Ethiopia Customs Commission
5.2K subscribers
2.69K photos
3 videos
51 files
309 links
Download Telegram
ባለፉት 11 ወራትት 171 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል
*********

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም )
በጉምሩክ ኮሚሽን የዋናው መስሪያቤት አመራሮች እና ሰራተኞች ሀገራዊ የምጣኔ ሀብት እድገት ያለበትን ደረጃ እንዲሁም የኮሚሽኑን የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ ቀናት ስራዎች ክንውንን በሚመለከት ውይይት አድርገዋል፡፡

አጠቃላይ ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ተስፋና ስጋቶች እንዲሁም የኮሚሽኑ የ11 ወራት ዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በፕላን እና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ አብዲሳ ዱፌራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ፣ እንደ ሀገር ባለፉት ዓመታት በሁሉም መስኮች ተጨባጭ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገባቸውን ገልጸው ይህ ውጤት እንዲቀጥልም የጋራ ጥረትና ርብርብ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

ውይይቱ በ2016 የበጀት ዓመት የተሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያጋጠሙ ችግሮችንም መፍትሔ ለማበጀት እንዲሁም ለ2017 የበጀት ዓመት እቅድ ግብዓት ለመሰብሰብ እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት እንደተመላከተው፣ በ2016 የበጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት 191 ነጥብ 96 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን 171 ነጥብ 4 ቢሊዮን ወይም የእቅዱን 89.3 በመቶ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

የገቢ አሰባሰቡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ወይም በ6 ነጥብ 4 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

ኮንትሮባንድን በመከላከል እና በመቆጣጠር የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን በሪፖርቱ የተቀመጠ ሲሆን ባለፉት 11 ወራትም 9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የገቢ እና 4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የወጭ በድምሩ 14 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በውይይቱ ሀገራዊ እና ተቋማዊ አስቻይ ሁኔታዎች እንዲሁም ፈተናዎች የተነሱ ሲሆን በተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission