Ethiopia Customs Commission
5.41K subscribers
2.85K photos
3 videos
51 files
325 links
Download Telegram
ባለፉት 11 ወራትት 171 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል
*********

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም )
በጉምሩክ ኮሚሽን የዋናው መስሪያቤት አመራሮች እና ሰራተኞች ሀገራዊ የምጣኔ ሀብት እድገት ያለበትን ደረጃ እንዲሁም የኮሚሽኑን የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ ቀናት ስራዎች ክንውንን በሚመለከት ውይይት አድርገዋል፡፡

አጠቃላይ ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ተስፋና ስጋቶች እንዲሁም የኮሚሽኑ የ11 ወራት ዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በፕላን እና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ አብዲሳ ዱፌራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ፣ እንደ ሀገር ባለፉት ዓመታት በሁሉም መስኮች ተጨባጭ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገባቸውን ገልጸው ይህ ውጤት እንዲቀጥልም የጋራ ጥረትና ርብርብ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

ውይይቱ በ2016 የበጀት ዓመት የተሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያጋጠሙ ችግሮችንም መፍትሔ ለማበጀት እንዲሁም ለ2017 የበጀት ዓመት እቅድ ግብዓት ለመሰብሰብ እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት እንደተመላከተው፣ በ2016 የበጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት 191 ነጥብ 96 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን 171 ነጥብ 4 ቢሊዮን ወይም የእቅዱን 89.3 በመቶ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

የገቢ አሰባሰቡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ወይም በ6 ነጥብ 4 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

ኮንትሮባንድን በመከላከል እና በመቆጣጠር የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን በሪፖርቱ የተቀመጠ ሲሆን ባለፉት 11 ወራትም 9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የገቢ እና 4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የወጭ በድምሩ 14 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በውይይቱ ሀገራዊ እና ተቋማዊ አስቻይ ሁኔታዎች እንዲሁም ፈተናዎች የተነሱ ሲሆን በተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission
ከ247 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
************************************************

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም )
የጉምሩክ ኮሚሽን ከሰኔ 7 ቀን እስከ 13/ 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 233 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 14 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 247 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዋሽ፣ ድሬድዋ እና ሐዋሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 70 ሚሊዮን፣ 56 ሚሊዮን እና 52 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን ኮንትሮባንዱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 10 ተጠርጣሪዎች እና ሰባት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission
ሃገር አቀፍ የታክስ እና ቀረጥ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር የማጠቃለያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

**********

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም )

በታክስ እና ቀረጥ ላይ ትኩረት በማድረግ በአስር ክላስተር እና በ240 ት/ቤቶች ሲካሄድ የነበረው የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር የማጠቃለያ መርሃ ግብር በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።


በዚህ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ምክትል ኮሚሽነሮች ፣ ዳይሬክተሮች ፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል ።


በዚህ የማጠቃለያ መርሃግብር የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፤ " ግብር ለሃገር ክብር " በሚል መሪ ቃል ከፌደራል እስከ ታችኛው የመንግስት መዋቅር ድረስ የታክስ እና የጉምሩክ ህግ ተገዥነት የንቅናቄ መድረክ ሲካሄድ መቆየቱን ገልጸዋል ።


ኮሚሽነር ደበሌ አክለውም ፣ በኃይማኖት ተቋማት ፣ በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ህዝባዊ ተቋማት የታክስ ስርጸትን ለማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ ውይይቶች እና የንቅናቄ መድረኮች መከናወናቸውን አስረድተዋል ።


የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድሩ የዚህ ንቅናቄ አንዱ አካል መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነር ደበሌ ፣ ውድድሩ ስለ ታክስና የጉምሩክ ህጎች በቂ ግንዛቤ ያለው ትውልድ ለማፍራት ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል ።


ከአንድ ዓመት በላይ በቆየው በዚህ የንቅናቄ መድረክ የታክስ እና የጉምሩክ ህግ ተገዥነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ኮሚሽነር ደበሌ ጠቁመዋል ።


ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት :-

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsommission