🙏🙏
"...የሰፋ ሀገር ይዘን፣ ጠቦ መሞት ይብቃን፤..."
(ገጣሚት፥ ህሊና ደሳለኝ)
---------------------
አይችለው የለ እንጂ - የልባም ትከሻ፣
ከውርደቱ ደጃፍ - ነውሩን ማምለጥ ሲሻ፣
ገርፎ ማሳመን ነው፣ የፈሪ ሰው በትር፣ የሽንታም ሰው ጋሻ።
እንመን ግድ የለም…
ፍትሕ አይታለምም - ሐቁን እየሸሹ፣
የጠፋው እንዲገኝ፣ እስኪ መጀመርያ፣ ይፈተሽ ፈታሹ፤
አቀርቅራ ታዝግም፣ ትጎናበስ እንጂ፣ መሔድ እስኪያድላት፣
ሰብረህ ስታበቃ፣ 'ምርኩዝ እንቺ' ብለህ ደርሰህ አትደልላት፤
'በኔ ብቻ' በሽታ - ጥበት እየቀጣን፣
በ'ናታችን ርስት፣ ባባታችን መሬት፣ መደገፊያ እያጣን፤
ቁልቁል እያሰቡ - ምንድነው ከፍታ፣
መብት እየነጠቁ - ምንድነው ግዴታ?
እስከ መቼ ተረት - ግዴለም ይነጋል፣
መንገድ እየቀሙ - ምርኩዝ ምን ያደርጋል?
አንተ እንደሁ ልማድህ አለስልሶ መግደል አሳስቆ መግፋት፣
'ካብኩ' እያሉ 'ማቅለል' 'ሳምኩ' እያሉ 'መትፋት'፣
የበደል ላይ ጀግና - ሬሳ ላይ መዛት፣
መዋረድን ሽሽት - የአሽቃባጭ አፍ መግዛት፤
እየሸሹ ትግል - እየሮጡ ዛቻ፣
በጉንዳን ልቡና - የነብር ዘመቻ፤
የበላ እያሠረ - የቀማ ቢገፈው፣
የሳተ እያረመ - ያጠፋ ቢገርፈው፤
ጀግና ልማዱ ነው፣ ባርያ ሆኖ ታሽቶ፣ ንጉሥ ኾኖ መግዛት፣
እያነሰ ገዝፎ - እየሞተ መብዛት፤
ያ ሽንታም ላመሉ - በሬሳ ይፎክራል፣
ከፈሪ ገዳይ 'ድል' - የጀግና 'ሞት' ያምራል፤
ይልቅ……
በእኔ ልቅደም ትርክት- የዘር ደዌ አያጥቃን፣
ከጎጥ ቀንበር ፍቱን - ጠቦ መሞት በቃን፤
የጸደይ ወይን ኾኖ - የሐቅ እንባ ቢጥም፣
በድሎ መጀገን - ጀብድ ሆኖ ቢረግጥም፣
የትግላችን ልኩ - ያሳር ደም ቢያስምጥም፣
በሰፋ ሀገር ጠበን - ኢትዮጵያን አንሰጥም!!!
ለትውስታ
አገሬን አፋልጉኝ 💚💛😓😭🙏
ሀገሬ መሄጃሽ ጠፍብኝ መንገዱ
እያባረሩሽ ነው እብዶች እየነዱ
የትነው የምትቆሚው መድረሻሽን ልየው
ለምን ይሆን ጉዞሽ ፌርማታ የሌለው?
አንደኛው ልጅሽን ሌላው ይላል በለው
ግደለው ነው እንጅ ምን ገላጋይ አለው
ሲቃጠል ሲታመስ ሁሉ ነገር ሲጋይ
ሆ እያለ መጣ ያበደ ገላጋይ
ምጣዴም አልሰማ ዳቦየም አልወጣ
እሱ ከዘገየ ባይሆን እኔ ልውጣ
የለመድኩት አይደል ውቅያስኖስ ውስጥ መግባት
ሰላም መስሎኝ እንጅ ሀገሬን ሲያግባቧት
ለመታረድማ ሌላ ቦታ ላቅና
ባዕድ በላው ብሎ ወገኔ ይፅናና
ለመቃጠልማ ምን አለኝ ስደቱ
ይግደለኝ ይግፈፈኝ በጨቃኝ አንጀቱ
ሀገሬ መሬትሽ ስረግጠው ያመኛል
ጤፍ እየዘራሁት ጓያ ይሰጠኛል
የተራመድኩ ዕለት ሰብሮ ያስቀረኛል
አንደኛው ሲያለብስሽ አንዱ እየገፈፈሽ
አንደኛው ሲያባብልሽ አንዱ እየገረፈሽ
ይሄው እንደ ሟች ልጅ ማንም አስለቀሰሽ
መቸም አልታደልንም ለዘፈን ለአበባ
ላንችም ለኔም ሚሆን ይሄው ትኩስ ዕንባ።
የዝንጀሮ ዳኛ//
ተከሳሹ ነብር ከሳሿ ቀበሮ፣
ምስክሯ ጦጣ ዳኛውም ዝንጀሮ፣
አንበሳ ሲታዘብ ጅብ ሲሸመግለው፣
የቁልቁለት ጉዞ ዝቅጠት እንደዚህ ነው፡፡
ውሳኔው ፀደቀ በዝንጀሮ ችሎት፣
ፍንጥዝጥዝ ቀበሮ ፍትህ ዘመመላት፣
ወገኗ ዝንጀሮ ከጭንቅ ገላገላት፡፡
ነብር ይግባኝ ካለ ፍርድ የታየ እንድሆን፣
ወይ ቀበሮ ግፍሽ መግቢያሽ ወዴት ይሆን?
ተስማምቶ መኖሩ ነበረ ሚበጅሽ፣
ጊዜ የሰጠው ቅል ሆነና ነገርሽ፣
ነብርን ነካካሽ እንዲህ ሚቀር መስሎሽ፣
ፍርዱ ላይሰነብት ዝንጀሮን ተማምነሽ፡፡
አንበሳ ሲዳኘው በትዝብት ያየውን፣
መዳረሻም የለሽ በደልሽ ምን ሊሆን?
እንዲህ ነው ዘመኑ የተገላበጠ፣
ባለጊዜው ሁሉ አይኖር እንዳበጠ፡፡
ያላባት ዳኝነት የትም ላያደርስሽ፣
የዝንጀሮ ችሎት ከቶ ላያዘልቅሽ፣
የጅብ ሽምግልና ግምቱ ጠፍቶብሽ፣
ያላዋቂ ሸንጎ ዋጋ ሊያስከፍሉሽ፣
ለጊዜው ፈነጠዝሽ ሽቅብ አዘለሉሽ፡፡
በይ እንግዲ ቻይው ተስፈኛ ቀበሮ፣
ነብሩ ተነስቷል ፀጉሩን አንጨፍሮ፣
አንበሳ ነው ዳኛው ሊቀየር ዝንጀሮ፣
ቶሎ ጉድጓድ ግቢ ያልታደልሽ ቀበሮ፡፡
"እውር ናት ሃገሬ ማየት የናፈቃት፣
እንባ ላብስ ያለ ዓይን እየሰረቃት።"
ትናንትናም ዛሬ፣ ዛሬም ትናንትና

ዛሬሽን አየሁት፣ ትናንትና ሆኜ፣
ትናንትን አየሁት፣ ዛሬ አብሬሽ ሆኜ፣
ይህ ሁሉ መኳኳል፣ ምን ያደርግልሻል?
ያ... የተፈጥሮ ገላ፣ ብቻ ይበቃሻል፡፡

ትናንትናሽን ናፈቅሁ፣ ታሪክ ሊሆን ዛሬ፣
ዛሬሽንም ናፈቅሁ፣ ነገ ሊሆን ክብሬ፣
ግን መቼ ሆነ! ትናንት ሆነ ወሬ፣
አሁንም አልታደልኩ ቆሜም ፊትሽ ዛሬ፡፡

አይ.... አንቺዬዋ! ምኑ ይሻልሻል፣
ትናንትናን አልፈሽ፣ ዛሬ ላይ ደርሰሻል፣
ዛሬ ላይም ሆነሽ፣ ትናንትን ይዘሻል፣
ትውልድ ሲፈራረቅ አንቺው ነሽ ተብለሻል፣
የወላድ መካን ነሽ የሄደው የመጣው ዞሮ ይበላሻል።
እግዚአብሔር ይመስገን
በህግ ትምህርት በትናንትናው ዕለት በጎንደር ዩኒቨርስቲ ተመርቀናል።
ሕሌና ደሳለኝ🙏🙏🙏