Ethiopia Customs Commission
5.41K subscribers
2.85K photos
3 videos
51 files
325 links
Download Telegram
የኮሚሽኑ አመራሮች እና ሰራተኞች 17ተኛውን የሰንደቅ- ዓላማ ቀን አከበሩ
#######################
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም )

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ ምክትል ኮሚሽነሮች፣ የጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች ፣ የኮሚሽኑ ሰራተኞች እና የፌደራል ፖሊስ አባላት በተገኙበት 17ተኛው የሰንደቅ- ዓላማ ቀን ተከብሯል፡፡
17ተኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችን፤ለሉአላዊነትነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው፡፡

የኮሚሽኑ አመራሮች እና ሰራተኞች፣ በአንድነት በመቆም በዓመቱ የታቀዱ የልማት እና የመልካም አስተዳደር እቅዶች እንዲሳኩ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃል ገብተዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት :-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsommission
በኮሚሽኑ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ88 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል
#######################
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም )
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፤ በኮሚሽኑ በ2017 የበጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ለሚዲያ ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ።

ኮሚሽነር ደበሌ በመግለጫቸው፤ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 87.27 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 88.1 ቢሊዮን ብር ወይም የእቅዱን 100.86 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ገልጸዋል።
አፈጻፀሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ38.45 ቢሊዮን ብር ብልጫ ማሳየቱንም ተናግረዋል ።

ኮንትሮባንድን በመከላከል እና በመቆጣጠርም ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ኮሚሽነር ደበሌ ጠቁመዋል፡፡

በመጀመሪያው ሩብ ዓመትም 2.8 ቢሊዮን ብር የገቢ እና 842.8 ሚሊዮን ብር የወጪ በድምሩ ከ3.6 ቢሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር ደበሌ አክለውም፤ በንግድ ማጭበርበር እና በኮንትሮባንድ መንግስት ሊያጣው የነበረውን ከ50 . 5 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ከህገ ወጦች ማዳን እንደተቻለም አስረድተዋል።

በህግ ለተፈቀደላቸው የቀረጥ ነጻ ማበረታቻ መብት ተጠቃሚዎችም 34 ቢሊዮን የሚገመት የጉምሩክ አገልግሎት መሰጠቱንም ገልጸዋል፡፡

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በዋናነት በንግድ ማጭበርበር እና በኮንትሮባንድ ዝውውር ችግሮች ማጋጠማቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ ችግሮቹን ለመፍታት በርካታ እርምጃዎች የተወሰዱ መሆኑንና በቀጣይም በህገወጦች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም ከሚዲያ ባለሙያዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ኮሚሽነር ደበሌ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት :-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsommission